Telegram Web Link
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ3 ቢሊዮን ብር የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ.ር)እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲው 230 መምህርንን ተጠቃሚ የሚያደርግ አፓርታማ በ3 ቢሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ግንባታው የመዝናኛና የገበያ ማዕከላትን ጨምሮ ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የግንባታውን ሂደት በማፋጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የደብረ ብርሃ ከንቲባ ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በትልቅ ለውጥ ውስጥ ያለና ለከተማው ጥሩ ዕድል ያመጣ ነው ብለዋል፡፡

የመምህራንን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ የተጀመረው ግንባታ ትልቅ መሆኑን ገልጸው መምህራን ወደ ውጪ ሳያስቡ ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩና ትውልድ የመቅረጽ ኃላፊነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

@DBU11
@DBU111
ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡ 29 ሺ491 አመልካቾች መካከል 96 በመቶ ፈተናውን እንደወሰዱ አመልክቷል።

በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ይሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በ53 የፈተና ማዕከላት ነው የተሰጠው።

የፈተናው ውጤትም በቅርቡ ለተማሪዎች ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሌሎች አገር አቀፍ ፈተናዎች የተለየና የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ አመልካቾች ለትምህርቱ ምን ያክል ዝግጁ ናቸው የሚለውን ለማረጋገጥ ደረጃውን ጠብቆ የሚሰጥ ምዘና ነው።

@DBU11
@DBU111
ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ አዲሱን ደመወዝ ስኬል ለሰራተኞች የከፈለ የመጀመሪያው ዩኒቨርስቲ እንደሆነ ተገለፀ።

ከ2ሺህ 7 መቶ በላይ ሠራተኞችን ፋይል አጣርቶ፣ የደመወዝ ልዩነቱን የያዘ ደብዳቤ አዘጋጅቶ ለሁሉም ሠራተኛ እንዲደርስ አድርጓል።

በዚህም አዲሱን ደሞዝ መስከረም 28 /2018 ዓ.ም ከፍሏል ።

@DBU11
@DBU111
👏29
በጎደለው አለን ላላችሁ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ።


የደ/ብርሃን ዩንቨርሲቲ የሶስተኛ አመት የአማርኛ ዲፓርትመንተ ተማሪ የሆነው ተማሪ ነገሰ ይቻለዋል የኩላሊት ህመም እንዳጋጠመውና ባስቸኳይ የቀዶ ጥገና ህክምና ማድረግ እንዳለበት ተነግሮት እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን አሁን ላይም በበጎ አድራጎት ክበብ እና በጎ ፍቃደኞች በአጠቃላይ 31,153 ብር ተሰብስቦለታል።

በአሁን ሰዓትም የሲቲ ስካን ምርመራ አድርጎ በሪፈራል ሆስፒታል ህክምናውን ለማድረግ ለነገ ሀሙስ ቀጠሮ ተይዞለታል።

ሁላችሁንም ለተባበራችሁ አካለት ከልብ እናመሰግናለን።

           @DBU11
@DBU111
👏42👍6👌4
#ADVERTISING

🎉🎉🎉እንኳን ደስ አላችሁ🎉🎉🎉

BEST ONLINE MARKET  ለ ደብረ  ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከትምህርታቹ ጎን ለጎን ገንዘብ የምትሰሩበትን መንገድ በሚከተሉት ዘርፎች አብረን እንድንሰራ እድሉን አቅርበንላችኋል።

1. Sales ላይ የመሥራት ፍላጎት  ያላችሁ
2. በትርፍ ሰዓት ተማሪዎችን ለማስጠናት ብቁ የሆነ/የሆነች
3. በ Event Decors ስራ ላይ አቅም ያለው ወይም በ Decor ስራ ስልጠና የወሰዳችሁ
4. ሌላም የ business ሃሳብ ኖሯችሁ ከ እኛ ጋር መስራት ለምትፈልጉ በሚከተሉት አድራሻዎች ልታናግሩን ትችላላችሁ።

ለበለጠ መረጃ  እንዲሁም ከቢዝነስ ግሩፓችን የምትፈልጉትን እቃዎች ለመግዛት

BEST ONLINE MARKET
https://www.tg-me.com/DBUdressrental/
  Contact us
      @Bestonlinemarket16
       +251709000170
🤬4👍2
Fake News Alart

የኛን ቻናል ሊንክ በማያያዝ እየተዘዋወረ የሚገኝ የመሃል ሜዳ ካምፓስ የጥሪ ማስታወቂያ የእኛ አለመሆኑን እና ሃሰተኛ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

የመጀመሪያ ዓመት እና የማካካሻ ትምህርት ተማሪዎችን በተመለከተ ለጋራ ኮርሶች ማስተባበሪያ ባቀረብነው ጥያቄ የተወሰነ ውሳኔ እንደሌለ እና አዲስ ነገር ሲኖር በቻናላችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

@DBU11
@DBU111
👌9👍6
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከአለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት ጋር የሁለትዮሽ የጋራ ስምምነት ሰነድ የፊርማ ስነ-ስርአት አካሄደ፡፡


በፊርማ ስነ-ስርአቱ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች፣ እንዲሁም ከሜክሲኮ፣ከታይላንድ እና ከቻይና የመጡ የበጎ አድራጎት ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡

ስምምነቱ በተለይ ጎበዝ ተማሪዎች ተመርቀው ከወጡ በኋላ በኢትዮጵያም በደቡብ ኮሪያም የስራና የትምህርት እድልን በመፍጠር በኤስኤም ካምፓኒ ውስጥ እንዲሰሩ አንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ጋር ብዙ ስራዎችን አብሮ ለመስራት እና እገዛ ለማድረግ፣ ተማሪዎቹን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ ነው ተብሏል ።


@DBU11
@DBU111
👍13👏8😢4
2025/10/20 08:44:42
Back to Top
HTML Embed Code: