Telegram Web Link
#በጸሃይ #አማካኝነት #የሚፈጠር #የፊትመጥቆር #ለማስተካከል #የሚረዱ #ውህዶች #

የእሬት ጄል ፦ በእሬት ውስጥ ያሉ አሎሲን እና አሎይን ንጥረ ነገሮች የጠቆረ ቆዳን የማንጣት አቅም ስላላቸው ለዚህ ትልቅ አስተዋጾ ያደርጋሉ።

👉 ቲማቲም ጁስ ፦ የቲማቲም ጁስ ፊታችንን ንጹህ ካደረኝ በኋላ መቀባት እና 20 ደቂቃ አቅይቶ መታጠብ ።

👉 ፓፓዬ ፦ፓፓዬውን ወይም ልጣጩን ፊታችንን መቀባት ።

👉 ቫይታሚን ሲ፦ ይህን በምግባችን ለማካተት መሞከር እንዲሁም የቫይታሚን ሲ ውጤት የሆኑ የፊት ክሬሞችን መጠቀም።

👉 ቫይታሚን ኢ ፦ በቫይታሚን ኢ የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር፣ ከምግብ ውጪ ሰፕሊመንቶችን ከቫይታሚን ሲ ጋር አድርጎ መጠቀም፣ እንዲሁም የቫይታሚ ኢ ክሬሞች መጠቀም ።

👉 ቀይ ሽንኩርት ፦ የቀይ ሽንኩርት ጁስን ፊትን መቀባት እና 20 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ።

👉 የሎሚ ጁስ ፦ የሎሚ ሃውን ፊትን በመቀባት ከ5 _ 10 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ። ነገር ኝ መጀመሪያ ለቆዳዎ ተስማሚ መሆኑን የእጆ ክንድ ላይ በመቀባት ማረጋገጥ።

👉 ወተት፦ ወተት መጠጣት እንዲሁም ከአጃ ዱቄት ጋር በመደባለቅ በእስክራፕ መልክ በማዘጋጀት ፊትን መቀባት እና ከ15 _ 25 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ በሳምንት እስከ ሁለቴ መጠቀም።

👉 ማር፦ ማር ሙሉ ለሙሉ ጸረ ባክቴሪያነት ያለው ሲሆን ፊትን በመቀባት ፊትን ለማንጻት እንዲሁም አዳዲስ ሴሎች እንዲፈጠሩ ለማገዝ ይረዳናል።
#የወር #አበባ #ደም #የሚበዛባቸው #ምክንያቶች
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
👉👉 #የወር አበባ ኡደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡ በየወሩ ኦቫሪ (የእንቁላል አቃፊ) ከተባለው የሰውነት ክፍል ኦቩሌሽን (ውጻት) በተባለ ስርአት አንድ እንቁላል ይወጣል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የተለያዩ የሆርሞን ለውጦች ማህጸንን ለእርግዝና ያዘጋጁታል፡፡ እርግዝና ሳይከሰት ከቀረ ግን ይህ የተደረገ ዝግጅት ፈርሶ በወር አበባ መልኩ ከሰውነት ይወገድና ለሚቀጥለው ኡደት ዝግጅት ይጀመራል፡፡
👉👉 #ይሄ እንደ ሰዉ ሁኔታና ከሰው ሰውም ምክኒያቱ ይለያያል።አብዛኛውን ጊዜ ምንም ምክኒያት ሳይኖር የወር አበባ ሊበዛ ይችላል።
👉👉 #የወር አበባ ደም መብዛት መንስኤዎች
📌 ከኦቫሪዎቹ አንዱ ለአንድ ወር ወይም ከዚያም በላይ እንቁላል ማዘጋጀት ካቆመ
📌 የማህጸን እጢ (fibroids)
📌 በደም መርጋት ችግር
📌 አንዳንድ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ወይም ደም ለማቅጠን የሚወሰዱ መድሃኒቶች የጎን ተፅዕኖዎች
📌 ከየታይሮይድ ዕጢ ጋር (ሆርሞኖችን የሚያመነጭ ዕጢ) ጋር የተያያዙ ችግሮች
📌 የማሕጸን ካንሰር
👉👉 #በወር አበባ ወቅት የሚፈስ የደም መጠን የተለመደው ምን ያህል ነው?
የተለመደው የወር አበባ ጊዜ ከ 8 ቀናት ያነሰ ነው።
👉👉 #ከስር የተዘረዘሩት የወር አበባ የበዛ መሆኑ የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው
📌 ሙሉ በሙሉ እየራሰ በ1 ወይም 2 ሰአት ውስጥ አንድ ሞዴስ የቀየሩ እንደሆነ
📌 ከፍተኛ መጠን ያለው ደም (የረጋ ደም) የፈሰሰ እንደሆነ
👉👉 #የወር አበባ ደም መብዛት አደገኛ ሊሆን የሚችለው
📌 በ 2 ሰዓታት ውስጥ 4 ወይም ከዚያ በላይ ሙሉ በሙሉ የራሰ ሞዴስ ከቀየሩ ሃኪምዎን ያማክሩ ወይም ወደ ድንገተኛ ክፍል ይሂዱ።
📌 ነፍሰ ጡር ከሆኑና ደም ከፈሰሰም ድንገተኛ ነው
👉👉 #ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያለብኝ መቸ ነው?
📌 ነፍሰጡር ነኝ ወይም ልሆን እችላለሁ ብለው ካሰቡ
📌የወር አበባዎ ከ 8 ቀናት በላይ የሚቆይ ከሆነ
📌 ሙሉ በሙሉ እየራሰ በ1 ወይም 2 ሰአት ውስጥ አንድ ሞዴስ የቀየሩ እንደሆነ
📌 ብዙ ደም እየፈሰሰዎት ስለሆነ ሁለት ሞዴሶች ደራርበው መጠቀም ካስፈለግዎት
📌 ለሊት ተነስተው ሞዴስ መቀየር ካስፈለግዎት
📌 ከ 1 ኢንች የበለጠ የረጋ ደም የፈሰሰ እንደሆነ
📌 የወር አበባ ከጨረሱ በኋላ በድጋሚ ያለጊዜው የወር አበባ ካዩ
📌 መጸነስ እየፈለጉ ካልቻሉ
📌 ቢያንስ ለአንድ አመት የወር አበባ ሳያዩ ከቆዩ በኋላ ደም ከፈሰሰ ፤ ማለትም ካረጡ በኋላ ደም ካዩ
📌 ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ከታዩ እና የደም ማነስ ካስከተለብዎት
👉👉 #የወር አበባ ደም መብዛት ህክምናው ምንድን ነው?
ህክምናው እንደ መንስኤው ይለያያል። አብዛኛውን ጊዜ ሕክምና ላያስፈልግ ይችላል።ካስፈለገ ግን ህክምናዎቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ።
📌 ሆርሞኖች ያላቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች
📌 የደም መቅጠን የሚቀንሱ መድሃኒቶች
📌 እብጠት የሚቀንሱ መድሃኒቶች
📌 ፕሮጄስቲን የተባለ ሆርሞን ያላቸው መድሃኒቶች
📌 ኦቫሪዎችን ለአጭር ጊዜ ሥራቸውን እንዲያቆሙ የሚያደርጉ መድሃኒቶች
📌 በቀዶ-ህክምና ፋይብሮይዶች ወይም ሌሎች እባጮችን ማስወገድ
Follow my tictoc page
✍️#ካሮትና አቮካዶን ጨምሮ ለአይናችን ጤና እና የእይታ ጥራት የሚረዱ ምግቦች

ለዓይን ጥራት ከፍተኛ ጥቅም አለው በሚል ለምግብነት ከሚውሉት ውስጥ ካሮት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ ብዙዎቻችን እናውቃለን።
ተመራማሪዎች ከሰሞኑ ባወጡት የጥናት ውጤት ደግሞ ከካሮት በተጨማሪ አትክትሎችን ጨምሮ በርካታ ምግቦች የአይናችንን የእይታ ጥራት እና ጤና ለመጠበቅ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል።

የዓይንን ጤንነት እና የእይታ ጥራት ለመጠበቅ የሚረዱ ምግቦችም፦

1.አቮካዶ
አቮካዶ ሉተን እና ዠያንቲን የተባሉ አንቲ ኦክሲደንት ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘ በመሆኑ በብርሃን ምክንያት በዓይናችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት የመከላከል አቅሙ ከፍ ያለ ነው ተብሏል።

በፈረንሳይ የተሰራ ጥናት እንዳመለከተው፥ ዠያንቲን የተባለው አንቲ ኦክሲደንት በዕድሜ ምክንያት የሚከሰት የእይታ ችግር፣ በደም ግፊት፣ ለከፍተኛ የብርሃን ጨረር በመጋለጥ እና በአመጋገብ ችግር በዓይናችን ላይ የሚከሰተውን የጤና ችግር ይከላከላል።
በተጨማሪም አቮካዶ ቫይታሚን ሲ በውስጡ በመያዙ አይናችን ጤነኛ ሆኖ አንዲቆይ እንደሚረዳም ነው ጥናቱ ያመለከተው።

2.እንቁላል
እንቁላል የዓይናችንን ጤና በመጠበቅ በኩል ያለው ጠቀሜታም ከፍተኛ መሆኑ ይነገርለታል።
የቫይታሚን ኤ ምንጭ የሆነው እንቁላል ለዓይን ጤንነት ጠቃሚ ነው የተባለ ሲሆን፥ ልክ አንደ አቮካዶ የእንቁላል አስኳልም ዠያንቲን የተባለው አንቲ ኦክሲደንት በውስጡ በመያዙ በብርሃን ጨረር ምክንያት በዓይን ላይ የሚከሰትን ጉዳት ለመከላከል ይረዳል።

3.ካሮት
ካሮት የዓይናችንን የእይታ ጥራት እንደሚጨምር ከዚህ በፊት ሲነገር የነበረ ሲሆን ፥ በዚህኛው ጥናት ማረጋገጫ ማግኘቱም ተነግሯል።

በቫይታሚን ኤ የበለፀገው ካሮት ቤታ ካሮቲን የተባለ ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ የዓይናችን የእይታ ጥራት ከፍ ያለ እንዲሆን እንደሚያደርገው ጥናቱ አመልክቷል።
በጥናቱ ላይ እንደተመለከተው ቫይታሚን ኤ፣ ቤታ ካሮቲን፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኤ፣ ዚንክ እና ኮፐር ንጥረ ነገሮችን የሚወስዱ ሰዎች ከአድሜ ጋር ተያይዞ ለሚከሰት የዓይን ችግር የመጋለጥ እድላቸው 25 በመቶ የቀነሰ መሆኑ ተረጋግጧል።

4.አረንጓዴ ሻይ
አረንጓዴ ሻይ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት የሚነገርነት ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ የሰውነትን ክብደት ለመቀነስና የአእምሮን የመስራት አቅም መጨመር ተጠቃሽ ሲሆኑ፥ ከዚህ በተጨማሪም ለዓይናችን ጤንነት ጠቃሚ መሆኑ ተነግሯል።
በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ ያሉት እንደ ቫይታሚን ሲ፣ ሉተን እና ዠያንቲን የተባሉ አንቲ ኦክሲደንቶች ካንሰርን፣ የልብ ህመምን እና የዓይን በሽታን ለመከላከል እንደሚረዱ ጥናቱ አመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የሚገኘው ገሎካትቺን የተባለ ንጥረ ነገር ለዓይን ጤንነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑንም ነው ጥናቱ ያመለከተው።
✍️ #የኤች. አይ..ቪ #ተጋላጭነት #ኖርዎት #እነዚህን #ምልክቶች #ካስተዋሉ #ምርመራ #ያድርጉ!
🔵 # እነዚህን 13 ምልክቶች ካዩ የኤች. አይ..ቪ ምርመራ ማድረግ ይኖርቦታል፡፡
🔹 ትኩሳት ፡- ጥንቃቄ የጎደለዉ ጾታዊ ግንኙነት ከነበርዎት እና ያልተለመደ ትኩሳት ከተከሰተብዎት ምን አልባት ኤች. አይ..ቪ ሊሆን ስለሚችል ምርመራ ማረግ ይኖርቦታል፡፡
🔹 የጉሮሮ መቁሰል
🔹 የጡንቻ እና የመገጣጠሚያ ህመም
🔹 ደረቅ ሳል
🔹 የንፍፊት እብጠት
🔹 የራስ ምታት ህመም
🔹 ክብደት መቀነስ
🔹 የፈንገስ ኢንፌክሽን
🔹 ድካም እረፍት ሲያረጉበትም ለዉጥ የማያሳይ
🔹 የቆዳ ሽፍ ማለት በፊት፣ በላይኛዉ ጀርባ እና በብልት አካባቢ
🔹 ማታ ማታ ማላብ
🔹 ምች
🔹 ምንም ምልክት አለመኖር ፡- ጥንቃቄ የጎደለዉ ጾታዊ ግንኙነት ካለዎት በተደጋጋሚ ምርመራ ማድረጉ አስፈላጊ ነዉ፡፡
እነዚህን 10 የሰውነት ምልክቶች ካስተዋሉ ችላ አይበሏቸው!

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

🔵#ሰውነታችን እያንዳንዱ ክፍል ተግባሩን የሚያከናውንበት የራሱ ሂደት አለው፡፡እነዚህ ሂደቶች በሚታወኩ ጊዜ ሰውነታችን እንድናውቅ የሚረዱ ምልክቶችን ይልካል፤ ስለሆነም እነዚህን ምልክቶች ማወቅ እና በቶሎ እርምጃ መውሰድ ተባብሰው የሚያስከትሉትን የከፋ ችግር መግታት ያስችላል፡፡

1. #የድድ መድማት፡- ይህ የቫይታሚን ሲ (Vitamin C) እጥረት ነው ስለዚህ ሻይ ይጠጡ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ይመገቡ፡፡

2. #የቆዳ መድረቅ፡- የቫይታሚን ኢ (Vitamin E) እጥረት ሲሆን የአሳ ዘይት፣ ለውዝ እና የአትክልት ዘይት ይመገቡ፡፡

3. #ጨው የበዛበት ምግብ አብዝቶ ለመጠቀም መፈለግ፡- ይህ የሰውነት መጉረብረብ (መመረዝ) ወይም የመራቢያ አካል ኢንፌክሽን አመላካች ሊሆን ይችላል፡፡

4. #ጣፋጭ ነገሮችን መውደድ ወይም መፈለግ፡- ይህ የሚያሳየው መጨነቅ (ስጋት) እና ድካም ነው፡፡ ስለዚህ ግሉኮስ ፈጣን እረፍት ይሰጠናል ብለን እናስባለን ነገር ግን በምትኩ ማር እና ደረቅ ቸኮሌት ይውሰዱ፡፡

5. #የእንቅልፍ ችግር፣ የሀሃፍረት ስሜት እና ግልፍተኝነት፡- ይህ ምልክት ማለት የማግኒዢየም እና ፖታሲየም እጥረት በሰውነታችን ውስጥ ተከስቷል ማለት ነው፡፡ ለማግኒዚም እጥረት ለውዝ፣ ሱፍ እና ተልባ ይመገቡ ለፖታሲየም ደግሞ ሙዝ፣ ስኳር ድንች፣ አረንጓዴ እና ቅጠል ያላቸው አትክልቶች፣ ስፒናች ጎመን፣ የስዊዝ ቆስጣ ይመገቡ።

6. #ጥሬ ምግቦችን መውደድ/ መፈለግ፡- ከጨጓራ ወይም ከየጉበት ጋር የተያያዘ ሲሆን ጥሬ ምግቦች የሆድ መነፋት እና ቁርጠትን ያስታግሳሉ፡፡

7. #የክርን ቆዳ መድረቅ፡- የቫይታሚን ኤ እና ሲ (Vitamin A & C) እጥረት ሲሆን ካሮት፣ ብርቱካን፣ አትክልትና ፍራፍሬ ይመገቡ፡፡

8. #የባህር ውስጥ ምግቦችን በጉጉት መፈለግ፡- የባህር ውስጥ ምግቦችን ለመመገብ በጣም የሚጓጉ ከሆነ የአዮዲን እጥረት እንዳለ ያመላክትዎታል።

9. #ለመራራ ምግቦች ከፍ ያለ ጉጉት መኖር፡- መራራ ምግቦችን ለጉበት እና የሃሞት ከረጢት ተግባር/ ሥራ ያስፈልገናል ስለዚህ ሎሚና ክሬይንቤሪ ይመገቡ፡፡

10. #የፀጉር እና ጥፍር መሰባበር፡- ሰውነትዎ የካልሲየም እና ቫይታሚን ቢ (Calcium & Vitamin b) እጥረት አለ ማለት ነው ስለዚህ ወተት፣ ድንች፣ ጥራጥሬ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንብራ እና ስንዴ ይመገቡ፡፡
2025/07/06 05:15:28
Back to Top
HTML Embed Code: