Telegram Web Link
በአዕምሮ ጤና ላይ የተዘጋጀ የድጋፍ ቡድን እንድተቀቀላቀሉ ስንጋብዝዎት በትልቅ ደስታ ነው፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅታችን በሰለጠኑ ባለሙያዎቻችን የሚመራ፣ አስተማማኝ እና ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ ሁኔታ አዘጋጅቶላችኋል፡፡ ይህ የድጋፍ ቡድን ከተለያዩ የቡድኑ ተሳታፊዎች ጋር ለመተዋወቅ፣ ከእዚህ በፊት የጋጠማችሁን እና ሌሎች ያጋጠማቸውን በማዳመጥ የተሞክሮ መጋራት እንዲኖረው የሚያደርግ ሲሆን እርስ በእርስ በመተጋገዝ እና ከሰለጠኑ የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመሆን የበለጠ ራስን መንከባከብ እና የመቋቋም ችሎታ ለማዳበር የሚረዳ ነው፡፡
ለአዕምሮ ጤና ቅድሚያ ለመስጠት ወይም ድጋፍ ለማግኘት ወይም መደመጥ እና ስሜትዎትን በነፃነት መግለፅ የምትችሉበት መድረክ አዘጋጅተንልዎታል፡፡
የድጋፍ ቡድኑ በየሳምንቱ እሁድ የሚካሄድ ሲሆን መገናኛ፣ የካ ክ/ከ ሕንፃ አካባቢ በሚገኘው ሠላም ታወር 11ኛ ፎቅ ላይ ከ 9፡30 እስከ 11፡00 (ከሰዓት በኋላ) የሚቆይ ይሆናል፡፡
ለመመዝገብ እና ቦታ ለማስያዝ ይህንነ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ https://forms.gle/MNNTrKsRj6ZVdqsD9
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251965579192 ወይም +251919186182 ይደውሉ፡፡
አይቼ አልጠግብሽ ፤ ውጬ አልጨርስሽ
======================

በእርግጥ ከሕክምና መዘመን ጋር ተያይዞ አሁን ላይ ምክንያት ተኮር ህክምና (etiology based approach) እየጎለበተ ቢሆንም አንዳንድ የህክምና ምርመራ እጥረት ባለባቸው አከባቢዎች አሊያም በሌሎች ምክንያቶች ምልክት ተኮር ህክምና (symptom based approach) ሲዘወተር እናስተውላለን፡፡ በተለይ ምልክት ተኮር (symptom based approach) ህክምናዎች ዘነድ አብዝቶ ከሚስተዋሉት ነገሮች አንዱ ከደረጃ በላይ የሆኑ ህመም ማስታሻዎችን ሲጠቀሙ ማየት ነው፡፡

ዛሬ ስለ አንድ ከወራት በፊት ስለገጠመኝ አጋጣሚ ላወጋቹ ዘንድ ወደድኩ፡፡ ታካሚው በትምህርት ደረጃው የመጀመሪያ ደረጃን ያላጠነቀቀ ፣ በቀን ስራ እሚተዳደር ፣ የትኛውንም አይነት ሱስ አምጪ ንጥረ ነገር እማይጠቀም እና ከህክምና ጋር ዘርፍ ጋር ንኪኪ የሌለው በሀምሳዎቹ መጨረሻ አከባቢ ያለ ታካሚ ነበር ፡፡ታካሚው ወደ ድንገኛ ህክምና ክፍል የእሚጥል ህመም (አንፍርፍሪት/epilipsy) ምልክት እያሳየ በቤተሰቡ እርዳታ መጥቶ ህክምና ተደረገለት ፡፡ ከህክምናው ብኋላ ታካሚው ወደ እራሱ ሲመለስ ከሀኪሙ ጋር በነበረው ንግግር ከዚህ ቀደም እንዲ አይነት ነገር እንዳልነበረው ፣ በቤተሰብ ዘር ሀረግ ላይ እንዳልነበረ እንዲሁም ሌሎች ታሪኮችን ካወራው ብኋላ ነበር "እንዲ እምሆነው ትራማዶል ካልወሰድኩ ነው እሱን ከሰጠኸኝ ደና እሆናለው" ወደ እሚለው መደምደሚያ የመጣው ፡፡ በዚህ ምክንያት ነበር ከድንገተኛ ህክምና ብኋላ በሚከታተለው ሀኪም ወደ አዕምሮ ህክምና ክፍል ተዘዋውሮ ከእኔ ጋር የተገናኘነው ፡፡

በተለይ ከኦፖይድ ህመም ማስታገሻ ሱስ ጋር ተያይዞ ከማስተውላቸው ታማሚዎች በብዙ ነገር ወጣ በማለቱ ምክንያት በመጓጓቴ በነበረን ምርመራ ወቅት እንዴት ወደ ትራ፨ል መጠቀም እንደገባ አስረዳኝ፡፡ ከወራቶች በፊት በተደጋጋሚ የጎን ህመም ያስቸግረው እንደነበርና ለእለት ጉርሱ ውሀ በመቅዳት ይተዳደር ስለነበር ከስራው ጋር በጣም ስለተቸገረ ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ እንደታየው አስረዳኝ፡፡ ከምርመራ ብኋላ ችግሩ የሽንት ቧንቧ ኢንደፌክሽን እንደሆነ ተነግሮት ከትራ፨ል ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በዚያን እለት እንደተዋወቀ ነገረኝ ፡፡ ይህ ህመም ለጊዜው መሻሻልን ቢያሳም በተደጋጋሚ እያገረሸበት ከአምስት በላይ የተለያዩ የህክምና ተቋማት ቢሄድም ከትራ፨ል ጋር የተለያዩ መድኅኒቶች እንደተሰጠው አስረዳኝ፡፡ ከዛም በተጨማሪ ትራ፨ሉን ወስዶ በሚሰራ ወቅት እንደማይደከምና የደስታ ስሜት መስጠቱ ባያመውም የመድኃኒቱ ቤተኛ እንዳደረገው አጫወተኝ፡፡ ይህን ሲለኝ አቀንቃኝ ተሾመ ምትኩ "ሱሰኛሽ" ሲል ያቀነቀነው ዘፈን ወደ እዕምሮ መጣ

አመል ያለብኝ እኔ ሱሰኛሽ
አይቼሽ አልጠግብሽ ውጬ አልጨርስሽ
መውደድሽ ግሎ ልቤን ተኮሰው
እኔስ የት ልግባ ወዴት ልድረሰው
መውደድሽ ግሎ ልቤን ተኮሰው
እኔስ የት ልግባ ወዴት ልድረሰው ………… እያለ ያቀነቀነው

በሁሉም ህክምና ቦታዎች የተሰጠው መድኀኒት ውስጥ የትራ፨ል መደጋገም የህመሜ መድኀኒት ትራ፨ል ነው ወደ እሚል ድምዳሜ በመሄድ በየጊዜው መግዛት እና መጠቀሙን አስረዳኝ ፡፡ በቀን ሁለት ፍሬ የተጀመረው መድኀኒት በቀን ወደ አርባ ፍሬ ማደጉንና ከህመሙ በተጨማሪ እና ለስራም ጉልበት እንደሆነው አጫወተኝ፡፡ በትራ፨ል መደኀኒት ማዘዣ ወረቀት መቀየር ምክንያት መድሀኒቱን እንደ ልብ ማግኘት እንደተቸገረና ቢገኝም በዋጋ ረገድ ከበፊት ዋጋው አስር ብር ሁለት መቶ እጥፍ ሆኖ መግዛት እንዳልቻለ አስረዳኝ፡፡

መድኀኒቱን ባልወሰደባቸው ቀናቶች ከእንፍርፍሪቱ በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት ፣ የእንቅልፍ ማጣት ፣ ማስታወክ እና የመጨቅ ስሜት ስለሚያስጨግረው አንድ ስትሪፕ በሁለት መቶ ብር እየገዛ ለጥቂት ጊዜ መጠቀሙንም አጫወጠኝ፡፡ በስተመጨረሻ ይህ ችግር ህመም እንደሆነና ህክምና እንዳለው መግባቢያ ላይ በመድረስ በሆስፒታላችን ተሀድሶ እና ሱስ ማገገሚያ ክፍል በመቆየት ግልጋሎቱን አግኝቷል ፡፡ ይህ ሀኔታ ለሀኪሞች እና ሌሎች ባለሞያዎች "ማስታገሻ ከመፃፋችን በፊት ሁለት ጊዜ እናስብ " እሚል መልዕክት ያስተላልፋል ብዬ አስባለው ፡፡

"የኦፖይድ ህመም ማስታገሻዎች ሱስ የመሆን ባህሪ ስላለው ስንጠቀምም ሆነ ስናዝ ጥንቃቄ እናድርግ እላለው"
የአዕምሮ ህክምናን ለእርሶም ሆነ ለቤተሰቦ እምትሹ የድሬደዋ እና አከባቢዋ ነዋሪዎች በስልክ ቁጥር በ0254119722/0251130996/98 በመደወል ቀጠሮ በማስያዝ በኢፍቱ፣ በዴልት ሆስፒታል እና በሴንተራል ሲቲ ሆስፒታል እንዲሁም በሣቢያን ጠቅላላ ሆስታፒል ቢመጡ ግልጋሎቱን ከጥሩ መስተንግዶ ጋር ያገኛሉ::
ድሬደዋ, ኢትዮጲያ
ዶ/ር ቶፊቅ አብደላ(የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
🌟 Discover Hope and Healing at Asheten Psychiatry and Rehabilitation Center! 🌟

Are you or a loved one struggling with mental health challenges or substance abuse?

At Asheten Psychiatry and Rehabilitation Center, we offer compassionate, expert care to help you reclaim your life.

Our dedicated team of professionals provides personalized treatment plans designed to meet your unique needs.

🌿 Why Choose Us?

👉Experienced and caring staff
👉Evidence-based treatment approaches
👉Safe and supportive environment
👉Continuous support and aftercare

Your journey to recovery starts here. Take the first step towards a brighter future today!

Contact Us Today:
Visit Our :🌐 ashetenpsyc.com
“ስለኦቲዝም ያገባናል” በሚል ርዕስ በወላይታ ሶዶ የሁለት ቀናትግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተካሄደ

#Ethiopia | ልባም ኦቲዝም ማዕከል ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር እና ከኒያፋውንዴሽን (ጆይ ኦቲዝም) ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያክልላዊ መንግስት ወላይታ ሶዶ “ስለ ኦቲዝም ያገባናል” በሚል መሪ ቃል በኦቲዝምና ተዛማጅ የአዕምሮ ዕድገት እክሎችላይ ያተኮረ የሶስት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብርአካሂዷል።

ግንቦት አጋማሽ ላይ በተከፈተው በዚሁ መርሃ ግብርየመጀመሪያ ቀን የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት፣ ከፍተኛየመንግስት ባለስልጣናትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትተወካዮች በተገኙበት “ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ዜጎችናቤተሰቦቻቸው የማህበረሰቡን ፍቅር፣ መረዳት፣ እንክብካቤ እናድጋፍ ይሻሉ!" በሚል መሪ ቃል ከወላይታ ሶዶ ሃይሌ ሪዞርትሆቴል እስከ ጦና አደባባይ ድረስ በፖሊስ ማርሽ ባንድ የታጀበደማቅ የእግር ጉዞ ተካሂዷል።

በተጨማሪም በኦቲዝምና እና ተዛማጅ የአዕምሮ እድገትእክሎች ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ አዉደ ጥናት በወላይታ ሶዶጉተራ አዳራሽ ተካሄዷል።

በዚህ አዉደ ጥናት ላይ ስለኦቲዝም ምንነት፣ ስለቅድመምልክቶቹና አጋላጭ ሁኔታዎች፣ እንዲሁም የማሻሻያ ህክምናናቴራፒዎች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችተሰጥተዋል።ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች ወላጆችልጆቻቸውን እንዴት መርዳትና መረዳት እንዳለባቸው ፣ለልጅቻቸው በአመጋገብና በክህሎት ስልጠና ማድረግስላለባቸው ተግባራት ሰፊ ገለጻም ተሰጥቷል።

በአውደ ጥናቱ ላይ የወላይታ ከተማ ከንቲባን ጨምሮየአስተዳደሩ ባለስልጣናትና የልዩ ልዩ ክፍሎች የስራ ሃላፊዎችእንዲሁም ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች ወላጆች፣ ከልዩ ልዩተቋማት የተውጣጡ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸውየከተማው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ከግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሩ ጎን ለጎንም የወላይታ ሶዶክርስቲያን ሆስፒታል የህጻናት ፊዚዮቴራፒና ህክምናአገልግሎት ክፍል የሚሰጣቸው አገለግሎቶችምበባለስልጣናቱና የመርሃግብሩ ተካፋዮች ተጎብኝቷል።

በሀገራችን ከ6መቶ ሺህ በላይ ህፃናት ከኦቲዝም እና ተዛማጅየዐዕምሮ እክሎች ዕድገት እክሎች ጋር እንደሚኖሩ ጥናቶችይጠቁማሉ። ስለችግሩ በቂ ግንዛቤ ባለመፈጠሩ ምክንያት ከችግሩ ጋር የሚኖሩ ልጆች ከቤተሰቦቻቸው እና ከማህበረሰቡጭምር የሚደርስባቸው መገለል ከፍተኛ መሆኑምተረጋግጧል። በተመሳሳይም በወላይታ ሶዶ ከተማ በየደረጃውያሉና ለአስቸጋሪ ሁኔታ የተጋለጡ መሰል ህጻናት ቁጥር በርካታእንደሆነ ይገመታል። ድጋፍና እንክብካቤ ማግኘት ሲገባቸውከማህበረሰቡ እይታ እንዲሰወሩ እና የተገለለ ቦታ እንዲቀመጡመደረጉ ችግሩን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ፈታኝአድርጎታል።

ኦቲዝም የአዕምሮ እድገት ስርዓት መዛባት እንጂ የፈጣሪ ቀጠናወይም እርግማን አይደለም!
ኦቲዝም የምንነጋገርበትናመፍትሄ የምናበጅለት እንጂየምንደበቅበት ጉዳያችንም አይደለም!
ስለኦቲዝም ሁላችንም ያገባናል!
#ልባም ኦቲዝም ማዕከል #ወላይታ ሶዶ
Via Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
ትኩረት የማጣት እና የመረጋጋት ችግር (ኤዲኤችዲ)
(Attention Deficit hyperactivity Disorder)-ADHD

ኤዲኤችዲ ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል የእድገት እክል ነው።

አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች በተለየ ትዕግስት የለሽ፣ ቀዥቃዣና አስቸጋሪ ሆነውባቸው መፍትሔ ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው፣ አንድ ነገር ጀምረው አፍታም ሳይቆዩ ሌላ የሚያምራቸው፣ ለመናገርና ለመጠበቅ ትዕግስት የማይኖራቸውና ችኩል ናቸው፡፡
ይህ አይነት የስነባህሪና የስነአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ትኩረት ያጡ፣ ትዕግስት የለሽ ቀዥቃዣነት (ADHD) ህመም ተጠቂዎች ናቸው፡፡

የእነዚህ ህፃናት መሰረታዊ መገለጫዎች
 አንድ ነገር ጀምረው በቀላሉ ወደ ሌላ የሚሳቡና አንድን ነገር ጀምሮ
ለመጨረስ ትኩረት የሌላቸው
 በትምህርት ቤት ግዴለሽነት የሚታይባቸውና ቀላል ስህተቶችን በፈተና
ላይ በተደጋጋሚ የሚሰሩ
 የማያዳምጡና የተባሉትን የማያደርጉ
 የክፍልና የቤት ስራን ጀምሮ ለመጨረስ እንኳን ትዕግስት የሌላቸው
 በተሰጣቸው ስራ ላይ ሀሳባቸውን መሰብሰብ የማይችሉ
 ዝንጉነት በእጅጉ የሚታይባቸው
 በየአቅጣጫው የሚሮጡና እረፍት የሌላቸው፣ ዛፍም ሆነ ደረጃ ላይ
ላይ ለመውጣት የሚታገሉ
 እጅና እግራቸው የሚቅበጠበጥና አደብ የሌላቸው
 ከጓደኞቻቸው ጋር እየተጫወቱ ተራቸው አስኪደርስ መጠበቅ ሞት
የሚመስላቸው
 በቀላሉ የሚበሳጩና የሚናደዱ ናቸው፡፡

ስለዚህም ይህ ትኩረት የለሽነታቸውና ትዕግስት አልባነታቸው የትምህርት አቀባበልና አረዳዳቸውን በእጅጉ ይጎዳዋል ።

ለዚህ ህመም እንዲህ ነው የሚባል ምክንያት ባይኖርም በእርግዝና ጊዜ አልኮልና ሲጋራ መጠቀም እንደ አጋላጭነት ይጠቀሳሉ፡፡ ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል፡፡

አብዛኛው ትኩረት የለሽ ህፃናት በስነ ልቦና ህክምና፣ በአማራጭ ትምህርት(Special Education) እና በመድሀኒቶች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንዳንዶች የጎላ ችግር ያለባቸው ካደጉ በኋላም ራስን ዝቅ ማድረግና ከማህበራዊ ግንኙነቶች ማፈግፈግ ሊታይባቸው ይችላል፡፡
ወላጆች እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸውን ህፃናት በአግባቡ በማሳከምና በቤት ውስጥ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ፡፡
መልእክቱ ለሁሉም እንዲደርስ #Share ያድርጉት

በዩቲዩብ የአእምሮ ጤና መረጃ ለማግኘት https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386

በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ
(የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የልጅ በእድሉ አይደግ መፅሀፍ ደራሲ)
የቀዶ ህክምና እየተደረገላት በመሃል የነቃችው ናንሲ
****
Bessel Van Der Kolk ባዘጋጀው 'Body keeps the score' የተሰኘ በዋናነት ትኩረቱን Trauma ላይ ባደረገው መጽሃፍ አንድ አስገራሚ ታሪክ እናገኛለን::

ናንሲ ሶስተኛ ልጇን ከተገላገለች በኋላ ማህጸኗን ማስቋጠር ፈለገች:: የሰመመን መድሃኒት ተሰጧት ህክምናው ተጀመረ:: ታድያ በህክምናው መሃል ነቃች:: አዕምሮዎ ቢነቃም ከሰመመን መድሃኒቱ በተጨማሪ የተሰጣት ጡንቻዎችን የሚያዝል መድሃኒት(Muscle relaxant) መንቃቷንና ህመም እየተሰማት መሆኑን እንዳትናገር ከለከላት:: ከባድ የጭንቅ ጊዜ ነበር!

ይህን ጊዜ 'ህልም መሰል ሁነት ውስጥ እንዳለሁ ይሰማኝ ነበር' ብላ ትገልጸዋለች:: ለቀናት ደመነብሷን በድንግዝግዝ ስሜት ውስጥ እንደነበረች ታነሳለች:: ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ አንዳንድ ትውስታዎቿ ተመለሱላት:: ያኔ በህክምና ወቅት ምን እያደረጓት እንደነበር እና ምን ይባባሉም እንደነበር ማስታወስ ጀመረች..ችግሩ እነዚህ ትውስታዎች ያልተሰደሩ እና የተዘበራረቁ መሆናቸው ነበር:: fragmented traumatic memories.

ስሜቷን ውል ያጣ እና በመደንዘዝና(Numbness and dissociation) እና በመበርገግ(Hyper vigilance) አጽናፋት የመዳወር አይነት እንደሆነ ትገልጣለች::

በህክምናው ወቅት የነበሩት ድርጊቶች ቀን በእውኗ ድቅን እያሉ(flashback)፣ ማታ በህልሟ(Nightmare) እየመጡ ነብሷን እረፍት ነሷት::

ያንን ክስተት የሚያስታውሳትን ነገሮች ስታይ ትበረግግ ጀመር.. አንዳንዴም ስውር ያደርጋታል:: በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ ሊያስታውሷት የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች በወል መሸሽን አማራጯ አድርጋለች:: .... የኦፕሬሽን ክፍልን መሳይ አልባሳትን እና አቃዎቹን የሚያስታውሱ ማናቸውንም ነገሮች፣ የሰዎች ሳቅና ሁካታን(በህክምናው ወቅት እሷ ነቅታ እያመማት እየተሳሳቁ ሲያወሩ ስለነበር...ይህ በአዕምሮዎ መጥፎ ትዕምርት ፈጥሮ ኖሯል) .. እና የመሳሰሉ ነገሮችን ላለማስታወስ መሞከርና መሸሽ ጀመረች:: .. ባሏ ሲስቅና ሲጫወት ስታየው ያስጠላት እንደነበር ሁሉ ትናገራለች:: ይህም ቤተሰቧ ላይ ችግር ፈጠረባት::

ክስተቱ ለነገሮች ያላት እይታ አሉታዊ ማድረግ ጀመረ:: ሰዎች አስጠሏት..ወደፊቱ አስጠላት..ራሷን ጠላች:: የእንቅልፍ ማጣት፣ ትኩረት ለማረግ መቸገር፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሌሎች የፈተኗት ጉዳዮች ነበሩ:: ክብደትም ቀነሰች... አማረባት ተባለ... የውስጧን ጣር ማን አውቆላት😣

በዚህ ሁሉ የስሜት መረበሽ ውስጥ ሆናም ስራዋን ለመስራት አልተበገረችም ነበር:: This is resilience!

ናንሲ ክስተቱን ተከትሎ ድህረ አደጋ ሰቀቀን ገጥሟት ኑሯል:: ለብዙ ጊዜያት 'ምን እየሆንኩኝ ነው' እስክትል ግራ ያጋባትን ችግር ማወቋ አፎይታን ሰጣት:: የስነ-ልቦና ህክምና ጀምራ ጥሩ መሻሻል እንዳሳየች ትናገራለች:: በአግባቡ ያልተሰደሩ ትውስታዎቿን ፈርጅ አስይዛ መተረክ መቻሏ ለውጥ አምጥቶላታል::

በሙሉ አንስቴዢያ ላይ ሁኖ ማስታወስ እና መገንዘብ(Intraoperative awareness) ዙሪያ ዶ/ር ይስሃቅ አብርሃም የጻፈውን ጽሁፍ እንድታነቡ ጋበዝኳችሁ::

(https://www.facebook.com/100044029604041/posts/1001194054691572/?app=fbl)

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት

https://www.tg-me.com/DrEstif
https://www.facebook.com/DrEstif
2024/06/08 17:28:06
Back to Top
HTML Embed Code: