Telegram Web Link
የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አዲሱን ሞዴል ትምህርት ቤት ጎበኙ

ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በቅርቡ ሥራ የጀመረውን የሁለተኛ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤት ዛሬ ጉብኝት አደረጉ።

ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ሞዴል ትምህርት ቤት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና በአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ትብብር የተቋቋመ ሲሆን በከተማዋ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ጉዞ ላይ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበታል።

ኃላፊው በቆይታቸው ወቅት የመማሪያ ክፍሎችን ተዘዋውረው በመመልከት የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚከናወንበትን ሁኔታ በቅርበት ተከታትለዋል። ከዚህም ባሻገር ከተማሪዎች ጋር በቀጥታ በመገናኘት የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ሱልጣን ለተማሪዎቹ ባደረጉት ንግግር ትምህርት ቤቱ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ መገኘቱ በራሱ ትልቅና ልዩ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል። "ይህንን ታሪካዊ ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ጊዜያችሁን ለትምህርት ብቻ በማዋልና በትጋት በማጥናት ለውጤት መብቃት አለባችሁ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
6👍5🥰2🤣1
በድሬዳዋ እና በፈረንሳይ እህትማማች ከተሞች ትብብር በትምህርት ዘርፍ ትልቅ እርምጃ ተወሰደ

ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም – የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ከእህት ከተማው የለቡግ ከተማ ከፈረንሳይ የመጡ ልዑካንን በማስተናገድ በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለውን የትምህርት ትብብር ለማጠናከር ሰፊ ውይይት አድርጓል። ልዑካን ቡድኑ እመቤታችን ኖተርዳም፣ ማርያም ሰፈር እና ለገሀሬ ትምህርት ቤቶችን በአካል በመጎብኘት የትምህርት አሰጣጡን ተመልክቷል።

በጉብኝቱ ማብቂያ ላይ የፈረንሳይ የለቡግ ከተማ ልዑካን ቡድን የራግቢ ስፖርት ካስ እና የጅምላስቲክ ቁሶችን ለትምህርት ቤቶቹ ስፖርት መምህራን አስረክበዋል። ይህም በትምህርት ቤቶቹ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ለማጎልበት ታላቅ እገዛ ያደርጋል ተብሏል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ እንደገለጹት ጉብኝቱ የድሬዳዋ ተማሪዎች የፈረንሳይን የትምህርት ልምድ እንዲቀስሙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

የልዑካን ቡድኑ አስተባባሪ ወ/ሮ ገነት ወ/ስላሴ በበኩላቸው የትምህርት ዕድሉ ከ5ኛ እስከ 10ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የራግቢ ስፖርት ምልመላን የሚያካትት ሲሆን ቀጣይነት ያለው የሙያዊ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

ይህ ትብብር የድሬዳዋን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል፣ የመምህራን ልምድ ልውውጥን ለማስፋት እንዲሁም ወጣቶችን በአዲስ ስፖርት ለማሳተፍ ያለመ ዘላቂ መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል።
👍61
2025/10/20 07:17:41
Back to Top
HTML Embed Code: