የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በድሬዳዋ ትምህርት ቤቶች የግምገማና የውይይት መድረኮች ተካሄዱ
ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ስኬታማ ለማድረግና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማና የውይይት መድረኮችን አካሄዱ።
የመልካ ጀብዱ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ዓ.ም የትምህርት ቤት ማሻሻያ ዕቅድ ላይ ከመምህራንና ከአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ሰፊ ግምገማ አድርጓል። በዚሁ መድረክ ላይ በ2017 የትምህርት ዘመን በትምህርትና አስተዳደር ሥራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራን የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
በተመሳሳይ የሀፈት ኢሳ ትምህርት ቤትም በትምህርት አሰጣጥ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ዘላቂ መፍትሄ ለማስቀመጥ ያለመ ውይይት ከተማሪ ወላጆች ጋር አካሂዷል። ውይይቱ ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ክትትል በማጠናከርና ከትምህርት ቤቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማሳደግ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
በመድረኮቹ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ የትምህርት ስራ ዋነኛ አላማ እውቀትና ክህሎትን ከማስታጠቅ ባለፈ በስነ ምግባር የታነጹ ዜጎችን መፍጠር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። "የትውልድ ግንባታ የሚሳካው አካዳሚያዊ ብቃትን ከመልካም ስነ ምግባር ጋር ማዋሃድ ስንችል ነው" ያሉት ኃላፊው ይህን ግብ ለማሳካት የመምህራን፣ የወላጆችና የማህበረሰቡ የተቀናጀ ርብርብ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

❤8