ጊዜን በጥበብ ያለመጠቀም ጉዳቶች
ደጋግመን እንደተመለከትነው የአንድ ሰው የሕይወት ጥራት ከሚለካባቸው ሁኔታዎች መካከል ጊዜን በሚገባ የመጠቀሙ ጉዳይ ቀንደኛው ነው፡፡ ጊዜውን በሚገባ የሚጠቀም ሰው አስገራሚና ስኬታማ ሕይወትን የተቀዳጀ ሰው ነው፡፡ ጊዜን በአግባቡና ስኬታማ በሆነ መልኩ መጠቀም ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ጊዜውን በሚገባ የማይጠቀም ሰው ለብዙ ጉዳቶች የተጋለጠ ነው፡፡
ጊዜውን በአግባቡ የማይጠቀም ሰው “ተራ”፣ የተለመደና አማካኝ ሕይወትን ለመኖር ራሱን አሳልፎ የሰጠ ሰው ነው፡፡ ይህ “ተራ” ሕይወት የሚከተሉትን መለወጥ ያለባቸውን ሁኔታዎች ያካትታል፡፡
1. የባከነ ሕይወት፡- ጊዜውን በአግባቡ የማይጠቀም ሰው የባከነ ሰው የትኛውን ተግባሩን መቼ ማከናወን እንዳለበትና ያም ተግባር ምን ያህል ጊዜውን እንደሚወስድበት በቅጡ ስለማያውቅ እንደባከነ ይኖራል፡፡
2. የተበታተነ ሕይወት፡- የተበታተነ ሕይወት ያለው ሰው ማለት ዋነኛ ተግባሩ ላይ ከማተኮር ይልቅ በእለቱ በፊቱ ቀርቦ ባገኘው ነገር የሚወሰድ ሰው ማለት ነው፡፡
3. የድካም ሕይወት፡- ጊዜውን በአግባቡ የመጠቀምን ባህል ያላዳበረ ሰው ብዙ የሚለፋ ሰው ነው፡፡ ብዙ ይንቀሳቀሳል እንጂ ብዙ ውጤትን አያስመዘግብም፡፡
4. የማይረካ ሕይወት፡- ጊዜውን በቁጥጥሩ ስር ያላዋለ ሰው በቀኑ መጨረሻ እቤቱ ሲገባ ምንም እንዳላከናወነ የሚሰማው ሰው ነው፡፡ ሰርቷል፣ ነገር ግን አላከናወነም፣ ሮጧል ነገር ግን አልደረሰም፣ ብዙ አስቧል ውሳኔ ላይ ግን አልደረሰም፡፡
5. ተፈላጊነት የሌለው ሕይወት፡- በሰዓቱ የማይገኝን ሰው ማን ይፈልገዋል? አንድን ተግባር በተፈለገበት ሰዓት የማያደርስን ሰው ማን ያስጠጋዋል? በዚህ ዘመን ተፈላጊው ሰው እንደ ቃሉ የሚገኝና የጀመረውን ነገር እፈጽማለሁ ባለው ሰዓት የሚፈጽም ሰው ነው፡፡
6. ያልተረጋጋ ሕይወት፡- በጊዜ አጠቃቀም ያልበሰለ ሰው ያልተረጋጋ ሰው ነው፡፡ የጊዜ አያያዝ ብልሃቱ የገባው ሰው ፕሮግራም ለማውጣት ለፍቶ በኑሮውና በስራ መስኩ ግን መረጋጋትን የመረጠ ሰው ነው፡፡
7. በግዳጅ ውስጥ የሚኖር ሕይወት፡- ጊዜውን በጥንቃቄ የማይጠቀም ሰው “እምቢ” ለማለት የማይችል ሰው ነው፡፡ ሰዎች የጠየቁትን ነገር ሁሉ ቢመቸውም ባይመቸውም እሺ በማለት ራሱን ሳይፈልግ ግዳጅ ውስጥ ይጨምራል፡፡
8. እቅድ-የለሽ ሕይወት፡- የጊዜና አጠቃቀም ያልገባው ሰው ሕይወትን የሚኖራት በመላ- ምትና በዘፈቀደ ነው፡፡
9. ግምገማ-የለሽ ሕይወት፡- ጊዜውን የሚጠቀም ሰው እያንዳንዱ ቀን፣ ሳምንት፣ ወርና አመት ካፈ በኋላ መለስ በማለት ራሱንና ስኬታማነቱን ይገመግማል፡፡
10. “መዘዘኛ” ሕይወት፡- ሰአቱን በሚገባ የማይጠቀምና ራሱን፣ አመለካከቱንና ተግባሩን ያልሰበሰበ ሰው ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለትዳር ጓደኛው፣ ለስራ ባልደረባውም ሆነ ለወዳጆቹ ሁሉ የኋላ ቀርነት ምክንያት ነው፡፡
ነገ ማለዳ፣ መደረግ ወይም መወገድ ስላለባቸው ተግባሮች ባህሪያት ይዤላችሁ እመለሳለሁ፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
👍133❤57😢4🎉4🔥1😁1🤩1
የሚደረገው፣ የሚተላለፈውና የሚወገደው!
“አድርገው፣ አሳልፈህ ስጠው፣ አዘግየው፣ ወይም አስወግደው” – Jack Canfield፡፡
ከዚህ ታዋቂ የስኬት አሰልጣኝ አባባል እንደምንማረው አንድን ተግባር አያያዝ ብዙ ገጽታዎች አሉት፡፡ አንድ አንድ ሰዎች ተግባርን በማከናወን ዙሪያ ሲያስቡ ያላቸው አመለካከት በሁለት ጽንፈኛ አመለካከቶች የተወሰነ ነው፡፡ በእንደነዚህ አይነት ሰዎች አመለካከት መሰረት ምርጫው ሁለት ብቻ ነው - ማድረግ ወይም ደግሞ ማስወገድ፡፡
ተግባሮቻችንን በወቅቱ የማጠናቀቅን እውነታ አስመልክቶ ግን እውነታው እዚያ ጋር ብቻ አያበቃም፡፡ በማድረግና በማስወገድ መካከል ሁለት አስፈላጊ ሂደቶች አሉ፡፡ እነዚህ ሂደቶች “ማዘግየት” እና “አሳልፎ መስጠት” የተሰኙ ሂደቶች ናቸው፡፡ ይህንን በማድረግና በማስወገድ መካከል ያለውን ጥበብ ማዳበር በጊዜ አጠቃቀም ሂደታችን ላይ ታላቅ የሆነ ተጽእኖ ያመጣል፡፡
በዚህ ምድር ላይ ማድረግ የሚገባውን ወይም የሚፈልገውን ተግባር ሁሉ ለመተግበር በቂ ጊዜ ያለው ሰው የለም፡፡ ከዚያም በተጨማሪ፣ አንድን ነገር ለማድረግ በቂ ጊዜ የለኝም በማለት ብቻ ያንን እቅድ ጨምድዶ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ መጣልም አይቻልም፡፡
በማድረግና በማስወገድ መካከል ያሉትን ደረጃዎች በጥበብ መጠቀም የግድ ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው እነዚህ ደረጃዎች “ማዘግየት” እና “አሳልፎ መስጠት” የተሰኙ ናቸው፡፡
አራቱን አስፈላጊ ደረጃዎች አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡፡
1. አድርገው
በዚህ “አድርገው” በሚለው ክፍል ውስጥ የሚመደብ ተግባር፡- 1) ተግባሩ መደረግ ያለበት የግድ በእኔ ሲሆን፣ 2) ተግባሩ መደረግ ያለበት የጊዜ ገደብ ወሳኝ ሲሆን፣ 3) የተግባሩ መደረግ አስፈላጊነት የጎላ ሲሆን፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ነጠቦች ተመዝኖ ሚዛን ያልደፋ ተግባር ወደሚቀጥለው “አዘግየው” ወደተሰኘው የሂደት መደብ ይተላለፋል፡፡
2. አዘግየው
በዚህ “አዘግየው” በሚለው ክፍል ውስጥ የሚመደብ ተግባር፡- 1) ተግባሩ ለተወሰነ ጊዜ ቢተላለፍ ሊያመጣ የሚችለው ችግር አናሳ ሲሆን፣ 2) ተግባሩ ለሌላ ቀን የተላለፈበት ምክንያት አሳማኝ ሲሆን፣ 3) ለተግባሩ ሊመደብ የሚችል ሌላ በቂ ጊዜ የመኖሩ ጉዳይ እርግጠኛ ሲሆንና ቀጠሮ ሲሰጠው፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ነጠቦች ተመዝኖ ሚዛን ያልደፋ ተግባር ወደሚቀጥለው “አሳልፈህ ስጠው” ወደተሰኘው የሂደት መደብ ይተላለፋል፡፡
3. አሳልፈህ ስጠው
በዚህ “አሳልፈህ ስጠው” በሚለው ክፍል ውስጥ የሚመደብ ተግባር፡- 1) ተግባሩ በእኔ ባይከናወን ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት አናሳ ሲሆን፣ 2) ተግባሩን በሚገባ ሊያከናውን የሚችል ሰው ሲገኝ፣ 3) ተግባሩ በሌላ ሰው እጅ ሲገባ በወቅቱና በተጠበቀው ጥራት የመከናወኑን ሁኔታ መቆጣጠር ሲቻል፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ነጠቦች ተመዝኖ ሚዛን ያልደፋ ተግባር ወደሚቀጥለው “አስወግደው” ወደተሰኘው የሂደት መደብ ይተላለፋል፡፡
4. አስወግደው
በዚህ “አስወግደው” በሚለው ክፍል ውስጥ የሚመደብ ተግባር፡- 1) ተግባሩን ለማከናወን የምንችለውን ያህል ሞክረን ማድረግ ሲሳነን፣ 2) ተግበሩ ባይደረግ ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት በሚገባ ተጠንቶ እጅግ አናሳ ሲሆን፣ 3) የተግባሩ መከናወን ሁኔታ የሚመለከታቸውን ሰዎች ተገቢውን መረጃ የሰጠንለት ሁኔታ ሲሆን፡፡
የማድረግ፣ የማዘግየት፣ አሳልፎ የመስጠትና የማስወገድ ጥበብ ስኬታማነታችንን ያበዛዋል፣ ትኩረታችንንም ያጠናክረዋል፡፡ ነገሮችን እየጎተቱ ከመቆየትና ተግባሩንም ሆነ በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎችን ልብ ከመጎተት ይጠብቀናል፡፡
Have a nice weekend!
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-
1050816404958639/

👍88❤60🎉4😁1
ገና ያላገባችሁ ተከታታዮቼ ስለ ወደፊት ትዳር አጋራችሁ ሁኔታ በሚገባ እንድታስቡበት ለማንቃት ያህል የጠየኩትን ጥያቄ ተከትሎ ከመጡልኝ መልሶች በመነሳት የተወሰኑ መልሶችን እሰነዝራለሁ፡፡
የማንቂያ ጥያቄዬ አንዲህ የሚል ነበር፡-
“ልታገቡት የምታስቡት ሰው ላለፈው አንድ አመት ያሳያችሁን ባህሪ ንገሩኝና ወደፊት ምን አይነት የትዳር ሕይወት እንደሚኖራችሁ ልንገራችሁ!”
አንዷ ስለፍቅረኛዋ እንዲህ ትላለች . . .
“ስራ መስራት አይፈልግም ማገልገል ነው የሚወደው በጣም መንፈሳዊ ነገር ብቻ ነው ማውራት ያበዛል እኔ ብቻ እንድሰራ ነው የሚፈልገው”
መላ-ምት
ፍቅረኛሽ እስክትጋቡ ድረስ ወይም ደግሞ ከተጋባችሁ በኋላ ይህንን ባህሪይውን ሊለውጥ የመቻሉ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ . . .
• የቤታችሁን የገንዘብ ወጪ ሸክም እንደተሸከምሽ ልትኖሪ እንደመትችይ ጠብቂ . . .
• ልጆች ከወለድሽ በኋላ እንኳን ከልጆችሽ ጋር ብዙ ሳታሳልፊ ለኑሮ ብለሽ ወደስራ ተቻኩለሽ እንደምትመለሽ ጠብቂ . . .
• ለምን እንደማይሰራ ስትሞግቺው መንፈሳዊ ስራ እንደሚሰራ፣ ያንን እንዲተው እንደጠየቅሺውና አንቺ መንፈሳዊ ያልሆንሽ ሰው እንደሆንሽ በመናገር እንደኮነነሽ ልትኖሪ እንደምትችይ ጠብቂ . . .
• በመንፈሳዊ አገልግሎትን በመስጠት ወይም በዚያ ሰበብ ቤቱን ችላ እንደሚል፣ አአብዛኛው ጊዜ ከቤት ይልቅ ውጪ ውጪውን እንደሚልና ይህንንም ተግባሩን፣ “ፈጣሪን ማመን ነው” በሚል ሽፋን አንቺው እንድትወጪው እንደሚተውልሽ ጠብቂ፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የማንቂያ ጥያቄዬ አንዲህ የሚል ነበር፡-
“ልታገቡት የምታስቡት ሰው ላለፈው አንድ አመት ያሳያችሁን ባህሪ ንገሩኝና ወደፊት ምን አይነት የትዳር ሕይወት እንደሚኖራችሁ ልንገራችሁ!”
አንዷ ስለፍቅረኛዋ እንዲህ ትላለች . . .
“ስራ መስራት አይፈልግም ማገልገል ነው የሚወደው በጣም መንፈሳዊ ነገር ብቻ ነው ማውራት ያበዛል እኔ ብቻ እንድሰራ ነው የሚፈልገው”
መላ-ምት
ፍቅረኛሽ እስክትጋቡ ድረስ ወይም ደግሞ ከተጋባችሁ በኋላ ይህንን ባህሪይውን ሊለውጥ የመቻሉ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ . . .
• የቤታችሁን የገንዘብ ወጪ ሸክም እንደተሸከምሽ ልትኖሪ እንደመትችይ ጠብቂ . . .
• ልጆች ከወለድሽ በኋላ እንኳን ከልጆችሽ ጋር ብዙ ሳታሳልፊ ለኑሮ ብለሽ ወደስራ ተቻኩለሽ እንደምትመለሽ ጠብቂ . . .
• ለምን እንደማይሰራ ስትሞግቺው መንፈሳዊ ስራ እንደሚሰራ፣ ያንን እንዲተው እንደጠየቅሺውና አንቺ መንፈሳዊ ያልሆንሽ ሰው እንደሆንሽ በመናገር እንደኮነነሽ ልትኖሪ እንደምትችይ ጠብቂ . . .
• በመንፈሳዊ አገልግሎትን በመስጠት ወይም በዚያ ሰበብ ቤቱን ችላ እንደሚል፣ አአብዛኛው ጊዜ ከቤት ይልቅ ውጪ ውጪውን እንደሚልና ይህንንም ተግባሩን፣ “ፈጣሪን ማመን ነው” በሚል ሽፋን አንቺው እንድትወጪው እንደሚተውልሽ ጠብቂ፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍116❤23😁4🎉2😢1
የማንቂያ ጥያቄዬ አንዲህ የሚል ነበር፡-
“ልታገቡት የምታስቡት ሰው ላለፈው አንድ አመት ያሳያችሁን ባህሪ ንገሩኝና ወደፊት ምን አይነት የትዳር ሕይወት እንደሚኖራችሁ ልንገራችሁ!”
አንዱ ስለፍቅረኛው እንዲህ ይላል . . .
“ከሌላ ወንድ ጋ አብዝቶ መደዋወል”
መላ-ምት
ፍቅረኛህ እስክትጋቡ ድረስ ወይም ደግሞ ከተጋባችሁ በኋላ ይህንን ባህሪይዋ ልትለውጥ የመቻሏ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ . . .
• አንዲት ያገባች ሴት ከወንድ ጓደኛ ጋር በቅርብ አብሮ ማሳለፍ፣ መደዋወልም ሆነ “ቻት” ማድረግ ችግር የለበትም የሚል ፍልስፍናዋን አምነህበት እንድትኖ ወደመገደድ እንደምትወስድህ ጠብቅ . . .
• ይህንን ባህሪዋን ስትሞግታት፣ “ቀናተኛ እንደሆንክ” መልሳ አንተንው እንደምትከስህ ጠብቅ . . .
• ሁኔታውን ለማረም ካልፈለገች ጓደኝነቷ ሌላ መልክ እንደነበረው ወይም መልኩን እየቀየረ እንደሄደ ወደማወቅ እንደምትመጣ ጠብቅ . . .
• ሁኔታው ብዙ ከቆየና ከጎዳህ አንተም ሳትፈልገው ግድ የለሽ ወደሆነ ግንኙነት ልታዘነብል እንደምትችል ጠብቀ . . .
• በመጨረሻም አብራችሁ እየኖራችህ በስሜትና በአካል ወደመራራቅ፣ አልፎም እስከ ፍቺ ሊያደርሳችሁ እንደሚችል ጠብቅ፡፡

👍83❤42😱4🎉1
የማንቂያ ጥያቄዬ አንዲህ የሚል ነበር፡-
“ልታገቡት የምታስቡት ሰው ላለፈው አንድ አመት ያሳያችሁን ባህሪ ንገሩኝና ወደፊት ምን አይነት የትዳር ሕይወት እንደሚኖራችሁ ልንገራችሁ!”
አንዷ ስለፍቅረኛዋ እንዲህ ትላለች . . .
ብዙ ጊዜ ስደውልለት እና ቴክስት ስልክለት አያነሳም፡፡ አልፎ አልፎ ነው የሚደውልልኝ ፤ እሱም እኔ ያለሁበት ከተማ ሲመጣ ይደውላል፡፡ የማያቋርጥ እና ምርጥ ምርጥ የፍቅር የጽሑፍ መልክት በቀን በቁጥር በዛ ያሉ ይልክልኛል። በአካል ለማግኘት በጣም ይጥራል ለማሳመን ብዙ ይለፋል። እንደሚያፈቅረኝ፤ በዚህ አለም ላይ እንደ እኔ የሚያፈቅረው እንደሌለ እየማለ እየተገዘተ ይነግረኛል፡፡ ስንገናኝ አብረን እንድናድር/ ግንኙነት እንድናደርግ ፍላጎቱ ከፍተኛ ነው። በዚህም ነው ግጭታችን፤ ሰለማትወጅኝ እና ሰለማታምኚኝ ነው በሚል፡፡
መላ-ምት
ፍቅረኛሽ እስክትጋቡ ድረስ ወይም ደግሞ ከተጋባችሁ በኋላ ይህንን ባህሪይውን ሊለውጥ የመቻሉ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ . . .
• ከእሱ ጋር ያለሽ “ድራማ” ከመጋባታችሁ በፊት እንደጀመረ፣ ካልጀመረም በቅርብ እንደሚጀምር ጠብቂ፣
• አንቺ ከተማ በማይኖርበት ጊዜ ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት እንዳለው ልትሰሚ እንደምትችይ ጠብቂ፣
• ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ኖረውም አልኖረውም አንቺን የሚፈልግሽ ለወሲብና ለወሲብ ብቻ እንደሆነ የምትደርሺበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን ጠብቂ፣
• የፈለገውን የወሲብ ግንኙነት ካላገኘ ወይም ደገሞ አግኝቶ እንደረካ ሲሰማውና ስትሰለችው በድንገት ከሕይወትሽ እንደሚወጣ ጠብቂ፣
• ሁኔታው ከዚህ አልፎ ወደጋብቻ ከገባችሁ ለስሜትሽ ብዙም ግድ የሌለው፣ ብዙም የማያከብርሽና ለወሲብ እርካታ ብቻ ሲፈልግሽ መልካም ሆኖ የሚቀርብሽ አይነት ባል ሆኖ እንደምታገኚው ጠብቂ . . .
ምክረ-ሃሳብ
1. ከፍቅረኛሽ ጋር ባለሽ ግንኑነት፣ እንደ ሴክስ (sex) ማድረግና የመሳሰሉትን የግል ቀይ መስመር የሆኑትን ሁኔታዎችሽን በመግለጽ ደግሞ እንዳይጠይቅሽ አሳውቂው፡፡
2. በግንኙነታችሁ ላይ ያለውን የወደፊት አላማ በንግግርና በተግባር እንዲገልጽ እድል ስጪው፡፡
3. አንቺን በስልክና በቴክስት ለማግኘት ያለውን ፍላጎት እንዲያሳይ እንደመትጠብቂ አሳውቂው፡፡
4. ለውጥ የማያመጣ ከሆነ ከእሱ ጋር ምን ያህል ጊዜ በመቆየት እንደትምትጠብቂው የጊዜ ገደብ አስቀምጪና በዚያ የጊዜ ገደብ ለመመራት ሞክሪ፡፡

👍108❤27
የማንቂያ ጥያቄዬ አንዲህ የሚል ነበር፡-
“ልታገቡት የምታስቡት ሰው ላለፈው አንድ አመት ያሳያችሁን ባህሪ ንገሩኝና ወደፊት ምን አይነት የትዳር ሕይወት እንደሚኖራችሁ ልንገራችሁ!”
አንዷ ስለፍቅረኛዋ እንዲህ ትላለች . . .
ፍቅረኛዬ ስራ አለው፡፡ ደሞዙም ጥሩ ነው! ግን ተጋብተን አብረን እንኑር ብሎኝ አያውቅም፡፡ እንገናኛለን ጥሩ ጊዜ እናሳልፋለን በቀን 2 ጊዜ እንደዋወላለን በጣም በስራ ቢዚ ሰው ነው፡፡ ተቀጥሮ ነው ሚሰራው፡፡ 35 አመቱ ነው፣ እኔ 28፡፡ ከተዋወቅን 5 አመት ሆኖናል! በጣም መልካም ሰው ነው፡፡ መች ነው ምንጋባው ስለው እግ/ር ሲፈቅድ ነው ሚለው፡፡ ጊዜው ይሄዳል ምንም የተለየ ባህሪ አሳይቶኝ አያውቅም አንድ አይነት ባህሪ ነው ሚያሳየኝ!! እኔ በተማርኩበት ባይሆንም ተቀጥሬ እየሰራው ነው ደሞዜ እናቴን ከመደገፍ አልፎ አያውቅም!!

• በግንኙነቱ ገና ያላመነበት ሊሆን እንደሚችልና የተወሰኑ አመታቶችሽ ከባከኑ በኋላ ሃሳቡን ሊቀይር እንደሚችል ጠብቂ . . .
• ግንኙነታችሁን የሚያቆየው የሚፈልገውን ጊዜያዊ ጥቅም እስካገኘ ድረስ እንደሚሆንና ያንን ያስቀረሽበት የመሰለው ቀን ሊለይሽ እንደሚችለ ጠብቂ . . .
• በደሞዝና በመሳሰሉት ነገሮች እንደሚበልጥሽና የበላይነት እንዳለው ሊሰማው እንደሚችልና የትም አትሄድም በማለት በዚሁ ሊቀጥል እንደሚችል ጠብቂ . . .
• ከጥቂት አመታት በኋላ እድሜሽ እየሄደ እንደሆነ እንደምትባንኚ እና ስሜታዊ መሆንና መፍጨርጨር (desperation) ውስጥ አንደምትገቢ ጠብቂ . . .
• አንቺ ጠባቂ፣ እሱ ደግሞ አስጠባቂ . . . አንቺ ተለማምጠሸ፣ እሱ ደግሞ ኮራ ብሎ በግንኙነት እንደምትቆዩ፣ ከተጋባችሁም ያንንው ሁኔታችሁን ይዛችሁ እንደምትኖሩ ጠብቂ . . .
ምክረ-ሃሳብ
1. ከፍቅረኛሸ ጋር “ጥሩ ጊዜ እናሳልፋለን” በማለት ሰበብ ዘላቂ የሆነውን የጋራ አላማችሁን ችላ እንዳትይ ተጠንቀቂ፡፡
2. “እግዚአብሔር ሲፈቅድ” የሚለውን ሃሳቡን ከራሱ ፍላጎት ለይቶ እንዲነግርሽና የእሱን ፍላጎት ማወቅ እንደምትፈልጊ በጥብቅ አሳስቢው፡፡
3. የጋብቻ ጉዳይ የአንድ ሰው ብቻ ፈቃድና ፍላጎት ሳይሆን የሁለታችሁም እንደሆነ በማሰብ፣ “መቼ ነው የምንጋባው” ብቻ ሳይሆን፣ “በዚህ ጊዜ እንድንጋባ እፈልጋለሁ” የሚለውን ሃሳብ ጠንከር ባለ መልኩ ማቅረብ እንዳለብሽ ራስሽን አሳምኚ፡፡
4. አንዳንድ ወንዶች እውነተኛ ሆነው ሳለ ውሳኔ ላይ ድፍረት ሊጎድላቸው እንደሚችል በማሰብ ወደ ውሳኔ የምትሄዱበትን መንገድ አመቻችለት፡፡

👍135❤32🔥6😁3😱1
የጉንዳኗ ትምህርት
አንዲት ጉንዳን ከእሷ ክብደት አስር እጥፍ የሚከብድን አንድ ለምግብ የሚሆናትን ነገር ተሸክማ ወደፊት ትገሰግሳለች፡፡ አንድ መንገደኛ ሰው በዚያ ሲያልፍ አንገቱን አቀርቅሮ ካያት በኋላ እግሩን አንስቶ ሊጨፈልቃት ትንሽ እስከሚቀረው ድረስ በላይዋ ላይ አድርጎ፣ “ይህቺን ጉንዳን እኮ አንዴ በጫማዬ ብጨፈልቃት ያልቅላታል፣ ይህ ጉዞዋ፣ ስራዋና ሕይወቷ በእኔ ውሳኔ ስር ነው” እያለ ለራሱ ሲያወራ አንድ በዚያ የሚያልፍ ጓደኛው አየውና፣ “ብቻህን እንደ እብድ የምታወራው ምን ሆነህ ነው? አቀርቅረህ የምታየውስ ምንድን ነው?” አለው፡፡ መንገደኛውም በጉንዳኗ ላይ ሊያደርግ ያሰበውን ነገረው፡፡
መንገደኛውም ወደጓደኛው ዘወር በማለት፣ ለራሱ ያወራ የነበረውን የጉንዳኗ ሕይወት በእሱ ውሳኔና ቁጥጥር ስር እንዳለ ደገመለት፡፡ ጓደኛውም፣ “መስሎህ ነው እንጂ የጉንዳኗ ሕይወት በፈጣሪዋ እጅ እንጂ በአንተ እጅ አይደለም” አለው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ ከተከራከሩ በኋላ መንገደኛው፣ “እንግዲያውስ አሳይሃለሁ” ብሎ ሊጨፈልቃት ዘወር ሲል ለካ እሱ ሲዝትባትና ከጓደኛውም ጋር ሲከራከሩ ከሁኔታው የተነሳ ምንም ሳትቆምና ግራና ቀኝ ሳትል ዝም ብላ መንገዷ ላይ አተኩራ ትገሰግስ የነበረችው ጉንዳን ርቃ ሄዳ ተሰውራለች፡፡
የዚህች ጉንዳን ዋና መልእክት . . .
• ሰው ስለዛተባችሁ አይደለም የእናንተ ነገር የሚቆመው፣ እናንተ በዛቻው ምክንያት ስትቆሙ ነው የእናንተ ነገር የሚቆመው፡፡
• ሰው አጠፋችኋለሁ ስላለ አይደለም እናንተ የምትጠፉት፣ ይህ ሰው ሊያጠፋኝ ነው ብላችሁ ስትፈሩና ስትጨነቁ ነው የምትጠፉት፡፡
• ሰው አበቃላቸው ስላላላችሁ አይደለም እናንተ የሚያበቃላችሁ፣ እናንተ አለቀልኝ ስትሉ ነው የሚያበቃላችሁ፡፡
ምንም ሆነ ምንም ዝም ብላችሁ መንገዳችሁን ቀጥልሉ ምንም ተባለ ምንም ዝም ብላችሁ ስራችሁ ላይ አተኩሩ!

👍157❤68🔥11😱1🎉1
የብዙ ሰዎች “ጀምሮ የመጨረስ” ጥያቄ!
የማከናውናቸው ተግባሮችና ስራዎች በርካታ በመሆናቸው፣ እነዚህን ተግባሮች ለመጀመር እንዴት መነሳሳቱን (motivation) እንደማገኝ፣ እንዲሁም በምን አይነት ዲሲፕሊን እንደምቀጥልና እንደምጨርስ ከልምምዴ በመነሳት እንዳጋራቸው የሚጠይቁኝ ተከታታዮች በርካታ ናቸው፡፡
እነዚህ ጥያቄዎች ሲጨመቁ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-
1. አንድን ያሰቡትን ነገር መጀመር እንዴት ይቻላል? (ይህ የmotivation ጥያቄ ነው)
2. አንድን የጀመሩትን ነገር እንዴት ካለማቋረጥ መቀጠል ይቻላል? (ይህ የdiscipline ጥያቄ ነው)
3. አንድን የቀጠሉትን ነገር ታስቦ በተጀመረበት ጥራትና ብቃት እንዴት መጨረስ ይቻላል? (ይህ የfocus ጥያቄ ነው)
ከእነዚህ ተያያዥ ጥያቄዎች በመነሳት . . .
“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”) የተሰኝ ለአራት ቀናት ብቻ የሚቆይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡
• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)
• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡
• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡
• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡
• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡
ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

👍67❤22😢3😁1
የማንቂያ ጥያቄዬ አንዲህ የሚል ነበር፡-
“ልታገቡት የምታስቡት ሰው ላለፈው አንድ አመት ያሳያችሁን ባህሪ ንገሩኝና ወደፊት ምን አይነት የትዳር ሕይወት እንደሚኖራችሁ ልንገራችሁ!”
አንዷ ስለፍቅረኛዋ እንዲህ ትላለች . . .
“እጮኛዬ፣ 1) የሰዎች (ከሴትም ከወንድም) ስም አቆላምጦ የመጥራትና ከሁሉም ጋር እየሳቀ የማውራት የመቀለድ ባህሪ አለው ይሄ ባህሪው ለእኔ ምቾት አይሰጠኝም, 2) ሁሌም ቢሆን ሚስት ከባሏ ቀደማ እቤት መገኘት አለባት የሚል እምነት አለው፡፡
መላ-ምት
ፍቅረኛሽ እስክትጋቡ ድረስ ወይም ደግሞ ከተጋባችሁ በኋላ ይህንን ባህሪይውን ሊለውጥ የመቻሉ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ . . .
• ከተጋባችሁ በኋላ ጾታ ሳይለይ በቁልምጫ የሚጠራውንና የሚቀልደውን ባህሪውን ሊቀጥልበት እንደሚችልና በዚያም ምክንያት እንደተበሳጨሽ እንደምትኖሪ ጠብቂ፤
• ሴቶችን በቁልምጫ ሲጠራናቸው አንዳንዶቹ እሱ ባላሰበው መልኩ ተርጉመውት ወደአላስፈላጊ መቀራረብ የመሳብና እሱንም ለዚያ ሁኔታ የማጋለጥ ሁኔታ ለከሰት እንደሚችል ጠብቂ፤
• ምናልባት የቅንአት ችግር ካለብሽ ይህንን አቀራረቡ ለመቆጣጠር መሞከርሽ ስለማይቀር የከረረ ጸብ ውስጥ ልትገገቡና እንደተበጣበጣችሁ ልትኖሩ እንደምትችሉ ጠብቂ፤
• ከተጋባችሁ በኋላ እቤት ቀድመሽው የመግባትሽን ፍላጎቱን ወደ ግዴታ ለውጦት ስራ መስራት እንደለሌለብሽ ወደማስገደድ እስከመድረስ ሊሄድ አንደሚችልና ወይ ለሰላማችሁ ስትይ ከሕልምሽ እንደምትፋቺ፣ ወይም “እምቢ” በማለት በመካከላችሁ ክፍተት ሊፈጠር እንደሚችል ጠብቂ፤
• በወንድ የበላይነት የማመንን (chauvinist) ዝንባሌ እንዳለውና በዚያም አመለካከቱ ምክንያት ቤት ውስጥ ምንም አይነት ስራን ያለማገዝ ሁኔታን ሊያንጸባርቅ እንደሚችል ጠብቂ፡፡
ምክረ-ሃሳብ
1. የፍቅር ግንኙነት ወቅት የመጠናናትም ጊዜ በመሆኑ፣ በጠቀስሻቸው አሳሳቢ ሁኔታዎች አንጻር የመመጣጠናችሁን ሁኔታ በሚገባ ለመመልከት ጊዜ ውሰጂ፡፡
2. ፈጽሞ ልትቀበይው የማትችያቸውን ነገሮች በግለጽ ነግረሽው እንዲያስተካክል ጊዜን ስጪው፣ ካላስተካከለ ደግሞ ምን የሚኖርሽን ምላሽ በሚገባ ለይተሽ እውቂ፡፡
3. ሁኔታዎቹን ካላስተካከለና ከነችግሩ ወደ ትዳር መግባትን ካመንሽ፣ እስከወዲያኛው ለመሸከም ያመንሽባቸው ሁኔታዎች መሆናቸውን እርግጠኛ ሁኚ፡፡

👍76❤21😱2
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች “ጀምሮ የመጨረስ” ጥያቄ!
የማከናውናቸው ተግባሮችና ስራዎች በርካታ በመሆናቸው፣ እነዚህን ተግባሮች ለመጀመር እንዴት መነሳሳቱን (motivation) እንደማገኝ፣ እንዲሁም በምን አይነት ዲሲፕሊን እንደምቀጥልና እንደምጨርስ ከልምምዴ በመነሳት እንዳጋራቸው የሚጠይቁኝ ተከታታዮች በርካታ ናቸው፡፡
እነዚህ ጥያቄዎች ሲጨመቁ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-
1. አንድን ያሰቡትን ነገር መጀመር እንዴት ይቻላል? (ይህ የmotivation ጥያቄ ነው)
2. አንድን የጀመሩትን ነገር እንዴት ካለማቋረጥ መቀጠል ይቻላል? (ይህ የdiscipline ጥያቄ ነው)
3. አንድን የቀጠሉትን ነገር ታስቦ በተጀመረበት ጥራትና ብቃት እንዴት መጨረስ ይቻላል? (ይህ የfocus ጥያቄ ነው)
ከእነዚህ ተያያዥ ጥያቄዎች በመነሳት . . .
“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”) የተሰኝ ለአራት ቀናት ብቻ የሚቆይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡
• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)
• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡
• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡
• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡
• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡
ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::
@DrEyobmamo
የማከናውናቸው ተግባሮችና ስራዎች በርካታ በመሆናቸው፣ እነዚህን ተግባሮች ለመጀመር እንዴት መነሳሳቱን (motivation) እንደማገኝ፣ እንዲሁም በምን አይነት ዲሲፕሊን እንደምቀጥልና እንደምጨርስ ከልምምዴ በመነሳት እንዳጋራቸው የሚጠይቁኝ ተከታታዮች በርካታ ናቸው፡፡
እነዚህ ጥያቄዎች ሲጨመቁ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-
1. አንድን ያሰቡትን ነገር መጀመር እንዴት ይቻላል? (ይህ የmotivation ጥያቄ ነው)
2. አንድን የጀመሩትን ነገር እንዴት ካለማቋረጥ መቀጠል ይቻላል? (ይህ የdiscipline ጥያቄ ነው)
3. አንድን የቀጠሉትን ነገር ታስቦ በተጀመረበት ጥራትና ብቃት እንዴት መጨረስ ይቻላል? (ይህ የfocus ጥያቄ ነው)
ከእነዚህ ተያያዥ ጥያቄዎች በመነሳት . . .
“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”) የተሰኝ ለአራት ቀናት ብቻ የሚቆይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡
• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)
• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡
• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡
• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡
• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡
ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::
@DrEyobmamo
👍58❤7😁1
በቲፎዞ የሰከረ ማንነት!
ቻርልስ ብሎንዲን (Charles Blondin) በቀጭን ገመድ ላይ በመራመድ የታወቀ ፈረንሳዊ ነው፡፡ በዘመኑ እጅግ ዝነኛ የነበረው ይህ ሰው ከአንድ ግዙፍ ህንጻ ወደሌላኛው ህንጻ በተዘረጋ ቀጭን ገመድ ላይ በመራመድ ተመልካቹን ትንፋሽ በማሳጠር የታወቀ ሰው ነው፡፡
በቀጭን ገመድ ላይ ከተራመደባቸው የከፍታ ስፍራዎች አንዱ በአሜሪካና በካናዳ ጠረፍ ላይ በሚገኘው ናያግራ ፏፏቴ (Niagara Falls) ከፍታ ላይ ያደረገው ይደነቅለታል፡፡ ከአሜሪካ ግዛት እስከ ካናዳ ግዛት የፏፏቴው ጥጎች የተዘረጋውን ቀጭን ገመድ በመራመድ ከተሻገረ በኋላ እንደገና ወደ አሜሪካው ግዛት በገመዱ ላይ ሲመለስ የሚመለከተው ህዝብ ስለእርሱ ጭንቅ ይዞት ነበር፡፡ የሕዝቡ ጩኸት ቀልጧል፡፡ “አንተን የሚያክል የለም፣ ጀግና ነህ … ” አሉት፡፡
ሁሉም ሰው ከተረጋጋ በኋላና ሕዝቡን ካመሰገነ በኋላ አንድ ጥያቄ ጠየቃቸው፣ “በእርግጥም ጎበዝ እንደሆንኩ ታምናላችሁ?” አላቸው፡፡
ሕዝቡ በአንድ ድምጽ፣ “አንተ የምታደርገውን ሊያደርግ የሚችል ፈጽሞ አይገኝም፤ ምንም ነገር ማድረግ ትችላለህ” በማለት አረጋገጡለት፡፡
“ይህን ያህል ካመናችሁብኝ ከእናንተ መካከል በትከሻዬ ላይ ተሸክሜው እንደገና በዚህ ቀጭን ገመድ ላይ እንድራመድ ፈቃደኛ የሆነ ሰው ማን ነው?” አለ፡፡ ሕዝቡ በጸጥታ ተሞላ፡፡ አንድም ሰው ፈቃደኛ ሊሆን አልፈለገም፡፡
ብሎንዲን ወደ አንድ የቅርብ ወዳጁ ዘወር በማለት ፈቃደኝነቱን ጠየቀው፡፡ ይህ ወዳጁ ከፍታን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ ትንሽ የወላወለው ይህ ወዳጁ በመጨረሻ ተስማማና ትከሻው ላይ ሆኖ ያንን አስፈሪ ከፍታ አብረው ተሻገሩ፡፡ ይህ የቀጭን ገመድ ተራማጅ አድናቂዎቹ ብዙዎች፣ አጋሩ ግን አንድ ሰው ብቻ እንደ ነበር የተገለጠለትና ከደጋፊ ብዛት ከተጠናወተው ስካር ሰከን ያለው ያን ጊዜ ነው፡፡
የሰው ልጅ የሚሰክረው በአልኮል መጠጥ ብቻ አይደለም፡፡ የሰው ልጅ በስኬት፣ በገንዘብ ብዛትና በመሳሰሉት ጊዜያዊ ነገሮች ሊሰክር ይችላል፡፡ ከዚህ የከፋው የስካር አይነት ግን ከጀርባው የሚደግፈው ቲፎዞ የበዛ ሲመስለውና “ጀግና” የሚለው ሰው ሲበራከት ራሱን የመግዛት ብቃት ከሌለው የሚሰክረው ስካር ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ነው ልክ አንድ በመጠጥ ተጽእኖ ስር ወድቆ የሰከረ ሰው የሚያደርገውን እንደማያውቅ ሁሉ በመደነቅ ተጽእኖ ስር ወድቆ የሰከረ ሰውም ማመዛዘን የሚሳነው፡፡
አጭር ምክር …
• ያደነቀን ሁሉ አብሮን የሚዘልቅ አጋር እንዳይመስለን፡፡ ዛሬ “ሆ” ያለን ሰው ሁሉ ነገ ሕይወት የየራሱን የቤት ስራ (Assignment) ሲሰጠው ከእኛ ዘወር ሊል የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል፡፡
• ወደዚህ አለም የመጣነው ብቻችንን ነው፣ የምንሰናበተውም ብቻችንን ነው … በመካከሉ ግን በዚህ ምድር ላይ ባለን ቆይታ ለብቻችን ስንሆን የሚሞግት ህሊና ከፈጣሪ ተሰጥቶናል ሕሊናችንን ብናደምጠው ይበጀናል፡፡
• ከደጋፊዎችና ከአድናቂዎች ብዛት የሚኖርን ግለት አንድ ቀን በረድ እንደሚል አንርሳ፡፡ ያን ጊዜ የምንነጋገረው ከእውነት ጋር ነው፡፡ እውነት በመጀመሪያ ስትመክር ለስላሳ ነች፣ ካልሰማናት ግን በኋላ ስትፈርድ ጨካኝ ነች፡፡
• ከአእላፋት ደጋፊዎች ኃይል ይልቅ የአንዲት እውነት ጉልበት እንደምትበረታና እንደምታሸንፍ እናስታውስና ዛሬውኑ በሰከነ አእምሮ ከእውነት ጋር እንስማማ፡፡

❤89👍76🔥6
ጀምረን የመጨረሳችን ጉዳይ!
ያሰብነውን ነገር የማንጀምረው ለምንድን ነው?
የጀመርነውንስ ነገር የማንጨርሰው ለምንድን ነው?
• ምናልባት አንድን ነገር የምንጀምርበትን ዋና ዓላማ አላወቅነውም ይሆናል!
• ምናልባት ዓላማችንን አውቀን ሳለን የዲሲፐልን ጉድለት ይኖርብን ይሆናል!
• ምናልባት ደግሞ የመጀመር፣ የመቀጠልና ጥጉ ድረስ የመውሰድ ክህሎት ይጎድለን ይሆናል!
• ምናልባት ከራሳችን ጋር ወይም ከሰዎች ጋር የማያስማማ አጉል ባህሪይ አስቸግሮን ይሆናል!
ማንኛውም ሰው አንድን ነገር ካለምክንያት መጀመር አያስቸግረውም!
ማንኛውም ሰው አንድን የጀመረውን ነገር ካለምክንያት መቀጠልና መጨረስ አያስቸግረውም!
|በዚህ እውነታ ዙሪያ በመሰልጠን ጀምራችሁ የምትጨርሱ ሰዎች ለመሆን ከፈለጋችሁ ይሀቺ አጭር ስልጠና አያምልጣችሁ፡፡
• የስልጠናው ርእስ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

👍41❤9😁2🎉1