Telegram Web Link
#መድኀኔዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤
ዘሰተይከ በእንቲአየ ከርቤ ወሐሞተ፤
በሞተ ዚአከ ከመ ትቅትል ሞተ፡፡
"ፈጣሪዬ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ሆይ፤
በሞትህ ሞትን ታጠፋው ዘንድ ከርቤ የተቀላቀለበትን መራራ ሐሞትን ስለኔ ሕይወት የጠጣህ የአቀረብኳትን አነስተኛ የምስጋና መባዕ በቸርነትህ ተቀበል፡፡
#መድኀኔዓለም_ሆይ
ክቡር ልዑል ለሚኾን ጉሮሮህ ሰላም እላለሁ፡፡
በገመድ እየሳቡ ለጎተቱት ክሳድህም ሰላም እላለሁ፡፡
#ፈጣሪዬ_ክርስቶስ_ሆይ
በቀራንዮ አደባባይ የተሰቀልከው ለሰው ልጅ ድኅነት እንደመኾኑ መጠን፤
ስለ እናትህ ስለ ድንግል ማርያም ብለህ ምሬሃለሁ ይቅር ብዬሃለሁ በለኝ፤
ከአንተ በቀር ቸር ይቅር ባይ የለምና፡፡
👍1
🌿🌿🌿 #ሆሳዕና 🌿🌿🌿
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15

የዘንባባ ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

​​⛪️⛪️ ሆሣዕና ⛪️⛪️

1⃣🌿ሆሣዕና ማለት ምን ማለት ነው?
#መልስ🌿ሆሣዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው።
2⃣🌿 በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሠራችን የምን ምሳሌ ነው?
#መልስ🌿1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፦ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ።
2. ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3. ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4. ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስሐ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው።
3⃣🌿 ጌታችን በዕለተ ሆሣዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም?
#መልስ🌿ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ " አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።" ዘካ. 9፥9

🌿በአህያ መቀመጡ፦
•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል።
•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው የሚሄዱት፤ በቀላሉ ትወጣበታለህ፤ በቀላሉ ትይዘዋለህ፤ እንደፈለክም ታዘዋለህ፤
4⃣🌿ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘንባባ የመነጠፉ ምሥጢር የምን ምሳሌ ነው?
#መልስ🌿 1. ዘንባባ፡- ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃም ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግኗል።
2. ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል፤ የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
3. ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው፤ የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4. ዘንባባ የደስታ መግለጫ ነው፤ አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
5. ዘንባባ እሾሃማ ነው፤ አንተ ሕያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
6. ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ። ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው።
5⃣🌿 ሕዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት ዓይነት ቅጠል አነጠፉለት ምን ና ምን?
#መልስ🌿 ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፦ ለክብሩ መግለጫ ነው።
ሌሎችም ሦስት ዓይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤ የቴመር ዛፍ፤ የወይራ ዛፍ አነጠፉለት።
6⃣🌿 ትልቅዋ አህያ በምን ትመሰላለች ውርንጭላዋስ?
#መልስ🌿 ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ናት።
1. ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ሕገ ኦሪትም የተለመደች ሕግ ናትና።
2. የእስራኤል ምሳሌ ነው፦ ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ሕግ ለመፈጸም በሕግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው።
3. የአዳም ምሳሌ ነው፦ አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና፤
🌿ውርንጭላዋ
1. በሕገ ወንጌል ትመሰላለች፦ ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠረታት የሠራት አዲስዋ ሕግ ናትና።
2. በአህዛብ ትመሰላለች፦ ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ሕግህን የመቀበል የለመደ አይደሉም። ለሕግህ አዲስ ናቸውና።
3. የእመቤታችን ምሳሌ ናት፦ የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰላለች። እመቤታችን ድኅነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና።
7⃣🌿 አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል የሚለው ኃይለ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል???
#መልስ🌿 ዘካ. 9፥9
8⃣🌿 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ያልታሠሩ አህዮች እያሉ ለምን የታሠሩትን መረጠ?
#መልስ🌿አህዮቹ የታሠሩት ሌባ ሰርቆ ነው ያሠራቸው። ወንበዴ ሰርቆ ነው ያሠራቸው አህዮቹ ለጌታ ውለታ ሠርተዋል። ጌታ ሲወለድ አሙቀውታልና ለጌታ ውለታ ልንመልስ ያልቻልነው እኛ ሰዎች ብቻ ነን። የታሠሩት እዲፈቱ የመረጠበት ምሥጥር፦ እኔ ከኃጢአታችሁ ልፈታችሁ የመጣሁ ነኝ ሲል ነው። ወንበዴው አህዮቹን ሰርቆ በመንደር እንዳሠራቸው ዲያብሎስም ለሰው ልጅ በኃጢአት ሰንሰለት ከሲዖል መንደር አስሯቸው ነበርና። ሐዋርያቱ ሲልካቸው ምን ታደርጋላችሁ የሚላችሁ ሰው ቢኖር ጌታቸው ይሻቸዋል በልዋቸው አላቸው። የፈጠራቸው እሱ ነውና።
🌿🌿🌿🌿🌿🌱🌿🌿🌿🌿🌿
መልካም የሆሳዕና በዓል ይሁንልን።
ሆሳዕና በኣርያም!
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
👍1
#ጌታችን_መድሃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_በመስቀል_የተጓዛቸው_ጉዞዎች

☞✞ ጌታችንን ወደቀራኒዮ ሲወስዱት የተነሱብት ቦታ ገበታ/ገበጣ/ ይባላል፡፡ ይህ የጲላጦስ አደባባይ ነው፡፡ከዚህ ተነስቶ መስቀሉን ተሸክሞ እስከ ቀራኒዮ የደረሰበት ፍኖተ መስቀል ይባላል፡፡
#1ኛ_ምዕራፍ_የጲላጦስ_አደባባይ_ገበታ(ገበጣ)፦ ጌታችን ለፍርድ ከጲላጦስ የቀረበበት ምዕራፍ ነው ስሙም በዕብራይስጥ ገበታ በግሪክ ሊቶስትራ ይባላል፡፡
#2ኛ_ምዕራፍ_ጌታ_የተገረፈበት፦ ከሊቶስትራ ወደ ጌቴሴማኒ የሚወስደውን መንገድ ተሸግሮ ጲላጦስ ጌታን ገርፎ ይህ ሰው ያውላችሁ ያለበት ቦታ ነው የቦታው ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌታ የተገረፈበት ይባላል፡፡ ላቲኖች ገዳም ሰርተውበታል፡፡
#3ኛ_ምዕራፍ_ጌታ_መጀመሪያ_የወደቀበት_ቦታ፦ የቀድሞውን ስፍራ ወደግራ ትቶ ወደ ምዕራብ የሚወስደውን መንገድ ይዞ በደማስቆ በር መግቢያ የአርመን ቤተ ክርስቲያን ያለበት በሩ በሩ በብረት የታጠረ ትንሽ ክፍል ነው፡፡ ስሙም ጌታ የወደቀበት ቦታ ይባላል፡፡
#4ኛ_ምእራፍ_እመቤታችን_እያለቀሰች_ልጇን_ያገኘችበት_ቦታ፦ ከ3ኛ ምዕራፍ ትንሽ ዝቅ ብሎ ከአርመን ገዳም በስተግራ ካለው ማዕዘን ሲደርሱእናቱ ድንግል ማርያም እያለቀሰች ከላጇ ጋር የተገናኘችበት ቦታ ነው፡፡
#5ኛ_ምዕራፍ_ቀሬናዊ_ስምዖን_የጌታን_መስቀል_የተሸከመበት_ቦታ፦ ከ4ኛው ምዕራፍ 20ሜትር ያህል ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከተጓዙ በኋላ ወደቀኝ የሚታጠፈው መንገድ ነው፡፡ በዚህ ቦታ ላይ ስምዖን ቀሬናዊ የሚባል ሰው ከእርሻ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ወታደሮች አግኝተውት አስገድደው እየጎተቱ ወስደው የጌታን መስቀል ያሸከሙበት ቦታ ነው፡፡ በዚህ ቦታ ላቲኖች ትንሽ መቅደስ ሰርተውበታል የሰምዖን መቅደስ ይባላል፡፡ይህ ስምዖን የተባለ የእስክንድሮስ እና የሩፎን አባት ነው ማር፡5፥21 ፣ ሮሜ፡16፥13 የእነዚህ ልጆች ቁጥር ከሰባ ሁለቱ አርድዕት ነው፡፡
#6ኛ_ምዕራፍ_ቤሮና/ስራጵታ/፦ በመሐረብ የጌታን ፊት የጠረገችበት ቦታ
ቤሮና የምትባል ሴት ከግፋቱ ጽናትና ከመስቀሉ ክብደት (እርጥብስለሆነ) የተነሳ ፊቱ የደም ወዝ አልብሶ ስታየው አዝና ፊቱን በነጭ መሐረብ ስትጠርግለት ወድያዉኑ አምላክነቱንየሚገልጥ ለበጎ ስራዋም ተስፋ የሚሰጥ ፣ሐይማኖቷን የሚያበረታታ የፊቱ መልክ እንዳለ በመሐረቡ ላይ ተገኘ፡፡ እሷም በዚህ ምክንያት እምነቷ እጅግ የጸና ሆነ፡፡ በዚህ ቦታ ላይ ግሪኮች መቅደስ ሰርተውበታል፣ በየሳምንቱ አርብ አርብ ይከፈታል፡፡
#7ኛ_ምዕራፍ_የጎልጎታ_መቃረቢያ፦ ከ6ኛ ምዕራፍ በግምት እንደ 100ሜ ያህል ተጉዞ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በሚወስደው መንገድ ከሰሜን አቅጣጫ መጥቶ ወደ ጽርሐ ጽዮን በሚያሳልፈው መካከለኛ መንገድ ላይ ነው፡፡ በጌታች ዘመን የከተማው መጨረሻ የምዕራቡ በር ይህ ነበር ይባላል፡፡ በዚህ ቦታ ትንሽ መቅደስ አለበት መቅደሱ የላቲኖች ነው ጥንት የከተማው በር ይባል ነበር፡፡
#8ኛ_ምዕራፍ_የጌታችንን_ስቃይ_ሴቶች_አይተው_ያለቀሱበት_ቦታ፦ ከ7ኛ ምዕራፍ 15ሜ ያህል ወደ ላይ ወጣ ብሎ የገኛል ጌታ መስቀሉን ተሸክሞ መከራ መስቀልን እየተቀበለ ሲሄድ ሴቶች እይተው እያለቀሱ ሲከተሉት ወደ አነርሱ መለስ ብሎ እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ለኔ አታልቅሱ ለራሳችሁ አልቅሱ እንጅ ያለበት ቦታ ነው ሉቃ፡23፥27 ይህን ማለቱ ከ40 አመት በኋላ የሚመጣባቸውን መከራ በትንቢት ሲነግራቸው ነው! በዚህ ቦታ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የሆኑ መነኩሳት መኖሪያ አራት ቤቶች አሉ፡፡
#9ኛ_ምዕራፍ_መስቀል_ይዞ_የወደቀበት_ቦታ፦ አንድ የቆመ የድንጋይ አምድ አለበት በዚህ ቦታ ጌታ መስቀል ይዞ ወድቆበታል ፡፡ ይህ ቦታበወደ ጎልጎታ መውጫ በር ነው ቦታው የኢትዮጵያ ገዳማት መግቢያ ነው፡፡
#10ኛ_ምዕራፍ_የጌታችንን_ልብሱን_የገፈፉበት_ቦታ
#11ኛ_ምዕራፍ_ጌታችንን_የቸነከሩበት_ቦታ፦ ጌታችንን ልብሱን ገፈው እርቃኑን ካስቀሩ በኋላ እጆቹንና እግሮቹን በምስማር የቸነከሩበት ቦታ ነው፡፡
#12ኛ_ምዕራፍ_መስቀሉን_የቆሙበት_ቦታ፦ ጌታችንን መስቀል ላይ ከቸነከሩት በኋላ መስቀሉን ያቆሙበት ቦታ ነው፡፡
#13ኛ_ምዕራፍ_ቅዱስ_ስጋውን_ከመስቀል_ላይ_ያወረዱበት_ቦታ፦ ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ኒቆድሞስ ጌታችንን ከመስቀሉ ያወርዱበትና ያሳረፉበት ቦታ ነው፡፡
#14ኛ_ምዕራፍ_ቅዱስ_ስጋውን_የገነዙበት_ቦታ፦ ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ኒቆድሞስ ጌታችንን ስጋ የገነዙበት ቦታ ነው፡፡
#15ኛ_ምዕራፍ_ቅዱስ_ስጋው_የተቀበረበት_ቦታ፦ ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ኒቆድሞስ ጌታችንን ስጋውን በአድስ መቃብር ያሳረፉበት ቦታ ነው፡፡ መቃብሯ ቅዱስ ዮሴፍ ለራሱ ብሎ ከአልት ጠርቦ አዘጋጅቷት የነበረች አድስ መቃብር ናት፡፡

•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
#ስርዓተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘሰሙነ_ሕማማት
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••

ከሁሉም በፊት የሰዓቱ ተረኛ አገልጋይ ቃጭል እየመታ ሦስት ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ይዞራል። የሰባት ቀን ውዳሴ ማርያም ፣ አንቀጸ ብርሃንና መዝሙረ ዳዊት በሙሉ ይጸለያል። የእለቱ ተረኛ መምህር (መሪጌታ) የእለቱን ድጓ ይቃኛል: ድጓው ከአራቱ ወንጌላት ምንባብ ጋር እንዲስማማ ሆኖ የተሰራ ነው። የተቀኘው ድጓ እየተቀባበለ እየተዜመ ይሰገዳል: ሶስት ጊዜ እየተመላለሰ ይባላል።

#የወንጌላቱ_ድጓ_እንደሚከተለው_ነው:-

📖 #በማቴዎስ ወንጌል:-
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ስምዕዎኬ ለእግዚእነ ኲልክሙ አብያተ ከርስቲያናት ከመ ዘአክበሮሙ ከመ ዘአክበሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት በወንጌለ መንግሥት እንዘ ይብል ክርስቶስ ወልደ ዳዊት አማን አማን እብለክሙ: እስከ አመ የኃልፍ ሰማይ ወምድር የውጣ እንተ አሐቲ ኅርመታ ወአሐቲ ቅርጸታ ኢተኃልፍ እምኦሪት ወእምነቢያት: እስከ ሶበ ኲሉ ይትገበር ወይከውን ይቤ እግዚእ ዘበዕብራይስጢ ልሳን በወንጌለ ማቴዎስ ብርሃን ዘእምብርሃን።

📖 #በማርቆስ ወንጌል:-
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ስምዕዎኬ ለእግዚእነ ኲልክሙ አብያተ ከርስቲያናት ከመ ዘአክበሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት በወንጌለ መንግሥት እንዘ ይብል ክርስቶስ ወልደ ዳዊት ኢይምሰልክሙ ዘመጻዕኩ እስዐሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት ወኢከመ እንስቶሙ አላ ዳዕሙ ዘእንበለ ከመ ከመ እፈጽሞሙ ይቤ እግዚእ በወንጌለ ሰላሙ አማኑኤል ስሙ ማርያም እሙ።

📖 #በሉቃስ ወንጌል:-
ሃሌ ሉያ ይቤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዘ ይሜሕረነ በወንጌለ ሉቃስ ወባሕቱ ይቀልል ሰማይ ወምድር ይኅልፍ እምትደቅ አሐቲ ቃል እምኦሪት።

📖 #በዮሐንስ ወንጌል:-
ሃሌ ሉያ ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በወንጌል ለዘመሐረነ በኦሪት ወበነቢያት ለዘናዘዘነ በከመ መሐረነ እግዚእነ ስብሐት ለእግዚአብሔር ከመ ናምልኮ ለዘፈጠረነ።

ይህ ሦስት ጊዜ ተመላልሶ ከተዘለቀ በኋላ "ለከ ኃይል" የሚለውን በመቀባበል ፲፪ ጊዜ ይበሉ : በመጨረሻም በ፲፫ኛው ከ "ለከ ኃይል" እስከ "እብል በአኮቴት" ድረስ አንድ ጊዜ በኅብረት ይበሉ:-

ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም፤
አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም፤
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም፤
ኃይልየ ወፀወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት፤
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስመከ ትምጻእ መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት አላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኲሉ እኩይ እስመ ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።

ከዚህ በመቀጠል "ለአምላክ ይደሉ" የሚለውን መጀመሪያ በመሪ እየቀደሙ በአንሺ እየተከተሉ አንድ ጊዜ ይዝለቁ: በሁለተኛው ክፍል ደግሞ እያስተዛዘሉ አንድ ጊዜ ይበሉ:-

ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለሥልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለምኲናኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም (በአርብ):
ለከ ይደሉ ኃይል:
ወለከ ይደሉ ስብሐት:
ወለከ ይደሉ አኮቴት:
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም።

ከዚህ በመቀጠል የኦሪትና የነቢያት መፃህፍት ይነበባሉ: ቀጥሎም ከተአምረ ማርያም መቅድም እና ተአምር ጀምሮ ሎሎች ተአምራት ዘወትር በየጠዋቱ እንደተለመደው ይነበባሉ: መርገፋቸውን (የምንባባቱ የመግቢያ ጸሎታቸውና የመጨረሻ ጸሎታቸውን) ከሆሣዕና ሠርክ እስከ ዐርብ ሌሊት በአራራይ ዜማ ያድርሱ: ዐርብ ከጠዋት ጀምሮ ግን በዘወትር እንደተለመደው በዕዝል ዜማ ያድርሱ: ተአምረ ኢየሱስ ከተነበበ በኋላ ከወንጌል በፊት ዲያቆኑ ለሰዓቱ የተሰራውን ምስባክ መጀመሪያ በንባብ ቀጥሎም በዜማ ይበል: ሕዝቡም በአንድነት በዜማ ይቀበሉ።

ከዚያም ሁለተኛው ሥርዓተ ስግደት ይጀመራል: ዜማው የሚጀምረው አሁንም በቀኝና በግራ በመቀባበል ነው: አንዱ ይመራል ሌላው ይቀበላል:-

#በመሪ:- ክርስቶስ አምላክነ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዘወነ:
#በተመሪ:- ንሴብሖ ወናልዕል ስሞ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ:

ኪርያላሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ታኦስ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ማስያስ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን አማኑኤል ናይን ኪርያላይሶን፡
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይን ኪርያላይሶን።
ኪርያላይሶን የሚለውን ብቻ በመሪ ወገን ፳፩ ገዜ በተመሪ ወገን ፳ ጊዜ ይበሉ: ድምሩ ፵፩ ጊዜ ይሆናል።

✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
👍1😢1
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል_7ቱ_የመስቀሉ_ቃላት_7ቱ_ተዐምራት_5ቱ_ችንካሮች_6ቱ_ሰሙነ_ሕማማት_ቀናቶች___5ቱ_ኃዘናት
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል
1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ሰባቱ_የመስቀሉ_ቃላት
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ሰባቱ_ተዐምራት
ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የተቸነከረባቸው_አምስቱ_ችንካሮች
1. #ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. #አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. #ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
4. #አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
5. #ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#የሰሙነ_ሕማማት_ትርጓሜ
#ሰኞ
ይህ ዕለት አንጽ ሆ ተ ቤተመቅደስና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ማክሰኞ
የምክር ቀን ይባላል
ይኸውም የሆነበት ምክንያት ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ ሰጠ።
ጌታችን ፣ ሰኞ ባደረገው አንጽሐተ ቤተመቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ
ሥልጣኑ በጻሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋል ነው፡፡
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ረቡዕ
ይህ ዕለት የምክር ቀን ይባላል፣ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጻሕፋት
ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ወይም የያዙበት ቀን
ስለሆነ ነው፡፡
መልካም መዓዛ ያለው ቀን ይባላል
የእንባ ቀንም ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ሐሙስ
ጸሎተ ሐሙስ ይባላል
ሕፅበተ ሐሙስ ይባላል
የምስጢር ቀን ይባላል
የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል
የነፃነት ሐሙስ ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ዓርብ
ስቅለት ዓርብ ይባላል
መልካሙ ዓርብ (GOOD FRIDAY) ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ቅዳሜ
ቅዳምሥዑር
ለምለም ቅዳሜ ይባላል
ቅዱስ ቅዳሜም ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#አምስቱ_ኃዘናት
ልመናዋ ክብሯዋ በእኛ ለዘለዓለም በእውነት ይደርብንና አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችን ያደረገችው ተዓምር ይህ ነው።
በዕለታት ባንድ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ኃዘኖች ማናቸው ኃዘን ይበልጣል አላት፡፡ እመቤታችንም ፈጣሪዬ ጌታዬ ሆይ በእኔ ዘንድ እኒህ አምስቱ ኃዘኖች ይበልጣሉ አለችው፤
፩• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው። ሉቃ 2፥34-35
፪• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው። ሉቃ
2፥41-48
፫• ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19፥1
፬• አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው። ዮሐ 19፥17-22
፭• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነው። ዮሐ 19፥38-42
⛪️ ጌታችንም እናቱን ድንግል ማርያምን በእኔ ምክንያት ያገኙሽን እኒህን ኃዘኖችና መከራዎች በሰላመ ገብርኤልና አቡነ ዘበሰማያትን እየደገመ ያሰበውን ኃጢአቱን እኔ አስተሰርይለታለሁ፡፡ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ አላት፡፡ እናቴ ሆይ ከሞቱ አስቀድሞ በሦስተኛው ቀን ካንቺ ጋር መጥቼ እገለጽለታለሁ፡፡ ይህን ሲናገር ቅዱስ ደቅስዮስ ሰምቶ ምእመናን ያነቧት ዘንድ በእመቤታችን ተዓምር መጽሐፍ ውስጥ ጻፈው፡፡
⛪️ልመናዋ ክብሯዋ የልጅዋ ቸርነት በእኛ ለዘለዓም በእውነት ይደርብን🙏
🌻ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤
🌻ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤
🌻ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት
የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ።
🌻ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች ዕድፍን የምታውቂ አይደለሽም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ።
🌻ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለሽም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ።
(ሊቁ አባ ሕርያቆስ)
#ምንጭ፦ ታምረ ማርያም፣ ፹፩ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን አትታደስም! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
⛪️የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!🙏
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለአባ ይስሀቅ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን፤ አሜን!!!🙏
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው የፀጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
#ቅዳም_ሥዑር #ለምለም_ቅዳሜ #ቅዱስ_ቅዳሜ

የሰሞነ ሕማማት ቅዳሜ በዝምታ ድባብ የተዋጠች ሐዋርያት አዝነውና ተጨንቀው እንዳይወጡ የጌታ ወዳጅ ብለው አይሁድ እንዳይወግሯቸው ፈርተው በራቸውን ዘግተው ግራ ተጋብተው የዋሉበት ዕለት ከመሆኑም በሻገር ሊቃውንት በተለያየ ስያሜ ይጠሯታል።

#ቅዳም_ሥዑር
ይህ የተባለበት በሰንበት ከእህል ከውሃ መጾም አይፈቀድም፡፡ ነገር ግን በዚህ ዕለት ጌታ በመቃብር ውስጥ በመሆኑ ሐዋርያት ትንሣኤውን ሳናይ አንበላም አንጠጣም ብለው በማክፈል ስለጾሙትና ሰንበተ አይሁድነቱ በመሻሩ ነው፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ከሰዓት በፊት ቄጤማ እስኪዞር ሥራ ይሠራል፡፡

#ለምለም_ቅዳሜም
በዚህ ዕለት ለምለም ቄጤማ ስለሚታደልበት ነው፡፡ ቄጤማ የሚታደልበት ምክንያት ምሳሌያዊና ምስጢራዊ ትርጉም ስላለው ነው ምሳሌያዊ ትርጉም በኖኅ ዘመን የዘነበው ማየ አይኀ መድረቁን ለማረጋገጥ፣ ኖኅ ርግብን በመስኮት አውጥቶ ላከ በመጀመሪያው ዝም ብላ ተመልሳለች በሁለተኛው ስትላክ ‹‹ነትገ ማየ አይኀ ሐፀ ማየ ኃጢዓት›› እያለች ቄጤማ በአፏ ይዛ ስትመለስ ኖኅ እጁን ዘርግቶ ተቀብሏታል፡፡ የርግቢቱ ድርጊት የጥፋት ውሃ ደረቀ፣ የኃጢዓት ውሃ ደረቀ የሚል የምስራች አጉልቶ የሚያሳይ ነው፡፡ (ዘፍ 8፡6-11)
*ምስጢራዊ_ትርጉሙ ደግሞ ርግብ የተባለችው አማናዊት ርግብ እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፣ ለምለም ቄጠማ በአፏ ይዛ እንደመታየት፣ አምላክ ወልደ አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷን የሚያመለክት ነው፡፡ ከእርሷ የተወለደው ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ በሞቱ ሞትን እንዳጠፋልን "ማየ አይኀ" የተባለ ሞተ ነፍስን እንዳስቀረልን ለማመልከት የምስራች ሲሉ ካህናት ቄጤማ ያድላሉ፣ ምዕመናንም እስከ ትንሳኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያሥሩታል፡፡

#ቅዱስ_ቅዳሜ
ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ሲሆን፣ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው መቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎች ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡
በዚህ ዕለት በቤተክርስቲያን የሚፈጸሙ ሥርዓቶች መኀልየ መኅልየ ይነበባል ምክንያቱም ተስፋ ትንሳኤ አለባትና እስካሁን በሌሎች ዕለታት ሳይደርስ የሰነበተው
እግዚአ ሕያዋን (የሕያዋን ጌታ) ፣ ፍትሐተ ዘወልድ፣ ጸሎተ ዕጣን "ዘእንበለ ስኢም" ይደረሳል፣ ያለመሳሳም ወይም ያለ ሰላምታ ማለት ነው፡፡
ገብረ ሰላመ በመስቀሉ (በመስቀሉ ሰላምን አደረገ የሚለው መዝሙር ይዘመራል ምክንያቱም በሲኦል ያሉትን ነፍሳት በርብሮ በገነት ዕረፍተ ነፍስን (ሰላምን) ለሰው ልጅ የሰጠው በመስቀል ላይ ከተሰቀለ በኋላ ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ከላይ እንዳየነው ጌታ በዕፀ መስቀል ከመሰቀሉ በፊት መስቀል የሰላም ምልክት አልነበረም፡፡ እርሱ ከተሰቀለበት በኋላ ግን የሰላም ምልክት ሆኗልና ከፊተኛው ለመለየት ነው፡፡
ከዚህ ሁሉ በኋላ በረከተ ቄጤማ ይዞራል።

#አክፍሎት፥ ዓርብና ቅዳሜ ይሆናል፣ ያልቻለ አንድ ቅዳሜን ያከፍላል የዚህ አክፍሎት ጦም የተጀመረው በሐዋርያት ነው፡፡ ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ ሳለ ፈሪሳውያን እኛና የዮሐንስ ደቀመዛሙርት እንጦማለን አንተ ደቀመዛሙርት የማይጦሙት ለምንድን ነው? ብለው ጠይቀውት ነበር እርሱም ሙሽራ ከነሱ ጋር ስለ ሚዜዎች ሊጦሙ አይገባም ነገር ግን ሙሽራው ከነሱ የሚወስድበት ጊዜ ይመጣልና ያን ጊዜ ይጦማሉ ብሎ መለሰላቸው በዚህ መሠረት ሐዋርያት ሙሽራው ክርስቶስ ከነሱ ከተለየበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ትንሣኤው ድረስ ከሰው ርቀው፣ ከእህል ከውሃ ተለይተው፣ በዝግ ቤት ተወስነው ጹመዋል ካህናትና ምዕመናን የሐዋርያትን ፈለግ በመከተል ሐሙስ ማታ ከበሉ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ይቆያሉ ሁለቱን ቀን ያልቻሉ ግን ቅዳሜን ብቻ ያከፍላሉ፡፡
በሌላ መልኩ አክፍሎት ማለት ማካፈል ማለት ነው በዚህ ዕለት ካህናት ምዕመናን ካመጡላቸው የትንሣኤ መዋያ በረከት ለድሆች ያካፍላሉና፡፡

•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
2025/07/09 15:30:32
Back to Top
HTML Embed Code: