Telegram Web Link
✍️ #የሳይነስ #ኢንፌክሽን(#ሳይነሳይተስ)

👉👉#የሳይነስ #ኢንፌክሽን #ምንድን #ነዉ?

#በአፍንጫ ቀዳዳ ዙሪያ በሚገኙ አጥንቶች ላይ የሚገኙ አራት ጥንድ በአየር የተሞሉ ክፍት ቦታዎች ኢንፊክሽን ነዉ፡፡ ሳይነሳይተስ የአፍንጫ ቀዳዳዎች እንዲቆጡ እና እንዲያብጡ ያደርጋል፤ ይህም ከአፍንጫ ፈሳሽ እንዳይፈስ እና ንፍጥ እንዲጠራቀም ያደርጋል፡፡

👉👉#ሳይነሳይተስ #ምልክቶች #ምንምን #ናቸዉ?
🔺 በአፍንጫዎ ላይ የሚወርድ ፈሳሽ
🔺 ወፍራም፣ ቢጫ ወይም አረንጓዴ ፈሳሽ በአፍንጫዎ ወይም በአፍዎ የላይኛዉ ክፍል መፍሰስ/መዉጣት
🔺 የአፍንጫ መዘጋት፣ የአፍንጫ መታፈን ወይም በአፍንጫዎ ለመተንፈስ መቸገር
🔺 በአይን፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ እና ግንባር አካባቢ ህመም እና ክብድ ማለት በተለይም ዝቅ ሲሉ የሚባባስ ህመም
🔺 የጆሮ ህመም ወይም ዝግት ማለት
🔺 እራስ ምታት
🔺 የላይኛዉ አገጭ እና ጥርስ ቁርጥማት ወይም ህመም
🔺 የማሽተት እና የመቅመስ ስሜትዎ መቀነስ
🔺 ሳል፤ማታ ማታ የሚባባስ
🔺 መጥፎ የአፍ ጠረን
🔺 ድካም
🔺 ትኩሳት

👉👉#ሳይነሳይተስ #በምን #ምክንያት #ሊመጣ #ይችላል?

🔺 ብዙዉን ጊዜ በቫይረስ የሚመጣ ሲሆን አንዳንዴ በባክቴሪያ ይመጣል፡፡

👉👉#ለሳይነሳይተስ #ተጋላጭነት #የሚጨምሩ #ነገሮች #ምን #ሊሆኑ #ይችላሉ?
🔺 አለርጂ ያለባቸዉ ሰዎች
🔺 የአፍንጫ ቀዳዳዎች ችግር ያለባቸዉ ሰዎች (ለምሳሌ የአፍንጫ እጢ፣ የአፍንጫ ቀዳዳዎች አካፋይ መዛባት )
🔺 ሲስቲክ ፋይብሮሲስ፣ ኤችአይቪ-ኤድስ እና ሌሎች የበሽታ መከላከል አቅምን የሚያዳክ በሽታዎች መኖር

👉👉#ሳይነሳይተስ #ምን #ሊያስከትል?
🔺 ስር የሰደደ ሳይነሳይተስ
🔺 ማጅራት ገትር/ሜኒንጃይተስ/፡-የአንጎል እና የህብለ ሰረሰር (አከርካሪ ላይ ያሉ የነርቭ ሴሎች) ልባስ መቆጣት
🔺 የአጥንት ወይም የቆዳ ኢንፌክሽን
🔺 የማሽተት ስሜት መጥፋት ወይም መቀነስ
🔺 የእይታ ችግር

👉👉#መከላከያ #መንገዶቹ?
🔺 አለርጂዎን መቆጣጠር
🔺 አለማጨስ
🔺 የተበከለ አየር ላይ መራቅ
🔺 ጉንፋን አለመያዝ(ጉንፋን ካለበት ሰዉ መራቅ፣ እጆን መታጠብ)

👉👉 #ምርመራዎቹ #ምን #ምን #ናቸዉ?
🔺 የአካል ምርመራ
🔺 የአፍንጫ ኢንዶስኮፒ
🔺 ሲቲ ስካን /ኤም-አር-አይ ለተወሳሰበ ሳይነሳይተስ
🔺 የአፍንጫ እና የሳይነስ ካልቸር
🔺 የአለርጂ ምርመራ

👉👉 #ህክምናዉ
🔺 ብዙዉን ጊዜ በቫይረስ የሚመጣዉ ያለህክምና ይድናል፡፡
🔺 እንደአስፈላጊነቱ የተለያዩ መድሃኒቶች ሊታዘዙም ይችላል

👉👉 #የቤት #ዉስጥ #መፍትሔዎች
🔺 እረፍት ማድረግ
🔺 ፈሳሽ አብዝቶ መጠጣት
🔺 ሞቅ ባለ ዉሃ/ስቲም መታጠን
🔺 ፎጣ ሞቅ ያለ ዉሃ ዉስጥ በመንከር ፊቶ ላይ ማስቀመጥ
🔺 ጨዉ ያለዉ ለብ ያለ ዉሃ በአፍንጫ መማግ
🔺 እራሶን ከፍ አርገዉ መተኛት
#ስኪለስ #አዲስ #ለልጅዎ #ጥያቄ #ዘመናዊ #መልስ !

* ከራስዎ አስበልጠው #ለሚወዷቸው ልጆችዎም ሆነ ለራስዎ ፤ከዘመኑ ጋር አብሮ የዘመነ የጆሮ መብሻና የጆሮ ጉትቻዎችን እነሆ በረከት የሚልዎት ስኪለስ አዲስ ነው!

*ስኪለስ አዲስ ግዙፉ #የስቴዴክስ ካምፓኒ የንግድ አጋር በመሆኑ በሀያ አራት ካራት ወርቅ የተለበጡ የጆሮ መብሻን ከጆሮ ጌጦቻቸው ጋር በልዩነት #ድንቅ በሆነ ሁኔታ በሀገራችን #ብቸኛ #ወኪል በመሆን እያስመጣ ከበቂ ልምድ ጋር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

*በመሆኑም #የልጆችዎን #ጆሮ ለማስበሳትም ሆነ ጉትቻዎችን ለመግዛት ወደ ስኪለስ አዲስ መጡ ማለት ሙሉ በሙሉ #ከአለርጂና በጆሮ ላይ ከሚደርሱ ማንኛውም ህመሞች ነጻ እንደሚሆኑ ዋስትና ገቡላቸው ማለት ነው፡፡

*ምን ይሄ ብቻ #ሲጫወቱም ሆነ #ሲተኙ አልያም ሲታጠቡ ወድቆ ቢጠፋባቸውስ ከሚል ስጋትም በስኪለስ አዲስ ግሩም አቅርቦትና አገልግሎት ተገለገሉም እንጂ!

*ሌላስ ካሉ ፤ የስኪለስ አዲስ የአመብሻ ጌጦች የተሰሩት ከኒኬል ነፃ ስለሆነ #ማሳከክ ፣መቁሰል ማበጥ #መቆርቆርና #እንዲሁም አለርጂ የሚባል ነገር የለም።

በተጨማሪም በብዙ #ወላጆች #ጥያቄ መሠረት ከአራት ወር በታች ላሉ ልጆቾ በአይነቱ ለየት ያለ #ድምፅ አልባ የጆሮ መብሻ ለአንድ ልጅ ብቻ ተጠቅመዉ የሚጥሉት መብሻ መሳሪያ አስመጥተን አገልግሎት መስጠት ጀምረናል።

*ታዲያ ይሄን የመሰለ #መልካም #ዜና ስንነግርዎት ምን አሉ? ጉዞ ወደ ስኪለስ አዲስ አላሉም?

ለልጆቾ በማሰብ እንዲሁም ካለዉ የስራ መደራረብ #ጨቅላ ልጆቾን ይዘዉ ወረፋ በመጠበቅ እንዳይጉላሉ እንዲሁም ከኮሮና ቫይረስ እራስዎትንም ሆነ ጨቅላ ልጆቾን ለመጠበቅ በቀጠሮ ይስተናገዱ።

*ካሉበት ወደእኛ ለመምጣት ሲወስኑ ቀጠሮ እንዲያዝልዎት 0911799754 እነዚህን ቁጥሮች ይጠቀሙ።

አድራሻችን ኤድና ሞል ፊት ለፊት የሚገኘዉ ቦሌ መድሀኒያለም ሞል አንደኛ ፎቅ ቁጥር 107 እንዲሁም ጋራድ ሲቲ ሴንተር ወሎ ሰፈር ምድር ላይ ቁጥር G 13።

#ስኪለስ #አዲስ #የብልህ #ወላጆች #ምርጫ

***በተጨማሪም አዳዲስ ጌጣጌጦችን በየጊዜው ስናስገባ ለምርጫ እንዲረዳዎት

👉👉 የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/skillusjewelery
✍️ #የአረንጓዴ #ሻይ #የጤና #ጥቅሞች

# #አረንጓዴ ሻይ ለመድሀኒትነት ለሺህ አመታት ሲጠቀሙበት ኑረዋል፣ መነሻው ከቻይና ቢሆንም በመላው ኤስያ በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል፣ የአረንጓዴ ሻይ ከጥቁር ሻይ አንጻር ይበልጥ የጤና ጥቅሞች ያሉት በምርት ሂደቱ ምክንያት ነው:: የጥቁር ሻይ አመራረት በማብላላት መልኩ ሲሆን የአረንጓዴ ሻይ አመራረት ደግሞ የማብላላት ሂደትን በማስወገድ ነው:: በዚህም ምክንያት፣ አረንጓዴ ሻይ ከፍተኛ የሆነ የአንቲ ኦክሲዳንት እና ፖሊ_ፌኖልስ መጠን አሉት እነዚህም ነገሮች አረንጓዴ ሻይ ብዙ ጥቅሞች እንዲኖሩት ምክንያት ናቸው::

🔺 #ክብደት #ለመቀነስ: -
አረንጓዴ ሻይ ሜታቦሊዝምን ይጨምራል:: በአረንጓዴ ሻይ የሚገኘው ፖሊፌኖል የስብ ኦክሲዴሽንን የሚያጧጡፍ ስራ የሚሰራና ሰውነታችን ምግብን ወደ ካሎሪ የመቀየሩን ተግባር የሚያለሳልስ ነው::

🔺 #ለስኳር
ምግብ ከተመገብን በኋላ በደማችን ውስጥ የሚጨምረውን የግልኮስ መጠን፤ አረንጓዴ ሻይ ፍጥነቱ እንዲገታ ለማድረግ ይረዳል:: ይህም የከፍተኛ ኢንሱሊን ጡዘትንና የስብ ክምችት ማስከተሉን የሚከላከል ነው::

🔺 #ለልብ #በሽታ
ሳይንቲስቶች እንደሚያስቡት፣ አረንጓዴ ሻይ በደም ቧንቧ የላይኛው ገጻቸው ላይ ስራውን የሚሰራና፣ የደም ቧንቧወች ፋታ እንዲያገኙና ለደም ግፊት ለውጦች የተሻለ መቋቋም እንዲኖራቸው ይረዳል:: እንዲሁም ደግሞ የደም መርጋትን ይከላከላል፣ የደም መርጋት የልብ ችግር ግንባር ቀደም ምክንያት ነው::

🔺 #የጉሮሮ #ካንሰር
በጉሮሮ ካንሰር የመያዝ አደጋን የሚቀንስ ነው፣ ግን በስፋት እንደሚታወቀው የካንሰር ሴሎችን መግደል የሚችል እና በዙሪያው በሚገኙት ጤነኛ የሆኑ ቲሹዎች ላይ ጉዳት የማያደርስ ነው::

🔺 #ኮሌስትሮል
አረንጓዴ ሻይ በደም ውስጥ ያለን መጥፎ ኮሌስትሮል የሚቀንስና የጥሩውን ኮሌስትሮል ከመጥፎው ኮሌስትሮል የተሻለ የሚያመዛዝን ነው::

🔺 #አልዛይር #እና #ፓርኪንሰን
በአልዛይመር እና በፓርኪንሰን የሚመጡትን ችግሮች የሚያዘገይ እንደሆነ ይነገራል:: ጥናት እንደሚያሳየው አረንጓዴ ሻይ የአዕምሮ ሴሎችን ከመሞት የሚያድንና የተጎዱ የአዕምሮ ሴሎችን የሚጠግን ነው::

🔺 #የጥርስ #መበስበስ
ጥናቶች እንደሚያመልክቱት በሻይ የሚገኘው “ካቴቺን” የተባለው አንቲኦክሲደንት ኬሚካል የጉሮሮ መመርቀዝ፣ የጥርስ መበስበስ እና ሌሎች የጥርስ ችግሮችን የሚያስከትሉትን ባክቴሪያና ቫይረሶች የሚያወድም ነው፡፡

🔺 #የደም #ግፊት
አረንጓዴ ሻይን አዘውትሮ መጠቀም የደም ግፊት አደጋን እንደሚቀንስ ይታመናል::

🔺 #ድብርት
ቲያኒን በሻይ ቅጠሎች በተፈጥሮ የሚገኝ አሚኖ አሲድ ነው:: ይህ ንጥረ ነገር የሚያዝናና እንዲሁም የሚያረጋጋ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን ለሻይ ጠጪወችም ላቅ ያለ ጥቅም ይሰጣል::

🔺 #ፀረ-ቫይረስ #እና #ፀረ-ባክቴሪያል
ጠንካራ ፀረባክቴሪያል እና ፀረቫይረስ ባህርይ ያለው ሲሆን ከኢንፍሉየንዛ እስከ ካንሰር ያሉ በሽታወችን በማከም ውጤታማ ናቸው:: በአንዳንድ ጥናቶችም አረንጓዴ ሻይ የአብዛኞቹን የበሽታወች ስርጭት መግታት እንደሚችል ያመላክታል::

🔺 #ለቆዳ #ውበት
አረንጓዴ ሻይ የቆዳ መጨማደድንና የማርጀት ምልክትን ለመቀነስ የሚረዳ ነው፣ ለዚህ ምክንያትም ያላቸው ፀረ-ኦክሲደንት እና ፀረ-መመረዝ ተግባር ነው:: በእንስሳት ሆነ በሰው ላይ የተደረጉት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አረንጓዴ ሻይ በጸሀይ የሚመጣ ጉዳትን የሚቀንስ ነው::

#ምን #ያህል #እንጠቀም?
🔺 #በቀን ውስጥ ከአንድ እስከ ሁለት የአረንጓዴ ሻይ ስኒ መውሰድ ይመከራል፡፡

🔺 #ሌላው መጠቀስ ያለበት ጉዳይ በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ ካፊን እንደሚገኝ ነው፡፡ ስለዚህም ለካፊን ስሜታችሁ ስስ ከሆነ አንድ ስኒ በቂያችሁ ነው::

🔺 #አረንጓዴ ሻይ ታኒስ(የብረትን እና የፎሊክ አሲድን ውህደት የሚቀንስ) ይገኝበታል፣ ስለዚህም ነፍሰጡር ከሆንሽ ወይም ደግሞ ለማርገዝ እቅዱ ካለሽ አረንጓዴ ሻይ ለአንቺ አይሆንም::

🔺 #አረንጓዴ ሻይን እንደ ዝንጅብልና ሌሎች ጤናማ ንጥረ ነገሮች ላይ ማዋሀድ ይቻላል ።
#ደም #የቀላቀለ #ሰገራ
********

ውድ የዶክተር አለ ቤተሰቦች እንዴት አደራችሁ በየትኛው የጤና ጉዳዮች መረጃ መስጠት እንዳለብን አስተያየታችሁን ጠቁሙን። እኛ ለናንተ ይጠቅማን ያልናቸውን ወደናንተ ለማድረስ ዝግጁነን !!

ደም የቀላቀለ ሰግራ ማለት በየትኛውም የአንጀት ክፍል መድማት ሲያጋጥም በሰገራ መልኩ ደም ሲታይ ነው። ከተቀመጡ በኋላ ሰገራው ላይ እና የሽንት ቤት ወረቀት ላይ ደም ሲታይ ደም ሰገራ ላይ እንዳለ ይታወቃል ።

#ምክንያቶቹ
· የአንጀት ክፍል ላይ የወጣ ቀዳዳ መሰል ነገር(Diverticular Diseeas )
· የፊንጢጣ ኪንታሮት(Hemorrhoide)
· የፊንጢጣ መሰንጠቅ(Anal fissuer)
· የአንጀት መለብለብ(Colitis)
· የአንጀት አካባቢ ደም ስሮች ላይ ችግር ሲኖር(Angiodysplasia)
· የጨጓራ ቁስለት
· አንጀት ላይ ትርፍ ስጋ መሰል ነገር ሲያድግ(Polyps)
· አንጀት ካንሰር
· የምግብ ትቦ ላይ ችግር ካለ(Esophageal problem)
· የአንጀት ላይ ኢንፌክሽን

#ምልክቶቹ
አብዛኛው ሰው ምልክቶቹን ላያስተውል ይችላል ።በሌላ በኩል ደግሞ ከሚከሰቱ ምልክቶች ውስጥ
* የሆድ ህመም
*ማስመለስ
*ድካም
*ለመተንፈስ መቸገር
*ተቅማጥ
*ራስን መሳት
*የሰውነት ክብደት መቀነስ የማሳሰሉት ናቸው።

#ህክምናው
_ያመጣውን ነገር በምርመራ ከተረጋግጥ ወይም ከታወቀ በኋላ መንሰኤውን ማከም
_በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ መድሀኒቶችን በአግባቡ መውሰድ
_በፋይብር የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፣ ሙቅ ውሀ ላይ መዘፍዘፍ(የፊንጢጣ ኪንታሮት፣የፊንጢጣ መሰንጠቅ ከሆነ ያመጣው)
እንደማጠቃለያ ደም የቀላቀለ ሰገራ በትንሽ (በቀላል) እንዲሆም ከበድ ባሉ ምክንያቶች በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሰት እና ምልክቶቹ ቶሎ የማይስተዋሉ ሰለሆነ እንዳወቁ የጤና ባለሙያ ያማክሩ።

9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
#የጭንቀት #ምንጮች #ምንድን #ናቸው?

👉👉የጭንቀት ምክኒያቶች በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ለይቶ ማየት ይቻላል፡-
1. ስነ ልቦናዊ መንስሄዎች
2. አካላዊ

1.#ከስነ #ልቦናዊ #ምንጮች፦ በስራ ቦታ በሚፈጠር የሥራ ጫና፣ የሥራ አሰራር ግልፅነት ማጣት፣ ከሚወዱት ሰው ጋር የሚፈጠር ችግር፣ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ግዴታዎችን መወጣት አለመቻል፡- ለምሳሌ የቤት ኪራይ፣ አስቤዛ፣ ወርሃዊ የመብራት ክፍያ ወዘተ…፣ ለአዳዲስ ነገሮች መዘጋጀት፡- ለምሳሌ ልጅ መወለድ፣ አዲስን ስራ መያዝ፣ የትራፊክ መጨናነቅ፣ ከፍተኛ ድምፅ…

2. #አካላዊ #መንስሄዎች፦ ህመም፣ ከፍተኛ የአየር ሁኔታ፡- ለምሳሌ ከባድ ሙቀት ወይም ከባድ ቅዝቃዜአካላዊ ህመም፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣትና ሲጋራ ማጨስ በሰውነት ላይየሚፈጥሩት ጫና ወዘተ ናቸው።

👉👉የጭንቀት ውጤቶች ምንድን ናቸው?

የሰውነት ድካም
ከፍተኛ የራስ ምታት
ብስጭት
የምግብ ፍላጎት መዛባት
የማስታወስ ችሎታ መቀነስ
ለራስ የሚሰጥ ዋጋ ወይም ክብር መቀነስ(low self-esteem)
ከማህበራዊ ህይወት መገለል
የ ደም ግፊት መጨመር
ትንፋሽ ማጠር
የወሲብ ፍላጎት መቀነስ
የእንቅልፍ መዛባት
የጨጓራና አንጀት ስርዓት መዛባት
የልብ ህመም
የቆዳ ችግር (skin disorders)

👉👉ጭንቀት ለስነልቦናዊ ቀውሶች ለምሳሌ፡- ለፍርሃትና ለድብርት ይዳርጋል፡፡

👉👉 ጭንቀትን ለመቆጣጠር የሚከተሉትን መፍትሄዎች ይጠቀሙ።
በውስጣችን የሚያቆጠቁጠውን የተስፋ ቢስነት ስሜት ማወቅ
የቁጣ ስሜቶቻችንን መለየት
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ
የሚወዱትን ሥራ መሥራት
አስቂኝ ፊልሞችንን መመልከት
ራስን አለማማረር
ባለሙያ ማማከር
2025/07/05 20:15:53
Back to Top
HTML Embed Code: