Telegram Web Link
ምዝገባው ሊጠናቀቅ 2 ሰዓት ነው የቀረው!

ዛሬ ማታ ለሚጀምረው ስልጠና በርካቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡

መረጃውን ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ፖስተር ላይ ታገኙታላችሁ፡፡

የምዝገባውን መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ስትገልጹ መረጃው ይላክሎታል፡፡

@DrEyobmamo
👍202
ምዝገባው ልክ ከአንድ ሰዓት በኋላ ይጠናቀቃል!

ዛሬ ማታ በ3 ሰዓት ለሚጀምረው ስልጠና በርካቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡

መረጃውን ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ፖስተር ላይ ታገኙታላችሁ፡፡

የምዝገባውን መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ስትገልጹ መረጃው ይላክሎታል፡፡

@DrEyobmamo
👍194
የምዝገባ ሰዓት መራዘም!

በስራ ምክንያት ለስልጠናው ሳትመዘገቡ የዘገያችሁ ባቀረባችሁ ጥያቄ መሰረት እስከ 2፡00 ድረስ የመመዝገብ እድል ከፍተንላችኋልና ተጠቀሙበት፡፡

የምዝገባውን መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ስትገልጹ መረጃው ይላክሎታል፡፡

@DrEyobmamo
👍247
መሸከም የሌለብህ ሸክሞች (ክፍል አራት)

ከስራህ ጋር ያለህ ግንኙነት
9👍8🤩1
መሸከም የሌለብህ ሸክሞች (ክፍል አራት)

ከስራህ ጋር ያለህ ግንኙነት

የከበደህ የስራ ሸክም የቤት ውስጥ ይሁን፣ የትምህርት ቤት ይሁን፣ የንግድ ይሁን ሌላ፣ በየጊዜው ለማከናወን የምትፈልጋቸው ስራዎች ከአቅምህ በላይ ከሆኑና ከከበዱህ ከሚከተሉት ሁኔታዎች በአንዱ ራስህን ታገኘዋለህ ብዬ እገምታለሁ፡፡

በጊዜው ማድረግ ሲገባህ ያስተላለፍከው ተግባር ሸክም:-

ሰዎች በተለያየ ምክንያት በወቅቱ መስራት ያለባቸውን ስራ ይወዝፋሉ፡፡ አንዳንዶች ከግድ የለሽነት የተነሳ፣ ሌሎች ከመወላወልና ለነገ ከማስተላለፍ የተነሳ፣ ሌሎች ደግሞ ግልጽ ከሆነ ስንፍና የተነሳ ስራን ያጠራቅማሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ዛሬ ማድረግ ለሚገባህ ስራ ያለህን ጊዜና ጉልበት ከትናንትና ተንከባሎ የመጣው ስራ ስለሚሻማ ሸክሙ ይከብድሃል፡፡

አንተው ማድረግ ሲገባህ ለሰው ትተኸው ሳያደርጉት የቆየህ ሸክም:-

“አንድ ነገር እንዲደረግ እርግጠኛ መሆን ከፈለክ አንተው አድርገው” ይላሉ አንዳንድ ሁኔታውን በልምምድ ያጠኑት ሰዎች፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኛው መስራት የሚገባንን ወሳኝ ስራ ለሌሎች በመተውና በሚገባ ባለመከታተል ምክንያት ስራው ሳይጠናቀቅ ይቆይና በመጨረሻ እኛው ላይ ይከመራል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ የስራው መጠራቀምና በሰዎቹ ምክንያት የሚመጣብን የስሜት ቀውስ ኑሮን አሰልቺና አድካሚ ያደርገዋል፡፡

ካለአግባብ የምትሰበስባቸው የስራ ሸክሞች:-

የአንዳንድ አላስፈላጊ ሸክሞች ምንጭ ይህንንም ያንንም ስራ በሃላፊነት ከመረከብ፣ ሁሉንም ለማድረግ ከመሞከርና ያለአግባብ ስራ ከማብዛት የሚመጣ ነው፡፡ ከዋናው ዓላማችንና ሃላፊነታችን አንጻር የምንሸከመውን የስራ ሸከም ካልመረጥን ሁሉን ተሸካሚ መሆናችን አይቀርም፡፡ ውጤቱን ማስተዋል አያስቸግርም፡፡

አንዳንድ ሰዎች ማከናወን ያለባቸው ዋነኛ ስራ ከሌሎች አቻዎቻቸው ብዙም ባይለይም እነሱ ግን በበለጠ ሁኔታ ዝለውና ተስፋ ቆርጠው የታያሉ፡፡ ምናልባት እንደዚህ አይነቱ ልምምድ ውስጥ ካለህ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት ነጥቦች በሚገባ በማሰብ ለእያንዳንዳቸው ምን አይነት መፍትሄ ልትሰጣቸው እንደምትችል በሚገባ አስብበት፡፡

መሸከም የሌለብህ ሸክሞች በሚል ርእስ የተመለከትናቸውን ነጥቦች በመከታተል ስለተሳተፋችሁ ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡

ትክክለኛውን ሸክም በመለየት የሚመጥነንን ሸክም መሸከም ጤናማ ኑሮን ስንኖር ካለአግባብ ብዙ ከመልፋት በጥበብ ወደመስራት እንሸጋገራለን፡፡

ሆኖም፣ መሸከም የማይገባኝን ሸክም አልሸከምም በሚል ሰበብ ለሰዎች ማድረግ የሚገቡንን ድጋፎች ችላ እንዳንል አደራ እላለሁ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob


https://m.youtube.com/user/naeleyob623


https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍8629😁1🤩1
ክፍለ-ጊዜ ላመለጣችሁ!

“የስሜት ብልህነት” የተሰኘው የአምስት ኃሙሶች ስልጠና ትናንትና በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች በተገኙበት በስኬታማ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡

ትናንት ያለፋቸውን ስልጠና በ audio እና note (Manual) ማካካሻ በመውሰድ ለመቀላቀል በርካቶች በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

በዚህ ጥያቄ መሰረት ይህንን እድል በመጠቀም ለመቀላቀል የምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link በመጠቀም ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡

@DrEyobmamo
👍4611
ፈራችሁም አልፈራችሁም . . .
👍11
ፈራችሁም አልፈራችሁም . . .

(“ገዢው ስሜት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደገሰገሱት ሃገራት በእኛም ሃገር ጥርት ያሉ ጥናቶች እየተዘጋጁ የሚቀርብልን ሁኔታ እያደገ እንደሚሄድ ተስፋ በማድረግ፣ እስከዚያው ግን በጥናታዊ አቅርቦት ከበለጸጉት ሃገሮች አንዳንድ መረጃዎችን በመበደር ለእንቆቅልሾቻችን መፍቻ መፈለጋችንን እንቀጥላለን፡፡

እንደምሳሌ ለመውሰድ፣ በአሜሪካን ሃገር ውስጥ በተደረገው አንድ ጥናት (የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ውጤቶችን የማንጸባረቃቸው ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ) የሚከተለውን የፍርሃትን ገጽታ ከሃገራችን አውድ አንጻር እንድንመለከተው የሚያደርገንን መረጃ እናገኛለን፡፡

• ስልሳ በመቶው (60%) የምንፈራቸው ነገሮች ፈጽሞ ወደመሆን አይመጡም፡፡

• ሰላሳ በመቶው (30%) ከዚህ በፊት ፈርተናቸው የደረሱብን ሁኔታዎች ብንፈራም ሆነ ባንፈራ ከመሆን የማንቀይራቸው ነገሮች ናቸው፡፡

• ዘጠና በመቶው (90%) የምንፈራቸው ነገሮች ቢደርሱም ሆነ ባይደርሱ ብዙም የማይነኩንና አናሳ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

• ሰማኒያ ስምንት በመቶው (88%) ከጤንነታችን ጋር በተያያዘ ሁኔታ ይደርስብናል ብለን የምንፈራቸው ሁኔታዎች በፍጹም የማይደርሱብን ሁኔታዎች ናቸው፡፡

በዚህ ዓለም ላይ ምንም ሳይፈራ የሚኖር ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ ነገር ግን የፍርሃትን እውነታ በመቀበል፣ ብንፈራም ሆነ ባንፈራ ምንም ለውጥ ስለማናመጣባቸው ነገሮች መፍራትን በማቆም፣ የፍርሃትን ስሜት ለጥቅማችን በማዋል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግና ሕይወትን ቀና ብሎ በማጣጣም መኖር ፍርሃትን ያሸነፉ ሰዎች ልምምድ እንደሆነ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡

ፈራችሁም አልፈራችሁም . . . ወደፊት!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
73👍57
ተንቀሳቀሱ!

ለረጅም ጊዜ በሕልም፣ በራእይ ወይም በዓላማ መልክ በውስጣችሁ አምቃችሁ የቆያችሁት ነገር ካለና እስካሁን ወደፊት መንቀሳቀስ ካስቸገራችሁ፣ አንድን እውነታ ላስታውሳችሁ፡፡

ያንን ነገር ለመጀመር የግድ ጎበዝ መሆን የለባችሁም፡፡ ጎበዝ ለመሆን ግን የግድ ያንን ነገር መጀመር አለባችሁ፡፡

እነዚያ ሌላ ሃገር ያሉት፣ ብዙ ነገር የጀመሩትና የተዋጣላቸው . . . እነዚህ በቅርብ በሃገራችን ያሉት፣ ብዙ ነገር ጀምረው የተሳካላቸው፣ ያንን ነገር የጀመሩት ጎበዝ ስለሆኑ ነው ብላችሁ የምታስቡትን ከእውነት የራቀ ሃሳብ ተወት አድርጉት፡፡

እነዚህ ሰዎች ጎበዝ የሆኑት ያመኑበትን ነገር ባላቸው አቅም አንድ ብለው በመራመድ ስለጀመሩ ነው እንጂ ጎበዝ ስለሆኑ አይደለም የተራመዱት፡፡

የምትችሉትን ያህል በማቀድና አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል በመዘጋጀት ተንቀሳቀሱ!!! ጉብዝናው ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍12960🔥11🤩1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ክፍለ-ጊዜ ላመለጣችሁ!

“የስሜት ብልህነት” የተሰኘው የአምስት ኃሙሶች ስልጠና ትናንትና በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች በተገኙበት በስኬታማ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡

ትናንት ያለፋቸውን ስልጠና በ audio እና note (Manual) ማካካሻ በመውሰድ ለመቀላቀል በርካቶች በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

በዚህ ጥያቄ መሰረት ይህንን እድል በመጠቀም ለመቀላቀል የምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link በመጠቀም ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡

@DrEyobmamo
👍255
በውጭ ሃገራት ያላችሁ የቻናሌ ቤተሰቦች

ብዙዎቻችሁ ልጆቻችሁን አማረኛ መጻፍ እና ማንበብ ለማስተማር እንደምትቸገሩ አስባለሁ። እናም ይህንን ችግር የሚቀርፍ መፍትሄ ይዞ የመጣ ወጣት አለ!

በዚ ወጣት የተፃፈው ይህ መጽሐፍ አማርኛን ቀላል እና ለልጆች አስደሳች በሆነ መንገድ መማር እንዲችሉ የሚያግዝ ነው።

📖 መጽሐፉን ከታች ባለው ሊንክ አማዞን ላይ ማዘዝ ትችላላችሁ 👇

🔗 https://www.amazon.com/dp/B0CD91XR6H

ከመጽሐፉ ጋ ለተያያዘ መረጃ ፤ የጸሃፊውን ቴሌግራም ቻናል ▶️ @LearnAmharic ላይ ታገኙታላችሁ
👍4520
ራሳችሁን ለራሳችሁ አስመስክሩ!

ራሳችሁን ለሌሎች ሰዎች ለማስመስከር የምትታገሉትን ትግል አቁሙና ራሳችሁን ለራሳችሁ አስመስክሩ፡፡ ራስን በራስ ማስመስከር ማለት ባጭሩ ካወጣነው ጤናማ የሕይወት ከፍታና የኑሮ ሁኔታ አንጻር ለመኖር ከራስ ጋር በመስማማት የምንችለውን ማድረግ ማለት ነው፡፡

የዚህ ተቃራኒ ራስን ለሌላ ሰው የማስመስከር ጡዘት የእኛን ስኬታማነት ለሰዎቹ እይታ፣ ባህሪይና ማንነት አሳልፈን በመስጠት ዳኞቹ እነሱና እነሱ ብቻ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለሆነም ሩጫችንን ካልተቀበሉት የበለጠ እንሮጣለን፣ ሁኔታችን ካልጣማቸው ሌላ ሁኔታ ለመፍጠር እንታገላለን፡፡

• ምን ያህል እንደምታውቁ ለሌላ ሰው ለማስመስከር መታገል አቁሙና በተሰማራችሁበት ዘርፍ አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል እውቀትን አዳብሩ፡፡

• ምን ያህል ጨዋ እንደሆናችሁ ለሌላ ሰው ለማስመስከር መታገል አቁሙና ማዳበር የሚገባችሁን ጨዋ ባህሪይ በመለየት ያንን ጨዋነት አዳብሩ፡፡

• ምን ያህል ገንዘብና ሃብት እንዳላችሁ ለሌላ ሰው ለማስመስከር መታገል አቁሙና ላወጣችሁት የሕይወት ደረጃና ለምትከተሉት ዓላማ የሚመጥን የገንዘብ አቅም ላይ የመድረስን ትጋት አዳብሩ፡፡

• ምን ያህል አሪፍ የፍቅር አጋር እንደሆናችሁ ለፍቅረናችሁ ለማስመስከር መታገል አቁሙና ከአንድ እውነተኛ ፍቅረኛ የሚጠበቀው ባህሪይና ማንነት ምን እንደሆነ በመለየት ያንን አዳብሩ፡፡

ራሳችሁን ለማስመስከር የምትታገሉት ትግል የማያዛልቃችሁ፣ ስለሆናችሁትና አለኝ ስለምትሉት ነገር እንዲያዩላችሁ የምትፈልጓቸው ሰዎች መስፈርት እንደየግል እይታቸውና ባህሪያቸው የተለያየ ስለሆነ ምንም ያህል ብትታገሉም ከቁጥርም ላይከቱት ስለሚችሉ ነው፡፡ ይህ ጉዞ የማያልቅና አድካሚ ጉዞ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
👍11158
2nd Chance

ባለፈው ኃሙስ የተጀመረውን “የስሜት ብልህነት” ስልጠና መቀላቀል እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በርካቶች በመቀላቀል ላይ ናቸው፡፡

ያመለጣችሁ ክፍል የአንድ ኃሙስ ምሽት ክፍል ነው፡፡

ከፊታችን ኃሙስ ክፍለ-ጊዜ በፊት ስትቀላቀሉ፣ ያመለጣችሁን የአንድ ኃሙስ ምሽት ክፍለ ጊዜ በ audio እና በ manual የመከታተል እድል አላችሁ፡፡

ይህንን እድል በመጠቀም ለመቀላቀል የምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link በመጠቀም ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡

@DrEyobmamo
👍3910
የቋንቋ ለውጥ - ከተገደበው ወደ ተለቀቀው!!!

ዛሬ
ከመተኛታችሁ በፊት የሚከተሉትን የቋንቋ ለውጦች አድርጋችሁ ተኙ!

ከዚህ በታች የሚገኘውን ንጽጽር በማንበብና ተግባራዊ በማድረግ ከተገደበ ንግግር፣ አመለካከትና ሕይወት ለስኬት ወደተለቀቀ ሕይወት የመሸጋገርን ጎዳና ጀምር፡፡

የተገደበው፡- “ይህንን ነገር ለማድረግ ብቃቱ ስለሌለኝ ማድረገ አልችልም”
የተለቀቀው፡- “አሁን ብቃቱ የለኝም ሆኖም ብቃቱን በማዳበር ማድረግ እችላለሁ”

የተገደበው፡- “ይህንን ነገር ለማድረግ ስሞክር ካልተሳካ ችግር ውስጥ እገባለሁ”
የተለቀቀው፡- “አሁን ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ብዙ ወድቀውና ተነስተው ነው እዚህ የደረሱት፡፡ እኔም እንደዚያ አደርጋለሁ”

የተገደበው፡- “ይህንን እና ያንን እየሞከርኩ ባለመሳካቱ ክብሬን ከማስነካ ራሴን ጠብቄ ብኖር ይሻለኛል”
የተለቀቀው፡- “አዲስን የእድገት ጎዳና ካልሞከርኩት ባለሁበት መቅረት ይከተላል፡፡ ባሉበት በመቅረት ውስጥ ደግሞ ምንም ክብር የለም”

የተገደበው፡- “እድለኛ ብሆን ኖሮ አሁን የት በደረስኩ ነበር”
የተለቀቀው፡- “እድለኛ የምሆነው ጠንክሬ ስሰራና ካለማቋረጥ ስሞክር ነው”

የተገደበው፡- “ገንዘብ ቢኖረኝ ኖሮ ብዙ የፈጠራ ስራዎችን እሰራ ነበር”
የተለቀቀው፡- “ገንዘብ የፈጠራ ስራን አያመጣም፣ የፈጠራ ስራን ብጀምር ግን ፈጠራዬ ገንዘብን ያመጣል”

የተገደበው፡- “ሰዎች ይህንና ያንን ባያደርጉብኝ ኖሮ ብዙ እራመድ ነበር”
የተለቀቀው፡- “ለሆነብኝ ነገር ሁሉ ሙሉ ሃላፊነት በመውሰድ ከሰዎችና ከሁኔታዎች አጉል ተጽእኖ በላይ መኖር እችላለሁ”

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
94👍54🔥1
ወደ ቤተመንግስት የመግቢያው መንገድ
👍176
ወደ ቤተመንግስት የመግቢያው መንገድ

ምንጩ ያልታወቀ የጥንት አባባል እንዲህ ይላል፣

“ወደ ቤተ መንግስት የመግቢያው መንገድ ሁለት ነው፡፡ አንደኛው ንጉስ መሆን ነው፡፡ ሁለተኛ ግን የንጉሱ ታማኝ አገልጋይ በመሆን ነው”፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን አባባል ከፖለቲካና መሰል ሁኔታዎች አንጻር ብቻ ለመመልከት ጊዜህን ሳታባክን በቀጥታ በየእለት ሕይወትህ አድገህ ልታገኘውና ልትደርስበት ከምትፈልግበት የስራ፣ የእውቀትና የመሳሰሉት ደረጃዎች አንጻር ተመልከተው፡፡

ጥሩና አትራፊ ንግድ ውስጥ ለመግባት ከፈለክ እዚያ ውስጥ የገባን የንግድ “ንጉስ” በማገልገል ጀምር፤ መግባትህ አይቀርም፡፡

የላቀ የእውቀት ዘርፍ ውስጥ ለመግባት ከፈለክ በእውቀቱ አለም የላቀውን የእውቀት “ንጉስ” አገልግል፤ መግባትህ አይቀርም፡፡

በአንድ ስኬታማ መስሪያ ቤት ውስጥ የላቀው ደረጃ መድረስ ከፈለክ በዚያ መስሪያ ቤት ውስጥ ያለውን የአመራር “ንጉስ” በማገልገል ጀምር፤ መግባትህ አይቀርም . . . እያለ ተግባራዊነቱ ይቀጥላል . . .

በፉክክር፣ በጥላቻ፣ አንዱን ጥሎ ለመነሳት በመሞከር፣ ስም አጥፍቶ የራስን ስምና ዝና ለመትከል በመሞከር አንድ ደረጃ ለመድረስ ከመታገል ይልቅ የላቀው መንገድ ራስን ቀለል አድርጎና ከእኛ የቀደሙትን እንስቶ፣ አክብሮና አገልግሎ ከእነሱ ጋር አብሮ የመነሳት መንገድ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ይህንን ሃሳብ ገና ሲያነቡ፣ “በዚህ ዘመን ምን ደህና ‘ንጉስ’ አለ” ሊሉ እንደሚችሉ ጥርጥር የለውም፡፡ በተለያዩ የሕብረተሰቡ መስኮች ውስጥ ቁልፉን ቦታ ይዘውትና “ነግሰው” ሳለ ነገር ግን ለዚያ የሚመጥን ጨዋነት የሌላቸውን “ንጉሶች” ሊኖሩ እንደሚችሉ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ እነዚህ ሰዎች ዛሬ ችላ ያሉትን ስፍራ ነገ የሚረከቡት የወደፊት “ንጉሶች” ዛሬ በጨዋነት ራሳቸውን ያሳደጉት እንደሆኑም ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡

ላሉበት “የንግስና” ስፍራ የማይመጥንን አጉል ባህሪይ በያዙት ሰዎች ስር ሆነን የአገልግሎት ዘመናችንን በጨዋነት ስንጨርስ እውነተኛ ማንነትን ይዘን ከፍታውን የምንረከብበት መንገድ መፈጠሩና ጊዜው መምጣቱ አይቀርም፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍13024🤩1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
2nd Chance

ባለፈው ኃሙስ የተጀመረውን “የስሜት ብልህነት” ስልጠና መቀላቀል እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በርካቶች በመቀላቀል ላይ ናቸው፡፡

ያመለጣችሁ ክፍል የአንድ ኃሙስ ምሽት ክፍል ነው፡፡

ከፊታችን ኃሙስ ክፍለ-ጊዜ በፊት ስትቀላቀሉ፣ ያመለጣችሁን የአንድ ኃሙስ ምሽት ክፍለ ጊዜ በ audio እና በ manual የመከታተል እድል አላችሁ፡፡

ይህንን እድል በመጠቀም ለመቀላቀል የምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link በመጠቀም ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡

@DrEyobmamo
👍347
የፈቃድ መስኮታችሁ ጉዳይ!

“መስኮቴን የከፈትኩት ራሴው ሆኜ ሳለሁ፣ እኔው በከፈትኩት መስኮት በኩል ገብቶ ወረቀቶቼን የበታተነውን ነፋስ የምወቅስበት ነገርስ ???!!!”

• ፈቃጆቹም እናንተው፣ ወቃሾቹም እናንተው . . .

• ሲደረግባችሁ ዝም ባዮቹም እናንተው፣ በተደረገባችሁ ነገር ነጭናጮቹም እናንተው . . .

• ሰጪዎቹም እናንተው፣ ተወሰደብኝ ብላችሁ አውሪዎቹም እናንተው . . .

ስትሆኑ፣ ሁኔታው ከሚከተሉትን የውስጥ ችግሮች ቢያንስ አንዱ እንዳለባችሁ ጠቋሚ ምልክት ሊሆን ይችላል፡-

1. አቋም-የለሽነት

2. ከአለመግባባትን የሚመጣን ውጥረት መፍራት

3. ሰዎች እንዳይከፉበትን አብዝቶ መጨነቅ

4. የግል ቀይ መስመር (boundary) ማበጀት አለመቻል

5. ሰውን ሁሉ ለማስደሰት መሞከር
አብዛኛው የዚህ አይነቱ ችግር መነሻው ከተዘባ አስተዳደግ እና ከተለያዩ trauma ነክ ልምምዶች ሊሆን ስለሚችል ወደ መፍትሄ!

በነገራችን ላይ ባለፈው ኃሙስ የተጀመረው የስሜት ብልህነት ስልነጠና ለዚህ አይነቱ ችግር መፍትሄ ጠቋሚ ነውና የቀረውን ክፍል ለመካፈል እስከ ነገ የመመዝገብ እድል አላችሁ፡፡ ያመለጣችሁን ክፍል በ audio and note ታገኛላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link በመጠቀም ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡

@DrEyobmamo
👍6221😢2🤩1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?


(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)

1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመወጣት ስላቃታችሁ እገዛ ከፈለጋችሁ፣

2. የሕይወታችሁን ራእይ ወይም ዓላማ ባለማወቅ ከተወዛገባችሁና አቅጣጫን መያዝ ከፈለጋችሁ፣

3. ካለባችሁ አጉል ልማድ በመውጣ አዲስ ልማድን ማዳበር ካስቸገራችሁና ምክርና ድጋፍ ከፈለጋችሁ፣

4. መመለስ ያቃታችሁ የሕይወት ጥያቄዎች ከበዙባችሁና በአንድ ለአንድ ውይይት የመፍትሄ መንገድ ከፈለጋችሁ፣

5. በራሳችሁ መወጣት ያልቻላችሁት የተያዩ የስሜትና የስነ-ልቦና ጥያቄዎች ውስጥ እንዳላችሁ ከተሰማችሁና ከሁኔታው ለመውጣት ምክር ከፈለጋችሁ፣

ከግል በተጨማሪም ቁጥራችሁ ከአስር ባልበለጠ ሁኔታ በመሰባሰብ የGroup Coaching and Training ጥያቄም ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡

በቴሌግራም @DrEyobmamo inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍3512🤩3🔥1
ውድቀትን እንደውዳቂነት አትቁጠር
👍24
2025/07/10 12:48:16
Back to Top
HTML Embed Code: