Telegram Web Link
ረሱል አለይሂ ሰላም አቡ ሁረይራ በዘገቡት ሀዲስ  "አላህ ወደ ገፅታችሁ እና ንብረቶቻችሁ አይመለከትም።ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ግን ይመለከታል።

አላህ ዘንድ እዚህ መፎካከርያ የሆነው ስራችን ምንም ቦታ የለውም... ይመስለናል እንጂ ሰዎችም ጋር ይህ ቦታ አይኖረውም.... ሁለመናችሁ ይረሳል በቅፅበት ይረሳል... የሆነኛው ሰው ላይ የተዋችሁት እዝነት እና መልካምነት ሲቀር።


ሁላችንም እንሄዳለን ፋናችንም ይቀራል...!

ግን ምን አይነት ፋና ...?

@DinisNesiha
ዛሬ ነገ ሳትሉ ፣ምን ይዤ ሳትሉ ፣ማንንም ሳትጠብቁ ከጎኑ ልትሆኑለት ሚገባ ሰዉ ጋር ሁኑ !
🔥2
ተወዳጁ ቲቪ ብቅ ብሏል
=================
✍️ ላለፉት ጊዚያት ከኢትዮ ሳት ያጣነውና በናይል ሳት ብቻ የነበረው ተወዳጁ ነሲሓ ቲቪ፤ እነሆ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮሳት ብቅ ማለቱን አብስሮናል።

መልዕክታቸውን እንደወረደ ላካፍላችሁ፦
«📡 ውድ የነሲሓ ቲቪ ተከታታዬቻችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ኢትዮሳት የገባን መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን::

▫️ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-

Ethiosat

Frequency: 11545
Polarization: Horizontal
Symbol Rate: 45000

በተጨማሪም DSTV ላይ ያገኙናል !

ነሲሓ ቲቪ
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!»
👍7
🔶"አሳባችሁታል ግን (የቀብርን)ህይወት ዲንያ ላይ ቆይታችን በጣም እረዘመ ከተባለ100አመት አይበልጥም የበረዘኸ ቆይታች ግን 2ሺ 3ሺ አመት ሊሆን ይችላል.!!ይሄን ሁሉ አመት በቅጣት ወይም በእረፍት .!ያረብ🤲
👍4
ኸይር ነገር ከአላህ ብቻ ነው ሚከጀለው....🙌
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ..!
ከመካነ ሰላም መስጂድ የሚሰማው ነገር ወላሂ እጅግ ልብ ይሰብራል...💔
👍1🏆1

እኛ ....እኮ
እገሊትኮ ኒቃብ ለበሰች ስንባል....ውይ ድሮ'በሱሪ ነበር ምትሄደው
እገሊትኮ በማዕረግ ተመረቀች.... የምራቹን ነው? ድሮ'ኮ ሰነፍ ተማሪ ነበረች
እገሊትኮ እገሌን አገባች... ጥሩ ሰው ነው አሉ ሲባል... ኧረ ባክሽ ዝምበይ ድሮ'ኮ የለየለት ዱርዬ ነበር
እገሌኮ ኡስታዝ ሆነ...ምን? ያ በቁማር አብዶ የነበረው?
እገሌኮ ልታገባ ነው.... ውይ ድሮ'ኮ የሰፈሩ ወንድ ሁሉ ጓደኛዋ ነበር...
በሰው ለውጥ ለምን ማሻአላህ ደስ ይላል አላህ ይጨምርለት አንልም?
ድሮ'ኮ ድሮ'ኮ ድሮ'ኮ
"በድሮ በሬ ያረሰ የለም" ይላል ያ'ገሬ ሰው
ሰው በነበረበት አይቆይም..... ይለወጣል ይበስላል ያብባል ይስተካከላል.....
እራሳችንን እንገምግም
በሰው ስኬት እንደሰት ሲያልፍለት ደስ ይበለን ሲለወጥ ሲሻሻል እናበረታታ ድሮ እንዲህ ነበር እያልን አሁን ያለበትን ስኬት በዜሮ ለማባዛት አንቸኩል በቃ ተለወጠ ተሻሻለ
"ማሻአላህ ደስ ይላል" ማለትን እንልመድ...✌️

Be positive💪
@DinisNesiha
👌7💯2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚘ቁርአን.....🌸
የጨለመን ህይወት በብርሃን የሚሞላ፣
የተሳሳተን የሚገስፅና የሚያመላክት...
ውበቱ ማራኪ ተደምጦ የማይጠገብ
የማያቋርጥ የልብ ብርሃን ነው።🍃

🥀ተጋበዙልኝ🥀
👍6
ከትንሹ ሞት በኋላ ቀስቅሶ ይበልጥ
ወደርሱ እንድንመለስ ተጨማሪ ዕድል ሰጥቶናል
الحمد لله
ሰባህል ኸይር ...🙌

@DinisNesiha
🔥1
ከሰው የምትጠብቅ ከሆነ እንደ ሰፌድ ታረጃለህ

ትንሽ ስራ ከአላህ ጠብቅ...🙌
@DinisNesiha
ምንም ያህል ብናድግ፣ ብንበስል … ልባችን ግን እንክብካቤና ትኩረት የሚፈልግ ህፃን ሆኖ ይቆያል። የትኛውም የተጨበጨበለት ስኬት ላይ እንድረስ… አብዝተን ለምንወዳቸው ብቻ የምንገልጠው ድካም አለ። አድገናል…  ግን ከማይላቀቅ መሻት ጋር ፣ ትኩረት እንዲሰጠው ከሚፈልግ የህፃን ልብ ጋር፣ እንዲለማመጡት ከሚሻ ሩህ ጋር… አድገናል.....🌱

@DinisNesiha
👍1
ትዳር መጣልኝ ...አልኳት
አላህን ያውቃል አለችኝ ...
አዎ አልኳት ምን ማለቷ እንደሆነ ባይገባኝም ...
አግቢው አይበድልሽም አለችኝ...

አልኳት አላህን ማወቅ ግን ምን ማለት ነው..?የሚሰግድ ..የሚቀራ..የሚጾም...?

የሚሰግድለት ጌታው ባንቺ ሀቅ እንደሚተሳሰበው የሚያውቅ፤ያንቺ በሱ ህይወት መግባትሽ ..ኢማኑ እንዲሞላ..ሰላምና መረጋጋት በህይወቱ እንደሚኖር ሰበብ መሆንሽ የገባው...፤አላህ ያንቺን ህይወት ከጀነት ጋር አያይዞ ሲያበቃ ባልሽ የጀሀነም ህይወትን ላለማኖር ከአላህ  ጋር ለሚኖረው ሂሳብ ሲል የሚፈራ ነው አላህን የሚያውቅ...የሚባለው! በማለት ቋጨችልኝ እህትዬ ....✌️

@DinisNesiha
👏6
ክብራችሁ እንደ መድሃኒት ነው ሕፃናት ከማይደርሱበት ቦታ አርቃችሁ አስቀምጡት...ሁሉም ግንኙት ላይ ክብር ይቀድማል ያከበረን ያስከብረናል ...ያከበርነው ይከበርልናል ...🙌

@DinisNesiha
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🫀....
🏆3👍1
በነገራቶች ላይ ቁጭት እንዳይኖርህ ከፈለክ....ሁሉንም ለአላህ ስትል ስራ ..!
👍7
አነጋን ...
ንግስናም ለአሏህ ሆኖ አነጋ ፤
ምስጋና ለአሏህ የተገባ ነው ...አልሀምዱሊላህ
👌3🏆1
#መወደድ ሪዝቅ ነው...!

ሪዝቅህ በየትኛው ቀልብ ውስጥ እንዳለ የምታውቀው ነገር የለም ...!

@DinisNesiha
9/10/2025 ....Gaza ❤️
💯2👍1
የዛሬው ጁምዐ አላህ ሆይ🤲🤲

   "ለትጨነቀ ሁሉ መፍትሄን
  ለዱዐ ሁሉ ተቀባይነትን
ለህመም ሁሉ ፈውስን
  ለወንጀል ሁሉ ምህረትን
  ለተቸገረ ሁሉ እሪዝቅን
ለሞተ ሁሉ እዝነትን
እንጠይቅሀለን ያረብ

እንደ እኛ ወንጀል ሳይሆን በእዝነትህ ማረን መጨረሻችንንም አሳምርልን  አሚን🤲

@DinisNesiha
👍6
2025/10/21 23:38:29
Back to Top
HTML Embed Code: