Telegram Web Link
የዓለም ጨለማ የራቀብሽ ንጽሕት ብርህት
የሞት ጻዕር ማስፈራት የጠፋብሽ እመ ሕይወት
ክብርት ነሽ በእውነት(2) የአምላክ እናት
....
በምስራቅ ደጃፍ ከተተከለች የኤደን ገነት
ሁለት እጽ ካላት አንዱ የሕይወት አንደኛው የሞት
አንች ትበልጫለሽ የሕይወት ፍሬን የተሸከምሽው
የሞትን ተክል ነቅሎ የጣለ ልጅ የወለድሽው

አዝማች...

የአምላክን ሕግ በመተላለፍ በመጣ መርገም
ክህደት ጨለማ አለማወቁ ሰፍኖ በዓለም
ስንደናገር ቀንዲሉ ጠፍቶ ፍጹም ታውረን
ሰጠችን ድንግል የሚያበራውን የእውነት ብርሃን

አዝማች...

ከምርጦቹ ጋር የሚደርገውን የምሕረት ኪዳን
ለድንግል ሰጥቷል ከሁሉ የሚበልጥ የእናትነቷን
ኪዳኗን አምኖ ስሟን ለጠራ ዝክሯን ላረገ
በላይ ይኖራል በልጇ እልፍኝ እንደ ከበረ

ግጥምና ዜማ: ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://youtu.be/-q1hPuDHU6I
እየጾሙ ተዋግተው ከባርነት እስከ መጨረሻው ጾመኛ ላደረጉን የአደዋ ከዋክብት ሁሉ ክብር ይገባቸዋል!!!
የእግዚአብሔርን አባትነት በረሃብ እና በጥጋብ፣ በድህነት እና በባለጠግነት አትመዝነው። እርሱ ሲፈልግ በምግብ፣ ሲያሻው ደግሞ ያለ ምግብም ሊያኖርህ ይችላል። አባት ስለሆነ ግን ለአንተ ያዘጋጀው እና የፍቀ‍ሩ መታወቂያ ያደረገው መንግሥቱን ነው። ስለዚህ ከወራሽነት እንዳትወጣ ልጅነትህን ጠብቅ።

መልካም የዐቢይ ጾም ይሁንልን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
ሌሊቱን ከሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ መዝሙራት ጋር!

ስለ ቸርነትህ አምላክ ተመስገን
ለእኔስ ልዩ ነሽ ድንግል ማርያም

https://youtu.be/31lts21ppWw?si=RgF-hQ1cAoFuMrke
ስለ እርሱ ለመናገር እጅግ ከባድ ነው። የማይታይን አካል በእጅ ጠቁሞ ለማሳየት የመሞከር ያህል አስቸጋሪ ነገር ነው። ስለ "ዝምታ" እንዴት የእርሱ ተቃራኒ በሆነው "ንግግር" ልታብራራ ትችላለህ? ዝምታን በሚገባ ሊገልጽ የሚችለው አንድ ነገር ቢኖር ራሱ ዝምታ ነው። ዝዝዝምምም!

ጫጫታና ኹከት በነገሠበት በዚህ ዓለም ንግግር ሰው ሁሉ የሚግባባበት ቋንቋ ነው። የማይናገር ሰው እንደ ሞኝ ወይም ፈዛዛ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል። በእርግጥ ለተፈቀደለት ዓላማ እና መጠን ብናውለው ኖሮ "ንግግር" ግሩም የፈጣሪያችን ሥጦታ ነበር። መናገር እኮ ተአምር ነው። በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሱት ግዙፋን ፍጥረታ መካከል ነባቢው የሰው ልጅ ብቻ ነው። ምን ያደርጋል?! በጎውን ለክፋት፣ መልካሙን ለጥፋት ብናውለው ከንግግር ይልቅ ዝምታ የሚበልጥ ምግባር ሆነ። ንግግር በዚህ ዓለም ያለ መግባቢያ ሲሆን ዝምታ ግን ከሞት በኋላ በሚመጣው ዓለም ያለ ቋንቋ ሆነ። ከሞት በኋላ ያለችውን ዓለም ጣዕም ሳትሞት መቅመስ ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ መንገዱን በ"ዝምታ" ጀምር። የአገሩን ቋንቋ የማያውቅ ሰው ለአገሩ ባዳ እንደሚሆነው፣ የሰማዩ ቋንቋ ዝምታን በዚህ ምድር ያልተለማመደ ሰው በሚመጣው ዓለም እንግዳ ይሆናል።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
Evolution: it's a religion without revelation.

(When i think about evolution i feel like this)
ሁለተኛ

ዶ/ር ዳንኤል ፋኑስ በአቡነ ቄርሎስ 6ኛ የሕይወት ታሪክ ላይ ምርጥ የሚባል የPhD መመረቂያ ጽሑፉን ያዘጋጀ ሲሆን፣ አሁንም ስለ እርሳቸው “ቅዱስ ቄርሎስ 6ኛ፥ የጸሎት ሰው” በሚል ይህን ዳሰሳ አቅርቦልናል። በርግጥ ይህ Video ከተለቀቀ ሰንበትበት ያለ ቢሆንም ላላዩት በሚል አጋርቼዋለሁ። የቻለ ደግሞ “A Silent Patriarch” የሚለውን መጽሐፉን እንዲያነብ ግብዣዬ ነው።

መልካም ሱባኤ

https://www.youtube.com/live/wBMF1IVBpp0?si=XB4IPOb0qynaxw0x
ፍቅር ምን እንዳደረገው ተመልከቱ፤

በአርያም ካለው ከእሳት አዳራሹ ስቦ በቤተልሔም ዋሻ በከብቶች በግርግም አስተኛው።

ብርሃንን እንደ ልብስ የሚጎናጸፈው እርሱን በበለሳን ቅጠል እንዲጠቀለል አደረገው።

ዘመን የማይቆጠርለትን አምላክ ጽንስ፣ ሕፃን፣ ልጅ፣ ጎልማሳ አደረገው።

ፍቅር...

በአባቱ የሚወደደውን አንድያ ልጅ በአይሁድ ዘንድ የተጠላ አደረገው።

በመላእክት የሚመሰገነውን ጌታ በፈሪሳውያን መሪር አንደበት እንዲሰደብ አደረገው።

ፈታሒውን ዳኛ እጆቹን ታስሮ የሰውን ፍርድ ፍለጋ እንዲንከራተት አደረገው።

ፍቅር በኩሩቤል ጀርባ ለሚቀመጠው አምላክ የመስቀል ዙፋን አበጀለት። የመቃብር አልጋም አዘጋጀለት።

ፍቅር የእግዚአብሔርን ልጅ ሐፍረትን ንቆ በፊቱ ስላለው የምእመናን ደስታ እርቃኑን እንዲሰቀል አደረገው!

መድኃኒት በምትሆን ሕማሙ ከኃጢአት በሽታ ሁላችንንም ይፈውሰን!

መጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ለሰው ምጽአቱ ሞቱ!
ሰላም፣

በቅርብ ጊዜ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት የመጣችሁ (የተመለሳችሁ) እና ለሰው ማካፈል የምትችሉት አስተማሪ ታሪክ ያላችሁ ከታች ባስቀመጥነው email አጭር መልእክት ከነአድራሻዎ ያስቀምጡልን። ወይም በሥራ ሰዓት ብቻ ይደውሉልን።

[email protected]
@yanegagirun
0116588808
ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ | ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ
በግዮን ሆቴል እስከ ሚያዚያ 13 ፤ 2016 ዓ.ም ድረስ

በእኛው ዘመን ኢትዮጵያዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው ለታሪክ የተሠሩትን የብራና፣ የነሐስ፣ የእንጨት ውጤቶች ፤ የጥበበኛ እጆች በጥበብ ሲከውኗቸው እንድታዩ ጋብዣለሁ፡፡
2025/07/06 23:42:49
Back to Top
HTML Embed Code: