Telegram Web Link
የወደፊቱን አስመልክቶ ራእይ እና ሕልም የሌለው ሰው ሁል ጊዜ ወደ ትናንትናው የመመለስ ዝንባሌ አለው፡፡

የትናንትናው ስኬት ባላችሁት እንድትቆሙ ሲያደርጋችሁ፣ ያለፈው ስህተት ደግሞ በጸጸት እንድቶኖሩ ይጎትታችኋል፡፡

ራእያችሁና ሕልማችሁ ላይ ስሩ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
66👍41🔥2🎉1🤩1
እውነታን አምኖ የመቀበል (acceptance) አስፈላጊነት!

አንዳንድ ሰዎች የተነሳሳና ስኬታማ ሕይወት ማለት ያሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታ እንደሌለ መካድ ይመስላቸዋል፡፡

ይህ አመለካከት ጊዜያዊ የሆነ “ደህና” የመሆን ስሜት ቢሰጠንም የችግራችንን ስር መሰረቱን ግን አይፈታውም፡፡

• ያላችሁበትን ደስ የማይል የስሜት ሁኔታ አትካዱት፣ ነገር ግን ከሁኔታው ልትወጡ እንደምትችሉ ተስፋችሁን አትጣሉ፡፡

• ያላችሁበትን የኢኮኖሚ ትግል አትካዱት፣ ነገር ግን ለውጥ ለማምጣት አቅዱና ስሩ፡፡

• ያላችሁበትን በተለያዩ ምርጫዎች መካከል የመወላወል ሁኔታ አትካዱት፣ ያሏችሁን ምርጫዎች በትኖ በማየትና ምክር በመቀበል መወሰን ላይ ስሩ፡፡

• አጠገባችሁ ካሉ ሰዎች ጋር አብሮ የመቀጠልን አስቸጋሪነት አትካዱት፣ ራሳችሁን በመለወጥና አቅማችሁን በማዳበር ግን አልፋችሁት መሄድ ላይ ስሩ፡፡

ያላችሁበትን ሁኔታ መቀበል ማለት ለሆነው፣ በመሆን ላይ ላለውና ወደፊትም ለሚሆነው ነገር ሃላፊነትን መውሰድ ማለት ነው፡፡

ይህ ሃላፊነት የመውሰድ ልምምድ ምንም አይነት መፍትሄ ለማምጣት የመጀመሪያው ደረጃ እና መነሻው ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍8821🔥13😁1😱1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የስልጠና እድል!

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
👍418🎉2
🎺🎺🎺 ቅናሻችን አምልጧችሁ የነበረ  ደንበኞቻችን በዲያስፖራ ቁጥር 2 ሳይታችን ልንክሳችሁ መጥተናል


65,000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር

📣60% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

⚡️Aluminium form work Technology 24 ሰዓት እየተሰራ ያለ

👉ቅድመ ክፍያ ከ 8% ጀምሮ

💥2 ከርሰ ምድር ውሀ
💥standby generator
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥4 የ ሰው ሊፍት እና 1 የ እቃ መጓጓዣ
💥በቂ የመኪና ማቆሚያ ከ 3 እስከ 6 ቤዝመንት
💥5 መዋኛ ገንዳ የ ልጆች እና የ አዋቂ
💥የባስኬትቦል መጫወቻ
💥ቤተ መፃህፍት (library)
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ አዳራሽ
💥ዘመናዊ ለ እርድ የሚሆን ቦታ

ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉   ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ከነ መታጠቢያው ,ላውንደሪና  ስቶር ጋር

የተለያየ የካሬ አማራጭ:-

📌 ስቱዲዮ(studio)
        56.60 ካሬ
📌 ባለ አንድ መኝታ
         77.70ካሬ , 69 ካሬ ,85ካሬ, 98ካሬ
📌  ባለ ሁለት መኝታ
        99ካሬ,123ካሬ,128ካሬ እና 148.20 ካሬ
📌 ባለ ሶስት መኝታ
      118ካሬ,104ካሬ,123ካሬ, 139ካሬ, 146ካሬ,151ካሬ, 157ካሬ
📌 ባለ አራት መኝታ
       170ካሬ እና 186ካሬ



👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች 

✉️ ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን በDHL የቤት ባለቤት መሆን ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለሳይት ጉብኝት በ ☎️ +251929928392 ይደውሉልን
Telegram @BetelZewelde
👍2313
ከሃሳባ ባሻገር

ቁጭ ብሎ በማሰብ የትም አይደረስም፡፡

የምናስባቸውን ነገሮች ተግባራዊ ወደሆኑ እቅዶች፣ እቅዶቻችንን ደግሞ እውነታ-ተኮር ወደ ሆኑና የቀን ገደባቸው የታወቁ ግቦች፣ ግቦቻችንን ደግሞ ወደ እንቅስቃሴ እያሳደግን መሄድ ትክክለኛው የስኬታማ ሰው ጉዞ ነው፡፡

ይህንን የስኬት መንገድ ለመከተል፣ በመጀመሪያ የተነሳንለትን ዋና ዓላማችንን ካወቅን በኋላ ለዚያ ዓላማ የሚመጥን ከፍተኛ ዲሲፕሊን ማዳበር የግድ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍8921
የዋጋ ስሌት

• አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ነገሩን ባትጀምሩት የምታጡትን እድልና ብትጀምሩት የሚያስከፍላችሁን ዋጋ ስሌት ስሩ፡፡

• አንድን ነገር ከማቆማችሁ በፊት በነገሩ በመቀጠልና ነገሩን በማቆም መካከል ያለውን የዋጋ ስሌት ስሩ፡፡

• ከአንድ ሰው ከመለየታችሁ በፊት በግንኙነቱ በመቆየትና ግንኙነቱን በማቋረጥ መካከል ያለውን የዋጋ ስሌት ስሩ፡፡

• ለአንድ የሰው ሁኔታ፣ ንግግርም ሆነ ተግባር ምላሽ ከመስጠታችሁ በፊት ዝም ብትሉ በሚያስከፍላችሁ ዋጋ እና ምላሽ ብትሰጡ በሚያስከፍላች ዋጋ መካከል ስሌት ስሩ፡፡

በአጭሩ፣ አንድን ነገር ካደረጋችሁ በኋላ ከማሰብ፣ በቅድሚያ አስባችሁ ማድረግ አትራፊ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍13524🔥12
በስሜት ውጣ-ውረድ ውስጥ ከሚያልፉት ሰዎች አንደበት

• አንድ ነገር አቅድና ለመጀመር ከነገ ነገ እያልኩ ሳስተላልፈው በዚያው ይቀራል፡፡

• አንድን ነገር በከፍተኛ ተነሳሽነት እጀምረውና ብዙ ሳልሄድ አቆመዋለሁ፡፡

• ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እጀምርና ግንኙነቱን የሚረብሹ አንዳንድ ስሜታዊነቶች ስለምገልጽ ግንኙነቱ አይቀጥልም፡፡

• ካለፈው ስህተቴ አልፎ መሄድ ስለሚያስቸግረኝ በጸጸት ውስጥ ነው የምኖረው፡፡

• ሰዎች በእኔ እንደተከፉ ካሰብኩኝ እረፍት አጣለሁ፡፡

• ሁል ጊዜ ባላጠፋሁትም ነገር ቢሆን ይቅርታ ስጠይቅ ራሴን አገኘዋለሁ፡፡

• ለብቻዬ ስሆን የሚሰማኝን ስሜት ስለማልወደው ሁል ጊዜ በአካል ወይም በማሕበራዊ ሚዲያ ከሰዎች ጋር ማሳለፍ አለብኝ፡፡

• ከሰዎች ጋር ስሆን ምቾት ስለማይሰጠኝ ደስ ሳይለኝ በብቸኝነት አሳልፋለሁ፡፡

• ከአንድ አሉታዊ ስሜት ለመውጣት ብዙ ጊዜ ይፈጅብኛል፡፡

እነዚህና መሰል የስሜት ሁኔታዎች የሚያታግሏችሁ ከሆነ በስሜት እና በማሕበራዊ ብልህነት የመብሰል ሁኔታ ላይ መስራት ይኖርባችኋል፡፡

ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ በቀረበላችሁ ፖስተር ላይ ያለውን መረጃ ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ በረጃ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox በማድረግ ጥያቄያችሁን መላክ ትችላላችሁ፡፡

@DrEyobmamo
👍8016😢5😁4🔥3🎉1
🎺🎺🎺 ቅናሻችን አምልጧችሁ የነበረ  ደንበኞቻችን በዲያስፖራ ቁጥር 2 ሳይታችን ልንክሳችሁ መጥተናል


65,000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር

📣60% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

⚡️Aluminium form work Technology 24 ሰዓት እየተሰራ ያለ

👉ቅድመ ክፍያ ከ 8% ጀምሮ

💥2 ከርሰ ምድር ውሀ
💥standby generator
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥4 የ ሰው ሊፍት እና 1 የ እቃ መጓጓዣ
💥በቂ የመኪና ማቆሚያ ከ 3 እስከ 6 ቤዝመንት
💥5 መዋኛ ገንዳ የ ልጆች እና የ አዋቂ
💥የባስኬትቦል መጫወቻ
💥ቤተ መፃህፍት (library)
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ አዳራሽ
💥ዘመናዊ ለ እርድ የሚሆን ቦታ

ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉   ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ከነ መታጠቢያው ,ላውንደሪና  ስቶር ጋር

የተለያየ የካሬ አማራጭ:-

📌 ስቱዲዮ(studio)
        56.60 ካሬ
📌 ባለ አንድ መኝታ
         77.70ካሬ , 69 ካሬ ,85ካሬ, 98ካሬ
📌  ባለ ሁለት መኝታ
        99ካሬ,123ካሬ,128ካሬ እና 148.20 ካሬ
📌 ባለ ሶስት መኝታ
      118ካሬ,104ካሬ,123ካሬ, 139ካሬ, 146ካሬ,151ካሬ, 157ካሬ
📌 ባለ አራት መኝታ
       170ካሬ እና 186ካሬ



👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች 

✉️ ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን በDHL የቤት ባለቤት መሆን ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለሳይት ጉብኝት በ ☎️ +251929928392 ይደውሉልን
Telegram @BetelZewelde
👍192
አንድን ነገር አስር ሺህ ጊዜ!
👍152🤩1
አንድን ነገር አስር ሺህ ጊዜ!

ሆንግኮንግ/አሜሪካዊው ብሩስ ሊ (Bruce Lee) ታዋቂ አክተር፣ ብቁ የማርሻል አርት ባለሞያና አስተማሪ፣ እንዲሁም ስመ-ጥር ፈላስፋ ነበር፡፡ ይህ ሰው አንድ ጊዜ ስለስኬቱ ምስጢር እንዲህ ሲል ተደመጠ፣ “አስር ሺህ አይነት የተለያዩ የካራቴ ምቶችን በአንድ ቀን ከተለማመደ ሰው ይልቅ እኔ የምፈራው አንድን አይነት የካራቴ ምት አስር ሺህ ጊዜ ደጋግሞ የተለማመደን ሰው ነው”፡፡

አንድ ቀን ተነስተን የተለያዩ ነገሮችን ስለሞከርን የትም እንደማንደርስ አመልካች የሆነ ሃሳብ ነው፡፡ አስር ሺ አይነት ነገሮችን ከመሞካከር፣ ዓላማችንንና ግባችንን ከለየን በኋላ ያንን አንድን ነገር አስር ሺህ ጊዜ አድምተን ብንደጋግመውና ብንለማመደው ለምነገባበት ስኬት ወሰን አይኖረውም፡፡

የዚህ እውነታ ምስጢር ያለው በመነሳሳት (Motivation) እና በዲሲፕሊን (Discipline) መካከል ያለውን ልዩነት ነው፡፡ የተነሳሳን አንድ ቀን ከምናደርጋቸው አስር ሺህ የዘመቻ ስራዎች ይልቅ የያዝነውን አንድ ነገር በዲሲፕሊን አስር ሺህ ጊዜ ብንደጋግመው የተሻለ ውጤትን እናገኛል፡፡

በመነሳሳት (Motivation) እና በዲሲፕሊን (Discipline) መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግለን አንድ ነገር ቢኖር መመሪያ (Instruction) የተሰኘው ነገር ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ከአንዱ የመነሳሳትና የመነቃቃት (Motivation) ስብሰባ ወደሌላኛው ሲዳክሩ ከርመው አሁንም እዚያው እንደረገጡ የሚቀሩት፣ ከተነሳሱና ከተነቃቁ በኋላ በቂ መመሪያዎችንና መርሆችን ስለማያገኙና በዚያ ላይ በዲሲፕሊን ደጋግመው ስማይሰሩ ነው፡፡

በመነሳሳት የጀመርነውን አንድ ነገር መመሪያ አግኝተንበት በዲሲፕሊን መቀጠልን እስከምንለምድ ድረስ ስኬት የህልም እንጀራ እንደሆነ ይቀራል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍6521🎉1
ጅማሬው ቀጣይነቱን ይወስናል!
ላላገባችሁ . . .

የአሁን ፍቅረኛችሁ፣ የወደፊት የትዳር አጋራችሁ በሚሆንበት ጊዜ ግንኑነታችሁ ምን እንደሚመስል ከአሁኑ ለማወቅ ከፈለጋችሁ አንድን ጠቋሚ ነገር ላስታውሳችህ፡፡

በአጭሩ ወደ ፍቅር ግንኙነቱ የገባችሁበት መንገድም ሆነ የፍቅር ግንኙነቱ እንዲቆይ የተጠቀማችሁበት መንገድ የወደፊቱን ኑሯችሁን ጠቋሚ ነ፣ው፡፡

ወደ ፍቅር ግንኙነት የገባችሁትም ሆነ ግንኙነቱን ያቆያችሁት በልመናና በልምምጥ ከሆነ ከትዳር በኋላም በጋብቻ ለመቆየት መለመንና መለማመጣችሁ አንደማይቀር አትዘንጉ፡፡

ወደ ፍቅር ግንኙነት የገባችሁትም ሆነ ግንኙነቱን ያቆያችሁት በውሸትና በማታለል ከሆነ ከትዳር በኋላም በጋብቻ ለመቆየት መዋሸትንና ማታለልን እንደሚጠይቃችሁ አትርሱ፡፡

ወደ ፍቅር ግንኙነት የገባችሁትም ሆነ ግንኙነቱን ያቆያችሁት ምንም አይነት የራሳችሁ ሃሳብ ሳይኖርና ሁሉንም ውሳኔ የወሰነው ያኛው ወገን ሆኖ ከሆነ ከትዳር በኋላም የጋብቻውን ሁኔታ አስመልክቶ ሁሉንም ውሳኔ የሚያስተላልፈው ያኛው ወገን እንደሚሆን እወቁ፡፡

ጅማሬ ላይ የተጣመመ ግንኙነት ፈጽሞ አይቃናም ለማለት ባንችልም፣ ተጣምሞ የጀመረውን ግንኑነት ከትዳር በኋላ ለማቃናት ግን እጅግ እንደሚከብድና ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ዋጋ ከከፈላችሁ አይቀር አንደኛችሁን በፍቅር ጅማሬ ላይ የሚከፈለው ተከፍሎ የጋራ መተማመን፣ መከባበርና ጨዋነት የተሞላውን ግንኙነት መስርቱ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
118👍61
ምርጫችሁ የቱ ነው?

እኔ . . .

• ካልተሳኩልኝ ነገሮች ይልቅ የተሳኩልኝ ነገሮች ላይ ማተኮር መርጫለሁ!

• ከሚርቁኝ ሰዎች ይልቅ የሚቀርቡኝ ሰዎች ላይ ማተኮር መርጫለሁ!

• ከስህተቶቼ ይልቅ በሂደቱ ያገኘኋቸው ትምህርቶቼ ላይ ማተኮር መርጫለሁ!

• ከትናንትናው ታሪክ ይልቅ የነገው ተስፋ ላይ ማተኮር መርጫለሁ!

• ጉዞዬ ከሚያስከፍለኝ መስዋእትነት ይልቅ ነገ የሚከፍለኝ ዋጋ ላይ ማተኮር መርጫለሁ!

• ዛሬ ከሆንትና ከደረስኩበት ደረጃ ይልቅ ነገ ልሆንና ልድርስበት የምችለው ደረጃ ላይ ማተኮር መርጫለሁ!

• የምነቅፈውና የምቃወመው ሰው ላይ ከማተኮር ይልቅ የምቀበለውና የማበረታታው ሰው ላይ ማተኮር መርጫለሁ!

• መለወጥ በማልችላቸው ሁኔታዎች ላይ ከማተኮር ይልቅ ሰርቼ ለውጥ ማምጣት የምችላቸው ነገሮች ላይ ማተኮር መርጫለሁ!



https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
104👍56😢2🤩2
በስሜትእየበሰላችሁ ስትሄዱ

• ስለእናንተ ማን ምን እንደሚያስብ የመጨነቃችሁ ሁኔታ እየቀነሰ፣ እናንተው በራሳችሁ ላይ ስላላችሁ አመለካከት የመጠንቀቃችሁ መጠን እየጨመረ ይሄዳል፡፡

• በተለዋዋጭ ባህሪያቸው ምክንያት ከእናንተ እየራቁ ስለሚሄዱ ሰዎች የማሰላሰላችሁ ሁኔታ እየቀነሰ፣ ከእናንተ ጋር ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ላላቸው ሰዎች የማሰባችሁ ሁኔታ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

• ዛሬውኑ እጅ በእጅ ለምታገኙት ነገር የመሯሯጣችሁ ሁኔታ እየቀነሰ፣ ነገ እንዲበቅል ዛሬ የምትዘሩት ትጋታችሁ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

• ላይ ላዩን ስሜት ቀስቃሽ (sensational) ለሆነው ነገርና ንግግር ያላችሁ ፍላጎት እየቀነሰ፣ መርህ-ተኮርና ተግባራዊ በሆነው ነገር ላይ ያላችሁ ጉጉትና ትጋት እየጨመረ ይሄዳል፡፡

እግረ መንገዴን “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence) በሚል ርእስ በonline (telegram live)
ያዘጋጀሁላችሁ ስልጠና እንዳያመልጣችሁ ላስታውሳችሁ፡፡


መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍10946🔥3
ጉዞ ላይ ናችሁ!

ያላችሁበት ሁኔታና ቦታ የማይመች፣ አሰልቺ፣ ለእናንተ የማይመጥንና “ራሴን እዚህ ቦታ አገኘዋለሁ ብዬ አላስብም ነበር” የሚያሰኝ ቢሆንም፣ “እንኳን በዚያ ሁኔታ አለፍኩ” የምትሉበትን ሁኔታ መፍጠር ትችላላችሁ፡፡ ያንን ለመፍጠር ግን በጉዞ ላይ መሆን አለባችሁ፡፡

1. ትምህርት፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ የምታገኙትን ሁሉ ትምህርት ውሰዱ፡፡ አንዳንድ የሕይወት ትምህርቶች በሁኔታው ካላለፋችሁ በስተቀር በፍጹም አትማሯቸውም፡፡ አንድ ልምምድ ጎጂን የባከነ የሚሆነው ትምህርት ካልተገኘበት ብቻ ነው፡፡

2. ውሳኔ፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ ለመውጣት ተገቢውን ውሳኔ አድርጉ፡፡ ዋናው ነገር የላችሁበት ሁኔታ ሳይሆን በዚያ ላለመቆየት ያላችሁ ምርጫና ውሳኔ ጉዳይ ነው፡፡

3. እቅድ፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ የምትወጡበትን ተገቢውን እቅድ አቅዱ፡፡ ካላችሁበት ሁኔታ ለመውጣት መወሰን ለብቻው በቂ አይደለም፡፡ በሚገባ የታሰበበትና ተግባራዊ ሊሆን የሚችልን እቅድ ከጊዜ ገደብ ጋር ማስቀመጥ የግድ ነው፡፡

4. እንቅስቃሴ፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ ለመውጣ ተገቢውን እቅስቃሴ አድርጉ፡፡ ከትምህርቱ፣ ከውሳኔውና ከእቅዱ በኋላ፣ ባቀዳችሁት መሰረት ወቅቱን ጠብቃችሁ መንቀሳቀስ ከቻላችሁ የላቀ ማንነት ይዛችሁ መውጣታችሁ አይቀርም፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራዊ እውነታዎች ከተለማመዳችሁ ያላችሁበት ቦታ በእርግጥም የምትማሩበት፣ የምታድጉበትና ለነጋችሁ በስላች የምትወጡበት ትክክለኛ ሁኔታና ቦታ ይሆንላችኋል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍9536😱2
የስልጠና እድል!

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
👍253🎉1🤩1
🎺🎺🎺 ቅናሻችን አምልጧችሁ የነበረ  ደንበኞቻችን በዲያስፖራ ቁጥር 2 ሳይታችን ልንክሳችሁ መጥተናል


65,000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር

📣60% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

⚡️Aluminium form work Technology 24 ሰዓት እየተሰራ ያለ

👉ቅድመ ክፍያ ከ 8% ጀምሮ

💥2 ከርሰ ምድር ውሀ
💥standby generator
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥4 የ ሰው ሊፍት እና 1 የ እቃ መጓጓዣ
💥በቂ የመኪና ማቆሚያ ከ 3 እስከ 6 ቤዝመንት
💥5 መዋኛ ገንዳ የ ልጆች እና የ አዋቂ
💥የባስኬትቦል መጫወቻ
💥ቤተ መፃህፍት (library)
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ አዳራሽ
💥ዘመናዊ ለ እርድ የሚሆን ቦታ

ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉   ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ከነ መታጠቢያው ,ላውንደሪና  ስቶር ጋር

የተለያየ የካሬ አማራጭ:-

📌 ስቱዲዮ(studio)
        56.60 ካሬ
📌 ባለ አንድ መኝታ
         77.70ካሬ , 69 ካሬ ,85ካሬ, 98ካሬ
📌  ባለ ሁለት መኝታ
        99ካሬ,123ካሬ,128ካሬ እና 148.20 ካሬ
📌 ባለ ሶስት መኝታ
      118ካሬ,104ካሬ,123ካሬ, 139ካሬ, 146ካሬ,151ካሬ, 157ካሬ
📌 ባለ አራት መኝታ
       170ካሬ እና 186ካሬ



👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች 

✉️ ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን በDHL የቤት ባለቤት መሆን ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለሳይት ጉብኝት በ ☎️ +251929928392 ይደውሉልን
Telegram @BetelZewelde
👍192
እንደገና የመኖር እድል ባገኝ!

አንድ የሚከተሉትን የእድሜ ደረጃዎች ያለፈ ሰው ሁሉንም ነገር መለስ ብሎ ካሰበ በኋላ እንደዚህ አለ፡-

በ18 አመታችን ላይ ሁሉም ሰው አይኖቹ በእኛ ላይ እንዳለና ስለእኛ ብቻ የሚያስብ እየመሰለን እንጨነቃለን፡፡ አሁን ሳስበው፣ እንደገና የመኖር እድሉን ባገኝ፣ ሰዎች ስለእኔ ከሚያስቡት ነገር ይልቅ የበለጠ ተጽእኖ ያለው እኔው በራሴ ላይ ያለኝን አመለካከትና የወደፊት ዓላማዬን በሚገባ የመለየቴ ጉዳይ እንደሆነ በማሰብ በእሱ ላይ እሰራ ነበር፡፡

በ40 አመታችን ላይ ቀስ በቀስ ስለእኛ ማንም ሰው ምንም ነገር አሰበም አላሰበም ግድ ወደማይሰጠን አመለካከት መለስ እንላለን፡፡ አሁን ሳስበው፣ እንደገና የመኖር እድሉን ባገኝ፣ ስለሰው ግድ የለኝም በሚለው አመለካከት ተጋርጄ የተጽእኖ ሰው ከመሆን እንዳልገታ በወጣትነቴ ወደማወቅ በመጣሁት ማንነቴና ዓላማዬ ላይ በመገንባት የተጽእኖ ሰው እሆን ነበር፡፡

በ60 አመታችን ላይ ማንም ሰው ስለእኛ አስቦም ሆነ ትዝ ብሎትም እንደማያውቅ ወደማስተዋል ስለምንመጣ በሌለ ነገር ስንወዛገብ እንደኖርን በማሰብ ወደመራራነት እንወርዳለን፡፡ አሁን ሳስበው፣ እንደገና የመኖር እድሉን ባገኝ ሰዎች በእኔ ላይ የሚያስቡትና እኔው ራሴ በራሴ ላይ የማሰበው ነገር ሲታረቅና በሚዛናዊነት ሲያዝ ብቻ እኔም አርፌ፣ ለሌላውም ተርፌ መኖር እንደምችል በመገንዘብ ሚዛናዊ ሕይወት እኖር ነበር፡፡

ይህ ሰው ከራሱ ልምምድ አንጻርና በራሱ እይታ የነገረን ነገር ለሁላችንም ተመሳሳይ የሆነ ተግባራዊነት ሊኖረውም ሆነ ላይኖረው ቢችልም፣ ከምልከታው ግን በየእድሜ ደረጃችን ቅድሚያ ልንሰጣቸውና አስታርቀን በሚዛናዊነት ልንይዛቸው ስለሚገቡን ነገሮች ያስታውሱናል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob
👍10828😢4🎉2🤩2
የስሜት እና የማሕበራዊ ብልህነት

ማንኛውም የሰው ለሰውም ሆነ ማሕበራዊ ግንኙነታችን ከፍተኛ የሆነን ብስለት ይጠይቃል፡፡

ይህ ብስለት የስሜት እና የማሕበራዊ ብልህነት ተብሎ ይጠራል፡፡

የፍቅር ግንኙነታችን፣ የትዳር አጋርነታችን፣ የቤተሰብ ትስስራችን፣ የጓደኝነት ጉዟችንም ሆነ በስራም ሆነ በንግዱ መስክ ያለን ንክኪ ሁል ጊዜ ያላረፈና ለቀውስና ለውጣ-ውረድ የተጋለጠ ከሆነ በዚህ የብልህነት ዘርፍ ያለመብሰላችን ምልክት ነው፡፡

በስሜትና በማሕበራዊ ብልህነት ስናድግ የራሳችንን ስሜት በሚገባ ከመገንዘብና አያያዙን ከማወቅ አልፈን፣ የሌሎችን ሰዎችም ሁኔታ በሚገባ ማስተዳደርን እናውቅበታለን፡፡

በዚህ ዘርፍ ስንበስል በግንኙነቶቻችን ውስጥ ራሳችንን በሚገባ የመግለጥን ጥበብ እናዳብራለን፡፡

የሰዎች ሁኔታም ቢሆን ምንም እንኳን ቢያስቸግረንም፣ የአያያዙን መላ እያዳበርን እንሄዳለን፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ግንዛቤን ማዳበር የሚረዳችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

ለበለጠ ለመረጃ ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ የተለጠፈውን ፖስተር ይመልከቱ፡፡

ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link inbox ማድረግም ትችላላችሁ፡፡

@DrEyobmamo
38👍21🎉1
ከጥቃቅንና ደቃቃ አመለካከት መውጣት!
👍16
ከጥቃቅንና ደቃቃ አመለካከት መውጣት!

ከጥቃቅንና ከደቃቃ ነገሮችና አመለካከቶች እስምትወጡ ድረስ ወደ ትልልቅና የላቀ ነገር ውስጥ መግባት ያስቸግራችኋል፡፡
በየእለቱ የምታስቧቸውን፣ የምትናገሯቸውንና ራሳችሁን በጣልቃ-ገብነት የምታገኙበትን ሁኔታዎች ተመልከቷቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ጥቃቅን ከሆኑና ከአጠቃላይ የሕይወታች ዓላማና አቅጣጫ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ከሆኑ የወደፊታችሁ እጅጉን አሳሳቢ እንደሆነ ላስታውሳችሁ፡፡

በየእለቱ ማን ምን እንዳደረገ፣ ማን ከማን ጋር እንደታየ፣ ማን ከማን ጋር እንደ ተወዳጀና እደተፋቀረ፣ ማን ስለማን ምን እንዳሰበና እንደተናገረ፣ ማን ምን እንደገዛ፣ ማን ምን እንደለበሰ . . . ጥቃቅንና ደቃቃ አመለካከት ያለውን ሰው አእምሮና ንግግር ይዞና ወጥሮ የሚውለው ነገር ብዙ ነው፡፡

የወደፊት ሕይወታችሁ ትልቅ፣ የላቀና የማትጸጸቱበት እንዲሆን ከፈለጋችሁ ከእንደዚህ አይነት አናሳ አመለካከቶች መውጣት የግድ ነው፡፡

• ዓላማችሁንና እቅዶቻችሁን ተለቅ አድርጓቸው፡፡

• ለትልቁ ዓላማችሁ የሚመጥኑ መጻህፍትን አንብቡ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ተከታተሉ፡፡

• ለትልቁ ዓላማችሁ የሚመጥኑ፣ እነሱም ትልልቅ ነገር የሚያልሙና የሚያወሩ ጓደኞች ላይ አተኩሩ፡፡

• ጥቃቅን፣ ደቃቃ እና ዛሬ ተወርቶና ተደርጎ ለነገ ከማይሻገር ነገር ቀስ በቀስ ራሳችሁን አርቁ፡፡

• የምታወሯቸው፣ የምታደርጓቸውና ጊዜያችሁን የምታውሉባቸው ነገሮች ወይ ለእናንተ ወይም ለሌሎች ሰዎች እድገትና ጥቅም የመዋሉን ጉዳይ ማሰብ ልምዳችሁ አድርጉ፡፡


https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍10832🔥2😱1
2025/07/12 21:06:43
Back to Top
HTML Embed Code: