Telegram Web Link
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገመገመ 

ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አስተባባሪዎች ጋር ገምግሟል፡፡

በመድረኩ ላይ የቢሮው የሱፐርቪዥን ቡድን በትምህርት ቤቶች ያደረገውን ምልከታ መነሻ በማድረግ በመማር ማስተማር ሂደት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ላይ ግብረ መልስ ተሰቷል፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ የግምገማው ዓላማ ጥንካሬዎችን አስቀጥሎ ክፍተቶችን ማስተካከል መሆኑን ገልጸው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሁሉም በቁርጠኝነት እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት ሐሳቦች ላይ ውይይት ተደርጎ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።
3👍1
ወ/ሮ ዶል መሀመድ ኡመር ለሀጂ መሀመድ ኦክሰዴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ


ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም –በድሬዳዋ በሀጂ መሀመድ ኦክሰዴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ለ850  አቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉም ደብተር፣ እርሳስ፣ እስክሪብቶ እና ላጲስ ያካተተ ሲሆን  የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ በጋራ በመሆን ድጋፉን ለተማሪዎቹ አስረክበዋል።

አቶ አቡበከር ቁሳቁሶችን በሚያስረክቡበት ወቅት እንደገለፁት ወ/ሮ ዶል መሀመድ ኡመር የአባታቸውን ስም ለማክበርና የትውልድን እውቀት ለመደገፍ ላሳዩት ልባዊ ተነሳሽነትና በጎነት ከፍ ያለ አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል። እኚህ በጎ አድራጊት ሴት የትምህርት ቤቱን ተማሪዎች የወደፊት ዕድል በእጅጉ የሚያበራ ብርሃን እንደለኮሱ ገልጸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከእርሳቸው እንዲማሩ ጥሪ አቅርበዋል።
10👍5
2025/10/20 00:21:27
Back to Top
HTML Embed Code: