Telegram Web Link
መነሻው ፍርሃት ነው!

ከማንኛውም አሉታዊ ስሜታችሁ (negative emotions) ጀርባ የፍርሃት ስሜት እንዳለ ታውቃላችሁ?

ከማንኛው የፍርሃት ስሜት ጀርባ ደግሞ አንድ ነገር አጣለሁ የሚል ፍርሃት እንዳለስ ታውቃላችሁ?

ለምሳሌ፣ የመገፋት አሉታዊ ስሜት ካለ ከዚያ ጀርባ፣ ሰዎች ትተውኝ ብቻዬን እቀራለሁ ወይም የአንድን ሰው ወዳጅነት አጣለሁ የሚል ፍርሃት አለ፡፡

በስሜት ብልህነት የመብሰል አንደኛው ጥቅም አሉታዊ ስሜቶቻችንን በተገቢ ሁኔታ የመያዝንና ፍርሃቶቻችንን ለጥቅም የማዋልን ብስለት ማግኘት ነው፡፡

ይህንን እውነታ በሚገባ ስንገነዘበው ፍርሃትን ራሱን መፍራት እናቆምና የፍርሃቶቻችንን ምንጫቸውን በመለየት እና በመጋፈጥ ማሸነፍ እንጀምራለን፡፡

“የስሜት ብልህነት” በሚል ርእስ ስር ያዘጋጀሁላችሁ ስልጠና ይህንንና ሌሎች ተዛማጅ ስሜት-ነክ ሁኔታዎችን በሚገባ ያስረዳችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍707🔥7
🎺🎺🎺 ቅናሻችን አምልጧችሁ የነበረ  ደንበኞቻችን በዲያስፖራ ቁጥር 2 ሳይታችን ልንክሳችሁ መጥተናል


65,000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር

📣60% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

⚡️Aluminium form work Technology 24 ሰዓት እየተሰራ ያለ

👉ቅድመ ክፍያ ከ 8% ጀምሮ

💥2 ከርሰ ምድር ውሀ
💥standby generator
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥4 የ ሰው ሊፍት እና 1 የ እቃ መጓጓዣ
💥በቂ የመኪና ማቆሚያ ከ 3 እስከ 6 ቤዝመንት
💥5 መዋኛ ገንዳ የ ልጆች እና የ አዋቂ
💥የባስኬትቦል መጫወቻ
💥ቤተ መፃህፍት (library)
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ አዳራሽ
💥ዘመናዊ ለ እርድ የሚሆን ቦታ

ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉   ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ከነ መታጠቢያው ,ላውንደሪና  ስቶር ጋር

የተለያየ የካሬ አማራጭ:-

📌 ስቱዲዮ(studio)
        56.60 ካሬ
📌 ባለ አንድ መኝታ
         77.70ካሬ , 69 ካሬ ,85ካሬ, 98ካሬ
📌  ባለ ሁለት መኝታ
        99ካሬ,123ካሬ,128ካሬ እና 148.20 ካሬ
📌 ባለ ሶስት መኝታ
      118ካሬ,104ካሬ,123ካሬ, 139ካሬ, 146ካሬ,151ካሬ, 157ካሬ
📌 ባለ አራት መኝታ
       170ካሬ እና 186ካሬ



👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች 

✉️ ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን በDHL የቤት ባለቤት መሆን ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለሳይት ጉብኝት በ ☎️ +251929928392 ይደውሉልን
Telegram @BetelZewelde
👍204
ጤናማው እና ጤና-ቢሱ ስህተቶች!

አንድን አዲስ ነገር ያለመሞከር ስህተት ከምንሰራ፣ ሞክረን ስህተትን ብንሰራ ተመራጭ ነው፡፡

አንድን አዲስን ነገር እንዳንሞክር የሚደርጉን ተጽእኖዎች ብዙ ናቸው፡፡

• የመሳሳት ፍርሃት

• ሰዎች ምን ይሉኛል የሚል ፍርሃት

• ጀምሬ ባልቀጥለውስ የሚልፍ ፍርሃት እና ሌሎችም!

አዳዲስ ነገሮችን ከመጀመር ውጪ አዳዲስ እድገቶች ውስጥ ልንገባ አንችልም፡፡ ስለሆነም፣ አዲስን ነገር አለመጀመር በራሱ ስህተት ነው፡፡

ለዚያውም ጀምረን ክምንሳሳተው ስህተት የላቀ ስህተት!

ተነሳሱ! አስቡ! አቅዱ! ጀምሩ! የጀመራችሁትን ደግሞ ጥጉ ድረስ ውሰዱት! ስትሳሳቱ ደግሞ ከስህተታችሁ ተማሩና እንገና ቀጥሉ፡፡

ከዚህ ጤናማ ሂደትና ውጪ እድገት የለም!

ከዚህ ጤናማ ሂደት እና ስህተት ውጪ ያለ ሕይወት በራሱ የስህተት ሕይወት ነው!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍9231
22👍17
እድሎች አንዳንዴ ይመጣሉ አንዳንዴ ደግሞ ይፈጠራሉ!
👍154
እድሎች አንዳንዴ ይመጣሉ አንዳንዴ ደግሞ ይፈጠራሉ!

እድል የተሰኘው ሃሳብ ትክክለኛ እና የተዛባ ትርጓሜ ልንሰጠው እንችላለን፡፡

1. የተዛባው አመለካከት

ማንኛውም ነገር በእድል ወደ እኛ ካልመጣ በስተቀር ምንም ነገር ማድረግም ሆነ ማከናወን እንደማንችል ማሰብ የእድል የተዛባ ትርጓሜ ነው፡፡

ይህ አይነቱ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሌሎችን ስኬትና መልካም ጎን ይመለከቱና እነዚያ ሰዎች እድለኞች እንደሆኑ፣ እነሱ ግን እድለ-ቢስ እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ ከዚህ አስተሳሰብ የተነሳ፣ በአንድ በኩል “እድለኛ ስላልሆንኩኝ እድሜዬን ሙሉ በዚህ ሁኔታ ነው የማሳልፈው” በማለት ይቀመጣሉ፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች ሕይወት የእድለኞችና የእድለ-ቢሶች መስክ እንደሆነች ስለሚያስቡና ራሳቸውንም እድለ-ቢስ አድርገው ስለሚቆጥሩ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይኖራሉ፡፡

በተጨማሪም፣ አንዳንድ እነሱ ያልለፉባቸው ሁኔታዎች ሲገጥሟቸውም የተዘጋጀ ማንነትና አመለካከት ስለሌላቸው ገጠመኞቹን ወደ እድል የመቀየሩ አቅም የላቸውም፡፡

2. ትክክለኛው አመለካከት

ማንኛውንም ነገር ለማግኘት ከእኛ የሚጠበቀውን ነገር ማድረግ እንዳለብን በመገንዘብ መንቀሳቀስና መስራት የእድል ትክክለኛ ትርጓሜ ነው፡፡

ይህ አይነቱ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሌሎችን ስኬትና መልካም ጎን ይመለከቱና እነዚያ ሰዎች ምን ቢያደርጉ እዚያ ደረጃ ላይ እንደደረሱ በማጥናትና ምሳሌያቸውን እንደ መነሳሻ ነጥብ በመጠቀም ተግተው ይሰራሉ፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች የስራቸውንና የልፋታቸውን ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም፣ አንዳንድ እነሱ ያልለፉባቸው ሁኔታዎች ሲገጥሟቸውም የውስጥ ዝግጁነት ስላላቸው ገጠመኞቹን ወደ እድል ይቀይሯቸዋል፡፡

“እድል ማለት ገጠመኝና ዝግጁነት ሲገጣጠሙ” ማለት ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

ራሳችሁን በጥሩ የስነ-ልቦና ብቃት አዘጋጁ!

ራሳችሁን በአንዳንድ ክህሎቶች አዘጋጁ!

ራሳችሁን በጥሩ ዲሲፕሊን አዘጋጁ!

እንደዚህ ስታደርጉ በእውነትም እናንተ እድለኞች ናችሁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
83👍72🔥3😱1
የስሜት ብልህነት ማለት ምን ማለት ነው?

የአእምሮ ብልህነት ማለት ምን ማለት ነው?

በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነትና ልዩነት ምንድን ነው?

የስሜት ብልህነት በስኬታማነታችን ላይ የላቀ መዋጮ አለው የሚባለው ለምንድን ነው?

የስሜት ብልህነትን እንዴት ማዳበር ይቻላል?

የተጠቀሱትንና ተጨማሪ ጥያቄዎችን በሰፊው የሚመልስ ስልጠና ተዘጋጅቷል፡፡

የስልጠው ርእስ፡-
“የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍328🤩2
🎺🎺🎺 ቅናሻችን አምልጧችሁ የነበረ  ደንበኞቻችን በዲያስፖራ ቁጥር 2 ሳይታችን ልንክሳችሁ መጥተናል


65,000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር

📣60% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

⚡️Aluminium form work Technology 24 ሰዓት እየተሰራ ያለ

👉ቅድመ ክፍያ ከ 8% ጀምሮ

💥2 ከርሰ ምድር ውሀ
💥standby generator
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥4 የ ሰው ሊፍት እና 1 የ እቃ መጓጓዣ
💥በቂ የመኪና ማቆሚያ ከ 3 እስከ 6 ቤዝመንት
💥5 መዋኛ ገንዳ የ ልጆች እና የ አዋቂ
💥የባስኬትቦል መጫወቻ
💥ቤተ መፃህፍት (library)
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ አዳራሽ
💥ዘመናዊ ለ እርድ የሚሆን ቦታ

ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉   ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ከነ መታጠቢያው ,ላውንደሪና  ስቶር ጋር

የተለያየ የካሬ አማራጭ:-

📌 ስቱዲዮ(studio)
        56.60 ካሬ
📌 ባለ አንድ መኝታ
         77.70ካሬ , 69 ካሬ ,85ካሬ, 98ካሬ
📌  ባለ ሁለት መኝታ
        99ካሬ,123ካሬ,128ካሬ እና 148.20 ካሬ
📌 ባለ ሶስት መኝታ
      118ካሬ,104ካሬ,123ካሬ, 139ካሬ, 146ካሬ,151ካሬ, 157ካሬ
📌 ባለ አራት መኝታ
       170ካሬ እና 186ካሬ



👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች 

✉️ ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን በDHL የቤት ባለቤት መሆን ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለሳይት ጉብኝት በ ☎️ +251929928392 ይደውሉልን
Telegram @BetelZewelde
👍181😱1
አቅም ያጣ ማንነት


“ማድረግ ያለብኝን ትክክለኛው ውሳኔና እርምጃ አውቀዋለሁ፣ ያንን ማድረግ ግን አልችልም” ሲሉ የሚደመጡ ሰዎች ቁጥራቸው እየተበራከተ ነው፡፡

ይህ አቅም የማጣት ስሜት ከብዙ ነገሮች ጋር ሊገናኝ ይችላል፡፡ ይህ አይነቱ ችግር እንዳለባችሁ ካሰባችሁ “የአቅም ግንባታ” ስራ መጀመር ተገቢ ነው፡፡


አቅም ያጣ ማንነት አንዳንድ ምልክቶች . . .

- አንድ ሰው በንግግሩም ሆነ በሁኔታው ጥቃት እያደረሰብንና እየጎዳን እንደሆነ በሚገባ እያወቅነው እንኳን ከዚያ ሰው መለየት አለመቻል፡፡

- አንድ ነገር የግል መስመራችንን የሚጥስ እንደሆነ እያወቅን እምቢ ማለት ወይም ማስቆም አለመፈለግ ወይም መፍራት፡፡

- አንድ ጎጂ ልምምድ በአመለካከታችን፣ በጤንነታችንም ሆነ በስኬታማነታችን ላይ ችግር እንደሚያስከትል እያወቅን ለማቆም አለመፈለግ ወይም እየፈለጉ አለመቻል፡፡

- በሕይወታችን የሆኑትን ያለፉ ነገሮች መልሰን መቀየር እንደማንችል እያወቅነው እንኳን እሱን ሲያወጡና ሲያወርዱ ከመክረም ሃሳባችንን መግታት አለመቻል፡፡

- የዛሬው የሕይወታችን ሁኔታ ምን ብንሰራና ብናደርግ ሊቀየር እንደሚችል እያወቅነው እንኳን እርምጃን መውሰድ አለመቻል፡፡


ነቃ በሉ! ጎብዙ! ሆን ብለው በመስራት ራሳቸውን ከቀየሩት ሰዎች ማሕበር ተቀላቀሉ! ትችላላችሁ!

 

https://www.tg-me.com/Dreyob


https://m.youtube.com/user/naeleyob623


https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍11736
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የስልጠና እድል!

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
👍59
ፈጥኖ ፈራጅ!
የመላ-ምት ኑሮ
👍6
ፈጥኖ ፈራጅ!
የመላ-ምት ኑሮ


የምንኖርበት ዘመን ለፍርድ የሚቸኩል ትውልድ እንደጉድ የፈላበት ዘመን ነው፡፡ ሃሳብ ሰጪው ብዙ ነው፡፡ በመረጃ ብቻ ድምዳሜ ላይ የሚደርሰው ሰው ብዙ ነው፡፡

አንድ ዳኛ የአንድን ክስ መሰረታዊ መነሻ፣ እንዲሁም ግራና ቀኙን አይቶ እውነታ ጋር በመድረስ ለፍርድ ሊዘጋጅ ሲገባው ገና በሰማውና ባየው ብቻ ፍርድን ካስተላለፈ በኋላ ክስንና የግራ-ቀኝ ክርክር ልስማ ቢል እንደ እብድ ይቆጠራል፡፡ በመላ-ምት የሚኖር ሰውም እንዲሁ ነው፡፡

ጭፍንነት የተሞላበት መላ-ምት ከምክንያታዊነት ይልቅ ስሜታዊነትን፣ በአእምሮ ከመመራት ይልቅ በደመ-ነፍስ መነዳትን የሚያስቀድም ሰው አንዱ ምልክት ነው፡፡

የአንድን ሰው ተግባር ወይም የአንድን ሁኔታ ጅማሬ ገና ከማየታቸውና ከመስማታቸው ወዲያው ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የሚቸኩሉ ሰዎች የመላ-ምት ሰዎች ናቸው፡፡

እውነታውን እስከሚያረጋግጡ ድረስ ለመቆየት ትእግስት የሌላቸው እንደዚህ አይነት ሰዎች ከአንድ ነገር መሰረት ሳይሆን ከሰሙት ታሪክ ወይም ከደረሳቸው ማስረጃ-ቢስ መረጃ በመነሳት ደምድመው የሚነሱ ሰዎች ናቸው፡፡

እውነታውን እስከሚያረጋግጡ ድረስ ለመቆየት ትእግስት የሌላቸው እንደዚህ አይነት ሰዎች ከነገር መጀመሪያው ሳይሆን ከድምዳሜው የሚነሱ ሰዎች ናቸው፡፡

የመላ-ምት ሰው ራሱ በቀውስ ውስጥ ኖሮ በዙሪያው ያሉትንም ሰዎች ቀውስ ውስጥ የሚጨምር ሰው ነው፡፡

የመላ ምት ሰው ነህ? ራስህን መዝነው

1. የሰዎችን ተግባር አይተህ ያንን ያደረጉበትን የመነሻ ሃሳብ በመገመት የመናገር ልማድ አለብህ?

2. ከሰዎቹ ሳትሰማ ስለሰዎቹ በሰማኸው ነገር ብቻ በመነዳት ስለ እነሱ አመለካከትን ትቀርጻለህ?

3. አመለካከትህና ውሳኔህ ብዙ ጊዜ በሰዎች ወሬ ተጽአኖ ስር ሲወድቅ ታገኘዋለህ?

4. ስለ አመለካከትህና ስለተገባሮችህ ሁኔታ ነገሮችን ግልጽ ከማድረግ ይልቅ ሰዎቹ ገምተው ይደርሱበታል የሚል እምነት አለህ?

5. ሰዎች ባልጠበከው ስለ አንተ ሁኔታ ሲገምቱ ስለሁኔታህ ምንም ማብራሪያ ሳታደርግ እንዲሁ፣ “እንዴት አይገነዘቡኝም” የሚል አመለካከት አለህ?

6. የነገሮችን መደጋገም አይተህ የሚቀጥለው ሁኔታ ከድግግሞሹ ውጪ የተለየ ሊሆን እንደማይችል ታስባለህ?

7. በቋንቋና በባህል ከአንተ ከሚለይ ሰው ጋር በሚገባ ካልተግባባህ ትበሳጫለህ?

8 የሰዎችን ሁኔታ ካየህ በኋላ እንዲሁ የማመን ወይም የመጠራጠር ዝንባሌ አለህ?

9. ሰዎች እንዲሁ እንዲያምኑህ ትጠባበቃለህ?

10. ሰዎች እንዲሁ ካላመኑህ ትበሳጫለህ?

ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ በዚህ ምእራፍ ለተጠቀሱት ነጥቦች አስፈላጊ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡

መፍትሄው

1. የሰዎችን ሁኔታ ገና እንዳየን ወይም እንደሰማን ለድምዳሜ (conclusion) አለመቸኮል፡፡

2. መረጃ ሲደርሰን ምንም ነገር ከመወሰናችን በፊት ማሰረጃን እስከምናገኝ ድረስ ጊዜን መስጠት፡፡

3. በማሕበራዊ ሚዲያም ሆነ ባሉን የሰው-ለሰው ግንኙነቶች ከስሜታዊ comment ሰጪነት መቆጠብ፡፡

4. እኛን በማይመለከቱ ነገሮች ላይ ዝምታን መምረጥ፡፡

5. ሙሉ ታሪኩንና አመጣጡን (background) በማናውቅ ነገር ላይ የከረረ አቋም ከመያዝ መቆጠብን መለማመድ፡፡

እነዚህን የጨዋ ሰው ልምምዶች የምትለማመዱበት ቀን ይሁንላችሁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob


https://m.youtube.com/user/naeleyob623


https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍11527😱2
ከአሉታዊው ወደ አዎንታዊው!

አሉታዊ (negative) አመለካከት በፍጹም አዎንታዊ (positive) ሕይወት ሊሰጣችሁ አይችልም! ስለዚህ፣ ዝም ብላችሁ ሊበላሹ ስለሚችሉት ሁኔታዎች እንዲሁ መጨነቅ አቁሙና ሊሳካ ስለሚችለው ነገር በማሰብ ስሩ፡፡

አሉታዊ (negative) ሃሳቦችን እንደማንቂያ ደውል ተጠቀሙባቸው እንጂ በፍጹም ወደ አመለካከት (mindset) እና የሕይወት ዘይቤ (lifestyle) እንዲለወጡ አትፍቀዱላቸው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob


https://m.youtube.com/user/naeleyob623


https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
48👍14
በስሜት ብልህነት መብሰል የሚሰጣች መፍትሄ!

• አንድ ነገር ለመጀመር ካባችሁ ለነገ የማስተላለፍ ልመድ የመውጣት ተነሳሽነት!

• አንድን ነገር ከጀመራችሁ በኋላ ከማቆም ልማድ በመላቀቅ እስከ ፍጻሜ መውሰድ!

• ከሰዎች ጋር ያላቸሁን ግንኙነት በተረጋጋ ስሜት የመያዝ ብቃት!

• ስህተትን ወደ ውድቀት ሳይሆን ወደ ስኬት የመለወጥ አቅም!

• በሰዎች ተቀባይነትና መወደድ አገኛችሁም አላገኛችሁም ዓላማችሁ ላይ የማተኮር ጥንካሬ!

• ከሰዎች ጋር ሆናችሁም አልሆናችሁም ከራሳችሁ ጋር የመኖር መደላደል!

• በየጊዜው ከሚገጥማችሁ የስሜት መዛባት የመውጣት ብርታት!

እነዚህና መሰል ጤናማ ልምምዶችን ለማዳበር ከፈለጋችሁ በስሜት እና በማሕበራዊ ብልህነት የመብሰል ሁኔታ ላይ መስራት ይኖርባችኋል፡፡

ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ በቀረበላችሁ ፖስተር ላይ ያለውን መረጃ ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ በረጃ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox በማድረግ ጥያቄያችሁን መላክ ትችላላችሁ፡፡

@DrEyobmamo
👍6015🔥5🎉3
🎺🎺🎺 ቅናሻችን አምልጧችሁ የነበረ  ደንበኞቻችን በዲያስፖራ ቁጥር 2 ሳይታችን ልንክሳችሁ መጥተናል


65,000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር

📣60% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

⚡️Aluminium form work Technology 24 ሰዓት እየተሰራ ያለ

👉ቅድመ ክፍያ ከ 8% ጀምሮ

💥2 ከርሰ ምድር ውሀ
💥standby generator
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥4 የ ሰው ሊፍት እና 1 የ እቃ መጓጓዣ
💥በቂ የመኪና ማቆሚያ ከ 3 እስከ 6 ቤዝመንት
💥5 መዋኛ ገንዳ የ ልጆች እና የ አዋቂ
💥የባስኬትቦል መጫወቻ
💥ቤተ መፃህፍት (library)
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ አዳራሽ
💥ዘመናዊ ለ እርድ የሚሆን ቦታ

ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉   ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ከነ መታጠቢያው ,ላውንደሪና  ስቶር ጋር

የተለያየ የካሬ አማራጭ:-

📌 ስቱዲዮ(studio)
        56.60 ካሬ
📌 ባለ አንድ መኝታ
         77.70ካሬ , 69 ካሬ ,85ካሬ, 98ካሬ
📌  ባለ ሁለት መኝታ
        99ካሬ,123ካሬ,128ካሬ እና 148.20 ካሬ
📌 ባለ ሶስት መኝታ
      118ካሬ,104ካሬ,123ካሬ, 139ካሬ, 146ካሬ,151ካሬ, 157ካሬ
📌 ባለ አራት መኝታ
       170ካሬ እና 186ካሬ



👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች 

✉️ ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን በDHL የቤት ባለቤት መሆን ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለሳይት ጉብኝት በ ☎️ +251929928392 ይደውሉልን
Telegram @BetelZewelde
👍27
የራሳችን ሩጫ እና ግብ ጉዳይ!
9👍1🔥1
የራሳችን ሩጫ እና ግብ ጉዳይ!

የራስን ግብ ከሌላው ሰው ግብ ጋር ማስተያየት ኋላ ቀርነትን ያስከትላል! የሌሎች ሰዎች እይታ፣ ፍላጎት፣ የውስጥ ግለትና ሌሎች ወሳኝ ነገሮች ከእኛ እጅግ ያነሱ ሆነው ከተገኙ በዚያ ሰው ገደብ እኛም ተገደብን ማለት ነው፡፡

የራስን ጤንነት ከሌላው ሰው ጤንነት አንጻር መመዘን እንዴት አደገኛ ነገር ነው! አልጋው ላይ ተኝቶ ሞቱን የሚጠብቀውን ሰው አይተን ቆመን መሄዳችንን እንደ ሙሉ ጤንነት ከቆጠርከው አደገኛ ንጽጽር ውስጥ ነው ያለነው (ስለዚያ ሰው የማዘናችንና እኛም ስላለንበት የተሻለ ሁኔታ ሊኖረን የሚገባ ፈጣሪን አመስጋኝነት እንደተጠበቀ ሆኖ)፡፡

የራስን ደረጃ ሌላው ሰው ከደረሰበት ደረጃ አንጻር ብቻ መመዘን ኋላ ቀርነትን ያስከትላል! ስኬታማና መስመር ውስጥ የገባ ሕይወት የመመዘኛችን ሁኔታ አንጻራዊ ሲሆን እጅግ አደገኛ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ የራሴን ደረጃ ከገባኝ ነገርና ካወጣሁት ግብ አንጻር ሳይሆን ሌላው ሰው ካለበት ሁኔታ ጋር ብቻ ካነጻጸርኩት ያለሁበትንና የምሄድበትን የማላውቅ ግራ የተጋባሁ ሰው ነኝ፡፡

ትኩረቴን የሳበው እኔ ወዳየሁትና “መድረስ አለብኝ” ወዳልኩት ከፍታ የመገስገሴ ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ ማን ምን ደረጃ ደረሰ የሚለው ጉዳይ ከሆነ ከወዲሁ የተሸነፍኩ ሰው ነኝ፡፡

የሌላውን ሰው ልህቀት ለእኛ እንደመነሳሳሻ እንጂ የወደፊ እምቅ ብቃታችን መመዘኛ አናድርገው፡፡

የሌላውን ሰው ኋላ ቀርነት ለእኛ መማሪያ እንጂ ባለንበት ደረጃ የመርኪያ ምክንያት አናድርገው፡፡

አቻችን ነው ብለን በምናስበው ሰው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያለን አመለካከት ስላስቀመጥነው ግብና መድረስ ስለምንችልበት ደረጃ ብዙ እንደሚያወራ አንዘንጋ፡፡

የራሳችንን ራእይ፣ ዓላማ፣ ግብና ደረጃ እናውጣና በዚያ ልክ እንሩጥ!!!

https://www.tg-me.com/Dreyob


https://m.youtube.com/user/naeleyob623


https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
45👍24😱2
ስሜት እንደ ኳስ!

የስሜት ቋሚ ባህሪው ሁል ጊዜ የመለዋወጡ ጉዳይ ነው!

ስሜት ማለት በድንጋያማ (ኮረኮንች) ቦታ ላይ ኳስን እንደማንጠር ነው፡፡ ኳሱን ባነጠርነው ቁጥር አቅጣጫው እንደሚቀያየርና አቅጣጫው እንደማይታወቅ ሁሉ፣ የየእለት ስሜታችንም እንዲሁ ነው፡፡ የብዙዎች ስህተት በዚህ ተለዋዋጭ የስሜት ሁኔታ የመነዳት ስህተት ነው፡፡

ማድረግ የምንችለው . . .

• ስሜት ሲለዋወጥ ከዚያ ጋር አብሮ የማይለዋወጥ ዓላማ!

• ስሜት ሲቀያየር ከዚያ ጋር አብሮ የማይቀያየር መርህ!

• ስሜት ከፍና ዝቅ ሲል ከዚያ ጋር አብሮ ከፍና ዝቅ የማይል የራስ-በራስ ዋጋ!

• ስሜት ወዲህና ወዲያ ሲል ትኩረቱን የማይለቅ አመለካከት!

መያዝ ነው!

ይህ ብዙዎችን የሚያታግል የሕይወት ዘይቤ ግን እንዲሁ አይመጣም፡፡ በስሜት ብልህነት ለመብሰል ራስን ማሰልጠንን ይጠይቃል፡፡

ስለተዘጋጀላችሁ ስልጠና ለማወቅ ፖስተሩን ይመልከቱ!

ለበለጠ በረጃ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox በማድረግ ጥያቄያችሁን መላክ ትችላላችሁ፡፡

@DrEyobmamo
64👍43
👍14
መስቀለኛው መንገድ
👍175🎉2
2025/07/13 01:15:55
Back to Top
HTML Embed Code: