Telegram Web Link
#በባዶ #ሆድ #ውሃ #የመጠጣት #የጤና #ጥቅሞች

👉1. በባዶ ሆድ ውሃ መጠጣት አንጀትን በማጽዳት ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በቀላሉ እንዲመጥ ይረዳናል፡፡
👉2. አዲስ የደም እና የጡንቻ ሴሎች እንዲመረቱ ያደርጋል።
👉3. ክብደትን ለመቀነስ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ጠዋት ከእንቅልፍዎ ሲነሱ ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት ሜታቦሊዝምን ያፋጥናል፡፡
👉4. ሲያዩት የሚያምርና ጤናማ የሆነ ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ውሃ በደም ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ነገሮችን ጠራርጎ በማስወጣት ቆዳችን ንጹህ፣ ለስላሳና አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
👉5. የሊምፍ ሥርዓታችን (Lymph System) የተመጣጠነ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ እነዚህ ዕጢዎች የዕለት ከዕለት ተግባራችንን በትክክል እንድንወጣ፣ የሰውነታችን ፈሳሽ የተመጣጠነ እንዲሆን እና ኢንፌክሽንን እንድንዋጋ ይረዱናል፡፡
#ውሃን #በመጠቀም #የሚደረግ #ህክምና
በአሁኑ ጊዜ ከወደ ጃፓን የመጣ አዲስ ልምድ አለ ጃፓኖች በሚመገቡበት ጊዜ ለብ ሻይ ይጠጣሉ ይህም ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው ህክምና ሲሆን ይህ ህክምና ከጠዋት ጀምሮ ቀኑን ሙሉ በተወሰነ የጊዜ ልዩነት ውሃ መጠጣትን ያካትታል፡፡ ይህም ህክምና በሚጀምሩበት ሰሞን በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት የሚያጋጥም ሲሆን በጃፓን የህክምና ማህበር ከብዙ በሽታዎች የመፈወስ አቅሙ 100% መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
ከነዚህም በሽታዎች መካከል የራስ ህመም፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም፣ የልብ ህመም፣ አርትራይተስ፣ ለፈጣን የልብ ምት፣ ለሚጥል በሽታ፣ ለአስም፣ ቲቢ፣ መንጋጋ ቆልፍ፣ ለኩላሊትና ሽንት በሽታ፣ ማስመለስ፣ ጨጓራ፣ ተቅማጥ፣ ለሆድ ድርቀት፣ ለሁሉም የአይን በሽታ፣ ለካንሰርና የወር አበባ ችግር፣ ለጆሮ አፍንጫና ጉሮሮ ህመሞች ፈውስ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
#ቀዝቃዛ #ውሃ #መጠጣት
ምግብ በምንመገብበት ጊዜ ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት የራሱ የሆነ የጐንዮሽ ጉዳቶች አሉት፡፡ በተመገቡት ምግብ ውስጥ የሚገኝው ዘይት እንዲወፍር ያደርገዋል፤ ይህ ማለት የምግብ ስልቀጣ ሥርዓትን ከማዘግየቱ በተጨማሪ ምግብን ከሚፈጨው አሲድ ጋር ግጭት ይፈጥራል፤ አንጀታችን ምግብን በፍጥነት ይመጣቸዋል፣ ወደ ስብ(ፋት) ይቀይራቸዋል ስለዚህ ከምግብ በኋላ ያልቀዘቀዘ ወይም ትንሽ ለብ ያለ ውሃ ወይም ሾርባ ይጠቀሙ፡፡
#ህክምናው #እንዴት #ይተገበራል (የህክምናው ዘዴ)
1. ጠዋት ጥርስዎን ከመፋቅዎ በፊት 160 ሚ.ሊ. በሚይዝ ብርጭቆ አራት(4) ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡
2. ጥርስዎን ይቦርሹ ወይም ያጽዱ ነገር ግን ለ 45 ደቂቃ ምንም ዓይነት ምግብ ወይም ውሃ እንዳይወስዱ፡፡
3. ከ 45 ደቂቃ በኋላ ምግብ መመገብ ወይም ውሃ መጠጣት ይችላሉ፡፡
4. ቁርስ፣ ምሳ ወይም እራት ከበሉ ከ 15 ደቂቃ በኋላ ለሁለት(2) ሠዓት ያክል ምንም ዓይነት ምግብ ወይም ውሃ አይውሰዱ፡፡
5. ዕድሜያቸው የገፋና የታመሙ ሰዎች ከትንሽ ውሃ በመጀመር 4 ብርጭቆ ውሃ ላይ እንዲደርሱ ይመከራል፡፡
6. ይህ ህክምና በህመም ላይ የሚገኙ ወይም የታመሙ ሰዎችን የመፈወስ አቅም አለው፡፡
#ውሃ #ህይወት #ነው! 9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።

👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን:-

👉የዶክተር አለ የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/Doctoralle8809

👉 የዶክተር አለ የዩቱብ ቻነል Subscribe ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

👉 የዶክተር አለ የዶክተር አለ 8809 የቲክቶክ ገፅ Follow ያድርጉ
tiktok.com/@doctoralle8809

👉 የዶክተር አለ የአጭር መልእክት:-
👉👉👉 9102 OK
✍️ #በውጥረት #ምክንያት #የሚመጣ #ራስ #ምታት
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥️♥️#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥️♥️
👉👉 #ይህ አይነት ራስ ምታት የሚከሰተው የአንገት እና የጭንቅላት ጡንቻዎች ውጥረት ሲፈጥሩ ወይም ሲጨናነቁ ነው። የጡንቻ መጨናነቅ ለጭንቀት ፣ ለድባቴ ፣ ለጭንቅላት ጉዳት ምላሽ ሊሆን ይችላል። በማንኛውም ዕድሜ ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ ፣ ግን በአዋቂዎች እና በዕድሜ የገፉ ስዎች ላይ በጣም የተለመዱ ናቸው።
👉👉 #መንስኤ
🔵 የዓይን ውጥረት
🔵 አካላዊ ወይም ስሜታዊ ውጥረት
🔵 የአልኮል መጠቀም
🔵 ካፌይን (በጣም ብዙ መጠቀም ወይም ማቆም)
🔵 ጉንፋን
🔵 ሳይነስ ኢንፌክሽን
🔵 እንደ መንጋጋ መሰንጠቅ ያሉ የጥርስ ችግሮች
🔵 ከመጠን በላይ ማጨስ
🔵 ድካም ወይም ከልክ በላይ መሥራት
👉👉 #ምልክቶች
🔵 የሚያሠቃይ የጭንቅላት ህመም
🔵 በግምባር ላይ ወይም በጭንቅላት ጀርባ ላይ የጠበቀ ወይም የግፊት ስሜት
🔵 በጭንቅላት በአንገት እና በትከሻ ጡንቻዎች ውስጥ ህመም
👉👉 #ለህመሙ #የሚያጋልጡ #ሁኔታዎች
🔵 ሪህ
🔵 በሴቶች ላይ የሆርሞን መለወጥ ይህም በወር አበባ ዑደ በእርግዝና እና በማረጥ በሌሎች ሁኔታዎች ምክንያት ሊሆን ይችላል።
🔵 በእንቅልፍ ማጣት ወይም በሌሎች ምክንያቶች ድካም
🔵 በጭንቅላት ወይም በአንገት አካባቢ ላይ የሚደርስ ጉዳት
🔵 እንደ ጭንቀት ያሉ የአእምሮ ጤና ሁኔታዎች
🔵 ውፍረት
🔵 ጥርስ መፍጨት እና መንጋጋ መሰንጠቅ
🔵 በእንቅልፍ ልብ መታፈን
👉👉 #መከላከያ #መንገዶች
🔵 ጭንቀትን ለመቀነስ ይሞክሩ
🔵 በመደበኛ መርሃ ግብር መተኛት
🔵 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
🔵 መመገብዎን ያረጋግጡ
🔵 ኮምፒተርዎን በሚጠቀሙበት ጊዜ የብርሃን መጠኑን ይቀንሱ
🔵 እነዚህ የጤና ችግሮች ካሉብዎ ለድብርት ወይም ለጭንቀት ሕክምና ያግኙ
🔵 የራስ ምታት ማስታወሻ ደብተርን ለመጠቀም ይሞክሩ
👉👉 #ህክምናው
🔵 ጡንቻዎች ዘና ለማድረግ ሙቅ ውሃ ገላ መታጠብ
🔵 የሰውነት ክብደት መቀነስ
🔵 ዓይን ውጥረትን ለመከላከል በተደጋጋሚ የኮምፒተር ላይ ሲስሩ እረፍት ያድርጉ
🔵 በባለሙያ የታዘዙ የህመም ማስታገሻዎችን ይውሰዱ
የራሴን ጡት በራሴ መመርመር እችላለሁ ?

✍️“የራስን ጡት በራስ መመርመር” ይህ ማለት አንዲት ሴት በቤትዋ ወይም ምቾት በሚሰማት ቦታ የራስዋን ጡት መመርመር ምትችልበት ዘዴ ነው።

✍️ ይህንን ምርመራ ማንኛዋም ሴት ለ አቅመ ሄዋን ከደረሰችበት ጊዜ ጀምሮ እንድታደርግ ይመከራል። ️

✍️አንዲት ሴት የወር አበባዋ በመጣ በ መጀመርያ ሳምንት እንድትሰራ ይመከራል።

✍️ባንጻሩ ግን በተለያዩ ምክንያቶች የወር አበባዋን ማታይ ከሆነ ለምሳሌ በ እርግዝና፣በወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች ወይም እድሜዋ ገፍቶ በማረጧ፣ በየወሩ ትቀራራቢ ቀን በመምረጥ ማድረግ ትችላለች።

♦️ጥቅሞቹ

✍🏼 ለመስራት ቀላል መሆኑ እና ምንም አይነት መሳሪያ አያስፈልግም፣

✍🏼 የራስዋን ጤና እራስዋ መወሰን እንድትችል ያደርጋል፣

✍🏼ምቾትን በማይነሳ መልኩ መስራት ይቻላል፣

✍🏼 የጡት ካንሰር ገና ሳይሰራጭ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እያለ  ለማወቅ እና አስፈላጊውን ህክምና ለማድረግ ይጠቅማል፣

✍🏼 ከ 5 እስከ 10 ደቂቃ ይበቃል።
♦️የራሴን ጡት በራሴ ስመረምር ምን ምን ሂደቶችን ልከተል?

✍🏼 1. ካገኘን መስታወት ፊት አልያም ዝምብለን በምቆም፤ ክርኖቻችንን በማንቀሳቀስ እና ሁለቱንም ጡቶቻችንን በማወዳደር የተለየ ለውጥ ካለ መመልከት፣                                                                      

✍🏼2. በጀርባችን ምርመራ በምናደርግበት ጎን ከታች ትራስ በማስገባት እንጋለልና የምንመረምረውን ጡት ተቃራኒ እጆች (ግራ ጡት ከሆነ ቀኝ እጃችንን፣ ቀኝ ጡት ከሆነ ግራ እጃችንን) ጣቶች በመጠቀም፤ ከዛ ጡታችንን በማክበብ ሁኔታ እየዳበስን ማንኛውንም አይነት የተለየ ነገር ወይም እባጭ መፈለግ ነው።

✍️በመጨረሻም የጡታችንን ጫፍ ጫን በማለት ሚወጣ ፈሳሽ ወይም ደም ካለ ማየት ይኖርብናል።

✍️ዪሄንን በምንሰራበት ወቅት ማንኛውም አይነት የሚያስፈራ ወይም እንግዳ ነገር ካገኛቹ፣ አቅራቢያቹ ወዳለ የጤና ተቋም በመሄድ መታየት ይኖርባቹሃል።
መጠኑ የበዛ ጋዝ (ፈስ) አስቸግሮኛል ምክንያቱ ምን ይሆን?

👉 በአንጀታችን ውስጥ ጋዝ እንዲከማች የሚያደርጉ የተለያዩ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በትንፈሳ የምንምገው አየር፣ የምንመገበው ምግብ እንዲሁም በአንጀታችን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ባክቴሪያዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል።

👉 ለምሳሌ ምግብ አላምጠን ስንውጥ 10 ሚሊ ሊትር የሚሆን አየር አብረን እንውጣለን፣ ማስቲካ ስናኝክ በቋሚነት አየር እያስገባን ነው፤ በጥናቶች በታወቀው መሰረት በ24 ሰዓት ውስጥ 30 ሊትር የሚሆን አየር በአንጀታችን ያልፋል፡፡ ይህ አየር አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን ህይወት እንዲቀጥል የሚረዱ ነገሮችን ለሰውነት በማቀበል የድርሻውን የሚወጣ ነው፤ ከዚህ አየር ውስጥ ጠቃሚ የሆኑት ወደ ደም ይቀላቀላሉ፡፡ሌሎቹ በፈስ መልክ ይወገዳሉ፡፡

👉 ነገር ግን ፈስ ከለመዱት ውጪ ሲሆንና መጠኑ ሲበዛ ማስተካከል ያለብዎ ነገሮች እንዳሉ ጠቋሚ ነውና ሁኔታውን ለማስተካከል ማድርግ ስለሚገባዎት ነገሮች እንንገሮት፡፡

1. ምግብን ቀስ እያሉና እያሰቡ ይመገቡ
📌 በሆዳችን ውስጥ ከሚገኘው ጋዝ አብዛኛውን የሚሆነው በመዋጥ የሚገባ ነው፤ የምንውጠውን ጋዝ(አየር) ሙሉ ለሙሉ ማስቀረት ባንችልም መቀነስ ግን ይቻላል፡፡
📌 በፍጥነት ስንመገብ በዝግታ ስንመገብ ከምናስገባው አየር የበለጠ አየር ወደ ሆዳችን እናስገባለን፡፡ በመሆኑም በዝግታ መመገብዎ ከመጠን ያለፈ ፈስን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
#ጤናማ ሆነው ለመቆየት እነዚህን 10 ወርቃማ ምክሮች
ይከተሉ!!

1. ጤናማ አመጋገብ ይመገቡ👇
የሚመገቡት ምግብ ለሰውነታችን እንደ ነዳጅ በመሆን ያገለግላሉ። የተመገቡት የምግብ ዓይነት እና መጠን በቀጥታ የጤናዎን ሁኔታ ያስተጓጉላል። ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች
በሚመገቡበት ወቅት ሰውነትዎ ለበሽታ በጣም የተጋለጠ ይሆናል።

2. ፈሳሽ በብዛት ይውሰድ👇
ስለ አጠቃላይ የጤናችን ሁኔታ ስንመለከት ሰውነታችን የተትረፈረፈ ፈሳሽ ሊኖረው ግድ መሆኑን እናወራለን። በቂ የሆነ ፈሳሽ ሰውነታችን እንዲኖረው ቀኑን ሙሉ በቂ የሆነ ውሃ መጠጣት አለብን።

3. ስፖርታዊ እንቅስቃሴን የህይወትዎ አካል ያድርጉ👇
ጤናማና ከበሽታ ነፃ የሆነ ህይወት ለመምራት መደበኛ የሆነ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ብቸኛው የተሻለ አማራጭ ነው። እንደ ዕድሜዎ ወይም እንደ ብቃትዎ ሁኔታ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጊዜ መስጠት አስፈላጊ ነው።

4. በተመስጦ ወደ ውስጥ መተንፈስን ይለማመድ👇
ጥልቅ ትንፈሳ ወይም በሌላ አገላለጽ የሚቆጣጠሩት አተነፋፈስ ጤናማ እንዲሆኑ በጣም ጠቃሚ የሆነ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
በተጨማሪም ጠንካራ የሆነ የሰውነት እና የአእምሮ ግንኙነት እንዲፈጠር ይረዳናል።

5. የሰውነት ክብደትዎን በንቃት ይከታተሉ👇
ወደ ሚዛን ላይ መውጣት ልምድዎ በማድረግ የሰውነት ክብደትዎን ቼክ ያድርጉ ወይም ይቆጣጠሩ። የተመጣጠነ የሰውነት ክብደት እንዲኖርዎ በማድረግ ውፍረትን ተከትለው
የሚመጡ በሽታዎች እንደ አርትራይተስ፣ የደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመምን በቀላሉ መከላከል ይችላሉ።

6. ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ👇
ሲጋራ በጤናዎ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው። ሲዲሲ (CDC) ገለፃ ከሆነ በሲጋራ ውስጥ ከ 5,000 በላይ ኬሚካሎች ይገኛሉ እነዚህ ኬሚካሎች ለሰው ጤንነት በጣም ጎጂ ናቸው።

7. በዘመናዊነት/በሃላፊነት ይዝናኑ👇
የአልኮል መጠጥ ስንወስድ እንደ ቶኒክ ወይም እንደ መርዝ ይሰራሉ ነገር ግን ይህ የሚወሰነው በቀን ውስጥ የጠጡት መጠን ላይ ነው። መጠነኛ አልኮል መጠጣት ለልብና ለዝውውር ስርዓታችን በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ይወሰዳል። በተጨማሪም በዓይነት ሁለት የስኳር በሽታ እና የሀሞት ጠጠር የመያዝ ዕድላችንን ይቀንሳል።

8. መልካም አመለካከት ይኑርዎት👇
ለህይወት ጤናማና በጎ አመለካከት መኖር ሌላኛው ጤናማ ህይወት እንድንመራ የሚረዳ ሚስጥር ነው። አነጋገርዎና ለህይወት ያለዎት አመለካከት አጠቃላይ ጤንነትዎ ላይ ቀጥተኛ
የሆነ ሚና አለው።

9. በበዓላትና የዕረፍት ቀኖች ራስዎን ዘና ያድርጉ👇
እያንዳንድ ሰው በማንኛውም ዕድሜ፣ ፆታና የሃብት መጠን ላይ ቢገኙም መዝናናት ያስፈልጋቸዋል። ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ
ሲፋቱ እረፍትና መዝናናትን ይዞልዎት ይመጣል።

10. የቤተሰብዎን የጤና ሁኔታ ታሪክ ይወቁ👇
የቤተሰብዎን የጤና ታሪክ ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው። ስለራስዎና የቅርብ ቤተሰብዎ የተመዘገበ የጤና መረጃ መያዝ በየትኛው የበሽታ ዓይነት የመያዝ ዕድልዎ ከፍተኛ እንደሆነ ፍንጭ ይሰጥዎታል።

9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
ጡት የሚያጠቡ እናቶች በተደጋጋሚ የሚጠይቋቸው 12 መሰረታዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው ‼️

ስለ እናት ጡት ወተት ጥቅሞች በደንብ የተረዳች እናት የሚከተሉትን 11 መሰረታዊ ጥያቄዎችን ትጠይቃለች እኔም ለዚች ንቁ እና ጠንቃቃ እናት መልሶችን አቅርብያለው::

#ጥያቄ 1: ልጄን በቀን ዉስጥ ስንት ጊዜ ነው ማጥባት ያለብኝ❓️

✔️ ህፃናት ገና በተወለዱ በ 1 ሰአት ዉስጥ ጡት መጥባት መጀመር አለባቸው ከዛ ጀምሮ በ24 ሰአት ዉስጥ ቢያንስ ቢያንስ 8-12 ጊዜ ጡት መጥባት አለባቸው❗️
✔️ ሆኖም በተጨማሪም ሕፃኑ ለመጥባት በሚፈልግበት ጊዜ ሰአት ሁሉ ማጥባት ተገቢ ነው::

#ጥያቄ 2: ህፃናት ጡት ለመጥባት ሲፈልጉ ምን አይነት ምልክቶችን ያሳያሉ❓️
📌 እጃቸው መጥባት
📌 በደንብ ነቅተው አፋቸውን ማንቀሳቀስ
📌 ምላሳቸውን ወጣ ወጣ ማድረግ
(ይሄ የእንጥል መውረድ ምልክት አይደለም‼️)
📌 መነጫነጭ
📌 ማልቀስ : ሆኖም ልጅሽ እስከሚያለቅስ መጠበቅ የለብሽም ምክንያት አንዴ በኃይል ካለቀስ ጡትሽ ለማስያዝ ትንሽ ልትቸገሪ ትቺያለሽ::

#ጥያቄ 3: ልጄ ከተኛ ቀስቃሼ ማጥባት አለብኝ❓️
🔹 አዎ በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሶስት ሳምንት ዉስጥ በራሳቸው ከእንቅልፋቸው ካልነቁ ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ መቀስቀስ እና ማጥባት አለብሽ ::

#ጥያቄ 4: መነሳት ካለበት ሰአት በፊት ቢነሳስ ❓️
🛑 ልጅሽን ለማጥባት "ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ" ተባለ እንጂ የተለየ የሰዓት ቀመር የለውም❗️ ልጅሽ ጡት በፍለገ ጊዜ ሁሉ ማግኘት አለበት::

#ጥያቄ 5: ልጄ አንዴ ሲጠባ ለምን ያህል ደቂቃ መጥባት አለበት❓️
🤱 ሁሉም ህፃናት የሚጠቡበት ፍጥነት እና ብቃት ይለያያል ይሄ ማለት አንዳንዱ ህፃን በ 10 ደቂቃ ዉስጥ ጠብቶ እና ረክቶ ስተኛ አንዳንዱ ደሞ 30 ደቂቃ ሊፈጅበት ይቺላል::

#ጥያቄ 6 : የጡቴ ወተት እንደሚያጠግበው እና እንደማያጠግበው በምን አውቃለሁ❓️

👶 ጨቅላ ህፃን ልጅሽ በጡትሽ ወተት ከጠገበ የሚከተሉትን ነገሮች ያሳያል::(ከ 1 ሳምንት - 4 ሳምንት)

✔️ ጠብቶ እና ሆዱ ሙሉ ሆኖ ቢያንስ ለ 2 ሰአት ይተኛል
✔️ ሰውነቱ ላይ ከባድ ቢጫነት አይታይም
✔️ ኪሎ በየቀኑ እየጨመረ ይሄዳል
✔️ በቀን ቢያንስ 5-6 ሽንት ይሸናል
✔️ በቀን ቢያንስ 3-4 ካካ ይኖረዋል
(የመጨረሻው ለሁሉም ህፃናት ላይሰራ ይቺላል)

#ጥያቄ 7: ልጄ ሳጠባ ጡቴ ማቀየር ያለብኝ መቼ ነው❓️
🔹 ልጅሽ አንደኛውን ጡትሽን እየጠባ ሳይጨርስ ቶሎ ወደ ሁለተኛው ጡት መቀየር የለብሽም❗️
🔹 ምክንያቱም መጀመርያ የሚያገኘው ወተት(foremilk) አብዛኛው ዉሃማ ሲሆን ለ ሰውነቱ እድገት ዋና የሆነውን ምግብ (ቅባት እና ፕሮቲን) የሚያገኘው እስከ መጨረሻው ሲጠባ እና መጨረሻ ያለውን ወተት(hindmilk) ሲያገኝ ነው::

#ጥያቄ 8: ልጄ ለምንድነው ሌሊት ቶሎ ቶሎ እየነቃ የምያለቅሰዉ❓️

✔️ አንዳንድ ህፃናት በጣም በተደጋጋሚ እና ለ ረጅም ሰአት ጡት የሚፈልጉበት ሰአት አላቸው ይህ ባህሪ "cluster feeding " ይባላል::
✔️ በነዚህ ሰዓት ላይ ልጅሽ ነጭናጫ እና ወተቱ ያለበቃው ይመስላል ግን አይደለም‼️ ዝም ብለሽ በትዕግስት አጥቢው
✔️ ሌላው ጨቅላ ጨጓራ እና አንጀታቸው ትንሽ ስለሆነች ትንሽ ትንሽ ነው መጥባት የሚችሉት ስለዚህ ያቺ ትንሽ ወተት ወደ ታችኛው የአንጀት ክፍል ስታልፍ ይርባቸዋል ስለዚህ ቶሎ ቶሎ ይነቃሉ ያለቅሳሉም ::

#ጥያቄ 9: የጡት ወተቴን አልቤ ማስቀመጥ እና ከተወሰነ ሰአት በዋላ ማጥባት እችላለሁ ❓️

🔹 አዎ ትቺያለሽ❗️ በተለይ ወደ ስራ ቶሎ የምትገቢ ከሆነ ቀድመሽ ጡትሽን እያለብሽ ማስቀመጥ ልምድ ይኑርሽ::
🔹 የጡትሽን ወተት የምታልቢበት እና የሚታስቀምጭበት ዕቃ ንፁህናው በደንብ የተጠበቀ መሆን ይኖርበታል‼️

#ጥያቄ 10 አንዴ የታለበ ወተት ለምን ያህል ጊዜ መጠቀም ይቻላል❓️

💎 ከ ፍሪጅ ዉጭ 4-6 ሰአት መቆየት ይቺላል
💎 አንዴ ጠብቶ የተረፈውን በ 2 ሰአት ዉስጥ መጠቀም
💎 በ ፍሪጅ ዉስጥ (በኔጌትቭ 4 c)ከተቀመጠ እስከ 4 ቀን
💎 በበረዶ ቤት (በኔጌትቭ 18 c) ከተቀመጠ 6 ወር

#አጠቃቀሙም: ⚠️⚠️
🥛🥛ወተቱን ከፍርጅ ከወጣነው በዋላ ወተቱ ያለበትን ጡጦ/ኩባያ ሞቅ ያለ ዉሃ ዉስጥ በማስቀመጥ ሙቀቱን ለመለካት በክንድ ላይ ጠብ አርጎ የማያቃጥል መሆኑን ካየን በዋላ መስጠት ይቻላል::

#ጥያቄ 11: #ጡቴ ጫፍ የለውም ለልጄም ሊያዝለት አልቻለም መፍትሄው ምንድነው❓️

✔️ እናቶች ጡታቸውን ማየት እና ማስተካከል ያለባቸው ከወለዱ በዋላ ሳይሆን ቀድመው በእርግዝና ወቅት ነው
✔️ እርግዝና ወቅት የሚከታተልሽን ሀኪምሽ አማክረሽ በተለያዩ ዘዴዎች ጫፉ እንዲወጣ እና እንዲስተካከል ማድረግ አለብሽ
✔️ ከወለድሽ በዋላ ደሞ ጫፉ እስኪወጣ ድረስ ጡትሽን በማለቢያ እያለብሽ ወተቱን ለልጅሽ በጡጦ/ኩባያ መስጠት ይኖርብሻል ::
✔️ የጤና ባለሙያዎችን አማክሮ በተለያዩ ዘዴዎች ጫፉ እንዲወጣ መሳብ ለምሳሌ በ ተገለበጠ ሲሪንጅ

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም

9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።

👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን:-

👉የዶክተር አለ የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/Doctoralle8809

👉 የዶክተር አለ የዩቱብ ቻነል Subscribe ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

👉 የዶክተር አለ የዶክተር አለ 8809 የቲክቶክ ገፅ Follow ያድርጉ
tiktok.com/@doctoralle8809

👉 የዶክተር አለ የአጭር መልእክት:-
👉👉👉 9102 OK
✍️ #የኩላሊት #ህመም #ግንዛቤ


#መንስኤዎች

🔹 የስኳር ህመም
🔹ከፍተኛ የደም ግፊት –
🔹ሽንት መቋጠር
🔹 ሌላ የኩላሊት በሽታ
🔹 በእርግዝና ወቅት የሚፈጠር የኩላሊት እድገት ችግር
🔹አንዳንድ መድሃኒቶች – እንደ አስፕሪን እና አይቡ ፕሮፊን የመሳሰሉ መድሃኒቶች
🔹 ኩላሊት ላይ የሚደርስ ጉዳት

#ምልክቶች

🔹ብዙ ጊዜ ህመሙ አሳሳቢ ደረጃ እስኪደርስ እንደታመምን ላናውቅ እንችላለን።
🔹የደም ማነስ
🔹ደም የተቀላቀለበት ሽንት
🔹 የጠቆረ ሽንት
🔹 ንቁ አለመሆን
🔹 የሽንት መጠን መቀነስ
🔹 የእግር፣ የእጅ እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ
🔹 የድካም ስሜት
🔹 የደም ግፊት
🔹 እንቅልፍ እጦት
🔹የቆዳ ማከክ
🔹 የምግብ ፍላጎት መጥፋት
🔹ወንዶች ላይ የብልት መነሳት ችግር
🔹 በሌሊት ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ
🔹 የትንፋሽ እጥረት
🔹ሽንት ላይ ፕሮቲን መገኘት
🔹 በፍጥነት የሚቀያየር የሰውነት ክብደት
🔹ራስ ምታት

#የኩላሊት #በሽታ #ደረጃዎች

🔹 🔹 ጂኤፍአር ሬት(GFR rate) የኩላሊት ጤንነት የሚታወቅበት መለኪያ ነው። የጂኤፍአር መጠን የኩላሊታችንን ጤነንት ይናገራል።

🔹 #ደረጃ 1 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ጤነኛ ነው። ቢሆንም ግን የኩላሊት በሽታ እንዳለ ታውቋል።
🔹 #ደረጃ 2 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ከ90 ሚሊ ሊትር በታች ሲሆን ኩላሊታችን ውስጥ በሽታ እንዳለ ያሳውቃል፡፡
🔹 #ደረጃ3 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ከ60 ሚሊ ሊትር በታች ነው።
🔹 #ደረጃ 4 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ከ30 ሚሊ ሊትር በታች ነው።
🔹 #ደረጃ 5 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ከ15 ሚሊ ሊትር በታች ነው። የኩላሊት ማቆም ያጋጥማል፡፡

#አብዛኛው የኩላሊት በሽታ ታካሚ በሽታው ከስቴጅ 2 አያልፍበትም። ነገር ግን ህመሙ እንዳይባባስ ህክምና በማድረግ የኩላሊትን ጉዳት መከላከል ተገቢ ነው።

#ስኳር በሽታ ያላቸው ሰዎች ዓመታዊ ህክምና ማድረግ አለባቸው። ሽንታቸው ውስጥ ያለውን የፕሮቲን መጠን በመለካት ኩላሊታቸው አለመታመሙን ማረጋገጥ አለባቸው።

#ህክምና

🔹 🔹 የተለያዩ ህክምናዎች በሽታውን ለመቆጣጠር አገልግሎት ላይ ይውላሉ። ከባድ ኩላሊት በሽታ ያላቸው ሰዎች ብዙ መድሃኒቶችን መውሰድ ይገባቸዋል።
🔹 የደም ማነስ ህክምና
🔹 የደም ግፊትን ማከም
🔹 ዳያሊሲስ
🔹 ኩላሊት ንቅለ-ተከላ
🔹 የአመጋገብ ለውጥ

9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።

👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን:-

👉የዶክተር አለ የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/Doctoralle8809

👉 የዶክተር አለ የዩቱብ ቻነል Subscribe ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

👉 የዶክተር አለ የዶክተር አለ 8809 የቲክቶክ ገፅ Follow ያድርጉ
tiktok.com/@doctoralle8809

👉 የዶክተር አለ የአጭር መልእክት:-
👉👉👉 9102
"ሴት ልጅህ/ሽ በኢኮኖሚ እራሷን እንድትችል አስተምሯት፤ አግዟት። ስለዚህ ወደፊት የትዳር አጋር እንጂ የሚያስተዳድራትና የሚቆጣጠራት ሰው እንዳታገባ ይረዳታል።

ወንድ ልጅክ/ሽ የቤት ውስጥ ስራዎችን እንዲሰራ አስተምሩት፤ አግዙት። ምክንያቱም ወደፊት ሚስቱ የትዳር አጋሩ እንጂ የቤት ሰራተኛው እንዳልሆነች እንዲረዳ ያግዘዋል።"
✍️ ስትወያይ----ሁን አስተዋይ፤

✍️ ስትናደድ----ቶሎ ብረድ፤

✍️ ስትናገር-----በቁም ነገር፤

✍️ ስትቸገር-----መላ ፍጠር፤

✍️ ሳትመቀኝ-----ሰርተክ አግኝ፤

✍️ ከምታወራ-----ተግተህ ስራ።
✍️#የብርቱካን#ልጣጭ#
1.ሰውነት ውስጥ ያለን የማይፈለግ ኮልስትሮል ያስወግዳል በልጣጩ ላይ ያሉ ንጥረነገሮች የካንሰር ህዋስ እድገትንም ለመግታት ያግዛሉ
2. የሰውነት ክብድትን ለመቀነስ እዲሁም የልብ ህመም ስጋትን ለመቀነስም የሚጫወተው ሚና የላቀ ነው
3. ለመተንፈሻ አካላት ጤንነት በተለይም ሳምባን ንፁህ ለማድረግ እና አስምን ለማከም አጋዠ ነው
4. የምግብ መፈጨትን ስርአትን ለማስተካከል ፤ ቃርን ማስመለስን ለማስታገስም ይጠቅማል
5. ማስቲካን ከማኘክ በበለጠ የብርቱካንን ልጣጭን ማኘክ መጥፎ የአፍ ጠረንን ያስወግዳል
6. በቤት ውስጥ መልካም ጠረን እንዲኖር ለማድረግ የደረቀ የብርቱካን ልጣጭን ከቅርንፉድ ጋር አድርገን ብናፍላ እንፋሎቱ ግሩም መአዛ ይሰጠናል
7. የተፈጨ የብርቱካን ልጣጭን ከጥቂት ውሀ ጋር ደባልቆ የራስ ቅልን መቀባት ፎረፎርንም ያስወግዳል
8. ለ20 ደቂቃ ያህል በፈላ ውሃ ውስጥ የብርቱካን ልጣጭንና ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨውን ጨምሮ ማፍላት ማዋሀድና መጠጣት የመጠጥ ያደረ ስሜትን (hangover)ለማሻልም ያግዛል::
✍️ 9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን:-
👉 የዶክተር አለ የዩቱብ ቻነል Subscribe ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
👉 የዶክተር አለ የዶክተር አለ 8809 የቲክቶክ ገፅ Follow ያድርጉ
tiktok.com/@doctoralle8809
👉 የዶክተር አለ የአጭር መልእክት:-
👉👉👉 9102 OK
#ስኪለስ #አዲስ #ለልጅዎ #ጥያቄ #ዘመናዊ #መልስ !

* ከራስዎ አስበልጠው #ለሚወዷቸው ልጆችዎም ሆነ ለራስዎ ፤ከዘመኑ ጋር አብሮ የዘመነ የጆሮ መብሻና የጆሮ ጉትቻዎችን እነሆ በረከት የሚልዎት ስኪለስ አዲስ ነው!

*ስኪለስ አዲስ ግዙፉ #የስቴዴክስ ካምፓኒ የንግድ አጋር በመሆኑ በሀያ አራት ካራት ወርቅ የተለበጡ የጆሮ መብሻን ከጆሮ ጌጦቻቸው ጋር በልዩነት #ድንቅ በሆነ ሁኔታ በሀገራችን #ብቸኛ #ወኪል በመሆን እያስመጣ ከበቂ ልምድ ጋር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

*በመሆኑም #የልጆችዎን #ጆሮ ለማስበሳትም ሆነ ጉትቻዎችን ለመግዛት ወደ ስኪለስ አዲስ መጡ ማለት ሙሉ በሙሉ #ከአለርጂና በጆሮ ላይ ከሚደርሱ ማንኛውም ህመሞች ነጻ እንደሚሆኑ ዋስትና ገቡላቸው ማለት ነው፡፡

*ምን ይሄ ብቻ #ሲጫወቱም ሆነ #ሲተኙ አልያም ሲታጠቡ ወድቆ ቢጠፋባቸውስ ከሚል ስጋትም በስኪለስ አዲስ ግሩም አቅርቦትና አገልግሎት ተገለገሉም እንጂ!

*ሌላስ ካሉ ፤ ለልጅዎ የተበሳ ጆሮ በአፋጣኝ አድርቆ #ማሳከክ#መቆርቆርና #ማበጥ የሚባል ነገር የለም። #ማድረቂያ ጄል አብሮ ተዘጋጅቶልዎታል፡፡

በተጨማሪም በብዙ #ወላጆች #ጥያቄ መሠረት ከአራት ወር በታች ላሉ ልጆቾ በአይነቱ ለየት ያለ #ድምፅ አልባ የጆሮ መብሻ ለአንድ ልጅ ብቻ ተጠቅመዉ የሚጥሉት መብሻ መሳሪያ አስመጥተን አገልግሎት መስጠት ጀምረናል።

*ታዲያ ይሄን የመሰለ #መልካም #ዜና ስንነግርዎት ምን አሉ? ጉዞ ወደ ስኪለስ አዲስ አላሉም?

ለልጆቾ በማሰብ እንዲሁም ካለዉ የስራ መደራረብ #ጨቅላ ልጆቾን ይዘዉ ወረፋ በመጠበቅ እንዳይጉላሉ እንዲሁም ከኮሮና ቫይረስ እራስዎትንም ሆነ ጨቅላ ልጆቾን ለመጠበቅ በቀጠሮ ይስተናገዱ።

*ካሉበት ወደእኛ ለመምጣት ሲወስኑ ቀጠሮ እንዲያዝልዎት 0911233656 ወይንም 0911799754 እነዚህን ቁጥሮች ይጠቀሙ።

አድራሻችን ኤድና ሞል ፊት ለፊት የሚገኘዉ ቦሌ መድሀኒያለም ሞል አንደኛ ፎቅ ቁጥር 107 እንዲሁም እዛዉ ሞል ላይ ሶስተኛ ፎቅ 322A ያገኙናል ።

#ስኪለስ #አዲስ #የብልህ #ወላጆች #ምርጫ

***በተጨማሪም አዳዲስ ጌጣጌጦችን በየጊዜው ስናስገባ ለምርጫ እንዲረዳዎት

👉👉 የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/skillusjewelery
2025/07/08 20:27:12
Back to Top
HTML Embed Code: