Telegram Web Link
ሶስቱ የገንዘብ ችግሮች
ሶስቱ የገንዘብ ችግሮች

ሶስት አይነት የገንዘብ እጦት መሻዎች አሉ፡-

1. የኑሮ ወድነት እየባሰ ከመሄዱ የተነሳ የሚመጣ የገንዘብ ችግር

ይህ አይነቱ ችግር ጤናማ እና ሁሉም ሰው የሚያልፍበት ችግር ነው፡፡ የወቅቱ ሁኔታ የፈቀደለትን ስራ ጠንክሮ እየሰራና ለማግኘት የቻለውን ገቢ እያመጣ ያለ ሰው ራሱንና ቤቱ ለማቆም መቸገሩ እጅግ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንዳለ አመልካች ነው፡፡ ይህ ሰው ክህሎቱን እያሳደገና በስሜቱ ጠንካራ በመሆን ቢሰራ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ በገቢ እያደገ መሄዱ አይቀርም፡፡

2. በስንፍና ምክንያት ስራን ካለመስራት የሚመጣ የገንዘብ ችግር

ይህ አይነቱ ችግር ጤና-ቢስ እና የስራ ዲሲፕሊን የሌላቸው ሰዎች የሚያልፉበት ችግር ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰው ዘወትር የሰው ጥገኛ እንደሆነ የሚኖርና ላለበት ሁኔታ ሌላውን የሚወቅስ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው በራሱ ላይ የለው አመለካከት ከእለት እለት እየወረደ የሚሄድና ምንም አይነት የወደፊት ተስፋ የሌለው ሰው ነው፡፡

3. ከተሳሰቱ ውሳኔዎች የሚመጣ የገንዘብ ችግር

ይህ አይቱን ችግር የሚጋፈጡ ሰዎች ጠንክሮ በመስራትም ሆነ ክህሎታቸውን በማሳደግ ጎበዞች ቢሆኑም፣ ከገንዘብ አወጣጥ፣ ከብድርና ላገኙት ሁሉ ከመስጠት አንጻር የሚወስኗቸው ገንዘብ-ነክ ውሳኔዎች ግን ጥበብ ስለሚጎድላቸው እጃቸው መግባት ያለበትን ማጣት ብቻ ሳይሆን የገባውም በማይሆን ውሳኔ ያባክኑታል፡፡ ከዚህ ልምምድ ለመውጣት በገንዘብ አያያዝ ጥበብ መሰልጠንና ማደግ የግድ ነው፡፡

የምትችልትን ያህል ሰርታችሁ ለማደግ በመጣጣር ውስጥ እስካላችሁ ድረስ ትኩረታችሁን የወቅቱ ሁኔታችሁ ላይ በማድረግ አትረበሹ፡፡ ስሩ፣ ኑሮን ለማሸነፍ ታገሉ፣ እድሉን ስታገኙ እደጉ . . . የወደፊታችሁ ብሩህ እንደሆነም አትዘንጉ፡፡

በነገራችን ላይ ሰሞኑን በማስታወቅ ላይ ያለነው ስልጠና እንዳያመልጣችሁ፡፡ ማስታወቂያውን ቀደም ባለው ፖስት ላይ ተመልከቱት፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ጠንቃቃው ደፋር!
ጠንቃቃው ደፋር!

“ግድ-የለሽ የሆኑ የመዳፈር እርምጃዎች በእርግጥም አጥፊና አደገኛ ናቸው፡፡ ሆኖም፣ ከዚያ የበለጠ አባካኝ የሆነው ሁኔታ ግን በሚገባ ያልታሰበበትና መንቀሳቀስ እስክናቆም ድረስ የሚያደርሰን አጉል ጠንቃቃነት ነው፡፡ ይህ አይነቱ አጉል ጠንቃቃነት ውድቀትን ከማምጣቱ በላይ ታላላቅ እድሎችን እንዳንጨብጣቸው ያደርገናል” - Daily Living

አንድአንድ ሰዎች መልካም ውጤትንና እድገትን ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ለማግኘት ከፈለጉት ነገር አንጻር ካላቸው የመጓጓት ስሜት ይልቅ አንድ ነገር ይደርስብኛል የሚለው የስጋት ስሜት ልቆ ስለሚገኝ፣ ፍርሃቱና ስጋቱ ፍላጎታቸውን ምኞት ብቻ ሆኖ እንዲቀር ያደርገዋል፡፡ በዚህ አይነቱ የፍርሃት ሕይወት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ካሉበት ሳይንቀሳቀሱ የቀስ-በቀስ ውድቀትን ይወድቃሉ፡፡ በፍርሃት ምክንያት የማይንቀሳቀስ ሰው ወዲያውኑ የሚጋፈጠው አደጋ ባይኖርበትም ቀስ በቀ ወደ አደጋ መሄዱ ግን ጥርጥር የለውም፡፡

ከላይ ከተጠቀሰው ሁኔታ በተቃራኒው ደግሞ በሚገባ ያልታሰበበት አጉል ድፍረትና ጀብደኝነት ያለባቸው ሰዎች የድንገት ውድቀትን ይወድቃሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ጽንፎች በማስታረቅ የሚራመድ ሰው ደግሞ ሕይወትን ቀስ-በቀስ እያጣጣማት የሚኖራት ጠቢብ ሰው ነው፡፡ ይህ አይነቱ ሰው ጥበበኛ ሰው ስለሆነ የሚደፈረውንና የማይደፈረውን በሚገባ ያውቃል፡፡ ጥበበኛ ሰው በስጋትና በፍርሃት ምክንያት በቁሙ ከሚሞት ይልቅ ጥንቃቄ በተሞላበት ደፋርነት ውስጥ የሚገጥመውን አደጋ መጋፈጥ ይመርጣል፡፡

ጥበበኛ ሰው ከጅማሬው እስከ ፍጻሜው ድረስ ካለምንም እንከን እደርሳለሁ የሚልን ሞኝነት ፈጽሞ አያስተናግድም፡፡ ስለዚህም፣ በሕይወት ጎዳና ውስጥ ምንም እንቅፋት የሌለው ቀላል እንቅስቃሴ እንደሌለም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ነገር ግን ገና ለገና እንቅፋት ይገጥመኛል በማለት ደግሞ ከመራመድ አይገታም፡፡

የሚዛናዊነት ጥያቄዎች

• አሁን ካለሁበት የሕይወት ደረጃ አልፌ በመሄድ መድረስ የምፈልግበት የላቀ ደረጃ ምንድን ነው?

• ወደሚቀጥለው ደረጃ ለማደግ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ የሚገባኝ ይመስለኛል?

• ይህንን እርምጃ እንዳልወስድ ያደረገኝ ምንድን ነው?

• ይህንን እርምጃ ብወስድ ሊደርስብኝ የሚችለው የመጨረሻ አስጊ ሁኔታ ምንድን ነው?

• ይህ ሁኔታ ቢደርስብህ የማጣው ነገር ምንድን ነው?

• ይህ “አደገኛ” ነገር ባለሁበት ከመቅረት “አደጋ” ጋር ሲነጻጸር የትኛው ይጎዳኛል?

ቀና እንበል! እናመዛዝን! እንነሳ! እንራመድ! አንድ ነገር እንጀምር!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ሰባቱ የሁለንተናዊ እድገት ገጽታዎች
ሰባቱ የሁለንተናዊ እድገት ገጽታዎች

አንድ ሰው ሁለንተናዊ እድገት ውስጥ ለመግባት እነዚህ ሰባት ዘርፎች ላይ አንድ በአንድ በሚገባ ሊሰራ ይገባዋል፡፡ ከእነዚህ ከሰባቱ አንዱ ሲጎድል ሌሎቹን የመጎተት አቅም አለው፡፡

1. መንፈሳዊው ገጽታ - የሕይወቴን ዓላማ የያዘውን ፈጣሪዬን የማወቄና ከእርሱ ጋር ትክክለኛ ግንኙነት የማድረጌ ጉዳይ፡፡

2. የስሜት ገጽታ - በስሜት ብልህነት የመብሰሌና ስሜቴን በትክክለኛው ቦታ፣ ጊዜና መጠን የመጠቀሜ ጉዳይ፡፡

3. አካላዊው ገጽታ - ስጋዊ አካሌ እድሜዬን በሚመጥን ጤንነት እንዲቆይ በአካላዊ እንቅስቃሴ፣ አመጋገብና በመሳሰሉት ነገሮች የመጠበቁ ጉዳይ፡፡

4. ማሕበራዊው ገጽታ - በቤተሰብና በማሕበረሰብ ግንኙነት ዙሪያ ጤናማ፣ ሰላማዊና ሚዛናዊ ሕይወት የመመስረቴ ጉዳይ፡፡

5. የአእምሮው ገጽታ - በመደበኛ ትምህርት ወይም መደበኛ ባልሆነ መልኩ አእምሮዬን ካለማቋረጥ በአንድ የእውቀት ዘርፍ የማሳደጌ ጉዳይ፡፡

6. የፍቅር ሕይወት ገጽታ - በብቸኝነት፣ በፍቅር ወይም በትዳር ግንኙነትን ውስጥ ጤናማና ደስተኛ ሕይወት የመምራቴጉዳይ፡፡

7. የገንዘብ ገጽታ - ገንዘብን በትክክለኛው መንገድ በማግኘት፣ በማባዛት፣ በመጠቀም፣ በማጠራቀምና በመሳሰሉት ዘርፎች የመብሰሌ ጉዳይ፡፡

ከእነዚህ ወሳኝ ዘርፎች መካከል አንዱን፣ ማለትም ገንዘብን አስመልክቶ ወሳኝ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና ከወዲሁ ተመዝገቡ፣ አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠው ርእስ፡-
“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
ስህተትን ወደ ስኬት!

“ከተሳሳታችሁ በኋላ እንደገና መጀመርን አትፍሩ፡፡ እንደገና ስትጀምሩ እኮ የምትጀምሩት ከዜሮ ሳይሆን ከስህተታችሁ ትምህርትና ልምድ ካገኛችሁበት ደረጃ በመነሳት ነው - ካልታወቀ ምንጭ

ከትናንትናው ዛሬ አድጋችኋል፣ ተለውጣችኋል፣ በስላችኋል፣ ተሻሽላችኋል፣ ጥበብ አግኝታችኋል፣ በርትታችኋል፣ ነገሩ ገብቷችኋል . . . ፡፡

ከዛሬው ደግሞ ነገ የተሻላችሁ ሆናችሁ ማደጋችሁና መለወጣችሁ አይቀርምና ተነሱና ስሩ፣ ሞክሩ፣ ጀምሩ!

ብርቱ ነበራችሁ፣ አሁንም ብርቱ ናችሁ! ነገም ትበረታላችሁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የገንዘብ አቅም እጥረት ጉዳይ!
የገንዘብ አቅም እጥረት ጉዳይ!

የገንዘብ አቅም እጥረት በራሱ ምንም ችግር የለበትም፡፡ ምክንያቱም ሁል ጊዜ በራሳችን ምርጫና ስህተት ችግር ውስጥ ስለማንገባ ማለት ነው፡፡

ይህ ማለት፣ ከቤተሰብ የወረስነው፣ የምንኖርበት ሃገራዊና ሕብረተባዊ ሁኔታ አንዳንድ አጋጣሚዎችና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የገንዘብ አቅማችን አናሳ እንዲሆን ሊያደርገው ይችላል፡፡

ችግር ያለበት . . .

• ላለብን የገንዘብ እጥረትና የኑሮ ትግል የምንሰጠውን ትክክለኛ ምላሽ አለማወቅ፣

• ባለብን የገንዘብ እጥረት ምክንያት የስሜት ቀውስ ውስጥ መግባት፣

• የኑሮ ደረጃን ከማንነት ዋጋ ጋር በማጣረስ በራስ ላይ ያለ አመለካከት መውረድ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ናቸው፡፡

እነዚህና መሰል ሁኔታዎች ላይ በሚገባ ከሰራንና በተረጋጋ ሁኔታ ከተንቀሳቀስን፣ የኑሮ ደረጃችን እስከሚሻሻል በሂደቱ እንጠነክራን፣ ጊዜው ሲደርስ ደግሞ ካለብን ጫና መላቀቃችን አይቀርም፡፡

ገንዘብን በትክክለኛው መንገድ ማግኘት (earning)፣ በሚዛዊነት ማዋል (spending)፣ በብቃት ማባዛት (multiplying)፣ በዲሲፕሊን ማጠራቀም (saving) እና በትክክለኛ መርህ መስጠት (giving) ካለንበት ከማንኛውም የገንዘብ ውጥረት ውስጥ እንድንወጣ መንገዱን ይጠርግልናል፡፡

በዚህ ርእስ ላይ ለመሰልጠን ፍላጎቱ ካላችሁ መረጃው ለእናንተ ነው፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
ላለብን በኢኮኖሚ የማደግ ፍላጎት ከመጸለይና ፈጣሪን ከማን ባሻገር ማድረግ ያለብን . . .

በማንበብ፣ በመማር፣ በመሰልጠንና አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር ራስን ማሻሻል ነው፡፡

የተዘጋጀሎትን ስልጠና ለመከታተል መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
ሶስቱ የስፍራችንን ትክክለኛነት የሚለዩ ጥያቄዎች
ሶስቱ የስፍራችንን ትክክለኛነት የሚለዩ ጥያቄዎች

ስፍራ ማለት፣ የተሰማራንበት የስራ መስክ፣ ለመኖር የወሰነውን የመኖሪያ አካባቢ፣ የተቀላቀልናቸውን ጓደኝነቶችና ማሕበራዊ ግንኙቶች፣ እንዲሁም ሌሎችን የወደፊታችንን የሚወስኑ ሁታዎችን የሚወክል ጉዳይ ነው፡፡ ከተጠቀሱትና ከመሰል ሁኔታዎች አንጻር ውስጣችን ያመነበትን፣ ለእኛ ተስማሚና ትክክለኛ የሆነውን “ስፍራችንን” ማግኘት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

ወደበለጠ ማብራሪያ ከመግባታችን በፊት፣ ያለንበት ስፍራ ትክክለኛ መሆኑንና አለመሆኑን ለመለየት መጠየቅ የምንችላቸው ጥያቄዎች አሉ፡፡

1. በዚህ ሁኔታና ስፍራ ውስጥ የአእምሮ ሰላም አለኝ ወይስ እረበሻለሁ?

2. በዚህ ሁኔታና ስፍራ ውስጥ በመቆየቴ የሕይወት ደረጃዬ እያደገ ይሄዳል ወይስ እያሽቆለቆለ?

3. ያለሁበት ሁኔታና ስፍራ ትክክል እንዳልሆነ እያወኩት በዚያ የቆየሁት ከፍርሃት የተነሳ ነው?

ትክክለኛውን ስፍራችንን ለይተን ያለማወቃችን ቀንደኛው አጉል ውጤት ቀስ በቀስ የስነ-ልቦና ቀውስ ከመግባታችንም ባሻገር፣ ያለንበት ስፍራ ምንም እንኳ ለወደፊት መሻሻልን የማይሰጠን ቢሆንም እንዲሁ ተቀብለን እዚያው የመክረማችን ጉዳይ ነው፡፡

ይህ ሲሆን፣ እድሜያችንን እንዲሁ እናባክናለን፣ በአንድ ስፍራ ተተክለን በመቅረታችን ምክንያት ትክክለኛና ለእኛ መሆን የሚገባቸው እድሎች ያመልጡናል፣ ውስጥጣችን ተስፋ ይቆርጣል . . . ፡፡ ስለዚህ ስፍራችንን ለይተን ለማወቅ ማድረግ ያለብንን ማድረግ የግድ ነው፡፡

ስፍራችንን ከለየን በኋላ እዚያ እስከምንደርስ ድረስ አሁን ባለንበት የመቆየታችን ሁኔታ ምንም ችግር የለበትም፡፡ ስፍራችንን ከለየን በኋላ ግን አሁን ያለንበት ቦታ ሆነን ካለማቋረጥ ወደትክክለኛ ስፍራችን የምንደርስብትን እቅድ ማውጣ አለብን፡፡ ያንን እቅድ ካወጣን በኋላ ደግሞ ጉዞ በመጀመር ካለማቋረጥ ወደዚያ መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ይህ እንቅስቃሴ የሚያስከፍለንን ሁሉ መስዋእትነት ከመክፈልም ወደ ኋላ አንበል፡፡

ሆኖም፣ ያለንበት ስፍራ ትክክለኛው እንዳልሆነ በመገንዘብና ወደ የት አልፈን መሄድ እንዳለብን ከለየን በኋላ፣ ለውጥ በማምጣት እዚያ መድረስ ከባድ መስዋእትነት እንደሚያስከፍል እስበን ያለንበት ከቀረን ግን የበለጠ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡

አንድ ነገር አንዘንጋ፡- ወደ ትክክለኛው ስፍራችን ለመራመድ ከምንከፍለው ዋጋ የበለጠ የምንከፍለው ትክክለኛ ስፍራችን ባልሆነ ቦታ በመቆየት ነው፡፡ በመንቀሳቀስ የአጭር ጊዜ ዋጋ እንከፍላለን፣ ያለንበት በመቅረት ግን የረጅም ጊዜ ዋጋ እንከፍላለን፡፡

ያለህበትን ስፍራ እንመልከት፣ ትክክለኛውን ስፍራችንን እንለይ፣ ከዚያም በጥንቃቄ እንወስንና ካለንበት ስፍራ የመቀየርን ጉዞ እንጀምር!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የገንዘብ አያያዛችን ጉዳይ!

በሚከተሉት አምስት የገንዘብ ዘርፎች መብሰል፣ ማደግና ሚዛናዊ መሆን የገንዘብ ነጻነትን ይሰጣል፡፡

1. ገንዘብን የማግኘት ክህሎት - የገንዘብ ገቢያችሁን ይጨምረዋል!

2. ገንዘብን ለጤናማ ዓላማ የመጠቀም ጥበብ - ገንዘብን በበጀት የመጠቀም ብልሃታችሁን ያሳድገዋል!

3. ገንዘብን ኢንቨስት በማድረግ የማባዛት ብቃት - በኢኮኖሚ ልቆ የመገኘትን መንገድ ይጠርግላችኋል፡፡

4. ገንዘብን የማጠራቀም ዲሲፕሊን - ለድንገተኛ ነገር ዝግጁ ያደርጋችኋል!

5. ገንዘብን የመስጠት ፈቃደኝነት - የሰብአዊነትና የእርካታ ስሜትን ይሰጣችኋል!

በእነዚህ ወሳኝ የገንዘብ ሂደቶች በበሰልንና ሚዛናዊ በሆንን ቁጥር የገንዘብ ነጻነትንና እድገትን እናገኛለን፡፡

ለዚህና ለመሰል ከገንዘብ ጋር ለሚገናኙ እውቀቶች የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የማስገባትና የማቆየት ሕግ
የማስገባትና የማቆየት ሕግ

የማይለወጠው እውነታ፡- አንድን ነገር በእጃችን ባስገባንበት መንገድ ብቻ በእጃችን እናቆየዋለን!

እስቲ ቀድሞ የእኛ ያልነበረና አሁን ግን በእጃችን ላይ ያለ ማንኛውንም ነገር እናስብ፡፡ ከዚያም በእንዴት አይነት ሁኔታ በእጃችን እንዳስገባነውና የእኛ እንዳደረግነው እናስታውስ፡፡ ከዚያም ወደፊት ያንን ነገር በእጃችን ለማቆየት ያለንን ብቸኛ መንገድ ማወቅ ጊዜ አይፈጅብንም፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ነገሮችን በእጃችን ለማስገባት እንጣጣራን፡፡ ያፈቀርነውን ሰው የእኛ ለማድረግ፣ ስራን ለማግኘት፣ ንግድን ለመጀመር፣ የተለያዩ ንብረቶችና ቁሳቁሶች ባለቤት ለመሆን፣ ስልጣንን ለመጨበጥ . . . ፍላጎታችን ዘርፈ-ብዙ ነው፡፡ ይህ ፍላጎት ሲጋጋል ደግሞ ምንም አይነት መንገድ ተጠቅመንም ቢሆን ያንን ነገር በእጃችን የማስገባታችንን ሩጫ ጥጉ ድረስ ይወስደዋል፡፡

አንድን ነገር የእኛ ለማድረግ የመፈለጋችንን ያህል፣ ያንን ነገር እጃችን ለማስገባት የምንጠቀምበትን መንገድ ጉዳይ አብረን ማሰቡ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ማንኛውንም ነገር በእጃችን ለማስገባት በተጠቀምንበት መንገድ ብቻ ነው ነገሩ እጃችን ከገባ በኋላ ማቆየት የምንችለው፡፡ ከጊዜያዊው ያላለፈ አይነት ሕይወት የመኖር ፍላጎት ካላደረብን በስተቀር፡፡

ሲተነተን . . .

• በኃይል እጃችን የገባን ነገር በእጃችን ለማቆየት ካለማቋረጥ ኃይልን መጠቀም አለብን፣

• በማታለል እጃችን የገባን ነገር ለማቆየት ካለማቋረጥ ማታለል አለብን፣

• በውሸት እጃችን የገባን ነገር ለማቆየት ካለማቋረጥ መዋሸት አለብን . . .

እያለ እውነታው ይቀጥላል፡፡ ከተርታው ሰው እስከ ተጽእኖ አምጪውና አልፎም እስከ አገር አመራሩ ድረስ እውነታው ፈጽሞ አይለወጥም፡፡

አንዲትን ሴት ለማግባት ካለው ፍላጎት የተነሳ የሌለውን ነገር እንዳለው የዋሸን አንድ ሰው ብናስብ፣ ተሳክቶለት ያችን ሴት ቢያገባት፣ ነኝና አለኝ ብሎ ያስተዋወቀው እንደሌለ እንዳይታወቅበት ምን አይነት ጡዘት ውስጥ እንደሚገባ ማስላት አያዳግትም፡፡ ቀድሞ ለማስታወቂያነት የተጠቀመበትን ድራማ እውን ማድረግ ሲያቅተው ግንኙነት መዛባት ይጀምራል፡፡

በስራውም መስክ ቢሆን እውነታው ይኸው ነው፡፡ የሌለንን ችሎታ እንዳለን፣ ያልሆንነውን ማንነት ደግሞ እንደሆንን አሳይተን በውሸት በገባንበት የስራ መስክ ውስጥ ለመቆየት ምን ማድረግ እንዳለብን መገመት አያስቸግርም፡፡ ካለማቋረጥ ስንሸፋፍንና ስንዋሽ ልንኖር ነው፡፡

መፍትሄው፣ አታላይነትን፣ ዛቻን፣ ኃይልንና ጉልበትን ተጠቅመን በወጣንበት የውሸት ከፍታ ላይ ለመቆየት እድሜ ልካችንን ስንታገልና ስንፍጨረጨር ከመኖር ይልቅ፣ ያለንንና የሆንነውን ትክክለኛውን ነገር አቅርበን በተረጋጋ ሁኔታ ውሎ ማደርና በልክ መኖር እጅግ የተመረጠ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
በገንዘብ አቅም የማደግ ትርጉም!
በገንዘብ አቅም የማደግ ትርጉም!

“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎቶች ማዳበር” ማለት ምን ማለት አይደለም

1. በሕብረተሰቡ መካከል ታወቂ ሃብታም የመሆን ፍላጎት ማለት አይደለም፡፡

2. እንደፈለግን የምናወጣው ገንዘብ ማካበት ማለት አይደለም፡፡

3. ገንዘብን ለማግኘት ካለልክ መሯሯጥና ምንም መንገድን ለመጠቀም ክፍት መሆን ማለት አይደለም፡፡

“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎቶች ማዳበር” ማለት ምን ማለት ነው

1. ትክክለኛ የገንዘብ ማግኛ መንገዶችን በመከተል በኢንቨስትመንት እያደጉ መሄድ ማለት ነው፡፡

2. ለእኛ እና ለቤተሰባችን በቂ የገንዘብ ገቢን በማግኝኘት መደላደል ማለት ነው፡፡

3. ገቢያችን እኛን እና ቤተሰባችን ካደረላደለ በኋላ ለድንገተኛ ሁኔታ እና ለተቸገሩትን ለመደገፍ የሚያስችለን የገንዘብ አቅም ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡

ይህንን ሚዛናዊ አመለካከት ስናዳብር፣ የሚያስፈልገንን ነገር (our needs) ከማሟላት አልፈን ከዓላማችን አንጻር ማድረግ ወደምንፈልገው ነገር (our wants) የማለፍ አቅም ይኖረናል፡፡

በዚህ ርእሰ-ጉዳይ ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማዳበር የሚጠቅማችሁ ስልጠና እደተዘጋጀላችሁ አትርሱ፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
2025/07/06 20:28:04
Back to Top
HTML Embed Code: