Forwarded from HudHud Promotion🕊🕊️
🌺ነቢያችን የእኔ ስም ተነሥቶ{ﷺ}
ሰለዋት የማያወርድ ሰው__ብለዋል‼️
#ደስታ ጣዕሙ የሚታወቀው ከብዙ ጭንቀቶች መሀል ብቅ ሲል ነው ...🌸
አልሀምዱሊላህ
@DinisNesiha
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير
ረበና  እንዳንቺ  ዉብና የተግራራ ሀያት ያርግልሽ ...የኔ ቆንጆ ጓደኛ ሙሽራ..

አልሀምዱሊላህ ኢማን በኒካህ ሞላ....🌸

@DinisNesiha
👍4
مِّنَ الْمُؤْمِنِينَ رِجَالٌ صَدَقُوا مَا عَاهَدُوا اللَّهَ عَلَيْهِ ۖ فَمِنْهُم مَّن قَضَىٰ نَحْبَهُ وَمِنْهُم مَّن يَنتَظِرُ

إنا لله وإنا إليه راجعون...
አላህዬ በጀነቱ ያሳርፋችሁ 🤲🤲
ከ 33 ዐመታት እስር በኃላ እስራኤል ስሞኑን የለቀቀችው ፍልስጤማዊ ወንድም ወጣትነቱ እንክት አድርገው በሉበት እናቱ ለ29 አመታት ጠብቃው ሳታገኘው ይህችን አለም ተሰናበተች...💔
ሞት...!!
👍1
#7ቱ_ቁርአን ውስጥ_ #የተጠቀሱ ከንቱ #ምኞቶች

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ تُرَٰبًۢا﴾
" ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ "
[ሱረቱ ነበእ 40]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى قَدَّمْتُ لِحَيَاتِى﴾
" ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራን) ባስቀደምኩ ኖሮ "
[ሱረቱል ፈጅር 24]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى لَمْ أُوتَ كِتَٰبِيَهْ﴾
" ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ "
[ሱረቱል ሃቀህ 25]

⇦ ﴿يَٰوَيْلَتَىٰ لَيْتَنِى لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًۭا﴾
" ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ "
[ሱረቱል ፉርቃን 28]

‏⇦ ﴿يَٰلَيْتَنَآ أَطَعْنَا ٱللَّهَ وَأَطَعْنَا ٱلرَّسُولَا۠﴾
" ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ "
[ሱረቱል አህዛብ 66]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى ٱتَّخَذْتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِيلًۭا﴾
" ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ "
[ሱረቱል ፉርቃን 27]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًۭا﴾
" ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ "
[ሱረቱ ኒሳእ 73]

☞ ሁሉም የሟቾች ምኞት ናቸው ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው ...

☞ ቀብር ገብተህ/ሽ አንተም.አንቺም ይህን ከምትመኝ/ኚ ነፍስህ/ሽ አካልህ/ሽ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም/ሚ።

yaአላህ ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን አሚን 🤲
🏆2👍1
እውነት የሚመስሉ ልክ ያልሆኑ አስተሳሰቦች  በሴቶች እና በወንዶች ዙሪያ

ወንዱ: ሀብታሞ ከሆንኩ የፈለኳትን ሴት መርጨ  አገባለሁ...

ሴቷ: ቆንጆ ከሆንኩ የፈለኩትን ወንድ እንዲያገባኝ ማድረግ እችላለሁ...

እውነታው ግን ከቀደራቸው አያልፉም 🤷‍♀️
💯10
ምርጥ ተውበት!

የታላቁ ዓሊም ማሊክ ኢብን ዲናር የተውበት ታሪክ...

ማሊክ ኢብን ዲናር ህይወታቸውን በስካር በመጠጥ ነበር የጀመሩት፣ ከዛም በአንድ ግዜ አግብተው ልጅ መውለድ ተመኙ እናም አገቡም አላህ 1ሴት ልጅ ሰጣቸው ስሟንም ፋጢማ አሏት። የዛኔ ልባቸው ወደ ኢማን እየተቃረበ መጣ ውጪ ይጠጡ የነበረውን ቤት መጠጣት ጀመሩ። ፋጢማንም ጭናቸው ላይ አድርገው ነበር የሚጠጡት፣አንድ ቀን ፋጢማ በ2 አመቷ እያለ መጠጡን ገፍታ ደፋችባቸው የዛኔ ይህ አላህ በፋጢማ ተው እያለኝ ነው ብለው አሰቡ፣ ከአመት በኃላም ፋጢማ 3አመት ሞላት ከዛም ፋጢማ ሞተች። ከዛም ድጋሚ እንደበፊቱ መጠጣት መስከር ጀመሩ፣ ታዲያ አንድ ቀን ሸይጧን ወሰወሰኝ አሉ ዛሬ ሰክረኸው የማታውቀውን ስካር ነው የምትሰክረው አለኝ እሺ ብዬ መጠጥ መጠጣት ጀመርኩ በጣም ሰክሬ ወደቅኩ አሉ። ከዚያም በህልሜ ቂያማ የቆመ መሰለኝ ፀሀይቱ ጠቁራለች፣ ሰወ ሁሉ አላህ ፊት ተሰብስቧል፣ ባህሩ ይነዳል የሰው ሁላ ስም ሲጠራ ቆየና ማሊክ ኢብኑ ዲናር ና ለሂሳብ ትፈለጋለህ ተባልኩ ከዛም ትልቅ ዘንዶ ማሳደድ ጀመረኝ እሱን ለመሸሽ ስሮጥ አንድ ሽማግሌ አገኘሁ አግዘኝም አልኩት እኔ አቅሜ ደካማ ነው አለኝ ስሮጥ የእሳት ጫፍ ላይ ደረስኩ፣ ዘንዶውን ፈርቼማ እሳት አልገባም ብዬ ተመልሼ ሮጥኩ ድጋሚም ሽማግሌውን አገኘሁ አግዘኝም አልኩት አቅሜ ደካማ ነው እስቲ የምትድን ከሆነ ወደዛ ተራራ ሩጥ አሉኝ። ከዚህም እየሮጥኩ እያለ ከተራራው ላይ ህፃኖች ፋጢማ አባትሽን ዘንዶ ሊበላው ነው ሲሉ ሰማሁ። ለካ በ3 አመቷ የሞተች ልጅ አለችኝ ብዬ ወደ ፋጢማ ሮጥኩ ፋጢማም ዘንዶውን ገፍታ ጣለችው። እኔም ልጄ ሆይ እስቲ ያ ዘንዶ ምንድነው የሚያባረኝ አልኳት እሷም ያ መጥፎ ስራህ ነው አለችኝ እሺ ያ ሽማግሌውስ ያ ጥሩ ስራህ ነው አለችኝ ጥሩ ስራህ ደካማ ሰለሆነ ከመጥፎ ስራህ ሊያስጥልህ አልቻለም አለችኝ። ከዛም 1 የቁርአን አያ ቀራችልኝ።

"እነዛ ምዕመናን ልባቸው ለአላህ ግሳፄ የሚፈራበት ግዜ አልደረሰምን?" የሚለውን አነበበችልኝ። ልክ አኔም ከእንቅልፌ አዎ ግዜው ደርሷል አያልኩ እያለቀስኩ ተነሳሁ ሻወር ወሰድኩ ሱብሂ ወደ መስጂድም ሄድኩ። መስጂድም ኢማሙ ይህንኑ አያ እየቀሩት ነበር አልቅሼ ተመለስኩ ይሉናል ታላቁ ኢማም።

እኝህ ሰው ህዝቡን የሚያስተምሩ ታላቅ ኢማም ሆኑ። ሁሌም መስጂድ አንተ አላህን ያመፅክ ባሪያ ሆይ ወደ ጌታህ ተመለስ ይሉ ነበር።

ጌታችን ሆይ ምህረትህን ለግስን 🤲
👍3
ISLAMIC-QUOTES pinned «ምርጥ ተውበት! የታላቁ ዓሊም ማሊክ ኢብን ዲናር የተውበት ታሪክ... ማሊክ ኢብን ዲናር ህይወታቸውን በስካር በመጠጥ ነበር የጀመሩት፣ ከዛም በአንድ ግዜ አግብተው ልጅ መውለድ ተመኙ እናም አገቡም አላህ 1ሴት ልጅ ሰጣቸው ስሟንም ፋጢማ አሏት። የዛኔ ልባቸው ወደ ኢማን እየተቃረበ መጣ ውጪ ይጠጡ የነበረውን ቤት መጠጣት ጀመሩ። ፋጢማንም ጭናቸው ላይ አድርገው ነበር የሚጠጡት፣አንድ ቀን ፋጢማ በ2 አመቷ…»
ከሚግባቡት ከአብሮ አደግ ከቅርብ ሰው ተገናኝቶ እንደመጫወት የልብን እንደማውራት  የሚያስደስት ነገር የለም ሲጀመር ሰዐቱ ራሱ ይፈጥናል አላህ ይጠብቅልኝ ሙሽራዬ ...
👍2
«ከትዕግስት ጋር (የአሏህ) እርዳታ አለ፣ከጭንቅ ጋር ፈረጃ አለ፣ ከችግር ጋር ምቾት አለ።» ውዱ ነቢይ ﷺ
[ ሶሒሑል - ጃሚዕ : 6806 ]
👍4
ማታ ላይ ከመተኛቷ በፊት ስትኳኳል አይተዋት
"ምንድነው በእንቅልፍ ሰዓት እንዲህ የምትቀባቢው?" አሏት።
"አስከሬን እያበጃጀሁ፤ ለገናዦቼ ስራ እያቃለልኩ ነው " አለች አሉ አንዷ እብድ።

አስክሬን ነንና ዉዱዕ አድርገን፣ በልቦናም ንፁህ ሆነን፣ አዝካሮችን አድርገን፣ የምድር ላይ የመጨረሻ ንግግራችንን አሳምረን እንተኛ!!
👍7
"ሁሉም ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት"
[አል-ዒምራን 3:185]

አላህ ኻቲማችንን ያሳምርልን🤲
በአላህን ተስፋ አትቁርጡ ዕለቱን በአላህ ላይ ጥሩ የቂን ኖሮአቹሁ ጀምሩ።"
اللهم بارك لنا في هذا الصباح ووفقنا لكل خير...🌸
ሰባህል ኸይር
@DinisNesiha
2025/10/21 10:58:07
Back to Top
HTML Embed Code: