Telegram Web Link
ከነገሩ ውጪ መኖር ካልቻልክ ከነገሩ ጋር መኖር አትችልም
ከነገሩ ውጪ መኖር ካልቻልክ ከነገሩ ጋር መኖር አትችልም

ሰዎች አንድን ነገር በእጃቸው ለማስገባት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱት፣ ማስገባት ካቃታቸው ከሰው በታች እንደሆኑ የሚያስቡትና ተሳክቶላቸው ካስገቡ በኋለ ደግሞ ያንን ነገር ላለማጣት እንደገና ምንም አይነት የጭካኔም ስራ ቢሆን ከመስራት የማይመለሱት ከዚያ ነገር ውጪ ሙሉ ሕይወት ሊኖራቸው እንደማይችል ሲያስቡ ነው፡፡

ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ከስልጣን ውጪ መኖር እንደማይችል ካሰበ ስልጣንን በእጁ ለማስገባትም ሆነ አንዴ በእጁ የገባውን ስልጣን ላለመልቀቅ ሌላውን በጭካኔ እስከማጥፋት ድረስ ይደርሳል፡፡ ይህ እውነታ ከዝና፣ ከሃብትና ከመሳሰሉት “ውጫዊ” ሁኔታዎች አንጻር ሲታይ ተግባራዊነቱ ያው ነው፡፡

አየህ፣ ከስልጣን፣ ከዝና፣ ከሃብትና ከመሳሰሉት ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ሊሰጣቸው ከሚገባቸውን ነገሮች ውጪ መኖር እንደምንችል ራሳችንን ስናሳምነው ብቻ እነዚህ ነገሮች በእጃችን ሲገቡ በተረጋጋና ከእኛና ከቤተሰባችን አልፈን ለሕብረተሰቡ የሚጠቅም ነገር እናደርግባቸዋለን፡፡

ምናልባት ጊዜው ተለውጦ ደግሞ ቀድሞ የነበረን ነገር በእጃችን እንደማይቆይ ስናስብ አሁንም ቀድሞ ከሁኔታው ውጪ በነበርንበት ጊዜ የነበረንን የተረጋጋ ማንነት ይዘን መቀጠል አያስቸግረንም፡፡

እቅጩን ልንገርህ፡- ከመወደድና ከተቀባይነት ውጪ አርፈህ መኖር ካልቻልክ በመወደድና በተቀባይነት ውስጥ አርፈህ መኖር አትችልም፡፡

ከሃብት ውጪ ተረጋግተህ መኖር ካልቻልክ ሃብትን ሰብስበህ ተረጋግተህ መኖር አትችልም፡፡

ከስልጣን ውጪ ሰከን ብልህ መኖር ካልቻልክ ስልጣን ብታገኝም ሰክነህ አትኖርም፡፡

ከዝና ውጪ ዘና ብለህ መኖር ካልቻልክ ዝነኛ ስትሆን ዘና ብለህ መኖር አትችልም፡፡

ቀድሞውኑ ያላረፈ ሰው ይህንና ያንን ባገኝ አርፍ ነበር የሚለውን ነገር በእጁ ለማስገባት ሲግለበለብ ኖሮ፣ እጁ ካስገባው በኋላ ደግሞ ያንን ነገር ከእጁ ላለማጣት ሲግለበለብ ለራሱና ለሌላው የረብሻ ምክንያት ነው፡፡

ከላይ ወደተጠቀሱትና ወደመሰል ነገሮች ለማረፍ ብለህ አትግባ፤ ቀድሞውኑ ከእነሱ ውጪ ስለአረፍክ ግባ፡፡ ይህንን ብታደርግ ራስህ አርፈህ ለሕብረተሰቡም የእረፍት ምንጭ ትሆናለህ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ዛሬ (ግንቦት 18/2017) ማታ ስላለን የነጻ ስልጠና የቀረቡ ጥያቄዎች

ርዕሱ ምንድን ነው?
ርዕሱ፣ "ራስን የማሳደግ መመሪያዎች" (Principles of Self Development) የተሰኘ ነው፡፡

የስልጠናው ዓላማ ምንድን ነው?
የስልጠናው ዓላማ፣ በሕይወታችን ያሉን ወሳኝ ነገሮች እንዲያድጉ በመጀመሪያ እኛ ማደግ እንደሚገባንና በሂደቱም የገንዘብ አቅማችን እንደሚጨምርና ሌላ የማደግ እድል እንደሚሰጠን ማስገንዘብ ነው፡፡

ስልጠናው የሚጠው በስንት ሰዓት ነው?
ስልጠናው የሚሰጠው ከምሽቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ነው፡፡

ስልጠናው ለማን ተዘጋጀ?
ስልጠናው የተዘጋጀው ለቴሌግራም ቻናሌ ቤተሰቦች ሲሆን፣ ጓደኞቻችሁም ቻናሉን በመቀላቀል እንዲሳተፉ መጋበዝ ትችላላችሁ፡፡

እንዴት መሳተፍ ይቻላል?
ወደዚህ ቻናል በሰዓቱ ጎራ በማለት ስልጠናው ሲከፈት join የሚለውን በመጫን መከታተል ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ፡፡

ጓደኞቻችንን እንዴት እንጋብዝ?
ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመላክ ቻናሉን እንዲቀላቀሉ መጋበዝ ትችላላችሁ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob
በታሪካዊቷ  ካዛንቺስ ‼️
📌 በጉጉት የተጠበቀው አያት-ካዛንቺስ መንደር
📌 እጅግ ውብ ዕይታዎች ያሉት

10% (500,000)ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

📌ለመኖሪያ ምቹ የሆኑ አፓርታማዎችን
ልዩ ቅናሽ በመጠቀም
የግልዎ ያድርጉ ፤

📌የዋጋ መጨመር ሳያሳስቦ በተዋዋሉበት ምንም ጭማሪ ሳይኖረው ቤቶን ይግዙ ገንዘቦን ከ ዋጋ inflation ይታደጉ

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ 80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ 95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ 140 ,160 ካ.ሜ

📌በኢትዮጵያ ብር ይዋዋሉ::

ልዩ ቅናሽ

100%----ለከፈለ---20% ቅናሽ
85%-----ለከፈለ----17 %ቅናሽ
70%-----ለከፈለ ----14%ቅናሽ
55%----ለከፈለ-------11% ቅናሽ
40%----ለከፈለ------8%ቅናሽ ይደረጋል


📌በኢትዮጵያ ብር ተዋውለው
የህልምዎን በር ከፍተው ይግቡ!
የቤት ባለቤት ይሁኑ!


ለበለጠ መረጃ. 📲09-13-33-85-77 በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ይደውሉ (ዋናው ቢሮ)
የአንድ ተቋም ችግር ለምን እንደማይፈታ!

ለመሪዎች . . .


በቤተሰብ፣ በንግድ፣ በመንግስት መስሪያ ቤት፣ በሕዝብ አስተዳደርም ሆነ በማንኛውም ተቋም ባለ አመራር ውስጥ በሚገባ ከታሰበበት፣ አካላቱን ሁሉ ያሳተፈ ውይይት ከተደረገበትና ትክክለኛውን ስልት የተከተለ እርምጃ ከተወሰደበት የማይፈታ ችግር አይኖርም፡፡ ይህንን የመፍትሄ ሂደት ደግሞ ማስጀመር፣ ማራመድና ጥጉ ድረስ ተከታትሎ መውሰድ የሚገባው ብቸኛና ዋነኛው ሃላፊ መሪው ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን እውነታ ተግባራዊ ማድረግ የማይቻልበት ተቋም ካለ . . .

1. ምናልባት ተቋሙ የቆመለት አላማ ተሳካም አልተሳካም ምንም ግድ የሚለውና የባለቤትነት ስሜት የሚሰማው አካል የለውም፣

2. ምናልባት መሪው የአመራር ክህሎት ወይም ዲሲፕሊን ችግር ይኖርበታል፣

3. ምናልባት መሪው በነጻነት እንዳይመራ በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሰራተኞች ወይም የበላይ አካሎች አሉ፣

4. ምናባት የተዛባው ሂደት ለመሪው የግል አጀንዳና ጥቅም ስለሚመቸው ባላየ እያለፈው ነው፡፡

መሪዎች!!! እባካችሁ ወይ በትክክል ምሩ ወይም አንደኛውን በትክክል ለሚመራው ሰው ልቀቁና ተመሩ!!!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
"ራስን የማሳደግ መመሪያዎች" (Principles of Self Development) የተሰኘው የዛሬው (ከ2፡30 – 4፡00) ነጻ የስልጠና ጊዜ ከሁለት ሰዓታት በኋላ ይጀምራል፡፡

ጓደኞቻችሁ ይህንን ቻናል በመቀላቀል ስልጠናውን እንዲወስዱ ጋብዟቸው!

See you soon!
"ራስን የማሳደግ መመሪያዎች" (Principles of Self Development) የተሰኘው የዛሬው (ከ2፡30 – 4፡00) ነጻ የስልጠና ጊዜ ከአንድ ሰዓት በኋላ ይጀምራል፡፡

ጓደኞቻችሁ ይህንን ቻናል በመቀላቀል ስልጠናውን እንዲወስዱ ጋብዟቸው!

See you in one hour!
"ራስን የማሳደግ መመሪያዎች" (Principles of Self Development) የተሰኘው የዛሬው (ከ2፡30 – 4፡00) ነጻ የስልጠና ጊዜ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ይጀምራል፡፡

ጓደኞቻችሁ ይህንን ቻናል በመቀላቀል ስልጠናውን እንዲወስዱ ጋብዟቸው!

See you!
ስልጠናውን እንዴት እንደምትወስዱ ግራ ለገባችሁ!

ዛሬ ምሽት ልክ 2፡30 ሲል ከዚህ በታች ባለው የቻናሌ ሊንክ በመጠቀም ወደ ቻናሉ ትገባላችሁ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

ስልጠናው መጀመሩን የሚገልጽ JOIN የሚል ምልክት ሲመጣላችሁ ያንን በመጫን መቀላቀልና መከታተል ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ፡፡
Live stream started
ራስን የማሳደግ መመሪያዎች.pdf
189.1 KB
የዛሬው የነጻ ስልጠና note ቀርቧል - Enjoy!!!
ሰላም የቻናሎቼ ቤተሰቦች!

በየሶስት ወሩ አዳዲስ ስልጠናዎችን ለማዘጋጀት በገባሁት ቃል መሰረት ለሕይወታችሁ እድገት ወሳኝ የሆነን አንድ ስልጠና አዘጋጅቻለሁ፡፡

ለምዝገባ መረጃን ለማግኘት በሚከተለው user name በመጠቀም ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ይላክላችኋል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob
Live stream finished (1 hour)
Audio
ዛሬ የተሰጠው ነጻ ስልጠና ድምጽ ቀርቦላችኋል፡፡ ስለነበራችሁ ተሳትፎ አመሰግናለሁ
ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን . . .

ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ሌላ መንገድ አለ! ሌላ ሕይወት አለ! ሌላ አቅጣጫ አለ! ሌላ አማራጭ አለ!

• እውነት ነው፣ ተምሬ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር . . . የመማሩን እድል ካላገኘሁ ግን ሕይወትን ውብ የሚያደርጉ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሉ፡፡

• እውነት ነው፣ ፍቅረኛ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ትክክለኛ ፍቅረኛ ካላገኘሁ ግን ትክክለኛ ሕይወት የምመራበት ብዙ እድሎች አሉኝ፡፡

• እውነት ነው፣ ትዳሬ በሰላም ቀጥሎ ቢሆንና ባይፈርስ ጥሩ ነበር . . . አንዴ ከሆነና ሁኔታውን በፍጹም ማደስ ካልቻልኩ ግን የተዝረከረከውን ሕይወቴን አፋፍሼ፣ ሰብስቤና እንደገና አደራጅቼ በአዲስ መልኩ ሕይወት ይቀጥላል፡፡

• እውነት ነው፣ የምወደው ስራ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ሁኔታው ያንን ለማግኘት ካልፈቀደልኝ ግን ባለኝና ካለሁበት በመነሳት የማድግበትን መንገድ የመፈለግ መነሳሳቱ አለኝ፡፡

በአጭሩ፣ ሕይወት እኔ እንደምፈልጋት ብትሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ለምን አልሆነም ብዬ ደብቶኝ አልውልም፡፡ ቀና እላለሁ! ብርቱ ሰው ለመሆን እወስናለሁ! ስብር አልልም! አልደካክምም!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የስልጠና እድል!

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
እስቲ ትንሽ አንድ ጊዜ ጸጥ በሉና . . .

• ማሟላት የምትመኟቸውን ለሕይወታችሁ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች . . .

• ማሻሻል የምትፈልጉትን የኑሮ ሁኔታ . . .

• መደገፍ የምትፈልጓቸውን ቤተሰቦች . . .

• መማርና መሰልጠን የምትፈልጉትን ነገር . . .

• መጀመር የምትፈልጉትን አዲስ ሕይወትና የአኗኗር ደረጃ . . .

• መቀየር የምትፈልጉትን ቤት ወይም ሰፈር . . .

እና የመሳሰሉትን ሁኔታዎቻችሁን አስቧቸው፡፡

እነዚህና መሰል ነገሮች በአብዛኛው ካላችሁ የገንዘብ አቅም ጋር የተያያዙ እንደሆነ ታውቃላችሁ?

ለዚህ ነው ካለን መንፈሳዊ ሕይወትና ካሉን እሴቶች ቀጥሎ በሚገባ ሊሰራበት የሚገባው ነገር የገንዘብ አያያዛችን ሁኔታ የሆነው፡፡

በዚህ ጉዳይ በሚገባ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠና እድል!

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
በታሪካዊቷ  ካዛንቺስ ‼️
📌 በጉጉት የተጠበቀው አያት-ካዛንቺስ መንደር
📌 እጅግ ውብ ዕይታዎች ያሉት

10% (500,000)ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

📌ለመኖሪያ ምቹ የሆኑ አፓርታማዎችን
ልዩ ቅናሽ በመጠቀም
የግልዎ ያድርጉ ፤

📌የዋጋ መጨመር ሳያሳስቦ በተዋዋሉበት ምንም ጭማሪ ሳይኖረው ቤቶን ይግዙ ገንዘቦን ከ ዋጋ inflation ይታደጉ

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ 80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ 95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ 140 ,160 ካ.ሜ

📌በኢትዮጵያ ብር ይዋዋሉ::

ልዩ ቅናሽ

100%----ለከፈለ---20% ቅናሽ
85%-----ለከፈለ----17 %ቅናሽ
70%-----ለከፈለ ----14%ቅናሽ
55%----ለከፈለ-------11% ቅናሽ
40%----ለከፈለ------8%ቅናሽ ይደረጋል


📌በኢትዮጵያ ብር ተዋውለው
የህልምዎን በር ከፍተው ይግቡ!
የቤት ባለቤት ይሁኑ!


ለበለጠ መረጃ. 📲09-13-33-85-77 በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ይደውሉ (ዋናው ቢሮ)
2025/07/07 17:50:17
Back to Top
HTML Embed Code: