Telegram Web Link
#በፋይበር #የበለፀጉ #ምግቦች

👉 👉 በብዙ ጤና ነክ ምክሮች ላይ ፋይበር የመመገብን ጠቀሜታ በተደጋጋሚ ሲነሳ ይታያል፡፡ በዛሬው ጥንክራችን ይህንን ብዥታ ለመግለጥ እንሞክራለን፡፡

👉 👉 #ፋይበር #ምንድነው?

📌የምግብ ፋይበር የሚባለው ከምንመገበው እፅዋት ውስጥ ሰውነት ሊፈጨው ሊዋሃደን የማይችለው ክፍል ነው፡፡ ፋይበር ስለማይፈጭ እንዳለ ሆኖ የስነ-ልመት አካላቶችን እንደ ጨጓራ፣ ትልቁ እና ትንሹ አንጀትን በማለፍ ከሰገራ ጋር ይወጣል፡፡፡፡ሌሎች የምግብ አይነቶች እንደ ካርቦሃይድሬት፣ ስብ፣ ፕሮቲን ሰውነታችን ፈጭቶ ይዋሃደናል፡፡

👉 👉 #ፋይበርን #በሁለት #ከፍለን #ማየት #እንችላለን

👉 #የሚሟሟ #የፋይበር #አይነት

📌ይሄኛው የፋይበር አይነት ውሃ ውስጥ ሲሟሟ የሚዝለገለግ ይሆናል፡፡ የደም ውስጥ ኮሌስትሮል እና ስኳር መጠንን በመቀነስ ይታወቃል፡፡ የሚሟሟው ፋይበር በኦትስ፣ ባቄላ፣ ፖም፣ ገብስ እና ካሮት ውስጥ ይገኛል፡፡

#የማይሟሟ #የፋይበር #አይነት

📌ሌላው የፋበር አይነት የማይሟሟው ነው፤ ይህ አይነት ለምግብ መፍጨት ስርዓት ተቃሚው ነው፡፡ በውሃ ስለማይሟሟ የስነ-ልመት አካላትን ማለፍ ስለሚችል የሰገራን መጠን ይጨምራል፡፡ ስለዚህ በድርቀት ለሚሰቃዩ ሰዎች መፍትሔ ነው፡፡ ያልተፈተገ እህል፣ ኦቾሎኒ፣ ጥራጥሬዎች፣ አትክልት እንደ ጥቅል ጎመን፣ ድንች፣ አረንጓዴ እሸት በማሟሟ የፋይበር አይነት በለፀጉ ናቸው፡፡
📌ሁለቱ የፋበር አይነቶች በምግቦች ውስጥ በተለያየ መጠን ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም የተለያዩ በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው፡፡

👉 👉 #በፋበር #የበለፀገ #ምግብ #ለምን #ይጠቅማል?

📌የአንጀትን እንቅስቃሴ ያስተካክላል
📌የአንጀትን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል
📌የደም ውስጥ ኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል
📌የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ያስተካክላል
📌ጤናማ ክብደት እንዲኖር ይረዳል
📌ረጅም እድሜ ለመኖር ይጠቅማል

👉 👉 #ፋይበር #ከየት #ይገኛል?

👉 በቀላሉ የሚገኙ ነገር ግን የፋይበር ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ የምግብ አይነቶች፤
📌ያልተፈተገ እህል
📌ፍራፍሬ
📌አትክልት
📌ባቄላ፣ አተር እና ሌሎች ጥራጥሬዎች
📌ኦቾሎኒ እና ሌሎች ፍሬዎች

👉 👉 #ፋይበር እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም ከመጠን በላይ ከተወሰደ የሆድ መነፋት፣ ቁርጠት እና አየር (ፈስ) ሊያመጣ ይችላል፡፡ የሚወስዱትን የፋይበር መጠንን ቀስ በቀስ በሳምንታት ውስጥ መጨመር ይመከራል፡፡ እንዲህ ማድረግ የስነ-ልመት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተፈጥሮአዊ ጠቃሚ ባክቴሪያዎች እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡

👉 👉 #በተጨማሪም ውሃ በደንብ መጠጣት እጅግ ይጠቅማል፡፡ ፋይበር ውሃ ሲያገኝ የተሻለ ይጠቅማል፤ ከዚህ ጋርም ተያይዞ ሰገራን ለማለስለስ እና ለመጨመር ይረዳል፡፡
#የመገጣጠሚያ #ፈሳሽ #ማነስ #ችግር #ምንድን #ነዉ?
#የመገጣጠሚያ ፈሳሽ (synovial fluid) ማለት በሁለት አጥንቶች መገጣጠሚያ መካከል የሚገኝ ነጭ ፈሳሽ ሲሆን አጥንቶች እንዳይጋጩ/መፋፋቅ እንዳይኖር እና መገጣጠሚያ መንቀሳቀስ እንዲችል ያደርጋል፡፡
👉 #የመገጣጠሚያ #ፈሳሽ #ማነስ #ሊያስከትሉ #የሚችሉ #መንስኤዎች
የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን
መገጣጠሚያ አካባቢ የደረሰ አደጋ ካለ
የአጥንት ስብራት/ውልቃት
በእድሜ መግፋት
የቫይታሚን ማነስ
ሪህ (የዩሪክ አሲድ መጠን መጨመር)
በቂ ፈሳሽ ነገር አለመውሰድ
የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ
ያልተስተካከለ የሰውነት ክብደት
👉 #የመገጣጠሚያ #ፈሳሽ #ማነስ #ሲኖር #የሚታዩ #ምልክቶች
የመገጣጠሚያ ህመም
በእንቅስቃሴ ወቅት የመንቋቋት ድምጽ
ለመንቀሳቀስ/እግርን አጥፎ ለመቀመጥ መቸገር
የመገጣጠሚያ አካባቢ መቅላት እና እብጠት
👉 #የመገጣጠሚያ #ፈሳሽ #ማነስ #ሲከሰት #የሚደረጉ #ነገሮች
በጤና ባለሙያ የሚታዘዙ የመገጣጠሚያ ፈሳሽ የሚጨምሩ መድሐኒቶች እና ቫይታሚኖች መጠቀም
ለችግሩ መንስኤ የሆኑ ችግሮችን በአግባቡ ማከም
ውሃ እና ፈሳሽ በደንብ መጠጣት
አሳ፣ ለውዝ፣ የወይራ ዘይት፣ አትክልት እና ፍራፍሬ አዘዉትሮ መመገብ
ስኳር እና ጨው አብዝቶ አለመጠቀም
የተጠበሱ እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አለማዘውተር
የተመጠነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
✍️#ከወሊድ #በኋላ #ለሚከሰት #ኢንፌንክሽን #አጋላጭ #ነገሮች
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥️♥️#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥️♥️
#የተለመዱ #ከወሊድ #በኋላ #የሚከሰቱ #ኢንፌክሽኖች
👉👉 #1# ኢንዶሜትራተስ# (endometritis)
👉👉 ይህ ማለት የላይኛው የማህፀን ክፍል በኢንፌክሽን ሲጠቃ ማለት ነው፡፡ በምጥ ከወለዱ 1-3% እና በቀዶ ጥገና ከወለዱ ደግሞ 5-10 እጥፍ በኢንፌክሽን መጠቃትን ይጨምራል
👉👉 1 #ለኢንዶሜትራተስ #አጋላጭ #ነገሮች
🔵 በወሊድ ወቅት የእንሽርት ውሃ ከፈሰሰ በኋላ ምጥ ቶሎ አለመጀመር
🔵 በጣም የረዘመ ቀዶ ህክምና በወሊድ ጊዜ
🔵 ማህጸን በባክቴርያ መጠቃት
🔵 የተደጋገመ የብልት ምርመራ
👉👉 #2# #የጡት #ኢንፌክሽን
👉 #የጡት ኢንፌክሽን የሚከሰተው ልጅ ጡት በሚጠባበት ጊዜ በልጅ አፍ እና ቆዳ ላይ የሚገኙ ጎጂ ያልሆኑ ባክቴርያዎች ወደ እናትየው ጡት በሚገባበት ሰአት ነው ፡፡ በዚህም ጊዜ ጡት ላይ እብጠት ሊኖር ይችላል ነገር ግን እናት ጡት ማጥባት ማቆም የለባትም
👉👉 #3 #የሽንት #ቱቦ #ኢንፌክሽን
🔵 በምጥም በቀዶ ህክምናም ቢወልዱ ኢንፌክሽን የማጋጠም እድሉ እኩል ነው
👉👉 #4 #የቁስል #ኢንፌክሽን
🔵 ይህ የሚፈጠረው በቀዶ ጥገና የሚወለዱ እናቶች ላይ ነው፡፡
👉👉 #ምልክቶቹም
🔵 ቀዶ ጥገና የተሰራበት አካባቢ መቅላት
🔵 ትኩሳት
🔵 የታችኛው የሆድ ክፍል አካባቢ ህመም መሰማት
👉👉 መንስኤዎች
🔵 በተለያዩ የባክቴርያ አይነቶች
🔵 ከወሊድ በኋላ ኢንፌክሽን እንዳለ የሚያመላክቱ ነገሮች
🔵 ከማህፀን ሽታ ያለው የበዛ ፈሳሽ
🔵 የማህፀን እብጠት
🔵 አንድ ወይም ሁለቱም ጡት እብጠት
🔵 በተደጋጋሚ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
🔵 ለመተንፈስ መቸገር
🔵 ሽንት ሲሸኑ ህመም እና የጠቆረ ሽንት
🔵 ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት እና ትኩሳት
👉👉#ህክምና
🔵 ህክምናው መንስኤዎችን መሰረት ያደረገ ነው ፡፡
✍️#በብብት #አከባቢ #የሚፈጠር #እብጠት

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

#በብብትዎ ላይ እብጠት እንዲኖር የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ።

#በጣም ከተለመዱት ምክንያቶች አንዱ የንፍፊት እብጠት ነው።

#ንፍፊት የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት አካል ናቸው

#እነሱ እንደ ማጣሪያ ሆነው ፣ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት ያስወግዳሉ

#በብብት ላይ ያለው የንፍፊት እብጠት የኢንፌክሽን ወይም የአካል ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል

#መንስኤዎቹ

🔹 በሁለቱም ብብት አከባቢ ይህ ንፍፊት እብጠት ሲኖር የተላላፊ በሽታ ወይም ኢንፌክሽን እንዳለ ያሳያል
🔹 እብጠቱ በአንድ በኩል ብቻ ሲሆን የጡት ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል
🔹 ከእጅ በታች ያሉ ንፍፊቶች የጡት ካንሰር ከሚሰራጩባቸዉ የተለመዱ ቦታዎች አንዱ ነው

#ሆኖም ግን ፣ በአንድ በኩል ብቻ የንፍፊት እብጠት ከሚያስከትሉ ምክንያቶች መሀል፡-

🔺 የጡት ኢንፌክሽኖች ፣ ለምሳሌ ማስታይተስ ወይም መግል የያዘ እብጠት
🔺 የክትባት ምላሾች …………………….

#ምልክቶቹ

#አንዳንድ የብብት እብጠቶች ምንም ምልክቶች የላቸውም ፣ ህመም የሌላቸው እና ምንም ያለመመቸት ስሜት አይፈጥሩም።

#ሆኖም ፣ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከእብጠት ጋር ተጨማሪ ምልክቶችን ያስተውላ

#እነዚህ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ :-

🔺 ትኩሳት
🔺 በብብት አካባቢ ህመም ወይም ምቾት ማጣት
🔺 የተከፈተ ቁስል ወይም መግል መዉጣት
🔺 መቅላት
🔺 በአንገት ፣ በላይኛው ደረት ወይም በሌሎች ቦታዎች ላይ የንፍፊት ማበጥ
🔺 በላይኛው የመተንፈሻ አካላት የኢንፌክሽን ምልክቶች

#ህክምናዉ

#በአብዛኛዉ ጊዜ የብብት እብጠት ምንም ዓይነት ህክምና ባያስፈልጋቸውም አንዳንዶቹ መንስኤዎች ግን ህክምና ይሻሉ

#የንፍፊት ማበጥን በቤት ውስጥ ለማከም :-

🔺 ያበጠዉን አካባቢ ሞቅ ባለ ዉሃ ፎጣ እየነከሩ ቦታዉ ላይ ጫን ጫን ማረግ
🔺 ብዙ ፈሳሽ መጠጣት ፣ እንደ ውሃ እና ትኩስ ጭማቂዎች
🔺 እረፍት ማረግ
🔺 የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ
✍️ #የጀርባ #አጥንትን #የሚጎዱ #መጥፎ #ልማዶች
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

👉 #እግርን #አጣምሮ #መቀመጥ ፡-
🔺 ይህ ብዙዎቻችን እንደ ቀልድ የምናየው ልማድ ነው እንደውም አንዳንዶቻችን ከልምድ የተነሳ እግራችንን ሳናጣምር መቀመጥ አንችልም፡፡ እግራችንን አጣምረን በምንቀመጥበት ጊዜ የአከርካሪ አጥንት ቀጥ ማለት አይችልም/ይጣመማል ይህም በዳሌ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ከመጠን በላይ እንዲለጠጥ ስለሚያደርግ የጀርባ ህመም እንዲያጋጥመን ከማድረጉም ሌላ የደም ዝውውርን በማስተጓጎል ቫሪኮስ ቬን ለተባለ በሽታ እና ለአጥንት መጎዳት ያጋልጣል፡፡

👉 #ለረጅም #ሰአት #አንገትን #አዘንብሎ #ወይም #ደፍቶ #መቆየት ፡-
🔺 በምንቀመጥበት፣ በምንቆምበት እና በምንሄድበት ጊዜ ማጎንበስ አንገት አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እንዲዝሉ በማድረግ የአንገት ህመም እና አንገት አካባቢ ያለው የጀርባ አጥንታችን እና ጅማታችን ከአቅም በላይ ይለጠጥና ዲስካችን እንዲወጠር ያደርጋል፡፡

👉 #በሆድ #መተኛት፡-
🔺 በሆድ ተደፍቶ መተኛት በጀርባ እና በአከርካሪ አጥንት ላይ ተጨማሪ ሸክም እንዲጨምርበት ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ የጀርባ አጥንት እንዲጎዳ ስለሚያደርግ ለጀርባ ህመም እንድንጋለጥ ያደርገናል፡፡

👉 #የምናደርገው #ጫማ ፡-
🔺 የምናደርገው ጫማ ከፍታ ካለው፣ የጠበቡን ከሆኑ የጀርባ አጥንትን አቋም እንዲዛባ እና የጀርባ ህመም እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

👉 #ከመጠን #በላይ #ውፍረት ፡-
🔺 ይህ ከሌሎች በሽታዎች በተጨማሪ ለጀርባ መጣጠሚያ እና ለጡንቻዎች አብዛኛውን ጊዜም ለዳሌ እና ለታችኛው የጀርባ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ይጨምራል፡፡ የአኗኗር ዘይቤያችንን በማስተካከል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ሰውነታችን በጥሩ ሁኔታ እንዲቆይ ማድረግ የጀርባዎን ጤና እና ሰውነታችን ከተለያዩ ህመሞች ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊው መንገድ ነው ፡፡

👉 #የሚተኙበት #ፍራሽ
🔺 ፍራሽዎ ስስ ከሆነ የጀርባ አጥንታችን እንዲጎዳ እና የታችኛው የጀርባ አጥንታችን እንዲሰምጥ ያደርጋል ይህ የጀርባ አጥንት ፣ጡንቻዎች እና መገጣጠሚያዎች ላይ ውጥረት እንዲጨምር እና አቀማመጣቸው እንዲዛባ ያደርጋል። ስለዚህ ጥቅጥቅ ያለ እና ተጓዳኝ ፍራሽዎችን ለጀርባዎ ጤና በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡

👉 #ላፕቶፖች #እና #ስማርት #ስልኮች ፡-
🔺 በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን የጀርባ ህመም መጨመር የመከሰቱ ሁኔታ የዚህ መሳሪያ አጠቃቀምን ይጨምራል ፡፡ በጭንቅላት እና በትከሻዎ መካከል በስልክዎ መነጋገር ለአንገትዎ እና ለጀርባዎ በጣም መጥፎ ነው ፡፡ ስለዚህ ሌሎች ነገሮችን በሚያደርጉበት ጊዜ ገመድ አልባ የጆሮ ማዳመጫዎችን መጠቀሙ የተሻለ ሆኖ እንዲሠራ ያድርጉ ፡፡ ሌላኛው ችግር ላፕቶፕ በሚጠቀሙበት ጊዜ እግሮት ላይ አድርገው ሳይሆን እርሶ ከተቀመጡበት ትይዩ በማድረግ ጠረዼዛ ላይ ማስቀመጥ፡፡

👉 የጀርባ አጥንት መጎዳት ሌሎች ምክንያቶች ወስጥ መውደቅ፣ ዕጢዎች ፣
አደጋዎች… ወዘተ ናቸው ፡፡ ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ-ጥንቃቄዎች መተግበር እና ለከባድ ሁኔታዎች ዶክተርዎን ማየትዎን ማረጋገጥ የጀርባ ጉዳት እንዳያጋጥመን ይጠቅመናል፡፡
ይህን ያውቁ ኖሯል????
============
በHIV የተያዙ ህፃናቶች 50 በመቶ የሚሆኑት የ 2 አመት ልደታቸውን ሳያከብሩ ህይወታቸው ያልፋል፣

🖲30 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት ደሞ እስከ 10 አመት በህይወት የመቆየት እድል አላቸው።

🖲በህፃናቶች ላይ የሚከሰት የHIV ስርጭት 90 በመቶ የሚሆነው፣ መነሻው፣ ከእናት ወደልጅ በሚተላለፍበት ግዜ ነው

🖲በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ግዜና፣ ጡት በማጥባት ፣ HIV ከእናት ወደልጅ የመተላለፍ አቅም አለው

👉የቅድመ ወሊድ ክትትል ከሌለ
👉በምጥ ወይም በቤት ውስጥ መውለድ
👉ከምጥ በፊት
የሚመጣ የሽርት ውሀ ፍሰት መኖር
👉የፀረቫይረስ መዳኒት አለመውሰድ
👉እንዲሁም፣ ጡት ማጥባት ፣ የጡት ወተት እና ሌላ ምግብ እያፈራረቁ መስጠት

የተወለደው ልጅ በHIV የመያዝ እድሉ እንዲጨምር ያደርጋል።

🖲የቅድመ ወሊድ ክትትል በግዜ የጀመረች አንድ በHIV የተጠቃች እናት፣ የፀረቫይረስ መዳኒት በግዜ ስለምትጀምር ፣ የባለሞያ ክትትልና ምክር ስለማይለያት፣ ከ ቫይረሱ ነፃ የሆነ ልጅ የመውለድ እድሏ ከፍተኛ ነው።

በግዜ የሚጀመር የቅድመወሊድ ክትትል፣ ትልቅ ባለውለታ ነው።
✍️ #የግንኙነት #ፍላጎት #መቀነስ #መንስኤዎች
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

👉👉 #ውድ የገጻችን ቤተሰቦች በዛሬው ጽሁፋችን ይዘን የቀረብነው በወንዶች በኩል የጾታዊ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ በምን ምክንያት እንደሚከሰት እንዲሁም ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብን ልንጠቁሞት ወደድን ተከታተሉን፡፡

👉👉 #ምክንያቶች ፡-

📌 የቴስቴስትሮን መጠን መቀነስ
📌 እድሜ ከ 45 በላይ መሆን
📌 በራስ መተማመን መቀነስ
📌 ለሌላ ህመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች (ለምሳሌ ፡- ለድብርት)
📌 የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ ወይም በጣም የበዛ እንቅስቃሴ ማድረግ
📌 ከፍተኛ አልኮል ተጠቃሚ መሆን
📌 አደንዛዥ እጾችን መጠቀም
📌 ድብርት
📌 የስራ ጫና እንዲሁም ጭንቀት
📌 ከግንኙነት አጋር ጋር አለመግባባቶች ካሉ
📌 የኮሌሰትሮን መጠን መብዛት
📌 ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የስኳር ህመም እና የልብ ህመም

👉👉 #እንዴት #መከላከል #እንችላለን?

📌 የአኗኗር ዘይቤን ጤናማ ማድረግ
📌 አመጋገብን ማስተካከል
📌 የአካል እንቅስቃሴን በተገቢው ማከናወን
📌 በቂ እንቅልፍ ማግኘት
📌 መጨናነቅን ማሰውገድ የቴስቴስትሮን መጠንን በመለካት ችግር ካለ ህክምና ማድረግ
የግንኙነት ፍላጎት መቀነስ በጥንዶች መካከል የሚያስጨንቅ እና በመካከላቸው ግጭት እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው ነገር ይህን ችግር በመነጋገር እና የህክምና ድጋፍ በማድረግ ከገጠሞት ችግር መውጣት ይችላሉ ፡
✍️ #ማንኮራፋት
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

#ማንኮራፋት የሚፈጠረው ላይኛው የመተንፈሻ አካሎቻችን ላይ በሚፈጠር መርገብገብ ነው።

#ምክንያቶቹ #ምን #ይሆኑ?

🔹 የአየር ማስተላለፊያ ትቦ መደፈን /አለርጂ፣ ሳይነስ፣ጉንፋን ፣ ቶንሲል በሽታ ፣አፍንጫ ውስጥ የሚበቅል ትርፍ ስጋ../
🔹 የመተንፈሻ ትቦ መጥበብ
🔹 አፍ ከፍቶ መተኛት
🔹 የሰውነት ክብደት ከመጠን በላይ መጨመር
🔹 የእንጥል ማበጥ
🔹ከፍተኛ ድካም
🔹 አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ እና ጫት መቃም
🔹 በጀርባ መተኛት
🔹 በቂ ውሃ አለመጠጣት
🔹 አንዳንድ መድሃኒቶች

#በቤት #ውስጥ #ምን #ማድረግ #አለብኝ?

🔹 በጎን በኩል መተኛት
🔹 ሲጋራ አለማጨስ እና አልኮል አለማዘውተር
🔹 ከፍያለ ትራስ መጠቀም (ትራስ አዘቅዝቀን በምንተኛበት ጊዜ የመተንፈሻ ትቦን ስለሚጫነው ለመተንፈስ እንድነቸገር እና እንድናኮራፋ ያደርገናል)
🔹 ውሃ በቀን ከ2.5 ሊትር በላይ መጠጣት (ጤናማ የሆነ የአተነፋፈስ ስርአት እንዲኖረን ያደርጋል)
🔹 የምንተኛበትን ክፍል ማፅዳት (ብዙውን ጊዜ የሽታ አለርጂ ካለ ማንኮራፋት እንዲመጣ ያደርጋል)
🔹 ውፍረት መቀነስ
🔹 ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች አለማዘውተር
🔹 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
2025/07/07 15:04:12
Back to Top
HTML Embed Code: