Telegram Web Link
#Remidial

እንኳን ደስ አላችሁ!
94.13 % Passing Rate

@DBU11
@DBU111
👏30👌1
የሐዘን መግለጫ
===========
የደብረ ብርሃን ዩኒሸርሲቲ ሠራተኛ የነበሩት ወ/ሮ ቁምነገር አለሙ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል:: በመሆኑም የደብረ ብርሃን ዩኒሸርሲቲ ማህበረሰብ በባለደረባችን በወ/ሮ ቁምነገር አለሙ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን::

ደብረብረሃን ዩኒሸርሲቲ
😢60🤔3👏2
ለክረምት ልዩ የመምህራን ሰልጣኞች

@DBU11
@DBU111
👍3
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ለሰልጣኞች ገለፃና ትውውቅ አደረገ፡፡


የፕሮግራሙ አስተባባሪ ከትምህርት ሚኒስቴር አቶ ገበየሁ ስለሺ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመምህራን ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ መሆኑን በመግለፅ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለሚሰጠው ልዩ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ስልጠና ላይ ስልጠናው እስኪጠናቀቅ ድረስ በአስተባባሪነት ክትትልና ቁጥጥር  በማድረግ ቆይታ እንደሚያደርጉ በመናገር ሰልጣኞች በጥንቃቄ ስልጠናችውን መከታተል ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡


በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የግቢው ሰላምና ደህንነት ስራ አስፈፃሚ ሳ/ን አበበ መንግስቱ እንደገለፁት ስልጠናችሁን በሰላም አጠናቃችሁ ለመውጣት የዩኒቨርሲቲውን ህግና ደንብ መጠበቅ ይኖርባችኋል በማለት ተናግረዋል፡፡

አክለውም ንብረት የመጠበቅ፣ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ስትወጡና ስትገቡ የመውጫና የመግቢያ ሰዓትን የማክበር እና የምግብ ቤት ስርዓትና ደንብን ጠንቅቆ ማወቅ እንዲሁም ብሄርን፣ ሃይማኖትን እና ቋንቋን መሰረት  በማድረግ ግጭት ማስነሳት በህግ የሚያስቀጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


@DBU11
@DBU11
👍3
" ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸውና ስለሚሠሩት ሥራ ትክክለኛ መረጃ ስጡን ብለን ከጠየቅን ሦስት ዓመት አልፎናል፡፡ ሆኖም እስካሁን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ችግር ሆኖብናል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ እውነተኛ መረጃ መስጠት አልተለመደም፡፡

ባለፈው ዓመት ከተማሪዎች ምገባ ጋር ተያይዞ የውሸት ሪፖርት ሲቀርብ ነበር፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቁጥር በውሸት በመጨመር በጀት እንዲጨመርላቸው ያደርጉ ነበር።

ዩኒቨርሲቲዎች አሉን የሚሏቸውን የተማሪዎች መረጃ ከእነፎቷቸው አምጡ ስንል ግን፣ አሉን ብለው ካስመዘገቧቸው ተማሪዎች 251 ሺህ ያህሉ የት እንደገቡ አያውቁም፥ ለማምጣትም አልቻሉም፡፡

አንድ ዕውቀት ላይ እሠራለሁ የሚል ተቋም በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ ከሆነና እውነተኛ መረጃ መስጠት የማይፈልግ ከሆነ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲመጣ የምንፈልገውን ለውጥ አዝጋሚ ያደርገዋል። "
- የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የዩኒቨርሲቲዎች መረጃ አሰጣጥን በተመለከተ የተናገሩት፦
Source: Tikvah
@DBU11
👏28👌6🤔1🤬1
የሀዘን መግለጫ

@DBU11
@DBU11
😢56👍1
መግቢየ ቀን ይፋ ሆኗል ❗️❗️

የ2018 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደር ዝርዝር ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልኳል፡፡

መስከረም 05-06/2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች (ሪሚዲያል ተማሪዎችን ጨምሮ) በየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡

መስከረም 08-09/2018 ዓ.ም የሁሉም የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች (ሪሚዲያል ተማሪዎችን ጨምሮ) ምዝገባ ያደርጋሉ፡፡

መስከረም 12/2018 ዓ.ም📌 የሁሉም የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች በቅጣት ምዝገባ፣

@DBU11
@DBU11
👍22🤬16😢15👏1🤔1👌1
ለድህረምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

@DBU11
👍2
የጃፓን ሰዓት አክባሪነት‼️

በጃፓን ለ35 ሰኮንድ ባቡር በመዘግየቱ ካፒቴኑ በይፋ ይቅርታ ጠይቆ ለአገልግሎት የከፈሉትን ገንዘብ መንግሥት ተመላሽ(refund) አድርጓል።
ይህ ጃፓኖች ያላቸውን የሰዓት አክባሪነት (punctuality) እና  ለጊዜ (ሰዓት) ያላቸውን ክብር ያመለክታል።
ጃፓኖች ሰዓት ማክበር የባህላቸው ቁልፍ ጉዳይ ነው።
በሰዓት አክባሪነት የሚታወቁት ጃፓኖች አማካይ አመታዊ የባቡር መዘግየት 1 ደቂቃ ብቻ መሆኑን የመገናኛ ብዙኃን ዘግበውታል። ለህዝብ አገልግሎት ላላቸው ትልቅ ቦታና ክብር ለሰከንዶች መዘግየት ካጋጠመ ህዝብን እንደመናቅ ስለሚቆጠር በይፋ ይቅርታ ይጠይቃሉ፤ተገቢ እርምጃዎችንም ይወስዳሉ። ይህ እርምጃ በተለይ shinkansen ተብሎ በሚጠራው ፈጣን ባቡር ላይ ጠንከር ይላም ነው የሚባለው።
ሰዓት ማክበር እና ለጊዜ ዋጋ መስጠት የስልጣኔ መገለጫ ነው።

በብዙ ነገራቸው የሚደነቁት ጃፓኖች በአካባቢ ንጽህና አጠባበቃቸውም አንቱታን ያተረፉ ህዝቦች ናቸው።

በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ የ daily news ቤተሰቦች ሐበሾችን ጨምሮ በመላው የአለም ህዝብ የሚደነቅ እና ይሁንታን የተቸረው የጃፓኖች ስርዓት (ልምድ) ወይም ባህል በክፍል በክፍል እንድናቀርብላችሁ ከወደዳችሁ በመልዕክት መስጫ ሳጥናችን አሳውቁን መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ።



@dbu1
@dbu111
👍8👌1
''አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጉ'' - ትምህርት ሚኒስቴር

በ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ እንዲደረግላችሁ የምትፈልጉ ተመሳሳይ ጾታ መንትዮች፣ የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም የተለያዩ የጤና ዕክል ያለባቸው ተማሪዎች የ 2017 ዓ.ም 12ኛ መልቀቂያ ፈተና ውጤት እስኪገለጽ ድረስ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።

የሚያስፈልጉ ሰነዶች

1. ለተመሳሳይ ጾታ መንትያ አመልካቾች
1.1. የሁለቱም አመልካቾች የልደት ካርድ
1.2. ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ

2. የሚያጠቡ እናት አመልካቾች
2.1. ስድስት (6) ወር ያልሞላው የህጻኑ/ኗ የክትባት ካርድ
2.2. ከተማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ

3. የተለያዩ የጤና ዕክል ያለባቸው አመልካቾች
3.1. ከመንግስት ሆስፒታሎች የቦርድ ወሳኔ የተሰጠበት የህክምና የምስክር ወረቀት
3.2. ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ የመያስፈልጉ መሆኑን እንገልጻለን።

መረጃው ለሚያስፈልጋቸው በማጋራት እገዛችሁን አድርጉ።

@dbu11
@dbu111
👌1
አስደሳች ዜና

ከነሐሴ 20-ጷግሜ 5/2017 ዓ.ም


"በጎፈቃደኝነት ለጤናማ ማህበረሰብ" በሚል መሪ ቃል በደብረብርሀን ዩንቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሐኪም ግዛው ሆስፒታል በምስሉ ላይ በተያያዙት የጤና ምርመራ አገልግሎቶች ነፃ የምርመራ አገልግሎት እንደሚሰጥ በይፋዊ የ ማህበራዊ ሚዲያ ገፁ አስታውቋል።☝️☝️☝️

@dbu11
@dbu111
👏6😢2
ደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ስልክ እንዳይዙ መከልከሏን የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገበዋል።

ደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ ስማርት ስልኮችን እንዳይዙ የሚከለክል እና በፈረንጆቹ 2026 ተግባራዊ የሚደረግ ህግ ማፅደቋ ተሰምቷል፡፡

በመንግስት ጥናት መሰረት ከሀገሪቱ ህዝብ 25 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የስማርት ስልኮች ሱስ ውስጥ እንደሚገኝ እና እድሜያቸው ከ10 እስከ 19 ከሚሆኑት ታዳጊዎች 43 በመቶ ያህሉን ድርሻ እንደሚወስዱ ነው የተዘገበው።

@dbu11
@dbu111
👍17👏3
ማስታወቂያ!
የNGAT ፈተና ለመፈተን ፍላጎቱ ላላችሁ!

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ለሚሰጠው የNGAT ፈተና ለመፈተን ፍላጎቱ ያላችሁ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር (National Id Number) አስፈላጊ መሆኑን አውቃችሁ፤ የምዝገባ ጊዜ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እስኪገለጽ ድረስ አስፈላጊውን ቅድም ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።

@DBU11
@DBU111
👍4👏2
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠበቅባቸውን መሥፈርቶች ማሟላት ካልቻሉ ሰፋ ያለ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚደረጉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፡፡

ሚንስትሩ ይህን የተናገሩት ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በዳግም ምዝገባ አፈጻጸም ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ነው።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በወቅቱ ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ቦታ እየሰጡ መሄድ ያስፈልጋል በሚል ከግል ተቋማት ጋር ከአራት ዓመታት ጀምሮ እየተሠራ እንደሆነ፣ ዳግም ምዝገባን በተመለከተም ባለፉት ሦስት ዓመታት ስለመሥፈርቱ የማሳወቅ ሥራ ሲከናወንና የማያሟሉ በዘርፉ መቀጠል እንደማይችሉ ሲገለጽ መቆየቱን አንስተዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም ባለፉት ዓመታት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰብሰብ ብለው እንዲሠሩ ሲጠየቅ እንደነበር፣ በተደረገው ግምገማ ውጤት መሠረትም እንዲሻሻሉ የጊዜ ገደብ መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡

በዚህ ጊዜ ውስጥም አሻሽለው የሚመጡ ተቋማት በዘርፉ እንደሚቀጥሉ የገለጹት ሚንስትሩ፣ ያላሻሻሉት ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ለኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንደማይመጥኑ እና ከዚህ በፊት በነበረው ሁኔታም መቀጠል እንደማይቻል አመላክተዋል፡፡

የግል ኮሌጆች እንዲዘጉ የተለየ የግል ምክንያት እንደሌለ ገልጸው፣ “ፍላጎታችን ግን ሳይማር ዲግሪ የሚሰጠው ተማሪ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይኖርና እንደ አገርም ተቀባይነት ስለማይኖረው ነው” ብለዋል።

አያይዘውም መሰል ግምገማ በመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይም እንደሚደረግ ጠቅሰው በዚሁ አሠራር መሠረት ይዘጋሉ ብለው የሚታሰቡት የግሎቹ ብቻ ሳይሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ጭምር መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በዚህም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተቀመጡ መሥፈርቶችን ማሟላት ካልቻሉ የሚኖራቸው ጥቅም እንደሚጤን በመግለጽ፣ ሰፋ ያለ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚደረጉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል መግለጻቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

በመድረኩ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለዳግም ምዝገባ የተቀመጡ መሥፈርቶች ከፍተኛ ወጪና ጊዜ የሚጠይቁ በመሆናቸው የተሰጣቸው ጊዜ እንዲራዘም መጠየቃቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

በመዲናዋ በዳግም ምዝገባ ከተመዘገቡ 290 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሶስቱ ብቻ መስፈርቱን አሟልተው መገኘታቸውን በመድረኩ ላይ መገለጹ ተዘግቧል።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለመመዝገብ በተዘጋጀው አዲሱ የዳግም ምዝገባ መገምገሚያ መስፈርት 375 ተቋማትን ለመመዝገብ ታቅዶ 290 ተቋማት መመዝገባቸውን በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሕይወት አሰፋ ገልጸዋል።

290 ተቋማት ተመዝግበው በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ግምገማ መስፈርቱን ያሟላ ተቋም ባለመኖሩ መስፈርቱ ተሻሽሎ ሁለተኛ ዙር ግምገማ መካሄዱን አንስተዋል፡፡

ተቋማቱ ራሳቸውን አብቅተው በትምህርት ሥርዓቱ እንዲቀጥሉ በማሰብም 3ኛ ዙር መስፈርቱን በማሻሻል ዝቅተኛውን መስፈርት እንዲያሟሉ ዕድል መሰጠቱን ገልጸው፤ በአዲስ አበባ ከተማ 3 ተቋማት በ3 ካምፓስ በ17 የትምህርት መስክ ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልተው ፈቃዳቸው መጽናቱን ተናግረዋል።

በ12 ወራት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን እንዲያሟሉ ቅድመ ሁኔታ የተሰጣቸው ደግሞ 25 ተቋማት ፤ በ37 ካምፓስ በ146 የትምህርት መስክ የተገጓደሉትን እንዲያሟሉ መደረጉን አስረድተዋል።

@DBU11
@DBU111
👍5👌4👏1🤬1
2025/10/25 09:53:28
Back to Top
HTML Embed Code: