ውድቀትን እንደውዳቂነት አትቁጠር
ታዋቂው የአመራር ሊቅ ጃን ማክስዌል “Failing Forward” በተሰኘው ዝነኛ መጽሐፉ ውስጥ፣ “ከወደክ፣ ውዳቂ ነህ ማለት ነው?” የሚልን ምእራፍ ጽፏል፡፡ ይህንን ምእራፍ የሚጀምረው፣ “ውድቀት ልብን ካልጎዳ ችግር የለበትም፣ ስኬት ደግሞ ጭንቅላት ላይ እስካልወጣ ድረስ ጥሩ ነገር ነው” የሚለው የግራንት (Grantland Rice) አባባል በመጥቀስ ነው፡፡ ከዚያም፣ የሚከተሉትን ታዋቂና ስኬታማ ሰዎች ልምምድ ለምሳሌነት አስፍሯል፡፡
በሙዚቃ እውቀቱ በአለም ታዋቂ የሆነው Wolfgang Mozart በዘመኑ በነበረ ገዢ በፈርዲናንድ፣ “ዜማህ ብዙ ይጮሃል፣ ብዙ ቃላትም ታበዛለህ” የሚልን ተስፋ አስቆራጭ መልእክት የሰማ ሰው ነበር፡፡
በዓለም የታወቀውና በአንድ ስእል ሽያጭ በአለም ከፍተኛ ገቢ ያስገኘው ሰአሊ Vincent Van Gogh በሕይወት ዘመኑ ሁሉ አንዲትን ስእል ብቻ ነው የሸጠው፡፡
በፈጠራ ግኝቱ በአለም ታዋቂ የሆነው Thomas Edison በልጅነቱ፣ “ትምህርት የማይገባው” ተብሎ ነበር፡፡
የታወቀው ፈላስፋና አዋቂ Albert Eintsein ከአስተማሪ የሰማው ተስፋ አስቆራጭ ቃል፣ “ለምንም ጥቅም የማትውል ሰው ነህ” የሚል ነበር፡፡
እነዚህን ሰዎች ከነበሩት ሁኔታ አልፈው ወደስኬት ጎዳና እንዲገቡ ያደረጋቸው የጋራ ባህሪይ፣ ውድቀትን እንደውዳቂነት አለመቁጠር ነው፡፡
አንድ ግብ ጋር ለመድረስ መስራት፣ መንቀሳቀስና አዳዲስ ነገሮችን መጀመር እንዳለብኝ በማወቅ ወደፊት መገስገስ የስኬት ዋነኛው መንገድ ነው፡፡ ጉዞ ካለ እንቅፋት አለ፤ ሙከራ ካለ አለመሳካት አለ፤ ንግድ ካለ ክስረት አለ … ስሌቱ ይኸው ነው፡፡
በተቃራኒው ምንም አይነት ስህተትና አለመሳካት እንዳይደርስብኝ ከፈለግኩኝ ቀላሉና ብቸኛው መንገድ አለመንቀሳቀስ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች መውደቅ እንዳይከተል ሲሉ ምንም ነገር አለመሞከርን ይመርጣሉ - ሌላ የከፋ ስህተትና ውድቀት!
ስህተትንና ውድቀትን በጥብቅ የሚፈሩ ሰዎች አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ስለወደቁ ብቻ ውዳቂ እንደሆኑ የሚያስቡ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ አመለካከት እርምጃዎቻችንን ሊደርሱብን ከሚችሉት ውድቀቶች ጋር አመዛዝነን የመንቀሳቀሳችንን ሁኔታ የሚወስን አመለካከት ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የአንድ ጊዜ ውደቀት ውዳቂነት አይደለም፣ የአንድ ጊዜ አለመሳካት ስኬተ-ቢስነት አይደለም፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

👍107❤31🔥7🎉2
ባለፈው ኃሙስ ምሽት የተጀመረው “የስሜት ብልህነት ስልጠና” በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች እየተከታተሉት ነው፡፡
ነገ ክፍል ሁለትን ከመሰልጠናችን በፊት ያለፋችሁን በaudio and note በመከታተል join የማድረግ ትችላላችሁ፡፡
ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link በመጠቀም ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡
@DrEyobmamo

👍31❤9🤩1
ምክንያት እና መንገድ
• አንድ ሰው እናንተን በማግኘት ከእናንተ ጋር ጊዜን ማሳለፍ ካልፈለገ ያንን ላለማድረግ ምክንያትን ይፈጥራል፣ ማግኘት ከፈለገ ግን ተጣቦም ቢሆን መንገድን ይፈልጋል፡፡
• አንድ ሰው እናንተን ለመደገፍና ለመርዳት ካልፈለገ ያንን ላለማድረግ ምክንያትን ይፈጥራል፣ መደገፍ ከፈለገ ግን በዚህም በዚያም ብሎ መንገድን ይፈልጋል፡፡
• ፍቅረኛችሁ የፍቅር ግንኙነቱን ወደ አንድ ደረጃ መውሰድ ካልፈለገ ያንን ላለማድረግ ምክንያትን ይፈጥራል፣ ለመውሰድ ከፈለገ ግን እንደምንም ብሎ መንገድን ይፈልጋል፡፡
“ፍላጎት ካለ፣ መንገድ አለ!” የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡
• አንዳንድ ሰዎች ፍላጎቱ እያላቸው ብቃቱ የላቸውም - እነዚህን ሰዎች ታገሷቸው፡፡
• አንዳንድ ሰዎች ብቃቱ እያላቸው ፍላጎቱ የላቸውም - እነዚህን ሰዎች የቀን ገደብ አብጁላቸው፡፡
• አንዳንድ ሰዎች ፍጎቱም ሆነ ብቃቱም የላቸውም - እነዚህን ሰዎች ቀስ በቀስ ከውስጣችሁ አውጧቸው፡፡
• አንዳንድ ሰዎች ፍላጎቱም፣ ብቃቱም አላቸው - እነዚህን ሰዎች በሙሉ ልባችሁ አስተናግዷቸው፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
• አንድ ሰው እናንተን በማግኘት ከእናንተ ጋር ጊዜን ማሳለፍ ካልፈለገ ያንን ላለማድረግ ምክንያትን ይፈጥራል፣ ማግኘት ከፈለገ ግን ተጣቦም ቢሆን መንገድን ይፈልጋል፡፡
• አንድ ሰው እናንተን ለመደገፍና ለመርዳት ካልፈለገ ያንን ላለማድረግ ምክንያትን ይፈጥራል፣ መደገፍ ከፈለገ ግን በዚህም በዚያም ብሎ መንገድን ይፈልጋል፡፡
• ፍቅረኛችሁ የፍቅር ግንኙነቱን ወደ አንድ ደረጃ መውሰድ ካልፈለገ ያንን ላለማድረግ ምክንያትን ይፈጥራል፣ ለመውሰድ ከፈለገ ግን እንደምንም ብሎ መንገድን ይፈልጋል፡፡
“ፍላጎት ካለ፣ መንገድ አለ!” የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡
• አንዳንድ ሰዎች ፍላጎቱ እያላቸው ብቃቱ የላቸውም - እነዚህን ሰዎች ታገሷቸው፡፡
• አንዳንድ ሰዎች ብቃቱ እያላቸው ፍላጎቱ የላቸውም - እነዚህን ሰዎች የቀን ገደብ አብጁላቸው፡፡
• አንዳንድ ሰዎች ፍጎቱም ሆነ ብቃቱም የላቸውም - እነዚህን ሰዎች ቀስ በቀስ ከውስጣችሁ አውጧቸው፡፡
• አንዳንድ ሰዎች ፍላጎቱም፣ ብቃቱም አላቸው - እነዚህን ሰዎች በሙሉ ልባችሁ አስተናግዷቸው፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
❤112👍85🔥1
የምርጫ ናዳ!
“የምርጫ ናዳ” ሰዎች በበርካታ ምርጫዎች ሲከበቡና ሲዋከቡ ለመምረጥ የመቸገር ሁኔታቸውን የሚጠቁም ሃሳብ ነው፡፡
ሰዎች በምርጫ ብዛት ግራ ሲጋቡ አንዱን ነገር የመምረጥ ትኩረታቸው ከመወሰዱም ባሻገር የተሳሳተ ምርጫን ወደ መምረጥም ሊያዘነብሉ ይችላሉ፡፡ የምርጫ ናዳ ሲበዛ ግራ መጋባት፣ መወላወል፣ ከትክክለኛ የምርጫ እርምጃ መቆጠብና የመሳሰሉት አሉታዊ ተጽእኖዎች ይኖሩታል፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ቀንደኛ የሆነውና በሚገባ ልናስብበት
የሚገባው ጉዳይ ለተሳሳቱ ምርጫዎች የመጋለጣችንን ሁኔታ ነው፡፡
ከዚህ በታች ከምርጫ ናዳ ጋር የሚነካኩ የተለያዩ ለተሳሳተ ውሳኔ የሚዳርጉንን ሁኔታዎች እንመለከታለን፡፡
1. በምናየው ነገር ብቻ መወሰድ:- ፊት ለፊት ከሚታየው ጀርባ ያለውን እውነታ ሳናጣራ መምረጥ ለስህተት ያጋልጠኛል፡፡
2. በዓላማ ቢስ ሃሳብ መወሰድ፡- አንድ ነገር ከመምረጣችን በፊት ከዋናው ዓላማችን አንጻር ካልገመገምነው ለስህተት አንጋለጣን፡፡
3. በጊዜያዊ ጥቅም መወሰድ፡- አብዛኛውን ጊዜ የቅርብ ጊዜ ፍላጎቶቻችን ምርጫችንን የመጎተት ባህሪይ አላቸው፡፡ ስለዚህ ስንመርጥ አርቀን በማሰብ እንምረጥ፡፡
4. መካሪ አለመኖር፡- ጥሩ አማካሪ በአጠገባችን በማኖር ለምርጫዎቻችን ትክክለኛነት ጥበብን የምንቀስምበትን የሕይወት ዘይቤ ማመቻቸት የእኛ ድርሻ ነው፡፡
5. እውቀት የጎደለው ችኮላ፡- ትእግስት ማጣት፣ ስንፍና፣ ሁኔታዎችን አጥንቶ የመገንዘብ ብቃት እንደሌለን በማሰብ አእምሮን መዝጋትና የመሳሰሉት እንቅፋቶች ልናስብባቸው የሚገባን የስህተት ምንጮች ናቸው፡፡

👍94❤34🤩6
ባለፈው ኃሙስ ምሽት የተጀመረው “የስሜት ብልህነት ስልጠና” በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች እየተከታተሉት ነው፡፡
ዛሬ ክፍል ሁለትን ከመሰልጠናችን በፊት ያለፋችሁን በaudio and note በመከታተል join የማድረግ ትችላላችሁ፡፡
ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link በመጠቀም ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡
@DrEyobmamo
ዛሬ ክፍል ሁለትን ከመሰልጠናችን በፊት ያለፋችሁን በaudio and note በመከታተል join የማድረግ ትችላላችሁ፡፡
ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም link በመጠቀም ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡
@DrEyobmamo
👍34❤2
የመጨረሻ እድል!
ዛሬ ምሽት የሚደረገውን “የስሜት ብልህነት” 2ኛ ሳምንት ስልጠና በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ለመከታተል እየጠበቁ ነው፡፡
ዛሬ ክፍል ሁለትን ከመሰልጠናችን በፊት ያለፋችሁን በaudio and note በመከታተል join ለማድረግ ያላችሁን እድል ለመጠቀም ሰዓታት ብቻ ይቀራችኋል፡፡

❤28👍13😁1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo

👍39❤4
መብራቱን አብራው!
አንድ ጊዜ በአንድ ከተማ አንድን ስልጠና ለመስጠት በነበርኩበት ጊዜ የተከሰተ የግል ልምምዴን ላካፍላችሁ፡፡
ያረፍኩበት ሆቴል ከፍ ያለ ኮረብታ ላይ ስለነበረና አካባቢው በዛፎች በመከበቡ ምክንያት የራሱ ውበት ስላለው በዚያ ማረፍን እመርጣለሁ፡፡ በዚያ ባደርኩበት አንድ ሌሊት ግን አንድ ነገር ተከሰተ፡፡
ሌሊት ነቅቼ ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድ ስላስፈለገኝ ከአልጋዬ ለመውጣት ተንቀሳቀስኩኝ፡፡ ከውጪ በመስኮት በኩል በመጋረጃው ሾልኮ የሚገባው ደብዛዛ ብርሃን ለእንቅስቃሴዬ በቂ ስለነበር ልክ ከአልጋዬ ስወርድ ወደ መታጠቢያ ቤቱ በሚወስደው አቅጣጫ አንድ “እባብ” ተጋድሞ አየሁኝ፡፡ ከብርሃኑ ደካማነት የተነሳ ይህንን “እባብ” ቅርጹን እንጂ መልኩንና ሁኔታውን መለየት አልቻልኩም፡፡ በጣም ደነገጥኩ፣ በጣምም ፈራሁ፡፡
ወደኋላዬ በመሰብሰብ ሁለንተናዬን ትራሴ ላይ አገኘሁት፡፡ ብዙ አሰብኩኝ፡፡ ብዙ አወጣሁኝ፣ አወረድኩኝ፡፡ ትንሽ ጊዜ ካቃጠልኩኝ በኋላ፣ በመጨረሻ ያለኝ ብቸኛ አማራጭ እንደምንም የእባቡን ክልል አለፌ መብራቱን ማብራት ነው፡፡ ትንሽ ከወላወልኩኝ በኋላ የፈጣሪዬን ስም እየጠራሁ፣ ጨለማውን ለማሸነፍ አይኖቼን አፍጥጬ፣ ጥግ ጥጉን ተራምጄ መብራቱን ልክ ሳበራው ለካ ያየሁት “እባብ” ማታ በድካም ስሜት ወደ አልጋ ስቸኩል የጣልኩት ቀበቶዬ ነበር፡፡
በዚህ ገጠመኜ የገባኝ ነገር ይህ ቀበቶ እባብ መስሎኝ በነበረበት ሰዓት፣ ልክ እውነተኛ እባብን ብጋፈጥ የሚሰማኝን የፍርሃት ስሜት ነው የሰጠኝ፡፡ ከዚህ ስሜት የተነሳ ልጮህ እችል ነበር፣ እዚያው አልጋዬ ላይ ሆኜ እስከሚነጋ አፍጥጬ ልጠብቅ እችል ነበር፣ ሰዎች ጋር ስልክ በመደወል ልበጠብጥ እችል ነበር . . .፡፡ በፍርሃት ተወጥሮና ታስሮ የነበረውን ማንነቴን ነጻ ያወጣው እውነቱን ለማወቅ መብራቱን ማብራቴ ነው፡፡
ለካ እይታ የእውነታን ያህል ጉልበት አለው፡፡ በሕይወታችን አንድ ነገር ባይኖርም እንኳን፣ እንዳለ ከቆጠርነውና ከፈራን ማንነታችንን አስሮ ሊያስቀምጠን እንደሚችል በሚገባ የተገነዘብኩት ያን ጊዜ ነው፡፡ መድሃኒቱ መብራቱን ማብራት ነበር፡፡
አንዳንድ ሰዎች ገና ለገና ሆኖብኛል . . . ሳይሆንብኝ አይቀርም . . . አለብኝ . . . ሳይኖብኝ አይቀርም . . . ሊሆን ነው . . . መሆኑ አይቀርም ከሚሉት ምክንያት-የለሽ ፍርሃት የተነሳ ታስረው አመታት ያሳልፋሉ፡፡ ይህ ፍርሃት፣ እምቅ ብቃታቸውን አፍኖ፣ ነጻነታቸውን ነፍጎ፣ የሌለውን ችግር እንዳለ አድርጎ፣ ያለውን ችግር ደግሞ እጅግ አግዝፎ በማሳየት ከሰው በታች ያደርጋቸዋል፡፡
መፍትሄው መብራቱን ማብራት ነው!!! መብራቱን ማብራት ማለት እውነታውን ለመጋፈጥ አይንን መግለጥ፣ ስለሁኔታችን ከበሰለ ሰው ጋር መወያየት፣ ምንም ነገር ቢሆን በፍርሃት ታስሮ ከመኖር እውነታውን ተጋፍጦ በነጻነት መኖር እንደሚመረጥ መገንዘብ ማለት ነው፡፡
አይህንን አትርሱ፣ መፍራት እስከምታቆሙ ድረስ መኖርን አትጀምሩም!

Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
❤176👍110🎉4😱2🤩1
ዓለም እኮ ሰፊ ነች!
ዓለም እናንተ ስታጠቧት ትጠባለች፣ ሰፊነቷን ስትቀበሉና ስታዩላት ደግሞ በስፋቷ ልክ ታስተናግዳችኋለች፡፡
ቀና በሉ!
• ከሰፈራችሁ ውጪ ሌላ ሰፈር አለ!
• ከቡድናችሁ ውጪ ሌላ ቡድን አለ!
• ከመስሪያ ቤታችሁ ውጪ ሌላ መስሪያ ቤት አለ!
• በአካባቢች ካሉት ሰዎች ውጪም ሌሎች ሰዎች አሉ!
• አሁን ካላችሁ የገቢ ምንጭ ውጪ ሌላ የገቢ ምንጭ አለ!
ከፈጣሪ የተሰጣችሁን ሰፊ ዓለማችሁን አታጥብቧት፡፡ ምርጫችሁ አንድና አንድ ብቻ እንደሆነ ስታስቡና በዚያ ዙሪያ ብቻ ስትሽከረከሩ ዓለማችሁ እሱ ብቻ እስከሚመስል ድረስ ትጠባላችሁ፡፡
“ከዚህ ሁኔታ ውጪ መኖር በፍጹም አልችልም” ብላችሁ ያሰባችሁትን ሁኔታ በብዙ የሚያስንቁ ሁኔታዎች አሉ፡፡
“ከእነዚህ ሰዎች ውጪ በፍጹም መኖር አልችልም” ብላችሁ ካሰባችኋቸው ሰዎች በብዙ የላቁ ሰዎች አሉ፡፡
“ከዚህ ስራ ውጪ በፍጹም መኖር አልችልም” ካላችሁት የስራ መስክ በብዙ የተሸሉ የስራ እድሎች አሉ፡፡
አትወጣጠሩ! አትጨናነቁ! ለክክለኛው ነገር ታማኝ መሆናችሁን ሳትለቁ በዙሪያች ብዙ እድሎች እንዳሉ አትዘንጉ፡፡

❤188👍126🔥22
የጊዜ አጠቃቀማችሁ ጉዳይ!
እንደምን አመሻችሁ የማሕበራዊ ገጾቼ ተከታታዮች!
ከነገ ሰኞ ማለዳ ጀምሮ እስከ ዓርብ ባሉኝ “ፖሰቶቼ” ጊዜያችሁን በሚገባ እንድትጠቀሙ የሚያግዟችሁን ሃሳቦች አጋራችኋለሁ፡፡
ሕይወታችሁን በስኬታማ ሁኔታ ለመምራት ከፈለጋችሁ ጊዜያችሁን እንዴት እንደምትጠቀሙበት መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡
በስኬታማ እና በስከተ-ቢስ ሰዎች መካከል ካሉ ዋና ዋና ልዩነቶች መካከል ቀንደኛው የጊዜ አጠቃቀም ብቃት ጉዳይ ነውና አስቡበት፡፡
ነገ ማለዳ በ11፡00 ሰዓት እስከማገኛችሁ ሰላም እደሩልኝ!
የ YouTube ቻናሌን Subscribe ማድረግን አትርሱ

❤156👍86🔥16😱2🎉2
ጊዜ ያላችሁ አይምሰላችሁ!!!
አንድ እድሜውን ሁሉ ሰዎችን በሕይወት ክህሎት ዙሪያ በማስተማር ያሳለፈ የእድሜ ባለጠጋ፣ “ወጣቶች ሊሰሩት ከሚችሉት ስህተት እጅግ የከፋው የትኛው ነው?” ተብሎ ሲጠየቅ፣ ከልምዱ በመነሳት እንዲህ ሲል መለሰ ይባላል፣ “ብዙ ጊዜ እንዳላቸው ማሰብ”፡፡
ልጆች ተጫውተው ለማለፍ ያላቸው ዓመታት አስቡት! እጅግ ውስን ነው!
ወጣቶች ለትምህርትና ማሕበራዊ ግንኙነትን በማዳበር ለመብሰል ያላቸው ዓመታት አሰላስሉት! ጥቂት ናቸው!
ጎልማሶች በስራው ዓለም ባላቸው ስምሪት ለአሁኑ ቤተሰባቸው ፍላጎትና ለወደፊት የሽምግልና እድሜያቸው ለማስቀመጥ ያላቸውን የእድል መስኮት አስቡት! ብዙም አይደለም!
እነዚህ ጊዜያቸውን ጠብቀው የሚመጡ ሂደቶች በትክክለኛ የጊዜ አጠቃቀም ብልሃት ካልተያዙ በብርሃን ፍጥነት ያልፋሉ፡፡ አንዴ ካለፉ ደግሞ አይመለሱም፡፡
“የአፍሪካ ጊዜ”
እንደ አፍሪካዊ፣ ከዚያም ጠበብ ሲል እንደ ኢትዮጵያዊ፣ የጊዜ አጠቃቀም ሁኔታችን ምን ያህል የተበላሸ እንደሆነ ለማወቅ ምንም አይነት ጥናታዊ አቅርቦቶችን ለማግኘት መጣጣር የለብንም የራሳችንንና በአካባቢአችን ያለውን የጊዜ አጠቃቀም ሁኔታና ዝንባሌ ማጤኑ ከበቂ በላይ ነው፡፡
ለአንድ ስብሰባ ስንጠራ በሰዓቱ ብንደርስ የሚገጥመንን ቁጭ ብሎ ያልመጡትን የመጠበቅ ሁኔታ ወይም ደግሞ በሰዓቱ መድረስ የሚሰጠንን “የመዋረድና የመናቅ” መንፈስ ስለምንፈራው ዘግይቶ መድረስ እንመርጣለን፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የማይቋረጥን ዑደት ፈጥሮብናል፡፡ የሰርጎቻችንን ሁኔታ እናስባቸው፡፡አንድ ሰው የሰርግ ጥሪውን አክብሮ በሰዓቱ ቢገኝ ከአንድና ከሁለት ሰዓታት በላይ ቁጭ ብሎ ሰርጉ እስኪጀመር መጠበቅ የተለመደ ነው፡፡
አንድ የጋና ተወላጅ እንዲህ ሲል ተናግሯል፣ “ክፍለ ዓለማችን ሳታድግ የመቀጠሏ ዋነኛ ምክንያት በጊዜ ላይ ያለን ግድ የለሽ ዝንባሌና ማሻሻል ያለብን የጊዜ አባካኝነት ዝንባሌ ነው፡፡ ሰዓትን ያለማክበር ችግራችን ከልክ ያለፈ ከመሆኑ የተነሳ ቀጠሮን አለማክበርና በሰዓት አለመገኘት የአፍሪካ ጊዜ በመባል ተቀባይነት አግኝቷል”::
እንደሚታወቀው ሁሉ ሁላችንም እንደማንኛውም በቀደሙት ዘመናት ኖረው እዳለፉ ሰዎች በቀን ውስጥ 24 ሰዓታት አሉን፡፡ ነገር ግን በዚህ በምንኖርበት ክፍለ- ዘመን ያለው የኑሮ ጫናና ሩጫ እነዚህን ቢሰራባቸውም ሆነ ባይሰራባቸው ከማለፍ ፍንክች የማይሉ ሰዓታት አጭር ያደርጋቸዋል፡፡ የየቀኑ ሩጫና መጨናነቅ ቀኑ እንደ አንድ ደቂቃ ታጥፎ የሄደ እስኪመስል ድረስ ያዋክበናል፡፡ ያለን ምርጫ አንድ ነው፣ ሰዓትን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር!
ይህንን አስበህ ታውቃለህ? ሰዓትህን በአግባብ በመጠቀም ሁኔታዎችን ካልመራሃቸው ሁኔታዎች ራሳቸው አንተን ይመሩሃል፡፡ በሰዎችም በቀላሉ የምትመራና የምትነዳ ሰው ትሆናለህ፡፡ ውጤቱም የምርታማነትና የስኬታማነት መቀነስ ነው፡፡
ጊዜህን በአግባብ የመጠቀም ብቃት እንደጎደለህ ለማወቅ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እራስህን መጠየቅ ትችላለህ፡-
• አንድን የጊዜ ገደብ ያለውን ስራ ለመጨረስ ዘወትር በመጨረሻው ሰዓት የመሯሯጥ ባህሪ አለህ?
• አብዛኛውን ጊዜ ለቀጠሮም ሆነ ለሌላ የጊዜ ገደብ የመዘግየት ዝንባሌ አለህ?
• በተመሳሳይ ጊዜ ከአንድ በላይ ቀጠሮ ወይም ፕሮግራም በመያዝ ግራ የመጋባት ባህሪይ ያጠቃሃል?
ለእነዚህና ለመሰል ጥያቄዎች ያሏችሁ መልሶች “አዎን” ከሆነ፣ ስለጊዜ አጠቃቀማችሁ በሚገባ አስቡበት
ነገ ማለዳ፣ ጊዜን በአግባቡ የመጠቀም ወሳኝነትን ይዤላችሁ እመለሳለሁ፡፡

👍214❤67🔥11🎉3
ጊዜን በአግባቡ የመጠቀም ወሳኝነት
“ሕይወቴ ያልፋል ብለህ አትፍራ፣ ይልቁንስ ሕይወትን ሳልጀምራት ላልፍ ነው ብለህ ፍራ” - John Henry
ዶ/ር ጆን ማክስዌል “ፓራብልስ” ከተሰኘው ጽሑፍ ያገኙትን አንድ ጠቃሚና አስተማሪ ታሪክ (Developing The Leader Within You) በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1940ዎቹ ዓመተ ምህረት በአለም ላይ እጅግ ዝነኛ የነበረ የሰዓት አይነት “ስዊስ” ሰዓት ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ በአለም ላይ የሚሸጠው 80 በመቶው ሰዓት ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚመረት ይህ “ስዊስ” የተሰኘ የሰዓት አይነት ነበር፡፡ በ1950ዎቹ ዓ.ም መጨረሻዎች ላይ ዲጂታል የሆነ ሰዓትን የመፈልሰፍ ሃሳብ ለስዊስ ሰዓት መሪዎች እንደቀረበላቸው ይነገራል::
“በአለም ላይ አለ የተባለ የሰዓት አምራች” እኛ ነን በሚል ሃሳብ የተሞሉት እነዚህ የስዊስ ሰዓት አምራች መሪዎች ሃሳቡን ከማስተናግ እጅግ ዘገዩ፡፡ እነሱ በጊዜው ምላሽ ባለመስጠታቸው ምክንያት የዲጂታል ሰዓት ፈልሳፊ ሰው ይህንን ሃሳብ ችላ ሲሉበት ዘወር በማለት ለሴይኮ ሰዓት አምራቾች ሃሳቡን አቀረበላቸው፡፡ የሴይኮ ሰዓት አምራቾች ሃሳቡን ለማስተናገድ ጊዜም አላባከኑም፡፡
በ1940 ዓ/ም የስዊስ ሰዓት አምራች ድርጅት 80 ሺህ ሰራተኞች ነበሩት፡፡ በዚያው ዓመት ውስጥ በአለም ላይ የሚሸጠው ሰማንያ በመቶው ሰዓት የሚመረተው በስዊስ ካምፓኒ ነበር፡፡ ዛሬ ከ80 በመቶው በላይ ሰዓት ዲጂታል ነው፡፡ የስዊስ ካምፓኒ ችላ ያለውን ቴክኖሎጂ የሴይኮ ካምፓኒ ፈጥኖና ጊዜውን ሳያባክን በመቀበሉ ምክንያት የአለምን ገበያ ተቆጣጠረ፡፡
ከላይ ከተጠቀሰው ታሪክ እንደምንማረው፣ አንድን ነገር በተገቢው ጊዜ ካላደረግነው እድሉ ከእጃችን ሊያመልጥ እንደሚችል ነው፡፡ የስዊስ ሰዓት ሃላፊዎች የመጣላቸውን እድል ከማየት ባይዘገዩና በጊዜው መልስን ሰጥተው ቢራመዱ ኖሮ ገበያውን ለሴይኮ አም ራቾች ባልሰጡትም ነበር፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የመጣውን እድል ለማየትና ለመያዝ በጊዜ እርምጃ የወሰዱት የሴይኮ ባለቤቶች የአለምን ገበያ ከስዊስ ሰዓት ለመቀማት በቁ፡፡
ጊዜ በተለያዩ አስገራሚ እድሎች የተሞላና ለሁሉም ሰው በእኩል ሁኔታ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ ጊዜ ሊለያይ በማይችልበት መልኩ ከእድል ጋር የተቆራኘ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ ከላይ ከተጠቀሰው ታሪክ የምንማረውም ይህንኑ እውነት ነው፡፡ ወቅቱንና ጊዜው ያገናዘበ ተግባር በውጤታማነታችን ላይ ያለው ተጽእኖ እጅግ ወሳኝ የመሆኑን ጉዳይ ነው፡፡ የባህል፣ የአመለካከትና የቴክኖሎጂ ለውጦች ከጊዜ ጋር አብረው የሚመጡ ክስተቶች ናቸው፡፡
እነዚህ ክስተቶች ይዘው የሚመጡትን እድሎች በሚገባ ካላስተዋልናቸውና እንደ አመጣጣቸው ለማስተናገድ የሚያስችል ብቃትና ንቃት ከሌለን ጊዜዎቻችንና በውስጣቸው የያዙት እድሎች አብረው ያልፋሉ፡፡ ለዚህ ነው የጊዜ አጠቃቀምን ጥበብ ማዳበር ወሳኝ ነው ብለን የምናምነው፡፡
ነገ ማለዳ፣ ጊዜን በጥበብ የመጠቀምን ጥቅሞች ይዤላችሁ እመለሳለሁ፡፡

👍162❤54🔥6
ጠንከር በሉ!
ከእናንት ቁጥጥር ውጪ ስለሆኑት እና ምንም ብታደርጉ ለመለወጥ ስለማትችሏቸው ነገሮች መጨነቅ አቁሙና ለፈጣሪ ስጡት!
ምንም አትሆኑም!

❤186👍59🔥4😢2🎉2
ጊዜን በጥበብ የመጠቀም ጥቅሞች
በየቀኑ 1,440 ብር ባንክህ ውስጥ ቢጨመርልህና በዚያው ቀን ካልተጠቀምክበት ወደሚቀጥለው ቀን የማይዘዋወር ቢሆን ምን ታደርጋለህ? “ሕይወት” የተሰኘ “ባንክ” አለህ፡፡ በዚህ ባንክ ውስጥ በየቀኑ 1,440 ደቂቃዎች ይጨመርልሃል፡፡ እነዚህን ደቂቃዎች በዚያው ቀን ካልተጠቀምክባቸው ለነገ አይዘዋወሩልህም፡፡
በዚህ የሕይወት ባንክ ውስጥ የተንቀሳቃሽ ሂሳብ እንጂ የማጠራቀሚያ ሂሳብ መክፈት አይቻልም፡፡ በዚህ “የሕይወት ባንክ” ብለን በሰየምነው ባንክና በገንዘብ ማጠራቀሚያ ባንክ መካከል ዋና የሆነ ልዩነት አለ፡፡
በገንዘብ ማስቀመጫ ባንክ ውስጥ ገንዘብ ማጠራቀም፣ እንዲያውም እንዲወልድልህ ማድረግ የሚቻል ሲሆን፣ በሕይወት ባንክ ውስጥ ግን የተንቀሳቃሽ ሂሳብ ብቻ ነው ያለው፡፡
ከዚያም በተጨማሪ በሕይወት ባንክ ውስጥ የተሰጠህን ጊዜ ዛሬውኑ ካልተጠቀምክበት ነገ በፍጹም አታገኘውም፡፡ ዛሬ ያልተጠቀምክበት ጊዜ ከአጠቃላይ የሕይወት ዘመንህ ላይ ይቀነስና ሕይወት ከሚያልቀው ዘመንህ ላይ ሌላ ጊዜን ይዛ ትጠብቅሃለች፡፡በጊዜ የማይገደብ ፍጥረት የለም::
ጊዜ ደግና ጨዋ ነው፣ ለሁሉም እኩል እድልን ይሰጣል፡፡ ጊዜ ጨካኝም ነው፣ ላልተጠቀሙበት ሰዎች ምህረትንና ሁለተኛ እድልን አይሰጥም፡፡ ይህንን የጊዜ ባህሪይ ሲያስብ የራሱን ሕይወት ማየት የማይጀምር ሰው ካለ ያስገርማል፡፡ ለዚህ ነው ጊዜያችንን በሚገባ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር ያለብን፡፡
ጊዜያቸውን በአግባቡና በጥበብ የሚጠቀሙ ሰዎች ከሌሎቹ በጊዜ ላይ ግድ የለሽ አመለካከት ካላቸው ሰዎች የሚለዩባቸው ብዙ ጉልህ የሕይወት ጥራቶች አሉ፡፡ ጊዜአቸውን በአግባቡ የማይጠቀሙ ሰዎች የጊዜ ባሪያዎች እንደሆኑ ይኖራሉ፡፡ ይህ ማለት ጊዜ ያመጣውን በመቀበል ወዲህና ወዲያ ሲንገላቱ፤ ይህንና ያንን ለመፈጸም ሲሯሯጡ ይታያሉ፡፡ በእለቱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፕሮግራሙን የሚያወጣላቸው ጊዜ ያመጣው ገጠመኝ እንጂ የራሳቸው እቅድ አይደለም፡፡
በአንጻሩ ጊዜያቸውን በሚገባ መጠቀም የበሰሉ ሰዎች ጊዜን እንደ አገልጋይ ይጠቀሙበታል፡፡ ጊዜ አይደለም ለእነሱ ፕሮግራሙን የሚያወጣላቸው፣ በተቃራኒው ጊዜያቸውን በማቀናጀት ያዙታል፡፡
ጊዜን ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠቀም ከሚሰጠን ጠቀሜታዎች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
1. የውጥረትና የጭንቀት መቀነስ፡- ጊዜህን በሚገባ የመጠቀምን ጥበብ ስታዳብር ከስራ ብዛትና መጨናነቅ የሚመጣን ውጥረት የመቀነስ እድልህን ትጨምረዋለህ፡፡
2. የአእምሮ ሰላምና የመከናወን ስሜት፡- በጥንቃቄ እቅድ አውጥተህ የምትተገብራቸው ክንዋኔዎችህ በመጨረሻው ላይ ትርፍ ጊዜን ስለሚሰጡህ አረፍ ለማለትና ከተግባርህ ገለል ብለህ ደስ የሚልህን ነገር የማድረግን አድል ይሰጥሃል፡፡
3. የጉልበት መጨመር፡- በቅጡ የተደራጀና በጊዜው የሚጠናቀቅ ተግባር የትኩረትን መጠን፣ ከዚያም ለስራም ሆነ ከስራ በኃላ ለሚኖረን የእረፍት ጊዜ ይህ ነው የማይባል ጉልበትን ይሰጠናል፡፡
4. የገንዘብ መደላደልና ነጻነት፡- ጊዜህ በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውል በገንዘብ አያያዝህ ላይ እና በገቢህ ላይ ታላቅ ተጽእኖ አለው፡፡
5. ጥራት ያለውና ጠንካራ የቤተሰብ ትስስር፡- በሚገባ ያልተደራጀ የጊዜ አጠቃቀም ሲኖርህ ተግባሮችህን በጊዜው ስለማትጨርሳቸው ከቤተሰብ ጋር ሊኖርህ የሚገባውን ሰዓት የመንካት ባህሪይ ይኖረዋል፡፡
6. የተሻለ ጤንነት፡- ጊዜህን በሚገባ ስትጠቀም ስራህን በሚገባ ካጠናቀቅህ በኋላ በቂ ጊዜ ስለሚኖርህ ጤንነትህን እንዴት በሚገባ እንደምትጠብቅ የማሰብ ጊዜ ታገኛለህ፡፡
ነገ ማለዳ፣ ጊዜን በጥበብ ያለመጠቀም ጉዳቶችን ይዤላችሁ እመለሳለሁ፡፡

👍172❤46🎉3🔥2🤩2
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች ጥያቄ!
ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡
በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-
1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)
2. እሴት-ተኮር (Value-based)
እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡
ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡
እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡
ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡
https://www.tg-me.com/impactyouthmentorship

👍58❤18🔥6