ከአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር (“Trauma Bonding”)

ካለማቋረጥ ከሚጎዳን ሰው ጋር ተጣብቀን የምንቆየው ለምንድን ነው? መዘዙስ ምንድ ነው?
ምክንያቱ

• ከተለየሁ አንድ ነገር ይደርስብኛል ብሎ የሚል ፍርሃት

• ከተለየሁ አንድ ነገር አጣለሁ የሚል ስጋት

• እንደ ትዳር ያለ በቀላሉ ሊላቀቁት የማይችሉት የኪዳን ትስስር

• ጥቃት አድራጊዎቹን መውደድ፣ ማፍቀር ወይም ከእነሱ ተለይቶ መኖር እንደማይችሉ ማሰብ

መዘዙ

• ውብ የሆነን ጊዜ ማባከን

• የጤና ቀውስ

• የወደፊት ጸጸት

• ሊረዱን ከሚችሉ ሰዎች እየተለያዩ መሄድ

ከዚህ በታች የቀረበላችሁን የቲክቶክ ሊንክ በመጫንና በመመልከት ራሳችሁን አንቁ!

ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ለመረጃው

@DrEyobmamo

ቴሌግራም inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡


https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ከአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር (“Trauma Bonding”) የመላቀቅ እርምጃዎች?

1. ችግሩ እንዳብን አምኖ መቀበል

2. የግል ቀይ መስመርን ማበጀት መማር

3. ከሰዎቹ ውጪ መኖር እንደምንችል ራስን መሳመን

4. የግል ሕይወት እድገት ላይ ማተኮር

5. የጤንነት አደጋ ላይ ከደረሰ መለየር

6. ለሰወቹ ስሜት ምንም ሃላፊነትን እንደሌለን መገንዘብ

7. ለስላሳ ግን ጠንካራ መሆን

8. ስሜታዊ በመሆን አቅርቦት አለመስጠት

9. እርዳታን መፈለግ

ከዚህ በታች የቀረበላችሁን የቲክቶክ ሊንክ በመጫንና በመመልከት ራሳችሁን አንቁ!


ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ለመረጃው

@DrEyobmamo

ቴሌግራም inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡


https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
እባካችሁ!

• የምታወሩት መልካም ነገር ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ ክፉ ነገር ከማውራት ዝም በሉ!

• የመለገስ ፍላጎቱ ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ የሰውን አትውሰዱ!

• የምትገነቡት ነገር ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ ሰዎች የገነቡትን አታፍርሱ!

• የምትጀምሩት አዲስ ነገር ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ ሰዎች የጀመሩትን ነገር አታደናቅፉ!

• የምታደንቁት ሰው ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ ሰዎችን አታንቋሹ!

• ከሰዎች ጋር ለአንድ ዓላማ የመተባበር ፍላጎቱ ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ የሰዎችን አንድነት አታውኩ!

ፈጣሪ የሰላም ሰው ያድርገን!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
አእምሮህን አሰልጥን!
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
አዎንታዊነትና ስኬት!

ብዙ ሰዎች ለረጅም ጊዜ ይዘው የሚቀዩትንና በዚያም ምክንያት ከስኬታማነት የሚገቱበትን አንድ የተዛባ አመለካከት ዛሬ አብረን ለማረም እንሞክር፡፡ ስኬታማ ሰዎች ስኬታማ ስለሆኑ አይደለም ደስተኛና አዎንታዊ የሆኑት፡፡ ከዚያ በተቃራኒው፣ ስኬታማ ሰዎች ደስተኛና አዎንታዊ ስለሆኑ ነው ስኬታማ የሆኑት፡፡ ደስተኛና አዎንታዊ ለመሆን ስኬታማ የሆናችሁ እስኪመስላችሁ ድረስ አትጠብቁ፡፡ አሁኑኑ የደስተኛነትንና የአዎንታዊነትን ዝንባሌ ስትይዙ ከዚያ ስኬት ይከተላል፡፡

መልካም እንቅልፍ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ስሜታዊውና ምክንያታዊው
ስሜታዊውና ምክንያታዊው

ስሜታዊነት ማለት ለአንድ ገጠመኝ ወይም ክስተት የሚሰጥ ድንገተኛ ምላሽ ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ምላሽ ውጤት ምን እንደሆነ አይታወቅም፡፡

በተቃራኒው ምክንያታዊነት ማለት ለአንድ ገጠመኝ ወይም ክስተት በቂ ጊዜ ወስዶ፣ ውጤቱን አውጥቶና አውርዶ ውጤቱን ከጅማሬ አይቶ ምላሽ መስጠት ማለት ነው፡፡

አንድን ነገር ለማድረግ ስታስብ መነሻህ ስሜታዊነት ይሁን ወይስ አእምሮህ ያሰበበትና አጥጋቢ ምክንያት ያለው ተግባር ለይተህ የማወቅን ልምምድ አዳብር፡፡ ይህንን መለማመድ ዘወትር በስሜት እየተነዳህ ውሳኔና እርምጃ ውስጥ ከመግባትና ውጤቱ አፍራሽ ከሆነ ሁኔታ ይጠብቅሃል፡፡

ለምሳሌ፣ ከዚህ በፊት ለነበረህ ገጠመኝ የሰጠኸውን ምላሽ አስብና ያንን ምላሽ የሰጠህበትን መነሻ አሳብ አጢነው፡፡ “ያነሳሳኝ ስሜት ነው ወይስ አእምሮዬን ተጠቅሜ በቂ ምክንያት አግኝቼ ነው?” የሚል የማስታወሻ ጽሑፎችን በመጻፍ ልዩነቱን ማየት ትችላለህ፡፡ እንዲህ አይነት ልምምዶችን በመደጋገም በማድረግ ስሜታዊ ልማዶችህን ቀስ በቀስ ልትቀርፋቸው ትችላለህ፡፡ አንዲት ደቂቃ በመታገስ የእለቱን የጋለ ስሜት ማሳለፍ ሲችሉ የመጣላቸውን የስሜት ንዝረት በማስተናገድ የሌላውንና የራሳቸውን ታሪክ ያበላሹ ሰዎች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው፡፡

በየእለት የሰው ለሰው ግንኙነት መካከል በሚነሱ ነገሮች ሁሉ የሚፈነዱና ቁጣ ቁጣ የሚላቸው ሰዎች፣ በትዳርና በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ በስሜት በተናገሩት ንግግር ከተቆሳሰሉ በኋላ ለመወያየት የሚሞክሩ ሰዎች፣ በማሕበራዊውና በሃገር ደረጃ አንድን ነገር ገና ከመስማታቸው ስለሁኔታው በሚገባ ሳያጠኑና የምክንያታዊነት ሂደት ሳይከተሉ ለጥፋት የሚነሳሱ ሰዎች ምክንያታዊ ሳይሆኑ ስሜታዊ ሰዎች ናቸው፡፡

ምክንያታዊነት የበሳሎች መንገድ ነው፡፡ ምክንያታዊነት የአዋቂዎች ምርጫ ነው፡፡ ምክንያታዊነት ሚዛናዊ በራስ የመተማመን ደረጃ የደረሱና ከፍ ያሉ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡

ስሜታዊነት ጠባብነት ነው፡፡ ስሜታዊነት አርቆ ማሰብ ያለመቻል ምልክት ነው፡፡ ስሜታዊነት የተስፋ መቁረጥ ምልክት ነው፡፡ ስሜታዊነት የመሸነፍና አቅም የማጣት ምልክት ነው፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ከስሜታዊነት ወደ ምክንያታዊነት የመሸጋገርን ጉዞ እንድትጀምርና የግልህን፣ የቤተሰብህንና የሕብረተሰቡን ሕይወት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ የምትሰራ ብልህ ሰው እንድትሆን ላበረታታህ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”

ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡

በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡

ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡

ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡

አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን?

መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች …

• ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡

• ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡

• አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡

እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ?

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የስልጠና እድል!

With Dr. Eyob Mamo

ከሃገር ቤት ውጪ ለምትገኙ ሁሉ የተዘጋጀ በ Zoom የሚሰጥ የስልጠና እድል፡፡

ራእይ . . .

• የተፈጠርንነትን የሕይወት ትርጉም የምናገኝበት . . .

• ከተሰላቸንበት የሕይወት ዑደት የምንወጣበትና ወደ ዓላማችን አቅጣጫን የምንይዝበት . . .

• ለራሳችን ብቻ ከመኖር ባሻገር በሌሎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት መትረፍረፍ ውስጥ የምንገባበት . . .

. . . ብቸኛው መንገድ!

በማስወቂያ ፖስተሩ ላይ ባለው መረጃው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ! አያምልጣችሁ!


https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ይህ የስጠና ማስታወቂያ በZoom የሚሰጥ ሲሆን በተለይም ከሃገር ቤት ውጪ ለምትኖሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

በፖተሩ ላይ ባለው የቴሌግራም አድራሻ ማለትም @Helinakeb የመመዝገብ ፍላጎታችሁ ገልጻችሁ inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

በሃገር ውስጥ ላላችሁ አዲስ አበባ በአካል የሚሰጥ ስልጠና በመዘጋጀት ላይ ስለሆነ ማስታወቂያውን እስክንለቅ ታገሱን፡፡

በሃገር ውስጥ የምትኖሩና የሰዓቱን ልዩነት አጣጥማችሁ የ Zoom ስልጠናውን መሳተፍ ከፈለጋችሁ በ @Helinakeb ፍላጎታችሁ ገልጻችሁ inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
ምን አደርግ ነበር?

አንድ ጊዜ ቆም በሉና ሃሳባችሁን ከሶስት እስክ አምስት አመት መለስ በማድረግ ራሳችሁን ይህንን ጥያቄ ጠይቁት፡-

አሁን የማውቀውን ነገር ያን ጊዜ ባውቅ ኖሮ ወይም አሁን የገባኝ ነገር ያን ጊዜ ገብቶኝ ቢሆን ኖሮ ምን አደርግ ነበር? ምንስ እለውጥ ነበር?

በሉ ጊዜው አልረፈደም ዛሬ አስቡ፣ አቅዱ እና አድርጉት! ዛሬ ለለውጥ ተነሱ!

ምናልባት ያን ጊዜ ማድረግና መለወጥ ትችሉ የነበረው ነገር አሁ በፍጹም እድሉ እንደገና የማይመጣ ስለሆነ አልፎበታል ካላችሁ፣ ዛሬ እጃችሁ ካለው ነገር አንጻር በመነሳት ምን ማድረግና ምን መለወጥ እንደምትችሉ ማሰብ ትችላላችሁ፡፡ ቢያንሰ ቢያንስ ይህንን የሕይወት ዘይቤ መጀመርና ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ፡፡

መልካም ቅዳሜ የምወዳችሁ የሃገሬ ሰዎች!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ችግር ሲታየን!
ችግር ሲታየን!

በምንም አይነት ሕብረተሰብ ውስጥ ብንኖርም፣ በዚያ ሕብረተሰብ መካከል አንድ ችግር ወይም ክፍተት ሲታየን ለሁኔታው የምንሰጠው ምላሽ በሁለት ይከፈላል፡፡

የመጀመሪያውና ፈጽሞ የማይመከረው፣ መነጫነጭ፣ ስህተተኛውን ፈልጎ መክሰስ፣ ሰውን መውቀስ፣ አሉታዊ ወሬን ማራባትና የመሳሰሉት አይነት መንገድ ነው፡፡ ይህ ዝንባሌና ልምምድ ለሕብረተሰቡም ሆነ ለእኛ ለራሳችን እጅግ አክሳሪና ጤና-ቢስ ነው፡፡

ሁለተኛውና የሚመከረው፣ ችግሩ ለእኛ ስለታየን እንደቤት ስራችንና እንደተልእኳችን ማየት፣ በታየን ነገር ላይ አንዳንድ የመፍትሄ መንገዶችን መፈለግና የማበርከት መንገድ ነው፡፡ ይህ ዝንባሌና ልምምድ ለሕብረተሰቡም ሆነ ለእኛ ለራሳችን ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለው፡፡

1. ለችግሩ መፍትሄ በማምጣታችን ምክንያት ይህ ነው የማይባል እርካታ ይሰጠናል፡፡

በሕብረተሱ መካከል ጤናማ እና ሚዛናዊ በራስ መተማመን ያላቸው ሰዎች በየጊዘው የሚያዩትን ችግር ለመፍታት ራሳቸው የሚያቀርቡ ሰዎች ናቸው፡፡

2. ለፈታነው ችግር የገንዘብ ክፍያ እገኛለን፡፡

በዙሪያችን ብንመለከት ሰዎች የገቢ ምንጭን የሚያገኙት ለሚቱት ችግር ነው፡፡ የሰዎችን ችግር ስናቃልልላቸው ሰዎቹ ደስ ብሏቸው ገንዘብን ይከፍሉናል፡፡

3. የስነ-ልቦና ጤንነት እናገኛለን፡፡

የሚያዩት ችግር ይዘው ከሚነጫነጩ ይልቅ መፍትሄ ለማምጣሰ የሚሰሩ ሰዎች አዎንታዊ አመለካከት ስለሚዳብሩ ጤናማ ማንነት ይኖራቸዋል፡፡

እድሉ አያምልጣችሁ!

• እኛ ያለን ነገር የሌላቸው ሰዎች መብዛት - እኛ ያለንን የመስጠት ታላቅ እድል ነው!

• እኛ ያየነውን ነገር ያላዩ ሰዎች መብዛት - እኛ ያየነውን የማሳየት ታላቅ እድል ነው!

• እኛ የገባን ያልገባቸው ሰዎች መብዛት - እኛ የገባንን የማስረዳት ታላቅ እድል ነው፡፡

• እኛ የምናውቀውን የማያውቅ ሰዎች መብዛት - እኛ የምናውቀውን የማሳወቅ ታላቅ እድል ነው!

• እኛ የምንችለውን የማይችሉ ሰዎች መብዛት - እኛ የምንችለውን እንዲችሉ የማሰለጠን ታላቅ እድል ነው!

ሰዎችን ለውጡ! ሃሳብ ሽጡ! መፍትሄን አምጡ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ሁሉም ነገር ለበጎ ነው!
ሁሉም ነገር ለበጎ ነው!

አንድ ሃብታም ጎብኚ ወደ አንዲት ሃገር ከተጓዘ በኋላ ከከተማ ራቅ ወዳለ ስፍራ ለጉብኝት ሄደ፡፡ በዚያም አንድን እጅግ በጣም ደሃ የሆነ አስጎብኚ ቀጠረውና አካባቢውን እያሳየው ሲጓዙ ሳለ ጎብኚው አንድ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቀው አይነት ዛፍ ተመለከተ፡፡ በነገሩ ተገረመና ውስጡ ምን እንደሆነ ለማወቅ ለጉዞ የያዘውን አነስተኛ መጥረቢያ አንስቶ ዛፉን እቆርጣለሁ ብሎ ተሳስቶ ጣቱን ቆርጦ ጣለው፡፡

ይህ ባለጠጋ ጎብኚ በስቃይ ሲጮህ አስጎብኚው፣ “አይዞህ ሁሉም ለበጎ ነው” እያለ በመደጋገም ሲነግረው እጅግ ተበሳጨና አጠገባቸው የሚገኝ ጉድጓድ ውስጥ ገፍትሮ ጥሎት ሄደ፡፡ ይህ ጎብኚ ትንሽ ከተጓዘ በኋላ ጸጉረ ልውጥ ሰው ሲያገኙ ቀቅለው የሚበሉ ጎሳዎች አገኙት፡፡ የሚበላ ሰው በማግኘታቸው የተደሰቱት እነዚህ ሰዎች ጥፍር ካሰሩት በኋላ እንደልማዳቸው እሳታቸውን አንድደውና መቀቀያውን ጥደው በዙሪያው ከጨፈሩ በኋላ ጎብኚውን መቀቀያው ውስጥ ሊጨምሩት ሲሉ በድንገት የተቆረጠውን ጣቱን ተመለከቱ፡፡ በእምነታቸው መሰረት እንደዚህ አይነት ሰው መብላት ክልክል ስለሆነ ሃሳባቸውን ቀይረው እንዲሄድ ለቀቁት፡፡

ይህ ጎብኚ የነበረበት የፍርሀት መንቀጥቀጥ ረገብ ሲልለት መጀመሪያ ትዝ ያለው በንዴት ገደል ውስጥ ገፍቶ የጣለው አስጎብኚው ነበረና ሄዶ ጎትቶ በማውጣት ይቅርታን ጠየቀው፡፡ የአስጎብኚው መልስ አሁንም እንደተለመደው፣ “ችግር የለውም፣ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው” የሚል ነበር፡፡ ጎብኚው ይህንን መልስ በድጋሚ በመስማቱ፣ ምን ለማለት እንደፈለገ ጠየቀው፡፡

የአስጎብኚው መልስ እንደዚህ የሚል ነበር፡- “አንዱ ጣትህ በመቆረጡ ምክንያት በእነዚህ ሰዎች ከመበላት ዳንክ ስለዚህ አንዱ ጣትህ መቆረጡ ጥሩ ልምምድ ባይሆንም የኋላ ኋላ ግን ለበጎ ሆነ፡፡ አንተ ደግሞ እኔን በንዴት ገደል ውስጥ መክተትህ ምንም ጥሩ ነገር ባይሆንም፣ ያንን በማድረግህ ምክንያት እዚሁ ባልቀርና አብሬህ ብጓዝ ኖሮ አንተን ትተው እኔን ይበሉኝ ነበረ፡፡ ይህም ለበጎ ሆነ”፡፡

ካጠፋ በኋላ የሚመለስና ይቅርታ የሚጠይቅ ማንነት ላለው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው!

ይቅርታ ሲጠየቅ መለስ ብሎ ይቅር የሚል ጨዋ ማንነት ላለው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው!

በሁሉም ነገር በፈጣሪው ላይ ያለውን እምነት ለማይተው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው!


በአሁኑ ወቅት የምታልፉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለበጎ እንዲለወጥላችሁ ጸሎቴና ምኞቴ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
2024/05/14 05:04:55
Back to Top
HTML Embed Code: