ለቅዱሳን ቤተሰቦቹ የጸሎት መልስ የሆነው፣ ለዚህች ዓለም የሚነድና የሚያበራ መብራት የነበረው፣ የሥጋን ጣዕም ያልቀመሰው ፍጹም ተሐራሚ፣ ተፈጥሮው የሰው ኑሮው የመልአክ የነበረው፣ ዕረፍትን የማያውቅ የበረሃው ሰው የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ልደቱ ዛሬ (ሰኔ 30) ይታሰባል።
ቅዱሱ ሰማዕት እንደ ኖኅ ጻድቅ የነበረ፣ እንደ አብርሃም በእግዚአብሔር የተወደደ፣ እንደ ዮሴፍ የታሰረ፣ እንደ አቤል በአመጻ የተገደለ፣ እንደ ሄኖክ አካሄዱን ከአምላኩ ጋር ያደረገ ነው።
በመንፈስ ቅዱስ አሳዳጊነት በመላእክት አገልግሎት በበረሃ ያደገው ዮሐንስ ክብሩ እንዴት ያለ ነው? እርሱ እንደ ሕፃናት ባለቀሰ ጊዜ የሚያባብለው ሰው አልነበረም። "አይዞህ ልጄ" እያለች የምታጽናናው እናቱም ገና በልጅነቱ ተለይታዋለች። ነገር ግን እግዚአብሔር ብቻውን በበረሃ አልተወውም። አጥንት በሚያለመልም የመላእክት ምስጋና አረጋጋው። በልዩ ጥበቡም አሳድጎ በመንፈስ እንዲጠነክር አደረገው። የእግዚአብሔር አብን ልጅ ዮሴፍ በናዝሬት (የሰው ልጅ) እንዳሳደገ፣ የዘካርያስን (ለሰውን) ልጅ ዮሐንስን እግዚአብሔር በበረሃ አሳደገ።
ዮሐንስ ነቢይ ነው። ግን ከነቢያትም ይበልጣል። እርሱ እንደ ሌሎቹ ነቢያት የመሲሑን መምጣት በመንፈስ ዓይቶ "ይመጣል" ብቻ አላለም። "እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ" ብሎ ወደ እርሱ በመጠቆም ሲጠበቅ የኖረው ለመምጣቱም አብሣሪ ሆኗል። እርሱ ነቢያቱ ሊያዩ የወደዱትን ግን ያላዩትን፣ሊሰሙ የፈለጉትን ግን ያልሰሙትን አይቷል፤ ሰምቷልም። ወልድን የዳሰሰ፣ አብን የሰማ፣ መንፈስ ቅዱስን ያየ እንደ ዮሐንስ ያለ ነቢይ ማን አለ?
ዛሬ የተወለደው ቅዱስ ዮሐንስ አምላኩን ማገልገል የጀመረው ገና በእናቱ ማኅጸን ሳለ ነው። ነቢዩ ለፈጣሪው በደስታ የሰገደው ገና ከተፈጠረ በ180ኛው ቀኑ ነው። ታዲያ እኛ እግዚአብሔርን ለማገልገል ለምን ቀጠሮ እናረዝማለን? ገና ነን እንደርስበታለን እንዴት እንላለን? ከዛሬው ባለ ልደት አንጻር ለአገልግሎትና ለምስጋና በጣም የዘገየን አይመስላችሁም? የታደለው ቅዱስ ዮሐንስ በስድስት ወሩ ሰገደ። የእኛስ ይህ አፈርና ትቢያ የሚሆን ሰውነታችን ሳይወድቅ በፊት ፈጣሪውን የሚያገለግለው መቼ ነው?
"በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል"
ሉቃ 1፥14
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በዓለ ልደት፣ 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ቤተሰብ ይሁኑ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com

‹‹ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ›› ማር 3፥13
ጌታችን በሰንበት ወደ ምኩራብ ገብቶ እጁ የሰለለችበትን ሰው ባዳነ ጊዜ፣ በሥራው የተቆጡ አይሁድ እንዴት እንዲያጠፉት ከሄሮድስ ወገን ጋር ይማከሩ ጀመር፡፡ እነርሱ በሰንበት የተወሰነ መንገድ (የሰንበት መንገድ) ከመሄድ ጀምሮ ቀላል የሆኑ የሰውነት እንቅስቃሴ የሚፈልጉ ተግራትን በነጻነት ሲያከናውኑ፣ እርሱን ግን በቃሉ እንኳን ተናግሮ ሕሙማንን እንዳይፈውስ ይከላከሉት ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ መድኃኒታችን ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ወደ ገሊላ ባሕር ፈቀቅ አለ፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ ብቻ አይደሉም፡፡ ያደረጋቸውን ታላላቅ ተአምራት የሰሙ ብዙዎችም ከተለያዩ ቦታዎች እርሱ ወዳለበት መጥተው ነበር፡፡
ጌታችን ኢየሱስ የተሰበሰቡት ሰዎቹ እንዳያጋፉት ታንኳ ያዘጋጁለት ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፡፡ የሚገርመው ከዚህ ታሪክ መፈጸም በፊትም ሆነ በኋላ ጌታችን በብዙ ሰዎች መካከል ተከቦ አስተምሯል፡፡ የልብሱንም ጫፍ ለመዳሰስ የለመኑትን ሳያሳፍራቸው ዳሰሰዉት እንዲፈወሱ አድርጓል፡፡ አሁን ግን ሰዎቹ ‹እንዳያጋፉት› ሐዋርያቱ ታንኳ እንዲያዘጋጁለት አዘዘ፡፡ ልብ በሉ ‹እንዳይዳስሱት› አላለም፣ ‹እንዳያጋፉት› እንጂ፡፡ ይህ ስለ ምን ሆነ? ካላችሁ፣ ልብሱን ለመዳሰስ የሚቀርቡት ሰዎች አቀራረባቸው ‹በልመና›/‹በጸሎት› ሲሆኑ፣ የሚጋፉት ሰዎች ግን ቃሉም እንደሚገልጸው ወደ እርሱ ለመቅረብ የሚሞክሩት በጉልበታቸው ነው፡፡ ስለዚህ በትሕትና ሆነው ለሚለምኑት ቅርብ ሆኖ ሲዳሰስላቸው፣ በጉልበታቸው ለሚጋፉት ግን ሊደርሱበት ወደማይችሉት ባሕር ተሳፍሮ ይርቅባቸዋል፡፡ እግዚአብሔርን በእምነት ብርሃንነት ስትፈልገው ቅርብ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ በራስህ ማስተዋል ግን በመደገፍ ላስሰው ብትል መሰወሪያውን ጨለማ ያደርግብሃል፡፡
በሕዝቡም መካከል ሲያልፍ በሥጋ ደዌ የሚሰቃዩ ሰዎች ዳስሰውት ከሕመማቸው ይፈወሱ ዘንድ ከፊቱ ይወድቁ ነበር፡፡ ርኩሳት መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ እየሰገዱ ‹አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ› እያሉ ጮኹ፡፡ አይሁድ በላያቸው የወደቀውን የርግማን ቀንበር ለማንሣት የመጣውን የአብ ልጅ ‹የዮሴፍ ልጅ› እያሉ ሲያናንቁ፣ የጥፋታቸው አጋፋሪዎች የሆኑ አጋንንት ግን ‹አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ› ሲሉ ስለ እርሱ መሰከሩ፡፡ ‹አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ› የሚለው ንግግር በቤተ ክርስቲያን ያለው ቦታ ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ የሚበልጥ የምስክር ቃልም የለም፡፡ በዚህ ቃል ቅዱስ ጴጥሮስ ‹አንተ ብፁዕ ነህ!› ተብሎ ተመስግኖበታል፣ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ ጥምቀተ ክርስትናን አግኝቶበታል፡፡
ታዲያ ቅዱስ ጴጥሮስ ተናግሮ ሳይመሰገንበት፣ ባኮስም መስክሮ ሳይጠመቅበት በፊት ይህንን ቃል ለተናገሩ ለአጋንንት ጌታችን ምን መልስ ሰጣቸው? መልሱ ግልጽ ነው፤ ‹እንዳይገልጡት በጣም አዘዛቸው›፡፡(ማር 3፡12) ለምን? ምክንያቱም ፍቅርና ትሕትናን የማያውቁ አጋንንት መቼም ቢሆን የእውነት ምስክር መሆን ስለማይችሉ ነው፡፡ የሚናገሩት ነገር እንኳን በቤተ ክርስቲያን የሚታመን እውነት ቢሆንም፣ አጋንንቱ ግን ይህን የሚሉት እውነትን ወድደው ሳይሆን ቀጥለው ለሚያቀርቡት መርዝ ማጣፈጫነት ያህል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እነርሱን እንደ ጌታችን ‹እውነትን እንዳይገልጡ በጣም ከማዘዝ› ውጭ መቼም ቢሆን ጆሮ ሰጥተን ልናደምጣቸው አይገባም፡፡
የአጋንንት ምስክርነትን ጠልቶ እንዳይገልጡት ያዘዛቸው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዲያውኑ የወደዳቸውን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ጠርቶ ምስክሮች ይሆኑት ዘንድ የጽድቅ ሐዋርያት አደረጋቸው፡፡ በዚህም ተግባሩ ከአጋንንት ይልቅ የሐዋርያቱና በሐዋርያት እግር የሚተኩ የካህናትና የመምህራነ ቤተ ክርስቲያን ምስክርነትን በእርሱ ዘንድ የተወደደ እንደሆነ አሳየን፡፡ ደግሞም ሐዋርያቱን ወደ እርሱ የጠራቸው እንዲሰብኩ ብቻ ሳይሆን ‹ከእርሱም ጋር እንዲኖሩ› ጭምር ነው፡፡(ማር 3፡14) ከጌታው ጋር መኖር የማይችል ስለ ጌታው መስካሪ ሆኖ ሊጠራ አይችልም፡፡ የአጋንንት ትልቁ ድክመታቸውም ይህ ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሊናገሩ ይችላሉ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ግን መኖር (በቅድስና) አይችሉም፡፡
በመጨረሻም ውሸት የማይቀላቅሉ የእውነት ሐዋርያት ከተመረጡ በኋላ በመንገዳቸው ሁሉ የሚፈታተኗቸው የሐሰት ምስክሮች አጋንንት ሊወገዱ ይገባቸዋል። ስለዚህ ክርስቶስ ወድዶ ለመረጣቸው አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አጋንንትን ያወጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጣቸው፡፡ በርግጥም አጋንንት ተባራሪ፣ ወጭ እንጂ ተሰሚ፣ መስካሪ ሊሆኑ አይገባም።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
ጥቅምት 18/ 2013 ዓ.ም.

+++ "እየጠላን የምናደርገው" +++
ብዙ ሰው ‹‹እኔ ሐሜት አልወድም፡፡ ግን ማማት የሚወዱ ጓደኞች አሉኝ›› ይላል፡፡ አሁን እርሱ ምን እያደረገ ነው? ‹‹ወዳጆቼ ሐሜተኞች ናቸው›› ሲል እያማቸው አይደለምን? ወይስ ለእርሱ ሲሆን ሐሜቱ ተለውጦ የመረጃ ቅብብል ይሆናል?! በነገራችን ላይ ይህ የዚህ ጽሑፍ መግቢያ ራሱ ሐሜት ነው።
የማንወደው ነገር ግን እየጠላንም ቢሆን የምናደርገው ኃጢአት ሐሜት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሜተኛ ሆኖ የተጠቀሰው በእባብ ያደረው ሰይጣን ነው፡፡ በመጀመሪያ የታማው ደግሞ እግዚአብሔር ሲሆን፣ ሐሜቱን ሰምታ ሳትመረምር የተቀበለችውና ለስሕተት የቸኮለችው ሴት ሔዋን ነበረች፡፡(ዘፍ 3፥1-5)
የሰይጣን ሐሜት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንደኛ "አትሞቱም፤ እንደ እርሱ እንዳትሆኑ ነው የከለከላችሁ" በሚለው ንግግሩ "እግዚአብሔር ዋሽቷችኋል" እያለ ፍቅሩን እንድትጠራጠር እያደረገ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ከዛፉ ብትበሉ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ በማለት የእግዚአብሔር አምላክነት "የዛፍ ፍሬ" በመብላት የተገኘ መሆኑንና እርሱም እንደ እነርሱ የነበረበት ጊዜ እንዳለ እንድታስብ እየገፋፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት (Character assassination) ከየት ሊገኝ ይችላል? ሰይጣን በነገር ሁሉ ፍጹም የሆነን አምላክ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሐሰት ፈጥሮ ለማማት ወደ ኋላ ካላለ፣ አንዳች ጉድለት የማያጣብን እኛማ ከሐሜቱ ጅራፍ ልናመልጥ እንደማንችል ሊታወቅ ይገባል፡፡
በተለይ በአሁን ጊዜ ሐሜት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሥሩን ሰድዷል። እንደውም ባልንጀራን ማማት እንደ ምግብ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን በዚህች ደሃ አገር ከመጠን በላይ ወፍረን እንቸገር ነበር። ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን የሐሜት አውድማዎች ሆነዋል። በየገጾቻችን ከሽነን የምናቀርባቸው ጽሑፎች ጠረናቸው የሰው ሥጋ የሰው ሥጋ ይላሉ። ፊታችን በሐሜት ወይቦ ሁለት መልክ ካወጣን ቆየን። ይኸው ሳንባችን በማማት አየር ተመርዞ ሳሉ ከበረታብን ሰነባብተናል። ወዳጃችንን የማናማበት ብቸኛው ጊዜ ከእርሱ ጋር የምንሆንበት ሰዓት ነው። ያውም ደግሞ ያንኑ ጊዜ ሌላኛውን ሰው ለማማት ካልተጠቀምንበት ማለቴ ነው።
ሊቁ ዮሐንስ ካዝያን እንደሚናገረው ሰው ከሚጠቅመው ቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የማይጠቅመው ሐሜት ያጓጓዋል። የአምላክ ቃል ሲነገር እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለው ሁሉ፣ የሐሜት ነገር ሲሆን ግን እንደ እርሱ ንቁ የሚሆን የለም። በጥፍሩ ቆሞ ይሰማል። ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኛ ቢያድር ደስ ይለዋል።
ለመሆኑ ባልንጀራችንን ስለ ምን በቀስታ እናማዋለን? የወዳጃችንንስ ውድቀት በማውራት በእኛ ላይ የምንጨምረው ምን በጎ ነገር አለ? በሰው ፊት መልካም እየመሰልን ከኋላው ግን ስለ እርሱ ውድቀት በማውራት የራሳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይቻልም። ስለ ሌሎች በማውራት የምናጠፋውን ሰዓት ራሳችንን ለማሳደግ ብንጠቀምበት ኖሮ "መኖራችንን ትርጉም እንዲኖረው" ማድረግ ይቻለን ነበር።
"ንጹሕ ወዳጅነት" ሐሜትና ማሾክሾክ የሌለባት የታማኞች ጌጥ ናት። የሐሜት ስለታቸውን ያልጣሉ ሰዎች "እውነተኛ ባልንጀርነት"ን አያውቋትም። አንተ በፍቅር ወዳጅ አድርገህ ከፊትህ ስታቀርባቸው እነርሱ ከኋላህ ሆነው የሚያሙህን አትጥላቸው፤ አትጣላቸው። ነገር ግን የሐሜቱ እርሾ እንዳያገኝህ ቶሎ ተለያቸው። ከፊትህም አድርገህ አታሰቃያቸው። የእነርሱ ቦታ ከኋላህ መሆን ነው።
ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።
ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።
"ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" ገላ 5፥15
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg

Forwarded from Dn Abel Kassahun Mekuria
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
+++ "ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና" +++ ፊል 1፥21
እነሆ ምሳሌ፣
በምንኩስና ይኖር የነበረ አባት ከዕለታት በአንዱ ቀን ወደ ገነት ሄደ። ከውጭም ቆሞ እንዲከፈትለት ደጁን ያንኳኳ ጀመር። ወዲያውም "ማን ነህ?" የሚል ድምጽ ከውስጥ ሲወጣ ሰማ። መነኩሴውም "እኔ ነኝ" ሲል መለሰ። ይሁን እንጂ ያንኳኳው በር ግን ሊከፈትለት አልቻለም። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም እንደ ገና ተመልሶ ወደ ገነት በመምጣት ደጁን አንኳኳ። እንዳለፈውም ጊዜ ከውስጥ "ማን ነህ?" የሚል ድምጽ ሰማ። እርሱም እንደ ለመደው "እኔ ነኝ" አለ። አሁንም በሩ ሳይከፈትለት ቀረ።
መነኩሴው በዚህ ተስፋ አልቆረጠም። ይህ ከሆነ ከብዙ ዓመታት በኋላ እርሱም በመንፈሳዊው ጥበብ ጎልምሶ ተመልሶ ወደ ገነት ሄዶ በሩን አንኳኳ። እንደ ከዚህ በፊቱም "ማን ነህ?" የሚል ድምጽ ሰማ። ያም አባት የቀድሞው መልሱን ተወና "በእኔ ውስጥ የምትኖረው አንተ ነህ" ሲል ለጠየቀው አካል መለሰ። በዚህ ጊዜ ተዘግቶ የነበረው በር ተከፈተለት ይባላል።
ክርስትና ምንድር ነው? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ ማብራሪያዎች ሊሰጡ ይችላሉ። በአጭሩ ግን እንመልሰው ካልን፣ ክርስትና ማለት "ክርስቶስ የሚያድርበት መቅደስ መሆን" ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ሲገልጽልን "እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል" ይለናል።(ገላ 2፥20) ክርስቲያን ማለት "አንተ ማን ነህ?" ተብሎ ሲጠየቅ ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "በእኔ የሚኖር ክርስቶስ ነው"፣ "አነ ዘክርስቶስ" - "እኔ የክርስቶስ ነኝ" ብሎ መመለስ የሚችል ነው።
ጌታችን በወንጌል ለደቀ መዛሙርቱ "በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ" ሲል እንደ ተናገረ፣ እኛ ለክርስቶስ መኖር ስንጀምር እርሱ ደግሞ በእኛ ይኖርብናል፤ እኛ ለክርስቶስ ማደር ስንጀምር እርሱ ደግሞ በእኛ ያድርብናል።(ዮሐ 15፥4)
እንዲህ ያለውን ሕይወት የሚኖር እውነተኛ ክርስቲያን የሥጋን ሞት አይፈራም። ስለ ሃይማኖቱ መከራ መቀበልን አይሰቀቅም። ክርስቶስን ከሚያሳጣው ሕይወት ይልቅ ወደ ክርስቶስ የሚወስደውን ሞት ይመርጣል። ፈጣሪው ከሌለበት ምቾት ይልቅ ፈጣሪን ይዞ መሰቃየት ለእርሱ ያስደስተዋል።
ሰይፍ ይዘው በሚያስፈራሩትም ጨካኝ ወታደሮች ፊት "ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና" እያለ በሐሴት ይዘምራል።(ፊል 1፥21)
በሰይፍ ለሚገድለው ወታደር በኩራት የልብሱን ኮሌታ ከፍ አድርጎ አንገቱን ስለ ክርስቶስ በደስታ የሰጠ፣ የታላቁ ሐዋርያ የቅዱስ ጳውሎስ የአገልግሎቱ ድካም፣ በረከት በሁለችን ላይ ይደርብን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
የጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓለ ዕረፍት፣ 2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ቤተሰብ ይሁኑ
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
አብ የማይጠልቅ ፀሐይ እንደ ሆነ ፣ ወልድም ዘወትር በቅዱሳን ላይ የሚያበራ ፀሐይ ነው። መንፈስ ቅዱስም ቤተ ክርስቲያንን የሚያስጌጣት ብርሃን ነው።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፣ እንደ እስጢፋኖስ የድንጋይ ልብስ አልለበስኹም፣ እንደ ቂርቆስም በእሳት አላጌጥኹምና ምሕረታችሁ ልብስ ሆኖ እርቃኔን ይሸፍንልኝ።
እንኳን አደረሳችሁ!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፣ እንደ እስጢፋኖስ የድንጋይ ልብስ አልለበስኹም፣ እንደ ቂርቆስም በእሳት አላጌጥኹምና ምሕረታችሁ ልብስ ሆኖ እርቃኔን ይሸፍንልኝ።
እንኳን አደረሳችሁ!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስማቸውን የምንጠራቸው ቅዱሳን ሁሉ የእግዚአብሔር የመሐሪነቱ ምልክቶች ናቸው። ዛሬ የእግዚአብሔር ወዳጆች ብለን የምናከብራቸው ንጹሐን፣ ትናንትና በሕይወታቸው ወድቀው የተነሡ እና በንስሐ እንባ ታጥበው ይቅርታን ያገኙ ኃጥአን ነበሩ። አሁን በቤተ ክርስቲያን ሰማይ ላይ ሲያንጸባርቁ የምናያቸው ቅዱሳን፣ ውበት የሚሰውረውን የኃጢአት ግርዶሽ በንስሐ አስወግደው በቸርነቱ ብርሃን የደመቁ ከዋክብት ናቸው። አምስት መቶም ይሁን ሃምሳ ብቻ ያልተበደረ እና ምሕረት ያልተደረገለት ጻድቅ አይገኝም።(ሉቃ 7)
ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚነገረው "ከአንዲት ድንግል" በቀር ነው። ይህችም ድንግል ከተፈጠረች ጀምሮ በምንም ምን አልረከሰችም። እንኳን በሥራዋ በሐሳቧም ኃጢአትን የማታውቅ ኅትምት በመሆኗ፣ ከርኩሰት የሚያነጻና ከበደል የሚመልስ ንስሐ አላስፈለጋትም። እርሷ ከእናቷ ማኅጸን ጀምሮ ከበረዶ ይልቅ ነጭ ነበረች። በእድገቷም ጊዜ የዚህ ዓለም ክፋት አንዳች አላገኛትም። እርሷ የኃጢአት ጉድፍ ያልወደቀባት ንጹሕ ምንጭ ናች። በመርዙ ብዙዎችን ወግቶ የጣለ አዳኙ(ይጠብቃል) አውሬ ያልተነፈሰባት በመንፈስ ቅዱስ የታጠረች የገነት ተክል ነች። ይህች ድንግል በኃጢአት ተፍገምግመው ለወደቁ የሚነሡበትን የንስሐ ምርኩዝ ለሰጠ የይቅርታ አምላክ እናቱ ነች።
ጻድቃን ሁሉ ከተፈጠሩበት ልዕልና ዝቅ ካሉ በኋላ በንስሐ መሰላልነት ወደ ክብር ሲመለሱ፣ ድንግል ግን ከዚያ ልዕልና ለአንዲት ሰዓት እንኳን ሳትናወጽ በጽናት ኖረች። ስለዚህም የእርሷ ንጽሕና ያለ ንስሐ ሆነ!!!
"እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ" የሚለውን አምላካዊ ትእዛዝ እንደ እመቤታችን ፈጽሞ የተገኘ ማን ነው?!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚነገረው "ከአንዲት ድንግል" በቀር ነው። ይህችም ድንግል ከተፈጠረች ጀምሮ በምንም ምን አልረከሰችም። እንኳን በሥራዋ በሐሳቧም ኃጢአትን የማታውቅ ኅትምት በመሆኗ፣ ከርኩሰት የሚያነጻና ከበደል የሚመልስ ንስሐ አላስፈለጋትም። እርሷ ከእናቷ ማኅጸን ጀምሮ ከበረዶ ይልቅ ነጭ ነበረች። በእድገቷም ጊዜ የዚህ ዓለም ክፋት አንዳች አላገኛትም። እርሷ የኃጢአት ጉድፍ ያልወደቀባት ንጹሕ ምንጭ ናች። በመርዙ ብዙዎችን ወግቶ የጣለ አዳኙ(ይጠብቃል) አውሬ ያልተነፈሰባት በመንፈስ ቅዱስ የታጠረች የገነት ተክል ነች። ይህች ድንግል በኃጢአት ተፍገምግመው ለወደቁ የሚነሡበትን የንስሐ ምርኩዝ ለሰጠ የይቅርታ አምላክ እናቱ ነች።
ጻድቃን ሁሉ ከተፈጠሩበት ልዕልና ዝቅ ካሉ በኋላ በንስሐ መሰላልነት ወደ ክብር ሲመለሱ፣ ድንግል ግን ከዚያ ልዕልና ለአንዲት ሰዓት እንኳን ሳትናወጽ በጽናት ኖረች። ስለዚህም የእርሷ ንጽሕና ያለ ንስሐ ሆነ!!!
"እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ" የሚለውን አምላካዊ ትእዛዝ እንደ እመቤታችን ፈጽሞ የተገኘ ማን ነው?!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++
ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ።
ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከ15 ቀናት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ።
አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ።
የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!!
(*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ም.
ዝዋይ (ብፁዕነታቸው ብዙ ሥራ በሠሩበት ክፍለ አገር ሆኜ)

+++ "እኔ" ብቻ +++
ዕውቁ ሩስያዊው የልብ ወለድ ደራሲ ዶስቶየቩስኪ "Brothers Karamazov" በተሰኘው ድርሰቱ ስለ አንዲት ምናባዊት ንፉግ ሴት ታሪክ እንዲህ ይተርካል። በአንድ ዘመን በግብርና ሥራ እየተዳደረች የምትኖር ክፉ ሴት ነበረች። ታዲያ በሕይወት እያለች አንድ በጎ ነገር እንኳ ሳትሠራ ይህን ዓለም በሞት ተሰናበተች። ነፍሷም በወጣች ጊዜ ወዲያው አጋንንት እየተናጠቁ ይዘዋት ሄደው ወደ እሳት ባሕር ወረወሯት። ጠባቂ መልአኳም ይህን ባየ ጊዜ ከፈጣሪ ፊት ቆሞ የሚያዘክርላት ጥቂት በጎ ሥራ ሠርታ እንደ ሆነ ለማስታወስ ሞከረ። ወዲያውም "አንድ ጊዜ ከማሳዋ ላይ አንድ ራስ ሽንኩርት ነቅላ ለአንዲት ነዳይ መስጠቷን" ለአምላኩ አሳሰበላት። እግዚአብሔርም "በል ያን ሽኝኩርት ውሰድና ወደ እርሷ ሂድ። እርሱን ይዛ መውጣት ከቻለች ወደ ገነት ታስገባታለህ። ካልሆነ ግን እዚያው ሲኦል ትቀራለች" አለው።
መልአኩም እንደ ተባለው ሴቲቱ የሽንኩርቱን ራስ እንድትይዝ አድርጎ በጥንቃቄ ወደ ውጭ ይስባት ጀመር። ነገር ግን ሌሎች በዚያ የእሳት ባሕር ውስጥ የነበሩ ኃጥአን ስትወጣ ሲመለከቱ አብረዋት ለመውጣት እርሷ ላይ ተንጠላጠሉ። ያቺ ጨካኝ ሴት ግን ክፉኛ በመወራጨት ከላይዋ ላይ እያራገፈቻቸው "እኔ ነው እየሳበኝ ያለው እናንተን አይደለም። ይህ ሽንኩርት የእኔ ነው። የእናንተ አይደለም።" አለች። ይህን እየተናገረች ሳለም የያዘችው የሽንኩርቱ ጫፍ ተበጥሶ ወደ እሳቱ ተመልሳ ገባች። መልአኩም በሁኔታው እያዘነ ከእርሷ ተለይቶ ሄደ።
ያን የሽንኩርት ጫፍ የበጠሰው ምን ይመስላችኋል? እርሷ ላይ የተንጠለጠሉት ነፍሳት ወይስ የእርሷ ጭካኔ እና ንፋግነት?
ይህ የዶስቶቩስኪ ምናባዊ ትርክት በዚህ ዘመን ያለነውን የእያንዳንዳችንን ማንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ይመስለኛል። ከመጠን በላይ ለራስ በመጨነቅና የራስን ምቾት ብቻ መፈለግ የእኛ ጊዜ መለያ ጠባይ ሆኗል። በንግግራችን ውስጥ "እኔ" "ለእኔ" "የእኔ" የሚሉት ቃላት እየረቡ "እኛ" የሚለው ቃል እየሳሳ መጥቷል። በብዙዎች የሚመለክ በየቤቱ የቆመ የዘመኑ አዲስ ጣዖት ቢኖር "እኔ"ነት (ራስ) ነው።
ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የትኩረት ማዕከል ለመሆን የማይቆፍሩት ጉድጓድ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በተገኙበት ሁሉ ስለ እነርሱ እንዲወራ ይፈልጋሉ። ለቀብር እንኳን ሄደው ለሞተው ሰው ከሚሰጠው ትኩረት አንጻር በዚያች ቅጽበት ያን አስከሬን ቢሆኑ አይጠሉም። ስማቸውን በየሰው አፍ ለማስገባትና መነጋገሪያ ለመሆን የትኛውንም ዓይነት ዋጋ ይከፍላሉ። ይህን ጊዜ "ራስን መውደድ" በሽታ ይሆናል። በራስ ዓለም ውስጥ እንደ መጥፋት፣ ራስን በራስ እንደመዋጥ ያለ ሊታከም የሚገባው ጽኑ ደዌ!
ሁልጊዜ በስግብግብነት እና ለእኔ ብቻ በማለት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች መንፈሳቸው የተሰበረ ይሆናል። የገዙት አያስደስታቸውም፣ የሰበሰቡት አያረካቸውም። በሕይወታቸው ውስጥ ያስወጡት መልካም ነገር ስላለ መቼም የውስጥ ዕረፍት አያገኙም። ያ ከሕይወታቸው ያስወጡት መልካም ነገር ምንድር ነው? "ብቻ ያለ መሆን" መልካምነት ነዋ!
"ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም" ዘፍ 2፥18
በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ግለኝነትና "ለእኔ ብቻ" ማለት ፈጽሞ የተወገዘ ነው። ምድር ላይ ባለችው ቤተ ክርስቲያን በኅብረት መንፈስ ካልኖርህ "በሰማያት ወደ ተጻፉት የበኩራት ማኅበር" ልትገባ አትችልም።(ዕብ 12፥23) በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ ቆመው የሚያመሰግኑት ሱራፌል ክንፎቻቸው እርስ በርስ የተያያዘ ነው። ይህንንም አንድ ሊቅ ሲተረጉም በአምላክ ዙፋን ፊት ለመቆምና ከእነዚህ አመስጋኝ መላእክት ጋር አብሮ ለመቆጠር ሰዎች በአንዲት ኅብረት ሊኖሩ እንደሚገባቸው ያሳያል ሲል ተርጉሞታል። ክርስትና ራስን ማዕከል የማድረግ ሳይሆን ሌሎችን የማገልገልና ስለ ብዙዎችም በፍቅር መሥዋዕት የመሆን ሕይወት ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
ጥቅምት 10/ 2015 ዓ.ም.

+++ ከፊልጶስ ቂሣሪያ እስከ ታቦር ተራራ +++
ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ የደብረ ታቦርን መገለጥ በጻፈበት በአሥራ ሰባተኛው ምዕራፍ ላይ ሲጀምር ‹ከስድስት ቀንም በኋላ› በማለት ሲሆን፣ የቅዱስ ማርቆስም ቀን አቆጣጠሩ ከማቴዎስ ጋር ተመሳሳይ ስድስት ቀን ነው፡፡(ማቴ 17፡1 ፣ማር 9፡2) ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ጌታና ሐዋርያቱ ታላቁን የታቦር ተራራ ሲወጡ የወሰደባቸውን ሁለት ቀን ጨምሮ ይህንኑ ተመሳሳይ ታሪክ ሲመዘግብ ‹ስምንት ቀን ያህል ቆይቶ› በማለት ይጀምራል፡፡ በእነዚህ በሦስቱ ወንጌላት ላይ የተቀመጡት የቀናት ቁጥር ከደብረ ታቦር ጋር ተያይዘው ሊታወሱ የሚገባቸው መነሻ ሐሳቦች እንዳሉና ሐዋርያት በታቦር ተራራ ከቀናት በፊት የነበረባቸው ጥያቄ እንደ ተመለሰላቸው አመላካች ናቸው፡፡ እኒህ የደብረ ታቦር ቅድመ ታሪኮች ምን ምን ናቸው?
☝.አንደኛ
በደብረ ታቦር ከተፈጸመው ታሪክ ጋር ተያያዥነት ያለውን ጉዳይ ለማወቅ ከእርሱ በፊት አምላካችን የሄሮድስ ወንድም የፊልጶስ ግዛት በሆነችውና ለንጉሥ ጢባርዮስ ቄሣር ለክብሩ መታሰቢያ በስሙ ቂሣርያ ተብላ በተሰየመችው ቦታ ከሐዋርያቱ ጋር ያደረገውን ንግግር ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡(ማቴ 16:13)
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን አምላክነቱን የሚያረጋግጥ ምልክትን ከሰማይ እንዲያሳያቸው ለምነውት ነበር፡፡ እርሱ ግን የልባቸውን ክፋትና አመዝረኛነት ነቅፎ ምልክት ሆኖ ከተሰጠውና የእርሱ ምሳሌ ከሆነው ከዮናስ በዓሣ አንበሬ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ማደር በቀር አንዳች ምልክትን ከለከላቸው፡፡ ሐዋርያቱም እንዲህ ካለው ተአምርን ከመከተል ፈሪሳዊ፣ ሰዱቃዊ ትምህርት ራሳቸውን ይጠብቁ ዘንድ ‹ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ› ብሎ አስተማራቸው፡፡(ማቴ 16፡6) ቀጥሎም ወደ ፊሊጶስ ቂሣርያ አገር በደረሱ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ ጌታ ለምን ሐዋርያቱ በፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን መካከል እያሉ አልጠየቃቸውም? ቢባል ጥያቄው የክርስቶስን ማንነት የሚመለከት በመሆኑ እውነተኛውን መልስ በግልጽ ቢናገሩ የሚደርስባቸውን ውግራት በማሰብ ገና ያልጸኑት ሐዋርያት በነጻነት አይመሰክሩምና ከዚህ ሥጋት ነጻ ሊያደርጋቸው ወደ ፊሊጶስ ቂሣርያ ይዟቸው ዞር አለ፡፡
ስለ እርሱም ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ጥያቄን ሊጠይቃቸው በወደደ ጊዜ ‹አምላክ ስለሆንኩት፣ ጌታ ስለሆንኩት ስለ እኔ› የሚሉ ኃይልና ሥልጣንን የሚገልጹ ቃላቶችን በማስቀደም አልጠየቃቸውም። ራሱን ዝቅ በማድረግና በማያስደነግጥ ቃል ‹ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?› ሲል በትሕትና ጠየቃቸው እንጂ፡፡ ኃይሉንና ጌትነቱን በሚገልጽ ቃል ቢጠይቃቸው ኖሮ ‹እንደ ነቢይ ፣እንደ አንድ ጻድቅ ሰው ይመለከቱሃል› የሚለውን በሕዝቡ ዘንድ ያለውን አመለካከት ለመንገር ሐዋርያቱ በተሰቀቁ ነበር፡፡
ይህ ለተማሪዎቹ ሐዋርያት የቀረበው "ሰዎች ስለ እኔ ምን ይላሉ?" የሚለው የአምላካችን ጥያቄ ዛሬ ለእኛም ቢሆን ሁለት ቁም ነገሮችን ያስተላልፍልናል፡፡ የመጀመሪያው ብዙዎች በውጪ ስለሚያደርጉት አጉል ምግባር ‹ተዉ ሰዎች ይሰናከሉባችኋል!› የሚል አስተያየት ሲሰጣቸው፣ "እኔ ሰለ ሰዎች ምን ቸገረኝ፣ ‹ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን›" ብለው ለሚከራከሩ፣ አይደለም በኃጢአት ባሕር የምንዋኝ እኛ ቀርቶ በውስጥም በውጪም ነውር የሌለበት አምላክ እንኳን የሰዎችን አስተያየት ጠይቋል። ስለዚህ ስለ ሰዎች ስሜት መጨነቅና ኃላፊነት መሰማትን ከእርሱ እንማራለን፡፡ ሁለተኛው ቁም ነገር ደግሞ ስለ ራሱ በሰዎች ዘንድ የሚሰጠውን ትክክለኛ አስተያየት መስማት የሚፈልግ ሰው ጥያቄውን ቀላልና ሥልጣንን በማይገልጽ መንገድ እንዴት ለአስተያየት የማይቆረቁር አድርጎ ማቅረብ እንዳለበት ይህ ታሪክ ትምህርት ይሰጣል፡፡
ከጌታችን ጥያቄ የቀረበላቸው ሐዋርያቱም በሕዝቡ ዘንድ ሲነገር የሰሙትን አስተያየት ተራ በተራ ወደ እርሱ ሰነዘሩ፡፡ እነርሱም:- የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት አታገባም እያለ ይወቅሰው የነበረን መጥምቁ ዮሐንስን ንጉሥ ሄሮድስ ይፈራው ነበረና፣ ከሞተ በኋላ እንኳን የመጥምቁ ዮሐንስ ጌታ ስለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማ ጊዜ ዮሐንስ ከሞት የተነሣ እየመሰለው ይታወክ ነበር፡፡ ስለዚህም ሄሮድስና በእርሱ ወገን ያሉት አንዳንዶች "መጥምቁ ዮሐንስ ነህ ይሉሃል" አሉት፡፡ በሮማውያን ግዞት የነበሩም አይሁድ በኃይል እሳት አዝንሞ፣ ሰማይ ለጉሞ ጠላቶቻችንን በማስጨነቅ ነጻ ያወጣናል ብለው በማሰብ "ኤልያስ ነህ" የሚሉም አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ንጽሕናህን የተመለከቱ ከእናቱ ሆድ ጀምሮ በእግዚአብሔር የተመረጠ "ኤርምያስ ይሆንን" ይላሉ፡፡ የቀሩትም ደግሞ ‹ከነቢያት አንዱ (ሙሴ) ነህ› ይላሉ በማለት ነገሩት፡፡
በመቀጠልም መድኃኒታችን እነርሱ ማን እንደሚሉት ‹እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንኹ ትላላችሁ?› በማለት ጠየቃቸው፡፡ ከሐዋርያት መካከል ፈጣን የነበረው አረጋዊው ስምዖን ጴጥሮስም ‹አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ› ሲል መለሰ፡፡ ጌታችንም መልሶ ‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ› በማለት አመሰገነው፡፡
ይህ የቅዱስ ጴጥሮስ ምስክርነት በእውነትም በሥጋ በደም ዕውቀት የተነገረ አይደለም፡፡ ፀሐይን ትኩር ብለን መመልከት ቢሳነን እንኳን የምንችለውን ያህልም ቢሆን የምናያት ራሷ በምትለግሰን ብርሃን እንደሆነ ሁሉ፣ እግዚአብሔርንም በምልዐት ማወቅ ባይቻለንም ስለ እርሱ የምናውቃት ጥቂት ነገርንም ያገኘነው እርሱ ራሱ ወዶ ባደረገልን "የራስ መገለጥ" (Self Revelation) ብቻ ነው፡፡ ራሱ ቅዱስ ጴጥሮስም "ይህን እንዴት ዐወቅህ?" ተብሎ ቢጠየቅ ‹እግዚአብሔር አብና መንፈሱ ገልጦ ካሳወቀኝ በቀር ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርኩም ነበር› ብሎ የሚመልስ ይመስላል፡፡(ገላ 1፡16) በእርግጥም ስለ ወልድ ለማወቅ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በላይ መምህር ከየት ሊገኝ ይችላል?
ታስታውሱ እንደሆነ በዮሐንስ ወንጌል ናትናኤል የተባለ ሰው ጌታን ‹ከወዴት ታውቀኛለህ?› ብሎ በጠየቀው ጊዜ፣ ‹ፊሊጶስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ› ብሎ የቀድሞ ድብቅ ታሪኩን ነግሮት ነበር፡፡ በዚህም የተደነቀው ናትናኤል ‹መምህር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ› ሲል መስክሮለታል፡፡(ዮሐ 1፡50) በናትናኤልና በቅዱስ ጴጥሮስ ምስክርነት መካከል ምን ልዩነት አለው? ሁለቱም እኮ ‹የእግዚአብሔር ልጅ ነህ› ብለው ነው የመሰከሩት፡፡ ታዲያ ለምን ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተመሰገነው ናትናኤልም አልተመሰገነም? ከተባለ ምንም የሁለቱም ምስክርነት በቃል ደረጃ ይመሳሰል እንጂ ውስጣቸው የነበረው ትርጉም ግን ይለያይ ነበር፡፡ ናትናኤል ‹የእግዚአብሔር ልጅ› ሲለው በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች ከተባሉት ነቢያትና የብሉይ ኪዳን ጻድቃን ጋር በማመሳሰል ሲሆን፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ‹የእግዚአብሔር ልጅ› ያለው ቀዳሚና ተከታይ የሌለው የአብ አንድያ የባሕርይ ልጅ መሆኑን በመረዳት ነው፡፡ ስለዚህ የሚበልጠው አምላክነቱን ያየ ቅዱስ ጴጥሮስ ሲመሰገን፣ እምነቱ ገና ሙሉ ያልሆነው ናትናኤል ግን ‹የሚበልጠውን ታያለህ› ተብሎ ተስፋ ተሰጠው፡፡ አያችሁ! እግዚአብሔር የቃል መመሳሰልን ሳይሆን በልባችን ውስጥ ያለውንም የቃሉን ትርጉም አይቶ ነው የሚለየን!፡፡

ይህም የቅዱስ ጴጥሮስ የእምነት ምስክርነት ዓለት ሲሆን በዚህችም ዓለት (እምነት) ላይ ቤተ ክርስቲያን የተባሉ ምእመናን በጥምቀት እንደሚታነጹ ጌታችን ተናግሯል፡፡ በርግጥም ኢየሱስ ክርስቶስን ‹እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም› ብሎ የተናገረው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ የማያምን ሁሉ ከተመሰገነች ከቅዱስ ጴጥሮስ እምነት የወጣ ነው፡፡
አረጋዊው ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን የማወቅ ጥበብ ከባሕርይ አባቱ ከአብና ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ እንዳገኘ፣ እንዲሁ የማሰርና የመፍታት ሥልጣንን ከጌታችን ተቀበለ፡፡በዚህም ሰው የሆነ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ብቻ ገንዘብ የሆነውንና ማንም የማይፈታውን የኃጢአትን ማሰሪያ ይፈታና ያስር ዘንድ ሥልጣንን ለሐዋርያው ሰጥቶ "የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር" መሆኑን በመግለጥ እምነቱን አጸናለት፡፡
‹ሰዎች_የሰውን_ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?› በሚለው ንግግር ውስጥ የወልድን ፍጹም ሰው መሆን ስንረዳ፣ ‹አንተ ክርስቶስ የሕያው_እግዚአብሔር_ልጅ ነህ› በሚለው የቅዱስ ጴጥሮስ መልስ ደግሞ አምላክነቱን እናያለን፡፡ ታዲያ ምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርት ባጭሩ ይህ አይደለምን?! የሂፖው ሊቀ ጳጳስ አውግስጢኖስ "የእምነት ሽልማቱ ያመኑትን ነገር ማየት ነው" እንዲል ይህ ቅዱስ ጴጥሮስ አምኖ የመሰከረውን አምላክነት በዓይኑ ደግሞ የሚያየው በታቦር ተራራ ነበር፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++++
✌.ሁለተኛ
ጌታችን በፊሊጶስ ቂሣርያ ይህን ጥያቄ ከጠየቀበት ቀን ጀምሮ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይሞት ዘንድ እንዳለው፣ በሦስተኛውም ቀን እንደሚነሣ ለሐዋርያቱ ያስተምራቸው ነበር፡፡ እሞታለሁ ማለቱም ያሳሰበው ቅዱስ ጴጥሮስ አምላኩን ወደ እርሱ አቅርቦ ‹አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም› ሲል በመራራት ቃል ሊገስጽ ጀመረ፡፡ ጌታ ግን የቅዱስ ጴጥሮስን ፍቅሩን ተጠቅሞ ዓለም የሚድንበትን ሞቱን የሚቃወመውን ርኩስ መንፈስ በሚጠቁም ኃይለ ቃል ‹ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና እንቅፋት ሆነህብኛል› በማለት በረቂቅ ያናገረውን የጠላት መንፈስ አራቀለት፡፡ ይሁን እንጂ ‹አይሁንብህ!› የሚለው የቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር ግን በዚህ የአምላካችን ተግሳጽ ብቻ የሚያቆም ባለመሆኑ ይህን ጥፋቱን ለማረም ከፊቱ የታቦር ተራራ ትምህርት ቤቱ ፣ እግዚአብሔር አብም መምህሩ ሆነው ይጠብቁት ነበር፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++++
👌.ሦስተኛ
በዚያው ሰሞን ጌታችን ከሐዋርያት መካከል እርሱ ዳግመኛ ለፍርድ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ እንዳሉ (ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ አልሞተም) ቢያስተምራቸውም፣ በሐዋርያቱ ኅሊና ግን ‹ሞትን ሳይቀምሱ ለዘመናት መሰንበት እንዴት ይቻላል?› የሚል ጥያቄ ተፈጥሮ ነበር። ስለዚህም ይህን ጥያቄ በጠየቁ በስድስተኛው ቀን ሞትን ያልቀመሰ ኤልያስን በማየት መልሱን ያገኙ ዘንድ ወደ ታቦር ተራራ ይዟቸው ወጣ፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++
ስለ ደብረ ታቦር ታሪክ ከአራቱ ወንጌላት መካከል በሉቃስ፣ በማቴዎስና በማርቆስ ወንጌል ተጽፎ የምናገኘው ሲሆን፣ በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ግን በፊሊጶስ ቂሣርያ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ መሰከረና በጌታው እንደተመሰገነ ብቻ ነው የተጻፈው፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የታቦር ተራራ ላይ የተፈጸመውን ታሪክ ሳይመዘግብ አልፎታል። ይህም ያለ ምክንያት የሆነ እንዳይመስለን። በዚህ የወንጌላውያኑ ተግባር ውስጥ የምንፈናየው የትሕትና ትምህርት አለ፡፡ ይኸውም በደብረ ታቦር ተራራ ከጌታችን ጋር ለመውጣት የተመረጡት ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ እና ያዕቆብ ቢሆኑም እነዚህ ሦስቱ በተራራው ላይ ያልነበሩ የወንጌል ጸሐፊዎች ግን እኛ ያልተጠራንበትን፣ እኛ ያልተመረጥንበትንማ እንዴት እንጽፈዋለን በማለት በምቀኝነት መንፈስ የሐዋርያቱን ክብር አልሸፈኑም፡፡ ደግሞ ወደ ተራራው ከወጡ ከሦስቱ ሐዋርያት አንዱ የነበረውም ቅዱስ ዮሐንስ፣ ከነበረው የትሕትና ሕይወት የተነሣ ‹እኔ ነበርኩ› ብሎ መጻፍን እንደሚገባ ነገር ስላልቆጠረው የወንድሙ የቅዱስ ጴጥሮስን ምስክርነትና ስለ እምነቱ መመስገን ሲጽፍ፣ እርሱ የተመረጠበትን የደብረ ታቦርን ታሪክ ግን ሳይጽፍ ቀርቷል፡፡ በአገልጋዮች ሐዋርያት መካከል ያለውን የትሕትና እና የገርነት መንፈስ ተመለከታችሁ?!
ጌታችን ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል ‹አዕማድ መስለው የሚታዩ›ና ለፍቅሩ የሚናደዱ ሦስቱን የምሥጢር ሐዋርያት ጴጥሮስ ፣ያዕቆብና ዮሐንስን መረጣቸው፡፡(ገላ 2፡9) የቀሩት ስምንቱን ግን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቷቸው ወጣ፡፡ ይህንንም ማድረጉ ‹የአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዓይ ስብሐተ እግዚአብሔር›/‹ኃጢአተኛን የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ያርቁታል› እንዲል፣ ከመካከላቸው የእግዚአብሔርን ክብር ሊያይ የማይገባው ኃጢአተኛው ይሁዳ ስለ ነበር ነው፡፡ ነገር ግን ሃብተ ትርጓሜን እንደ ሸማ የተጎናጸፉት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እንደሚነግሩን ከይሁዳ በቀር ለቀሩት ሐዋርያት ወደ ተራራ መውጣት እንጂ በተራራው ጫፍ ለነበሩት ሦስቱ ሐዋርያት የተገለጠላቸው ምሥጢር አልጎደለባቸውም፡፡
ወደ ረጅሙ ተራራ ወደ ታቦር ጌታ ሦስቱን ሐዋርያት ይዟቸው ከወጣ በኋላ እያዩት በፊታቸው ተለወጠ። ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡ አበቦች ከቅርንጮፎቻቸው ላይ ተሸፍነው (ተጠቅለው) ኖረው ኖረው በኋላ እንዲገለጡ፣ አምላካችንም ቀድሞ በእርሱ ዘንድ ሰውሮት የነበረውን ክብር ገለጠላቸው፡፡ ሐዋርያቱም ያዩት ክብር ከዚያ በፊት ያልነበረው አሁን እንግዳ ሆኖ የመጣ ብርሃን አልነበረም፡፡ ይህንንም ክብሩን ሲገልጥላቸው ሐዋርያት ሊያዩትና ሊረዱት በሚችሉት መጠን እንደ ነበረ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ‹በፊታቸው ተለወጠ› በምትል አጭር ገላጭ ቃል ያስረዳናል፡፡ ለቅዱሳን ብርሃን የሚሆን ‹የጽድቅ ፀሐይ› አምላካችን ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፡፡(ሚል 4፡2) ኸረ እንደውም የፊቱስ ብርሃን ከፀሐይም ይበልጥ ነበር፡፡ ምክንያቱም እኛ ጠዋት ጠዋት ከቤታችን ስንወጣ የፀሐይን ብርሃን ባየን ቁጥር በግንባራችን አንደፋም፤ ሐዋርያት ግን ከፀሐይ ሰባት እጥፍ የሚያበራ የክርስቶስን ፊት ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ተደፍተዋል፡፡
የለበሰውም ልብስ አጣቢ በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ፡፡ ይህ የአምላካችን አንጸባራቂው ልብስ ምሳሌና ምሥጢሩ ምን ይሆን? ሊቁ ጎርጎርዮስ ዘየዐቢ ከበረዶ ይልቅ የነጣውን የክርስቶስን ልብስ በምዕመናን መስሎ ያስተምራል፡፡ ኢትዮጽያውያን ሊቃውንትስ ቢሆኑ ‹አልባሲሁሰ ለክርስቶስ መሃይምናን ውእቱ›/‹የክርስቶስ ልብሶቹ ምዕመናን ናቸው› ሲሉ በትርጉም ከእርሱ ጋር ይተባበራሉ አይደል እንዴ!፡፡ የልብሱም ነጭ መሆን የቅድስና ምልክት ሲሆን፣ በኃጢአት ይህን ነጭነቱን ላቆሸሸ በደለኛ ደግሞ ተነሳሒው ቅዱስ ዳዊት እንዲህ የሚል ጸሎትን ደርሶ ሰጥቶታል :- ‹በሂሶጵ እርጨኝ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ›፡፡(መዝ 51፡7) ነጩን የክርስቶስን ልብስ በኃጢአት ጭቃ ከማቆሸሽ፣ አቆሽሾም ከመቅረት ፈጣሪያችን ይጠብቀን፡፡

ቅዱስ አምብሮስም ያንጸባረቀው የክርስቶስን ልብስ "የወንጌል ምሳሌ ነው" ብሎ ይተረጉመዋል፡፡ ልብስ ማንነትን እንዲያሳይ ክርስቶስም በተጎናጸፋት ወንጌል ማንነቱን ዐውቀናልና በደብረ ታቦር ላይ ብርሃን የፈነጠቀባት ልብሱ የወንጌል ምሳሌ ናት፡፡ ነቢዩ ዳዊትም በመዝሙሩ ‹ብርሃንን እንደ ልብስ ለበስህ› ሲል የተናገረላት ብርሃናዊ የሆነች የጌታ ልብሱ ወንጌል ናት፡፡(መዝ 104፡2)
ከዚህም በኋላ ሙሴና ኤልያስ ከክርስቶስ ጋር ሲነጋገሩ ሐዋርያቱ በታቦር ተራራ ሆነው ይመለከቱ ጀመር፡፡ ከመድኃኒታችን ጋር የነበሩት ሐዋርያት ከነቢያቱ ከሙሴ እና ከኤልያስ ጋር መሆን ቻሉ፡፡ ጌታን የሚቃወሙት አይሁድ ግን እናውቃቸዋለን ከሚሏቸው ከነቢያቱም ጋር መሆን አልቻሉም፡፡ ምክንያቱም የነቢያት የትንቢታቸው ማዕከል ከሆነው ከክርስቶስ ጋር ካልሆኑ በቀር ሙሴና ኤልያስን ማየት አይቻልምና ነው፡፡
ጌታ ስለምን ከብዙ የብሉይ ኪዳን ጻድቃን መካከል ሙሴና ኤልያስን መረጠ? ቢባል
✴ ሐዋርያቱ ከዚህ ቀደም ሰዎች ሙሴ ፣ ኤልያስ ነህ ይሉሃል ብለው ስለነበር፣ በጌታ እና በሎሌ መካከል ያለውን ልዩነት ያውቁ ዘንድ ‹የእኔን የሙሴን ጌታ ማን ሙሴ ይልሃል? የሙሴ ጌታ ይበሉህ እንጂ› እያሉ እንዲመሰክሩ ሙሴን ከብሔረ ሙታን ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቷቸዋል፡፡
✴ ሙሴ አምላኩን ከአምስት መቶ ሰባ ጊዜ በላይ ቃል በቃል ቢያናግረውም ፊቱን ግን አይቶ አለማወቁ ይቆጨው ነበር፡፡ከዕለታትም በአንዱ ቀን ‹ፊትህን አሳየኝ?› ብሎ በለመነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ‹ፊቴን አይቶ የሚድን የለምና ጀርባዬን ታያለህ› ብሎ ቃል ገባለት፡፡ ጀርባዬን ታያለህ ሲል ልጅ በጀርባ እንዲታዘል በኋላ ዘመን ሰው ሆኖ የሚመጣ ‹የባሕርይ ልጄን› ታያለህ ማለቱ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ከሞት በፊት ለሙሴ የተገባ ቃል ኪዳን የተፈጸመው ከሞት በኋላ በዚህች ዕለት ነው፡፡ ኤልያስንም ‹አንተስ በኋላ ዘመን ምስክር ትሆነኛለህ› ብሎት ነበርና ኤልያስም ቀነ ቀጠሮውን ጠብቆ በታቦር ተራራ ተገኘ፡፡
✴ አይሁድ ክርስቶስን ሕግ አፍራሽ አድርገው ይከሱት ነበር፡፡ ለእግዚአብሔርም ክብር የቀኑ እየመሰላቸው ‹ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሏል› ብለው በመወንጀል ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፡፡ ስለዚህም ሕግን ከእግዚአብሔር የተቀበለ ሙሴንና ለእግዚአብሔር ክብር የሚቀና ኤልያስን ምስክር አድርጎ የአይሁድን ሐሰት ለሐዋርያቱ ገለጸላቸው፡፡
✴ በሞት እና በሕይወት ላይ ሥልጣን ያለው አምላክ መሆኑን ሲያሳይ ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከሕያዋን ሀገር እንዲመጡ አደረገ፡፡
(ከዚህም የሚበዛ ትርጓሜ ስላለው የቀረውን በትርጓሜ ወንጌል መጽሐፍ ይመልከቱ)
የሙሴና የኤልያስን ንግግር የተመለከተው ቅዱስ ጴጥሮስም ጌታችንን ‹በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው ፤ ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ› አለ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በባለቤቱ በእግዚአብሔርና በመረጣቸው ቅዱሳን መታሰቢያ ቤተ ክርስቲያን በማነጽ የሚያገለግሉ ሰዎችን ይመስላል፡፡ አንድም የእግዚአብሔርን ክብር ካዩ በኋላ ‹በዚህ መኖር ለእኔ መልካም ነው› ብለው ሀብት ንብረታቸውን፣ ርስት ጉልታቸውን ጥለው ለሚመንኑ መናንያን ምሳሌ ሆኖ ይታያል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ግን ስለ ጴጥሮስ ንግግር ከዚህ የተለየ ነገርን ያሳየናል፡፡ ይኸውም አምላካችን አስቀድሞ ከዚህ ታሪክ መፈጸም በፊት ለሐዋርያቱ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድና በዚያም እንደሚሞት ነግሯቸው ቅዱስ ጴጥሮስ ተቃውሞት ነበር፡፡ ጌታም ዓለም የሚድንበት ሞቱን ስለተቃወመ የገሰጸው ቢሆንም፣ እርሱ ግን ከልቡ አልተቀበለውም፡፡ ስለዚህ አሁንም ከደብረ ታቦር ከወረዱ በኋላ እንደ ተናገረው ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱ እና መሞቱ እንደማይቀር ስላሰበ ዳግመኛ ሞቱን ሲከላከል ‹በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው› ወይም እንደ ቅዱሱ አገላለጽ ‹ከዚህ ተራራ አንውረድ። ከወረድን ትሞታለህና፤ ጌታ ሆይ ለራስህ ምሕረትን አድርግ› ሲል እንደ ተናገረ ያመለክተናል፡፡ ስለዚህ "አትሙት" ብሎ የሚከራከረው ቅዱስ ጴጥሮስ ቀድሞ በሚያየው አምላክ ወልድ እንደ ተገሠጸ፣ አሁን ደግሞ በማያየው አምላክ እግዚአብሔር አብ ‹እርሱን ስሙት› የሚል ወቀሳ ደረሰበት፡፡
አንድም ቅዱስ ጴጥሮስ ተምረው፣ ምሥጢር አይተው፣ በአገልግሎት ምክንያት የሚመጣባቸውን ረብሻና ሁካታ ፍርሃት በሰማነው ጸንተን እንኑር እንጂ ምስክርነቱ (አገልግሎቱ) ይቅርብን የሚሉ ሰዎችን ይመስላል፡፡ እግዚአብሔር አብ ግን ከሰማይ ለቅዱስ ጴጥሮስ የሰጠው ምላሽ ‹የምወደው ልጄ እርሱ ነውና እርሱን ስሙት› የሚል ነበር፡፡ጌታችንን ቢሰሙት ምን የሚል ይመስላችኋል? ‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ› ነዋ!
ይቆየን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ነሐሴ 12 2008 ዓ.ም.
(በድጋሚ የተለጠፈ)

+++ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" +++
ጌታችን ከሐዋርያቱ መካከል "አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንም" ወደ ቅዱሱ የታቦር ተራራ ብቻቸውን ይዟቸው ወጣ።(ገላ 2፥9) ከተራራውም ጫፍ ሲደርሱ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የመምህራቸው ፊት እንደ ፀሐይ ሲያበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሲሆን ተመለከቱ። እነሆም ከቀደሙት ጻድቃን ታላላቆቹ ሙሴና ኤልያስ በታቦር ተገኝተው ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።
እነዚህ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የትንቢታቸው ፍጻሜ ከሆነው ክርስቶስ ጋር ምን ተነጋገሩ? መቼም በጊዜው ከጌታ ጋር ውለው ያድሩ እንደ ነበሩት ተማሪዎቹ ሐዋርያት "አትሙትብን" አይሉትም። በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሱባኤ የያዙለትና ደጅ የጠኑት የድኅነት ተስፋ እናዳይፈጸም "ይቅር አትሙት" እንዴት ይላሉ? ስለዚህ ከብሔረ ሕያዋን የመጣው ኤልያስና ከብሔረ ሙታን የመጣው ሙሴ በአንድ ላይ "በኢየሩሳሌም ሊፈጸም ስላለው ስለ መውጣቱ (ስለ መከራው፣ ሞቱ)" ያነጋግሩት ነበር።(ሉቃ 9፥31)
በታቦር ተራራ ላይ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መልእክተኞች ተገናኙ። በባሕር ላይ በእግሩ የተራመደው ጴጥሮስ፣ የኤርትራን ባሕር እጁን ዘርግቶ የከፈለው ሙሴን አየው።(ማቴ 14፥29፣ ዘጸአ 14፥21) የሰማርያ ሰዎች በተቃወሙ ጊዜ "እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው" ያሉ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ከሰማይ እሳት አዝንሞ ሃምሳ አንዱን ወታደሮች ያስበላ ኤልያስን ተመለከቱት።(ሉቃ 9፥54፣ 2ኛ ነገ 1፥10)
ሁለቱ ምስክሮች እንደ ተሰወሩም ወዲያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ ሦስት ዳሶች እንሥራ ብሎ ጌታውን ጠየቀ። ሐዋርያው በዚህ ተራራ ላይ መቅረት የፈለገው ያለ ምክንያት አይደለም። መድኃኒታችን አስቀድሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ዘንድ ብዙ መከራ ይቀበልና ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲነግራቸው ቅዱስ ጴጥሮስ "አይሁንብህ፤ አይድረስብህ" ሲል ሊከላከለው ሞክሮ ነበር። ለዚህም በጊዜ "ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል" ተብሎ ተገስጾበታል።(ማር 9፥31-33) ይሁን እንጂ አሁንም ቅዱስ ጴጥሮስ ያለውን ሁሉ እድል ተጠቅሞ ጌታን ወደ ኢየሩሳሌም ከመሄድና በካህናት አለቆች እጅ ተላልፎ ከመሰጠት ማስቀረት ስለሚፈልግ "ጌታ ሆይ፦ በዚህ(በታቦር ተራራ) መሆን ለእኛ መልካም ነው" ብሎ ተናገረ።
እርሱም ይህን ገና ሲናገር ሳለ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው። ከደመናው "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ መጣ። ሐዋርያቱ ይህን ድምጽ የሰሙት ሙሴ እና ኤልያስ ከክርስቶስ ተለይተው ከሄዱ፣ እነርሱም ወድቀው ከነበሩበት ከተነሡ በኋላ ነው። ይህም ከደመናው ውስጥ ሲወጣ ስለ ሰሙት ቃል "ለማን የተነገረ ይሆን?" ብለው እንዳይጠይቁና ምስክርነቱ ለክርስቶስ ብቻ የተሰጠ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ እንዲረዱ ነው። በዚሁም ላይ ደመናው ወርዶ የጋረደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ሳይሆን ሐዋርያቱንም ጭምር ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ደመናው ጌታን ብቻ ጋርዶት ቢሆን ኖሮ፣ ሐዋርያቱ "እርሱን ስሙት" የሚለውን ቃል ራሱ ክርስቶስ ለራሱ የተናገረው ሊመስላቸው በቻለ ነበር።
ቅዱስ ጴጥሮስ "አትሙት" ያለው መምህሩን በፍጹም ልቡ ስለሚወደው መሆኑ አያጠራጥርም። ነገር ግን ጴጥሮስ ጌታን የቱንም ያህል ቢወደው፣ ፍቅሩ ግን ከወለደው ከባሕርይ አባቱ ከአብ አይደለም ሊበልጥ ሊነጻጸርም አይችልም። ታዲያ አብ በእርሱ ደስ የሚለው፣ የሚወደው፣ አንድያ ልጁ እንዲሞት ፈቃዱ ከሆነ፣ የአብን ያህል ሊወደው የማችለው አረጋዊው ጴጥሮስ ለምን "አትሙት" እያለ ይቃወማል?!
አብ ምትክ የሌለው ልጁ ወልድ ሰው ሆኖ በክፉዎች እጅ ሲንገላታ እና እስከ መስቀል ሞት ሲደርስ እያየ ዝም ያለው ስለማይወደው አይደለም። ዓለም ያለ ልጁ መከራና ሞት ስለማትድን ነው እንጂ። ከዚህ ምን እንማራለን? ዛሬም ወደ መከራ የምንገባ የጸጋ ልጆቹ የምንሆን እኛ ክርስቲያኖች "እግዚአብሔር እንዲህ ስሆን ዝም ያለኝ ስለማይወደኝ ነው" አንበል። ባገኘን ጥቂት የሥጋ መከራና ሕመም የሚበልጠውን የነፍስ ጤና የምንሸምት ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ይላል። ዝም የሚለው መከራችንን ስለማያይ ሳይሆን ከመከራው ጀርባ ያለው ዓላማ ታላቅና የተቀደሰ እንደ ሆነ ስለሚያውቅ ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ነሐሴ 13፣ 2014 ዓ.ም.
ደብረ ታቦር፣ እስራኤል

በክንፎቻቸው ተሸፋፍነው በፊቱ የሚቆሙለት ቅዱሳን መላእክት፣ ፈጣሪያቸው "እኔ በምድር ወዳጅ አለኝ። እርሱም አብርሃም ነው" ብሎ በነገራቸው ጊዜ እጅግ በመደነቅ ወደ አብርሃም ሄደው "አብርሃም አርከ እግዚአብሔር"/"አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ"/ እያሉ ዘምረውለት ነበር። በእውነት እግዚአብሔር "ወዳጅ አለኝ" ስላላቸው እንዲህ የተደነቁ መላእክት፣ "እኔ በምድር እናት አለኝ" ሲላቸው ምን ያህል ተገርመው ይሆን? እመቤታችንንስ በምን ዓይነት ቃል አመስግነዋት ይሆን?
በዛሬው እለት የአምላክን እናት ልዩ በሆነ ምስጋና እና እልልታ ያሳረጓት መላእክት፣ በምድር ሳለች "እይዋት የአምላክን እናት በምድር ትመላለሳለች" እያሉ በስስት የሚያይዋትና መምጣቷን የሚጠባበቁ እመቤታቸው ነበረች። ለዚህም ነው አባቶቻችን በሌሊት ማኅሌት "ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፣ ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ" እያሉ ሲወርቡ ያደሩት።
እኛም ንግሥታችንን ወደ ልጇ እልፍኝ ለሸኘንበት፣ መላእክትም እርሷን በደስታ ለተቀበሉባት ለበዓለ ዕርገቷ እንኳን በሰላም አደረሰን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ነሐሴ 16፣ 2014 ዓ.ም.
ኢየሩሳሌም፣ እስራኤል
ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
በዛሬው እለት የአምላክን እናት ልዩ በሆነ ምስጋና እና እልልታ ያሳረጓት መላእክት፣ በምድር ሳለች "እይዋት የአምላክን እናት በምድር ትመላለሳለች" እያሉ በስስት የሚያይዋትና መምጣቷን የሚጠባበቁ እመቤታቸው ነበረች። ለዚህም ነው አባቶቻችን በሌሊት ማኅሌት "ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፣ ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ" እያሉ ሲወርቡ ያደሩት።
እኛም ንግሥታችንን ወደ ልጇ እልፍኝ ለሸኘንበት፣ መላእክትም እርሷን በደስታ ለተቀበሉባት ለበዓለ ዕርገቷ እንኳን በሰላም አደረሰን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ነሐሴ 16፣ 2014 ዓ.ም.
ኢየሩሳሌም፣ እስራኤል
ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ይህን ጥዑም ፍሬ ከናፍር እንካችሁ ብለውናል።
እስኪ ከእነርሱ ጋር የጊዮርጊስ አምላክ ማረን፣ ራራልን፣ ተለመነን እያልን በመዝሙር እንማጸን!
https://youtu.be/873EtjlIOvs?si=4UfvgYo56rFLRU9g

YouTube
🔴 አዲስ ዝማሬ " የጊዮርጊስ አምላክ " የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት @-mahtot
🔴 በማኅቶት ቲዩብ የተለቀቁ ተወዳጅ መዝሙሮችን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡፡
👇 👇 👇
https://bit.ly/3C2YHGp
አዲስ ዝማሬ " የጊዮርጊስ አምላክ " የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት @-mahtot

ለንስሐ ጥሪ ቀጠሮ አንስጥ። መጠየቅን ወደሚወድ አምላክ የምንሄድበትን ጊዜ አናውቅምና ዘወትር ለመልካም ነገር የተነሣሣ ልቡና ይኑረን። "ንስሐ ግቡ፣ ቁረቡ" ስንባል "ወጣት አይደለሁ? ገና ምኑን አየኹትና? ቆይ ትንሽ!" እያልን መንፈሳዊነትን ከኃጢአት በተረፈ ጉልበት የሚሠራ የጡረታ ሥራ አናድርገው። የተመረጠውን የወጣትነት ዕድሜ ለበደል ሳይሆን ለጽድቅ እናውለው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]