ገብርኤል ሆይ፤ ከሰው ወገን ጠዋትና ማታ ከቶ እንደ እኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም፣
ከመላእክትም ወገን እንደ አንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም፣
ገብርኤል ሆይ፤ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ ያቀረብኩትን ይህን ጸሎት እንደ ትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የሚያረጋጋ ቃልህን አሰማኝ።
መልክአ ገብርኤል
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።

በንጽሕና ለመኖር እየታገለ የሚወድቅን እግዚአብሔር አያዝንበትም። ድካሙን እና ያልተቋረጠ ጥረቱን አይቶ ድል የሚነሣበትን መንፈሳዊ ጸጋ ይሰጠዋል እንጂ። እንድትኖር በታዘዝከው ልክ ለመኖር ሞክረህ ስላልሆነልህ በራስህ ተስፋ አትቁረጥ። መሆንህን ብቻ ሳይሆን ፈልገህ መሞከርህን እግዚአብሔር ይጽፍልሃል። ሰይጣን አቁስሎህ ስለሻረው ጠባሳህ አትቆጭ። ብዙ ጠባሳ እኮ ለሚዋደቅ ጀግና ወታደር የክብር ምልክቱ ነው። አፈ ወርቅ ዮሐንስ እንደሚለው የማይቆስለው የማይዋጋ ብቻ ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
+++ ስሙም "ድንቅ" ነው+++
ዓለምን "ይሁን" ብሎ የፈጠረ፣ አዳምን የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ አድርጎ በእጁ ከኅትምት መሬት ያበጃጀ አምላክ በዛሬዋ ቀን ከድንግል ተወልዶ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኛ፣ የዚህ ሕፃን ስሙም "ድንቅ" ነው!
"ምድር ታብቅል" ብሎ ለሰው ልጅ መዓዱን የሠራ፣ ፍትረታትን ሲመግብ እጁ የማያጥርበት አምላክ በዛሬዋ እለት እንደ ሕፃናት ከእናቱ ጡት ምግብን ፈልጎ አለቀሰ፣ የዚህ ሕፃን ስሙም "ድንቅ" ነው!
የቀደሙት ሰዎች በሰናዖር ምድር እስከ ሰማይ፣ እስከ አምላክ ማደሪያ የሚደርስ ግንብ ሊሠሩና ስማቸውን ሊያስጠሩ ተነሡ። ነገር ግን በትዕቢታቸው ጠፉ። በኋለኛው ዘመን ግን ራሱ ልዑል ትህትና ያላትን ድንግል መሠላል አድርጎ በፈቃዱ ወደ ምድር ወረደ። በዋሻም ውስጥ ተገኘ፣ የዚህ ሕፃን ስሙም "ድንቅ" ነው!
ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ የሚኖር፣ ፊቱን አይቶ የሚድን የለም የተባለለት አምላክ ዛሬ ከድንግል ተወልዶ የሕጻንነት መዓዛው የሚሸተት፣ የሚያሳሳ የፊቱም ጉንጭ የሚሳም ሆነ፣ የዚህ ሕፃን ስሙም "ድንቅ" ነው!
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg

ለበዓላት የገዛናቸው በጎች እና ፍየሎች ከመብልነት በተጨማሪ ቆዳቸውን የታሪክ እና የሃማኖት መዝገብ ላድርገው ስጡኝ እያለ ነው፥ ሐመረ ብርሃን። ታዲያ እነዚህን እንስሳት የሥጋ ብቻ ሳይሆን ቆዳቸውን ለሐመረ ብርሃን በመስጠት የኀሊና ቀለብ በማድረግ ለምን አሟጠን አንጠቀምባቸውም።
#የፍየልእናየበግቆዳለሐመረብርሃን
#የፍየልእናየበግቆዳለሐመረብርሃን
የቀደሙት ሰዎች በሰናዖር ከምድር እስከ ሰማይ፣ እስከ አምላክ ማደሪያ የሚደርስ ግንብ ሊሠሩና ስማቸውን ሊያስጠሩ ተነሡ። ነገር ግን በትዕቢታቸው ጠፉ። እነዚህ የባቢሎን ሰዎች ምንኛ ችኩሎች ሆኑ?! ጥቂት ዘመን ቢታገሱ ኖሮ ራሱ አምላክ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሰው ሆኖ በግርግም ተኝቶ ያገኙት አልነበር?!
እነዚህ የሰናዖር ሰዎች ትንሽ ቢታገሱ ኖሮ ከምድር ወደ ሰማይ መሻገሪያ የምትሆን በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ታላቋን የብርሃን ድልድይ ድንግል ማርያምን ያገኙዋት ነበር። በዚህችም የብርሃን ድልድይ (መሰላል) እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ የሰው ልጆች ሁሉ ስም እንደ ተጠራ አይተው ደስ ይሰኙ ነበር።
====
አቤቱ ጾም፣ ጸሎት፣ መንፈሳዊ ትሩፋቶቻችን የአንተ ረድኤት የሌለባቸው በትዕቢት ያቆምናቸው የሰናዖር ግንቦች አይሁኑብን። እንዲህም ከሆኑ፣ በሥራዬ እያለ ልባችን እንዳይኮራ፣ ዓይናችንም ወደታች እያየ ወዳጆቹን እንዳይንቅ ወደ አንተ የማያደርሱንን እነዚህን የሐሰት ግንቦች አፍርስልን። በእነርሱም ፈንታ በትሕትና እና በፍቅር ያጌጡ ውብ ግንቦችን እናንጽ ዘንድ ረድኤትህን ላክልን።
እንኳን አደረሳችሁ!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
እነዚህ የሰናዖር ሰዎች ትንሽ ቢታገሱ ኖሮ ከምድር ወደ ሰማይ መሻገሪያ የምትሆን በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ታላቋን የብርሃን ድልድይ ድንግል ማርያምን ያገኙዋት ነበር። በዚህችም የብርሃን ድልድይ (መሰላል) እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ የሰው ልጆች ሁሉ ስም እንደ ተጠራ አይተው ደስ ይሰኙ ነበር።
====
አቤቱ ጾም፣ ጸሎት፣ መንፈሳዊ ትሩፋቶቻችን የአንተ ረድኤት የሌለባቸው በትዕቢት ያቆምናቸው የሰናዖር ግንቦች አይሁኑብን። እንዲህም ከሆኑ፣ በሥራዬ እያለ ልባችን እንዳይኮራ፣ ዓይናችንም ወደታች እያየ ወዳጆቹን እንዳይንቅ ወደ አንተ የማያደርሱንን እነዚህን የሐሰት ግንቦች አፍርስልን። በእነርሱም ፈንታ በትሕትና እና በፍቅር ያጌጡ ውብ ግንቦችን እናንጽ ዘንድ ረድኤትህን ላክልን።
እንኳን አደረሳችሁ!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ዛሬ ወደ ዮርዳኖስ እንዴት ወረድን?
እድሜ ዘመኑን በበረሃ የኖረው ቆዳ ለባሽ፣ ጠፍር ታጣቂው መናኝ ቅዱስ ዮሐንስ "ንስሐ ግቡ" እያለ በመስበክ የጌታን መንገድ ያዘጋጅ፣ ጥርጊያውንም ያቀና ነበር። በዮርዳኖስም ወንዝ ሲያጠምቅ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳ፣ በዮርዳኖስም ዙሪያ ባሉ አገራት የሚኖሩ ሰዎች ወደ እርሱ እየመጡ ኃጢአታቸውን በመናዘዝ ይጠመቁ ነበር። ራሱ አጥማቂው ቅዱስ ዮሐንስ "እኔ ለንስሐ በውኃ አጠምቃለሁ" ሲል እንደ ተናገረ ጥምቀቱ ሰው በደሉንና ክፋቱን አስቦ በመጸጸት የሚጠመቀው "የንስሐ ጥምቀት" ነበር።
ንስሐ ለሚለው ቃል የግሪኩ አቻው ሜታኖያ (metanoia) ሲሆን ትርጉሙም የአስተሳሰብ ለውጥ (change of mind) ማለት ነው። ስለዚህ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ ይመጡ የነበሩት ተጠማቂዎች የቀድሞ ክፋታቸውን ትተው፣ በተቀደሰ ቁጭት ሕሊናቸውን ወደ ጽድቅ ለመመለስ እና ራሳቸውን ለመለወጥ የወሰኑ ነበሩ። አመጣጣቸውም በተሰበረ ልብ ነው።
ይሁን እንጂ ልባቸው እንደ ዐለት የጸና ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን ግን እንደ ሌሎች ሰዎች በጸጸትና በትሕትና ሳይሆን በትዕቢት እንደ ታጀሩ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ መጡ። እንደ ቅዱስ ዳዊት የተሰበረ አጥንት (ልብ) ሳይኖራቸው፣ በኃጢአት ያረጀ ፊተኛው ልባቸውን በመጠየፍ "አቤቱ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ" ብለው ሳይለምኑ፣ ታጥበው ብቻ ከበረዶ ይልቅ ነጭ ለመሆን ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወረዱ።
ቅዱሱም መናኝ ባያቸው ጊዜ አመጣጣቸውን ያውቀዋልና "እናንተ የእፉኝት ልጆች" ሲል ገሰጻቸው። ከእፉኝት ጠባያት ውስጥ አንዱ ተናድፋ ወደ ውኃ (በቅርቧ ወዳለ ባሕር) መሸሿ ነው። ፈሪሳውያኑም እንዳሻቸው ክፋት አድርገው ሲያበቁ፣ የእርሱን የንስሐ ጥምቀት መሸሸጊያ ለማድረግ ወደ ዮርዳኖስ ያለ ምንም ጸጸት ይሮጣሉና እንዲህ አላቸው። እኛስ የዮርዳኖስ ባሕር ተምሳሌት ወደምትሆነው ጥምቀተ ባሕር እንዴት ወረድን? በንስሐ እና በጸጸት፣ የቀደመውን ክፋት ለመተው በቆረጠ የተለወጠ ሕሊና ወይስ እንዲሁ ባልተጸጸተ ፈሪሳዊና ሰዱቃዊ ሕሊና? ዛሬ ወደ ዮርዳኖስ እንዴት ወረድን?
እንኳን ለበዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com

+++ "ሰማያት ተከፈቱ" ማቴ 3፥16 +++
ጌታችን እንደ አይሁድ ሕግ በአደባባይ የሚያስተምርበትና አገልግሎቱን የሚጀምርበት እድሜው ሲደርስ (በ30 ዘመኑ) ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ሊጠመቅ መጣ። የጽድቅ ፀሐዩ ክርስቶስ ለጥቂት ጊዜ እያበራ እና እየነደደ ሕዝቡን ደስ ያሰኝ ወደ ነበረው የአጥቢያው ኮከብ ዮሐንስ ዘንድ ሊጠመቅ በትሕትና መጣ።(ዮሐ 5፥35) ቅዱስ ዮሐንስ ግን እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል እንጂ አንተ ወደ እኔ ለመጠመቅ ትመጣ ዘንድ አይገባም? በጎ ሥጦታዎች ሁሉ ፍጹምም በረከት የብርሃናት አባት ከሆንከው ከአንተ ወደ እኛ ይወርዳሉ እንጂ እንዴት ከምድር ወደ ሰማይ ይወጣሉ? ይህስ አይሆንም ብሎ ይከለክለው ነበር። ጌታም ዮሐንስን "አጥምቀኝ እኮ ነው የምልህ?!" ሲል አልተቆጣውም። ይልቅስ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና "አሁንስ ፍቀድልኝ" ሲል ሊነገር በማይችል ትሕትና ለመነው። ይህን ታላቅ አምላካዊ ተማጽኖ ሰምቶ እንዴት የዮሐንስ ልብ ሊጸና ይችላል?! ያን ጊዜ ሎሌው ዮሐንስ ፈቀደና ጌታውን አጠመቀ።(ማቴ 3፥15)
ጌታችን ኢየሱስም ተጠምቆ ከውኃ ሲወጣ እነሆ ሰማያት ተከፈቱ። ወንጌላዊው "ሰማያት ተከፈቱ" እንጂ "ሰማያት ተከፈቱለት" ብሎ አልጻፈም። ምክንያቱም እርሱ እኛን ለመቤዠት ሰው ቢሆንና በባሕር መካከል ቆሞ ቢታይም በሰማይ ካለው መንበሩ ስላልጎደለ በሰማያትም ለሚኖረው ለእርሱ "ሰማያት ተከፈቱለት" አይባልም። ይልቅስ "ሰማያት ተከፈቱ" የሚለው ቃል ለእኛ በጌታ ጥምቀት ያገኘናቸውን ሰማያዊ በረከቶች የሚያሳይ ነው።
ጌታችን ተጠምቆ ወዲያው ከውኃው እንደ ወጣ ሰማያት ተከፈቱ ማለቱ፣ መድኃኒታችን በሰማይ ወዳለው መንግሥቱ እንድንገባ ተዘግቶ የነበረውን በር በጥምቀቱ እንደ ከፈተልን ለማስረዳት ነው። የማዳን ሥራውን ሲጀምር ተጠምቆ የሰማዩን ደጅ እንደከፈተልን፣ ማዳኑን ሲፈጽም ደግሞ ተሰቅሎ በመሞት የሲዖልን ደጆች ሰባብሮልናል።
ሌላው ከጥምቀቱ በኋላ ሰማያት መከፈታቸው፣ ተዘግቶ የቆየ ቤት በሩ በተከፈተ ጊዜ በውስጥ ያሉ ነገሮች እንዲታዩ በዘመነ ብሉይ ተሰውሮ የነበረው በሰማያት የሚኖረው የእግዚአብሔር የሦስትነቱ ምሥጢር አሁን ግልጥ ሆኖ መታየቱን ያመለክታል። ይኸውም ወልድ እግዚአብሔር በባሕረ ዮርዳኖስ ቆሞ በመታየቱ፣ አብ በደመና "የምወደው ልጄ ይህ ነው" ብሎ በመናገሩ እና መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በርግብ አምሳል በመውረዱ ነው።
ሁላችንም እንደምናውቀው ሰማይ ለሚያምንም ሆነ ለሚጠራጠር ሁሉ የሚታይ ነገር ነው። ይሁን እንጂ ሁሉም የሚያዩት ሰማይ ግን "ሲከፈት" ለመመልከት መጠመቅ ያስፈልጋል። ልክ እንደዚህ ሰማይ በሚያምነውም በማያምነውም እጅ የሚገኝ እና ሁሉም የሚያየው (የሚያነበው) መጽሐፍ "መጽሐፍ ቅዱስ" ነው። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስን ሁሉም ያንብቡት እንጂ የምሥጢር በሩ እንዲከፈትና ውሳጣዊ መልእክቱን ለመረዳት ግን መጠመቅ ያስፈልጋል።
እንኳን ለበዓለ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን!!!

"የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም"
"በልቡ ለተከማቸ ፍቅሯ በሚሻል ነገር መለሰላት። እርሷ ስለ ምድራዊ ወይን ለመነችው፣ እርሱም ስለ ጎኑ የደሙ ወይን በምሥጢር መለሰ"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ መጽሐፈ ምሥጢር
መልካም የቃና ዘገሊላ በዓል!

እንደ እመቤታችን ይህ ዓለም ያልተገባው ማን ነው? የእርሷ ስደት የሚጀምረው ገና በእናቷ ማኅጸን ሳለች ነው። ከተወለደችም በኋላ ሰይጣን ዕረፍት አልሰጣትም። ክፉ መንፈስ ባደረባቸው አይሁድ ምክንያት ብዙ መከራ ተቀብላለች። ከወለደችው የበኩር ልጇ የተነሣ እንደ ሰይፍ የሚወጉ ብዙ የልብ ኃዘኖች ደርሰውባታል። ልጇ የተሰደባቸው ስድቦች በላይዋ ወድቀዋል። በጅራፍ መገረፉ፣ በዘንግ መመታቱ፣ በጦር መወጋቱ የእናትነት አንጀቷን እንደ እሳት አቃጥለዉታል። የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከዐረገ በኋላም የትንሣኤው ጠላት የነበሩት አይሁድ የትንሣኤን እናት ድንግልን አሳድደዋታል። ይህች ዓለም ለአንዲት ደቂቃ እንኳን ለእመቤታችን ተገብታት አታውቅም ነበር።
ስለዚህ ከምድራዊቷ ወደ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ሊያሸጋግራት፣ ከክፉው ወደ መልካሙ ዓለም ሊጠራት ልጇ በታላቅ ልዕልና ወደ እርሷ ወረደ። ጌታ ወደ ማኅጸኗ እቅፍ በገባ ጊዜ "ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች። መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች። የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና" ስትል እንዳመሰገነችው፣ ዳግመኛም እናቲቱ ወደ ልጇ እቅፍ በገባች ጊዜ በዚህ ቃል መልሳ አመስግናዋለች።
እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሰን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ስለዚህ ከምድራዊቷ ወደ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ሊያሸጋግራት፣ ከክፉው ወደ መልካሙ ዓለም ሊጠራት ልጇ በታላቅ ልዕልና ወደ እርሷ ወረደ። ጌታ ወደ ማኅጸኗ እቅፍ በገባ ጊዜ "ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች። መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች። የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና" ስትል እንዳመሰገነችው፣ ዳግመኛም እናቲቱ ወደ ልጇ እቅፍ በገባች ጊዜ በዚህ ቃል መልሳ አመስግናዋለች።
እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሰን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
+++ የማርታ ጸሎት +++
ማርያም: ትእዛዙን ሰሚ
ማርታ: የማይታዘዘውን አምላክ አዛዥ፣ "ንገራት" ባይ። (ሉቃ 10፥40)
እኛስ የእርሱን ትእዛዝ በትሕትና እንሰማለን ወይስ እንደ ማርታ "እንዲህ አድርግ? እንዲህ ተናገር?" ብለን የምንፈልገውን እናዘዋለን?
እስኪ ጸሎታችንን እናስተውል?!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ማርያም: ትእዛዙን ሰሚ
ማርታ: የማይታዘዘውን አምላክ አዛዥ፣ "ንገራት" ባይ። (ሉቃ 10፥40)
እኛስ የእርሱን ትእዛዝ በትሕትና እንሰማለን ወይስ እንደ ማርታ "እንዲህ አድርግ? እንዲህ ተናገር?" ብለን የምንፈልገውን እናዘዋለን?
እስኪ ጸሎታችንን እናስተውል?!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
“ብዙ እናቶች ስቃይ ካለበት የወሊድ ሰዓት በኋላ ልጆቻቸውን ሌሎች እንዲመግቡላቸው ለእንግዶች ይሰጣሉ። ክርስቶስ ግን እኛ ልጆቹን በብዙ መከራ እና ስቃይ በመስቀል ላይ ከወለደን በኋላ ሌሎች እስኪመገቡን ድረስ አይተወንም። በገዛ ሥጋ እና ደሙ እየመገበ ራሱ ያሳድገናል። በዚህ ሁሉ መንገድም ከራሱ ጋር አንድ ያደርገናል”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቤትህ ውስጥ ከፍተህ የረሳኸው ባንቧ ቢኖርና ድንገት ሌሊት ከእንቅልፍህ ስትነቃ መሬቱ እንዳለ በውኃ ተጥለቅልቆ ብታገኝ በቅድሚያ ምን ታደርጋለህ? የፈሰሰውን ውኃ ለመጥረግ ወይስ የሚፈሰውን ቧንቧ ለመዝጋት ነው የምትቸኩለው?
ቧንቧውን ሳትዘጋ መሬት ላይ ያለውን ውኃ ለማፈስ ብትሞክር ትርፉ ድካም ነው። ቀኑን ሙሉ ስትዝቅ ብትውል ቤትህ የሞላውን ውኃ አታጎድልም። እናስ? ቧንቧውን ዝጋዋ!
በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ መፍትሔ በማታገኝበት ነገር ላይ ጊዜህን አታባክን። ለዚህ የሚዳርገኝ መነሻው ምክንያት ምንድን ነው? ብለህ ራስህን ጠይቅ። አእምሮህ ውስጥ የሞሉትን ክፋቶች ከመቁጠር በላይ እነዚያ ክፋቶች የገቡበትን አንድ ቀዳዳ ወይም ሽንቁር ለማወቅ ጣር። እርሱን ያወቅኸው ቀን ለችግርህ ትልቁን መፍትሔ አብረህ ታገኛለህ። ያን ቀዳዳ ከዘጋህ ወይም ምንጩን ካደረቅኸው የቀረው ቀስ እያለ ተኖ መጥፋቱ አይቀርም። ከመውደቅህ በላይ የውድቀትህ ምክንያት ያስጨንቅህ።

ኦሪት ታዝ ነበረ በመንጻቷ ወራት
ሴት እንድታመጣ የዓመት በግ ለመሥዋዕት
ዛሬ እናት ድንግል ከምኩራብ ብትመጣ
ርግብ ዋኖስ ያዘች በጉ ግን በግ አጣ
ዲ/ን አቤል ካሳሁን
[email protected]
ዛሬ ጌታን በመውለድ ያልረከሰች የእመቤታችን የንጽሕናዋ እለት ነው። መሥዋዕተ ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምኩራብ በመጣ ጊዜ በኦሪቱ ካህን በስምዖን አረጋዊ ክንድ የታቀፈበት ቀን ነው።

ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።
ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።