Telegram Web Link
ደጋግሞ ለምን እንደማይሳካልን!

አብዛኛውን ጊዜ የምንጀምራቸው ነገሮች የማይሳኩልን ከሆነ፣ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማጤን ተገቢውን ማስተካከያ እናድረግ፡፡

1. ጽናት ማጣት

ማንኛውንም በአንድ አቅጣጫ ስኬት ያገኘን ሰው ጠይቁ፣ የስኬት ጎዳና የፈተና ጎዳና ነው፡፡ የጀመርነውን ነገር በማድረግ ካልጸናን ስኬት የሚባል ነገር የለም፡፡

2. የጽኑ ፍላጎት እጦት

በአንድ በጀመርነው ነገር ዙሪያ ገና ከመጀመሪያው በጽኑ ፍጎት ካልተነሳን የመጣው እንቅፋት ሁሉ የማቆሚያ ምክንያት ስለሚሆነን እስኪሳካ ድረስ መቀጠል ያስቸግረናል፡፡

3. ምክንያት ማብዛት

በሕይወታችን ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ሙሉ ሃላፊነቱን ካልወሰድን፣ ሌሎችን ስንወቅስ ራሳችንን ስለምናገኘው ለችግሮች መፍትሄ የማግኘት ብቃታችን ይወሰዳል፡፡

4. ያለፉትን ስህተቶች መካድ

ከዚህ በፊት የሰራናቸውን ስህተቶች ለማስታወስ ከማፈራችን የተነሳ እንዳልተከናወኑ በማሰብ አይናችንን ስንጨፍን ከትምህርት ይልቅ ውድቀትን እናስተናግዳለን፡፡

5. ፍጸሜያችን ተወስኖ እንደተወለድን ማሰብ

አንዳንድ ሰዎች የሕይወታቸው አቅጣጫና ፍጻሜ ገና ሳይወለዱ እንደተመደበና ከዚያ ሁኔታ ንቅንቅ የማለት አቅም እንደሌላቸው ስለሚያስቡ የመጣውን ነገር ለመለወጥ ከመስራት ይልቅ እንዲሁ በመቀበል ያስተናግዱታል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍15044🔥3🎉1🤩1
ነጻ የስሜት ብልህነት ስልጠና!
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በሕይወታችን ከ80 በመቶው በላይ ስኬታማነታችንን የሚይዘው የአእምሮ ብልህነት (IQ - Intelligence Quotient) ሳይሆን የስሜት ብልህነታችን (EQ - Emotional Quotient) ነው፡፡

ይህ ማለት በስራው አለምም ሆነ በማሕበራዊው ስምሪታችን ብዙ እውቀት እያላቸው የስሜት ብልህነት ከጎደላቸው ሰዎች ይልቅ አናሳ እውቀት ይዘው ከፍተኛ የስሜት ብልህነት ያላቸው ሰዎች ልቀው ይገኛሉ፡፡

በዚህ እውነታ ላይ መሰረታዊውን ግንዛቤ እንድትጨብጡ የአንድ ምሽት ስልጠናን አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

ለዚህ የቴሌግራም ግሩፕ ተከታታዮቼ በሙሉ፡፡

ቀን - ኃሙስ የካቲት 20

ሰዓት - ማታ ከ2፡30 – 3፡30

የስልጠናው ርእስ - የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence)

ክፍያ - በነጻ!!!

ወዳጆቻችሁም ይህንን telegram channel join በማድረግ እንዲከታተሉ ጋብዟቸው፡፡

በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዚሁ ቻናል በመግባት ስልጠናውን live መከታተል ትችላላችሁ!
147👍69🔥7🤩5
የአፋልጉኝ ጩኸት!

የበፊቱ “እኔ” ስለጠፋብኝና ስለናፈቀኝ አፋልጉኝ!

• ደስተኛና ተጫዋች የነበረው “እኔ”!

• ብሩህና የሚገባው የነበረው “እኔ”!

• ፈገግተኛና ሳቂታ የነበረው “እኔ”!

• ሰዎችን ያምንና ይቀበል የነበረው “እኔ”!

• ያፈቅርና ይፈቀር የነበረው “እኔ”!

• በሰላም ይተኛና ይነሳ የነበረው “እኔ”!

• ለነገ ይጓጓና ዓላማ-መር የነበረው “እኔ”!

• ላመነበት እውነት ቆራጥና ጽኑ የነበረው “እኔ”!

• ልኩንና ሚዛኑን ያውቅ የነበረው “እኔ”!

• ራሱን ተቀብሎና ሆኖ ይኖር የነበረው እኔ!

ቀድሞ የነበረው አሁን ግን የጠፋብኝና እዚህ የሌለው ትክክለኛው እኔነቴ ናፈቀኝ!

• ሰውን ሁሉ በማስደሰት ለመኖር ስሯሯጥ የጠፋብኝ ማንነቴ!

• አንድ ሰው ስለተለየኝ ብቻ ኑሮ ያከተመለት ያህል በማሰብ የጠፋብኝ ማንነቴ!

• ስኬትን ፍለጋ ይህንና ያንን ስሞክር የጠፋብኝ ማንነቴ!

• የሰውን ሁሉ ሃሳብ ሳስተናግድ አንድም ቀን ራሴን ሳላዳምጥ የጠፋብኝ ማንነቴ!

• አብዛኛውን ጊዜዬን በአካል እንኳን ማንነታቸው ከማላውቃቸው ሰዎች ጋር በማሕበራዊ ሚዲያ ሳሳልፍ የጠፋብኝ ማንነቴ!

• ማንነቴን ወደመኖር ካመጣው ከፈጣሪዬ ጋር ያለኝን ግንኙነት ችላ በማለቴ የጠፋብኝ ማንነቴ!

ይመለስ!!!!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍23278😢31🔥7🎉4😱1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ነጻ የስሜት ብልህነት ስልጠና!
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በሕይወታችን ከ80 በመቶው በላይ ስኬታማነታችንን የሚይዘው የአእምሮ ብልህነት (IQ - Intelligence Quotient) ሳይሆን የስሜት ብልህነታችን (EQ - Emotional Quotient) ነው፡፡

ይህ ማለት በስራው አለምም ሆነ በማሕበራዊው ስምሪታችን ብዙ እውቀት እያላቸው የስሜት ብልህነት ከጎደላቸው ሰዎች ይልቅ አናሳ እውቀት ይዘው ከፍተኛ የስሜት ብልህነት ያላቸው ሰዎች ልቀው ይገኛሉ፡፡

በዚህ እውነታ ላይ መሰረታዊውን ግንዛቤ እንድትጨብጡ የአንድ ምሽት ስልጠናን አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

ለዚህ የቴሌግራም ግሩፕ ተከታታዮቼ በሙሉ፡፡

ቀን - ኃሙስ የካቲት 20

ሰዓት - ማታ ከ2፡30 – 3፡30

የስልጠናው ርእስ - የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence)

ክፍያ - በነጻ!!!

ወዳጆቻችሁም ይህንን telegram channel join በማድረግ እንዲከታተሉ ጋብዟቸው፡፡

በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዚሁ ቻናል በመግባት ስልጠናውን live መከታተል ትችላላችሁ!
142👍87😱3🎉3
ልክ ያጣው ጥበቃ!

የእናንተን የወደፊት ሕይወት በሚነካ ጉዳይ ላይ የሚወላውልና ያልወሰነን ሰው ከልክ ባለፈ መልኩ ስትጠባበቁ፣ ደግሞ የማይመለሰው ይህ እድሜ እና ከዚህ እድሜ ጋር አብሮ የመጣው እድል እንዳያልፋችሁ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
149👍58😱6😢4
ፍልሚያህን በጥበብ ምረጥ!
👍43
ፍልሚያህን በጥበብ ምረጥ!

“ፍልሚያህን በጥበብ ምረጥ፡፡ ሕይወት የምትመዘነው ብዙ ጊዜ ከሌሎች ጋር ለመፋለም በመቆምህ አይደለም፡፡ ደስተኛነትህ ያለው ባሸነፍከው የጦርነት ብዛት ሳይሆን ከመዋጋት ይልቅ ወደሌላ ወደተሻለ ነገር ፊትህን ለማዞር በወሰንካቸው ውሳኔዎች ብዛት ነው፡፡ ሕይወት እጅግ አጭር በመሆኗ በጦርነት ልታባክናት አይገባህም፡፡ እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑትን ጦርነቶች ብቻ መርጠህ በመዋጋት የቀሩትን ልቀቃቸው” - C. JoyBell C.

ከማን ጋር እየተፋለምክ ነው? ከምን ሁኔታ ጋር ጦርነት ጀምረሃል? ይህንን ጦርነት ለምን ጀመርከው በእልህ? ላለመበለጥ? ለበቀል? በአትንኩኝ ባይነት? ወሬ ሰምተህ?

አየህ፣ አንዳንድ ጊዜ የምንጀምራቸው ጦርነቶች ብናሸንፍም ሆነ ባናሸንፍ ምንም ፋይዳ የላቸውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የማሸነፍ ስሜት ከማግኘት ውጪ ምንም ነገር የማናተርፍባቸው ጦርነቶች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የማይሆን ጦርነት እንጀመርና የተሸነፍን ሲመስለን የመጨሻውን ድል ማስመዝገብ እንዳለብን ስለምናምን ሌላ የጦርነት መስክ እንከፍታለን፡፡

የማይሆን ጦርነት መዘዙ ብዙ ነው፡፡ የስሜት መባከን፣ የጊዜ መባከን፣ የገንዘብ መባከን . . . መባከን! ከዚህ በተጨማሪ፣ በማይሆን ጦርነት ላይ ሁሉን ነገር ስናስተባብር በጎን ብዙ ወዳጆቻችንን እንከስራለን፡፡ ምክንያቱም ይህንና ያንን አላስፈላጊ ጦርነቶች ለመዋጋት ጊዜን ስንወስድ፣ ወዳጅነትን ለመገንባት ልንወስድ ከምንችለው ጊዜ ላይ እየወሰድን ስለሆነ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎችና ሁኔታዎች እንኳ ለፍልሚያ ለምንም ነገር ጊዜ ሊሰጣቸው እንደማይገባ አትርሳ፡፡

ፍልሚያ ውስጥ ከመግባትህ በፊት መጠየቅ የሚገቡህ ጥያቄዎች፡-

1. ይህንን ፍልሚያ መፋለም ያለብኝ እኔ ነኝ?

2. ለዚህ ፍልሚያ ያነሳሳኝ ምንድን ነው?

3. ይህንን ፍልሚያ ብተወው ምን እጎዳለሁ?

4. ይህንን ፍልሚያ ከተፋለምኩ በኋላ ባሸነፍ የማገኘው ጥቅም ምንድን ነው?

5. ይህንን ፍልሚያ ከተፋለምኩ በኋላ ብሸነፍ የምጎዳው ጉዳት ምንድን ነው?

6. ለዚህ ፍልሚያ የምሰጠውን ጊዜ ወደሌላ ገንቢ ተግባር ባዞረው ምን መገንባት እችላለሁ?

በሁሉም ነገር ፍልሚያ ውስጥ አትግባ!!! ፍልሚያህን በጥበብ ምረጥ!!!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍14529🔥3
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ነጻ የስልጠና እድል!
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

ለዚህ የቴሌግራም ግሩፕ ተከታታዮቼ በሙሉ፡፡

ቀን - ኃሙስ የካቲት 20

ሰዓት - ማታ ከ2፡30 – 3፡30

የስልጠናው ርእስ - የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence)

ክፍያ - በነጻ!!!

ወዳጆቻችሁም ይህንን telegram channel join በማድረግ እንዲከታተሉ ጋብዟቸው፡፡

በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዚሁ ቻናል በመግባት ስልጠናውን live መከታተል ትችላላችሁ!
54👍16🤩3
በፊታችን ኃሙስ በ telegram live የምሰጠው ስልጠና የሚጠው በዚሁ ቻናል ሲሆን ከእናንተ የሚጠበቀው ከታች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ወደዚህ ቻናል በመምጣት ስልጠናው ሲጀምር join የሚለውን ምልክት በመጫን መቀላቀልና መሰልጠን ነው፡፡

ነጻ የስልጠና እድል! ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

👍14655🔥14
እንደተደበቀ የሚኖር ሕይወት

አንዳንድ ሰዎች የሚተኙት እረፍት ለማግኘት አይደለም፤ ካለባቸው የስሜት ስቃይ፣ ኃዘን፣ ድብርትና ይህችን አለም ለመጋፈጥ አቅም የማጣት ስሜት ለመደበቅ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ጓደኛም ሆነ ፍቅረኛ የሚይዙት የትክክለኛን ግንኙነት ጣእም ለማጣጣምና አብሮ ለማደግ አይደለም፤ ካለባቸው የብቸኝነት፣ ተቀባይነት የማጣትና ለብቻ የመቅረት ፍርሃት ለመደበቅ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ለሁሉም ሰውና ነገር “እሺ” በማለት ሁል ጊዜ ተባባሪና ተሳታፊ የሚሆኑት ያንን ማድረግ ደስታ ስለሚሰጣቸውና የሕይወታቸው መርህ ስለሆነ አይደለም፤ የራሳቸውን አመለካከት፣ ትክክለኛ የሆነውን ነገርና እነሱን ደስ የሚያሰኛቸውን ነገር ካደረጉ ሰዎች በእነሱ ላይ ሊኖራቸው ይችላል ብለው የሚያስቡትን አመለካከት ስለሚፈሩትና ከዚያ ለመደበቅ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ቀን-ከሌት ካለማቋረጥ በማሕበራዊ ግንኙነት እና በማሕበራዊ ሚዲያ ታጅበው የሚኖሩት በዚያ ሁኔታ ውስጥ የሚያከናውኑት አንድ ጠቃሚ ዓላማ ስላላቸው አይደለም፤ ከራሳቸው አመለካከትና መቀበል ካቃታቸው የራሳቸው ማንነትና ሁኔታ ለመደበቅ ነው፡፡

ከተደበቀባችሁበት ውጡ!

ትክክለኛውን የሕይወት መስክ ፈልጉና ድረሱበት!

ማንነታችሁን ተቀበሉ!

ያንንም ሕይወት በነጻነት ኑሩ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍20375😢11🤩5🔥4😱1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
በፊታችን ኃሙስ በ telegram live የምሰጠው ስልጠና የሚጠው በዚሁ ቻናል ሲሆን ከእናንተ የሚጠበቀው ከታች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ወደዚህ ቻናል በመምጣት ስልጠናው ሲጀምር join የሚለውን ምልክት በመጫን መቀላቀልና መሰልጠን ነው፡፡

ነጻ የስልጠና እድል! ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

ለዚህ የቴሌግራም ግሩፕ ተከታታዮቼ በሙሉ፡፡

ቀን - ኃሙስ የካቲት 20

ሰዓት - ማታ ከ2፡30 – 3፡30

የስልጠናው ርእስ - የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence)

ክፍያ - በነጻ!!!

ወዳጆቻችሁም ይህንን telegram channel join በማድረግ እንዲከታተሉ ጋብዟቸው፡፡

በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዚሁ ቻናል በመግባት ስልጠናውን live መከታተል ትችላላችሁ!
👍1048🎉6🤩1
ነጻ ስጦታዎች!

ምንጩን የማላስታውሰውና በወቅቱ አስተምሮኝ ያለፈ አባባል፡-

“እጅግ የላቀው ብልጽግና ጥበብ ነው፡፡ ጠንካራ የተባለው መሳሪያ ትእግስት ነው፡፡ አለ የተባለው ጥበቃ በፈጣሪ ላይ ያለን እምነት ነው፡፡ ፈዋሽ የተባለው መድሃኒት ሳቅ ነው፡፡ እጅግ አስገራሚ የሆነው እውነታ ደግሞ እነዚህ የጠቀስናቸው ሁሉም ነገሮች ሙሉ በሙሉ ነጻ መሆናቸው ነው"

እነዚህን ስጦታዎች ከተጠቀለሉበት ከፍተን እናውጣቸው! እንጠቀምባቸው!

መልካም እንቅልፍ ለሁላችሁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
159👍75🔥10😢2😁1😱1
ቀስ በቀስ የምታጡት ነገር!

አላግባብ የአስተዳደራችሁትን (manage ያላደረጋችሁትን ወይም mismanage ያደረጋችሁትን) ነገር ቀስ በቀስ ታጡታላችሁ፡፡

በእጃችሁ ያለው የገንዘብ መጠን በዛም አነሰም፣ በትክክል manage ካደረጋችሁት ትጠብቁታላች፣ ታባዙትማላችሁ፡፡ አለዚያ ግን ቀስ በቀስ ከእጃችሁ ይወጣል፡፡

የእኔ ናቸው የምትሏቸው ቤተሰቦች፣ ቀድሞውኑ (by default) የእናንተ ስለሆኑ ብቻ የትም አይሄዱም ብላችሁ ችላ ካላችኋቸውና ግንኙነታችሁን በትክክል manage ካላደረጋችሁት ትዳርም ሆነ የቅርብ ቤተሰብ ሁኔታ ቀስ በቀስ ከእጃችሁ መውጣት መጀመሩ አይቀርም፡፡

በነጻ የተሰጣችሁ ጤንነት የተሰኘውን የፈጣሪ ስጦታ፣ ስሜትን በሚገባ በመያዝ፣ በጥሩ አመጋገብ፣ በስፖርትና በበቂ እረፍት በትክክል manage ካላደረጋችሁት፣ በኋላ ካጣችሁት በኋላ ነው የምትባንኑት፡፡ አብዛኛው ጊዜ ደግሞ ስትባንኑ ሁኔታውን ለመቀልበስ ጊዜው አንዳለፈበት ትገነዘባላችሁ፡፡

የምትመሩትና የምታስተዳድሩት የሰው ኃይልም ሆነ ሕዝብ በትክክል ካላስተዳደራችሁት (mismanage ካደረጋችሁት) አብሮነቱንና አጋርነቱን ቀስ በቀስ እያጣችሁት መሄዳችሁ አይቀርም፡፡

የጀመራችሁት ንግድ (business) ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ በትክክል manage ካደረጋችሁት ታሳድጉታላች፡፡ ካላደረካችት ደግሞ ቀስ በቀስ እያሽቆለቆለ ይሄዳል፡፡

እያለ መርሁ ከብዙ ዘርፎች አንጻር እውነታነቱ ያው ነው፡፡

አንድን ነገር በትክክል manage ማድረግ ማለት፣ ትክክለኛውን መርህ መከተል፣ በእቅድ መኖር፣ ስህተት ሲኖር ቶሎ ማረም እና የመሳሰሉትን አስፈላጊ ሂደቶች ተግባራዊ ማድረግ ማለት ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
👍24275🔥1😁1🎉1
ልክ እንደ ወንዝ!
👍27😱1
ልክ እንደ ወንዝ!

“ወንዝ ሲፈስ አነስተኛ የመቋቋም ብቃት ወዳለው አቅጣጫ እየተጣጠፈ ነው የሚዘልቀው” ይባላል፡፡ አቅሙ የሚፈቅድለት ቁልቁለቱ እያለለት ወንዝ ከአቅሙ በላይ ወደሆነው ወደዳገቱ አይፈስም፡፡ እንደ አቅሙ የሆነው እያለለት ወንዝ ከአቅሙ በላይ የሆነውን፣ “ለምን አያሳልፈኝም” እያለ አይታገልም፡፡ አሁን ስለቀለለው ወደቀኝ ታጥፎ፣ ወዲያው ሲከብደው ወደግራ ሊታጠፍ ይችላል፡፡ በዚህ የፍሰት ባህሪይው የወንዝ መጨረሻው ቀጥ ብሎ ከመሄድ ይልቅ እየተጣመሙ መኖርና የአካባቢው ዝቅተኛው ስፍራ ላይ መውረድ ነው፡፡

የወንዝ ባህሪይ ግን ከላይ የተገለጸው ብቻ አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኮ ወንዝ ወደከፍታም የሚፈስበት ጊዜ አለ፡፡ ወንዝ አቅሙን ሲያጠራቅም፣ ሲበረታና ኃይል ሲኖረው በፊቱ ያለውን ከፍ ያለ ነገርም ቢሆን ሞልቶና አልፎ ይሄዳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወንዝ ሲበረታ ከፍተኛውን ስፍራ እስኪሞላ ድረስ “ወደ ላይ ይፈስሳል”፡፡

ከወንዝ እንማር! ከአቅምህ በላይ የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙህ ለምን መንገድ አይለቁም ብለህ እስክትደማ አትታገል፣ ወይም ደግሞ ወደኋለ አትመለስ፡፡ ብልሃት ፈልገህ ዘወር ብለህ እለፍ፡፡ ሆኖም ያንን እያደረክ ሳለህ፣ አቅምህን አጠራቅም፡፡ አቅም በጨመርክ ቁጥር መንገድ እየቀየርክና ጠመዝማዛ ጎዳናን በመጓዝ መድከምህ ያበቃና ቀጥ ብለህና በፊትህ የሚቆመውን እየገረሰስክ ማለፍ ትጀምራለህ፡፡

• የስሜት ጽንአት አቅምህን አጠራቅም፣ እስከዚያ ግን የወቅቱን የስሜት ጽንአት ባገናዘበ ሁኔታ ተራመድ፡፡

• የገንዘብ አቅምህን አጠራቅም፣ ለጊዜው ግን ኑሮህን ካለህ የገንዘብ አቅም ጋር በማገናዝ ተንቀሳቀስ፡፡

• የግንኙነት መረብህ (Network) አቅምህን አጠራቅም፣ እስከዚያው ግን አጠገብህ የሚገኙ ሰዎች በሚደግፉህ ደረጃ ተራመድ፡፡

• የእውቀት አቅምህን አጠራቅም፣ እስከዚያው ግን ባለህ እውቀት የምትችለውን ስራ በመስራት ኑሮህን ግፋ፡፡

ልክ እንደወንዝ!!!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍21687🔥4🎉4
ዛሬ ማታ በ telegram live የምሰጠው ስልጠና የሚጠው በዚሁ ቻናል ሲሆን ከእናንተ የሚጠበቀው ልክ ከምሽቱ በ2፡30 ወደዚህ ቻናል በመምጣት ስልጠናው ሲጀምር join የሚለውን ምልክት በመጫን መቀላቀልና መሰልጠን ነው፡፡

ቀን - ዛሬ የካቲት 20

ሰዓት - ማታ ከ2፡30 – 3፡30

የስልጠናው ርእስ - የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence)

ክፍያ - በነጻ!!!

ወዳጆቻችሁም ይህንን telegram channel join በማድረግ እንዲከታተሉ ጋብዟቸው፡፡

በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዚሁ ቻናል በመግባት ስልጠናውን live መከታተል ትችላላችሁ!
👍15147😱6🔥4🤩4
ነጻው ስልጠና ከአንድ ሰዓት በኋላ ይጀምራል!

የስልጠናው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ዛሬ ምሽት ከ2፡30 እስከ 3፡30

በሰዓቱ እዚሁ ቻናል ላይ በመግባትና join የሚለውን በመጫን ይከታተሉ!

See you later!
👍58🤩4125🎉9😁2
ነጻው ስልጠና ከ 30 ደቂቃ በኋላ ይጀምራል!

የስልጠናው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ዛሬ ምሽት ከ2፡30 እስከ 3፡30

በሰዓቱ እዚሁ ቻናል ላይ በመግባትና join የሚለውን በመጫን ይከታተሉ!
45👍41
2025/07/13 22:06:08
Back to Top
HTML Embed Code: