በኢያሪኮ መንገድ ቆመው ይለምኑ የነበሩ ሁለት ዓይነ ስውሮች ክርስቶስ በዚያ እያለፈ መሆኑን ሲሰሙ "የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን" እያሉ ፈውስ ይማጸኑት ጀመር። ነገር ግን ከጌታችን ፊት ቀድመው ይሄዱ የነበሩ ሰዎች እኒህን ነዳያን "ዝም በሉ!" ብለው ገሰጿቸው።(ሉቃ 18፥39) ልብ በሉ፤ የገሰጿቸው ሰዎች ጌታን ከኋላ የሚከተሉ ወይም ከአጠገቡ አብረው የሚሄዱት አልነበሩም። ከፊት ከፊት የሚቀድሙት እንጂ። በእርግጥም ከጌታው ፊት ቀደም ቀደም የሚል ሰው ጠባይ ይህ ነው። ራሱን ከባለቤቱ በላይ ዐዋቂ ያደርጋል። ምስኪኖችን "ዝም በሉ" እያለ የሚያሳቅ፣ የጌታውን ቸርነት የሚሸፍን አጉል ጠበቃ ይሆናል። እስኪ አሁን "ማረን" ማለት ምን ነውር አለው? ቃሉስ የስድብ ያህል የሚያስቆጣና "ዝም በሉ" የሚያሰኝ ነው? እነዚህ ሁለቱ ዕውሮች የገጠሟቸው እንዲህ ያሉ "በባለቤቱ ያልተወከሉ ጠበቆች" ነበሩ። ግን አልተበገሩም "ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ ማረን" እያሉ ከቀድሞው ይልቅ አብዝተው ጮኹ። እርሱም ልመናቸውን ሰምቶ ወደዚህ አምጧቸው አለ፣ ፈወሳቸውም።
እነ እገሌ ፊት ነሱኝ፣ ተቆጡኝ፣ አመናጨቁኝ ብለህ ከቤተ ክርስቲያን አትቅር ጸሎትህንም አታቋርጥ። ጉዳይህን ከባለቤቱ ጋር ብቻ አድርግ። ያኔ የልመናህን ድምፅ ይሰማል። ሊፈውስህም ወደ እርሱ የሚያቀርቡ ወዳጆቹን ይልክልሃል።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel

ክቡራን፣
ክፍል ስድስት ትምህርታችንን ዛሬ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በዚህ https://www.tg-me.com/Dnabel የቴሌግራም ቻናል በlive stream ትምህርቱ ይሰጣል።
እንደ አማራጭ ይህን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ደግሞ በzoom ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።
https://us05web.zoom.us/j/84709079682?pwd=obn6Rc8YrJjSTaAAeRwKmNbMC2kY8n.1

ጥያቄ!
1. “እርሱም የክብሩ መንጸባረቅ” የሚለውን ቃል ይዘን ፀሐይን እንዴት በምሳሌነት እንዳነሣነው ዘርዝራችሁ ጻፉ።

የኃጢአት ሸክም ያጎበጠህ፣ በሁሉ የተናቅህ፣ አላፊ አግዳሚው ምራቁን ጢቅ እያለ ስድብ የሚያዋጣብህ ጎስቋላ ትሆናለህ። ሌሎች እነርሱን ስላልመሰልክ ይንቁህና ያንቋሽሹህ ይሆናል። ነገር ግን በፈጣሪህ ዘንድ ያለህን ተፈላጊነት ሰዎች በሚያሳዩህ ዝቅ ያለ አመለካከት አትለካ። ዛሬ የሚሰድቡህና የሚያዋርዱህ ሰዎች በአንተ መፈጠርና ሰው ሆኖ መኖር ላይ ምንም ዓይነት አስተዋጽዖ የላቸውም። የሕያውነት እስትንፋስ አልሰጡህም ሞተህ እንዳትቀር ስለ አንተ አልተሰቀሉልህም። ላንተ ሲሉ የከፈሉት ዋጋ ስለሌለ ለእነርሱ ከቁስ ያነስክ ልትሆን ትችላለህ።
ነገር ግን በእጁ የለወሰህ፣ ቁርበትና ሥጋ ያለበሰህ፣ በአጥንትና በጅማት ያጠረህ ሕይወት ሰጥቶ ሰው ያደረገህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚበልጥበት ሀብት የለውም። በፀሐይና በጨረቃ በሌሎች ብርሃናት ሁሉ ያላስቀመጠው በአንተ ውስጥ ብቻ የቀረጸውን መልኩን ፈጽሞ ሊረሳ የማይችል አምላክ ይፈልግሃል። ጥበቡን አፍስሶ ስለ ፈጠረህ ስትጠፋ ዝም አይልም። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ደሙን ስላፈሰሰልህ ፈጽሞ አይተውህም።
የሆሣዕና በዓል በሰዎች ፊት እንደ ምናምንቴ ለሆንን ለእኔ እና ለአንተ ነው። ጌታ ከኢያሪኮ ወደ ቤተ መቅደስ ይዟቸው የመጣው እንደ በርጤሜዎስ ያሉ የተናቁ ነዳያንን፣ እንደ ዘኬዎስ ያሉ የተጠሉ ኃጢአተኞችን ነበር። "ሆሣዕና በአርያም" የሚለው መዝሙራቸውም እንደዚያ ያማረው በመገፋት እና በመጠላት ልባቸው የቆሰሉትን በፍቅርና በምሕረቱ ፈውሶ መድኃኒትነቱን ስላቀመሳቸው ነው።
ለጌታ እናስፈልገዋለን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg

ላትሞት ነው የምትፈታው?
(የሆሣዕና ፍትሐት)
ቤተ ክርስቲያናችን በበዓለ ሆሣዕና ቀን ከምታከናውናቸው ነገሮች መካከል አንዱ ለክርስተኢያኖች ሁሉ ፍትሐት ማድረግ ነው። ይኸውም ከሆሳዕና ቀጥሎ ባሉት ቀናት ሌሎቹን አገልግሎት ሁሉ ለጊዜው አቁማ ልክ እንደ ሰጎን ዕንቁላል ከክርስቶስ ሕማም እና ሞት ላይ ዓይኗን ስለማታነሣ፣ በዚህ ሳምንት የሚያንቀላፋ ቢኖሩ ቀድማ በዕለተ ሆሳዕና ፍትሐት ታደርግለታለች።
ይሁን እንጂ የፍትሐቱ ዋናው ምሥጢር ያለው ግን እዚህ ላይ ነው። ክርስቶስ የተቀበለው መከራ እና ሞቱ በሚታሰብበት በመጪው ሳምንት ልጆቿ ምእመናን የሥጋ ፈቃዳቸውን በመስቀል ሰቅለው ስለ እነርሱ ሲል ለሞተው አምላክ፣ እነርሱም ለዚህ ዓለም ፍትወት የሞቱ ሆነው እንዲያሳልፉ ለማሳሰብ ነው። ስለዚህም ክርስቲያኖችን ሁሉ በቁማቸው ሳሉ እንደ መነኮሳቱ (ለዓለሙ ፈቃድ እንደ ሞቱት) ፍትሐት ታደርግላቸዋለች። ታዲያ በሆሣዕና ሰንበት ወደ ቤተ ክርስቲያን ለፍትሐት ስትመጣ ለራስህ ፈቃድ ሙት ሆነህ ለክርስቶስ ለመኖር ወስነህ ነው? ወይስ ላትሞት ነው ለመፈታት የምትሄደው?
“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ”
2ኛ ቆሮ 5:15

ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የአይሁድ ፋሲካ ሊደርስ አምስት ቀናት ብቻ ቀርተውት ነበር። በእርግጥ አምስት ቀናት የቀሩት እስራኤል ከግብጽ ባርነት መውጣታቸውን ለሚያስቡበት እና የፋሲካውን በግ ለሚያርዱበት በዓል ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም ሁሉ ግብጽ ከተባለ ሲዖል ነጻ ለሚወጣበት እና የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሠውቶ አማናዊው ፋሲካ ለሚደረግበትም የሥርየት ዕለት ነበር። ስለዚህ ሰውን ሁሉ ከሲዖል ወደ ገነት፣ ከባርነት ወደ ነጻነት የሚያሻግረው የፋሲካው በግ ክርስቶስ ወደሚሠዋባት ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ሕዝቡ በደስታ ተቀበለው። መድኃኒትነቱን ተጠምቶ በናፍቆት ሲጠባበቀው የነበረ ነፍስ ሁሉም “አቤቱ እባክህ አሁን አድን” እያለ ዘንባባ ይዞ ዘመረለት።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
በእስራኤል ታሪክ አህያ ይጠብቅ እና በእርሱም ይጓጓዝ የነበረ እንደ ሳኦል ያለ ሰው ነግሥዋል። ይሁን እንጂ የሹመት ዘውድ ከደፋ በኋላ ግን ሳኦል በፈረስ እና በሠረገላ እንጂ በአህያ ዳግም አልተጫነም። ንጉሠ ሰላም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ሐዋርያቱን ፈረስ ወይም በቅሎ እንዲያዘጋጁለት አላዘዘም። ትሑት ሆኖ በአህያ ላይ ለመጫን አህያይቱን ከነግልገሏ ፈተው እንዲያመጡለት ላካቸው እንጂ። ምናልባት በፈረስ የተጫነ በሠረገላ የተፈናጠጠ ንጉሥ ይፈራ ይሆናል፣ ነገር ግን በአህያ ላይ ትሑት ሆኖ እንደ ተሳፈረ ንጉሥ ግን ሊወደድ እና ልብስ ሊነጠፍለት አይችልም። ክርስቶስ አስፈራርቶ ሳይሆን ተወዶ የሚገዛ ንጉሥ መሆኑን ያሳየው በዚህች በሆሳዕና ዕለት ነው። ሕዝቡ ለዚህ ትሑት አምላክ የጎበጠውን መሬት ማቅናት መደልደል፣ ቆሻሻውንም ማጽዳት ባይችሉ የለበሱትን ልብስ ትቢያ ላይ አንጥፈው “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” እያሉ አዳኛቸውን ተቀበሉ።
መሰናበቻ!
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም፥
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
መሰናበቻ!
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም፥
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
ንጹሕ ሆነን የረከሰ ምራቅን አለመጠየፍ እንዴት ይቻለናል? ያለ በደል የሚደረግ ውንጀላ እና ግፍንስ "በቃ" አለማለት እንዴት ይሆናልናል?
ያለ ጥፋት የሚመጣብንን ምን ያህል ጥፊዎች እንታገሳለን? ስንት ጅራፎችንስ እንቀበላለን? ስንት ውርደቶችንስ እንሸከማለን? መድኃኔዓለም ይህን ሁሉ ነገር የተቀበለው ስለ እኛ መዳን ነው።
እኔ ግን ስለ ራሴ መዳን በጀርባህ ላይ ካረፉት ጅራፎች የአንዲቱን ሰንበር ያህል እንኳን መከራ ለመቀበል ትዕግስቱ የለኝም።
"ተሰሃለኒ እግዚኦ በከመ ዕበየ ሳህልከ" - "አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ" መዝ 50፥1
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
ያለ ጥፋት የሚመጣብንን ምን ያህል ጥፊዎች እንታገሳለን? ስንት ጅራፎችንስ እንቀበላለን? ስንት ውርደቶችንስ እንሸከማለን? መድኃኔዓለም ይህን ሁሉ ነገር የተቀበለው ስለ እኛ መዳን ነው።
እኔ ግን ስለ ራሴ መዳን በጀርባህ ላይ ካረፉት ጅራፎች የአንዲቱን ሰንበር ያህል እንኳን መከራ ለመቀበል ትዕግስቱ የለኝም።
"ተሰሃለኒ እግዚኦ በከመ ዕበየ ሳህልከ" - "አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ" መዝ 50፥1
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
ይስሐቅ በሞሪያ ተራራ ሊሠዋ ሲሄድ የምትወደው እና እንደ ዓይኗ የምትሳሳለት እናቱ ከእርሱ ጋር አልነበረችም። አብርሃምም ኀዘኗን ማየት ስለ ፈራ ከእግዚአብሔር ስለ ተቀበለው ከባድ ትእዛዝ ለሣራ አልነገራትም። የይስሐቅ ቤዛው ክርስቶስ ግን ያ ሁሉ ጅራፍ ሲወርድበት፣ ደሙ በየመንገዱ እንደ ውኃ ሲፈስ፣ በገመድ አስረው እየጎተቱ ሲጥሉትና ምራቃቸውን እየተፉ ሲዘባበቱበት እናቱ ድንግል ማርያም አይታለች። አንድ ልጇ ላይ ብዙ የሆኑ አይሁድ እና ሮማውያን ተባብረው ሲጨክኑበት በዓይኗ በብረቱ ተመልክታለች። ወደ መሬት ወድቆ በረገጡት ጊዜ በስቃይ ከሚቃትት ልጇ ጋር ዓይን ለዓይን ተያይታለች።
ለልጅም ለእናቱም ቢሆን ከዚህ ዕለት በላይ የሚከብድ ምን ዓይነት የኀዘን ቀን ሊኖር ይችላል?
በዚህ ምድር እንደ አምላካችን ክርስቶስ የሰቃየ እንደ እመቤታችን ማርያምም ያዘነ ማንም የለም!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
ለልጅም ለእናቱም ቢሆን ከዚህ ዕለት በላይ የሚከብድ ምን ዓይነት የኀዘን ቀን ሊኖር ይችላል?
በዚህ ምድር እንደ አምላካችን ክርስቶስ የሰቃየ እንደ እመቤታችን ማርያምም ያዘነ ማንም የለም!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
+++‹‹በለምጻሙ ስምዖን ቤት ሳለ›› ማቴ 26፥6+++
አይሁድ በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ግቢ ውስጥ ተሰብስበው በጌታ ሞት ላይ ሲመክሩ፣ መድኃኒታችን ግን በቢታንያ በስምዖን ቤት እራት ግብዣ ተቀምጦ ነበር፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ጌታ እራት የተጠራበት ቤት ባለቤት ‹ለምጻሙ ስምዖን› እንደ ሆነ ይናገራል፡፡ ጸሐፊው ስለ ምን ይህንን ሰው ስምዖን ብቻ ብሎ አልጠራውም? ‹ለምጻሙ› የሚለው ገላጭ ቃል መጠቀም ለምን አስፈለገው? በርግጥ ስምዖን በለምጽ ንዳድ የተያዘና በአይሁድ ዘንድም እንደ ረከሰ እና በደለኛ ተቆጥሮ የሚገለል ብቸኛ ሰው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ግን ጌታ ከሐዋርያቱ ጋር ሆኖ በእርሱ ቤት ለእራት በተቀመጠ ጊዜ፣ ቅዱስ ጄሮም እንደሚናገረው ይህ ሰው ካለበት ለምጽ ሁሉ ነጽቶ ነበር፡፡ ታዲያ ወንጌላዊው ስለ ምን ከለምጹ የነጻውን ስምዖን ‹‹ለምጻሙ›› ሲል ጠራው?
ይህ ያለ ምክንያት አልሆነም፡፡ ጌታችን በስምዖን ቤት ለእራት ተቀምጦ ሳለ የሚፈጸም ቀጣይ ወሳኝ ታሪክ ስላለ፣ ‹ለምጻሙ› የሚለው ገላጭ ለዚያ መግቢያ የሚሆን ወሳኝ ቃል ነበር፡፡ ቀጥሎ የምናገኘው ታሪክም አንዲት በኃጢአት የተመረረችና ነፍሷ የጎሰቆለባት ሴት፣ መንፈሳዊውን ምሕረት ፈልጋ ጌታችን ወዳለበት መምጣቷና የያዘችውን እጅግ ውድ የሆነውን ሽቱ ከፍታ በጌታ በራሱና በእግሮቹ ላይ ማፍሰሷን የሚናገር ነው፡፡ ይህች ሴት ቀድሞ በዝሙት ትኖር ነበረች ብትሆንም ዛሬ ግን የሽቱና የእንባን መባ ይዛ ወደ ክርስቶስ ቀርባለች፡፡ በዘመኑ ብዙዎች ያስጨንቃቸውና የክርስቶስን መድኃኒትነት ይፈልጉት የነበረው ለሥጋዊ ሕመማቸው ነበር፡፡ ምንም የሥጋ ሕመም የሌለባት ይህች ሴት ግን ባልተለመደ ሁኔታ የነፍሷን ሕመም (ኃጢአት) በምሕረቱ መድኃኒትነት ለመሻር ወደ ጌታችን ስትሮጥ መጣች፡፡ ይህም ሥራዋ እጅግ በጣም የምትደነቅ መንፈሳዊት ሴት ያደርጋታል፡፡
በዚህ ወንጌል የተጠቀሰችው ባለ ታሪክ ትሠራ የነበረው ሥራ በሁሉ ዘንድ አስነዋሪ የነበረውን፣ እንኳን በአምላክ ፊት ቀርቶ በሰው ፊት እንኳን ቀና ብሎ የማያስቆመውን ዝሙት ነበር፡፡ ታዲያ ወደ ክርስቶስ ለመምጣት ድፍረት የሰጣት ነገር ምንድር ነው? እንዴት ወደ መድኃኔዓለም ቀርባ ‹‹ማረኝ›› ለማለት በቃች? ካልን መልሱ ቀላል ነው፤ ጌታ ‹በለምጻሙ ስምዖን› ቤት እንደ ተገኘ አይታ ነው፡፡ ክርስቶስ ራሳቸውን ከሚያመጻድቁ ፈሪሳውያን መካከል በአንዱ ቤት ተገኝቶ ቢሆን ኖሮ ባለ ሽቱዋ ማርያም ድፍረት አግኝታ ወደ እርሱ ባልመጣች ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ሰዎች እንደ ርኩስና በደለኛ ቆጥረው ያገሉት በነበረው ስምዖን ቤት ነውሩን ሁሉ አስወግዶለት አብሮት ለእራት እንደ ተቀመጠ ስላየች፣ የሚበዛው ድካሜን አይቶ የበለጠ ይራራልኝ እንደ ሆነ እንጂ ለእርሱ ያደረገውን ቸርነት ለእኔ አይነሳኝም ብላ በተስፋ ወደ ፈጣሪዋ ገሰገሰች፡፡ እጅግ የሚያስደንቅ ተስፋ ነው!!!
ዛሬም መድኃኔዓለም ክርስቶስ በለምጻሙ ስምዖን ቤት አለ፡፡ ስለዚህ ‹አይሰማኝ ይሆን› የሚለውን ጥርጣሬያችንን ትተን ወገባችንን ያጎበጠውን ኃጢአት በንስሐ ከእግሩ ስር ለማራገፍ ፈጥነን ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡ በለምጻሙ ስምዖን ቤት ለእራት የተቀመጠ አምላክ በፍጹም ጸጸት ብንመለስ የእኛንም ቤት (ሰውነት) አይንቅም፡፡ ይልቅ ሳይረፍድ ቶሎ ሄደን ከእግሮቹ ስር እንውደቅ!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
2015 ዓ.ም.

“የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው” ዮሐንስ 13:1
ሲወድድ ምክንያት አልነበረውም። ያለ ምክንያት የወደዳቸውን ግን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው!
ጸጥ፤ ዝም የሚያሰኝ ቃል!!!
ለመወደድ የሚያበቃ ምንም ምክንያት የለኝም። እርሱ ግን እስከ መጨረሻው ወድዶኛል!!!

ፍቅር ምን እንዳደረገው ተመልከቱ፤
በአርያም ካለው ከእሳት አዳራሹ ስቦ በቤተልሔም ዋሻ በከብቶች በግርግም አስተኛው።
ብርሃንን እንደ ልብስ የሚጎናጸፈው እርሱን በበለሳን ቅጠል እንዲጠቀለል አደረገው።
ዘመን የማይቆጠርለትን አምላክ ጽንስ፣ ሕፃን፣ ልጅ፣ ጎልማሳ አደረገው።
ፍቅር...
በአባቱ የሚወደደውን አንድያ ልጅ በአይሁድ ዘንድ የተጠላ አደረገው።
በመላእክት የሚመሰገነውን ጌታ በፈሪሳውያን መሪር አንደበት እንዲሰደብ አደረገው።
ፈታሒውን ዳኛ እጆቹን ታስሮ የሰውን ፍርድ ፍለጋ እንዲንከራተት አደረገው።
ፍቅር በኩሩቤል ጀርባ ለሚቀመጠው አምላክ የመስቀል ዙፋን አበጀለት። የመቃብር አልጋም አዘጋጀለት።
ፍቅር የእግዚአብሔርን ልጅ ሐፍረትን ንቆ በፊቱ ስላለው የምእመናን ደስታ እርቃኑን እንዲሰቀል አደረገው!
መድኃኒት በምትሆን ሕማሙ ከኃጢአት በሽታ ሁላችንንም ይፈውሰን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
በአርያም ካለው ከእሳት አዳራሹ ስቦ በቤተልሔም ዋሻ በከብቶች በግርግም አስተኛው።
ብርሃንን እንደ ልብስ የሚጎናጸፈው እርሱን በበለሳን ቅጠል እንዲጠቀለል አደረገው።
ዘመን የማይቆጠርለትን አምላክ ጽንስ፣ ሕፃን፣ ልጅ፣ ጎልማሳ አደረገው።
ፍቅር...
በአባቱ የሚወደደውን አንድያ ልጅ በአይሁድ ዘንድ የተጠላ አደረገው።
በመላእክት የሚመሰገነውን ጌታ በፈሪሳውያን መሪር አንደበት እንዲሰደብ አደረገው።
ፈታሒውን ዳኛ እጆቹን ታስሮ የሰውን ፍርድ ፍለጋ እንዲንከራተት አደረገው።
ፍቅር በኩሩቤል ጀርባ ለሚቀመጠው አምላክ የመስቀል ዙፋን አበጀለት። የመቃብር አልጋም አዘጋጀለት።
ፍቅር የእግዚአብሔርን ልጅ ሐፍረትን ንቆ በፊቱ ስላለው የምእመናን ደስታ እርቃኑን እንዲሰቀል አደረገው!
መድኃኒት በምትሆን ሕማሙ ከኃጢአት በሽታ ሁላችንንም ይፈውሰን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“እንደ ውኃ ፈሰስሁ፤ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ። ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጕሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ”
መዝሙር 22:14-15
መዝሙር 22:14-15
ሰላም ክቡራን፣
እንኳን አደረሳችሁ። የዛሬው የክፍል 7 የዕብራውያን መልእክት ሐተታ ትምህርታችንን በYouTube ለቀነዋል። ትምህርቱን ለዛሬ ድካማችንን ባገናዘበ መንገድ አጠር አድርገን ነው ያቀረብነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ቀጣይ ሳምንት በተለመደው ሰዓት እንገናኛለን።
https://youtu.be/fnbrIW4MEI0?si=lHa-Hl9vggYvkEe9

YouTube
የዕብራውያን መልእክት ሐተታ ክፍል 7 I Orthodox Bible study - @Dnabelkassahun
#biblestudy #share