Telegram Web Link
ጥያቄ፡

ሰላም ዶክተር በቅድሚያ ስለምትሰጣቸው ምክሮች ላመሰግንህ እወዳለሁ...... የምክር አገልግሎት ፈልጌ ነበር የመጣሁት ጾታዬ ወንድ ነው፡፡ ወደ ጥያቄዬ ስገባ አሁን የጊቢ ተማሪ ነኝ። ጊቢ ከመግባቴ በፊት በእንጀራ አባቴ በተደጋጋሚ የመደፈር ጥቃት ደርሶብኝ ነበር ከዛ በኋላ እኔም ከተለያዩ ወንዶች ጋር ግንኙነት እፈፁም ነበር።

አሁን ይሄ ሁሉ ነገር አልፎ ከእንደዚህ አይነት ልምምድ ውስጥ ከወጣሁኝ አንድ አመት ሆኖኛል። ግን በቅርቡ ጊቢ ገብቼ ከተዋወኩት ጓደኛዬ ጋር ተጣልተን አንድ ላይ መሆን አቁመናል። በጣም ነበር የምንዋደደውና የምንተሳሰበው እርሱ የራሱን ዶርም ትቶ ከእኔ ጋር አንድ አልጋ ላይ ነበር የምናድረው አንድ ላይ ነበር ምንቀሳቀሰው ልጁ በጣም ጥሩ ልጅ ነው። ግን ከተጣላን በኋላ ሁሉም ነገር ሲቀየር እኔ በጣም እየተጎዳው ነው፡፡

አንድ class ስለሆንን ሳየው በጣም ይከፋኛል ዶርም ገብቼ አለቅሳለሁ፡፡ እርሱ ግን በመጣላታችን ምንም አልመሰለውም፡፡ እኔ ግን የሌለ ድብርት ውስጥ ገብቻለሁ ብዙ ነገር የማደርገው ከእርሱ ጋር ስለሆነ አሁን ብቻዬን ስሆን እንኳን በጣም ይከፋኛል። ዶክተር መፍትሄው ምንድነው ምንአልባት የበፊት ህይወቴ ተጽእኖ አድርጎብኝ ይሆን እንደዛም ነው ብዬ እንዳልል ደግሞ ልጁን በንፁሁ ጓደኝነት ብቻ ነው የምቀርበው ሌላ ነገር አስቤ እንኳን አላውቅም። እና ከልጁ ጋር ከመጣላቴ ብቻ የእኔ እንደዚህ መሆን ትክክለኛ ነገር ይመስልሃል???

መልስ፡

ከደረሰብህ የወሲብ ጥቃትና በማገገምህና ከዚያም የመውጣት ምልክት በማየትህ እንኳን ደስ አለህ፡፡ ሆኖም፣ አብሮህ ከሚማር ልጅ ጋር ያለህ ትስስርና የገለጽካቸው ሁኔታዎች ጤናማ የግንኙነትን ቅርበትንና ሂደትን አያመለክቱም፡፡

1. ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ሰዎች አንተ በምትለው መልኩ ሊለያዩ እስከማይችሉ ድረስ “መጣበቃቸው” የጥሩ ጓደኝነት መልክ የያዘ ቢመስልም ሚዛኑን የሳተ ነው፡፡

2. ከዚህ በፊት ከነበረህ የተመሳሳይ ጾታ የተሳሳተ ግንኙነት አንጻር ሲታይ፣ ከአንድ ወንድ ጋር በዚህ መልኩ አብራችሁ እንከማደር ድረሰ መቀራረብህ አንተ በማታስበው መልኩ የተመሳሳይ ጾታ ትስስርና ፍላጎት እንዳለ ጠቋሚ ነው፡፡

3. ይህ ተማሪ ጓደኛህ ሲለይህ ስሜታዊ መሆንህ፣ ብቻህን ሆነህ ማልቀስህና ኑሮ አልገፋ ማለቱ የሚጠቁመው ሁለት ተቃራኒ ጾታ ያላቸው ሰዎች ያላቸው ግንኑነት ሲቋረጥ የሚሳዩት አይነት ባህሪይ መኖሩን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ፈጽሞ የተበላሻ ልምምድ ነው፡፡

4. “ልጁን በንፁሁ ጓደኝነት ብቻ ነው የምቀርበው ሌላ ነገር አስቤ እንኳን አላውቅም” የሚለው አባባልህ ፈጽሞ በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል ሊታሰብና ሊነሳ የማይገባ አገላለጽ በመሆኑ፣ በውስጠ-ሕሊናህ የምትታገልበት ነገር እንዳለ አመልካች ነው፡፡

ሲጠቃለል፣ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር በዚህ መልኩ ተስስር (attachment) ውስጥ መግባትህ ጤናማ አይደለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ ወጣት ጋር ስትለያይ ዞር በማለት የራስህን ሕይወት መከተል ሲገባህ ተሰብረህ መቅረትህም ጤናማ አይደለም፡፡

1. ከነበረህ ተገድዶ የመደፈር ጠባሳ ትክክለኛውን ሂደት በመከተል ነጻ የምትወጣበትን መንገድ ፈልግ፡፡ እንደዚህ አይነት ልምምዶች ከስር መሰረታቸው እስካልነቀልናቸው ድረስ ተደብቀው ብቅ የማለት ባህሪይ አላቸው፡፡

2. ከዚህ በፊት የነበረህ የወንድ-ለወንድ ግንኙነት ያስከተለብህ በርካታ የስነ-ልቦና ቀውስ የመኖሩን ጉዳይ በመቀበል እርዳታ በማግኘት መለወጥህን እርግጠኛ ሁን፡፡

3. ከቀድሞ አጉል ተጽእኖ ሙሉ ለሙሉ ነጻ እስከምትሆን ድረስ ከወንዶች ጋር ያለህን ግንኑነት በጥቃቄ ብታደርገው መልካም ነው፡፡

4. ወደ መንፈሳዊ እምነትና ልምምድ ቀረብ ብለህ ራስህን ብትለውጥም ጥሩ ነው፡፡

በዶርም ለሚኖሩ ተማሪዎች እግረ-መንገዴን የምለግሰው አጠቃላይ ምክር

1. ከተቃረኒ ጾታ ጋር ያላችሁ ግንኙነት በመርህ የሚመራና ዋናው ትኩረታችሁ ሊሆን ከሚገባው ከትምህርታችሁ የማያስጓጉላችሁ መሆኑን አስታውሱ፡፡

2. ከተመሳሳይ ጾታ ጋር አብራችሁ ውላችሁ ካላደራችሁ ስሜታችሁ የሚጎዳ ከሆነ ይህንን ጤና-ቢስና የተለያዩ ስሜቶች የተደበላለቁበትን ትስስር በሚገባ እንድታጤኑትና አስፈላጊውን ማስተካከያ እንድታደርጉ ትመከራላችሁ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍13024😢16😱4😁3🔥2🤩2
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች “ጀምሮ የመጨረስ” ጥያቄ!

የማከናውናቸው ተግባሮችና ስራዎች በርካታ በመሆናቸው፣ እነዚህን ተግባሮች ለመጀመር እንዴት መነሳሳቱን (motivation) እንደማገኝ፣ እንዲሁም በምን አይነት ዲሲፕሊን እንደምቀጥልና እንደምጨርስ ከልምምዴ በመነሳት እንዳጋራቸው የሚጠይቁኝ ተከታታዮች በርካታ ናቸው፡፡

እነዚህ ጥያቄዎች ሲጨመቁ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-

1. አንድን ያሰቡትን ነገር መጀመር እንዴት ይቻላል? (ይህ የmotivation ጥያቄ ነው)

2. አንድን የጀመሩትን ነገር እንዴት ካለማቋረጥ መቀጠል ይቻላል? (ይህ የdiscipline ጥያቄ ነው)

3. አንድን የቀጠሉትን ነገር ታስቦ በተጀመረበት ጥራትና ብቃት እንዴት መጨረስ ይቻላል? (ይህ የfocus ጥያቄ ነው)

ከእነዚህ ተያያዥ ጥያቄዎች በመነሳት . . .

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”) የተሰኝ ለአራት ቀናት ብቻ የሚቆይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍579😱1🎉1🤩1
የወቀሳ ሸክም
👍9
የወቀሳ ሸክም

እናቴና አባቴ ሲነታረኩ በማየትና በመስማት ነው ያደኩት፡፡ የየእለት ጠቡን ወደ መልመዱ ባደላም በጣም እስካሁን ድረስ በስሜቴ ላይ መላቀቅ ያልቻልኩት ተጽእኖ ያመጣብኝ አንድ ቀን አባቴ ለእናቴ በታላቅ ቁጣ የተናገራት ንግግር ነው፡፡ ከትምህርት ቤት መጥቼ እቤት መግባቴን ስላላወቁ ብቻቸውን እንደነበሩ ነበር የመሰላቸው፡፡

በዚያ ደስ በማይል ከሰዓት በኋላ እርቦኝና ደክሞኝ ከትምህርት ቤት ስመጣ በጣም ተበሳጭቶ እንዲህ ብሎ ሲጮህ ሰማሁት፣ “ይህች ሰበበኛ ልጅ ባትጸነስ ኖሮ እኔና አንቺ ያን ጊዜ ተለያይተን እንቀር ነበር”፡፡

በዚያን ጊዜ ነው በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተሰቦቼ ከዚህ በፊት ያደረጉት የመለያየት ሙከራ እኔ በመጸነሴ ምክንያት እንደከሸፈና አብረው እየተጣሉ የመኖራቸው ምክንያት እኔ እንደሆንኩኝ ወደማመን የመጣሁት፡፡ ዞረብኝ! ብዙ ደስ የማይሉ ስሜቶች ወረሩኝ፡፡

እስከማስታውሰው ድረስ ቤተሰቦቼ ጥሩ ነገር ነግረውኝ አያውቁም፡፡ ለነገሩ ለእኔ ብቻ አይደለም፤ እርስ በርሳቸውም ጥሩ ነገር ሲነጋገሩ ሰምቼ አላውቅም፡፡ አባቴም ሆነ እናቴ ላደረጉት አንድ ነገር ሲመሰጋገኑ ሰምቼአቸውም አላውቅም፡፡ እንደውም አንደኛቸው ለቤተሰቡ የሚጠቅም ነገር ሲያደርጉ እንኳ፣ የተደረገው ነገር ጉድለት ይነሳና ሲወቃቀሱ ይውላሉ፡፡ ለካ ሳላስበው እኔም በየቦታው ስሄድ የተበላሸውን፣ ያልተሳካውን፣ የሰዎችን ስህተትና የመሳሰሉትን መልቀም ጀምሬአለሁ፤ የገባኝ አሁን ነው፡፡

ሌሎች በእድሜዬ ያሉ ሰዎች ባየሁ ቁጥር መጀመሪያ ወደ ሃሳቤ የሚመጣው፣ “ይሄን ጊዜ እኮ በጣም ደስ የሚል ሕይወት ነው ያላቸው” የሚል ነው፡፡ ሌላውን ሰው ለመምሰልና እነሱ አላቸው ብዬ የማስባቸውን ነገሮች ለማግኘት እንደተመኘሁ ከራሴ ጋር ሳልኖር ጊዜዬን እንዳባከንኩ ይሰማኛል፡፡ እኔ እንጃ! ራሴን ለመቀበል የምችልበት ጊዜ ይመጣል ብዬ አላስብም፡፡ ቁመቴ ያሳስበኛል፣ የመልኬ ሁኔታ ያሳፍረኛል፣ ሃሳቤን ስገልጥ ሰው ሁሉ በውስጡ፣ “ምን ሞኟ ናት” የሚለኝ ይመስለኛል፡፡ ብቻ እንዳላበዛ እዚህ ላቁም!? … ወይስ ልቀጠል?

ይህ ከላይ የተጻፈው ታሪክ በሃሳብ የተሰኘችው የሃያ አመቷ ወጣት ለአምስተኛ ጊዜ ላገኘችው የስነ-ልቦና አማካሪ ያቀረበችው ጽሑፍ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በነበራቸው አራት እያንዳንዳቸው አንድ ሰዓት የፈጁ የምክር ጊዜያቶች ውጤት እንዳላገኘ የተሰማው አማካሪዋ በመጨረሻ “እስቲ የሕይወት ታሪክሽንና ስሜቶችሽን በአንድ ገጽ ጽፈሽ አምጪልኝ” ባለው መሰረት የቻለችውን ያህል አሳጥራ ማቅረቧ ነው፡፡ የውስጧን በሙሉ ብትዘከዝከው የእሷ ታሪክ ተከታታይ መጽሐፍቶች ሊወጣው እንደሚችል ብታስብም፣ በአጭሩ ጨምቃ አሰፈረችለት፡፡

ምናልባት ከዚህች ሴት ጋር የሚዛመድ ስሜት ካላችሁ …

• ካለጥፋታችሁ ሰዎች በእናንተ ላይ ያሳበቡትን ሸክም ያለመሸከም ምርጫ እንዳላችሁ አትርሱ፡፡

• የራሳችሁን የኑሮ ሸክም ለመሸከም በቂ ብርታት ከፈጣሪህ ተሰጥቷችኋል፤ የኑሮ ሸክም የሚከብዳችሁ ሌሎች የሚጭኑባችሁን ሸክም ስትሸከሙ እንደሆነ አስታውሱ፡፡

• እናንተን የሚወቅሱት ሰዎች ያንን የሚያደርጉት ከራሳቸው የስነ-ልቦና ችግርና ጫና የተነሳ እንደሆነ ተገንዘቡ፡፡

• ሰዎች እናንተን አለመፈለጋቸው በዚህች ምድር ላይ ያላችሁን ተፈላጊነት በፍጹም እንደማይነካው እወቅ፡፡

• ሰዎች የሚጭኑባችሁን የወቀሳ ጭነት አራግፉና ከሌሎች ሰዎች ላይ ስለምታቃልሉት ጫና በማሰብ ውስጣችሁን በራእይ ሙሉት፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
88👍69😱3🎉1
በአራት ምሽቶች የሚጠናቀቅ ስልጠና!

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-

➡️ ጀምሮ የመጨረስ መሰረታዊ ግንዛቤ

➡️ የመጀመር መነሳሳትና ብልሃት

➡️ የመቀጠል መርሆችና ዲሲፕሊን

➡️ ጠንክሮ እና በጸዳ ሁኔታ የመጨረስ ጥበብና መመሪያ

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍45🔥5🎉2
ችግራችሁን ለዩት!

አንድን ነገር ለመጀመር ብዙ ካሰባችሁ በኋላ፣ ነገር ግን ሳትጀምሩት በዚያው የሚቀር ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ “በሃሳብ መጥገብ” ይባላል፡፡ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ብዙ ነገር ለመጀመር ያስቡና አንዱንም ሳይጀምሩት ወደ ሌላ ሃሳብ ይዞራሉ፡፡

አንድን ነገር ለመጀመር ምንም ችግር ከሌለባችሁና ከጀመራችሁት በኋላ ግን የማትቀጥሉት ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ “የመነቃቃት ሱስ” ይባላል፡፡ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች በሰሙትና ባዩት ነገር ለመነሳሳትና ለመነቃቃት ችግር የሌለባቸውና ከጀመሩ በኋላ ካለማቋረጥ የሚያነቃቃቸው ነገር ካላገኙ ይተውታል፡፡

አንድን ነገር ጀምራችሁ፣ ቀጥላችሁና ጨርሳችሁት ሳለ፣ የጨረሳችሁት ነገር ዝርክርክ ያለና ከታሰበበት የጥራት ደረጃ የወረደ ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ “የልህቀት ጉድለት” ይባላል፡፡ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች አንድን ነገር መጨረሳቸውን እንጂ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ የመጨረስ ነገር ትዝም አይላቸው፡፡

በእነዚህና በተመሳሳይ ሁኔታዎች የምቸገሩ ከሆነ በቅርቡ ሊሰጥ የተዘጋጀው ስልጠና ይመለከታችኋል፡፡

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍5514😁2😢1🎉1
ያቀለምኳቸው ገጾች!

አንድ ቀን በቤቴ ባለኝ library ውስጥ በሚገኘው የመጽሐፍ መደርደሪያ ላይ ያሉትን አንዳንድ መጽሐፍት በማንሳት ገለጥ ገለጥ ሳደርግ አንድን ነገር አይቼ ገረመኝ፡፡

መጽሐፍ ሳነብ ጎላ ብለው የታዩኝንና ያስተማሩኝን ሃሳቦች ማቅለም (highlight ማድረግ) እወዳለሁና ያንን መመልከት ጀመርኩ፡፡ የገረመኝ ነገር ግን አብዛኛዎቹ መጽሐፍቶች ላይ highlight ያደረኩት የመጀመሪያዎቹ የተወሰኑት ገጾች ላይ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት እነዚህን መጽሐፍቶች ማንበብ እየጀመርኩኝ ሳልጨርስ ስላቆምኳቸው ነው፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንድን መጽሐፍ ለማንበብ ከመጀመሬ በፊት በሚገባ አስቤና መርጬ መጀመር እንዳለብኝ፣ ከጀመርኩኝ በኋላ ደግሞ የመጨረስ ልማድን ማዳበር እንዳብኝ ውሳኔ አደረኩኝ፡፡

አንድን ነገር እየጀመራችሁ የማቋረጥ ችግር ካለባችሁ፣ በቅርቡ ለመሰጠት የተዘጋጀው ስልጠና በመጀመር፣ በመቀጠልና በመጨረስ ልምምድ ዙሪያ አስፈላጊውን ግንዛቤ ያስጨብጣችኋል፡፡

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍7516🎉5🔥4😱1
ውብ እና ድንቅ የሚዛናዊነት ሃሳቦች!

• ለሰዎች መልካም መሆንን ሳይለቁ የሰዎች መጫወቻ ከመሆን ራስን መጠበቅ . . .

• ሰዎችን የማመንን ልምምድ
ሳይተው በሰዎች ከመታለል ለራስ መጠንቀቅ . . .

• ባለን ነገር መርካትንና መረጋጋትን ሳያጎድሉ ካለማቋረጥ ራስን የማሻሻልን ስራ መስራት . . .

• ደጋግመው የሚጎዱንን ሰዎች ይቅር የማለትን የሕይወት ዘይቤ ሳይጥሉ የወደፊትን ግንኙነት ግን በግል ቀይ መስመር መርህ መምራት . . .

• ከሰዎች ጋር የመቀራረብን መልካም ልምምድ ሳይለቁ ከሰዎቹ ውጪ የመኖር ሁኔታ ሲከሰት ግን ያንን የሚያስችል ጥንካሬን ማዳበር . . .

• በፈጣሪ ላይ መደገፍንና መጸለይን ሳያቆሙ የግል ሃላፊነትን ለመወጣት በእቅድና በዓላማ መሰማራት . . .

ሕይወት የምታምረው ሁሉም ነገር በሚዛናዊነት ሲያዝ ነው!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
106👍50🔥6🎉3
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች “ጀምሮ የመጨረስ” ጥያቄ!

የማከናውናቸው ተግባሮችና ስራዎች በርካታ በመሆናቸው፣ እነዚህን ተግባሮች ለመጀመር እንዴት መነሳሳቱን (motivation) እንደማገኝ፣ እንዲሁም በምን አይነት ዲሲፕሊን እንደምቀጥልና እንደምጨርስ ከልምምዴ በመነሳት እንዳጋራቸው የሚጠይቁኝ ተከታታዮች በርካታ ናቸው፡፡

እነዚህ ጥያቄዎች ሲጨመቁ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-

1. አንድን ያሰቡትን ነገር መጀመር እንዴት ይቻላል? (ይህ የmotivation ጥያቄ ነው)

2. አንድን የጀመሩትን ነገር እንዴት ካለማቋረጥ መቀጠል ይቻላል? (ይህ የdiscipline ጥያቄ ነው)

3. አንድን የቀጠሉትን ነገር ታስቦ በተጀመረበት ጥራትና ብቃት እንዴት መጨረስ ይቻላል? (ይህ የfocus ጥያቄ ነው)

ከእነዚህ ተያያዥ ጥያቄዎች በመነሳት . . .

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”) የተሰኝ ለአራት ቀናት ብቻ የሚቆይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍3821🎉2😱1
በትንሹ ጀምሮ በልህቀት መጨረስ!

አንድን ነገር በሃሳብ ደረጃ እያወጣችሁና እያወረዳችሁ ለመጀመር ካስቸገራችሁ መንስኤው ዘርፈ-ብዙ ሊሆን ቢችልም፣ ዋነኛውቹ ችግሮች ግን ፍርሃት እና ወላዋይነት ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥርጥር የለውም፡፡

የምትጀምሯቸውን ነገሮች እስከመጨረሻው ያለመቀጠል ሁኔታ ካስቸገራችሁ ከብዙ ችግሮች መካከል በዋናነት ዲሲፕሊን እና ትኩረት ማጣት እንዳሉበት እርግጠኛ ሁኑ፡፡

ጀምራችሁ የምታጠናቅቋቸው ነገሮች በመጨረሻ ለምንም ጥቅም የማይውሉና ጉድለት የበዛባቸው እየሆኑ ከተቸገራችሁ፣ ብዙ እንቅፋቶች ሊኖሩባችሁ ቢችሉም በዋናነት ግን የጥራት ደረጃ አቅዶ አለመነሳት እና የማመቻመች ችግር ሊጠቀሱ እንደሚችሉ ጥርጥር አይግባችሁ፡፡

ይህንን አስገራሚ ልምምድ ለመለማመድ የሚያስችላችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና አያምልጣችሁ፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡ በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

• ስልጠናው፡-
በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍505🔥3🎉3
የማያዛልቃችሁን ሰው ለዩ!

ከሚከተሉትን ባህሪያቶች ቢያንስ አንዱን የምታዩባቸው ሰዎች ምናልባት ብዙም የማያዛልቋችሁና አንድ ቀን ለስሜት ጉዳት አጋልጠው የሚሰጧችሁ አይነት ሰዎች እንደሆነ ጠርጥሩ፡፡

• ራሳችሁንም ሆነ ያላችሁን ነገር በነፃ ስላቀረባችሁላቸው ልክ እንደ ርካሽ የሚቆጥሩና የማያመሰግኑ ሰዎች፡፡

• በዓላማችሁና ለማደግ በምታደርጉት የየእለት ጥረት የሚያላግጡና የሚያሾፉ ሰዎች፡፡

• እየጠፉና እየቆዩ ለአንድ ነገር አማራጭ ሲያጡና ያንን ነገር ከእናንተ ብቻ እንደሚያገኙ ሲያውቁ ብቻ የሚፈልጓችሁ ሰዎች፡፡

• እናንተን እና ወዳጅነታችሁን ሳይሆን የእናንተን እና ያላችሁን ነገር ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች፡፡

• በፍጹም የማያምኗችሁ ሰዎች፡፡

• ስህተታችሁን እየቆጠሩ የሚወቅሷችሁና በፍጹም ይቅር የማይሏችሁ ሰዎች፡፡

• ስህተታቸው እንዳይገኝባቸው እናንተን አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች፡፡

• ሰዎችን ለእናንተ የሚያሙና ስለሰው ክፉን የሚያወሩላችሁ ሰዎች፡፡

• እናንተ የጀመራችሁትን ነገር እነሱ እንደጀመሩት አድርገው ለማሳየት የሚጣጣሩ ሰዎች፡፡

• ለእነሱ መኖር፣ መስጠትና መልካም ነገር ማድረግ ልክ እንደ ግዴታችሁ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
120👍84🔥7😁1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች “ጀምሮ የመጨረስ” ጥያቄ!

የማከናውናቸው ተግባሮችና ስራዎች በርካታ በመሆናቸው፣ እነዚህን ተግባሮች ለመጀመር እንዴት መነሳሳቱን (motivation) እንደማገኝ፣ እንዲሁም በምን አይነት ዲሲፕሊን እንደምቀጥልና እንደምጨርስ ከልምምዴ በመነሳት እንዳጋራቸው የሚጠይቁኝ ተከታታዮች በርካታ ናቸው፡፡

እነዚህ ጥያቄዎች ሲጨመቁ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-

1. አንድን ያሰቡትን ነገር መጀመር እንዴት ይቻላል? (ይህ የmotivation ጥያቄ ነው)

2. አንድን የጀመሩትን ነገር እንዴት ካለማቋረጥ መቀጠል ይቻላል? (ይህ የdiscipline ጥያቄ ነው)

3. አንድን የቀጠሉትን ነገር ታስቦ በተጀመረበት ጥራትና ብቃት እንዴት መጨረስ ይቻላል? (ይህ የfocus ጥያቄ ነው)

ከእነዚህ ተያያዥ ጥያቄዎች በመነሳት . . .

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”) የተሰኝ ለአራት ቀናት ብቻ የሚቆይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍396😱1
“የምነው ባደረኩት” ጸጸት!

ለጸጸት የሚዳርጉንን ሁኔታዎች በጥቅሉ በሁለት ከፍለን እናያቸዋለን፡፡

1. ማድረግ የማይገባንን ከማድረግ የሚመጣ ጸጸት፣

2. ማድረግ ሲገባን ሳናደርግ ከምናልፋቸው ነገሮች የሚመጣ ጸጸተረ

በርካታ ጥናቶች እንደሚጠቁሙን በሕይወታችን እጅግ ጎጂ የተባለውና እድሜ ልካችንን የማይለቀን ጸጸት፣ ማድረግ ሲገባን ሳናደርግ ካለፍናቸው ነገሮች የሚመጣ የጸጸት ጉዳት ነው፡፡

ማድረግ የሚገባን ነገር ምን እንደሆነ እያወቅን ያንን ነገር ለመጀመር አለመቻል፣ መወላወል፣ ለነገ ማስተላለፍ፣ ጀመር እያደረጉ ማቆም እና የመሳሰሉት ችግሮች በርካቶች የሚታገሏቸው ሁኔታዎች ናቸው፡፡

ከዚህ እና ከመሰል ችግሮች በመላቀቅ የማሰብ፣ የማቀድ፣ የመጀመርና የጀመሩትንም ጥጉ ድረስ በመውሰድ የማጠናቀቅን ጥበብና ዲሲፕሊን ለማዳበር የሚጠቅማችሁ ስልጠና በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍4610🤩4
🎓 የስልጠና እድል!

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን”
በ ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

📅 የስልጠና ቀናት: ሚያዚያ 27 , 30 ፣ ግንቦት 4 , 7

🕒 ሰዓት: ከምሽቱ 2፡30 - 4፡30

💻 ስልጠናው የሚካሄደው: በቴሌግራም / Live

📥 በስልጠናው መሳተፈ ከፈለጉ በዚህ 👉 @DrEyobmamo ፍላጎትዎን ይግለጹ!
👍4322😱1
መለስ በሉና አስቡ!
👍194
መለስ በሉና አስቡ!

የሕወታችሁን ስኬታማነት ከምትመዝኑበት መንገድ አንዱ፣ መለስ ብላችሁ የቀድሞ ልምምዶቻችሁን መመልከት ነው፡፡

ይህ ሕይወትን የመመልከትና የመገምገም ሁኔታ ከሚነካቸው ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ከዚህ በፊት ሆን ብዬ (intentionally) አስቤና አቅጄ የጀመርኳቸው ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

2. ከእነዚህ ከጀመርኳቸው ሁኔታዎች መካከል በቀጣይነት በመስራት የጨረስኳች የተኞቹን ነው?

3. እስከጥጉ ድረስ ወስጄ አጠናቅቄአቸዋለሁ ካልኳችሁ ሁኔታዎች መካከል በጥሩ ሁኔታ የተጠናቀቁትና ለታሰበብት ዓላማ የዋሉት የትኞቹ ናቸው?

ትንሽ ከራሳችሁ ጋር ጊዜ ወስዳችሁ እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን በመጠየቅ የሕይወታችሁን ስኬታማነት በቀላሉ መገምገም ትችላላችሁ፡፡

ይህንን ማድረግ . . .

• ብዙ ከመልፋት በጥበብ ወደ ወደስራት ያሻግራችኋል፡፡

• ብዙ የማይገናኙና የተበታተኑ ነገሮች እየሰሩ ዘመንን ከማሳፍ በትኩረት በመስራት አንድን ነገር ወደ መገንባት ያሳድጋችኋል፡፡

• በስሜት እና በወቅቱ “ሙድ” እየተነሳሱ ይህንንም ያንንም ከመነካካት በእቅድና መጨረሻውን አስቦ በመጀመር ስኬታማ ወደመሆን ያሻሽላችኋል፡፡

• ጀምረው የሚያቆሙትን ሰዎች አልፎ በመሄድ (outlast በማድረግ) ተወዳዳሪ ያደርጋችኋል፡፡

አስቡ! አቅዱ! አንድን ነገር ጀምሩ! ከጀመራችሁ ደግሞ አታቁሙ!

የማሰብ፣ የማቀድ፣ የመጀመርና የጀመሩትንም ጥጉ ድረስ በመውሰድ የማጠናቀቅን ጥበብና ዲሲፕሊን ለማዳበር የሚጠቅማችሁ ስልጠና በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

• ርእሱ፡-
“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍7921🎉2🤩1
ሰዎች ምን ይሉ ይሆን ??? !!!
👍176😁2
ሰዎች ምን ይሉ ይሆን ??? !!!

ሁል ጊዜ ሰዎች ስለሚሉት እና ገና ለገና ሊሉ ስለሚችሉት ነገር የመጨናነቅ ባህሪይ ካለብን ምንም ነገር ለመጀመር ያስቸግረናል፣ ብንጀምርም እንኳን የጀመርነውን ነገር ጥጉ ድረስ በመቀጠል ማጠነቃቅ አንችልም፡፡

ይህ የሚሆንበት ምክንያት የምናደርጋቸውን ነገሮች ከሌሎች ሰዎች አመለካከትና ሃሳብ አንጻር የማድረግና እንደ ሰዎቹ ሁኔታ የመሄድ ዝንባሌ ስላለን ነው፡፡

አንድን ነገር በመጀመርና በመቀጠል ሂደት ውስጥ የሰዎች ተሳትፎ አስፈላጊነት ያለው፣ ሚዛናዊ ምክርን በመቀበል፣ የእነሱን ስኬት በማየት በመነሳሳትና ስህተታቸውን በማየት ትምህርት በማግኘት ዙሪያ ሊሆን ይገባዋል፡፡

የሰዎች አመለካከት እና ሃሳብ በእኛ ላይ አጉል ተጽእኖ የሚያስከትልብን አይነት ሰዎች ከሆንን የራሳችንን ሃሳብ ሳይሆን የሌሎችን ሃሳብ እንዳራመድን ዓመቶቻችንን እናባክናለን፡፡

ለዚህ ነው እንደዚህ የሚባለው . . .

• ምንም አሰባችሁ ምንም፣ ሃሳቡ የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

• ምንም ተሰማችሁ ምንም፣ ስሜቱ የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

• ምንም አቀዳችሁ ምንም፣ እቅዱ የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

• ምንም ወሰናችሁ ምንም፣ ውሳኔው የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

ከሁሉም በፊት የራሳችሁ ዓላማ፣ አመለካከት፣ አቋምና እቅድ ይኑራችሁ! ከዚያም ጀምሩ! ከጀመራችሁ ደግሞ አታቁሙ!

በዚህ ልምምድ ዙሪያ ጥበብንና ዲሲፕሊንን ለማዳበር የተዘጋጀውና በዶ/ር ኢዮብ ማሞ የሚሰጠው ስልጠና አያምልጣችሁ፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍5924🔥2😁2🎉1
የብዙ ሰዎች “ጀምሮ የመጨረስ” ጥያቄ!

የማከናውናቸው ተግባሮችና ስራዎች በርካታ በመሆናቸው፣ እነዚህን ተግባሮች ለመጀመር እንዴት መነሳሳቱን (motivation) እንደማገኝ፣ እንዲሁም በምን አይነት ዲሲፕሊን እንደምቀጥልና እንደምጨርስ ከልምምዴ በመነሳት እንዳጋራቸው የሚጠይቁኝ ተከታታዮች በርካታ ናቸው፡፡

እነዚህ ጥያቄዎች ሲጨመቁ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-

1. አንድን ያሰቡትን ነገር መጀመር እንዴት ይቻላል? (ይህ የmotivation ጥያቄ ነው)

2. አንድን የጀመሩትን ነገር እንዴት ካለማቋረጥ መቀጠል ይቻላል? (ይህ የdiscipline ጥያቄ ነው)

3. አንድን የቀጠሉትን ነገር ታስቦ በተጀመረበት ጥራትና ብቃት እንዴት መጨረስ ይቻላል? (ይህ የfocus ጥያቄ ነው)

ከእነዚህ ተያያዥ ጥያቄዎች በመነሳት . . .

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”) የተሰኝ ለአራት ቀናት ብቻ የሚቆይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍6916🔥1
ሁለቱ የአጀማመር ገጽታዎች

በሕይወታችን የሚጀመሩ ነገሮችን ጀምሮ ከመጨረስ አንጻር በሚገባ ስንመለከታቸው በሁለት ቀላል ክፍሎች ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡

1. ከምርጫችን ውጪ የሆኑ ጅማሬዎች

እነዚህ ጅማሬዎች ሲጀመሩ ምንም አይነት የእኛ ተሳትፎ የሌለባቸው ሁኔታዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ፈጣሪ ጀምሮ በአደራ የተሰጠን ሲሆኑ፣ ሌሎቹ ደግሞ ሰዎችና ሁኔታዎች የጀመሩልን ነገሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ ሕይወታችንን በመጀመር ሂደት ላይ ምንም አይነት የእኛ ምርጫና ተሳትፎ የለበትም፡፡ ነገር ግን፣ ያንን የተጀመረልንን ሕይወት በትክክለኛው መልኩ ለመኖር መጀመር፣ መቀጠልና በተሳካለት መልኩ የመጠናቀቁ ጉዳይ ላይ የሚጠበቅብንን ያህል ማድረግና መሳተፍ አስፈላጊ ነው፡፡ አንድን ነገር እኔ አልጀመርኩትም ማለት ለቀጣይነቱና ለመጠናቀቁ ከሚኖረኝ ሃላፊነት ነጻ ነኝ ማለት አይደለም፡፡

2. በምርጫችን ውስጥ የሆኑ ጅማሬዎች

ከላይ እንደተገለጸው አንዳንድ በሕይወታችን የሚጀመሩ ነገሮች ልክ እንደ ሕይወት ከእኛ ምርጫ ውጪ የተጀመሩ ናቸው፡፡ ሆኖም፣ አብዛኛዎቹ ግን በእኛ ፈቃድ፣ ምርጫና ፍላጎት የተጀመሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ጅማሬዎች በትክክለኛው መንገድ የመጀመራቸው፣ ተገቢውን ሂደት ተከትለው የመቀጠላቸውና በታሰበለት የጥራትና የሙላት ልክ መጠናቀቃቸውን እርግጠኛ መሆን ያለብን እኛው ነን፡፡ ይህ ሃላፊነታችን በሚገባ ሲገባን የአንድን ነገር ውጤት የሚወስነው የእኛ ምርጫ እንደሆነ ስለምንገነዘብ ስለምናደርገው ምርጫና ውሳኔ በሚገባ ማሰብ እንጀምራለን፡፡

አንድን ነገር መጀመር፣ መቀጠልና የማጠናቀቅ ጥበብንና ዲሲፕሊንን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ እጅግ ወሳኝ በሆነ የሕይወት ሂደት ላይ ተገቢውን ግንዛቤ ለማግኘት የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍6216😢2🎉1
2025/07/09 05:41:34
Back to Top
HTML Embed Code: