Telegram Web Link
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ለጥፊያት የነበረች ምናልባትም የመጀመሪያዋ የኔ meme😁😁
የቴሌግራም አካውንታችን ለጥቂት ተረፈ ሪፖርት ተደርጎ.. ይሄንን ቻናል
አጥተነው ነበር ማርያምን😁😁

ኧረ ሪፖርት ምታደርጉ ፋራዎች እረፉ.. በእርግጥ አሁን ቻናሉ ላይ ሌሎች ሰዎችንም አድሚናት እያደረኩ ስለሆነ ወደነሱ ስለሚተላለፍ አያሳስብም..

እና እረፉ እረፉ እዚ ኮፒ ሊንክ የለ ነገር ሎል
ኢስላም የነቢያቱ ሁሉ ሃይማኖት ነው ይልሁና.. እሺ የነቢያቱን ሃይማኖት ለማወቅ የእነሱን እምነት የሚያሳይ የራሳቸውን ምስክርነት ስጠኝ እስቲ ስትለው አይ ተበርዟል ይልሃል ሎል

እና ምን አርጉ ነው ምትሉን ስትላቸው ያው ቁርአን እንደዛ ብሏል ይሉሃል.. በማን በኩል የመጣው..?? በሙሐመድ.. እዋይ ስለዛ በሙሐድ በኩል ብቻ የተላለፈ ነገር ከሆነ ያለህ ስለሌላው “ነቢያት” አታውራ ብራዘርዬ..

እንዲሁ ምንም ማስረጃ ስለሌለው ይልቁንም ከእውነተኛ ነቢያት ሁሉ ጋር ተቃርኖ ስለመጣው የአረብ “ነቢይ” ብቻ አውራ..

@Apostolic_Answers
ከሙስሊሞች ቀጥሎ ሚገርሙኝ እኮ እኛ ሃገር ያሉ ካልቪኒስቶች ናቸው😁😁

እዚህ ያሉት አንዳንድ ካልቪኒስቶች ከክርስቲያኖች ጥያቄ ለመዳን ሲሉ "ጥምቀት ለመዳን ነው" ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ😁😁

አይ ጀግናው ሎል

ሲጀመር እናንተ ሰው በሃጢአት ሙሉ በሙሉ ስለ ሞተ ለእግዚአብሔር ቃል መመለስ ወይም ጥሪውን መቀበል ወይም ማመን አይችልም ትሉናላችሁ.. ታድያ እንዴት ነው ሰው ሚድነው ስንላችሁ ያው እግዚአብሔር ከዛ ከሞቱት ሰዎች ለተወሰኑት መርጦ ወስኖ እንዲሁ እምቢ ማይባለውን ከሞት ወደ ሕይወት የሚያመጣውን የሚያድነውን ጸጋ ይለቅባቸዋል ከዛ ወደ ሕይወት ከመጡ በኋላ ያምናሉ ትሉናላችሁ..

ታድያ ዳግም ለመወለድ እምነትን እንኳን ማትጠቅሱ ሰዎች ጥምቀት ለድኅነት ነው ብላችሁ የማታምኑትን እንደምታምኑ ስታወሩ ትንሽ አይከብድም..?? ከእናንተ ደግሞ የጴንጤው ይሻላል እዚህ ላይ😁😁

አታምታታም ስልህ ብራዘርዬ።

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ እንዲህም ነበረች.. ብሔራዊ መዝሙሯ ከመዘመሩ በፊት አባታችን ሆይ ይጸለይ ነበር.. አሁን ከ60 ዓመት በፊት አካባቢ

ይገርማል ብቻ..
የኢዮብ ዘሚካኤል ፖድካስት ሎጎ

1️⃣የመጀመሪያ ትርጉም:

-> ኢ - ኢየሱስ

-> ኢ ላይ አግድም መስቀል - ጌታ ኢየሱስ ስለሁላችን መስቀልን እንደተሸከመ


2️⃣ ሁለተኛው ትርጉም:

-> ኢ - ኢዮብ

-> መስቀሉ - መስቀሉን ተሸክሞ የማይከተለኝ ለኔ ሊሆን አይገባውም እንዳለ ጌታችን እሱን ማመልከት

-> ሰይፋም መስቀል ነው - ተዋጊውን የጌታ መልአክ ሚካኤልን ለማመልከት ነው.. ያው ስሙም ኢዮብ ዘሚካኤል ስለሆነ ማለት ነው.. አንድም ደግሞ ሰይፍ የእግዚአብሔር ቃል ምሳሌ ነውና የእግዚአብሔርን ቃል ተሸክሞ መምጣቱን ለማሳየት..

—————///———————///———

በጓደኛዬ ላዛሩ ነው የተሰራው እና እሱ ሲሰራ በቃ ቀለል ያለ ግን መልእክት ያለው ነው እና በጣም ነው የወደድኩት.. በድጋሜ ጌታ ያክብርልን ብሮ.. ሁሌ በቅንነት ብቻ ከጎናችን የሆንክ ሰው ነህ..
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኢዮባን ዩትዩብ ለመቀላቀል ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ.. ከዛም ለሌሎችም ሼር ያድርጉ

👇👇👇👇

m.youtube.com/@Eyob_z_mikael

———————-
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ልብን የሚነካ ታሪክ

አንድ ሰው ነበር ከተወሰኑ መቶ አመታት በፊት በመንገድ በፈረሱ በሚጓዝበት ወቅት በሥፍራው እጅግ ትልቅ ተፈጠሮአዊ አደጋ ይፈጠራል.. መብረቅ ሳይቀር አጠገቡ መውደቅ ጀመረ እና እርሱንም ከፈረሱ ላይ ጣለው..

ያኔ ያ ወጣት ወደ ቅድስት ሃና ይማጸን ጀመር፡ "ቅድስት ሃና ሆይ እርጂኝ እና እመነኩሳለሁ" እያለ ጮኸ.. ከዛም ከዛ ውስጥ በሰላም ወጣና መሃላውን አክብሮ መነኮሰ..

ምን ዋጋ አለው.. ከተወሰኑ አመታት በኋላ ያንን ከሞት ያመለጠበትን ነገር ረስቶ መሃላውን በመስበር ልክ እንደሱ በምንኩስና ሕይወት ውስጥ የነበረችን ሰው ጭራሽ አስወጥቶ በኋላ አገባት.. እሷ ካትሪና ትባላለች.. እሱ ደግሞ ዋናው ሰው the one and only😁😁 ማርቲን ሉተር ነው..

አይ ጀግናው🤦‍♂️🤦‍♂️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መኩን ፎሎው አድርጉት ኮፒሊንክ ምናምን

https://vm.tiktok.com/ZMSS7ryHM/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ እኛ ጋር የተነበቡት ጠቅላላ ምንባባት የትንሳኤ ሆኑብኝ.. እናንተም ጋር ነው..??😁😁

በቃ ቆይ ከዛሬው ታላቅ በአል ጋር ተያይዞ ቪዲዮ አስቀምጥላችኋለሁ..
መቼስ ይሄንን የሚያክል ማይክ ሰጥተህ ያስበላኸን አንተው ነህና የኔን የሃገር የተሰራብኝን ትቼው ያንተንው ለጠፍኩት😭😭

በእውነት ምን ያልተባልኩት ነገር አለ..?? ምንስ ያልደረሰብኝ ግፍ አለ..??😭😭 ዋሽንት ነው ወይስ ማይክ..?? አኬ አጥንት ይዞ ነው በሉኝ..?? በቆሎ ነው..?? ኧረ አርሞኒካም ይመስላል😭😭😭አስጨፈጨፍከኝ ሎል..

እኔ ሲጀመር ሲያመጡት ሰልፊ ስቲክ ነበር የመሰለኝ እኮ😭😭
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች ኦርቶዶክሶችን ርእስ አሳጣናቸው እያሉ ሰማሁ😆😆

ያው እያሉን ያሉት ከዚህ በፊት ስትከሱን የነበረው ሳታውቁን ነው እያሉን ነው.. ጥምቀትም ለድኅነት ነው ብለን እናምናለን እያሉ ነው ሎል.. በጣም ነው እንዴ ይህንን ሰው ሰራሽ ትምህርታቸውን እንዲሸማቀቁበት ያደረግነው..??

አታምታታም ስልህ ብራዘርዬ ላይቭ እንግባላቸውና ምን ሲናገሩ እንደነበር እናሳያቸው መሰለኝ😁😁 ከዛ ደግሞ በጴንጤው ዘንድ የሚታመነውንም ከራሳቸው ሊቃውንት እናሳያቸው ቆይ😁😁
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማነህ እፎይ.. አቡነ እፎይ.. ምንድን ነው ያልከው አንተዬ.. ኧረ ዜማ.. መስጅድ ነው እንዴ ምታስቀድሰው “ወንድምነት” ሎል
ቤተ ክርስቲያን በጣም ልትሰራ ሚገባው ብዬ ማስበው ሌላው ነገር በባልና ሚስት መካከል ያለው ግንኙነት ላይ ነው..

በተለይ ባል አምባገነን መሆን የለበትም.. በጣም ብዙ ባል እየሰከረ የሚገባ ሚስቱን የሚያስመርር ጭራሽ የሚማታም በአጠቃላይ ሕይወቷን የሚያከብድ አለ.. ጭራሽ ልጆች ደግሞ ሲኖሩ አስቡት ምን ያህል እንደሚያሳቅቅ..

እና ያው የብዙ ሰው አስተዳደግ እግዚአብሔርን በመፍራት እና በማፍቀር ውስጥ ስላልሆነ የሕይወት መንገዱ እንደ ስሜቱ እንጂ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም.. እና እንደው እናቶችን/ሚስቶችን የሚያሳቅቁ ዘግናኝ ባሎች መስመር እንዲይዙ ቤተ ክርስቲያን ያው የራሷ ሃላፊነት አለባት..

@Apostolic_Answers
ወልድ ያለው..
ሕይወት አለው።

@Apostolic_Answers
2025/07/01 16:05:11
Back to Top
HTML Embed Code: