Telegram Web Link
#የእግር #ፈንገስ #ምንድን #ነው?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

#የእግር ፈንገስ በእግሮቹ ላይ ቆዳን የሚጎዳ ተላላፊ የፈንገስ በሽታ ነው። እንዲሁም ወደ ጥፍር እና እጆች ሊሰራጭ ይችላል፡፡ የእግር ፈንገስ በቀላሉ ማከም ይቻላል አንዳንድ ጊዜ ከባድ የሚሆንበት ጊዚያት ይኖራል ። የስኳር በሽታ ካለብዎ ወይም
በሽታ የመከላከል አቅሙ ደካማ ከሆነ እና እግር ፈንገስ እንዳለዎት ከተጠራጠሩ ወዲያውኑ ለሐኪምዎ በመሄድ መታከም ይኖርብዎታል ፡፡

👉👉 #እግርን #ፈንገስ #መንስኤ #ምንድ #ነው?

📌 የእግር ፈንገስ ቲኒያ በተባለ ፈንገስ በእግር ላይ ሲያድግ የሚከሰት ሲሆን ፡፡ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በቀጥታ
በመገናኘት ወይም በፈንገስ የተበከሉ ቦታዎችን በመንካት ፈንገሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ ፡፡ ፈንገሱ በሞቃት እና እርጥበት አካባቢዎች ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

👉👉 #እግርን #ፈንገስ #ምልክቶች

📌 የጥፍር መበስበስ
📌በጣቶችዎ መካከል ወይም በእግርዎ ላይ ማሳከክ ፣ ማበጥ እና ማቃጠል
📌 በእግር ጣቶችዎ መካከል እና በእግርዎ መካከል አብዛኛውን ጊዜ በእግርዎ ላይ ቆዳ መሰንጠቅ እና መፋቅ
📌 ደረቅ ቆዳ መኖር
📌 ቀለም መቀየር ፣ ወፍራም ቆዳ መኖር

👉👉# እግር #ፈንገስ #አጋላጭ #ሁኔታዎች

📌 ባዶ እግሮችን መጓዝ
📌 መታጠቢያ ቤቶችን እና የመዋኛ ገንዳዎችን በጋራ የሚጠቀሙ
📌 ካልሲዎችን ፣ ጫማዎችን ወይም ፎጣዎችን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር መጋራት
📌 ጠባብ ፣ ሽፍን ጫማዎችን መልበስ
📌 እግርዎን ለረጅም ጊዜ እርጥብ በማድረግ እና ንፁህና በአግባቡ አለመጠበቅ
📌እግሮች ላብ
📌 በእግርዎ ላይ ትንሽ የቆዳ ወይም የጥፍር ቁስለት መኖር

👉👉 #እግርን #ፈንገስ #ለመከላከል

📌 በየቀኑ እግርዎን በሳሙና እና በውሃ መታጠብ እና ማደራረቅ በተለይ በእግር ጣቶች መካከል
📌 ካልሲዎችን ፣ አንሶላ እና ፎጣዎችን በፍላ ውሃ ማጠብ
📌 ካልሲዎችን ፣ ጫማዎችን ወይም ፎጣዎችን ከሌሎች ጋር አይጋሩ ፡፡
📌 በሕዝብ መታጠቢያዎች ፣ በሕዝብ መዋኛ ገንዳዎች እና በሌሎች ሕዝባዊ ቦታዎች ላይ ጫማዎችን ያድርጉ ፡፡
📌 እንደ ጥጥ ወይም ሱፍ ቃጫዎች የተሠሩ ካልሲዎችን ወይም ከቆዳዎ ርቀትን ከሚወስዱ ሰው ሠራሽ ክሮች የተሠሩ ካልሲዎችን ያድርጉ ፡፡
📌 እግርዎ በሚያልቦ ሰአት ካልሲ መቀየር (ድጋግሞ ካልሲ አለማድረግ )
📌 እግርን አለማፈን (አየር እነዲነካው ማድረግ)
📌 ክፍት ጫማዎችን መዘውተር
#ደም #የቀላቀለ #ሰገራ
********

ውድ የዶክተር አለ ቤተሰቦች እንዴት አደራችሁ በየትኛው የጤና ጉዳዮች መረጃ መስጠት እንዳለብን አስተያየታችሁን ጠቁሙን። እኛ ለናንተ ይጠቅማን ያልናቸውን ወደናንተ ለማድረስ ዝግጁነን !!

ደም የቀላቀለ ሰግራ ማለት በየትኛውም የአንጀት ክፍል መድማት ሲያጋጥም በሰገራ መልኩ ደም ሲታይ ነው። ከተቀመጡ በኋላ ሰገራው ላይ እና የሽንት ቤት ወረቀት ላይ ደም ሲታይ ደም ሰገራ ላይ እንዳለ ይታወቃል ።

#ምክንያቶቹ
· የአንጀት ክፍል ላይ የወጣ ቀዳዳ መሰል ነገር(Diverticular Diseeas )
· የፊንጢጣ ኪንታሮት(Hemorrhoide)
· የፊንጢጣ መሰንጠቅ(Anal fissuer)
· የአንጀት መለብለብ(Colitis)
· የአንጀት አካባቢ ደም ስሮች ላይ ችግር ሲኖር(Angiodysplasia)
· የጨጓራ ቁስለት
· አንጀት ላይ ትርፍ ስጋ መሰል ነገር ሲያድግ(Polyps)
· አንጀት ካንሰር
· የምግብ ትቦ ላይ ችግር ካለ(Esophageal problem)
· የአንጀት ላይ ኢንፌክሽን

#ምልክቶቹ
አብዛኛው ሰው ምልክቶቹን ላያስተውል ይችላል ።በሌላ በኩል ደግሞ ከሚከሰቱ ምልክቶች ውስጥ
* የሆድ ህመም
*ማስመለስ
*ድካም
*ለመተንፈስ መቸገር
*ተቅማጥ
*ራስን መሳት
*የሰውነት ክብደት መቀነስ የማሳሰሉት ናቸው።

#ህክምናው
_ያመጣውን ነገር በምርመራ ከተረጋግጥ ወይም ከታወቀ በኋላ መንሰኤውን ማከም
_በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ መድሀኒቶችን በአግባቡ መውሰድ
_በፋይብር የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፣ ሙቅ ውሀ ላይ መዘፍዘፍ(የፊንጢጣ ኪንታሮት፣የፊንጢጣ መሰንጠቅ ከሆነ ያመጣው)
እንደማጠቃለያ ደም የቀላቀለ ሰገራ በትንሽ (በቀላል) እንዲሆም ከበድ ባሉ ምክንያቶች በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሰት እና ምልክቶቹ ቶሎ የማይስተዋሉ ሰለሆነ እንዳወቁ የጤና ባለሙያ ያማክሩ።

9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
►በሕይወት ውስጥ አንዴ #ከሄዱ የማይመለሱ ሦስት ነገሮች
☞ ጊዜ፣ ቃል እና አጋጣሚ

►በሕይወት ውስጥ #ልታጣቸው የማይገቡ ሦስት ነገሮች
☞ ሰላም፣ ተስፋ እና ታማኝነት

►በሕይወት ውስጥ እጅግ #ዋጋ ያላቸው ሦስት ነገሮች
☞ ፍቅር፣ እምነት እና ባልንጀሮች

►በሕይወት ውስጥ #እርግጥ ያልሆኑ ሦስት ነገሮች
☞ ሕልም፣ ስኬት እና እድል

►አንድን ሰው ሰው የሚያደርጉ ሦስት ነገሮች
☞ጠንክሮ መስራት፣ ቅንነት እና ጽናት

►በሕይወት ውስጥ አንድን ሰው ሊያጠፉ የሚችሉ ሦስት
ነገሮች
☞ ሱስ፣ ትዕቢት እና ጭንቀት
#ለጨጓራ #መቆጣት #መፍትሄዎች

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

👉👉 የጨጓራ ህመም፡- የጨጓራ መቆጣት፣ መብገን ወይም ጨጓራ ላይ ያለው ፈሳሽ ወደ ላይ መመለስን ያጠቃልላል ይህም የሚሆነው የጨጓራ አሲድ በሚበዛበት ወቅተ ነው፡፡

👉👉 #እንዴት በቤት ውሰጥ ማከም ይቻላል

👉#ከልክ በላይ አይመገቡ

📌 የአሲድ ከመጠን በላይ መመረትን ለመቀነስ የሚረዳ አንድ እርምጃ ከመጠን በላይ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ ነው
📌#ክብደት መቀነስ

👉#በሆድ ውስጥ በስብ ምክንያት ከመጠን በላይ ግፊት የአሲድ ከሚፈለገው በላይ መጨመር መንስኤ ከሆኑት ምክንያቶች አንዱ ነው። የሆድ ስብን ወይም ቦርጭን መቀነስ አንዳንድ የሕመም ምልክቶችዎን ያስታግሳል

📌 ዝቅተኛ-ካርቦሃይድሬት አመጋገብን ይከተሉ
📌 የአልኮል መጠጥዎን ይገድቡ
📌 በጣም ብዙ ቡና አይጠጡ
📌 የአልጋዎን ትራስ ከፍ ያድርጉት
📌 ወደ መኝታ ከሄዱ በሶስት ሰዓታት በፊት ቀደም ብለው ይመገቡ

👉👉 #የአሲድ #ወደ #ላይ #መመለስን #ለመከላከል #የሚረዱ #ምግቦች

📌 ከፍተኛ ቃጫማ ይዘት ያላቸው ምግቦች
📌 የቃጫ ምግቦች የመጥገብ ስሜት እንዲሰማዎት ያደርጉዎታል ስለሆነም ከመጠን በላይ የመብላት እድሉ አነስተኛ ነው ፡፡

👉#ቃጫማ ይዘት ካላቸው ምግቦች ውስጥ

📌 እንደ፤ ኦትሜል ፤ኩስኩስ እና ቡኒ ሩዝ ያሉ ሙሉ እህሎች
📌 እንደ ድንች ድንች ፣ ካሮት እና ባቄላ ያሉ ሥር አትክልቶች
📌 እንደ አረንጓዴ ፣ አትክልት ፣ ብሮኮሊ እና አረንጓዴ ባቄላ ያሉ አረንጓዴ አትክልቶች
📌 የአልካላይን ምግቦች

👉#ከፍ ያለ ፒኤች ያላቸው አልካላይን ናቸውና ጠንካራ የሆድ አሲድን ለመቀነስ ይረዳሉ ፡፡የአልካላይን ምግቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ

📌 ሙዝ
📌ሐብሐብ
📌 አበባ ጎመን
📌 ለውዝ
📌 ውሃማ ምግቦች

👉#ብዙ ውሃ የያዙ ምግቦችን መመገብ በሆድ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የአሲድ መመረትን እንዲቀንሱ ይረዳል ፡፡ እንደዚህ ያሉ ምግቦችን ይምረጡ

📌 ሰሊጥ
📌 ኪያር
📌 ሰላጣ
📌 ሐብሐብ
📌 ፓፓያ
📌 ሾርባዎች
📌 ከዕፅዋት የተቀመመ ሻይ

👉👉 #ደረት አካባቢ ማቃጠል ምልክት ላለው የጨጓራ ህመም ለማከም የሚረዱ

📌 ወተት
📌 ዝንጅብል
📌 አፕል ኮምጣጤ
✍️ #ህፃናት #የወይራ #ዘይት #መቼ #መጀመር #አለባቸው?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

🔹 ከ 6 ወር ጀምሮ ምግባቸው ላይ ጠብ እያደረግን መመገብ እንችላለን፡፡

#የትኛውን #መምረጥ #አለብን?

🔹 ተጨማሪ ምግብን በተመለከተ ኤክስትራ ቨርጅን የወይራ ዘይት የተሻለ እና ተስማሚ ነው።

🔹 የወይራ ዘይት ስብጥር ለሚያድግ አካል በጣም አስፈላጊ የሆኑት “ጠቃሚ” ኮሌስትሮል እና ያልተሟሉ የሰባ አሲዶች አሉት(fatty acid) ቅንብሩ በተጨማሪ በጡት ወተት ውስጥ ከሚገኙ ቅባቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን ቅባቶችን ያጠቃልላል ፡፡

🔹 የወይራ ዘይት ከሌሎቹ የአትክልት ዘይቶች ሁሉ በተሻለ የህጻናት ሰውነት ላይ በዳይፐር አማካኝነት የሚፈጠርን ሽፍታ ለማጥፋት፣ እንዲሁም ህፃናት ላይ የሚወጣን ብጉር ለማጥፋት ይጠቅማል፡፡

#ስለልጅዎ እንዲሁም በማንኛውም የጤና ጉዳይ ጋር በተያያዘ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞች ላይ በመደወል ያማክሩ!! ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!
ወድ የዶክተር አለ ቤተሰቦች ዛሬ ይዘንላቹ የቀረብነው በሆዳችን ክፍል ህመማችንን ለመለየት የሚረዳን ፅሁፍ ነው ተከታተኩን።

በሆድ ክፍል ህመምን የመለየት ዘዴ

👉 ዘጠኝ አይነት የሆድ ክፍሎች በእነሱ እንዴት ህመማችንን መለየት እንችላለን?
1. የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል
• የጉበት ህመም
• የሆድ ቁስለት
• የሃሞት ጠጠር
• የቀኝ ኩላሊት ህመም

2. የላይኛው የመሃል የሆድ ክፍል
• የጨጓራ ህመም
• የምግብ አለመፈጨት
• የሆድ ቁስለት
• የጣፊያ ኢንፌክሽን
• የጉበት ህመም

3. የግራ የላይኛው የሆድ ክፍል
• የሆድ ቁስለት
• የአንጀት ቁስለት
• የግራ ኩላሊት ህመም
• የሃሞት በሽታ
• የጣፊያ ህመም

4. የቀኝ የጎን መሁለኛው የሆድ ክፍል
• የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
• የሆድ ድርቀት
• የኩላሊት ጠጠር

5. የእንብርት አካባቢ የሆድ ክፍል(center)
• ትርፍ አንጀት
• የአንጀት መታወክ
• የእንብርት መቁሰል
• የጣፊያ ህመም

6. የግራ ጎን መሃለኛው የሆድ ክፍል
• የኩላሊት ጠጠር
• የአንጀት መታወክ
• የአንጀት ኢንፌክሽን

7. የቀኝ ጎን የታችኛው የሆድ ክፍል
• ትርፍ አንጀት
• የሆድ ድርቀት
• የማህጸን አካባቢ ህመም
• ትንሹን እና ትልቁን አንጀት የሚያገናኘው ህዋስ ህመም

8. የሆድ ታችኛው መሃለኛው ክፍል
• የፊኛ ኢንፌክሽን
• የማህጸን አካባቢ ህመም
• የትልቁ አንጀት ህመም

9. የግራ ጎን የታችኛው የሆድ ክፍል
• የትልቁ አንጀት ህመም
✍️ #ደረቅ #ሳል #አይነተኛ #ምልክታቸው #የሆኑ #ህመሞች

#ደረቅ ሳል በምናስልበት ወቅት ተከትሎ አክታ እማናስወግድ ከሆነ( ከሌለ)ነው፡፡

#ዋና #ዋና #ምክንያቶች

🔵#አስም፡- አስም የምንለው የመተንፈሻ ትቦ ሊያብጥና በማበጡም ሲጠብ የሚፈጠር ነው፡፡ተያይዞም እነዚህ ምልክቶች ሊስተዋሉ ይችላሉ ፡-

🔹 ሲርታ ድምጽ መሰማት
🔹 የትንፋሽ ማጠር
🔹 የደረት ውጋት
🔹 ሳል ከእንቅልፍ የሚረብሽ

🔵#ቃር፡- ይህ ችግር የጨጓራ አሲድ ከመጠን በላይ በመመረቱ ወደላይ (ወደ ምግብ ትቦና ጉሮሮ) ሲመለስ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ይህ አሲድ ሳል እንዲቀሰቀስ ያደርጋል ተያይዞም ፡-

🔹የደረት ማቃጠል
🔹 የምግብ / ፈሳሽ ወደ ላይ መመለስ
🔹 ረጅም ጊዜ የሚስተዋል ደረቅ ሳል
🔹ጉሮሮ አካባቢ ያበጠ ስሜት መሰማት
🔹 የድምጽ መቀየር

🔵#የቫይረስ #ኢንፌክሽን፡- እንደ ጉንፋን ፣ ኮሮና የመሳሰሉት ቫይረሶች ደረቅ ሳልን የማስከተል አቅም አላቸው፡፡

🔵#ለኬሚካሎች #እና #ብናኞች #መጋለጥ፡- ይህ ሁኔታ በስራችን / በአካባቢያችን ተጋላጭነት ካለ አለርጂን በመፍጠር ደረቅ ሳልን ያስከትላሉ ፡፡

🔵#አንዳንድ ለሌላ ህመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች

🔵#ትክትክ በተለይ በህጻናት ላይ

🔵#የሳንባ ካንሰር

🔵#የልብ ድካም

🔵#የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) ተያይዞ ያሉ ምልክቶች

🔹 ለሶስት ወይም ከዚያ በላይ ሳምንታት ማሳል
🔹 የደረት ህመም
🔹 በሚተነፍሱበት ወቅት ወይም በማሳል ወቅት የደረት ህመም
🔹 ክብደት መቀነስ
🔹 ድካም
🔹 ትኩሳት
?? የምሽት ላብ
🔹 ብርድ ብርድ ማለት

#ደረቅ #ሳልን #ለመከላከል

🔹 #በጨው #መጉመጥመጥ፦ በመጠኑ ለብ ባለ ውሃ ውስጥ አንድ ማንኪያ ጨው በመጨመር ቀና ብለን ጉሮሯችንን እንዲያጸዳ በማድረግ መጉመጥመጥ ደረቅ ሳልን ለመከላከል ወይም በቀላሉ ለማስቆም ይችላል።

🔹 #ፍራፍሬዎችን #አዘውትሮ #መመገብ፦ ፍራፍሬዎችን በጭማቂ መልክም ይሁን ጥሬያቸውን አዘውትሮ መጠቀም ፍራፍሬዎቹ በውስጣቸው ባለው ንጥረ ነገር አማካኝነት ለደረቅ ሳል እንዳንጋለጥም ይረዱናል።

🔹 #አረንጓዴ #ሻይ፦ አረንጓዴ ሻዩን በሻይ ቅጠሉ ማሸጊያ ጀርባ ላይ ባለው አጠቃቀም መሰረት ካፈላን በኋላ አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ጨምሮ መጠጣትም ደረቅ ሳልን ለማከም ፍቱን ነው ። የአረንጓዴ ሻይ እና የማር ጥምረት ደረቅ ሳልን ከማከም ባሻገርም በደረቅ ሳል ወቅት የሚከሰቱ የጉሮሮ ህመሞችንም ለማከም ይረዱናል።

🔹 #የዝንጅብል #ሻይ፦ በፈላ ሻይ /ከተገኘ አረንጓዴ ሻይ / ውስጥ አንድ የሻይ ማንኪያ ዝንጅብል በመጨመር መጠቀምም ለደረቅ ሳል መፍትሄ ነው።
✍️#የጡንቻ #ህመም #ምልክቶች
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
#በቅንነት #ሼር #ያድርጉ
#ድንገት ሰውነትን ሽምቅቅ የሚያደርግ ስሜት አጋጥሞት ያውቃል ወይም ከፍሎ የሰውነት ክፈሎትን በተለይም ጡንቻዎች አካባቢ የህመም ስሜት አስተውለው ያውቃሉ እንግዲያውስ ቀጥሎ የቀረበው ጽሁፍ መልስ ይሆኖታል ይከታተሉን፡-
#ምልክቶች
🔵 የሰውነት ህመም ስሜት
🔵 ሰውነትን እንደተፈለገ ማንቀሳቀስ አለመቻል
🔵 ቁርጥማት
🔵 ብርድ ብርድ ማለት ይጠቀሳሉ፡፡
#መንስኤዎቹ
🔵 ከባድ ስራዎችን ማዘውተር
🔵 ረፍት አለማድረግ
🔵 የመውደቅ ወይም የመመታት አደጋ
🔵 የታይሮይድ ሆርሞን ችግር
🔵 ለኮሌስትሮል ማስተካከያ ተብለው የሚወሰዱ መድሀኒቶች
🔵 የጡንቻ መቆጣት
🔵 የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ሳያሟሙቁ መጀመር
🔵 በሰውነት ውስጥ የፖታሲየም ንጥረ-ነገር እጥረት መከሰት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
#በቤት #ውስጥ #ሊያደርጓቸው #የሚችሉት #መፍትሄዎች
🔵 ረፍት ማድረግ
🔵 የህመም ማስታገሻ መድሀኒቶችን መውሰድ
🔵 የታመመው ጡንቻ ላይ በበረዶ መያዝ ነገር ግን 3 ቀን ካለፈው ለብ ያለ ውሀን መጠቀም
🔵 ሰውነትን ለማሳሳብ መሞከር
🔵 ከባድ ስራዎችን ማቆም
🔵 የዮጋ እንቅስቃሴዎችን መስራት ይጠቀሳሉ፡፡
#ቀይ ሽንኩርት ለጸጉር እድገት ያለውን ጠቀሜታ ያውቃሉ?

ብዙዎቻችን ቀይ ሽንኩርት ምግብ ለማዘጋጀት ከሚኖረው ፋይዳ ባለፈ ለጸጉር እድገት የሚረዱ ንጥረ ነገሮች መያዙን አንረዳም።

• የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ግን ቀይ ሽንኩርት የጸጉር መበጣጠስን ለመከላከልና የአዲስ ጸጉር እድገትን ለማፋጠን የሚረዳ መሆኑን አረጋግጠዋል።

• ቀይ ሽንኩርትን በምግብ መልክ አልያም በጭንቅላታችን ላይ ዘወትር መጠቀም እንደ ፎረፎር እና ሌሎች የጭንቅላትና ከጸጉር ጋር የተያያዙ በሽታዎችን ለመከላከል አይነተኛ ሚና ይጫወታል።

• ቀይ ሽንኩርት በዘር ወይም ከእንክብካቤ ጉድለት የሚከሰት የጸጉር መበጣጠስን ለመቀነስና ካለጊዜ የሚመጣ የጸጉር ቀለም ለውጥ ወይም ሽበትን ለመከላከል ይረዳል።

• ጥሬ ሽንኩርትን በስሱ ክብ አድርጎ በመክተፍ ጸጉር ላይ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ማድረግ ከዛ በኋላ በቀዝቃዛ ውሃ በሳሙና መታጠብ የፀጉር እድገትን ለማፋጠን ይረዳል።

• ቀይ ሽንኩርትን በጁስ መልክ በማዘጋጀት መጠቀምም የደም ዝውውርን በማቀላጠፍ የጸጉር እድገት እንዲፋጠን ያግዛል።

• በሰልፈር የበለጸገው ሽንኩርት የጸጉር ቅንጣቶች እንዲቀጥኑ በማድረግ በርካታ ጸጉር እንዲኖረንም ከፍተኛ ጥቅም አለው።
2025/07/06 18:59:05
Back to Top
HTML Embed Code: