Telegram Web Link
#ሕያውን_ከሙታን_መካከል_ስለ_ምን_ትፈልጋላችሁ__ተነሥቶአል_እንጂ_በዚኽ_የለም (ሉቃ 24፡5)"
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ይህ የትንሣኤ በዓል ሞት የተሸነፈበት፣ መቃብር የተረታበት፣ ሕይወት ያገኘንበት ታላቅ በዓል ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ በሞቱ ሞትን ድል መንሣቱን፣ ሙስና መቃብር መጥፋቱን፣ ዓለም በብርሃን መመላቱን ትመሰክራለች፡፡

ክብር ይግባውና ለአዳም በሰጠው ተስፋ መሠረት ወልደ እግዚአብሔር ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ተወልዶ በሚያስተምርበትም ጊዜ 3 ቀንና 3 ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ እንደሚነሣ ያስተምር ነበር፡፡ ጥቅሶቹም፦ (ማቴ 12:40፤ ሉቃ 9:21፤ ዮሐ 2:19)

የዚኽም አቈጣጠር ሁለት ዐይነት ነው የመጀመሪያው “መዓልት ይስሕቦ ለሌሊት ወሌሊት ይስሕቦ ለመዓልት” (ቀን ሌሊትን ሌሊት ቀንና ይስባል) በሚለው የአቈጣጠር ዘዴ ጌታ ቅድስት ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ዐርብ በሠርክ ወደ መቃብር ስለወረደ ዐርብ እንደ አንድ ቀን ሲቈጠር፤ ቅዳሜ ያው አንድ ቀን፣ እሑድ ደግሞ መንፈቀ ሌሊት ስለተነሣ እሑድ እንደ አንድ ቀን ይቈጠራል።

ሌላው አቈጣጠር ደግሞ ዕለት የሚለው ፍቺ አንድ እጅ ብርሃን አንድ እጅ ጨለማን ያካተተ ነው፤ ሰለዚህ በዚህ ተመርጒዘን ካየነው
► የስቅለት ዕለት ዐርብ ከጠዋት እስከ ስድስት ሰዓት ብርሃን ስለሆነ አንድ እጅ ብርሃን
► ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ስለኾነ አንድ እጅ ጨለማ
► በሠርክ ደግሞ ብርሃን ሆኗል አንድ እጅ ብርሃን
► ቅዳሜ ደግሞ ሙሉ ቀን ሙሉ ሌሊት ስለሆነ አንድ እጅ ብርሃን አንድ እጅ ጨለማ
► ጌታ የተነሣው እሑድ ሌሊት ስለሆነ አንድ እጅ ጨለማ ነበር፡፡
ስለዚህ ሦስት እጅ ብርሃን ሦስት እጅ ጨለማ 3 መዓልት 3 ሌሊት ተብሏል፡፡

ጌታችን ለምን ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐደረ ቢሉ?
ሀ) 1) አዳምን 2) ሔዋንን 3) ሕፃናቱን እንዳደነ ለማስረዳት 3 ዕለት ዐደረ
ለ) 1) ለሥጋችን 2) ለነፍሳችን 3) ለደመ ነፍሳችን እንደካሰልን ለማስረዳት
ሐ) የሰው 3 ጠላቶች ይኸውም 1) ሞት 2) ፍዳ 3) ኀጢአትን እንዳጠፋ ለማጠየቅ ነው

ክብር ይግባውና ትንሣኤና ሕይወት የኾነው አምላካችን ክርስቶስ ሞትን ድል ነሥቶ በድንቅ ምስጢር መቃብሩ እንደተዘጋ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ያን ጊዜ ዓለም በብርሃን ተዋጠ፡፡

የፅንሰቱና የልደቱ ምስጢር ከትንሣኤው ምስጢር ጋር ይስማማል፤ ይኸውም በፅንሰቱና በልደቱ የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያምን ማኅተመ ድንግልና ሳይከፍት እንደተፀነሰና ሳይከፍት እንደተወለደ ሁሉ አሁንም በተዘጋ በተገጠመ መቃብር በድንክ አምላካዊ ጥበብ ረቂቅ ዘእምረቂቅ የሆነው አምላክ ተነሣ፡፡

ለዚህ ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዐተ ቅዳሴዋ ላይ “ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪን” (ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሣልፎ የሚኖረውን በድንቅ አምላካዊ ሥራ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ጌታችንን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በበፍታ ገነዙት) በማለት ለልጆቿ የትንሣኤውን ታላቅነት እየመሠከረች “ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ” (ትንሣኤህን ለምናምን ለእኛ ብርሃንህን ላክልን ወደኛ) እያለች በፍጹም ደስታ ትዘምራለች፡፡

ዕለተ እሑድ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ የተነሣባት ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት እናከብራታለን፤ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ የዕለተ ዐርቡን የመከራ እና የዕለተ እሑድን የደስታ ቀን እንዲኽ ያነጻጸረውን እነሆ ብያችለኊ፡-

ከትላንትና ወዲያ አይሁድ እየተዘባበቱበት “ራስኽን አድን” ይሉት ነበር (ማቴ ፳፯፥፵)፤ ዛሬ ግን ርሱ ጥሎት የተነሣበትን መቃብር መላእክት እየሳሙት ነው፤ ትናንት ሞቶ በመቃብር በተቀበረ ሰው ልማድ በታተመ መቃብር በዝምታ ነበር፤ ዛሬ ግን ሕያው ኾኖ ለሙታንም ሕይወትን በመስጠት ኹሉንም ወደ ሕይወት አስነሣቸው።

ከትናንትና ወዲያ ጦር፣ ኾምጣጤ እና ኀሞት እሾኽ እንዲኹም ስቅለት ነበር፤ ዛሬ ግን መላእክት በክብር እና በደስታ ዘመሩለት፤ ከትናንትና ወዲያ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የእግዚአብሔር ልጅ ነፍሱን በአባቱ እጅ አደራ ሰጠ (ሉቃ ፳፫፥፵፮)፤ ዛሬ ግን ኹሉንም የማዘዝ ሥልጣን ያለው ርሱ ነፍሱን ከሥጋው ጋር አዋሐዳት።

ትላንት የመሰቀያውን መስቀል አቆመ፤ ዛሬ ግን ጥንካሬ፣ የሙታን ትንሣኤና ኀይል ኾነ፤ ከትናንት ወዲያ ስምዖን አላውቀውም በማለት በተደጋጋሚ ካደው (ማቴ ፳፯፥፸)፤ ዛሬ ግን ሞትን ድል ነሥቶ በመነሣቱ መቃብሩን ለማየት ሲሮጥ ኼደ (ዮሐ ፳፥፬)፤ የዕለተ ዐርብ መከራው ለሐዋርያት ጉባኤ መሸመቂያ አዘጋጀ፤ እሑድ ግን ዐዲስ ራእይና ደስታ ኾነ።

ትናንት ንጉሡ በመቃብር ተኝቶ ነበር፤ ዛሬ ግን ወይኑ እንደተወው ኀያል ተነሣ (መዝ ፸፯፥፷፭)፤ ባላፈው ቀን ቅዱሳት አንስት በመከራ እና በለቅሶ ውስጥ ነበሩ (ሉቃ ፳፫፥፳፯)፤ ዛሬ ግን ርሱን እንደ አትክልተኛ አይተውት ታላቅ ደስታ ሐሴትን አደረጉ፤ በዐሳዛኙ ሰንበት ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ርሱ በኩረ ሙታን ከሙታን መኻከል ነበር፤ እሑድ ግን በመላእክት ጉባኤ ታጀበ (ማር ፲፮፥፭)።

በዕለተ ዐርብ የሐዋርያት ጉባኤ በሐዘን ተበተነ፤ ዛሬ ግን ትንሣኤውን በመደነቅ ለማየት የደቀ መዛሙርት ጉባኤ ወጥተው ነበር፤ በሌላኛው ቀን ሽሽት፣ በመበታተንና ራሳቸውን መደበቅ ነበረባቸው፤ ዛሬ ግን ለመሮጥ፣ በአንድ ላይ ለመሰብሰብ እና የምሥራቹን ለማምጣት ቻሉ፡፡

ትናንት እረኛው ተመትቶ የርሱም ጠቦቶች ተበታትነው ነበር (ዘካ ፲፫፥፯፤ ማቴ ፳፮፥፴፩)፤ ዛሬ ደግሞ ተኲላዎቹ ፈረጠጡ፤ መንጋዎቹ በደስታ ተመሉ፤ ትናንት ይሁዳ ገንዘብ ተቀበለ፤ ቀያፋ ምክር ሲሰጥ ሃናም ሲያወግዝ ተሰማ፤ ጸሓፍት በሁካታ ውስጥ ነበሩ፤ ጲላጦስ ተቀምጧል፤ ጌታችንም ምሰሶውን ይዞ ቆሟል፤ ስምዖን ክዷል፤ እንድርያስ ሸሽቷል፤ ዮሐንስ ርቀቱን ጠብቋል፤ ፊሊጶስ አይታይም፤ ማቴዎስ ተደብቋል፤ በርተሎሜዎስ ጸጒረ ልውጥ ኾኗል፤ ቀነናዊው ተርበትብቷል፤ ኹሉም በያለበት ተበትኗል (ማቴ ፳፯፥፭-፵፭)።

ዛሬ ግን ቀያፋ ኀፍረት ተከናንቧል፤ ሃና ግራ መጋባት ውስጥ ገብቷል፤ ይሁዳም ብሩን በትኖ ራሱን ዐንቋል (ማቴ ፳፯፥፭)፤ ጸሓፍትም መናገር ተስኗቸዋል፤ የምኲራብ አለቆች በኀፍረት ራሳቸውን ሸፍነዋል፤ ሌዋውያን ርስ በርሳቸው እየተወቃቀሱ ነው፤ ጲላጦስ ተደንቋል፤ የዚኽ ኹሉ ጠንሳሾች ከነጭራሹ በቦታው የሉም፤ የተኲላ መንጋዎች ተበትነዋል።

እረኛው ከበጉ ጋር ይነጋገራል፤ መንጋዎቹን ሲሰበስባቸው መዐዛውን ሳቡት፤ ማርያም ተደስታለች (ማር ፲፮፥፩)፤ ሰሎሜም በኀሤት ተመልታለች፤ ማርታ መልካም ዜና ይዛለች፤ ዮሐና የሰላም ዜና ታመጣለች (ሉቃ ፳፬፥፲)፤ ደቀ መዛሙርት ራሳቸውን ገልጠዋል፤ ሐዋርያት ከተደበቁባቸው ቦታዎች ወጥተዋል፤ ስምዖንና ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ሮጠዋል፤ ማቴዎስና በርቶሎሜዎስ ጭንቀታቸውን ረስተዋል፤ እንድርያስና ያዕቆብ በደስታ ውስጥ ናቸው፤ ቶማስ ተናዝዟል፤ ፊሊጶስ ምስጋናን አቅርቧል።
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
🌺በስመአብ🌺
🌺 ወወልድ 🌺
🌺ወመንፈስ ቅዱስ🌺
🌺
🌺
🌺አሃዱ🌺
🌺አምላክ🌺
🌺አሜን🌺
✞“#ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን” (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ)
✞“#በዐቢይ_ኀይል_ወሥልጣን” (በገናና ኀይልና ሥልጣን)
✞“#ዐሠሮ_ለሰይጣን” (ሰይጣንን ዐሰረው)
✞“#አግአዞ_ለአዳም” (አዳምን ነጻ አወጣው)
✞“#ሰላም” (ፍቅር አንድነት ሆነ)
✞“#እምይእዜሰ” (ከእንግዲህስ)
✞“#ኮነ” (ሆነ)
✞“#ፍሥሐ_ወሰላም” (ደስታ ሰላም)
አሜን እንኳን አደረሳችሁ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #ሕያውን_ከሙታን_መካከል_ስለ_ምን_ትፈልጋላችሁ_ተነሥቶአል_እንጂ_በዚኽ_የለም፡፡ሉቃ 24፡5
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #በመስቀሉ_ደም_ሰላምን_አደረገ_በሰማያትም_ላሉት_እርቅን_ሰላምን_አደረገላቸው፡፡ ቆላ፡1÷19
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ለኃጢአት_ሞትን_ለፅድቅ_እንድንኖር_እርሱ_ራሱ_በሥጋዉ_ኃጢያታችንን_በእንጨት_ላይ_ተሸከመ_በመገረፉ_ቁስል_ተፈወሳችሁ_እንደ_በጎች_ትቅበዘበዙ_ነበረና_አሁን_ግን_ወደ_ነፍሳችሁ_እረኛና_ጠባቂ_ተመልሳችሃል። 2ኛ ጴጥ 2÷24 •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#የመሰቀሉ_ቃል_ለምጠፉት_ሞኝነት_ለእኛ_ለምድን_ግን_የእግዚአብሔር_ኃይል_ነው፡፡ 1ኛ ቆሮ፡1÷18
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ከጌታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ_መስቀል_በቀር_ሌላ_ትምክህት_ከእኔ_ይራቅ፡፡ገላ፡6÷14
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
💐ሰላም💐
💐ለአንተ💐
💐ይሁን💐
💐ውድ የተዋህዶ ልጆች💐

🌹እንኳን🌹
🌹ለብርሃነ🌹
🌹
🌹
🌹
🌹ትንሳኤው🌹
🌹
🌹
🌹በፍቅር🌹
🌹በሰላምና🌹
🌹በጤና🌹
🌹
🌹
🌹አደረሳችሁ🌹
🌹 አደረሰን🌹
🌹
🌹
🌹መልካም🌹
🌹የትንሳኤ🌹
🌹 በአል🌹
🌹ይሁንላችሁ🌹

🌹🌹
✞አሜን✞🌹🌹✞አሜን✞
🌹🌹

✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
✞“#ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን” (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ)
✞“
#በዐቢይ_ኀይል_ወሥልጣን” (በገናና ኀይልና ሥልጣን)
✞“
#ዐሠሮ_ለሰይጣን” (ሰይጣንን ዐሰረው)
✞“
#አግአዞ_ለአዳም” (አዳምን ነጻ አወጣው)
✞“
#ሰላም” (ፍቅር አንድነት ሆነ)
✞“
#እምይእዜሰ” (ከእንግዲህስ)
✞“
#ኮነ” (ሆነ)
✞“
#ፍሥሐ_ወሰላም” (ደስታ ሰላም)

#የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ተጋድሎ_በኢትዮጵያ_ሊቃውንት
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖ የዚኽም ቅዱስ አባቱ በቀጶዶቅያ መስፍኑ አንስጣስዮስ ሲኾን እናቱ
ቴዎብስታ ትባላለች፤ የተወለደውም በልዳ በሶርያ ፍልስጥኤም በ፪፻፹ ዓ.ም.
ነው፤ ታናሽ ኾኖ ሳለ አባቱ ዐርፏል፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ፈረስ ግልቢያን ተምሮ
ኻያ ዓመት በኾነው ጊዜ ቢሩት ሀገር በመኼድ በዚያ ሀገር ይመለክ የነበረውን
መንፈሰ ሰይጣን ያደረበትን የመኰንኑን ልጅ እንዲበላት የተሰጠውን ዘንዶ
በክርስቶስ ስም ከገደለው በኋላ እጅ መንሻ ይዞ ወደ ንጉሠ ፋርስ ኼደ፡፡
❖ በዚያ ሀገር ግን ነገሥታቱ ጣዖታትን በማምለክ ክርስቲያኖችን
ሲያሳድዷቸው አይቶ ዐዘነ፤ ልቡም በክርስቶስ ፍቅር ነድዶ ወደ ሀገሬ
አልመለስም ስለ ክርስቶስ ስም እሞታለኊ አለና “ክርስቲያናዊ አነ ወአአምን
በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ” (እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ነው) በማለት መሰከረ፡፡
❖ ከዚያም ንጉሡ ልብሱን ገፍፈው በዕንጨት ላይ እንዲሰቅሉት፤ ዳግመኛ
የዘንባባ እሾኽ የመሳሰሉ ፸ የብረት ችንካሮች ሠርተው በነዚያ እንዲቸነክሩትና
ዐጥንቱን ኹሉ እንዲቀጠቅጡት አዘዘ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በትዕግሥት
በመኾን “እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ
መስቀል” (ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል እንደተሰቀለ እንዴት አላስብም)
አለ፡፡
❖ ዳግመኛም በውስጡ ረዣዥም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማን
ባጫሙት ጊዜ “ሠጠቅዎ ወመተርዎ ዐሥራዊሁ እስከ ውኅዘ ደሙ ዲበ ምድር
ከመ ማይ ወሶበ ስዕነ ሠጊረ ድቡተ ሖረ” ይላል ችንካሮቹ ደሙ እንደ ውሃ
በምድር ላይ እስኪፈስስ ድረስ እግሩን ዘልቀው ሥሩን በጣጠሱት፤ መኼድም
ባልቻለ ጊዜ አጐንብሶ ኼዷል፤ ከዚያም የፈላ የብረት ጋን ውስጥ ከትተው
ሰውነቱ በደም እስኪጥለቀለቅ ድረስ ራሱን በመዶሻ ሲመቱት ወደ ጌታችን ጸለየ፤
ያን ጊዜ “ጊዮርጊስ ሆይ ከአንተ ጋር ነኝና ጽና” የሚል ቃል ከሰማይ መጣለት፤
ቅዱስ ሚካኤልም ተገልጾ ከሕመሙ ፈውሶታል፡፡ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች
በጌታችን አመኑ፡፡
❖ ንጉሡም ይኽነን ባየ ጊዜ እጅግ የሚያስጨንቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀን
አሠርቶ ለቅዱስ ጊዮርጊስ “እመሰ ትሠውዕ ለአጵሎን ትነሥእ ጌራ መንግሥት
ወእመሰ ኊልቊ አንተ ከመ ትትልዎ ለክርስቶስ ነጽር ዘንተ መንኰራኲረ
ዘግበርኩ ለከ ከመ እግድፍ በውስቴታ ታማስን ሥጋከ” (ለአጵሎን ብትሠዋ
የመንግሥትን ዘውድ ትቀዳጃለኽ፤ ግን ክርስቶስን ለማገልገል የቈረጥኽ
ብትኾን ሥጋኽን ትፈጭ ዘንድ በውስጧ ልትጣልባት ያዘጋጀኋትን መንኰራኲር
ተመልከት) አለው፤ ይኽ ሲኾን ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጣሪው ክርስቶስን አመሰገነ፡፡
❖ እነርሱም ወደ መንኰራኲሩ በመወርወር ፵ ሰዎች ያዞሩት ዠመር
ከዚያም ሰውነቱ ለዐሥር ክፍል ተከፋፈለ፤ እነርሱም ሥጋውን በጒድጓድ ውስጥ
ቀበሩት፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመምጣት እንደገና
ከሞት አስነሣውና ባረከው፡፡
❖ ርሱም ከሞት ተነሥቶ እንደገና ወደ ከተማ ገብቶ ስለ ክርስቶስ
አምላክነት መሰከረ፤ እነርሱም እጅግ ለመስማት የሚከብዱ መከራዎችን
አደረጉበትና ሰውነቱን ጨምቀው አንጀቱን ዘረገፉት፤ ከዚያም ሥጋውን አቃጥለው
በዕንጨት ቀፎ በማድረግ ይድራስ ወደተባለ ተራራ ወስደው ዐመዱን በትነውት
ተመለሱ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመውረድ አራቱን
ነፋሳተ ምድር የተበተኑትን የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋዎች እንዲሰበስቡ አዝዞ
እንደገና ከሞት አስነሥቶታል፤ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በክርስቶስ አምነው
የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡
❖ በመጨረሻም ብዙ ተጋድሎዎችን ለሰባት ዓመታት ከፈጸመ በኋላ ንጉሡ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ራስ በሰይፍ እንዲቈረጥ አዝዞ ወደ መሰየፊያው ቦታ ሲኼድ
እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም
ከክርስቲያኖች ጸጥ ይል ዘንድ ጸለየ፤ ወዲያውኑም እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን
ነገሥታት አቃጥሏቸዋል፤ ከዚያም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብዙ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፤
ከዚያም ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ራሱን ዘንበል አድርጎ ሚያዝያ ፳፫ በሰይፍ
ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅቷል፡፡
❖ ከአገልጋዮቹ የቀሩት ሥጋውን ወስደው በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ወደ
ሀገሩ ልዳ በመውሰድ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በውስጡ አኖሩት፤ ከርሱም
ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ተገልጠዋል፡፡
❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌ ድርሰታቸው ላይ፦
“ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ
አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ”
(የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከኾነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ
የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ
ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለርሱ ኹሉን
ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) ርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል) ይሉታል፨
❖ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቁ አርከ ሥሉስም የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ
ጊዮርጊስን ተጋድሎ፡-
“ሰላም ለከ ሰርዌ ሰማዕታት አእላፍ
ዘሞገሰ ስምከ በጽሐ መንገለ ኲሉ አጽናፍ
በቅድመ ፀሓይ ብሩህ ዘኢየዐርብ ለዘልፍ
ሕማምየ ዝሩ ነሢአከ ወጸዊረከ እስትንፋሰ አፍ
ጊዮርጊስ ቀሊለ ክንፍ ከራድዮን ዖፍ”
(ዘወትር በማይጠልቅ በብሩህ ፀሓይ ፊት በምድር ዳርቻዎች ኹሉ የስምኽ
ባለሟልነት የደረሰ የአእላፍ ሰማዕታት አለቃቸው ሰላምታ ለአንተ ይገባል፤ ክንፈ
ፈጣን ከራድዮን ዖፍ የተባልኽ ጊዮርጊስ ሆይ የአፍ እስትንፋስን ተቀብለኽና
ተሸክመኽ ሕማሜን በትን) እያለ ተማፅኖታል፡፡
❖ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለጊዮርጊስ ሰማዕት ዘፀሓየ ጽድቅ
ዘተአምሪሁ ከመ ኆጻ ባሕር
ዘኢይትኌለቊ ኮከበ ክብር
ዘማእከለ ሰማይ ወምድር
ዘአርአየ ኀይለ በዲበ ሰሌዳ መንበር
ብእሲ አዛል ወመስተጋድል
ኀያል ዝሕዙሐ ገድል”፡፡
(ገድሉ የበዛ የተትረፈረፈ ኀያል፤ ተጋዳይ ጐልማሳ (ብርቱ) ሰው፤ በተዘረጋ ዙፋን
ላይ ኀይልን ያሳየ፤ በሰማይና በምድር መኻከል ያለ የማይቈጠር የክብር ኮከብ፤
ተአምሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ የኾነ፤ የፀሓየ ጽድቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት
ለኾነ ለጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፨
❖ የስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ ደራሲ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ፦
"እምብሩር ወወርቅ ይትበደር ሞገሱ
ለጊዮርጊስ ቅዱስ በዲበ ጸዐዳ ፈረሱ
ለረዲኦትነ ይምጻእ ወያንሶሱ"
(ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን
ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም) ይለዋል፨
🕊 † ዐቢይ ወክቡር: ጊዮርጊስ: ሰርዌ አዕላፍ: ወመክብበ ሰማዕታት † 🕊

መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ፯ [7] ዓመታት ስቃይ በሁዋላ በዚህ ቀን ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ :-- ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ [አንስጣስዮስ] እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም [ልዳ] ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::

ቅዱስ ጊዮርጊስ ፳ [20] ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት [የአሁኗ ቤይሩት-ሊባኖስ] ሰዎች ዘንዶ [ደራጎን] ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና ፸ [70] ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ [ዐውደ ስምዕ] ደረሰ::

ከዚያም ለተከታታይ ፯ [7] ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: ፫ [3] ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ የሰማዕታት አለቃቸው: ፀሐይና የንጋት ኮከብ በሚል ይጠራል::

"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ:
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ" እንዲል መጽሐፍ::

ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: ፸ [70] ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ [በመቶ ሺ የሚቆጠሩ] አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ::

በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት::

በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ [ደብረ ይድራስ)] ወጥተውም በነፋስ በተኑት::
"ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ" እንዲል:: [ምቅናይ]

እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ::

ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ: አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: ፸ [70] ው ነገሥታት ግን አፈሩ::
ከ፯ [7] ዓመታት መከራ በሁዋላም በዚሕች ቀን ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: ፯ [7] አክሊላትም ወርደውለታል::

በ፫፻፺ [390] ዎቹ አካባቢ [ሰማዕት ከሆነ ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ] በዚያው በሃገሩ ደብር አንጸው: አጽሙን አፍልሠው ቀድሰዋታል::
ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነው:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ አራዊት [ነገሥታት] መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ፵፯ [47] ሚሊየን ክርስቲያኖችን ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ::

በ፫፻፭ [305] ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ:: የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ::

ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ግን ቀንዲሉ ተገልብጦ መሐል አናቱን መታው:: እንደ እብድ ሆኖ ሞተ:: ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ ሸሸ:: ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ:: ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት::

እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን [ደወሉን] ለቀቀበት:: ራሱን ቢመታው ደነዘዘ:: የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ፯ [7] ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮሰ ይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል::

አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትእግስት: ከበረከቱም ይክፈለን::

🕊

ሚያዝያ ፳፫ [23] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፪. ቅዱስ ሮቆ ጻድቅ [በስሙ ለተማጸነ ከወባ በሽታ እንዲጠብቀው ጌታ ቃል ኪዳን ገብቶለታል]

ወርኀዊ በዓላት

፩. ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
፪. ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
፫. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፬. አባ ሳሙኤል
፭. አባ ስምዖን
፮. አባ ገብርኤል

"የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ::" [ዕብ.፲፩፥፴፭-፴፰] (11:35-38)

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
#የአምላክ_እናት_ልደት____ልደታ_ለማርያም

በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መተርጒማን እንዳስተማሩንና እንደጻፉልን በእናቷ በሐና በኩል ያሉ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ጴጥሪቃ ቴክታ ሲባሉ “ወኮኑ ክልኤሆሙ ጻድቃን ወፈራህያነ እግዚአብሔር ወይትአመንዎ ለአምላኮሙ በጥቡዕ ልብ እንበለ ኑፋቄ” ይላል (ኹለቱም ሰዎች ደጋጐችና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ያለምንም መጠራጠር በፍጹም ልቡናቸው በአምላካቸው የሚተማመኑ ነበሩ)፤ እነርሱም በጊዜው ይኽ ቀራችኊ የማይባሉ ባለጠጎች ነበሩ፤ ከሀብታቸው ብዛት የተነሣ ወርቁን ብሩን እንደ ዋንጫ እያሠሩ በላሙ በበሬው ቀንድ ላይ ይሰኩት ነበር፤ ይኽን ያኽል አቅርንተ ወርቅ፣ አቅርንተ ብሩር እየተባለ ይቈጠር ነበር፤ የዕንቊ ጽዋ እንኳ ፸፣ ፹ ያኽል ነበራቸው ይላል፡፡

ከዕለታት ባንዳቸው ጴጥሪቃ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ የሀብቱን ብዛት አይቶ ሚስቱ ቴክታን “ለመኑ ዘዘገብነ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ አንቲኒ ወአነሂ መካን ንሕነ” (የሰበሰብነው ገንዘብ ስንኳን ለኛ ለልጅ ልጅ ይተርፍ ነበር አንቺም እኔም መካኖች ነንና የሚወርሰን ልጅ የለንም) በማለት ተናገራት፤ ርሷም እንዲኽ ማለቱ ወላድ የፈለገ መስሏት በሐዘን ኾና “አምላከ እስራኤል ከኔ ልጅ ባይሰጥኽ ከሌላ ይሰጥኽ ይኾናልና ሌላ አግብተኽ ውለድ” አለችው፤ ርሱም “አነሂ ኢይፈቅድ የአምር አምላከ እስራኤል ከመ ኢየሐስቦ ለልብየ” (ይኽንስ እንዳላደርገው በልቤም እንዳላስበው የእስራኤል አምላክ ያውቃል) በማለት ተናገረ፡፡

ርሷም ዐዝና ሳለ ራእይ ታያለች፤ ነጭ እንቦሳ ከማሕፀኗ ስትወጣ እንቦሳዪቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ሰባት ስትደርስ ሰባተኛዋ ጨረቃን ስትወልድ፤ ጨረቃ ፀሓይን ስትወልድ አይታ በአድናቆት ለባሏ፦ ❖ “ግሩም ግብሩ ለእግዚአብሔር ትማልም ርኢኩ በሕልምየ ጸዐዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርሥየ ይእቲኒ ወለደት ጸዐዳ ጣዕዋ እስከ ሰብዐቲሆን ወሳብዕታኒ ወለደት ወርኀ ወወርኅኒ ወለደት ፀሓየ”

(የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው፤ ትናንትና ማታ በሕልሜ ነጭ ጥጃ ከማሕፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ደግሞ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንደዚኽ እየኾነ እስከ ሰባት ትውልድ ሲደርሱ ሰባተኛዪቷም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየኊ) በማለት አስረዳችው።

ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ሕልም ወደሚፈታ ሰው ዘንድ በመኼድ የሚስቱን ራእይ ነገረው፤ ያም ሕልም ተርጓሚ ምስጢር ተገልጾለት ሰባት አንስት ጥጆች መውለዳችኊ ሰባት ሴቶች ልጆች ይወለዳሉ፤ ነጭ መኾናቸው ደጋጎች ልጆች መኾናቸው ሲኾን “ወሳብእታኒ ትከብር እመላእክት ወትትሌዐል እምኲሉ ሰብእ ወበእንተ ፀሓይኒ ኢያእመርኩ” (ሰባተኛዪቱ ጨረቃን መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ናት፤ የፀሓይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም) በማለት ተረጐመለት፤ ርሱም ለሚስቱ ነገራት፤ ርሷም “የእስራኤል አምላክ የሚያደርገውን ርሱ ያውቃል” በማለት ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡

ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሔሜን አሏት፤ ሔሜን → ዴርዴን ወለደች፤ ዴርዴም → ቶናን፤ ቶናም →ሲካርን ወለደች፤ ሲካርም→ ሴትናን፤ ሴትናም →ሔርሜላን ወለደች፤ ሔርሜላም የተከበረችና የተመረጠች ዓለሙን ኹሉ ለፈጠረ ጌታ አያት ለመኾን የበቃች ሐናን ወልዳለች።

ሐናና ኢያቄምንም “ወክልኤሆሙ ኄራን ወሥሙራን እሙንቱ ወየሐውሩ በሕገ እግዚአብሔር እስመ እግዚአብሔር ኀረዮሙ ወአፍቀሮሙ ትካት” ይላቸዋል እግዚአብሔርን የሚወድዱ በሕጉ የሚኖሩ ደጋጎችና አምላክም የመረጣቸው ሲኾኑ ሐና መካን በመኾኗ ምክንያት ኹለቱም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት በመኼድ ለዐይናቸው ማረፊያ ለልባቸው ተስፋ የሚኾን ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ እንደነበር፤ “Protoevangelium of James” (ፕሮቶቫንጊሊዩም ኦፍ ጀምስ) የሚለው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊዉ መጽሐፍ በስፋት ይገልጻል፡፡

ከዕለታት ባንደኛው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ሲመለሱ “ወርእዩ አርጋበ እንዘ ይትፌሥሑ ምስለ ውሉዶሙ” ይላል ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ደስ ብሏቸው ሲጫወቱ አይተው ሐና “አቤቱ ጌታዬ ግዕዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠኽ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሣኸኝ” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፤ ወዲያው ሱባዔ ይገባሉ፤ ኢያቄም ወደ በረሓ ኼዶ ሲጸልይ ሐና ደግሞ በቤቷ ዙሪያ ባለው የተክል ቦታ ሱባዔ ያዘች።

በሱባዔያቸው ፍጻሜ ኹለቱም ራእይ አይተው ተነጋግረዋል፡፡ “ይቤላ ኢያቄም ለሐና ብእሲቱ እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ” ይላል ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዎፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ብሎ የተገለጸለትን ለሐና ነግሯታል።

ይኸውም የራእዩ ምስጢር፡- ወፍ የተባለው አካላዊ ቃል ክርስቶስ ሲኾን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፤ ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ ሲያጠይቅ ሲኾን፤ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ምልአቱ፣ ስፍሐቱ፣ ርቀቱ፣ ልዕልናው፣ ዕበዩ ናቸው፡፡

ሐናም ተገልጾላት “ትቤሎ ሐና ለኢያቄም ብእሲሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ” ይላል ለባሏ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ብላዋለች።

ይኽ የራእይ ምስጢር፡- ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትኾን፤ ነጭነቷ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፤ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ ወደ ዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በዦሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መኾኗን ሲያጠይቅ ነው፡፡

ኢያቄምና ሐናም ይኽነን ራእይ ሐምሌ ፴ ቀን ካዩ በኋላ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ይኾናል፤ ሴትም ብንወልድ ለቤተ እግዚአብሔር መጋረጃ ፈትላ ትኑር” ብለው ስእለት ከተሳሉ በኋላ ራእይ አየን ብለው ዕለቱን አልተገናኙም፤ አዳምንና ሔዋንን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት” ብሎ የተናገረው አምላክ ለእኛም ይግለጽልን ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ድረስ እየብቻቸው ሰነበቱ።

ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን “ከሰው የበለጠች ከመላእክት ኹሉ የከበረች ልጅ ትወልዳላችኊ" ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሐና ነግሯት በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን ነሐሴ ሰባት እሑድ ተፀንሳለች፤ በእናቷ ማሕፀን ሳለችም “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ” እንዲል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥንተ አብሶ ባመጣው መርገም እንዳትያዝ ጠብቋታል፡፡

ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም መፀነስ ከሊቃውንት መኻከል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፦

“ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ
ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ
ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ
እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ
ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ”

(ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ) በማለት ዓለምን ኹሉ በደሙ ፈሳሽነት ያዳነ ንጉሣችን፣
ፈጣሪያችን ክርስቶስን በድንቅ ተአምር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ የወለደችልን ምክንያተ ድኂን ርግበ ሰሎሞን የተባለች የቅድስት ድንግልን የመፀነሷን ነገር በአድናቆት ገልጸዋል፡፡

“ወእምድኅረ ስድስቱ አውራኅ ተዐውቀ ፅንሳ ለሐና” ይላል፤ ከስድስት ወርም በኋላ የሐና ፅንሷ እየታወቀ ሲመጣ ጎረቤቶቿ መፅነሷን ይረዱ ዘንድ በአድናቆት ማሕፀኗን ይዳስሱ ነበር፤ በተለይም ዐይኗ የታወረ የሐና ዘመዷ የአርሳባን ልጅ የምትኾን አንዲት ሴት የሐናን ማሕፀን ዳስሳ ዐይኗን ብትነካው በርቶላት በታላቅ ደስታ ኾና “ብፅዓን ለኪ ኦ ሐና እስመ እም ፍጥረተ ዓለም አልቦ ዘከማኪ ዘይፌውስ በከርሡ አዕይንተ ዕውራን” (ሐና ሆይ ብፅዓን ይገባሻል ዓለም ከተፈጠረ ዠምሮ እንዳንቺ በማሕፀኑ የዕውራንን ዐይን የሚያበራ የለምና) በማለት አመስግናታለች፤ ከዚኽ በኋላ ዝናዋ በሀገሩ ኹሉ ተሰምቶ ሕሙማን ኹሉ ማሕፀኗን እየዳሰሱ ይፈወሱ ነበር፡፡

አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ይኽነን ሲገልጹ፦
“ጸግይየ ሣዕረ ዘኪሩቤል ልሳነ
ተአምረኪ በነጊር እመ ኢፈጸምኩ አነ
ባሕቱ አአኲት ማርያም ዘጾረተኪ ማሕፀነ
እንዘ ሀለወት ፀኒሳ ኪያኪ ርጢነ
ለለገሰስዋ ላቲ ትፌውስ ዱያነ”

(ሳርን የኾንኊ እኔ የኪሩቤል አንደበትን ገንዘብ አድርጌ ታምርሽን በመንገር በማስተማር ባልፈጽምም ነገር ግን ማርያም የተሸከመቺሽን ማሕፀን አመሰግናለኊ፤ መድኀኒት አንቺን ፀንሳ ሳለች ርሷን የዳሰሷትን ድዉያንን ኹሉ ትፈውስ ነበር) በማለት እመ መድኅነ ዓለም ገና ሳትወለድ የተሠራውን ድንቅ ተአምር አመስግነዋል፡፡

ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል በመላው ዓለም የሚታወቅ ሲኾን ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የአምላክ እናት የተፀነሰችበት ይኽነን በዓል ነሐሴ ፯ ቀን በታላቅ ድምቀት በማሕሌት፣ በቅዳሴ የምታስበው ሲኾን በዓሉም “ፅንሰታ ለማርያም” በመባል ይታወቃል።

በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ደግሞ በዓሉን “The conception of the Theotokos” (የአምላክ እናት መፀነስ) በማለት ሲያከብሩት ወሩን ግን የልደት በዓልን ለማክበር በሚዘጋጁበት በታኅሣሥ አድርገው በ፱ኛው ቀን “December 9” ላይ ያስቡታል ፡፡

በእጅጉ የሚደንቀው ደግሞ “ሳሚናስ ወልደ ጦሊቅ ዘይነብር ውስተ ቤተ ዶይቅ” ይላል ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጐቱ ቤት ኼዶ ሞተ፤ ሐናም በሀገራቸው ልማድ የአልጋውን ሸንኮር ይዛ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ፈጥኖ ተነሥቶ “ሰላም ለኪ ኦ ሐና እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ” (ሰማይና ምድርን ለፈጠረው አምላክ አያቱን የተባልሽ ሐና ሰላም ላንቺ ይኹን) አላት።

ከዚያ የነበሩ አይሁድም በመደናገጥ “ሳሚናስ ምን አየኽ? ምን ትላለኽ?” አሉት፤ ርሱም “ከዚች ከሐና ማሕፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ኹሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው፤ እኔንም ያነሣችኝ ርሷ ናት” አላቸው፤ እነርሱም ይኽነን በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔርን ከማመስገን ይልቅ በቅናትና በክፋት ተመልተው ሐና በማሕፀን ባለ ፅንሷ ካዳነች በኛ ላይ ልትሠለጥን አይደለምን? “ንዑ ንገሮሙ ለሐና ወለኢያቄም” ሳትወልድ አስቀድመን ሐናና ኢያቄምን በድንጋይ ወግረን እንግደላቸው ብለው ተነሣሡባቸው።

ያን ጊዜ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ሐናን ሊባኖስ ወደሚባል ተራራ እንዲወስዳት ነገረው፤ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ እመቤታችን በሊባኖስ ተራራ እንደምትወለድ ተገልጾለት፡-
“ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት” (ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ ከሊባኖስ ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ) በማለት የተናገረው ትንቢት ሊፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም በ፭ ሺሕ ፬፻፹፭ (5485) ዓመተ ዓለም በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች (ማሕ ፬፥፲)፡፡

ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ የነገረ ማርያም መጽሐፋቸው ላይም፦
“ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ
በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ
ማእከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ እንዘ እነቡ
እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዐጽ እሌቡ
ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ”

(ትንቢት ከተነገረለት ከአንበሳ ጉድጓድ፤ ድንግል ሙሽራ በተገኘሽ ጊዜ የንጉሦች ንጉሥ የሰሎሞን ልቡ እንደተደሰተ፤ ደስ ባላቸው በመላእክት አንድነት ፊት ታምርሽን እየተናገርኊ የሐና አበባ ማርያም እዘምርሻለኊ፤ ወተትን ጠብቶ እንደሚዘልል እንቦሳም ዝለል ዝለል ይለኛል) በማለት ሰሎሞን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቶ ታላቅ ደስታን ለኹላችን እንደሰጠን አብራርተው ገልጠዋል፡፡

ይኽ የእመቤታችን ልደት ለሰማያውያን መላእክትና ለደቂቀ አዳም ደስታ ሲኾን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከርሷ ተወልዶ ዲያብሎስ ፭ሺሕ፭፻ ዘመን በሲኦል ያኖራቸውን ነፍሳት ወደ ገነት የሚያስገባቸው ነውና፤ ሰይጣን በተቃራኒው ልደቷ እንዳላስደሰተው ሲገልጹ፦

“ተፈሥሐት ምድር ወሰማይ አንፈርዐጸ
በዕለተ ጸገዩኪ አብላስ ወአውጽኡ ሠርጸ
ተአምረ ሕይወት ማርያም ዘአልብኪ ቢጸ
እስከ ፈርሀ መልአከ ሞት ወሰይጣን ደንገጸ
ዜና ልደትኪ ነጐድጓድ እስከ (ውስተ) ሲኦል ደምፀ”
(በለሶች (ኢያቄምና ሐና) ቡቃያ አንቺን ባስገኙሽ ጊዜ ምድር ደስ አላት ሰማይም ደስ አለው፤ ጓደኛ (ምሳሌ) የሌለሽ የድኅነት ምልክት ማርያም፤ መልአከ ሞት እስከ ፈራና ሰይጣንም እስከ ደነገጠ ድረስ የመወለድሽ ዜና እስከ ሲኦል ድረስ (በሲኦል) ተሰማ) በማለት አስተምረዋል፡፡

ጠቢቡ ሰሎሞን አስቀድሞ በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ በማሕልዩ ላይ “መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎሕ ሠናይት ከመ ወርኅ ወብርህት ከመ ፀሓይ” (ይኽቺ እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ እንደ ጨረቃ የተዋበች፤ እንደ ፀሓይም የጠራች ዐላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሰራዊት የምታስፈራ ማን ናት?) በማለት እንደ ፀሓይ የሞቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ ንጽሕናዋና ቅድስናዋ የመልኳ ደም ግባት በነቢያት ትንቢት አስቀድሞ የተጐበኘላት የእውነት ፀሓይ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብርና ደም ግባቷን እንደተናገረ በሊባኖስ ተራራ በግንቦት ፩ በተወለደች ጊዜ ፊቷ በእጅጉ ያበራ ነበር፤ መዐዛዋም ከሽቱ ኹሉ ይበልጥ ነበር፡፡

ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም የመዐዛዋን አስደናቂነት በሰሎሞንን ቃል በመነሣት የመዐዛዋን ነገር ሲያደንቅ፡-
“ወእወዲ ውስተ አፉየ እምፍሬ ከርሥኪ…” (ከማሕፀንሽም ፍሬ ወደ አፌ እጨምራለኊ፤ የፍሬሽ ደምም ለጉሮሮዬ የጣፈጠ ነው፤ የሽቱሽ መዐዛም ለአፍንጫዬ ያማረ ነው፤ የድንግልናሽ ክብርም ልቡናዬን እንደ ከረመ ንጹሕ ወይን ደስ ያሰኘዋል፤ ስለ አንቺ ያለኝ ደስታ ምን ያኽል ነው፤ አነጋገርሽ ያማረ ነው፤ ቃልሽም የጣፈጠ ነው።
ከንፈሮችሽም የደስታ ምንጮች ናቸው፤ አንደበትሽም የምስጋና መፍለቂያ ነው፤ እጅግ በጣም አማርሽ፤ ቁመትሽም እንደ ዘንባባ ዛፍ ነው፤ የልብሶችሽ መዐዛም አፈው በመባል እንደሚታወቀው ሽቱ፤ የአፍንጫሽ መዐዛም እንደ ወይን አበባ ሽታ የሚኾንልሽ ድንግል ሆይ ደስታሽን እወደዋለኊ (ማሕ ፯፥፰) የአፍሽም አከፋፈት እንደ ቀናንሞስ አበባ የጣፈጠ ነው፤ ከሊባኖስ ዕንጨቶች ኹሉ ጋር (ማሕ ፬፥፲፬)) በማለት እንደ ሰሎሞን ርሱም የፈጣሪውን እናት አመስግኗል፡፡

የፈጣሪያችን እናት ቅድስት ድንግል የተወለደችበትን ግንቦት አንድን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን “ልደታ ለማርያም” በማለት ከጥንት ዠምሮ በታላቅ መንፈሳዊ ሐሤት በቅዳሴ፣ በማሕሌት የምታከብርላት ሲኾን፤ በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት ያሉ ክርስቲያኖችም ይኽነን በዓል “The Nativity of the blessed Virgin Mary” (የተባረከችው የድንግል ማርያም ልደት (መወለድ)) በማለት ያስባሉ።

በጥንት ምሥራቃውያን (እንደ ቤዛንታይን ባሉ) ዘንድ ዐዲሱ ዓመት ልክ እንደኛ መስከረም ወር “September” ላይ ይውል ስለነበር ከዚኽ አያይዘው መስከረም ፰ (September 8) ያከብሩት የነበረ እንደነበር ታሪክ ሲያስረዳ ይኽነን ይዘው በዚኽ ዕለትም የሚያከብሩት ብዙዎች የዓለማት ሀገራት አሉ፡፡

ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
[ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፤ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል አንድ ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ]
#የአምላክ_እናት_በረከቷ_በእኛ_በአደራ_ልጆቿ_ላይ_በዝቶ_ይደር፡፡
🌿🌾 #ደብረ_ምጥማቅ 🌾🌿

ግንቦት ፳፩
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ በወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ነው።
ጌታችን ፈጣሪና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ወደ ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ፣ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር። ቦታውንም ባርኮና ቀድሶ ይህ ቦታ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎ ለእናቱ ለእመብርሃን ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር። ቦታው ደብረ ምጥማቅ ከመቀደሱ የተነሳ አካባቢውን በርካታ መነኮሳት ይኖሩበት ነበር።
እመቤታችንም በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን በልጇ ፈቃድ ግንቦት ፳፩ ቀን አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት ትገለጽላቸው ነበር።
በዚህም መገለጥ እመብርሃን ድንግል ማርያም ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ሌላ እምነት የነበራቸውም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየሀገሩ ያሉ ሰዎች
ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ ፤ድንግልም ከግንቦት ፳፩ ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር።
ህዝቡም የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል?! ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን?! ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን?! አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል፤ እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር።
አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር፤ ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር፤ ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው። ወይ ግሩም ታዲያ ይህ በዚያ ደጉ ዘመን ነበር፤ አሁን ግን ኃጢያታችን ስለበዛም በገሃድስ ተገልጻ አትታይም። በረድኤቷ ብዛት እና ለበቁ ጻድቅ አባቶቻችን ካልሆነ በስተቀር።
የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባት ነበረች። ፈልገው የሚያጡት፣ ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም። እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች ምንኛ የታደሉ ናቸው፤ እነዚያ በፊቷ የቆሙ እግሮች ምንኛ የተመረጡ ናቸው...። አምስቱን ዕለታትም ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል ነበር። እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በብርሃን መስቀል ባርካቸው አጅበዋት ከመጡት ከቅዱሳኑ መላዕክት ጋር ታርጋለች።
"የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ። ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው። ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው። በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ።... በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ። በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ። ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ። (መዝ. 44፥12-17)

🌿🌾 #አባ_መርትያኖስ🌾🌿
ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን አባ መርትያኖስ አረፈ፤ ይህም በህጻንነቱ መንኩሶ ለ፷፯ ዓመት በፍጹም ተጋድሎ የኖረ ነው። ይህ ገድል ትሩፋቱ በሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ እነሆ አንዲት በዝሙት ስራዋ እጅግ የምትታወቅ ሴት ዘንድ ወሬው ደረሰ፤ እርሱ እኮ የሴት ፊት ስላላየ ነው እንጂ በፍትዎት ይወድቃል፤ ከክብሩም ይዋረዳል አለቻቸው ባልንጀሮቿም የለም በፍጹም አያደርገውም አሏት፤ እኔ በዝሙት ከጣልኩት ምን ትሰጡኛላችሁ አለቻቸው ብር እንሰጥሻለን አሏት፤ በዚህ ተወራርደው ሄደች፤ ሽቶ ተቀባብታ
አምራ ተውባ ሄደች።
ስንክሳሩ እጅግ ውብና መልከ መልካም ነበረች ይላታል፤ እስኪመሽ ከገዳሙ አቅራቢያ ቆይታ በሩን አንኳኳች የመሸቢኝ እንግዳ ነኝ አሳድረኝ ትለዋለች፤ ነፍሱ ተጨነቀች ባስገባት የዝሙት ጦር ይነሳብኛል ብተዋት እንግዳ ሆኜ መጥቼ መቼ ተቀበላችሁኝ ብሎ ይፈርድብኛል ደግሞም አውሬ ይበላታል ብሎ አሰበ፤ ባስገባት ይሻለኛል ብሎ አስገባት የተቀበችው ሽቶ ዝሙት የሚቀሰቅስ ነው። ቀረበችው፤ አባቴ በዚህ ማንም አያየንም አብረን እንተኛ አለችው፤ እሳት እያነደደ ነበርና እሺ ምን ችግር አለው እዚህ አሳት ላይ ምንጣፍሽን አንጥፊና እንተኛለን አላት።
አንድም እግሩን ወደ እሳቱ ማገደው ይላል፤ አይንህ ብታሰናክልህ ካንተ
አውጥተህ ጣላት አይደል የሚለው መጽሐፉ፤ ደነገጠች ምንድን ነው አባቴ
አለችው፤ ይህ ያስደንቅሻልን የገሃነም እሳትን ታዲያ እንዴት ልትችይው ነው
አላት። እግሩ ስር ወድቃ ይቅር በለኝ አለችው እርሱም ሌሊቱን ሙሉ ሲያስተምራት አደረ። ሲነጋ አልተመለሰችም አመንኩሰኝ ከዚህ በኃላ ወደ ዓለም አልመለስም አለችው። አመነኮሳት ከደናግል ገዳም ወስዶ ለእመምኔቷ አደራ ሰጣት። የሚገርመው ይህች እናት ከብቃቷ የተነሳ የመፈወስ ሀብት ተሰጣት ብዙ በሽተኞች ወደርሷ እየመጡ ይፈወሱም ነበር።
አባ መርትያኖስ ግን ድጋሚ ሌላ ሴት
መጥታ እንዳትፈትነው ሰው የማይደርስበት ከባህር መካከል ባለች ደሴት ብቻውን መኖር ጀመረ። ከብዙ ዘመን በኃላ መርከብ ተሰብሮ ብዙዎች ሲሞቱ አንዲት ሴት በመርከቡ ስባሪ ተጣብቃ እርሱ ካለበት ደሴት ደረሰች ባያት ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ከእርሷ ጋር በአንድነት ስለመኖሩም አዘነ። የምትበላውን ሰጥቷት የምትለብሰውን አዘጋጅቶላት ሲያበቃ ተወርውሮ ወደ ባህሩ ገባ ዓሳ አንበሪም ተሸክሞ ወደ የብስ አደረሰው ከዚህ በኃላ በአንድ ቦታ ላለመቀመጥ ወስኖ በመቶ ስምንት አገሮች የሚገኙ ታላላቅ ገዳሞችን ዞረ። በመጨረሻም በዛሬዋ ቀን ግንቦት ፳፩ በክብር አረፈ።

🙏የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ ጣዕም፣ ፍቅር፣ ረድኤትና በረከት አይለየን፤ የጻድቁ አባታችን የአባ መርትያኖስ ጽናት፣ ተጋድሎና ዕምነት ሁላችንንም ይጠብቀን አሜን።

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
🌿🌾#ቅዱስ_ላሊበላ🌾🌿

📖ሰኔ ፲፪
ቅዱስ ላሊበላ የተወለደው በላስታ ሮሃ ቤተመንግሥት በዋሻ እልፍኝት ውስጥ ታህሳስ ፳፱ በ፲፩፻ወ፩ ዓ/ም ሲሆን በዛሬው ዕለት ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ያረፈበት ነው።
ይህ ቅዱስ ጌታችን የጠጣውን መራራ ሐሞት እያሰበ ዓርብ ዓርብ ኮሶ ይጠጣ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ ቅዱሳን መካናትን፤ ወደ ሰማይም ወስዶ የቤተ መቅደሶቹን አሠራር አሳይቶታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚሠራበትን እግዚአብሔር እንዲገልጥለት ሱባኤ ቢገባ ቤተ ማርያም ከተፈለፈለችበት ቦታ የብርሃን ዐምድ ተተክሎ አይቷል።
ቅዱስ ላሊበላ ጎጃም በመሔድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን ተምሯል። ላሊበላ ከወንድሙ ቀጥሎ እንደሚነግሥ ትንቢት ተነግሮ ስለነበር ንጉሡ ሊገድለው ምክንያት ይፈልግበት ነበር፡፡ በእናትም በአባትም እኅት የምትሆነው፣ ለላሊበላ ግን በአባት ብቻ እኅት የሆነችው ላሊበላን ለመግደል አጋጣሚ ትጠብቅ ነበር፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን መራራ ሐሞት መጠጣቱን እያሰበ ዓርብ ዓርብ ከጾመ በኋላ ኮሶ ይጠጣ ነበርና እኅቱ አጋጣሚውን በመጠቀም መርዝ ጨምራ ሰጠችው።
ለቅዱስ ላሊበላ መርዝ ጨምራ የሰጠችውን እርሱ ከመጠጣቱ በፊት ያገለግለው የነበረ ዲያቆን ሲቀምሰው ወዲያው ሞተ፡፡ ዲያቆኑ ያስመለሰውን የጠጣው ውሻም ወዲያው ሞተ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም አገልጋዩ ለእሱ የተዘጋጀውን መርዝ ጠጥቶ እንደሞተ ባየ ጊዜ መርዙን ጠጣው፡፡ የጠጣው መርዝም ከሆዱ ውስጥ ሆኖ ያሰቃየው የነበረውን አውሬ አወጣለት። እሱም በተአምር ተረፈ።
በዚህ ምክንያት ቅዱስ ላሊበላ ለሦስት ቀናት አያይም አይሰማም ነበር። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ሰማይ ወስዶ ሰባቱን ሰማያት አሳየው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በመጀመሪያ አክሱም ከዚያም ኢየሩሳሌም ወስዶ በዚያ የነበሩትን ቅዱሳት መካናት አሳየው። ኢትዮጵያውያን ወደ ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉዞ ሲያደርጉ ይደርስባቸው የነበረውን መከራ እያሰበ ያዝን ነበርና በሮሐ ዐሥራ አንድ አብያተ ክርስቲያናትን ፈለፈለ።
ቅዱሱ አባት በሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በድፕሎማሲም የተዋጣለት ስለነበር በቱርኮች ተይዞ የነበረውና በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሡልጣን ገዳማችን እንዲመለስልን አድርጓል። ከውቅር አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ በርካታ ቤተ ክርስቲያኖችንም ሠርቷል፣ ንግሥናን ከክህነት፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አስተባብሮ የያዘው ቅዱስ ላሊበላ በዚች ሰኔ ፲፪ ቀን አርፏል።
🙏የቅዱሱ አባት የቅዱስ ላሊበላ ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን!!🙏
🌾#ቅዱስ_ሚካኤል
#ቅድስት_አፎምያን_ያዳነበት_ቀን🌾

📖ሰኔ ፲፪
ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፤ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ እርሷም በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ደገኛ ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ፳፱ ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ፳፩ የእመቤታችንንና ወር በገባ በ፲፪ የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡
ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፤ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ
መሥራት ቀጠለች፡፡ ባሏም ታሞ ሞቶ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡
ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኩሴ መስሎ አጋንንትን መነኮሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡ እርሷም "ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ" አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም "እኛማ በነግህ ጸልየናል?" አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን.." እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ
መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ ጎመን ዝሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ" አላት፡፡
ቅድስት አፎምያም "አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ አትጸልይ ያልከኝ፤ ጌታ ምጽዋት አበድር እመስዋዕት ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? እርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?" ብላ ሞገተችው። የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ ከላይ እንዳየነው በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን
ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት። ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደ አቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡
በሰኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድር ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም
አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡
ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና "የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?" በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡ ለጊዜው "በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም" ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ። ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእርሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ በመቀጠልም ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ሰይጣናዊ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት። ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን "ድረስልኝ" እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡
የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡
🙏የመልዐኩ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤትና በረከት፤ ጥበቃውና ምልጃው በእኛ የተዋሕድ ልጆች ላይ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን።🙏

✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
‹‹ #መቼም_የማይጾሙ ›› #እና ‹‹ #መቼም_የማይበሉ ››
በቤተክርስቲያናችን ትምህርት ‹‹መቼም የማይጾሙ›› ወይም ‹‹ሁሌም የሚበሉ›› የሚባሉ ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህም በጾምም ይሁን በፍስክ የሚበሉ ወይም የሚደረጉ ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል የሕያው እግዚአብሔርን ቃል መመገብ፣ ለእርሱና ለቅዱሳኑ ምስጋናን ማቅረብ፣ መልካም ነገርን መሰማት፤ ማየት፤ ማሰብ፣ መናገርና መሥራት ይገኙበታል፡፡ አንድ ሰው ሁልጊዜ የእግዚብሔርን ቃል መመገብ ምስጋናውንም ምግብ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ትዕዛዙንም ዘወትር
በመፈጸም ለአምላኩ ያለውን ፍቅር ሊገልጽ ይገባዋል፡፡ እነዚህ ጾም ሲገባ
ምግብን ተክተው የሚገቡ፣ ጾም ሲወጣ ደግሞ ሥጋን ተክተው የሚወጡ
አይደሉም፡፡ ሁል ጊዜ ሙሉ የሕይወት ዘመናችንንም ልናደርጋቸው የሚገቡ ናቸው እንጂ፡፡ ስለዚህ ነው ‹‹መቼም የማይጾሙ›› የተባሉት፡፡ ከእነዚህ መከልከል በራሱ ኃጢአት ነውና፡፡
በተመሳሳይ ‹‹መቼም የማይበሉ›› ወይም ‹‹ሁሌም የሚጾሙ›› የሚባሉ ነገሮችም አሉ፡፡ እነዚህም የኃጢአት ሥራዎችና ወደ ኃጢአትም የሚመሩ ነገሮች ናቸው፡፡ ክፉ ማየት፣ ክፉ መስማት፣ ክፉ ማሰብ፣ ክፉ መናገር፣ ክፉ ማድረግና እነዚህም የመሳሰሉት ነገሮች መቼም መበላት ወይም መደረግ የሌለባቸው ስለሆኑ ሁልጊዜ ከእነዚህ መጾም ያስፈልጋል፡፡ በስህተትም ከእነዚህ የቀመሰ ወይም የበላ ዋናውን ጾም ገድፏልና በቶሎ ወደ ንስሐ ሊቀርብ ይገባዋል፡፡ እነዚህ በጾም ወቅት የሚከለከሉ የጾም ወቅት ሲያልፍ ደግሞ የሚፈቀዱ አይደሉም፡፡ በማንኛውም ጊዜ የሚጾሙ ናቸው እንጂ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ለአባታችን አዳምና ለእናታችን ለሔዋን ‹‹መልካምና ክፉውን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብሉ (ዘፍ 2፡18›› ሲል መቼም ቢሆን አትብሉ ማለቱ እንደሆነ ያለ ነው፡፡
በጾም ወቅት በፈቃዳችን ሥጋችንን ስለምናደክም ‹‹መቼም የማይጾሙትን››
የበለጠ ልናደርግ፣ ‹‹መቼም ከማይበሉት›› ደግሞ የበለጠ ልንከለከል እንችል ይሆናል፡፡ ይህ ማለት ግን የጾም ወቅት ሲያልፍ ወደ ነበርንበት እንመለስ ማለት አይደለም፡፡ በጾም ወቅት የነበሩንን መልካም ነገሮች ከጾሙም በኋላ ይዘናቸው ልንቀጥል ይገባል እንጂ፡፡ በጾም ወቅት የተውናቸውን የሚጎዱን ነገሮች ደግሞ ከጾም በኋላ መልሰን ልንይዛቸው አይገባም፡፡ እንደተውናቸው ልንቀጥል ይገባል እንጂ፡፡ ሰለዚህ በጾም ወቅት ያለንን ተሞክሮ በማጽናት ‹‹ መቼም የማይጾሙትን›› መቼም አለመጾም፣ ‹‹መቼም የማይበሉትን›› ደግሞ መቼም አለመብላት ይገባናል፡፡ ይህንን ስናደርግ ‹‹የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥
የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል። የዚያን ጊዜ ትጠራለህ
እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ኢሳ 58፡8-9››
እንደተባለው ይሆንልናል፡፡

<< #የቀሳውስት_ጾም >> #ወይስ_የክርስቲያኖች_ሁሉ_ጾም?
የሐዋርያትን ጾም አንዳንዶች ‹‹የቀሳውስት ጾም›› ሲሉት ይሰማል፡፡ ይህም ከአሰያየሙ ጋር የተያያዘ ብዥታን በመጠቀም ላለመጾም የሚፈልጉ ወገኖች ያመጡት አስተሳሰብ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች ‹‹የሐዋርያት›› የሚለውን ቃል ብቻ በመውሰድ ጥንት ይህንን ጾም ሐዋርያት ብቻ እንጂ ሕዝቡ አልጾመውም፤ ዛሬ ደግሞ በሐዋርያት እግር የተተኩ ካህናት (ቄሶች) ናቸውና ጾሙም የእነርሱ ነው ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ብዙውን ጊዜም ቀሳውስት አበክረው ስለሚጾሙትና በሕዝቡም ዘንድ ይህ ስለሚታወቅም ጭምር ነው ይህ አስተሳሰብ የመጣው፡፡
ቤተክርስቲያን ግን ይህን የአዋጅ ጾም ጳጳስ፣ ቄስ/መነኩሴ፣ ዲያቆን፣ ሰንበት
ተማሪ ምዕመን ሳይል በ40 እና በ80 ቀን የተጠመቀና ዕድሜው ከሰባት ዓመት
በላይ የሆነው ሁሉ እንዲጾም አውጃለች፡፡ እኛም እነርሱን ተከትለን፣ በእነርሱ ሥርዓት በመመራት፣ በሐዋርያት ላይ ያደረው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብት
በእኛም ላይ እንዲያድርብን በየዓመቱ ጾመ ሐዋርያትን ሌሎችንም አጽዋማት
አክብረን መጾም እንደሚገባን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስኗል (ፍት.ነገ. 15፡
586)፡፡

#የሐዋርያት_ጾም_የእኛም_ጾም_ነው
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል›› እንዳለ (ኤፌ 2፡20) በሐዋርያት መሠረትነት ላይ ለታነጽን ለእኛ ለክርስቲያኖች የሐዋርያት ጾም የእኛም ጾም ነው፡፡ የሐዋርያት ጾም ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ስብከተ ወንጌልን ለመፈጸም በየሀገሩ ከመሰማራታቸው
በፊት በሁሉም ነገር እግዚአብሔር እንዲረዳቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ እኛም
የሐዋርያትን ጾም ስንጾም ሁል ጊዜ በንስሐ ታጥበን እና ነጽተን ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን ቀሪ ዘመናችንን እግዚአብሔር አምላክ እንዲባርክልንና ሰላምን ፍቅርን እና ጤናን እንዲሰጠን መጾም ይኖርብናል:: ይህ የሐዋርያት ጾም በሐዋርያት እግር የተተኩ የቤተክርስቲያንን አገልጋዮችም አገልግሎታቸውን እንዲባርክላቸውና ምዕመኑን ወደ መልካም ጎዳና እንዲመሩ የሚጸልዩበት ጾም ነው፡፡
በአጠቃላይ በሐዋርያት ጾም የሐዋርያት ክብራቸውና አገልግሎታቸው ይታሰባል፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን ነው፡፡ በዚህ ጾም ሐዋርያት ሁሉን ትተው ጌታን መከተላቸው፣ ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውና ስለ ቅዱስ ስሙ
በጽናትና በጥብዐት መከራ መቀበላቸው ይዘከራል፡፡ ምዕመናን እና ካህናትም
የቅዱሳን ሐዋርያትን መንፈሳዊ ተጋድሎ እያሰብን በዘመኑ ሁሉ በፍቅር በተዋበ
የመታዘዝ ፍርሃት የየራሳችንን መዳን እንፈጽም ዘንድ (ፊልጵ. 2፡12) ጾምን
በመጾም፣ ጸሎትን በመጸለይ ከእግዚአብሔርና በንፁህ ደሙ ከዋጃት ቅድስት ቤተክርስቲያን ጋር ያለንን ፍጹም አንድነት ልናጸና፣ ራሳችንን ከኃጢአት ከበደል አርቀን በመታዘዝ ጸጋ የጾምን በረከት ልንቀበልበት ይገባል፡፡ ለዚህም
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ሐዋርያት ጸሎት
ይርዳን። አሜን🙏
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
🌾#ዘሰኔ_ጎልጎታ🌾
⛪️ሰኔ ፳፩⛪️

https://www.tg-me.com/EOTC2921
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ።
🙏✞ልመናዋ ክብሯ የልጅዋም ቸርነት ከወዳጆቿ #ከተዋሕዶ_ልጆች ጋር ለዘለዓለሙ አድሮ ይኑር✞ አሜን፡፡✞🙏
🌾✞ አምላክን የወለደች በውስጥ በአፍአ ንጽሕት የምትሆን የብርሃን እናቱ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በሰኔ ፳፩ ቀን በመካነ ጎልጎታ ይኸውም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር በሚሆን እንዲህ ስትል የጸለየችው ጸሎት ይህ ነው፡፡
#ልጄ_ወጃዴ_ጌታዬ_አምላኬና_ንጉሤ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሰውን ለማዳን ስትል በፈቃድህ ከኔ ተወልደህ ጡቶቼንም ጠብተህ በግዕዘ ህጻናት ብታድግ ሰማይና ምድር አይችሉህም እኮን፡፡ የዓለም ዳርቻዎች አይወስኑህም ምድርም ልትሸከምህ አትችልም፤ ቀላያትና አብርሕትም ከጥልቀታቸው የተነሳ የክረምት ማዕበል በእልፍኝህ አይመሉም፤ ኃያላት መላእክትም ቢሆኑ ወደ አንተ ሊቀርቡ አይችሉም። አቤቱ እኔ እናትህና ገረድህ የምሆን በማኅፀኔ ፱ ወር ከ፭ ቀን ተሸክሜሃለሁና ጡቶቼንም ፬ ዓመት እየጠባህ አድገሀልና እለምንሃለሁ አማልድሀለሁ። ሄሮድስ በምቀኝነት ሊገድልህ በፈለገ ጊዜ አንተን በጀርባዬ አዝዬ አራት ዓመት ከአንዱ ሀገር ወደ አንዱ ሀገር ተሰድጃለሁና፤
#አቤቱ_ጌታዬና_አምላኬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ሆይ! ጸሎቴንና ልመናዬን ስማኝ፡፡
#አቤቱ_ማኅፀኔን ዓለም አድርገህ ፱ ወር ከ፭ ቀን የተሸከምኩህን፤ አቤቱ በቁርና በብድር ወራት በቤተልሔም ከኔ መወለድክን አስብ፡፡
#አቤቱ_ከአንተ_ጋር ከሀገር ወደ ሀገር መሰደዴን ስለአንተም የደረሰብኝን ጭንቅና መከራ ረሀብና ጥም አስብ። የምለምንህም ለደጋጎች ለጻድቃን ብቻ አይደለም በዚህ ዓለም ሳሉ ስሜን ለሚጠሩ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ በአማላጅነቴ ለሚተማመኑ ኃጥኣንም ነው እንጂ፤ አቤቱ ጸሎቴንና ልመናየዬን አስተውል ከአንተ ዘንድ የምሻውን የቃሌን ልመና ትሰማኝ ዘንድ የልቦናዬን ሀሳብ ትፈጽምልኝ ዘንድ።
#በዚህች_ዕለትና በዚህች ሰዓት ፲፪ የብርሃን መላእክትን ፪ የይቅርታ መላእክት ፳፬ የምህረት መላእክት ከእኔ ጋር ቁመው የልመናዬን ቃል ይፈጹሙልኝ ዘንድ ላክልኝ፤ ካንተ ዘንድ የምሻውን ቸርነትህን አታርቅብኝ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! የዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ከአንተ ጋር በነበረ በእግዚአብሔር አብ በባህርይ አባትህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ።
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ሰማይና ምድር ተራሮችና ኮረብቶች ሰውና መላእክት ፀሐይ ጨረቃና ከዋክብት ሳይፈጠሩ፤ ቀንና ሌሊት ሳይለዩ በነበረ በእግዚአብሔር ስምህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! የአብ የባሕርይ ሕይወቱ የሆነ ከአብ የተገኘ የአንተም የባሕርይ ሕይወትህ በሆነ ከአንተ ጋር የተካከለ በጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ከኮከብ መውጣት በፊት ከአንተ ጋር በነበረ አሁንም ያለ ለዘለዓለምም የሚኖር በአብና በመንፈስ ቅዱስ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ሰማይ ምድር ሊወስኑህ የማይቻላቸው አንተን ፱ወር ከ፭ ቀን በተሸከመችህ ማኅፀኔ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ።
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ፬ዓመት ወተታቸውን እየጠባሕ(እየተመገብህ) ባሳደጉህ ሁለቱ ጡቶቼ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ።
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! "እለ ብዙኃት አዕይንቲሆሙ" በተባሉ ፀወርተ መንበርህን በረዓድ እየተንቀጠቀጡ መንበርህን የሚሸከሙ አንተን ባዘለችህ ጀርባዬ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ከርጉም ሄሮድስ ፊት ሽሽትን ወደ ግብፅ አካባቢ እስክንደርስ ድረስ በደረሰብኝ ረኃብና ጥም ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ።
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! አንተን ይገድሉሃል እያልኩ ሳስብ ከዓይኖቼ እንደ ሰን ውሃ እየፈሰሱ በክብርት ሥጋህ ላይ በወረዱት ዕንባዎቼ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ምን ምን ሊቀርብህ የማይችል አንተን በሳሙ ከንፈሮቼ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ከአንተ ጋር ቃል ለቃል በተነጋገረ አንደበቴ ሱራፌል ኪሩቤል ድምፅህን ሰምተው ፀንተው ለመቆም የማይቻላቸው ጥዑማት ቃላትህን በሰሙ ጆሮቼ ፴፫ ዓመት ከአውራጃ ወደ አውራጃ ከአንተ ጋር በተመላለሱ እግሮቼ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ልብሱ እሳት ክዳኑ እሳት እየተባልክ የምትመሰገን አንተ እሳተ መለኮት ስትሆን በጨርቅ ተጠቅልለህ በተጣልክበት ዋሻ (በረት) ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! መልአከ ምክርህ በሆነ ቅዱስ ሚካኤል አንተን በክብር እወልድ ዘንድ የመወለድህንም ዜና(ምስራች) በነገረኝ #በቅዱስ_ገብርኤል ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! በምጥ የተያዙትን፡ ሴቶች ማህፀን ይፈታ ዘንድ ሥልጣን በሰጠኸው በቅዱስ ሩፋኤል ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! የሰላምና የደኀንነት መልአክ በሆነ በቅዱስ ዑራኤል ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ያዘኑትን የሚያረጋጋ በሰዳክያል መልአክ፤ ጻድቅና ትሑት በሆነ በሰላትያል መልአክ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ዙፋንህን በሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር እያሉ አኗኗርህን በማመስገን መንበርህን በሚያጥኑ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ተልእኮቻቸውን ለማፋጠን በሚፋጠኑ ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! እልፍ ሆነው በፊትህ በሚቆሙ እልፍ ሆነው በኋላህ በሚቆሙ እልፍ ሆነው በቀኝህ በሚቆሙ እልፍ ሆነው በግራህ በሚቆሙ መላእክት ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! በመንበርህ ዙሪያ በሚቆሙ እልፍ አእላፍት ትጉሃን መላእክት ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! በሰማይና በምድር ስፋታቸው በደመና ውስጥ በሚመላለሱ ረቂቃን መላእክት ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ተራሮችና ኮረብቶች ከመፈጠራቸው አስቀድሞ በፀሐይና በጨረቃ ውስጥ በሚመላለሱ ብርሃናውያን መላእክት ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! በእሳት ውስጥ በሚመላለሱ እሳታውያን መላእክት ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡

#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! በሰማይ ተድላ መንበርህ በእግርህ መረገጫ በሆነ በምድር ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ሀገርህ ብርሃነ መለኮትህ በተገለጠበት በደብረታቦር ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! በደብረ ዘይት በበአተ መንግስህ በደብረ ጽዮንም ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ሥርዓተ ጥምቀትን ለመመሥረት በትሕትና በቆምክበት በማዕከለ ዮርዳኖስ በቅዱስ መንፈስንና ከአንተም ዘንድ በወጣው ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ይቀጥላል✤✤✤
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! በተቸነከሩት እጆችህ እና እግሮችህ በቅዱስ ሥጋህና በክቡር ደምህን ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ለሰው ልጅ ስትል በተቀበልከው መከራና ሞትህ ቃል ኪዳን ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ሦስት ሌሊትና ሦስት መዓልት በከርሠ መቃብር ባደርክበት ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! አዳምን ከነልጆቹ ለማውጣት በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል በመውረድህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ሙስና መቃብርን አጥፍተህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይተህ በመነሳትህ በታላቅ ምስጋና ወደ ሰማይ በማረግህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ይህን ዓለም ለማሳለፍ ዳግመኛ በመምጣትህ ነበልባላዊ እሳት በሚጋርደህ ፍጹም በሆነ በአርያም ማደሪያህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡

#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! በማይሻረው መንግሥትህ በሚያልፈው ዘመንህ ጉድለት በሌለበት የደስታ ወንዝ ዝቅ ከፍ ዓፅንኖ በሌሉበት መንበርህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ጼቃና ሴቃ በተባሉ ስሞችህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ጠላትን በሚያሸንፍ በኢያኤል በጠላት በማይጠቃ በታዳኤል ስምህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ለመናገር በማይቻል በኀቡእ ስምህ ለመተርጎም በማይቻል በክሱት ስምህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ሳዶር አላዶር ዳናት አዴራ ሮዳስ በተባሉ በአምስቱ ቅንዋተ መስቀልህ ቃል ኪዳን ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ከኔ ጋር ቆመህ የልቦናዮን ሃሳብ ትፈጽምልኝ ዘንድ የተዘጉ በሮችን ተከፍተው የሞት ስልጣን ይወገድ ዘንድ የርኩሳን መናፍስት ሥልጣን ተሸሮ የጨለማ ኃይል ከሁሉ ቦታ እንደ ስም ቀልጦ እንደ ውሃ ፈሶ ይቀር ዘንድ ጣኦታትም ተደምስሰው የጣኦታትም ቦታና አዳራሽ ተመዝብረውና ተቀጥቅተው ይጠፋ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
🌾✞ ዳግመኛ በዚህ ጸሎት የሚተማመኑትን ከኃጢያት ማሠሪያ ሰማያዊ በሆነ በአባትህ ሥልጣን ማሕያዊ በሚሆን በአንተ ስልጣን የኃጢያት ሥር ተቆራርጦ የሚጥል፡፡ ነፍስን ከሥጋ የሚለይ ስሑል ነበልባላዊ በሆነ በመንፈስ ቅዱስ ስም ቃል የተፈቱ እና ነፃ የወጡ ይሆኑ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡
#ልጄ_ወዳጄ_ሆይ! ጸሎቴንና ልመናዬን ሰምተህ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ አለምንሃለሁ እማልድሃለሁ፡፡
🌾✞ ከመዓርና ከወተት ይልቅ ስሟ ጣፋጭ የሆነው አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ እመቤታችን ማርያም እንዲህ ብላ በጸለየች ጊዜ ምድር ተነዋወጠች ድንጋዮች (አለቶች) ተሰነጣጠቁ መቃብራትና የተዘጉ በሮችም ተከፈቱ፡፡
🌾✞ በዚህ ጊዜ ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ከአለቆቻቸው ጋር ከሰማይ ወርደው በግራ እና በቀኝ ቆሙ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ከፀሐይና ከጨረቃ ሰባት እጅ የሚያበሩ አራቱ ብርሃናት ከፊት እና ከኋላው እያበሩ እልፍ አእላፋት ወትእልፊት አእላፋት መላእክት በግራ በቀኝ ተሰልፈው ወረደ።
https://www.tg-me.com/EOTC2921
🌾✞ እመቤታችን ማርያም ይኸን ባየች ጊዜ ልጅዋን ወዳጅዋን በታላቅ ግርማ አየችው ፈጽሞም አደነቀች፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም እናቱ ማርያምን ይህ ያስደንቅሻልን? ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኀፀንሽ የተሸከምሺኝ አይደለምን? አላት፡፡ ቡርክት ማርያምም እንዲህ ስትል መለሰችለት ቀድሞ በዚህ አኳኋን አላየሁህም የሰውን ሥጋ ለብሰህ በማህፀኔ ተሸከምኩህ እንጂ ዛሬ ግን እጅግ በሚያስደነግጥና በሚያስፈራ በመለኮት ግርማ አየሁህ፡፡
🌾✞ ጌታችንም መለሰ እንዲህም አላት እናቴ ወላጄ ሆይ ፱ ወር ከ፭ ቀን በማህፀንሽ የተሸከምሽኝ በጀርባሽም ያዘልሽኝ ከመዓር ከስኳር ይልቅ የሚጣፍጥ ከበረድ የነፃ ከገነት ፈሳሽም ይልቅ የሚጣፍጥ ከበረድ የነፃ ከገነት ፈሳሽም ውሃም ንጹህ የሆነ ጡትሽን ያጠባሽኝ እናቴ ማርያም ሆይ! ምን ላደርግልሽ ትፈቅጃለሽ፤ እነሆ የለመንሽውን ሁሉ የምትሽውንም እፈጽምልሻለሁና፡፡
🌾✞ ቡርክት መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት ማርያም ለልጅዋ ለወዳጅዋ እንዲህ ስትል መለሰች፡- ልጄ ወዳጄ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ተስፋዬ አምባ መጠጊያዬ አንተ ነህ እምነቴም በአንተ ላይ ነው ገና በእናቴ ማህፀን ሳለሁ አንተ ጠበቅኸኝ አፀናኸኝም ለሁል ጊዜም መታሰቢያዬ እና አለኝታዬ አንተ ነህ በኋለኛውም ዘመን ትንቢቱ ሲፈጸም ሰዓቱ ሲደርስ በአንተ ፈቃድ በአባትህም ፈቃድ ማኀየዊ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ከእኔ ተወልደሃልና ዛሬ የአንደበቴንም ቃል ጸሎቴን እና ልመናዬን ስማኝ እኔ ወላጅ እናትህ ማርያም የምነግርህን ሁሉ አድምጥ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ በስሜ ቤተክርስትያን ስለሚሰሩ አንተ የብርሃን ማህደር አዘጋጅላቸው፡፡
🌾✞ አቤቱ ስለእኔ የታረዘውን ያለበሰ በሰው እጅ ያልተሰራውን ዕፁብ ድንቅ የሆነውን የማይጠፋውን የማያረጅውን ዕውነተኛውን ልብስ አልብሰው፡፡
🌾✞ አቤቱ በእኔ ስም በሽተኞችን የጎበኘ (የጠየቀ) በቸርነትህ እና በይቅርታህ ጎብኘው፡፡
🌾✞ አቤቱ ስለስሜም ብሎ ለተራበ ያበላውን የሕይወት እንጀራ አብላው፤ ሰማያዊ በሆነ ማዕድህም አስቀምጠው፣ ለተጠማ ያጠጣውንም በዔዶም ገነት ከሚፈሰው የሕይወት ውሃ አጠጣው፡፡
🌾✞ አቤቱ ስለኔ ስም ያዘነውን ያረጋጋ ነፍሱ ከሥጋው በምትለይበት ጊዜ አጽናናው ያዘነውንና የተከዘውንም ያስደስተ እና ያጽናናው ስለስሜ ብለህ አስደስተው እድል ፈንታውንም በዚህ ዓለም ሳሉ አንተን በምግባር በሃይማኖት ደስ ካሰኙህ ከቅዱሳን ጋር አድርገው፡፡
🌾✞ አቤቱ ምስጋናዬን የሚናገሩትን መጸሐፍት የጻፈ ያጻፈ በእኔ ስምም የጸለየ ሰማያዊ በሆነ ዓምደ ብርሃን ስሙን ጻፈው በጸሎቱ ተማምኖ ይህን መጽሐፍ በአንገቱ ያነገተ በሰው ልብ ያልታሰበውን ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን መልካሙን ዋጋ ክፈለው፡፡
🌾✞ አቤቱ በስሜ የሚያምኑ ሁሉ ከሲዖል ሞት ነፃ የወጡ ይሆኑ ዘንድ አለምንሃለሁ እማልድሃለሁ፡፡ አስቦ መታሰቢያዬን ያደረገ (ዝክሬን የዘከረ) በበዓሌም ቀን በምመሰገንበት ምስጋና የሚያመሰግኑ እና የሚዘምሩትን አቤቱ ዝማሬ መላእክትን አሰማቸው፡፡
🌾✞ ጌታችንም፡- ይሁን እንደወደድሽ ይደረግልሽ አላት፡፡ በአንቺ ስም ቤተክርስትያን ያሳነፀ የብርሃን ቦታ፤ አዘጋጅለታለሁ፤ በመንግስተ ሰማያትም ንፁህ ማደሪያ እሰጠዋለሁ፡፡ ከባሕርይ አባቴ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቴ ከመንፈስ ቅዱስ ፊት አቀርበዋለሁ፡፡ የታመመን በስምሽ የጎበኘ ታሞ በአልጋ ላይ በተኛ ጊዜ አጎበኘዋለሁ፡፡ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም በሞት በተለየ ጊዜም መሪር የሆነ የሞት ጽዋዓ አላጠጣውም ወደ መንግሥተ ሰማያት እስኪገባ ድረስ አልለየውም ርኩሳን መናፍስትም በተከራከሩት ጊዜ እኔ ጠበቃ እሆነዋለሁ፡፡ በችግሩ ጊዜም እድርስለታለሁ፡፡
🌾✞ ዳግመኛም በስምሽ ለታረዘ (ለተራቆተ) ያለበሰ በሰው እጅ ልተፈተለ እና ያልተሰራ ኀብሩ ዕጹብ ድንቅ የሆነ የሕይወት ልብስ፤ አለብሰዋለሁ፡፡ የማይጠፋ የማይጠወልግ የሕይወት አክሊልም አቀዳጀዋለሁ ስለ አንቺም ብሎ ከዕለት ጉርሱ ለተራበ ያበላ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ የሆነ የሕይወት እንጀራ አበላዋለሁ ለተጠማ ያጠጣ ከመዓር ከስኳር የሚጣፍጥ ወተት እጅግ ነጭ የሆነ ከዔዶም ገነት ከሚፈሰው የሕይወት ውሃ አጠጣዋለሁ፡፡
#ይቀጥላል✤✤✤
🌾✞ በስምሽ ያዘነውን የተከዘውን ያስደሰተ ስለ ስምሽ ብዬ በሰማያዊ አባቴ ፊት ደስ አሰኘዋለሁ፡፡ የምስጋና መጽሐፍሽን የጻፈ ያጻፈ እኔ በሕይወት መፅሐፍ ስሙን እጽፈዋለሁ ስለ አንቺ መብራት ዘይት ዕጣንም ለቤተክርስቲያን መብዓ የሰጠ እኔ ከፀሐይ ከጨረቃ ይልቅ ሰባት እጅ የሚያበራ መብራት በመንግሥተ ሰማያት አበራለታለሁ፡፡ ንፁህ መዓዛ ዕጣንም የሰጠ መዓዛ ሽታውን እንደ መላእክት መዓዛ አደርገዋለሁ፡፡
🌾✞ ሴት ወይንም ወንድ ልጁን በአንቺ ስም የሰየመውን በምድራውያን ሰዎች እና በሰማያውያን መላእክት ዘንድ ከፍ ያለ ግርማ ሞገስ ያገኛል፡፡ ይህ መጽሐፍ ባለበት ቦታ ሁሉ እስከ ዘለዓለም ድረስ ምሕረት ቸርነት ተድላ ደስታ ጥጋብ በረከት ይሁን፡፡
🌾✞ ስምሽ በተጠራበት ስእልሽም ባለበት መታሰቢያሽም በተደረገበት በስምሽም በሚጸለይበት ቦታ ሁሉ እኩያን አጋንንት አይቀርቡም በረቂቅ ሰውን የሚያሰቃዩ ጸሊማን ዛር ውላጆችም ይርቃሉ፡፡ ይህን መጽሐፍ በክብር ይዞ ለሚጸልይ የጨለማ ኃይል አይጋርደውም ርኩሳን መናፍስትም የቀትር አጋንንትም ሊቀርቡት አይችሉም፡፡
🌾✞ በሌሊት በህልም የሚያስደነግጡ በመዓልት በእሾህ መውጋት ቢሆን በእንቅፋት የሚመሰሉ በምግብ ማሳነቅ ወይም በውሃ ትንታ የሚመሰሉ በስካር እና በቁጣ የሚመሰሉ ልብን በመፋቅ በቃር የሚመሰሉ በጥርስ በሽታ አፍን በማምረር በራስ ምታት እና በዓይን ህመም ወይም በሆድ ቁርጠት የሚመሰሉ በንዳድ (በወባ) በማነቅ የሚመሰሉ በባህር እና በየብስ በእንጨት በድንጋይ የሚመሰሉ በእሳት እና በዲን የሚመሰሉ በፍቅር እና በሰላም ወይም በጠብ የሚመሰሉ በአራዊት እና በአዕዋፋትም የሚመሰሉ በፀሀይ ሐሩር ወይም ቁርና በአመዳይ በውርጭ በነፋስ ንውጽውጽታ ኃይል ወይም በውሻ መንከስም የሚመስሉ በእፍኝት መንደፍም ቢሆን በእሳት ማቃጠል የሚመሰሉ በሌሊት ጨለማ በቀን ብርሃንም የሚመሰሉ እነዚህ ሁሉ አይቀርቡም፡፡
🌾✞ ይህን መፅሐፍ በንጹህ ህሊና፤ በቅን ልቦና የያዘ የቡዳ ዓይን አያስፈራውም ይህ መጽሐፍ በምትደገምበት ቦታ ሁሉ ሰላቢዎች (ሟርተኞች) መድኃኒተኞች፣ የሌሊትና የቀን የዱር አራዊቶች የሚታየውም የማይታየውም በረድ ከብኩባ አንበጣም ቢሆን ሊቀርቡ አይችሉም፡፡ በሬም ላምም ቢታመሙ ይህን ጸሎት ቢደግሙላቸው ክፉ በሽታ አይነካቸውም፡፡
🌾✞ ይህችን መጽሐፍ በንጽህና የሚይዝ ሁሉ ከደዌው አድነዋለሁ፡፡ ከሚያስጨንቅ ችግርም እሠውረዋለሁ ኃጥአትም ቢኖርበትም ይሠረይታል ደዌው ለሞት የሚያዘዝ ቢሆን እኔ አስቀድሜ መላእክተ ብርሃን እልክለታለሁ ነፍሱንም በክብር ተቀብለው ወደ እኔ ያመጧታል፡፡ ከሦስተኛው ሰማይም በደረሰ ጊዜ መናፍስተ ርኩሳን አይቃወሙትም ጸዋጋን አጋንንት ከእርሱ ጋር አይቆሙም ሊቀርቡትም አይችሉም፡፡
🌾✞ ዳግመኛም እኔ በዚያን አስፈሪ በሆነ ሰዓት እረዳት እሆነዋለሁ እኔ እና የባሕይ አባቴ አብ የባሕርይ ሕይወቴ የእውነት መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ወደ እርሱ እንመጣለን፡፡ አስራ ሁለቱም ሊቃነ መላእክትም ከዝርግፍ ወርቅ ጋር የወርቅ ጥናቸውን ይዘው ይመጣሉ፡፡ ቀስተ ደመና በመሰለ በናርዱ ሽቱ መብረቅም በመሰለ የእሳት ሰረገላ ሆነን ይህን መጽሐፈ ጸሎት የያዘን ሰው እንቀበለው ዘንድ እስከ አምስተኛው ሰማይ ድረስ እንወርዳለን በደረቴ አቅፌ ባህረ እሳትን አሻግረዋለሁ፡፡
🌾✞ ወደ መንበረ መንግሥቴም አቀርበዋለሁ፡፡ መንፈሳውያን የመላዕክት አለቆችም በአዩት ጊዜ ደስ ይላቸዋል፡፡ ይህን ጸሎት በንጽህና እየፀለየ የያዘን ሰው እያሸበሸቡ ይቀበሉታል፡፡ በቅዱስ ወንጌል የተነገረውን አልሰማሽምን መቶ በጎች ያሉት ሰው ከመቶው አንዷ ብትጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጣፋችውን በግ ሊፈልግ እንደሄደ በአገኛትም ጊዜ በትከሻው ተሸክሞ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ በጎች ይልቅ ጠፍታ በተገኘችው በግ ደስ እንደሚለው ባልንጀሮቹን እና ጎረቤቶቹን ጠርቶ የጠፋችው በጌ ተገኝታለች እና ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል፡፡
🌾✞ እውነት እውነት እላችኋለሁ ንስሐ ከማይገቡ ፃድቃን ይልቅ ንሰሐ በሚገባ አንድ ኃጥአ ሰው በሰማይ ታላቅ ደስታ እንደሚደረግ፡፡ ሁለተኛም ይኸን መጽሐፍ የሚደግም እና በሚይዝ ሰው ሰማያውያን መላእክት ደስ ይሰኛሉ፡፡ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ነፈሱ ከሥጋው ተለይታ በምትወጣበት ሰዓት ደብረ መቅደሴን አወርሰዋለሁ፡፡ ከባሕርይ አባቴ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቴ ከመንፈስ ቅዱስም ዘንድ አቀርበዋለሁ፡፡
🌾✞ ይህ መጽሐፍ ካለበት ቦታ ይቅርታ ቸርነት ምህረት ጥጋብ ተድላ ደስታ እስከ ዘለዓለም ድረስ ይሆናል፡፡ በእውነት ይህ ጸሎት በተደገመበት እና በተነበበበት ቦታ ንዳድ እንቅጥቅጥ በያይነቱ በሽታ ሁሉ አይቀርቡም፡፡ ይህን የጸሎት መጽሐፍ በንጹህ የያዘ እርሱን ልጆቹን ገንዘቡን ሀብቱን እባርካለሁ፡፡
🌾✞ በዚህ መጽሐፍ አምኖ በንጹህ ልቦና በቀና ሃይማኖት ያለጥርጥር በማየ ጸሎቱ የተጠመቀ የጠጣ በቤቱ (በስራው ቦታ) የረጨ እኔ ጸሎቱን እሰማዋለሁ እንደ ልቡም ፈቃድ እፈጽምለታለሁ፡፡ ሚካኤልና ገብርኤልም ፈቃዱን ይፈጽሙለት ዘንድ ዘወትር ወደ እርሱ ይመጣሉ፡፡
🌾✞ ይህን መጽሐፍ በንጽህና የያዘ ሁሉ የሰራዊተ መላእክት አለቆች ዘወትር እየመጡ ይጎበኙታል፡፡ እናቴ ማርያም ሆይ በሰማይና በምድር ይህን ሁሉ ቃል ኪዳን (አስራት) ሰጠሁሽ፡፡
🌾✞ ቡርክት መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት እመቤታችንም፡- ልጄ ወዳጄ ሆይ ይህ የምትለኝ ሁሉ እውነት ነውን አለችው፡፡ ጌታም መለሰ እንዲህም አላት፡- እናቴ ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር አባቴ በክርስቶስ ስሜ በዕውነት መንፈስ በጸቅሊጦስ እውነት እንደሆነ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ አላት፡፡ መልአከ ምክሬ በሆነው በሚካኤል፣ የመወለዴን ዜና በአበሰረሽ በገብርኤል ቃል ኪዳን ባሁልሽ አላት ክንፋቸው ስድስት በሆኑ ምሉዓነ አዕይንት በሆኑ መንበሬን በሚሸከሙ ዐራቱ እንስሳት (ኪሩቤል) ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ አኗኗሬን በአንድነት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ እያመሰገኑ መንበሬን በሚያጥኑ በሃያ ዐራቱ ካህናተ ሰማይ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ እልፍ ሆነው በቀኝ እልፍ ሆነው በግራ እልፍ ሆነው በኋላ እልፍ ሆነው በፊቴ በሚቆሙ መላእክት ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ በእልፍ አእላፋት ብዙ የብዙ ብዙ በሚሆኑ ትጉሃን መላእክት ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡
https://www.tg-me.com/EOTC2921
🌾✞ የፍጥረት ተቀዳሚ በሆነ በአዳምና በልጆቹም በአቤልና በሴት በቃይናን በመላልኤል ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ በኄኖክና በኄኖስ በያሬድ እና በማቱሳላም ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ዳግመኛም ምድርን በንፍር ውሃ እንዳላጠፋት ኪዳነ ሰማይ ወምድር በሰጠሁት በባሪያዬ በኖህ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ የትዕዛዜ ጠባቂ በኩር በሆነ በሴም ምሳሌየ በሆነ በመልከ ጼዴቅ ካህን ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ስለ ወዳጄ ስለ አብርሃም ስለ ባለሟሌ ስለ ይስሐቅ ዘሩን በአስራ ሁለቱ ነገድ ከፍዬ ስለ አከበርኩት ስለ ያዕቆብ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ንጹሃን ቅዱሳን በሆኑ በቀደሙ አባቶች በይሁዳ እና በፋሬስ በዮሴፍ እና ብንያም በሌዊ እና በይሳኮር በአስራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ቁጥር ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ጸሐፍተ ትዕዛዝ በሆኑ በሄኖክ እና በኤልያስ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡
#ይቀጥላል✤✤✤
🌾✞ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በተቀመጥኩባት ንጽህት በሆነች ማኀፀንሽ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ጣፋጭቱ ከመዓር ከስኳር የሚጥመው ንጹሕነቱ ከኤዶም ምንጭ ውሃ ንጣቱ ከበረዶ እና ከወተት የበለጠውን ወተት መግበው ባሳደጉኝ ጡቶችሽ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ትእዛዜን እና ሕጌን ባስተማሩ አስራ አምስቱ ነብያት ሄሮድስ ባስገደላቸው አስራ አራት እልፍ የቤተልሔም ሕፃናት ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ የወንጌልን መንግስት ለዓለም በሰበኩ ሐዋርያት ስለ እኔ ነፍሳቸውን ለሞት አሳልፈው ስለ ሰጡ ሰባ ሁለቱ አርድእት ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ዙፋኔ በተዘጋጀባት ሉዓላዊት ሰማይ የእግሬ መረገጫ በሆነች ታህታዊት ምድር ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ነደ እሳት በሆነ የእሳት መጋረጃዬ ፍጹም ማደሪያዬ በሆነ በአርያም ሰማይ ቃል ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡
🌾✞ በተሰቀልኩበት ዕፀ መስቀል እጅና እግሬ በተቸነከረበት ቅኖት (ችንካር) በጦር በተወጋው ጎኔ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ በዕለተ ዓርብ በፈሰሰው ደሜ በሕመሜ እና ሞቴ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊትም በከርሰ መቃብር ባደርኩበት ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ከመቃብር ወጥቼ አዳምን ከነ ልጆቹ ከሲኦል ለማውጣት ወደ ሲኦል በመውረዴ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቼ ሙስናን መቃብርን አጥፍቼ በመነሳቴ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ በማረጌ ዳግመኛው ዓለምን ለማሳለፍ በታላቅ ምስጋና በምመጣበት ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ክቡር በሆነ ደሜ ቅዱስ በሆነ ስጋዬም ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ሰማያዊት በሆነች በኢየሩሳሌም ሀገሬ በክቡር በምስጋና በተጌጠች በጽዮን ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ የሙሽራ አምሳል በሆነች በቅድስት ቤተ ክርስትያን ከዕለታት መርጬ የተወለድኩባት የተጠመቅኩባት ለሰው፡ ልጅ ድኀንነትን የምታስገኝ ትንሳኤዬንም በገለጥኩባት ሰንበተ ክርስትያን ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡
🌾✞ በደብረ ዘይት በተቀደሰውም በጽዮን በደብረ መንግስቴ በመቃብሬ በጎልጎታ ንጹህ ብሩሕ በሆነ ደም ግባትሽ ንጹሐት ክቡራት በሆኑ ልብሾችሽ በዚህ ሁሉ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ አናቴ ድንግል ማርያም ሆይ የሰጠሁሽን ቃል ኪዳን እንዳልነሳሽ እማንዬ ብዬ በራሴ ማልሁልሽ፡፡ በአንቺ ስምም የሚቀደስበትን ቦታ እኔ እባርካለሁ፡፡ እንደ አቤልም መሥዋዕት እቀበለዋለሁ፡፡
🌾✞ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት እመቤታችንም መለሰች እንዲህም አለች፡- እንተ ብሩክ ነህ ሰማያዊ አባትህም ብሩክ ነው፣ የባሕርይ ሕይወትህ መንፈስ ቅዱስም የተባረከ ነው፡፡ ይህን ሁሉ በቸርነትህ ስለሰጠኸኝ አቤቱ ለአንተ ምስጋና ይገባል፣ ለቸር አባትህም ምስጋና ይገባል ማኀየዊ ለሚሆን ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
🌾✞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናቱ ይህን ነግሯት ከፈጸመ በኋላ ሰላምታ ሰጥቷት በታላቅ ምስጋና ወደ ሠማይ ዐረገ እርሷም እግዚአብሔርን እያመሠገነች ወደ ቤቷ ተመለሠች እንዲህ እያለች፡- አቤቱ አንተ የተመሠገንህ ነህ ስምህም የተመሠገነ ነው፣ የመንግሥትህም ስም ይባረክ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ጽንዕ ለአንተ ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
#ተፈጸመ ✞✞✞
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከወዳጅ ልጅሽ(ከጌታ አምላክሽ) በተሠጠሽ በዚህ ቃል ኪዳን ከክፋ ነገር ሁሉ ጠብቀሽ በልጅሽ በክርስቶስ ስጋና ደም ታትመን ዘላለማዊ ሕይወት ወዳለበት ተስፋ መንግስተ ሰማያት አውርሽን፤ አድኚንም አሜን፡፡
🙏✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!✞🙏

✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯‌‌
2025/07/09 22:18:05
Back to Top
HTML Embed Code: