Telegram Web Link
የሙዳችሁ ጉዳይ
የሙዳችሁ ጉዳይ

በሕይወታችሁ ለስኬታችሁ ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የየእለት “ሙዳችሁ” ጉዳይ ነው፡፡

የየእለት “ሙዳችን” በመጠኑ ሊለዋወጥ የመቻሉ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ቶሎ ቶሎ የሚለዋወጥ ከሆነ ሁለት ነገሮችን ይነካብናል፡-

1. ለአንድ ተግባር ያለንን መነሳሳት

2. ከሰዎች ጋር የሚኖረንን ግንኙነት

በሕይወታችን የምንሰራቸው ነገሮች “በሙዳችሁ” ምክንያት ካልተሳኩ፡፡ እንዲሁም ያለን ማሕበራዊ ግንኙነት በዚሁ “የሙድ” መዛባት ምክንያት ከተበላሸ - ምን ቀረን?

የሙዳችሁ ሁኔታ በየእቱ ሊለዋወጥ የመቻሉ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ልኩን ጠብቆ እንዲቆይ ከፈለጋችሁ . . .

1. ከሰዎች የምትጠብቁትን (Expect የምታደርጉትን) ነገር ሚዛናዊ አደርጉ፡፡

ሰዎች ሁል ጊዜ ሰዎች ናቸው፡፡ እኛ የምንጠባበቀውን ቀርቶ ቃል የገቡትን ነገር እንኳን ላይፈጽሙት ይችላሉ፡፡ ልባችንን ሙሉ ለሙሉ ከሰዎቹ በምንጠባበቀው ነገር ላይ ከጣልን የስሜት ቀውስ የማይቀር ነው፡፡ ያለፈው ታሪካችሁን መለስ ብላች ካስታወሳችሁ፣ የብዙ የስሜት ቀውስና የተስፋ መቁረጥ መንስኤዎች ከሰዎች የምንጠብቀውን ነገር ያለማግኘታችን ጉዳይ እንደሆነ እንደርስበታለን፡፡

2. መለወጥ ወይም መቆጣጠር ከማትችሉት ነገር ላይ ትኩረታችሁን አንሱ፡፡

አንድ ነገር እንደሚሆን ካሰባችሁ ወይም ከሆነባችሁ የመጀመሪያው ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ያንን ነገር መቆጣጠር ወይም መለወጥ የመቻላችሁ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም ብታደርጉ የማትለውጡት ነገር ከሆነ፣ አንደኛችሁን ትኩረታችሁን ከዚያ ነገር ላይ በማንሳት ወደ አስፈላጊው ነገር ላይ እንድታደርጉ ትመከራላቸሁ፡፡ መለወጥ የማትችሉትን ነገር ሲያብሰለስሉ መዋል መለወጥ በምትችሉት ነገር ላይ እዳትሰሩ ጉልበታችሁን ይወስደዋል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የገንዘብ አያያዛችን ጉዳይ!

በሚከተሉት አምስት የገንዘብ ዘርፎች መብሰል፣ ማደግና ሚዛናዊ መሆን የገንዘብ ነጻነትን ይሰጣል፡፡

1. ገንዘብን የማግኘት ክህሎት - የገንዘብ ገቢያችሁን ይጨምረዋል!

2. ገንዘብን ለጤናማ ዓላማ የመጠቀም ጥበብ - ገንዘብን በበጀት የመጠቀም ብልሃታችሁን ያሳድገዋል!

3. ገንዘብን ኢንቨስት በማድረግ የማባዛት ብቃት - በኢኮኖሚ ልቆ የመገኘትን መንገድ ይጠርግላችኋል፡፡

4. ገንዘብን የማጠራቀም ዲሲፕሊን - ለድንገተኛ ነገር ዝግጁ ያደርጋችኋል!

5. ገንዘብን የመስጠት ፈቃደኝነት - የሰብአዊነትና የእርካታ ስሜትን ይሰጣችኋል!

በእነዚህ ወሳኝ የገንዘብ ሂደቶች በበሰልንና ሚዛናዊ በሆንን ቁጥር የገንዘብ ነጻነትንና እድገትን እናገኛለን፡፡

ለዚህና ለመሰል ከገንዘብ ጋር ለሚገናኙ እውቀቶች የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ቻይናዊው የታክሲ ሹፌር!

"ትኩረታችሁን ቢዝነሳችሁ ላይ አድርጉ!"

አንድ ሰው ይህንን አጭር ታሪክ ሲናገር ሰማሁት፡-

አንዲት ራቁቷን የሆነች እንግሊዛዊት ሴት አንድ ቻይናዊ የሚያሽከረክረውን ታክሲ አስቁማ ገባች፡፡ ቻይናዊው የታክሲ ሹፌር ደጋግሞ ከላይ እስከታች ሲያያት ጊዜ እንግሊዛዊቷ አስተያየቱ ስላሳሰባት፣ “ምነው! ራቁቷን የሆነች ሴት አይተህ አታውቅም እንዴ?” አለችው፡፡

ቻይናዊው በመመለስ፣ “ከላይ እስከታች ያየሁሽ ራቁትሽን ስለሆነሽ ሳይሆን፣ ከላይ እሰከታች ደጋግሜ ያየሁሽ የምትከፍይኝን ገንዘብ የያዝሽበትን ስፍራ ስላጣሁት ነው፡፡”

ከታሪኩ የምንማረው ትምህርት፣ እንደ ቻይናዊ የታክሲ ሹፌር ሁኑ፡፡ ትኩረታችሁን ከሚስበውና ከሚበታትነው ነገር ላይ አንሱና ትኩረታችሁን ዋናው ተግባራችሁና ቢዝነሳችሁ ላይ አድርጉ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
እቅድ አላችሁ?

አሁን ያላችሁበን የገንዘብ አቅም ወደሚቀጥለው ደረጃ ለማሳደግ ግልጽ የሆነ እቅድ አላችሁ?

የምታስገቡትን ገንዘብ በምን ላይ እንደምታውሉት በሚገባ የምታውቁበት የወጪ በጀት እቅድ አላችሁ?

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርሳችሁ የኢንቨስትመንት እቅድስ አላችሁ?

በእነዚህና በመሰል ከገንዘብ ጋር በተያያዙ ርእሶች ላይ ሰፊ ግንዛቤ የሚሰጥ ስልጠና ተዘጋጅቶ በርካቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡

የስልጠው ርእስ፡-
“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
የማይሞላው ቀዳዳ
የማይሞላው ቀዳዳ

በሰጣችሁት ቁጥር የማይሞላ፣ የማይጠግብና ተጨማሪ የሚጠይቅ አመለካከት ያለው ሰው አጋሟችሁ ከሆነ ብቻችሁ አይደላችሁም፡፡

አንዳንድ በሕይወታችን የሚገኙ ሰዎች ፈቅደንና ወደን ማፍሰስ የምንችለውን ነገር ሁሉ በእነሱ ላይ እናፈሳለን፡፡ ቢደክመንም፣ ቢሰለቸንም አምነንበት እንደሸክማችንና እንደግዴታችን ስለተቀበልናቸው የፍቅራችን ጥልቀትና የደስታችን ብዛት ከሸክሙ ክብደት ስለሚልቅ እንገፋበታለን፡፡

አንዳንድ ጊዜ ግን በፍጹም ግዳጅና ሃላፊነት የሌለብንን ሰዎች የማይጠግብ ፍላጎት በመመገብ እንዝላለን፡፡ እንዳንገፋበት ዝለናል፣ እንዳናቆመው የውሸት ሃላፊነት ስሜት፣ ይሉኝታና “ሰዎችን እንዳላስቀይም” የሚሉ ትብታቦች ይይዙናል፡፡

ከሚከተሉት አይነት በሰጣችኋቸው ቁጥር የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማችሁ ጨምራችሁ እንደትሰጧቸው ከሚጫኗችሁ ሰዎች ዛሬ ፈታ እንድትሉ ላደፋፍራችሁ፡፡ (በቅድሚያ ግን ምናልባት እኛው ራሳችን ላይ እነዚህ ባህሪዎች እንዳሉና እንደሌሉ መመልከታችንን አንዘንጋ)

1. ለማስደሰት በጣራችሁ ቁጥር ፈጽሞ የማይደሰቱና “ተጎድቻለሁ” የሚያበዙ፣

2. ገንዘብና ቁሳቁስ በሰጣችኋቸው ቁጥር ልክ ግዴታ እንዳለባችሁ ሳያመሰግኑ ሌላ የሚፈልጉ

3. ይቅርታ በጠየቃችኋቸው ቁጥር ሌላ ክስ፣ ፍርድና ኩነኔ ይዘው የሚመጡ፣

4. ትኩረት በሰጣችኋቸው ቁጥር ሁል ጊዜ በቂ ጊዜ እንዳልተሰጣቸው የሚነጫነጩ፡፡

የማይረካ ፍላጎት (Appetite) ያለበት ሰው በሰጠነው ቁጥር ፍላጎቱ እየጨመረ ስለሚሄድ ከዚህ ቀውስ የሚድነው ሲከለከል ብቻ ነው፡፡ ምናልባት ለእንደዚህና ለመሰል አይነት ሰዎች መድሃኒቱ፣ ለእነሱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት ሳንለቅ አምጡ አምጡ የሚለውንና በፍጹም የማይረካውን ፍላጎታቸውን አንደኛውን ከልክሎ በማስራብ እንዲሞት ማድረግና ወደጤናማው የፍላጎት ልክ እንዲመለሱ ማገዝ ሳይሆን አይቀርም፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ራስን በማሳደግ ውስጥ ያለ ስኬት!

ራስን ከማሳደግ የሚመጣ ስኬት ዘላቂ ያለው ስኬት ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ማንኛውም ከእኛ ጋር የሚነካከ ሁኔታ በእኛ ማደግና አለማደግ የተገደበ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ እውነታ ከገንዘብ ማግኘት እና አያያዝ ጋር በቀጥታ ይገናኛል፡፡

እኛ ሳንሻሻልና ሳናድግ አዳዲስ ነገሮች በእጃችን የመግባታቸው ሁኔታ አጠራጣሪ ነው፡፡ እነዚህ አዳዲስ ነገሮች ገንዘብን በማግኘትና ያገኘነውን ገንዘብ በትክክለኛው መንገድ በመጠቀም ሂደት ውስጥ ትልቅ ስፍራ አላቸው፡፡

እኛ ካልተሻሻልንና ካላደግን በእድልና በአጋጣሚ ያገኘነው ነገር ሁሉ ካላደገው ማንነታችን ጋር የመቆየቱ ሁኔታ አጠራጣሪ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በእጃቸው የገባውን ገንዘብ በሚገባ ለመያዝና ለማስተዳደር የያሚበቃን ብስለት ቀድሞውኑ ካለማዳበር ነው፡፡

በመሻሻልና በማደግ ውስጥ ቀድሞ ያልነበረውን ነገር ለማምጣት የሚያስችል ብቃት አለ፡፡ በመሻሻልና በማደግ ውስጥ እጃችን የገባውን ነገር በትክክለኛው መንገድ የመያዝ ብስለትም አለ፡፡

ይህንን የስኬት ልምምድ ለማዳበር የተዘጋጀ ስልጠና አለ፡፡

የስልጠው ርእስ፡-
“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
ለወጣት ተማሪዎች የተደረገ ቅናሽ!

ወጣት ተማሪዎች ለዚህ ስልጠና የተደረገላችሁን 50% ቅናሽ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ተማሪ መሆናችሁ እና የምትማሩበትን ትምህርት ቤት በመጥቀስ inbox አድርጋችሁ ጥያቄ ስታቀርቡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
እስቲ ትንሽ አንድ ጊዜ ጸጥ በሉና . . .

• ማሟላት የምትመኟቸውን ለሕይወታችሁ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች . . .

• ማሻሻል የምትፈልጉትን የኑሮ ሁኔታ . . .

• መደገፍ የምትፈልጓቸውን ቤተሰቦች . . .

• መማርና መሰልጠን የምትፈልጉትን ነገር . . .

• መጀመር የምትፈልጉትን አዲስ ሕይወትና የአኗኗር ደረጃ . . .

• መቀየር የምትፈልጉትን ቤት ወይም ሰፈር . . .

እና የመሳሰሉትን ሁኔታዎቻችሁን አስቧቸው፡፡

እነዚህና መሰል ነገሮች በአብዛኛው ካላችሁ የገንዘብ አቅም ጋር የተያያዙ እንደሆነ ታውቃላችሁ?

ለዚህ ነው ካለን መንፈሳዊ ሕይወትና ካሉን እሴቶች ቀጥሎ በሚገባ ሊሰራበት የሚገባው ነገር የገንዘብ አያያዛችን ሁኔታ የሆነው፡፡

በዚህ ጉዳይ በሚገባ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠና እድል!

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
ጥያቄ፡

ሰላም ዶ/ር
በየቀኑ በነጻ ስለምታቀርብልን ትምህርትና ከዚህም በተጨማሪ በየጊዜው ስጠናዎችን ስለምታዘጋጅልን በተከታዮችህ ስም ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

ሰሞኑን ለወጣት ተማሪዎች ለስልጠናው ክፍያ ቅናሽ እንደምታደርግ ተመለከትኩኝና ሲንግል እናቶች (single mom) ለሆንነውም እንደዚያ ብደርግልን ካለብን የገንዘብ እጥረት አንጻር ይጠቅመናል ብዬ አሰብኩኝ፡፡ ምን ታስባለህ?

መልስ፡

አዎን ተማሪዎች በስራ መስክ ላይ ስለሌሉ ከስልጠናው እንዲጠቀሙ ለመደገፍ ያንን አደርጋለሁ፡፡ የሲንግል እናቶችን ሁኔታ በዚህ መልኩ ስላላየሁት ነው፡፡

ልጃችሁን ለብቻችሁ በማሳደግ የኢኮኖሚ ውጥረት ካለባችሁ ቅናሽ እንዲሰጣችሁ ከዚህ በታች ባለው ሊንክኢንቦክስ በማድረግ መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡

@DrEyobmamo
ስልጠናው ከ 10 ቀናት በኋላ ይጀምራል!

በርካቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው!

እርሶም ይመዝገቡ!

የስልጠው ርእስ፡-
“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
ከራሳችሁ ጋር!

ከተወለዳችሁ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ፣ በቀን 24 ሰዓት አብራችሁት የኖችሁትን ራሳችሁን ካላወቃችሁት፣ ካልተገነዘባችሁት፣ ካልመራችሁትና አቅጣጫ ካላስያዛችሁት፣ ሌሎች ሰዎች እነዚህን ነገሮች ያደርጉልኛል ብላችሁ አትጠብቁ፡፡

ይህንን ማንነታችሁን ከሰጣችሁ ፈጣሪ ጋር ያላችሁን ግንኙነት መስመር ካስያዛችሁ በኋላ . . .

• ከራሳችሁ ጋር አሳልፉ!

• ከራሳችሁ ጋር ተዋወቁ!

• ከራሳችሁ ጋር ተስማሙ!

• ከራሳችሁ ጋር ተወያዩ!

• ከራሳችሁ ጋር ወስኑ!

ይህንን ስታደርጉ፣ ሰዎች ስለሚያስቡት፣ ስለሚሉትና ስለሚያደርጉት የመጨነቃችሁ ሁኔታ እየቀነሰ ይሄዳል፣ ራሳችሁን ም ታሳድጋላችሁ፡፡

መልካም እንቅልፍ ይሁንላችሁ የምወዳችሁ የሃገሬ ሰዎች!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የተሻለው ውድ!

መማር ውድ እና ከባድ ከመሰለህ፣ አለመማርን ሞክረው!
መማር አሁን ውድ እና ከባድ ቢሆንም፣ ነገ ግን ሕይወትን ያቀልልናል!
አለመማር አሁን ርካሽ እና ቀላል ቢሆንም፣ ነገ ግን ብዙ እንደከፈልን እንድንኖር ያደርገናል፡፡

ጠንክሮ መስራት ውድ እና አሰልቺ ከመሰለህ፣ አለመስራትን ሞክረው!
ጠንክሮ መስራት አሁን ውድ እና አሰልቺ ቢሆንም፣ ነገ ግን ሕይወትን የሚያጓጓ ያደርገዋል፡፡
ጠንክሮ አለመስራት አሁን ዘና ቢያደርገንም፣ ነገ ግን እንደተጨናነቅን እንድንኖር ያደርገናል፡

ስፖርት መስራት ውድ እና አድካሚ ከመሰለህ፣ አለመስራትን ሞክረው!
ስፖርት መስራት አሁን ውድ እና አድካሚ ቢሆንም፣ የወደፊት ሕይወታችንን ግን ብርቱና ጠንካራ ያደርገዋል፡፡
ስፖርት አለመስራት አሁን ለሌላ ነገር ጉልበትና ጊዜ የሰጠን ቢመስለንም፣ ነገ ግን ለምንም ነገር አቅም አጥተን እንድንኖር ያደርገናል፡፡

የተሻለውን ውድ እንምረጥ!

ይህንን እውነታ በገንዘብ አቅም ከማደግ አንጻር የሚያመላክታችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ለወጣት ተማሪዎች የተደረገ ቅናሽ!

ወጣት ተማሪዎች ለዚህ ስልጠና የተደረገላችሁን 50% ቅናሽ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ተማሪ መሆናችሁ እና የምትማሩበትን ትምህርት ቤት በመጥቀስ inbox አድርጋችሁ ጥያቄ ስታቀርቡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
አይዟችሁ !!!

ወቅቱ ጥሩ ያልሆነላችሁ . . . ነገሮች ግራ የገቧችሁ . . . በሰው የተጎዳችሁ . . . ያዘናችሁ . . . ተስፋ የቆረጣችሁ . . . ነገሮች የጨለሙባችሁ . . . ያልተጠበቀ ነገር የደረሰባችሁ . . . የቤተሰብን ሃላፊነት ለብቻችሁ የተሸከማችሁ . . . የትም መሄጃ እንደሌላችሁ ስላወቁ ሰዎች የጨከኑባችሁ . . .

በቃ አይዟችሁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ከቅዠት አለም ውጡ!

“እውታውን አሁኑኑ በመቀበል የሚመጣ ጊዜያዊ ህመም፣ የሌለውን እንዳለ አድርጎ የማሰብ ቅዠት ከሚያመጣው የረጅም ጊዜ ሕመም የተሻለ ነው” (Daily Thoughts)

የሆነውን፣ እየሆነ ያለውንና የማይቀረውን እውነታ አስመልክቶ ያለን ብቸኛ ምርጫ መቀበል ይባላል! አንድ እውነታ መቀበል ማለት ለሁኔታዎች ተሸንፎ አንገትን ማቀርቀር ማለት አይደለም፡፡

በዚያ ምትክ፣ ከእውነታው የተነሳ የሚመጣውን ጊዜያዊ ህመም በመጋፈጥ እንዲወጣለት መፍቀድ ማለት ነው፡፡

ከዚህ ውጪ ያለን ምርጫ፣ በክህደትና በቅዠት አለም ውስጥ በመግባት የማይመጣን ተስፋ መጠበቅ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
በርካታ ሰዎች በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡

ስልጠናው እንዳያመልጣችሁ!

የምዝባ መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram user name መልእክት በመላክ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል፡፡

@DrEyobmamo
በገንዘብ አቅም እያደጉ መሄድ!

በገንዘብ አቅም እያደጉ መሄድ የቀስ በቀስ ሂደት እንጂ ቅጽበታዊ አይደለም፡፡ ስለሆነም፣ ትክክለኛውን መንገድ መከተል አስፈላጊ ነው፡፡

መጠናቸው ይለያይ እንጂ ሁላችንም በእጃችን ላይ ሶስት የሃብት ምንጮች አሉን፡፡ ከእነዚህ ከሶስት በወቅቱ የትኛው እጃችን ላይ እንዳለ በመለየት ከዚያ መነሳት እንችላለን፡፡

ሁላችንም ገንዘብ ለማግኘት ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ሶስት የስራ አቅጣጫዎች አሉ፡፡ እነዚህን ሶስቱንም አቅጣጫዎች መቼ እና እንዴት በመጠቀም አቅማችንን እንደምንገነባ መገንዘብ እንችላን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፣ እጃችን ላይ ያለውን ገንዘብ . . .

1. በሚገባ መጠቀም

2. በተገቢው ሁኔታ መቆጠብ

3. ኢንቨስት በማድረግ ማባዛት ከእኛ ይጠበቅብናል፡፡

በእነዚህና በሌሎች በገንዘብ አቅም በማደግ ሃሳቦች ዙሪያ ግንዛቤያችሁን የሚያሰፋ ስልጠና ተዘጋጅቷል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
በፍጹም አታቁሙ!

• ካለማቋረጥ የምትታገሉትን ነገር ማሸነፋችሁ አይቀርም፡፡ የምትሸነፉት መታገል ስታቆሙ ብቻ ነው፡፡

• ካለማቋረጥ የምትሞክሩት ነገር መሳካቱ አይቀርም፡፡ የማይሳካው መሞከር ስታቆሙ ብቻ ነው፡፡

• ካለማቋረጥ የምትከተሉት ነገር ላይ መድረሳችሁ አይቀርም፡፡ የማትደርሱት መከተል ስታቆሙ ብቻ ነው፡፡

• ካለማቋረጥ የምታነቡትን ነገር መገንዘባችሁ አይቀርም፡፡ የማትገነዘቡት ማንበብ ስታቆሙ ብቻ ነው፡፡

• ካለማቋረጥ የምትገነቡት ነገር ተገንብቶ ማለቁ አይቀርም፡፡ ቆሞ የሚቀረው ስታቆሙ ብቻ ነው፡፡

• ካለማቋረጥ የምትደጋግሙት መልካም ነገር ልማድ መሆኑ አይቀርም፡፡ ልማድ ሳይሆን የሚቀረው ስታቆሙ ብቻ ነው፡፡

በርቱ! በፍጹም አታቁሙ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
2025/07/01 03:41:34
Back to Top
HTML Embed Code: