ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
“ሁል ጊዜ እንደተሳሳትኩ ነው … አንድ ቀን ትክክል ሆኜ አላውቅም … አመለካከቴ የተሳሳተ ነው … ብቃት የለኝም ... ሰዎች ወደፊት ሲገሰግሱ እኔ ግን ኋላ ቀርቻለሁ … አልቻልኩበትም … ዓላማየን አላውቀውም … እና የመሳሰሉት ስሜቶች ብዙ ሰዎችን የሚያጠቁ ስሜቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በተገቢው መንገድ ካልተያዙ ማንነትህን የማኮሰስና ወደኋላ የማስቀረት አቅም አላቸው፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እነዚህ ስሜቶች ሁሉም ሰው የሚጋራቸው ስሜቶች ናቸው፡፡ ሆኖም፣ እንደ ማንቂያ ደወል ከተጠቀምክባቸው መልካም ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እነዚህን ስሜቶች ለተስፋ መቁረጥ ከተጠቀምክባቸው ወደ ኋላ ይጎትቱሃል፡፡
ይህንን እውነታ አንድ ሰው በዚህ መልክ ይገልጽዋል፡-
በብልሽት ምክንያት ልክ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ የቆመ (አናሎግ) ሰዓትን ተመልከተው፡፡ ይህ ሰዓት ምንም እንኳን የቆመና ትክክል ያልሆነ ሰዓት ቢሆንም፣ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የቆመ ሰዓት በቀ ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል - ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ እና ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ፡፡ አየህ የተበላሸ ሰዓት እንኳን በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል፡፡ አንተ ደግሞ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
የቆመ ሰዓት በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ከሆነ፣ ምንም ያህል ስህተት የሰራህ ሰው ብትሆን፣ ምንም ያህል ወደፊት መራመድ እንዳቃተህ ብታስብ፣ ምንም ያህል የመሻሻል ነገር እንዳልታየብህ ብታምን፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!! የዛሬ አስር አመት፣ የዛሬ አምስት አመት፣ የዛሬ ሶስት አመት፣ የዛሬ አመት . . . የነበርክበትን አስብ፡፡ በትንሹም ቢሆን አሁን ከዚያ ትሻላለህ፡፡
ምናልባት፣ “እኔ ባለሁበት የቆምኩ ሰው ነኝ” ልትል ትችላል፡፡ ምናልባትም፣ “እኔ ባለፉት አመታት ከነበርኩበት ደረጃ የወረደ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት” በማለት ታስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሁኔታ እንኳን የተማርከውን ትምህርት አስበው፡፡ ሁኔታህ አለመሻሻሉ እየሰጠህ ያለውን የመንቂያ ደውል አስታውሰው፡፡ ማሰብ፣ ራስን መገምገም፣ ያለፈውንና የወደፊቱን ማስላት የመቻልህን ብቃት አስበው፡፡
ከዚህ አመለካከት ለመውጣት ከፈለክ፣ ከተሳሳትከው፣ ከማትችለው፣ ካልተሳካውና ካልሆነው አትነሳ፡፡ ምንም እንኳን ትንሽ ነው ብለህ ብታስብም፣ ከትክክለኛነትህ፣ ከተሳካልህና ከሆነልህ ነገር ተነሳ፡፡ በዚህ ስሜት ጫና ውስጥ ሆነህ ዘንግተኸው ነው እንጂ፣ ሌሎች ማድረግ የቻሏቸው ለአንተ ግን ያቀቱህ በርካታ ነገሮች የመኖራቸውን ያህል፣ ሌሎች ሰዎች ያቃታቸው አንተ ግን ማድረግ የምትችላቸው በርካታ ነገሮች እንዳሉ አትርሳ፡፡
ያም ሆነ ይህ፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
የስልጠና እድል!
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል::
@DrEyobmamo
እናመሰግናለን!

ጥያቄ፡-
ሰላም ዶ/ር
ከስንት አመታችን ጀምሮ ስራ መስራት አለብን? ከእድሜው እና ከጥቅሙ አብራራልኝ፡፡
መልስ፡-
ማንኛውም ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ ስራን መስራት መልመድ አለበት፡፡ እዚህ ላይ “ስራ” በምንልበት ጊዜ በሁለት ከፍለን መመልከት ይኖርብናል፡፡
1. ካለ ክፍያ መስራት
አንድ ልጅ መናገር እና በእግሮቹ መሄድ ከጀመረበት እድሜው ጀምሮ ከእድሜው ጋር የሚመጥን ስራን በቤተሰቦቹ ምሪትና አበረታችነት ቢሰራ ጥሩ ነው፡፡
ለምሳሌ፣ ከተመገበ በኋላ የበላበትን ሳህን ከጠረቤዛ ላይ ማንሳት አይነት ቀላል ስራ ጀምሮ፣ እድሜው እየጨመረ ሲሄድ ቀላላል የጽዳት ስራዎችን ቢሰራ መልካም ነው፡፡ እድሜው ወደ አስራዎቹ ሲገባ ደግሞ ቤተሰቦች የሚሰሩት የግል ስራ ካለ እሱ ላይ በተወሰነ መልኩ ሃላፊነትን እየተማረ ቢሄድ ተመራጭ ነው፡፡
ጥንቃቄ
• ልጆች የሚሰሩት ስራ በልጅነታቸው ሊኖቸው የሚገባን የጨዋታ ጊዜ እንዳይነካባቸው ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
• ልጆች ሲሰሩ ምንም እንኳን የገንዘብ ክፍያ ባይሰጣቸውም የመመስገን፣ የማድነቅና አንዳንድ ነገሮችን በመስጠት ማበረታታት መልካም ነው፡፡
• ልጆች ሲሰሩ በትንሹ ገንዘብ መስጠቱ ችግር ባይኖረውም ገንዘቡን ግን አጠራቅመው አንድ የግል ፍላጎታች ላይ እንዲያውሉት በመቆጣጠርና ማየት እፈላጊ ነው፡፡
2. ለክፍያ መስራት
አንድ ልጅ 18 ዓመት ከሞላው ጀምሮ ገንዘብን እየተከፈለው ቢሰራ የሚበረታታ ነው፡፡
ለምሳሌ፣ ራሱ የፈጠረውን ስራ፣ የቅጥር ስራ፣ ወይም የቤተሰቦቹን ንግድ ወይም ሌላ ስራ በማገዝ አቅጣጫ በክፍያ ቢሰራ የሚመከር ነው፡፡ ይህንን በማድረጉ ከልጅነት ወደ አዋቂነት፣ በሰው ላይ ከመደገፍ በራሱ ላይ ወደመደገፍ የመዘዋወርን ሂደት ቀስ በቀስ እንዲለምድ ያግዘዋል፡፡
ጥንቃቄ
• ወጣቶች ስራን ሲሰሩ በተቻለ መጠን የቤተሰብን ሃላፊነት ከመሸከም አንጻር ሁሉም ነገር በእነሱ ትከሻ ላይ ሊቀመጥ አይገባውም፡፡
• ወጣቶች ሲሰሩ ትኩረታቸው ገንዘብ ላይ ከመሆኑ የተነሳ ትምህርታቸውንና ለእድሜያቸው የሚመጥንን ሁኔታ ችላ እንዳይሉ መመልከትና ምሪት መስጠት የግድ ነው፡፡
• ወጣቶች ሲሰሩ ገንዘባቸውን በትክክለኛው ነገር ላይ ማዋላቸውንና ወደ ተላያዩ ሶሶች እንዳይገቡ ክትትል ያስለፍጋቸዋል፡፡

የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (Trauma Bonding) ምንድን ነው?
በስነ-ልቦና ጤንነት ዘርፍ “Trauma Bonding” የተሰኘውን ሃሳብ ወደ አማርኛችን ለመመለስ ማብራራት የሚጠይቅ ጉይዳ ቢሆንም፣ የጉዳት (የስቃይ) የሚለው ትርጓሜ ለመነሻነት ያግዘናል፡፡ ሲብራራም በአንድ ሰው አመካኝነት አንድ የአእምሮ፣ የስሜት ወይም የስነ-ልቦና ጉዳት ሲደርስብን ከሁኔታው የተነሳ የሚከሰተውን መስመር የሳተ ሂደትንና ምላሽ ጠቋሚ ነው፡፡
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር የሚከሰተው የአእምሮ፣ የስሜት ወይም የስነ-ልቦና ክልላችን ሲጣስ ነው፡፡ ጥሰቱ የደረሰበት ሰው ቀስ በቀስ የደረሰበት ሁኔታ መብቱ ተጥሶ ሳይሆን ተገቢ ነገር እንደሆነ ወደማመን ሲመጣ ያለውን ሂደት የሚጠቁም ሃሳብ ነው፡፡ የሆነበት ነገር በአጋጣሚ እንደሆነና ጉዳቱን ያደረሰበት ሰው አውቆና ሆን ብሎ ሊጎዳው አስቦ እንዳላደረሰበት ወደማመን ሲመጣ ሂደቱ የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (Trauma Bonding) ይባላል፡፡
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (Trauma Bonding) በጓደኝነት፣ በፍቅር፣ በትዳርና በቤተሰብ ግንኙነቶች ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ ሲሆን ሰዎቹ ሆን ብለው እየጎዱንና ጥቃትን እያደረሱብን እንኳን ሁኔታውን እንደጉዳት ቆጥረን ተገቢውን ምላሽ የመውሰድ ፍላጎቱም ሆነ አቅሙ አይኖረንም፡፡
ለምሳሌ፡-
• የሆነብን ነገር ሁሉ በራሳችን ስህተት እንደሆነ አምነን እንድንቀበል (gas lighting) ያደርጉናል፡፡
• ከጎዳን ሰው ጋር ከተለያየን በኋላ ወደዚያው ጤና-ቢስና ጎጂ ግንኙነት ውስጥ እንደገና የመመለስ አዙሪት እንገባለን፡፡
• ሰዎቹ ለሚያደርሱብን ጉዳት ምክንያት በመፈላለግ እውነታውን ለመቀበል አለመፈለግ ያጠቃናል፡፡
• መርዛማና ጎጂ ከሆነ ግንኙነት ወስኖ ለመውጣት ያለመቻል ስሜት ይጫጫነናል፡፡
• ስለምናልፍበት ሁኔታ ለሌሎች ሰዎች ከተናገርን ሁኔታው ይፋፋማል በሚል ስጋት የጥቃቱን ሁኔታ ለሌሎች ሰዎች ለመናገር ድፍረት ማጣትና ዋጥ ማድረግ እናበዛለን፡፡
• እንደፈለጉ የሚያደርጉንንና የሚጎዱንን ሰዎች በግልጽነት ለመሞገት ፍላጎትና ድፍረት እናጣለን፡፡
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር” (“Trauma Bonding”) አስከፊ ውጤት
1. ውብ የሆነን ጊዜ ማባከን
ከነገ ነገ ይስተካከላል ብለን በምናስበው ሁኔታ ውስጥ እያለፍን አሁንም የማይስተካከል ከሆነና እኛም በዚያው ከቀጠልን፣ በጉዳት እና ራስን በማከም ሂደት ውስጥ ብዙ ልንሰራባቸውና ልንደሰትባቸው የምንችላቸውን አመታቶቻችንን እናባክናቸዋለን፡፡
2. የጤና ቀውስ
በተደጋጋሚ የስነ-ልቦና፣ የስሜትና የአካል ጥቃት የሚደርስት ሰው ብዙም ሳይቆይ ሊቀለበስ ለማይችል በሽታ ራሱን ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
3. የወደፊት ጸጸት
ዛሬ በዚህና በዚያ ያባከንናቸው አመታት፣ ያደከምነው የስሜት ሁኔታ፣ ያጣነው ጤንነትና መሰል ነገሮች ነገ እንደሚጸጽተን ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡
4. ሊረዱን ከሚችሉ ሰዎች እየተለያዩ መሄድ
በአሰቃቂ ትስስር ቁጥጥር ስር ስንውል ከሚያጋጥመን ሁኔታ አንዱ ከቅርብ ወዳጆቻችን መለየት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የሚከሰተው በአንድ በኩል በዚህ ውጣ ውረድ ውስጥ ስናልፍ ለማሕበራ ግንኙነት አቅም ስለምናጣ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሊረዱን የፈለጉ ሰዎችን ችላ በማለት ስለምናጣቸው ነው፡፡
ከተጠቀሰው ርእስ ጉዳይ እና በሌሎች የሕይወት አስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ጥያቄያችሁን ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ መላክ ትችላላችሁ፡፡
@DrEyobmamo
የዚህን ትምህርት ሁለተኛ ክፍል ዛሬ ከቀኑ በ6 ሰዓት ይጠብቁ፡፡
በሚቀጥለው ፖስቴ፣ “የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (“Trauma Bonding”) አስከፊ ውጤት” የሚለውን ሃሳብ እንመለከታለን፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
በስነ-ልቦና ጤንነት ዘርፍ “Trauma Bonding” የተሰኘውን ሃሳብ ወደ አማርኛችን ለመመለስ ማብራራት የሚጠይቅ ጉይዳ ቢሆንም፣ የጉዳት (የስቃይ) የሚለው ትርጓሜ ለመነሻነት ያግዘናል፡፡ ሲብራራም በአንድ ሰው አመካኝነት አንድ የአእምሮ፣ የስሜት ወይም የስነ-ልቦና ጉዳት ሲደርስብን ከሁኔታው የተነሳ የሚከሰተውን መስመር የሳተ ሂደትንና ምላሽ ጠቋሚ ነው፡፡
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር የሚከሰተው የአእምሮ፣ የስሜት ወይም የስነ-ልቦና ክልላችን ሲጣስ ነው፡፡ ጥሰቱ የደረሰበት ሰው ቀስ በቀስ የደረሰበት ሁኔታ መብቱ ተጥሶ ሳይሆን ተገቢ ነገር እንደሆነ ወደማመን ሲመጣ ያለውን ሂደት የሚጠቁም ሃሳብ ነው፡፡ የሆነበት ነገር በአጋጣሚ እንደሆነና ጉዳቱን ያደረሰበት ሰው አውቆና ሆን ብሎ ሊጎዳው አስቦ እንዳላደረሰበት ወደማመን ሲመጣ ሂደቱ የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (Trauma Bonding) ይባላል፡፡
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (Trauma Bonding) በጓደኝነት፣ በፍቅር፣ በትዳርና በቤተሰብ ግንኙነቶች ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ ሲሆን ሰዎቹ ሆን ብለው እየጎዱንና ጥቃትን እያደረሱብን እንኳን ሁኔታውን እንደጉዳት ቆጥረን ተገቢውን ምላሽ የመውሰድ ፍላጎቱም ሆነ አቅሙ አይኖረንም፡፡
ለምሳሌ፡-
• የሆነብን ነገር ሁሉ በራሳችን ስህተት እንደሆነ አምነን እንድንቀበል (gas lighting) ያደርጉናል፡፡
• ከጎዳን ሰው ጋር ከተለያየን በኋላ ወደዚያው ጤና-ቢስና ጎጂ ግንኙነት ውስጥ እንደገና የመመለስ አዙሪት እንገባለን፡፡
• ሰዎቹ ለሚያደርሱብን ጉዳት ምክንያት በመፈላለግ እውነታውን ለመቀበል አለመፈለግ ያጠቃናል፡፡
• መርዛማና ጎጂ ከሆነ ግንኙነት ወስኖ ለመውጣት ያለመቻል ስሜት ይጫጫነናል፡፡
• ስለምናልፍበት ሁኔታ ለሌሎች ሰዎች ከተናገርን ሁኔታው ይፋፋማል በሚል ስጋት የጥቃቱን ሁኔታ ለሌሎች ሰዎች ለመናገር ድፍረት ማጣትና ዋጥ ማድረግ እናበዛለን፡፡
• እንደፈለጉ የሚያደርጉንንና የሚጎዱንን ሰዎች በግልጽነት ለመሞገት ፍላጎትና ድፍረት እናጣለን፡፡
የጉዳት (የስቃይ) ትስስር” (“Trauma Bonding”) አስከፊ ውጤት
1. ውብ የሆነን ጊዜ ማባከን
ከነገ ነገ ይስተካከላል ብለን በምናስበው ሁኔታ ውስጥ እያለፍን አሁንም የማይስተካከል ከሆነና እኛም በዚያው ከቀጠልን፣ በጉዳት እና ራስን በማከም ሂደት ውስጥ ብዙ ልንሰራባቸውና ልንደሰትባቸው የምንችላቸውን አመታቶቻችንን እናባክናቸዋለን፡፡
2. የጤና ቀውስ
በተደጋጋሚ የስነ-ልቦና፣ የስሜትና የአካል ጥቃት የሚደርስት ሰው ብዙም ሳይቆይ ሊቀለበስ ለማይችል በሽታ ራሱን ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
3. የወደፊት ጸጸት
ዛሬ በዚህና በዚያ ያባከንናቸው አመታት፣ ያደከምነው የስሜት ሁኔታ፣ ያጣነው ጤንነትና መሰል ነገሮች ነገ እንደሚጸጽተን ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡
4. ሊረዱን ከሚችሉ ሰዎች እየተለያዩ መሄድ
በአሰቃቂ ትስስር ቁጥጥር ስር ስንውል ከሚያጋጥመን ሁኔታ አንዱ ከቅርብ ወዳጆቻችን መለየት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የሚከሰተው በአንድ በኩል በዚህ ውጣ ውረድ ውስጥ ስናልፍ ለማሕበራ ግንኙነት አቅም ስለምናጣ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሊረዱን የፈለጉ ሰዎችን ችላ በማለት ስለምናጣቸው ነው፡፡
ከተጠቀሰው ርእስ ጉዳይ እና በሌሎች የሕይወት አስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ጥያቄያችሁን ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ መላክ ትችላላችሁ፡፡
@DrEyobmamo
የዚህን ትምህርት ሁለተኛ ክፍል ዛሬ ከቀኑ በ6 ሰዓት ይጠብቁ፡፡
በሚቀጥለው ፖስቴ፣ “የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (“Trauma Bonding”) አስከፊ ውጤት” የሚለውን ሃሳብ እንመለከታለን፡፡
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
የስልጠና እድል!
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (“Trauma Bonding”) ሂደትና አስቸጋሪነት
ዛሬ ጠዋት፣ “የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (Trauma Bonding) ምንድን ነው?” የሚለውን ሃሳብ ተመልክተናል፡፡ አሁን ደግሞ ስለ ሂደቱና አስቸጋሪነቱ እንመልከት፡፡
በሕይወታችን ሰዎች አሰቃቂና ጎጂ የሆነ ነገር እያደረጉብን መለየት ወይም ሁኔታውን ማሸነፍ ሲያቅተን ሂደቱ ይህንን ይመስላል፡፡
1. ሰዎቹ እንደ ልማዳቸው ይጎዱናል
2. እኛም በሁኔታው እንጎዳና ከእነሱ ስለመለየት ወይም ጠንካራ ሆኖ ስለመመከት ማሰብ እንጀምራለን
3. ሰዎቹ ብዙም ሳይቆዩ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሆነው በጥሩ ሁኔታ ይቀርቡናል
4. እኛም ሰዎቹ የተለወወጡ ወይም የተጸጸቱ መስሎን መለስ እንላለን
5. ሰዎቹ ለተወሰነ ጊዜ በአስገራሚ ሁኔታ ጥሩ ሆነው በማሳለፍ ያዘናጉናል
6. እኛም ከተወሰነ የእፎይታ ጊዜ በኋላ ራሳችንን ተጋላጭ አድርገን በማቅረብ ነገሩን ተወት እናደርገዋለን
7. ሰዎቹ በቁጥር አንድ ላይ የተጠቀሰውን የጉዳት ሁኔታ በመድገም ዑደቱን ይቀጥላሉ፡፡
ሰዎች በእነደዚህ አይነት የአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር ውስጥ የሚቆዩት የተለያየ ምንያት ለራሳቸው እየሰጡ ቢሆንም፣ ሲጠቃለል ግን ስሙ ያው ነው - የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (“Trauma Bonding”)
እንደዚህ አይነት ጥቃት አድራሾች በአብዛኛው ጊዜ ለሰው ስሜት ግድ የማይሰጣቸው፣ ለራሳቸውና ለራሳቸው ብቻ የሚያስቡ እና ከፍተኛ የሆነ የማታለል ብቃት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በተጨማሪም ባዶ ቃልኪዳን በመስጠት እና እንደሚወዱንና እንደሚጠነቀቁልን የሚያሳምንበት ሁኔታና ቃል በመናገር የሚታወቁ ናቸው፡፡
ከአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር (“Trauma Bonding”) ለምን መላቀቅ ያቅተናል?
1. ከተለየሁ አንድ ነገር ይደርስብኛል ብሎ የሚል ፍርሃት
ከዚህ ሁኔታ የተነሳ በአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር ውስጥ ያለ ሰው ማሰብ ያለበት አሁን እየደረሰበት ካለው ሁኔታ የበለጠ ምንም ሊደርስበት እንደማይችል ነው፡፡
2. ከተለየሁ አንድ ነገር አጣለሁ የሚል ስጋት
ከዚህ ሁኔታ የተነሳ በአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር ውስጥ ያለ ሰው ማሰብ ያለበት አሁን ካጣው ማንነቱ የበለጠ ምንም ነገር ሊጣ እንደማይችል ነው፡፡
3. እንደ ትዳር ያለ በቀላሉ ሊላቀቁት የማይችሉት የኪዳን ትስስር
ከዚህ ሁኔታ የተነሳ በአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር ውስጥ ያለ ሰው ማሰብ ያለበት ምንም እንኳን ኪዳንን አፍርሶ የመሄድ ምርጫ በቀላሉ ሊወሰድ የማይገባው ቢሆንም እዚያው ባለበት ሁኔታና ቦታ ሆኖ ከጥቃት አድራሹ አጉል ተጽእኖ በልጦና ጠንክሮ የሚገኝትን መንገድ መፈለግ እንዳለበት ነው፡፡
4. ጥቃት አድራጊዎቹን መውደድ፣ ማፍቀር ወይም ከእነሱ ተለይቶ መኖር እንደማይችሉ ማሰብ
ከዚህ ሁኔታ የተነሳ በአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር ውስጥ ያለ ሰው ማሰብ ያለበት በእንደዚህ አይነት ግንኙነት ውስጥ ለአመታት በቆዩ ቁጥር የሚከተለው ጉዳት እነሱን በማፍቀር ለመቆየትም ሆነ ግንኙነቱን ወደሚቀጥለው ደረጃ ለመውሰድ የማይችሉበት ደረጃ እንደሚደርሱ ነው፡፡
በእንደዚህ አይነት የጉዳት (የስቃይ) ትስስር (“Trauma Bonding”) ውስጥ ራሳችሁን ካገኛችሁት አስፈላጊውንና ትክክለኛውን ምላሽ በመስጠት ራሳችሁን ነጻ እንድታወጡ ትመከራላችሁ፡፡
ከተጠቀሰው ርእስ ጉዳይ እና በሌሎች የሕይወት አስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ጥያቄያችሁን ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ መላክ ትችላላችሁ፡፡
@DrEyobmamo
የዚህን ትምህርት የመጨረሻ ክፍል ዛሬ ማታ በ12 ሰዓት ይጠብቁ፡፡
በሚቀጥለው ፖስቴ፣ "ከአሰቃቂ (ጉዳት) ትስስር (“Trauma Bonding”) የመላቀቅ እርምጃዎች?" የሚለውን ሃሳብ እንመለከታለን፡፡

ከአሰቃቂ (ጉዳት) ትስስር (“Trauma Bonding”) የመላቀቅ እርምጃዎች?
ከዚህ በፊት በተነጋገርናቸው የአሰቃቂ (ጉዳት) ትስስር ሃሳቦች አንጻር ችግር እንዳለበን ከተገነዘብን የሚከተሉትን የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡
1. ምንም አይነት ጥፋተኛ ብትሆኑም ሆነ ምንም አይነት ማንነት ቢኖራችሁ ማንም ሰው በምንም አይነት መልኩ በእናንተ ላይ ጉዳት የማድረስ መብት እንደሌለው አምናችሁ ተቀበሉ፡፡
2. ያለ-የሌለ አቅማችሁን ሰብስቡና ከሰዎቹ ሁኔታ የተነሳ እየደረሰባችሁ ያለውን ጉዳት ለራሳቸው ለሰዎቹ ግለጹላቸው፡፡
3. ስሜታችሁን ለሰዎቹ ለመንገር ስታስቡ የሚሰማችሁ የፍርሃት ስሜት ትክክለኛ የሆነ ስሜት እንደሆነ ተቀበሉት፣ ከመናገር ግን ወደኋላ አትበሉ፡፡
4. ሰዎቹን ለመናገር አቅም ካጣችሁ ወይም በመናገራችሁ ምክንያት የበለጠ ጉዳት እንደሚደርስባችሁ ካሰባችሁ ለሁኔታው ተገቢውን ምላሽ ሊሰጥ ለሚችል ሰው ለመናገር ሞክሩ፡፡
5. በጥቃት፣ በጉዳትና በጭቆና እድሜ ልካችሁን ከመኖር ይልቅ አንድ ጊዜ ወስናችሁና ለጊዜው ተጎድታችሁ የወደፊት ሕወታችሁን መስመር ማስያዝ የተሻለ እንደሆነ አትርሱ፡፡
ከተጠቀሰው ርእስ ጉዳይ እና በሌሎች የሕይወት አስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ጥያቄያችሁን ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ መላክ ትችላላችሁ፡፡
@DrEyobmamo
የዛሬው ትምህርት ተጠናቀቀ!!
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ከዚህ በፊት በተነጋገርናቸው የአሰቃቂ (ጉዳት) ትስስር ሃሳቦች አንጻር ችግር እንዳለበን ከተገነዘብን የሚከተሉትን የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡
1. ምንም አይነት ጥፋተኛ ብትሆኑም ሆነ ምንም አይነት ማንነት ቢኖራችሁ ማንም ሰው በምንም አይነት መልኩ በእናንተ ላይ ጉዳት የማድረስ መብት እንደሌለው አምናችሁ ተቀበሉ፡፡
2. ያለ-የሌለ አቅማችሁን ሰብስቡና ከሰዎቹ ሁኔታ የተነሳ እየደረሰባችሁ ያለውን ጉዳት ለራሳቸው ለሰዎቹ ግለጹላቸው፡፡
3. ስሜታችሁን ለሰዎቹ ለመንገር ስታስቡ የሚሰማችሁ የፍርሃት ስሜት ትክክለኛ የሆነ ስሜት እንደሆነ ተቀበሉት፣ ከመናገር ግን ወደኋላ አትበሉ፡፡
4. ሰዎቹን ለመናገር አቅም ካጣችሁ ወይም በመናገራችሁ ምክንያት የበለጠ ጉዳት እንደሚደርስባችሁ ካሰባችሁ ለሁኔታው ተገቢውን ምላሽ ሊሰጥ ለሚችል ሰው ለመናገር ሞክሩ፡፡
5. በጥቃት፣ በጉዳትና በጭቆና እድሜ ልካችሁን ከመኖር ይልቅ አንድ ጊዜ ወስናችሁና ለጊዜው ተጎድታችሁ የወደፊት ሕወታችሁን መስመር ማስያዝ የተሻለ እንደሆነ አትርሱ፡፡
ከተጠቀሰው ርእስ ጉዳይ እና በሌሎች የሕይወት አስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ጥያቄያችሁን ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ መላክ ትችላላችሁ፡፡
@DrEyobmamo
የዛሬው ትምህርት ተጠናቀቀ!!
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የስልጠና እድል!
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
እናመሰግናለን!
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
እናመሰግናለን!
የስልጠና እድል!
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
እናመሰግናለን!
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
እናመሰግናለን!
የገንዘብ ነጻነት ስንል!
ምን ማለት ነው?
• የወቅቱን ገንዘብ የማግኘት አቅማችንን በመቀበል ቀስ በቀስ የማደግን እንቅስቃሴ መጀመር ማለት ነው፡፡
• የግልን እና የቤሰተብን ፍላጎት ለማሟላት በቂ የገንዘብ ምንጭ መፍጠር ማለት ነው፡፡
• በእጃችን የገባውን ገንዘብ በትክክለኛው መንገድ መጠቀም፣ ማባዛትና አልፎም ለሌሎች መትረፍ ማለት ነው፡፡
ምን ማለት አይደለም?
• በገንዘብ ሃብታም ለመሆን ጤና-ቢስ መንገዶችን መጠቀም ማለት አይደለም!
• ከልክ በላይ ሃብታም መሆን ማለት አይደለም! (ቢሆን ጥሩ የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ)
• ካለአግባብ የተለያዩ ቁሳቁሶችን መሰብሰብና ታዋቂ ለመሆን መጣጣር ማለት አይደለም!
ባለን የገንዘብ አቅምና ደረጃ ባለመረበሽ መረጋጋትና ለበለጠ መስራት የገንዘብ ነጻነጽ መነሻው ነው፡፡
በዚህ ርእስ ላይ የተዘጋጀላችሁን ስልጠና ላስታውሳችሁ፡፡

የዶሮዋ የመንጫጫት አባዜ
“ኤሊ ማንም ሳያውቅ በሺዎች የሚቆጠሩ እንቁላሎችን ትጥላለች፣ ነገር ግን ዶሮ አንድ እንቁላል ስትጥል ለሃገሩ በሙሉ ይነገራል” - Malay proverbs
• አንድን ነገር ከመስራታችሁ በፊት ለመስራት ያሰባችሁትን ነገር ለብዙ ሰዎች የምታወሩ ከሆነ፣
• አንድን ነገር ከሰራችሁ በኋላ እናንተ መስራታችሁን ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁላችሁ የምትጣጣሩ ከሆነ፣
• ሰዎች የሰሩትን ስራ እንደራሳችሁ አድርጋችሁ የምታቀርቡ ከሆነ፣
• እናንት ብዙ እንደምትሰሩና ሌላው ሰው ግን ምንም እንደማይሰራ ለማሳየት የምትሞክሩ ከሆነ፣
• የሌሎች የስራ ውጤት ጊዜውን ጠብቆ ብቅ ሲል ውስጣችሁ ደስ የማይለው ከሆነና “ባላየ” እና “ባልሰማ” ለማለፍ የምትሞክሩ ከሆነ፣
• በማሕበራዊ ሚዲያ የምትለቁት ነገር ብዙና “አንጸባራቂ” በአካል የሚታየው ሁኔታ ግን ከዚያ ጋር የማይመጥንና እጅግ አናሳ ከሆነ፣
የዶሮዋ ትንሽ ሰርቶ ወይም ሳይሰሩ ብዙ የመንጫጫት አባዜ እንደተጠናወታችሁ ጠቋሚ ነው፡፡
በዝምታ እናቅድ!
በዝምታ ዝግጅታችንን እንጨርስ!
በዝምታ እንጀምር!
በመጨረሻም ስራችን ከዚያም አንደበታችን ይናገር!
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
“ኤሊ ማንም ሳያውቅ በሺዎች የሚቆጠሩ እንቁላሎችን ትጥላለች፣ ነገር ግን ዶሮ አንድ እንቁላል ስትጥል ለሃገሩ በሙሉ ይነገራል” - Malay proverbs
• አንድን ነገር ከመስራታችሁ በፊት ለመስራት ያሰባችሁትን ነገር ለብዙ ሰዎች የምታወሩ ከሆነ፣
• አንድን ነገር ከሰራችሁ በኋላ እናንተ መስራታችሁን ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁላችሁ የምትጣጣሩ ከሆነ፣
• ሰዎች የሰሩትን ስራ እንደራሳችሁ አድርጋችሁ የምታቀርቡ ከሆነ፣
• እናንት ብዙ እንደምትሰሩና ሌላው ሰው ግን ምንም እንደማይሰራ ለማሳየት የምትሞክሩ ከሆነ፣
• የሌሎች የስራ ውጤት ጊዜውን ጠብቆ ብቅ ሲል ውስጣችሁ ደስ የማይለው ከሆነና “ባላየ” እና “ባልሰማ” ለማለፍ የምትሞክሩ ከሆነ፣
• በማሕበራዊ ሚዲያ የምትለቁት ነገር ብዙና “አንጸባራቂ” በአካል የሚታየው ሁኔታ ግን ከዚያ ጋር የማይመጥንና እጅግ አናሳ ከሆነ፣
የዶሮዋ ትንሽ ሰርቶ ወይም ሳይሰሩ ብዙ የመንጫጫት አባዜ እንደተጠናወታችሁ ጠቋሚ ነው፡፡
በዝምታ እናቅድ!
በዝምታ ዝግጅታችንን እንጨርስ!
በዝምታ እንጀምር!
በመጨረሻም ስራችን ከዚያም አንደበታችን ይናገር!
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
በገንዘብ ለማደግ ጊዜው አላለፈም!
አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲያስቡ ገና፣ በዙሪያቸውና በተለይም በማሕበራዊ ገጾች ላይ ከልክ በላይ ገንዘብ እንዳገኙ የሚናገሩ ሰዎችን በመስማት ብቻ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይጫጫናቸዋል፡፡
እንደዚህ አይነቱ ስሜት ካለንበት ተነስተን ወደ አሰብንበት ደረጃ ለመድረስ መጀመር ስለሚገባን ትክክለኛ ጉዞ ማቀድም አይፈቅድልንም፡፡ ይህ የሚሆነው፣ ሁሉም ነገር ከአቅም በላይ እንደሆነና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ርቀው እንደሄዱ ከማሰብ ከሚመጣ ጫና የተነሳ ነው፡፡
አንድን ነገር ላስታውሳችሁ - ትክክለኛ ሕልም እስካላችሁ ድረስ በፍጹም ወደ ኋላ አልቀራችሁም፡፡
ሁኔታው ግን “ቅጽበታዊ” ሳይሆን “ሂደታዊ” መሆኑን ባለመዘንጋት በትእግስት ተንቀሳቀሱ፡፡
በገንዘብ ስለማደግ ስናስብ ለመኖር የፈለግነውን የኑሮ አይነት ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ካወጣን በኋላ ያንን ሕልም ለማሳካት መንቀሳቀስን እንደሚጠይቅ ማወቅ አለብን፡፡ የግል ሕልማችንን ከማንም ሰው ሕልም ጋር ማነጻጸር አሉታዊ እና አድካሚ ኃይል ነው፡፡
በዚህ ርእስ ዙሪያ ተገቢውን ግንዛቤ ለማዳበር የሚረዳችሁ ስልጠና መዘጋጀቱን አስታውሱ፡፡
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲያስቡ ገና፣ በዙሪያቸውና በተለይም በማሕበራዊ ገጾች ላይ ከልክ በላይ ገንዘብ እንዳገኙ የሚናገሩ ሰዎችን በመስማት ብቻ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይጫጫናቸዋል፡፡
እንደዚህ አይነቱ ስሜት ካለንበት ተነስተን ወደ አሰብንበት ደረጃ ለመድረስ መጀመር ስለሚገባን ትክክለኛ ጉዞ ማቀድም አይፈቅድልንም፡፡ ይህ የሚሆነው፣ ሁሉም ነገር ከአቅም በላይ እንደሆነና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ርቀው እንደሄዱ ከማሰብ ከሚመጣ ጫና የተነሳ ነው፡፡
አንድን ነገር ላስታውሳችሁ - ትክክለኛ ሕልም እስካላችሁ ድረስ በፍጹም ወደ ኋላ አልቀራችሁም፡፡
ሁኔታው ግን “ቅጽበታዊ” ሳይሆን “ሂደታዊ” መሆኑን ባለመዘንጋት በትእግስት ተንቀሳቀሱ፡፡
በገንዘብ ስለማደግ ስናስብ ለመኖር የፈለግነውን የኑሮ አይነት ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ካወጣን በኋላ ያንን ሕልም ለማሳካት መንቀሳቀስን እንደሚጠይቅ ማወቅ አለብን፡፡ የግል ሕልማችንን ከማንም ሰው ሕልም ጋር ማነጻጸር አሉታዊ እና አድካሚ ኃይል ነው፡፡
በዚህ ርእስ ዙሪያ ተገቢውን ግንዛቤ ለማዳበር የሚረዳችሁ ስልጠና መዘጋጀቱን አስታውሱ፡፡
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
ብዙዎች ከአሁኑ በመመዝገብ ላይ ናቸው!
መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል!
@DrEyobmamo
መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል!
@DrEyobmamo
ብንስማማስ ???!!!
እንዲህ የሚል ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ የአይሁዳውያን ተረት አለ፡-
አንዲት በጣም የተራበች ድመት ከአንድ ሱቅ ስጋ ሰረቀች፡፡ ያንን ሌብነቷን የተመለከተ አንድ ውሻ ነበረና እኩል ካላካፈልሽኝ አጋልጥሻለሁ አላት፡፡ ድመቷ መካፈል ስላልፈለገች መጣላት ጀመሩ፡፡
ሁለቱ በነበራቸው ጸብ ማንም ማሸነፍ ስላልቻለና ጸቡ ማቆሚያ ስላጣ የስጋው ሽታ ስቧት የመጣች በአካባቢው የነበረችን አንዲት ቀበሮ ጠሩና እንድትዳናኛቸው ጠየቋት፡፡
ቀበሮዋ፣ “ከምትጣሉ ስጋውን እኩል ተካፈሉ” የሚልን ቀላል ምክር ለገሰቻቸው፡፡ በምክሩ ሁለቱም በመስማማታቸው ድመት ስጋውን ለሁለት ቆርጣ ለውሻ አካፈለች፡፡
ሆኖም ውሻው፣ የተሰጠው ድርሻ አናሳ እንደሆነ በማሰብ ጸቡን አላበርድ አለ፡፡ በዚያን ጊዜ ቀበሮ የስጋውን መጠን በማስተካከል ሰበብ ከድመት ድርሻ ላይ ደህና አድርጎ በመቦጨቅ ዋጥ በማድረግ ውሻን አስደሰተና ለማስተካከል ሞከረ፡፡
አሁን ደግሞ ድመት የእሷ በመቀነሱ ምክንያት፣ “የውሻ ድርሻ በዝቷል” በማለት ጸቡን አላበርድ አለች፡፡ አሁንም ቀበሮ ድመትን ለማስደሰት በሚል ሰበብ ከውሻው ድርሻ ላይ ጠቀም ያለ መጠን ቦጨቅ በማድረግ ዋጥ አደረገ፡፡
አሁን ደግሞ ውሻ እንደገና የእሱ ማነሱን ሲያይ የድመት በዝቷል፣ ከዚያም ቀበሮ ድርጊቱን ሲደጋግም ድመት ደግሞ የውሻ በዝቷል ሲባባሉ፣ ቀበሮ ከዚህም ከዚያም ሲቀናንስ ስጋውን ጨረሰውና ድመትና ውሻ ምንም ሳይደርሳቸው ባዶ ቀሩ ይባላል፡፡
ተጣልተን ሁሉን ከምናጣ ተስማምተን ግማሽ ማግኘቱና አብሮ መኖሩ አይሻለንም?
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
እንዲህ የሚል ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ የአይሁዳውያን ተረት አለ፡-
አንዲት በጣም የተራበች ድመት ከአንድ ሱቅ ስጋ ሰረቀች፡፡ ያንን ሌብነቷን የተመለከተ አንድ ውሻ ነበረና እኩል ካላካፈልሽኝ አጋልጥሻለሁ አላት፡፡ ድመቷ መካፈል ስላልፈለገች መጣላት ጀመሩ፡፡
ሁለቱ በነበራቸው ጸብ ማንም ማሸነፍ ስላልቻለና ጸቡ ማቆሚያ ስላጣ የስጋው ሽታ ስቧት የመጣች በአካባቢው የነበረችን አንዲት ቀበሮ ጠሩና እንድትዳናኛቸው ጠየቋት፡፡
ቀበሮዋ፣ “ከምትጣሉ ስጋውን እኩል ተካፈሉ” የሚልን ቀላል ምክር ለገሰቻቸው፡፡ በምክሩ ሁለቱም በመስማማታቸው ድመት ስጋውን ለሁለት ቆርጣ ለውሻ አካፈለች፡፡
ሆኖም ውሻው፣ የተሰጠው ድርሻ አናሳ እንደሆነ በማሰብ ጸቡን አላበርድ አለ፡፡ በዚያን ጊዜ ቀበሮ የስጋውን መጠን በማስተካከል ሰበብ ከድመት ድርሻ ላይ ደህና አድርጎ በመቦጨቅ ዋጥ በማድረግ ውሻን አስደሰተና ለማስተካከል ሞከረ፡፡
አሁን ደግሞ ድመት የእሷ በመቀነሱ ምክንያት፣ “የውሻ ድርሻ በዝቷል” በማለት ጸቡን አላበርድ አለች፡፡ አሁንም ቀበሮ ድመትን ለማስደሰት በሚል ሰበብ ከውሻው ድርሻ ላይ ጠቀም ያለ መጠን ቦጨቅ በማድረግ ዋጥ አደረገ፡፡
አሁን ደግሞ ውሻ እንደገና የእሱ ማነሱን ሲያይ የድመት በዝቷል፣ ከዚያም ቀበሮ ድርጊቱን ሲደጋግም ድመት ደግሞ የውሻ በዝቷል ሲባባሉ፣ ቀበሮ ከዚህም ከዚያም ሲቀናንስ ስጋውን ጨረሰውና ድመትና ውሻ ምንም ሳይደርሳቸው ባዶ ቀሩ ይባላል፡፡
ተጣልተን ሁሉን ከምናጣ ተስማምተን ግማሽ ማግኘቱና አብሮ መኖሩ አይሻለንም?
https://www.tg-me.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ሶሰቱ የሃብት ምንጮች!
በገንዘብ በማደግ ራሳችንን ከመቻል አልፈን ለቤተሰባችንና ለወዳጆቻችን ለመትረፍ ከፈለግን ያለን የሃብት ምንጭ በገንዘብ ብቻ እንደማይወሰን መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡
እንደ ጤንነት እና የመሳሰሉን ወሳኝ ሁኔታዎች እንደ ሃብት የመቁጠራችን እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ . . .
1. ከገንዘብ የሚነሳ ሃብት አለ፣
2. ከጊዜ የሚነሳ ሃብት አለ፣
3. ከእውቀት የሚነሳ ሃብት አለ፡፡
የእነዚህን የሶስቱን የሃብት መነሻዎች መስተጋብር (interaction) በሚገባ ማወቅና ከየትኛው መነሳት እንዳለብን መገንዘብ በጣም መሰረታዊ ነው፡፡
አንዱ ካለን ሌላኛውን እንዴት መውለድ እንደምንችልና ያንን የወለድነውን ደግሞ መልሰን የመጀመሪያውን ለማባዛት እንዴት መስራት እንዳለብን የማወቅን ጥበብ ይጠይቃል፡፡
በዚህና በመሳሰሉት ተግባራዊ ክህሎቶች ለመሰልጠንና ለማደግ የተዘጋጀላችሁ ስልጠና አለና ከመመዝገብ ችላ አትበሉ፡፡