Telegram Web Link
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የህግ ኮሌጅ በዛሬው እለት ከተማሪዎቹ ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱም የ2017 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደት ግምገማ የተደረገ ሲሆን የ2018 ዓ.ም እቅድም ቀርቧል።

በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ እና በተማሪዎች ምዘናና ግምገማ ላይ ከዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሌጅስሌሽን መማሪያ አንፃር ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከተማሪዎች ለተነሱ ሀሳቦች እና ጥያዎችም ምላሽ ተሰቷል።

@DBU11
@DBU111
👍2
#Ads
💡Nadian Graphic Design Acadamy
2ተኛ ዙር የonline Telegram Graphic Design ስልጠና

- በመጀመሪያ ዙር ክላስ ተማሪዎችን የመጀመሪያ ስራቸውን ከእኛ አግኝተዋል

🎨አሁን በሁለተኛ ዙር ደሞ 20 ተማሪዎችን ብቻ በ3 ወር
📌 Adobe photoshop እና Adobe illustrator
📌 logo design
📌social media poster
📌flayer and brochure
📌 የ graphics design ስራን የሚያቀሉ AI ስልጠና

📍portfolio አብረን እንገነባለን የመጀመሪያ ስራችሁን እኛ እንሰጣችኋለን

ለመመዝገብ 👉💡@Nadians_Bot

📌 ምዝገባዉ ሚቆየዉ እስከ ጥቅምት 05/2018 E.C ብቻ ነዉ
🤬3😢1
#MESA

ለአዲስና ነባር የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች በሙሉ

የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር (MESA) አዲስ ወደ ሜካኒካል ምህንድስና የተመደቡ ተማሪዎችን ለመቀበል እና ከነባር የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች ጋር የትውውቅ መርሀግብር ስለተዘጋጀ በቀን 25/01/2018 ዓ.ም ማለትም እሁድ 8:30 SE 13 F2 04 እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር

@DBU11
@DBU111
የመካከለኛው ዘመን ታላቁ ንጉስ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን የሚመለከተው መፅሐፍ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በክብር ተመርቋል።

📘 የመፅሐፉ መረቃ
- ደራሲዎቹ ዶ/ር አንዷለም አባተ እና አቶ ቴዎድሮስ ደመቀ ናቸው።
- መፅሐፉ 542 ገጾች ያሉት ነው።

- የዩኒቨርሲቲው አስፈጻሚዎች፣ ዲኖች፣ ምሁራን፣ እንግዶች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች በምርቃት ዝግጅቱ የተሳተፉ ሲሆን የቋንቋና ታሪክ ማእከል በዩኒቨርሲቲው ስር ይህንን ፕሮግራም አዘጋጅቷል።

📚 የመፅሐፉ ይዘት
- የአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማቲክ፣ ወታደራዊና ሐይማኖታዊ ስራዎችን በታሪካዊ ሰነዶችና ምስሎች በመደገፍ ያቀረበ ነው።

🗣️ አስተያየቶች
- የታሪክ ተመራማሪዎች እና ምሁራን መፅሐፉን እንደ ታሪካዊ ምንጭ አከብረው አድናቆት አሳይተዋል።
- የዩኒቨርሲቲው አስተባባሪዎች የታሪክን ማስተዋወቅ እና ማስጠናት ላይ ድርሻ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

🌟 የመፅሐፉ አላማ
- የአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታሪክን ከተሳሳተ ትርክት አነጻጽሮ እውነተኛ መረጃ ማቅረብ እንዲሁም
- ኢትዮጵያ ከዓለም ጋር ያላትን ግንኙነት በታሪካዊ መሠረት ማብራሪያ ማቅረብ እንደሆነ ተገልፁአል።


@DBU11
@DBU111
👏16👍4👌4🤔1
የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ብሄራዊ የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑ ተገለፀ።

@DBU11
@DBU111
👏4🤬3
📦 BT Legacy Collection – Coming Soon!

We’re excited to announce the upcoming launch of BT Legacy Collection, a curated online shopping experience designed for everyday needs and student essentials.

From jewelry electronics, fashion, perfumes, and deodorants, to practical items for daily life and university use—we’ve got you covered.

Our products are sourced from trusted suppliers in
_Dubai, China, India, Europe_ and across Ethiopia, ensuring quality, variety, and affordability.

Whether you're looking for something stylish, functional, or unique—BT Legacy Collection is your new go-to destination.

🛍️ Launching soon. Stay tuned.

luxury you live, legacy you leave
👌2👏1
የሬሚዲያል ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ

@DBU11
@DBU111
2018 Academic Calendar.

@DBU11
@DBU11
👍1
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ከአሁን ሰዓት ጀምሮ፦
Website:  https://student.ethernet.edu.et
Telegram bot: @moestudentbot አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የRemedial ፕሮግራም ምደባ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@Dbu11
@Dbu111
👍1
ማስታወቂያ
notice

ተማሪ ብርቱካን ኤርሚያስ ት/ት ክፍል IS
ተማሪ ሀና ተስፋዬ ት/ት ክፍል  Agro Economics
የሆናችሁ ተማሪዎች የ Non-Cafe መረጃችሁ የተማሪዎች ምግብ ቤት ሄዳችሁ
እንድታስተካክሉ እናሳውቃለን።

@DBU11
@DBU111
👍2
እንኳን ደህና መጣችሁ 👏👏 የ2018 አዲስ ተማሪዎች

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ 130 ኪ.ሜ ርቀት ከክልሉ መዲና ባህርዳር 690 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች  ፡፡

ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሀን መንገድ  ከ2:00ሰአት እስከ 2:30 ሰአት ጉዞ ነው ፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን ለመጓዝ በዋነኝነት የላምበረት መነሀሪያን እንደ አማራጭ የቃሊቲ መነሃሪያን መጠቀም ትችላላችሁ ፡፡

ከአዲስ አበባ አስከ ደብረ ብርሀን ሲጓዙ  እነዚህ ከተሞች ይቃኛሉ ፡፡ ለገጣፎ፡ ለገዳዲ፡ ሰንዳፋ ፡ በኬ፡አሌልቱ ፡ፍቼ ገነት ፡ ሀሙስ ገበያ፡ ሸኖ፡ ሰምቦ ፡ጨኪ ፡ ጫጫን  በመጨረሻም ደብረ ብርሀን ፡፡

እንኳን ደህና መጣችሁ
👇👇👇👇👇👇👇
የደብረ ብርሀን ከተማ በ1446 ዓ.ም በአፄ ዘረያቆብ ተመሰረተች ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ዋና መናገሻም ሆና አገልግላለች ፡፡ ከተማዋ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚ እየተናቃቃች ያለች የኢንደስትሪ ከተማ ናት ፡፡ 

ከተማዋ ከባህር ጠለል በላይ 2750 እስከ 2850 ድረስ ከፍታ ያለው ነው በመሆኑም የአየር ሁኔታው ብርዳማ እንዲሆን ያደርገዋል ፡፡ የከተማው አመታዊ የሙቀት መጠን 10°ዲግሪ ሴልሲየስ ነው ፡፡

በ2000ዓ.ም  ግንቦት ወር የሙቀት መጠኑ ከዜሮ በታች 6.6 ማለትም -6.6 ደርሶ ነበር በወቅቱ የነበረው ከፍተኛ ብርዳማ አየር ከተማዋ በታወሰች ቁጥር ብርዳማዋ ከተማ እየተባለች እንድትነሳ አድርጓል ፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሙቀት መጡኑ ቀዝቃዛ ቢሆንም እንደቀድሞ ብርዳማ የሚባል አይደለም ፡፡( ቢሆንም ወፈር ያለ ልብስ ብትይዙ ይመረጣል)

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ
👇👇👇👇👇👇👇

የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተው 1999 ዓ.ም ነው ፡፡ 

ዩኒቨርሲቲው አገልግሎት ሲጀምር በ725 ተማሪወች  ነበር ።


ዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ  የሚገኘው ጠባሴ የሚባል አከባቢ ሲሆን ወደ ከተማ ለመሄድ  ታክሲ መጠቀም የግድ ነው ።


የህክምና ትምህርት  ግቢ(ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ)  በከተማው መሀል ላይ 04 ቀበሌ (ማዕከል) ይገኛል ፡፡


መንዝ መሀል ሜዳ ካምፖስ አዱስ የተገነባው ግቢ ሲሆን : ከደብረ ብርሀን በ150Km ርቀት ላይ ይገኛል ።

ለአዲስ ተማሪወች
👇👇👇👇👇👇

ለአዲስ ተማሪዎች ወደ ግቢ ስትመጡ
ከመግቢያው እስከ ዶርም የሚያደረሱ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች አሉ ፡፡ በግቢ ውስጥ 2ካፌ ፡  3 የተማሪወች ላውንጅ  5 ላይብረሪዎች ፡2 የተማሪ ሱቆች እንዲሁም 1 ጁስ ቤት  ይገኛሉ ፡፡

ለአዲስ ተማሪወች  መማር አማራጭ የሌለው ነገር ነው ፡፡ 👉ክላስ መከታተል ፡👉ማንበብ 👉ውጤት መስራት  እነዚህ የሁል ጊዜ ተግባሮች መሆናቸውን አትርሱ ፡፡

❗️❗️የዘመኑ አፃያፊ በሽታ ዘረኝነት፡ ጎጠኝነት ፡ መንደርተኛነት በዩኒቨርሲቲው ቦታ ስለሌላቸው እዛው ተፈውሳችሁ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን ፡❗️፡ ዩኒቨርሲቲው ከሁሉም የሀገሪቷ ክፍል የሚመጡ የኢትዮጵያ ልጆች መነሀሪያ ስለሆነ በመከባበር ፡ በመተሳሰብ መኖር ግዴታ ነው፡፡

ጥሩ ግዜ እንደምታሳልፉ ተስፋ እናደርጋለን ፡፡

ነፃ ሀሳብ እና አስተያየት በDbu Daily news discussion ግሩፕ  ላይ መስጠት ይቻላል ፡፡


@ wende abebe መ'ኪያ

@DBU11
@DBU111
👏39😢2👍1🤔1👌1
2025/10/19 22:31:52
Back to Top
HTML Embed Code: