Telegram Web Link
አውሮፕላኑ ደመናን እየሰነጠቀ በመብረር ላይ ነው፡፡ በድንገት ሚዛኑን በመሳት በአስፈሪ ሁኔታ መንገጫገጭ ጀመረ፡፡

ሁሉም ተሳፋሪ ከፍርሀት በመነጨ መልኩ መጮኽ ጀመረ፡፡ ነገር ግን አንድ የ8 አመት ህፃን ምንም ሳይሰማት በአሸንጉሊቷ ትጫወታለች፡፡

ከሰዓት በኀላ አውሮፕላኑ በሰላም አረፈ፡፡ አንድ ሰው ትንሿን ህፃን እንዲ ብሎ ጠየቃት፡፡ "ሁሉም ሰው እንደዛ በድንጋጤ እየጮኽ እንዴት አንቺ በአሸኔጉሊት ትጫወቻለሽ?"

ትንሿ ልጅ በፈገግታ እንዲ ስትል መለሰች፡፡ "አብራሪው አባቴ ነው፤ በሰላም እንደሚያሳርፈኝ ስለማውቅ ነው፡፡"

ፍቅር እምነት ነው፤ እምነት ደሞ ህይወት፡፡ እኛስ ከፈጣሪ በታች በአስቸጋሪ ወቅት እንኳን የምናምናቸውና ተስፋ የምንጥልባቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆን???
#1 ለምታሳድጋቸው ዶሮዎች እህልና አሽዋ ቀላቅለህ ብትሰጣቸው ዶሮዎቹ
የሚበሉት የትኛውን ይመስልሃል?
እህሉን እንደምትለኝ እርግጠና
ነኝ፡፡ አንተም ሕይወትህ የሚጠቅመውን ከማይጠቅመው መለየትን ልመድ፡፡
ምክንያቱም በመልካም ማሳ ውስጥ ማይጠቅም እንክርዳድ ወይም አረም አይጠፋምና፡፡

#2 አምስት ዶሮዎች አሉህ ብለን እንገምት፤ ለአምስቱ ዶሮዎችህ ሀያ አምስት ጥሬ ብትበትንላቸው ለእያንዳንዱ
ዶሮ ስንት ስንት ጥሬ ሚደርሳቸው
ይመስልሃል?

5 የሚል ከሆነ መልስህ በእርግጥም ተሳስተሀል፡፡ ምክንያቱም ዶሮዎቹ የሚደርሳቸው የጥሬ ብዛት በዶሮዎቹ ቅልጥፍና ይወሰናል፡፡ አንተም በህይወትክ ለመልካም እና ጠቃሚ ለሆኑ ነገሮች ቀልጣፋ ሁን፡፡
አንዲት ሴት በአንድ ወቅት እንዲህ ተብላ ተጠየቀች: አዘውትረሽ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይሽ ምን "ትርፍ" ታገኛለሽ?
እሷም መለሰች፡- ብዙውን ጊዜ "ምንም አላገኘሁም", ይልቁንም "ነገሮችን አጣለሁ".
እናም ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ያጣችውን ሁሉ ጠቀሰች፡-

ኩራቴን አጣሁ።
ትዕቢቴን አጣሁ።
ስግብግብነት አጣሁ።
ፍላጎቴን አጣሁ።
"ቁጣዬን" አጣሁ።
ፍትወት አጣሁ።
የመዋሸት ደስታ አጣሁ።
የኃጢአት ጣዕም አጣሁ።
ትዕግሥት ማጣት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ እና ተስፋ መቁረጥ ።

አንዳንድ ጊዜ የምንጸልየው አንድን ነገር ለማግኘት ሳይሆን በመንፈሳዊ እንድናድግ የማይፈቅዱልንን ነገሮች እንድናጣ ነው።

ጸሎት ያስተምራል፣ ያጠናክራል እናም ይፈውሳል።
ተገኘ ከፌስቡክ መንደር
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏


፦ፍቅር የለም ከማለትህ በፊት፣ እኔ ውስጥ ፍቅር አለ ወይ? ብለህ ፈትሽ!

፦ሚስት የምትሆን ሴት የለችም ፣ ከማለትህ በፊት እኔ ባል መሆን ችላለሁ ወይ? ብለህ ራስህን መርምር!

፦ወንድ እንጂ ባል የለም ከማለትሽ በፊት፣ እኔ ጥሩ ሚስት መሆን ችላለሁ ወይ? ብለሽ ራስሽን ጠይቂ!

፦ጥሩ ጉዋደኛ የለም ከማለትሽ በፊት እኔ ጥሩ ጉዋደኛ መሆን ችላለሁ ወይ? ብለሽ አስቢ!

፦ማንም ሰው ጥሩ ከሆነ፣ ጥሩ ነገሮች ሁሉ ከሱ መራቅ አይችሉም። ስለዚህ ጥሩነትን ከሰው ሳይሆን ከራሳችን ነው የምናገኘው።

መልካም ሁን፣
ቅን ሁን፣
ትሁት ሁን፣
ወዳጅ ሁን፣
ፍቅር ሁን፣
ሩህሩህ ሁን፣
ለጋሽ ሁን፣
አስተዋይ ሁን፣
ደስተኛ ሁን፣
ሳቂታ ሁን፣
መፍትሄ ሰጪ ሁን፣
ተፅዕኖ ፈጣሪ ሁን፣
አመስጋኝ ሁን፣
በትንሽ የምትደሰት ሁን፣
ብልህ ሁን፣
አስታዋሽ ሁን፣


በምድር ላይ ከሰው ልጆች ውጪ ምንም ውድ ነገር የለም። አንተን የሚገዛ የገንዘብ መጠን የለም።  ለራስህ ክብር ስጥ፤ አንተ ውድ መሆንህን ካመንህ ሰዎችም ውድ መሆናቸውን አትዘንጋ። አክብራቸው ሰው በመሆናቸው ብቻ!!!

🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን
#የሽንት #ቀለም #ስለጤናችን #ምን #ይነግረናል?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

#የውሃን ያህል ንፁህ የሆነ ሽንት
ይሄ የሚያሳየው አብዝተን ውሃ እንደምንጠጣ ሲሆን ሰውነታችን ከሚያስፈልገው የውሃ መጠን በላይ መውሰዳችንን ይጠቁማል ወይንም ከዚህ በተጨማሪ ቶሎ ቶሎ ሽንታችን ከመጣና ውሃ የሚጠማን ከሆነ የስኳር ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

👉👉 #ፈዛዛ ቢጫ ቀለም ያለዉ ሽንት
በአብዛኛው የጤናማ ሰው ሽንት የሚያሳየው ቀለም ሲሆን ውሃ በበቂ ሁኔታ መጠጣቱን ያመለክታል፡፡

👉👉 #ደማቅ ቢጫ ቀለም ያለዉ ሽንት
በቫይታሚን ቢ12 እጥረት ሲኖር ፤የጉበት እና ሀሞት ከረጢት ላይ ችግር እንዳለ ይጠቁመናል፡፡

👉👉 #ጠቆር ያለ ቢጫ ቀለም ያለዉ ሽንት:- ይሄ ደግሞ ውሃ በበቂ ሁኔታ እየጠጣን እንዳልሆነ እና በሰዉነታችን ዉስጥ የፈሳሽ እጥረት እንዳለ ይጠቁመናል፡፡

👉👉 #ቡናማ ቀለም ያለዉ ሽንት
ቡናማ የሽንት ቀለም በውስጡ ደም እንዳለ የሚያሳይ ሲሆን የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ፣ በጉበት እና በኩላሊት ችግር መኖሩን ጠቋሚ ነው።

👉👉 #አረንጓዴ ቀለም ያለዉ ሽንት
የሽንት ቀለም አረንጓዴ ቀለም ካለዉ  የሀሞት ከረጢት ላይ ችግር፣ ተቅማጥ እና የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ሲኖር ሊከሰት ይችላል፡፡

👉👉 #ቀይ ቀለም/ደም የቀላቀለ ሽንት
የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ወይም መዘጋት ፣የሽንት ፊኛ ጠጠር/ኢንፌክሽን፤ የኩላሊት ችግር፤ የፕሮስቴት እጢ ማደግ እንዲሁም ካንሰር እንዳለ ይጠቁመናል፡፡

👉👉 #ጥቁር ቀለም ያለዉ ሽንት
ጥቁር የሽንት ቀለም የጤና ሁኔታ ከባድ ችግር እንዳለ ስለሚጠቁመን በአፋጣኝ ተገቢዉን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነዉ፡፡

👉👉 #የሽንት ቀለም መለወጥ ከጤና ችግሮች በተጨማሪ ከምንመገበዉ ምግብ፣ከምንጠጣዉ መጠጥ እንዲሁም የምንወስዳቸዉ መድሐኒቶች ካሉ ሊከሰት ይችላል፡፡ እርስዎስ የሽንት ቀለምዎትን አስተዉለዉ ያዉቃሉ ለዉጥ ካስተዋሉ ይመርመሩ።
በህይወቴ ከተማርኩት ነገር ውስጥ አንደኛው ለሰዎች #መልካም ነገር ብታደርግ ለመልካምነትህ ከሰዎች ዘንድ ምላሽ መጠበቅ ሊጎዳ እንደሚችል ነው።

አንዳንዱ መልካም ስታደርግ ሞኝ
እንደሆንክ ሊቆጥርህ ይችላል።

አንዳንዱ ደግሞ ከእሱ የሆነ ነገር
ፈልገህ የምታደርግለት ይመስለዋል።

ሌላኛው ደግሞ ከምስጋና
ይልቅ ጠላትህ ሊሆን ይችላል።

እናም እልሀለሁ #ለመልካምነትህ
ከሰዎች ምላሽን አትጠብቅ!
ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ምላሹ
ምንም ይሁን ምን #መልካምነት አብሮህ ይሁን!  ፈጣሪ ይከፍልሀልና!!!
✍️#የትኛው #የደባቴ (#depression) #አይነት #ያጠቃዎታል?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

🔹ሜጀር ዲፕሬሲቭ ዲስኦርደር (ኤምዲዲ)/Major depressive disorder(MDD) ፡- ከፍተኛ የመንፈስ ጭንቀት ሲሆን (ክሊኒካዊ ዲፕሬሽን) ይባላል፡፡ ከሁለት ሳምንት በላይ የሚቆዩ ኃይለኛ ወይም አስጨናቂ ምልክቶች አሉት። እነዚህ ምልክቶች በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ጣልቃ ይገባሉ፡፡

🔹ባይፖላር ዲፕሬሽን/ Bipolar depression፡- ባይፖላር ዲስኦርደር ያለባቸው ሰዎች ተለዋዋጭ የዝቅተኛ ስሜት እና እጅግ በጣም ከፍተኛ ሃይል (ማኒክ) ወቅቶች አላቸው። በዝቅተኛ ጊዜ ውስጥ፣ እንደ ሀዘን ወይም ተስፋ መቁረጥ ወይም ጉልበት ማጣት ያሉ የመንፈስ ጭንቀት/ዲፕሬሽን ምልክቶች ሊኖራቸው ይችላል።

🔸 የፐርናታል እና የድህረ ወሊድ ጭንቀት/ Perinatal and postpartum depression ፡- “Perinatal” ማለት በወሊድ አካባቢ ማለት ነው። ብዙ ሰዎች ይህንን አይነት ዲፕሬሽን ከወሊድ በኋላ የመንፈስ ጭንቀት ብለው ይጠሩታል። የወሊድ ጭንቀት በእርግዝና ወቅት እና ልጅ ከተወለዱ በኋላ እስከ አንድ አመት ድረስ ሊከሰት ይችላል፡፡ ምልክቶቹ ሀዘን፣ ጭንቀት ወይም መረበሽን ያካትታሉ።

🔸 የማያቋርጥ ዲፕሬሲቭ ዲስኦርደር/ Persistent depressive disorder (PDD)፡- ፒዲዲ ዲስቲሚያ / dysthymia ተብሎም ይታወቃል። የ PDD ምልክቶች ከከባድ የመንፈስ ጭንቀት ያነሱ ናቸው፤ ነገር ግን PDD ያለባቸው ሰዎች ከሁለት አመታት ወይም ከዚያ በላይ የፒዲዲ ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡

🔹 ከወር አበባ በፊት የሚመጣ ዲስፎሪክ ዲስኦርደር/ Premenstrual dysphoric disorder (PMDD)፡ ከወር አበባ በፊት የሚመጣ ዲስፎሪክ ዲስኦርደር በጣም ከባድ የሆነ የቅድመ የወር አበባ መታወክ (PMS) ነው። ከወር አበባቸው በፊት ባሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ሴቶችን ያውካል፡፡

🔹 ሳይኮቲክ ዲፕሬሽን /Psychotic depression ፡- ሳይኮቲክ የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች ከባድ የጭንቀት ምልክቶች እና ውዥንብር ወይም ቅዠቶች አሉባቸው። ቅዠቶች በእውነታ ላይ ያልተመሠረቱ ነገሮች ማመንን ጨምሮ ማየትን፣ መስማትን ወይም በእውነታው የሌሉ ነገሮች መነካትን ያካትታሉ::

🔸 ወቅታዊ አፌክቲቭ ዲስኦርደር/ Seasonal affective disorder (SAD)፡ ወቅታዊ የመንፈስ ጭንቀት፣ ወይም ሴሶናል አፌክቲቭ ዲስኦርደር፣ ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በ ክረምት መጨረሻ እና በክረምት መጀመሪያ ወቅታ ላይ ነው። ብዙውን ጊዜ በፀደይ እና በበጋ ወቅት ይጠፋል::

🔸ዲፕሬሽን ጋር በተያያዘ የሥነ ልቦና ባለሙያ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞች ላይ እየደወሉ የየዕለቱን የሥነ ልቦና ላይ ለውጦችዎን በማማከር ነገ ከሚከሰት የሥነ ልቦና ችግር አስቀድመው ራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ ይንከባከቡ፡፡
ሁሌም እልሀለው ዛሬም እደግመዋለሁ "ትላንት በህይወትህ ያለፈውን መጥፎ ቀን ማጥፋትም መቀየርም መሰረዝም አትችልም፤ የምትችለው መቀበል ብቻ ነው"፡፡ ትላንትን አምነህ ተቀብለህ ዛሬን በደስታ ኑር፡፡

አስተውል ዛሬ አዲስ ቀን ነው ከቀኑ ጋር አዲስ መሆን ያንተ ፋንታ ነው፡፡

የተወለወለ ቤት በጭቃ እግርህ ብትገባ ቤቱን ታበላሸዋለህ፤ ልክ እንደዛው በትላንት መጥፎ ሀሳብ ዛሬንም ከተቀበልከው እንደዛው ነው!!! ስለዚህ ዛሬን ከቀኑ ጋር አብረን አዲስ እንሁን፡፡

🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን
#የአይን #ዙርያ መጥቆር #አጋጥሞዎታል?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

👉👉 #የአይን ዙርያ መጥቆር አብዛኛውን ጊዜ በዙርያው ላይ ማበጥ እና ቀይ ቀለም መቀየር በአጭር ጊዜ ሊከሰት ይችላል በመቀጠል ወደ ጥቁር ሰማያዊ ቀለም ይቀየራል ቀስ እያለ እየደበዘዘ ይመጣል የደበዘዘውም ከ 10 - 15 ቀናት ውስጥ ይጠፋል ፡፡

👉👉 #መንስኤዎች ምንድን ናቸው ?

🔵 በቂ እንቅልፍ አለመተኛት/እረፍት አለማድረግ
🔵 የቫይታሚን ሲ እና ኢ እጥረት
🔵 ተደጋጋሚ አይን ማሸት
🔵 ለጸሃይ ብርሃን መጋለጥ
🔵 በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ
🔵 የአይን ህመም/ኢንፌከሽን
🔵 የታይሮይድ ሆርሞን ችግር
🔵 በዘር
🔵 ደም ማነስ
🔵 ምት
🔵 እድሜ እየጨመረ ሲመጣ

👉👉 #ምልክቶች

🔵 የአይን ስር ወይም ዙርያው ቀለም መቀየር
🔵 እብጠት
🔵 አይን መቅላት ይጀምርና ዙሪያው ይጠቁራል
🔵 አይን አካባቢ የህመም ስሜት መኖር
🔵 የአይን እይታ መቀነስ
🔵 ቀለል ያለ ራስ ምታት ወይም የአንገት ህመም

👉👉 #የቤት ውስጥ ህክምና

🔵 በጥንቃቄ የበረዶ ፓክ ወይም በቀዝቃዛ ጨርቅ ከ 10 – 15 ደቂቃ ቦታው ላይ ማስቀመጥ
🔵 በቂ እረፍት መውሰድ፣ በቂ ፈሳሽ መውሰድ
🔵 በተጎዳው ቦታ ላይ ሙቅ ውሃ መጠቀም ህመሙ ካለ ይቀንሰዋል
🔵 ጭንቅላትን ቀና አድርጎ መተኛት
🔵 የታይሮይድ ሆርሞን መታየት
🔵 የደም ማነስ ካለ ያንን ማከም
🔵 ኩከምበር አይን ላይ መያዝ
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

"አቧራ የጠገበን ምንጣፍ በዱላ የምትመታው አቧራውን ለማራገፍ እንጂ ምንጣፉን ለመጉዳት አይደለም።

የሰውን ድክመት የምትነግረውም ስህተትን እንዲያርም እንጂ ሰውዬው በእራሱ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ አይደለም።"

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌
እርጉዝ ሴት እንዴት መተኛት አለባት?
********
በእርግዝና ወቅት በተለመደው መንገድ መተኛት ምቾት ለምን ይነሳናል ? ምክንያቱም በእርግዝና ወቅት ብዙ ለውጦች ስለሚመጡ ምቾት አይኖረንም
፡-የሆድ መጠን ይጨምራል
፡- የጀርባ ህመም
፡-የደረት ህመም
፡-የትንፋሽ ማጠር
፡-የእንቅልፍ እጦት እነዚህ ምቾት እንዳይኖር ያደርጋሉ

👉 በእርግዝ ወቅት ተመራጭ ወይም መሆን ያለበት አተኛኘት
በአብዛኛው ተመራጭ የሚሆነው በጎን መተኛት ነው ለፅንሱም ለእናትየውም መቾት ይሰጣል

 አንዱን እግር ዘርግቶ ከላይ ያለውን እግር ማጠፍ በሁለቱም እግር መሃል ትራስ መጠቀም

 የጀርባ ህመም ካለ በጎን መተኛት እናም ከሆድ ስር ትራስ ለመጠቀም መሞከር

 በምሽት የደረት ማቃጠል ካለ ከወገብ በላይ ትራሶችን መጠቀም

 ቀኑን ያሳለፈ እርግዝና ከሆነ የትንፋሽ ማጠር ይከሰታል በዚህ ጊዜ በጎን ተኝቶ ከፍ ለያደርግ የሚችል ትራስ መጠቀም፡፡

ይህም ማለት ሁልግዜ ምቾት ይሰማናል ማለት አይደለም ስለዚህ አቅጣጫ እየቀያየርን መተኛት አለብን የደም ዝውውራችን ጤናማ እንዲሆን መገላበጥ አለብን ስንገላበጥ ግን ተነስተን ትንሽ ቁጭ ብለን መሆን አለብት፡፡

👉👉 በእርገዝና ወቅት ማስወገድ ያለብን አተኛኘት
 በጀርባ መተኛት ፡- የጀርባ ህመምን ፡የአተነፋፈስ ችግርን ፡ የመቀመጫ ኪንታሮትን ፡ዝቅተኛ የሆነ የደም ግፊትን እና
የደም ዝውውርን ለልብ እና ለሰውነታችን መቀነስ የመሰሉትን ያመጣል

 በሆድ መተኛት፡-በእርግዝና ጊዜ ሆድ እየገፋ አካላዊ ለውጥ ይኖራል እና ሆድ መተኛት በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡
2025/07/09 20:11:24
Back to Top
HTML Embed Code: