✞✞✞ #አሥሩ_የቅድስና_ማዕርጋት ✞✞✞
1 ጽማዌ
2 ልባዌ
3 ጣዕመ ዝማሬ፣ ንጽሐ ሥጋ ይባላሉ።
4 ኩነኔ
5 ፍቅር
6 አንብዓ ንስሐ
7 ተሰጥሞ፣ ንጽሐ ነፍስ ይባላሉ።
8 ሑሰት
9 ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ
10 ከዊነ እሳት፣ ንጽሐ ልቡና ይባላሉ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የሰው ልጅ በዚህ ምድር ሲኖር በቅድስናና በንጽሕና እያደገ ሲመጣ የሚደርስባቸው አሥር መንፈሳዊ ማዕረጋት አሉ፡፡
እነዚህ አሥር መንፈሳዊ ማዕረጋት በሦስት የሚከፈሉ ሲሆን፡- ንጽሐ ሥጋ ፤ ንጽሐ ነፍስና ፤ ንጽሐ ልቡና ይባላሉ፡፡
አሥሩንም ማዕረጋት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
1⃣. ጽማዌ፡-
ይህ ማዕረግ የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን ትህትናን፤ ራስን ዝቅ ማድረግን፤ መታገሥንና ነገሮችን በውስጥ ይዞ ማሰላሰልን ወዘተ…ይይዛል፡፡
እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው የዚህን ዓለም ውጣ ውረድ ከማውራት ይከለከላል በብዙ ነገሮች ላይ ዝምታን ይመርጣል፡፡
2⃣. ልባዌ፡-
ይህ ማስተዋልና ልብ ማለትን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች የሚገኙበት ደረጃ ነው፡፡
እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች ልናገር ሳይሆን ልስማ ፤ ላስተምር ሳይሆን ልማር ይላሉ፡፡
የመጽሐፉ ቃል የሚለውን ማስተዋልና አብዝተው ኃጢአታቸውን ያሰላስላሉ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ፡፡
3⃣. ጣዕመ ዝማሬ፡-
እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው አንደበቱን ከንባብ ልቡናውን ከምሥጢር ያቆራኛል፡፡
እዚህ ደረጃ የደረሱ ቅዱሳን አንደበታቸው ዝም ቢል በልባቸው ግን ዝም ብለው አያውቁም ከሰውነታቸውም ንጽሕና አይለይም፡፡
የሚያነቡትን መጽሐፍና የሚጸልዩትን ጸሎት ምሥጢሩን በደንብ እየተረዱት ስለሚያደርጉት አይሰለቻቸውም፡፡ እነዚህ ከ1-3 ያሉት የንጽሐ ሥጋ ማዕረጋት ናቸው፡፡
4⃣. አንብዕ፡-
እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች የጌታቸውን ፍቅር እያሰቡ እስከ ሞትና መከራ የተጓዘውን ጉዞ እያሰቡ ዘወትር ያለቅሳሉ፡፡ ያለምንም ተጽዕኖ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይወርዳል፡፡
ይህንንም የሚያደርጉት ለዚህ ዓለም ፍላጎታቸው መሟላት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ምሕረትና ቸርነት በመናፈቅ ነው::
5⃣. ኩነኔ፡-
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ሥጋዊ ፈቃድ ሁሉ ለነፍስ ፈቃድ ይገዛል ፤ ነፍስ በሥጋ ፍላጎት ላይ ትሰለጥናለች፡፡ ምድራዊ (ሥጋዊ) ፍላጎቶች ይጠፉና ሰማያዊ (የነፍስ) ፍላጎቶች ቦታውን ይወርሳል፡፡
6⃣. ፍቅር፡-
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ማንንም ሳይመርጡ ወዳጅንም ጠላትንም መውደድ ይጀምራሉ፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ያደረገውን ታላቁን የፍቅር ሥራ እርሱን በመምሰል ሕይወት በመኖር በተግባር ይገልጻሉ፡፡
7⃣. ሁሰት፡-
ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ቅዱሳን ባሉበት ቦታ ሆነው ሁሉን ነገር ማየት ይችላሉ፡፡ የቦታ ርቀትና የገዘፉ ቁሶች ሳያግዳቸው ፤ ሁሉን ያያሉ፡፡
እነዚህ ከ4-7 ያሉት የንጽሐ ነፍስ ማዕረጋት ናቸው፡፡
8⃣. ንጻሬ መላእክት፡-
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ መላእክትን ሲወጡና ሲወርዱ ማየት ይቻላል፡፡
9⃣. ተሰጥሞ፡-
ከዚህ ማዕረግ የደረሰ ሰው በብርሃን ባሕር እየተመላለሰ በምድሪቱ ላይ ያለውን ሁሉ ማወቅ መረዳትና መመልከት ከመቻላቸውም አልፈው ሥሉስ ቅዱስ ከመመልከት በስተቀር በሰማያት ያለውንም ምሥጢር ወደ መረዳት ይደርሳሉ፡፡
🔟. ማዕረገ ከዊነ እሳት/ ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/፡-
ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ሰዎች ሥላሴን በዙፋኑ ላይ ሆኖ እንደ እስጢፋኖስ መመልከት ይጀምራሉ፡፡
እንዲሁም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በአካለ ነፍስ ተነጥቀው ወደ ሰማያት በመውጣት ሰማያትን መጎብኘት ወደ መቻል ይደርሳሉ፡፡
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✝✝✝ ✞✞✞ ✝✝✝
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
https://www.tg-me.com/EOTC2921

Telegram
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

🌾✞ #የኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔርነት ✞🌾
❖ የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት ትንቢትን በተናገሩ በቀደምት ነቢያት ፈንታ፤ በዓለሙ ኹሉ እግዚአብሔርነቱን በግልጥ ያስተማሩ ሐዋርያት ተተኩ፤ ከዚያም ምስጢሩን የሚያመሰጥሩ ሊቃውንት በሐዋርያት እግር ተተክተው የአምላካቸው የክርስቶስን እግዚአብሔርነት አምልተው አስፍተው
አስተምረዋል፤ ይኽም ትምህርታቸው ጥልቅና ሰፊ ሲኾን በጥቂቱ ትምህርታቸው እነሆ፡-
☞ “ወአግሐዶ ዮሐንስ ወአጥመቆ በውስተ ዮርዳኖስ፤ ተመከረ በገዳም
ወተዐውቀ ከመ እግዚአብሔር ውእቱ” (ዮሐንስ ገለጠው፤ በዮርዳኖስም
አጠመቀው፤ በገዳም ተፈተነ፤ ርሱም እግዚአብሔር እንደኾነ ታወቀ) (ቅዱስ
ሄሬኔዎስ)
☞ “ተሰቅለ በሕማመ ሥጋ ወሐይወ በኀይለ እግዚአብሔር ዘውእቱ መለኮቱ፤
ወወረደ ውስተ መትሕተ ዕመቀ ምድር ወጼወወ ነፍሳተ ሰብእ” (ለሥጋ
በሚስማማ ሕማም ተሰቀለ፤ በእግዚአብሔርነቱ ኀይል ተነሣ፤ ይኸውም መለኮቱ ነው፤ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ማረከ) (ቅዱስ ሄሬኔዎስ)
☞ “እግዚአብሔር ቃል ስለ እኛ እንደታመመ እግዚአብሔር ለእኛ ቤዛ እንደሞተ ብትሰማ፤ እኛ መለኮትን ከትስብእት ጋራ አንድ አካል አንድ ባሕርይ አድርገን ለእግዚአብሔርነቱ በሚገባ በዚኽ ባንድ ስም እንደምንጠራው ዕወቅ… የእኛ አምላክ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ፈቃድ በግብረ መንፈስ ቅዱስም ከዳዊት ዘር ከእመቤታችን ማርያም ተፀነሰ” (ቅዱስ አግናጥዮስ)
☞ “ክርስቲያኖች በምድር ከሚኖሩ ሰዎች ኹሉ በልጠው እውነትን አገኙ፤
በመንፈስ ቅዱስም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ወልድን፤ የኹሉ ነገር
ፈጣሪንና ሠሪን እግዚአብሔርን አወቁ” (አርስቲደስ)
☞ “እናንተ ግሪኮች እግዚአብሔር ከሰው ልጅ እንደተወለደ ስናስገነዝብ ስንፍናና
እየተጫወትን ወይም ተርታ ነገር እየተናገርን አይደለም” (ቴሽያን ሶርያዊ)
☞ “የእግዚአብሔር ቃል ክርስቶስ ከአብ ጋር በህልውና ያለ፤ እኛንም ያስገኘ፤
አኹንም ይኸው ቃል ሰው ኾኖ ተገለጠ፤ ርሱ ብቻ እግዚአብሔርም ሰውም የኾነ
እና የበጎ ነገራት ኹሉ ምንጭ ነው… በተዋሐደው ሥጋ ሲያዩት የተናቀ ቢኾንም እንደ እውነቱ ግን እጅግ ያማረ የተወደደ የተፈቀረ ነው፤ ኢየሱስ መድኀኒታችንና ኀጢአታችንን ይቅር ያለ ፈውሳችን የኾነ መለኮታዊ ቃል ሙሉ በሙሉ በርግጠኛነት በእውነት እግዚአብሔር ነው” (ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ)
☞ “እግዚአብሔር ክርስቶስ የኹሉም ነገር አምላክ በመኾኑ ከሰው ዘር በመላ
ኀጢአትን ጠራርጎ ዐጥቦ አሮጌውን ሰው ዐዲስ አድርጎታል” (ቅዱስ ሂፖሊተስ
(አቡሊዲስ))
☞ “ክርስቶስ ዕሩቅ ብእሲ ቢኾንማ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የኾንኽ አንተን
የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይኽች የዘላለም ሕይወት ናት”
በማለት ያስቀመጠውን ሕግ ለምን እንድናምን አደረገ? (ዮሐ ፲፯፥፫)፤
እግዚአብሔር መኾኑን እንድረዳው ባይፈልግ ኖሮማ ለምን “የላክኸውንም
ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ” ብሎ ለምን አከለበት? ይኽም እንደ
እግዚአብሔርነቱ እንድንቀበለው ነው፤ ይኽ ባይኾን ኖሮማ “የላክኸውን ሰው
ኢየሱስ ክርስቶስን” ይለን ነበር፤ በርግጥ ግን ርሱ ይኽነን አላከለበትም፤ ወይም
ክርስቶስ ራሱን ፍጹም ሰው ብቻ እንደኾነ አድርጎ አላቀረበልንም፤ ኾኖም ግን
ርሱ ራሱ እግዚአብሔር እንደኾነ እንድንረዳው ፈልጎ ራሱን ከእግዚአብሔር አብ ጋር አስተካከለ እንጂ፤ በዚኽ መልኩ እንድረዳው ባይሻ ኖሮማ ራሱን በመነጠል ያቀርብ ነበር” (ኖቬሺያን)
☞ “ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደኾነ የካደ ሰው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ
(መቅደስ) ሊኾን አይችልም” (ቆጵርያኖስ (ሲፕርያን ዘካርቴጅ (ዘቅርጣግና))
☞ “የሕያው አካላዊ ቃል አባት አንድ እግዚአብሔር አለ፤ ርሱም ሕያው ጥበብ፣ ኀይልና ዘላለማዊ አካል ያለው፤ ፍጹም የኾነው ወልድን አካል ዘእምአካል
ባሕርይ ዘእምባሕርይ የወለደ የአንድያ ልጁ የባሕርይ አባት ነው፤ አንድ ጌታ
ከብቸኛው ከአብ የተገኘ ዋሕድ፤ ከእግዚአብሔር የተገኘ እግዚአብሔር፤ አባቱን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው፤ ከሃሊው ቃል፤ የኹሉም ነገር መሠረትና ማጠቃለያ የኾነ ጥበብ ባለቤትና የፍጥረታት ኹሉ አስገኚያቸው፤
የእውነተኛው አብ እውነተኛ ልጅ ወልድ፤ ከማይታይ የተገኘ ኅቡእ፤ ኅልፈት
ውላጤ ከሌለበት የተገኘ ኅልፈት ውላጤ የሌለበት፤ ከማይሞት የተገኘ ሕያው፤
ከዘላለማዊ የተገኘ ዘላለማዊ … እናም ወልድ ፈጽሞ አብን ወደ መኾን
አይለወጥም፤ መንፈስ ቅዱስም ወልድን ወደ መኾን አይለወጥም፤ ግን ያለምንም ልዩነት እና ያለምንም ለውጥ በእግዚአብሔርነት የተካከሉት ሥላሴ
ለዘለዓለም ይኖራሉ” (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት)
☞ “እንግዲኽ የኾነ አንድ ቁጡ፤ የተናደደ እና የተደሰተ ሰው የእናንተ አምላክ
ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው? ብሎ ሊል ይችላል፤ በርግጥም ርሱ እግዚአብሔርና የተሰወሩት ኹሉ ኀይላት አምላካቸው ነው ብለን እንመልስለታለን” (አርኖቢዩስ)
☞ “ዝ ውእቱ ዘአጥፍኦ ለሞት ወሠዐሮ ለዲያብሎስ ዘምስሌሁ እዘዘ ሞት
በትንሣኤሁ ባሕቲቱ እግዚአብሔር ዘኮነ ሰብአ ወአስተርአያ በአርአያ ብእሲ” (ሞትን ያጠፋው ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ የሞት ሥልጣን የነበረው
ዲያብሎስን የሻረው ርሱ ነው፤ ሰው የኾነ በሰው ባሕርይ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው) (ቅዱስ አትናቴዎስ)
☞ “ዝንቱ ዘበአማን እግዚአብሔር ወወልደ እግዚአብሔር ወውእቱ እግዚእ ቡሩክ ላዕለ ኲሉ…” (ርሱ በእውነት እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ ከኹሉም በላይ የሚኾን የባሕርይ ገዢ ነው…) (ቅዱስ አትናቴዎስ)
☞ “ወውእቱ እግዚአብሔር ዘቦቱ ልደት በሥጋ በሕማማት ዲበ ዕፀ መስቀል
ወመዊት ወትንሣኤ” (በሥጋ መወለድ በመስቀል መከራ መቀበል መሞት፣
መነሣት ገንዘቡ የኾነ ርሱ እግዚአብሔር ቃል ነው) (ቅዱስ ፊልክስ)
☞ “ተፈሥሒ ኦ ማርያም ምድር ቅድስት ዘበጽሐኪ እግዚአብሔር እንዘ ይጼዐን
ዲበ ደመና ብሩህ ወቦአ ውስቴትኪ፤ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ዘአስተርአየ እምኔኪ
እግዚአብሔር ዘየዐርፍ በቅዱሳኒሁ፤ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ዘሠምረ እግዚአብሔር ዘሀሎ እምቅድመ ዓለም ይትወለድ እምኔኪ ቃል ዘንሰግድ ሎቱ ምስለ አብ ወመንፈስ ቅዱስ” (እግዚአብሔር በብሩህ ደመና ኾኖ ወደ አንቺ የመጣ፤ በአንቺም ያደረ ምድር ቅድስት ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በቅዱሳን ዐድሮ የሚኖር እግዚአብሔር ቃል ከአንቺ ተወልዶ የተገለጠ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምንሰግድለት ቃል ከአንቺ ይወለድ ዘንድ ዓለም ሳይፈጠር የነበረ እግዚአብሔር አንቺን የወደደ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ) (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)

☞ “…ለሊሁ እግዚአብሔር ዘበአማን ወወልደ እግዚአብሔር ዋሕድ ብርሃን
ዘእምብርሃን ወሕይወት ወኀይል ነሥአ ዘኢዚኣሁ…” (… አንድ የእግዚአብሔር ልጅ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ሕይወት ኀይል የሚኾን ርሱ እግዚአብሔር ባሕርዩ
ያልነበረ ሥጋን ተዋሐደ) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ወነአምን ቦቱ ከመ ውእቱ እግዚአብሔር ቃል ዘበአማን ወለድንግልሂ ንጽሕት ወላዲተ አምላክ ንሰምያ እመ እግዚአብሔር” (በእውነት ርሱ እግዚአብሔር ቃል እንደኾነ እናምንበታለን፤ አምላክን የወለደች ንጽሕት ድንግልንም የእግዚአብሔር እናት እንላታለን) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ምንት ውእቱ ተሳትፎ በእሉ ከመዝ ዘእንበለ ከዊኖቱ ከማነ በሥጋ ወደም እምድንግል ቅድስት ወላዲተ እግዚአብሔር ማርያም እንዘ ውእቱ አምላከ ጽድቅ…” (በሥጋ ሰዎችን መምሰሉ ምንድን ነው? የባሕርይ አምላክ ሲኾን እግዚአብሔርን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በነፍስ በሥጋ እንደ እኛ ሰው መኾኑ ነው እንጂ፤ ይኸውም ከአብ የተወለደ አካላዊ ቃል ነው፤ ለዘለዓለምም ከአብ ጋራ ትክክል ነው፤ በባሕርዩ ቀዳማዊ ነው፤ ልዕልና ባለው ጌትነት ርሱ ብቻውን ያበራል) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ወከመዝ ንሕነ ነአምን ከመ ድንግል ቅድስት ኮነት ታኦዶኮስ (ቴኦቶኮስ)
ዘውእቱ ወላዲተ እግዚአብሔር ብሂል ወሶበ ወለደቶ ለነ መንክረ ለዋሕድ
ክርስቶስ በተሣትፎቱ ደመ ወሥጋ ከማነ” (እንደኛ ነፍስን ሥጋን በመዋሐዱ አንድ
ክርስቶስ ድንቅ በሚያሰኝ ልደት በወለደችው ጊዜም ንጽሕት ድንግል ታኦዶኮስ (ቴኦቶኮስ) (Θεοτόκος,) እንደኾነች እናምናለን፤ ይኸውም እግዚብሔርን የወለደች ማለት ነው) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ወኮነ ሰማይ ዓለመ ወዓለምሂ ሰማየ ወኮነ እግዚአብሔር ሰብአ በታሕቱ
ወረሰዮ ለሰብእ ውስተ አርያም…” (ሰማይ ዓለም ኾነ፤ ዓለምም ሰማይን ኾነ፤
እግዚአብሔር ሰው ኾኖ በዚኽ ዓለም ተገኘ፤ ሰውንም በላይ በአርያም አደረገው፤ በሰማይ የሚቀርበው ምስጋና በዚኽ ዓለም ተደረገ፤ በአብ ዕሪና ያለ ርሱ
በማርያም ክንድ ተይዞ ታየ፤ እግዚአብሔር አብ በማይመረመር ምስጢር ያለ እናት የወለደውን ማርያም በማይመረመር ምስጢር ያለ ዘርዐ ብእሲ በሥጋ ወለደችው) (ቅዱስ ሳዊሮስ)
☞ “ወካዕበ ይቤ እስመ እግዚአብሔር አስተርአየ ለሰብእ በተወልዶ ወመጽአ ኀበ
ዕጓለ እመሕያው፤ ወዓዲ ይቤ ዝንቱ ውእቱ ቃለ እግዚአብሔር ዘኢይትገመር
ዘሀሎ እምቅድመ ኲሉ መዋዕል ዘአልቦቱ ሥጋ ነሥአ ሎቱ ሥጋ” (ዳግመኛ
እግዚአብሔር በመወለዱ ለሰው ተገለጠ፤ ወደ ሰውም መጣ አለ፤ ዳግመኛም የማይወሰን ከቀን ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እግዚአብሔር ቃል ይኽ ነው፤ ሥጋ ያልነበረው ሥጋን ነሣ) (ቅዱስ ሱኑትዩ)
☞ “በፈቃደ አቡሁ ወረደ ኀበ ማርያም ተአንገደ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ” (በአባቱ ፈቃድ ወረደ በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ
እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ) እንዲል ቅዱስ ዲዮስቆሮስ
በቅዳሴው
🙏[ከኹለት አካል አንድ አካል፤ ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የኾንኽ አምላካችን
ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፈጽመን እናመሰግንኻለን]🙏
[ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

አምላኬ ታሪኬን ለዉጠዉ /2/ ሠዉ አድረገኝ እና ሰዉን ይግረመዉ
ሰላም የጎጃም ልጅ/selam yegojam lije ኢትዩጲያዊ Ethiopiawi
🌾✞ አምላኬ_ታሪኬን_ለውጠው ✞🌾
https://www.tg-me.com/EOTC2921
አምላኬ ታርኬን ለውጠው(፪)
ጌታዬ ታርኬን ለውጠው(፪)
ሰው አርገኝና ሰው ይግረመው(፪)
እስከ መቼ በበደል እስከ መቼ በኃጢያት
አስመሳይ ማንነቴን ነፍሴን እያስጨነቃት
መሸከም ስላቃተኝ የበዛው እዳዬን
በጽድቅ ልመላለስ ለውጠው መዓዛዬን(፪)
#አዝ•••
ቃልህን ልኑረው በዕድሜ በዘመኔ
ታስባለህና ከእኔ በላይ ለኔ
የፍቅር ሰው ልሁን ደግሞም የይቅርታ
የሚሳንህ የለም ታስችላለህ ጌታ(፪)
#አዝ•••
በፍምህ ይዳሰስ የኃጢያት ለምፄ
በቃልህ መዶሻ ይስተካከል ቅርፄ
ቀራጩን ለክብርህ ታንበረክካለህ
ሰው ታደርገውና ሰው ታስገርማለህ(፪)
#አዝ•••
ፍሬ እንዳላፈራ በእሾህ መታነቄን
አጥብቀህ ስጠራኝ አብዝቼ መራቄን
ይብቃ በለኝ ጌታ ልቤን አነሳሳው
በመንፈስህ ቃኘኝ ኃጢያቴን ድል ልንሳው(፪)
#አዝ•••
የኋላዬን ትቼ ወደ ፊት ልዘርጋ
ዋጋ እንዳላሳጣው የደምህን ዋጋ
እንዳሸንፍ እርዳኝ ስምህን ታጥቄ
ዳግም ባርያ እንዳሆን ልጅነትን ንቄ(፪)
#አዝ•••
🎤ሊቀ-መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ
https://www.tg-me.com/EOTC2921
አምላኬ ታርኬን ለውጠው(፪)
ጌታዬ ታርኬን ለውጠው(፪)
ሰው አርገኝና ሰው ይግረመው(፪)
እስከ መቼ በበደል እስከ መቼ በኃጢያት
አስመሳይ ማንነቴን ነፍሴን እያስጨነቃት
መሸከም ስላቃተኝ የበዛው እዳዬን
በጽድቅ ልመላለስ ለውጠው መዓዛዬን(፪)
#አዝ•••
ቃልህን ልኑረው በዕድሜ በዘመኔ
ታስባለህና ከእኔ በላይ ለኔ
የፍቅር ሰው ልሁን ደግሞም የይቅርታ
የሚሳንህ የለም ታስችላለህ ጌታ(፪)
#አዝ•••
በፍምህ ይዳሰስ የኃጢያት ለምፄ
በቃልህ መዶሻ ይስተካከል ቅርፄ
ቀራጩን ለክብርህ ታንበረክካለህ
ሰው ታደርገውና ሰው ታስገርማለህ(፪)
#አዝ•••
ፍሬ እንዳላፈራ በእሾህ መታነቄን
አጥብቀህ ስጠራኝ አብዝቼ መራቄን
ይብቃ በለኝ ጌታ ልቤን አነሳሳው
በመንፈስህ ቃኘኝ ኃጢያቴን ድል ልንሳው(፪)
#አዝ•••
የኋላዬን ትቼ ወደ ፊት ልዘርጋ
ዋጋ እንዳላሳጣው የደምህን ዋጋ
እንዳሸንፍ እርዳኝ ስምህን ታጥቄ
ዳግም ባርያ እንዳሆን ልጅነትን ንቄ(፪)
#አዝ•••
🎤ሊቀ-መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ
🌾✞ #እርሱ_አምላኬ_ነው። 🌾✞
❖ በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በጨርቅ ተጠቅልሎ፣ በግርግም ውስጥ በድንግል እቅፍ ውስጥ ብታገኙት፣ እንዳይመስላችሁ፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡
❖ በዮርዳኖስ መሀል ቆሞ፣ በዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ፣ በገዳመ ቆሮንቶስ ሲራብና ሲጠማ ሲጸልይ ብታዩት፤ እንዳይመስላችሁ እርሱ በእሳት የሚያጠምቀው፤ መናን ከሰማይ፣ ውሃን ከአለት የሚያፈልቀው፣ ጸሎትን የሚቀበለው፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡
❖ ከተናቀችው ከናዝሬት ከገሊላ ቢመጣ፣ በአህያ ጀርባ ላይ ተጭኖ ኢየሩሳሌም ሲገባ ብታዩ፣ እንዳይመስላችሁ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ፣ በሱራፌል የሚመሰገነው፣ አለምን የፈጠረው፤ እርሱ አምላኬ ነው።
❖ በምድራዊ ንጉስ በጲላጦስ ፊት ቆሞ ሲከሱት፣ በደለኛ ነው ብለው በሀሰት ሲወነጅሉት ብታዩት፤ እንዳይመስላችሁ፤ ስለ እኔ ተገብቶ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡
❖ የእሾህ አክሊል በእራሱ ላይ ደፍቶ፣ ቀይ ልብስ ደርቦ፣ በአይሁድ ፊት እርቃኑን ቆሞ ብታዩት፤ ለእኔ ተገብቶ ነውና፣ የብርሃን አክሊል ያለው፣ የማይተረጎም ልብስ የሚጎናጸፈው፣ እርቃኔን የሸፈነው፤ እርሱ አምላኬ ነው።
❖ መስቀል አሸክመው፣ እንደ በደለኛ ሲገፉት፣ ሲገርፋት፣ ሲጎትቱት፣ በጥፊ ሲያጣፉት፣ በእርግጫ ሲረግጡት፣ በገመድ ሲጎትቱት፣ ምራቅ ሲተፉበት በቡጫ ሲመቱት ብታዩት፤ የእኔን ሀጢያት ተሸክሞ ነውና እንዳይመስላችሁ፤ እርሱ መዳህኒቴ ነው፡፡
❖ ከፕራይቶርዮን እስከ ቀራንዮ፣ ጎልጎታ ደም እየጎረፈው፣ ወዝ እየነጠበው፣ እልፍ ጊዜ ከመሬት ሲወድቅ ሲነሳ፣ መስቀል ሲጎትት፣ አቅም ሲያጥረው ብታዩት፤ እውነት እላችኃለሁ እርሱ የእኔን በደል ተሸክሞ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡
❖ በቀትር ጊዜ ተፈርዶበት፣ በወንበዴ መሀል በእንጨት መስቀል ተሰቅሎ፣ እጅ እግሩ ተቸንክሮ፣ ከኮረብታው ላይ ብታዩት፤ እንዳይመስላችሁ እኔ ወንበዴው ተላልፌ፣ ቀጥፌ በበላሁት በለስ ነውና፣ ለእኔ ተገብቶ ነው እንጅ፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡
❖ "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ" እያለ ከመስቀል ላይ ሲጸልይ፣ ሲጮህ ብታዩት፤ እውነት እውነት አላችኃለሁ የእኔን ጩኸት እየጮኸ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡
❖ በዕለተ አርብ ጀንበር ሲያዘቀዝቅ፣ ጎኑን ተወግቶ፣ ደምና ውሃ ሲፈሰው፣ አንገቱን ደፍቶ፣ ስጋውን ለመቃብር፣ ነፍሱ ወደ ሲኦል ሲያወርድ ብታዩት፤ እኔን ከሲኦል ወደ ገነት እየመለሰኝ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው።
❖ ሲገንዙት፣ በበፍታ ሲሸፍኑት፣ በአዲስ መቃብር ስጋውን ብታዩት፣ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት፣ በከርሰ መቃብር ቢቆይ፣ እንዳይመስላችሁ ሲኦልን በዝብዞ፣ ገነትን እየከፈተ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡
❖ ዛሬ በዚች ዕለት፣ ንጽሕት ከሆነችው፣ ከልጅ ልጄ ተወልዶ፣ ደሙን አፍስሶ፣ ስጋውን ቆርሶ፣ በደሌን ክሶ፣ ከወደኩበት አንስቶ፣ ጨለማውን ያጠፋልኝ፣ መድኅን አለም ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ሰው እንዳይመስላችሁ፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡
❖ እውነት እላችኃለሁ፤ እንዳይመስላችሁ እሩቅ ብዕሲ፤ እርሱ አምላኬ ነው!!!፡፡
❖ ክብርና ምስጋና፣ አምልኮና ውዳሴ፣ ለእርሱ ለአምላካችን፣ ለመድኃኒታችን፣ ለፈጣሪያችን፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ዘወትር ለዘለዓለሙ ይሁንልን አሜን።
📖✞ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✞📖
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞

🌾 ✞ #ጾመ_ሰብአ_ነነዌ ✞ 🌾
#የካቲት_፯_ሰኞ_ይጀምራል።
✔‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡
✔በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ዮናስ የስሙ ትርጓሜ ‹ርግብ› የሆነ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይን ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው (ሉቃ.፲፩፥፴)፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፤ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናገረ (፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩)፡፡
✔ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ሆነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል (፩ኛነገ.፲፯፥፲፱)፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ሆድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል (ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪)፡፡
❖ እግዚአብሔር አምላክም ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ።
❖ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡
❖ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይሆንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን አስረድቶታል፡፡
✔ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ። የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል (ትንቢተ ዮናስ)፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡
✔ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ነው፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ሁሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች (አስ.፬፥፲፭-፲፮)፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች (ሉቃ.፪፥፵፮)።
❖ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል (ሉቃ.፲፫፥፴፪)፡፡
✔ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኃጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኃጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ሆነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡ ስለሆነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡
✔ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡
✍በርዕሰ ደብር ብርሃኑ አካል
🌾✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞🌾
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞

🌾✞ #ዐቢይ_ጾም ✞🌾
🌾✞ #ጾም ማለት መተው መከልከል ማለት ነው፡፡ ጾም በእግዚአብሐር የተቀደሰ ተግባር ስለኾነ ወደ ቅድስና ጎዳና የሚመራ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ሥርዓት ሠርታ ጾመን ከአምላካችን ጋር ኅብረት እንዲኖረን፤ መንፈሳዊ ኃይል እንድናገኝ ታደርጋለች። በጾም ወራት ከመባልዕት መከልከል ብቻ ሳይኾን ዐይን ክፉ ከማየት፣ አንደበት ክፉ ከመናገር፣ ጆሮ ክፉ ከመስማት መቆጠብ እንደሚገባው በቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፎአል፡፡ ‹‹ይጹም ዐይን ይጹም ልሳን እዝንኒ ይጹም እምሰሚዓ ኀሡም በተፋቅሮ›› እንዲል ቅዱስ ያሬድ /ጾመ ድጓ/፡፡ በጾም ወራት ላምሮት፣ ለቅንጦት የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኃይል ተቃራኒ የኾኑ ሥጋዊ ፍትወትን የሚያበረታቱ፣ ሥጋንና የሚያሰክሩ መጠጦችን /ዳን.፲፥፪-፫/፣ ቅቤና ወተትን ከመጠቀም መታቀብ እንደሚገባ ታዟል መዝ.፻፰፥፳፬፣ ፩ቆሮ.፯፥፭፤ ፪ቆሮ.፮፥፮/፡፡
🌾✞ በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡፡ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር በሚገናኙበት ወራት እህልና ውኃ በአፋቸው አይገባም ነበር /ዘፀ.፴፬፥፳፰/፡፡ አስቴር አስቀድማ ሦስት ቀን ጾማ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስቴር ፬፥፲፭-፲፮/፡፡ በዘመኑ በኃጢአት ብዛት የታዘዘው የእግዚአብሔር መዓት የሚመለሰውም ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር /ዮናስ ፪፥፯-፲/፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይኾን ራሱ ክርስቶስ የሠራው ሕግ ነው /ማቴ.፬፥፪፤ ሉቃ.፬፥፪/፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም በየጊዜው ከመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ የሚቀበሉት በጾም በጸሎት ላይ እንዳሉ ነበር /ሐዋ.፲፫፥፪/፡፡ ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስትም የሚሾሙት በጾምና በጸሎት ነው ሐዋ.፲፫፥፫፤ ፲፬፥፳፫/፡፡ እንደ ቆርነሌዎስ ያሉ ምእመናን ያላሰቡትን ክብር ያዩና ያገኙ የነበረውም በጾምና በጸሎት ፈጣሪያቸውን በመማጸን ነው /ሐዋ.፲፥፴/፡፡
🌾✞ ዐቢይ ጾም ጌታችን ከተጠመቀ በኋላ ዐርባ ቀን የጾመው፤ እኛም እንድንጾማቸው በቤተ ክርስቲያናችን ከታዘዝናቸው ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው፡፡ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን ምሳሌ ተከትለን ጾሙን በየዓመቱ እንጾመዋለን፡፡ ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት (፶፭ ቀኖች) አሉት፡፡ በውስጡ ስምንት ቅዳሜዎች፣ ሰባት እሑዶች ይገኛሉ፡፡ ይኸውም ዐሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ እነዚህ ቀናት ከጥሉላት እንጂ ከእኽል ውኃ ስለማይጦሙ የጦሙ ወራት ዐርባ ቀን ብቻ ይኾናል፡፡
🌾✞ ጾሙ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፤ አንደኛ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው በመኾኑ፣ እንደዚሁም ‹‹ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኀይሉ ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኰቴቱ›› መዝ.፵፯፥፩፤ መዝ.፻፵፮፥፭/ የተባለ ጌታችን የጾመው ጾም ስለኾነ ‹‹ዐቢይ ጾም›› ይባላል፡፡ ሁለተኛ ‹‹ሁዳዴ ጾም›› ይባላል፡፡ ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲኾን፣ ዐቢይ ጾምም ከአጽዋማት ዅሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው /አሞ.፯፥፩/፡፡ ሦስተኛ ‹‹በአተ ጾም›› ይባላል፡፡ የጾም መግቢያ፣ መባቻ ማለት ነው፡፡ አራተኛ ‹‹ጾመ ዐርባ›› ይባላል። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ፵ ቀን ስለኾነ /ማቴ.፬፥፩/፡፡ አምስተኛ ‹‹ጾመ ኢየሱስ›› ይባላል፡፡ ጌታችን እርሱ ጾሞ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፡፡ ስድስተኛ ‹‹ጾመ ሙሴ›› ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ጾመ ድጓው ‹‹ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት›› እያለ ስለዘመረ /የሰኞ ዕዝል/፡፡
🌾✞ ከዐቢይ ጾም ሳምንታት መካከል የመጀመሪያው ሳምንት ‹‹ዘወረደ (ዘመነ አዳም)›› ይባላል፡፡ ዘወረደ ማለት ከላይ የመጣ፣ የወረደ ማለት ነው፡፡ ይህም አምላካችን አዳምንና ልጆቹን ከሞት ለማዳን ሲል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መኾኑንና የፈጸመውን የማዳን ሥራ ያመለክታል፡፡ ‹‹ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደሰማይ የወጣ የለም›› ካለው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በመነሣት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኵሉ ዘየሐዩ በቃሉ›› በማለት በጾመ ድጓው መጀመሪያ ላይ ይህን ዕለት ገልጾታል፡፡ ትርጕሙም ‹‹አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አምላክ አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይ ሥልጣን ያለው የዅሉ ጌታ እንደኾነም ምንም አላወቁም›› ማለት ነው፡፡ ይህም ድርሰት በቤተ ክርስቲያናችን የጾም መጀመሪያ የኾነው ዕለተ ሰንበት ዋዜማ፣ መግቢያ (መሐትው) ኾኖ ከዋዜማ በፊት ምንጊዜም በየዓመቱ ይቆማል፤ ይዘመራል፤ ይመሰገናል፡፡
🌾✞ በዚህ ሳምንት በተለይም እሑድና ሰኞ የሚነገሩት ውዳሴያት ከመጻሕፍተ ኦሪትና ነቢያት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ሁለተኛም ሳምንቱ ‹‹ሙሴኒ›› በመባል ይታወቃል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ለማዳን ከሰማይ መውረዱንና በመስቀል መሰቀሉን ስለሚያወሳ ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ይባላል። ሕርቃል (ኤራቅሊየስ) የቤዛንታይን ንጉሥ ነበር፡፡ ይህ ሳምንት በስሙ የተጠራበት ምክንያት በዘመኑ ፋርሶች ኢየሩሳሌምን ወርረው፣ የጌታችንን መስቀል ማርከው ወስደውት ነበር፡፡ እርሱ ወደ ፋርስ ዘምቶ መስቀሉን ከእነርሱ ነጥቆ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሷል፡፡
🌾✞ ሕርቃል ከፋርሶች ጋር ከመዋጋቱ በፊት ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው ‹‹ነፍስ የገደለ ሰው እስከ ዕድሜ ልኩ ይጹም›› ብለው ሥርዓት ሠርተዋልና ጾሙን ፈርቶ ስለነበር በኢየሩሳሌም የነበሩ ምእመናን አሳቡን ደግፈው ‹‹አንተ ጠላታችንን አጥፋልን፤ መስቀሉን አስመልስልን እንጂ የአንድ ሰው ዕድሜ ቢበዛ ሰባ፣ ሰማንያ ዓመት ነው፡፡ ጾሙን አምስት አምስት ቀን ተከፋፍለን እኛ እንጾምልሃለን›› ብለው ጾመውለታል፡፡ ይህንን መሠረት በማድረግ ያላወቁት አንድ ጊዜ ጾመው ትተውታል፡፡ ያወቁት ግን ቀድሞም ሐዋርያት ጾመውታል ብለው ሥርዓት አድርገው በዓመት በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ላይ ጾመ ሕርቃል እያሉ የሚጾሙት ኾነዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ይህንን ሥርዓት መሠረት በማድረግ ከጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንት ጾመ ሕርቃል በሚል ስም ሰይማ እንዲጾም አድርጋለች (የመጋቢት ፲ ቀን ስንክሳርን ይመልከቱ)፡፡

🌾✞ በቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ ዘወረደ እየተባለ የሚታወቀው፣ በጾመ ዐርባው ወቅት በተለይም በመጀመሪያው ሳምንት የሚገኘው ድርሰት በነግህ በሠለስት፣ በቀትርና በሠርክ እንደዚሁም ቅዳሜና እሑድ በሌሊት የሚዘመር ነው፡፡ በውስጡም የያዘው ፍሬ ሐሳብ የጾምን፣ የጸሎትን፣ የምጽዋትንና የፍቅርን ጠቃሚነት አጕልቶ የሚያስተምር ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ጾመ ድጓው ‹‹አዘዞ እግዚአብሔር ለሙሴ ወይቤሎ ሰብእከ ወላህምከ ወኵሉ ቤትከ ያዕርፉ በሰንበት፤ እግዚአብሔር ሙሴን ሕዝብህ የከብትህ መንጋህ ቤተሰብህ ዅሉ በሰንበት ቀን ከድካማቸው ይረፉ በማለት አዘዘው፤›› በማለት ሰንበት ለሰው ልጆች ብቻ ሳይኾን፣ ሕይወት ላለው ነገር ዅሉ ጸጥታና ሰላም የሰፈነባት የዕረፍት ቀን ስለመኾኗ ተናግሯል /ዘፀ.፳፥፲፤ ፳፫፥፲፪/፡፡ በዚህም ወቅቱ ‹‹ዘመነ ጾም›› ወይም ‹‹ጾመ ሙሴ›› ይባላል፡፡
🌾✞ በአጠቃላይ ጾምን መጾም የፈቃድ ብቻ ሳይኾን የትእዛዝም ነው፡፡ ነቢዩ ኢዩኤል ‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምሕላ …፤ ጾምን ያዙ፤ አጽኑ፡፡ ምሕላንም ዐውጁ፡፡ ሸማግሌዎቹን ከፈጣሪያችን ቤት ሰብስባችሁ በአንድነት ኾናችሁ ወደ እግዚአብሔር ጩኹ (ለምኑ)፤›› ብሏል ኢዩ.፩፥፲፩፤ ፪፥፲፪፤ ፲፪፥፲፭-፲፮/፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ወኩኑ ላእካነ ለእግዚአብሔር በጾም ወበንጽሕ፤ በጾም፣ በንጽሕና ተወስናችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤›› ብሏል /፪ቆሮ.፮፥፬-፮/፡፡ ጾም ባያስፈልግ ኖሮ ጌታችን ‹‹በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትኹኑ … ስለ ጽድቅ የሚራቡ የሚጠሙ ንዑዳን ክብራን ናቸው፤›› ባላለም ነበር /ማቴ.፭፥፮-፲፮/፡፡ ነቢዩ ዳዊትም ‹‹ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅባት በማጣት ከሳ፤›› /መዝ.፻፰፥፳፬/ ማለቱ የጾምን አስፈላጊነት ያስረዳል /ዳን.፱፥፫-፬፤ ፲፬፥፭/፡፡ በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ ርኩስ (ሰይጣን) እንኳን በጾም የሚወገድ መኾኑን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናግሮአል /ማቴ.፲፯፥፳፩፤ ማር.፱፥፪/።
🌾✞ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹ሙሽራውን ከእነሱ ለይተው የሚወስዱበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ያን ጊዜ ይጾማሉ፤›› ያለውን የጌታን ቃል መሠረት በማድረግ ጌታችን ሞቶ ከተነሣ እና ካረገ በኋላ ጾመዋል፤ የጾምንም ሕግ ሠርተዋል /ሐዋ.፲፫፥፫/፡፡ ሠለስቱ ምዕትም ‹‹ሐዋርያት የጾሙትንና እንዲጾም የወሰኑትን መጾም ይገባል›› ብለው አጽዋማትን እንድንጾም መወሰናቸው ይህን የጌታችንን ቃል መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሠራዔ ሕግ እንደመኾኑ ዐርባ ቀን ዐርባ ሌሊት ጾሞ እንጂ ዝም ብሎ ጾሙ አላለንም፡፡ ስለዚህ ጾም ትእዛዝ (ሕግ) መኾኑን ተገንዝበን ዅላችንም መጾም አለብን።
✍በሊቀ ጉባኤ ቀለመወርቅ ውብነህ
⛪️ መጪውን የዐቢይ ጾም የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርክልን፤ ተስፋ የምናደርጋትን መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በጾሙ በርትተን በጸሎትና በስግደት ታግዘን አምላካችን እግዚአብሔር መልካሙን ሁሉ ያደርግልን ዘንድ ልንማጸነው ይገባል፡፡
🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞🙏
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
🌾✞ በአጠቃላይ ጾምን መጾም የፈቃድ ብቻ ሳይኾን የትእዛዝም ነው፡፡ ነቢዩ ኢዩኤል ‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምሕላ …፤ ጾምን ያዙ፤ አጽኑ፡፡ ምሕላንም ዐውጁ፡፡ ሸማግሌዎቹን ከፈጣሪያችን ቤት ሰብስባችሁ በአንድነት ኾናችሁ ወደ እግዚአብሔር ጩኹ (ለምኑ)፤›› ብሏል ኢዩ.፩፥፲፩፤ ፪፥፲፪፤ ፲፪፥፲፭-፲፮/፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ወኩኑ ላእካነ ለእግዚአብሔር በጾም ወበንጽሕ፤ በጾም፣ በንጽሕና ተወስናችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤›› ብሏል /፪ቆሮ.፮፥፬-፮/፡፡ ጾም ባያስፈልግ ኖሮ ጌታችን ‹‹በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትኹኑ … ስለ ጽድቅ የሚራቡ የሚጠሙ ንዑዳን ክብራን ናቸው፤›› ባላለም ነበር /ማቴ.፭፥፮-፲፮/፡፡ ነቢዩ ዳዊትም ‹‹ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅባት በማጣት ከሳ፤›› /መዝ.፻፰፥፳፬/ ማለቱ የጾምን አስፈላጊነት ያስረዳል /ዳን.፱፥፫-፬፤ ፲፬፥፭/፡፡ በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ ርኩስ (ሰይጣን) እንኳን በጾም የሚወገድ መኾኑን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናግሮአል /ማቴ.፲፯፥፳፩፤ ማር.፱፥፪/።
🌾✞ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹ሙሽራውን ከእነሱ ለይተው የሚወስዱበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ያን ጊዜ ይጾማሉ፤›› ያለውን የጌታን ቃል መሠረት በማድረግ ጌታችን ሞቶ ከተነሣ እና ካረገ በኋላ ጾመዋል፤ የጾምንም ሕግ ሠርተዋል /ሐዋ.፲፫፥፫/፡፡ ሠለስቱ ምዕትም ‹‹ሐዋርያት የጾሙትንና እንዲጾም የወሰኑትን መጾም ይገባል›› ብለው አጽዋማትን እንድንጾም መወሰናቸው ይህን የጌታችንን ቃል መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሠራዔ ሕግ እንደመኾኑ ዐርባ ቀን ዐርባ ሌሊት ጾሞ እንጂ ዝም ብሎ ጾሙ አላለንም፡፡ ስለዚህ ጾም ትእዛዝ (ሕግ) መኾኑን ተገንዝበን ዅላችንም መጾም አለብን።
✍በሊቀ ጉባኤ ቀለመወርቅ ውብነህ
⛪️ መጪውን የዐቢይ ጾም የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርክልን፤ ተስፋ የምናደርጋትን መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በጾሙ በርትተን በጸሎትና በስግደት ታግዘን አምላካችን እግዚአብሔር መልካሙን ሁሉ ያደርግልን ዘንድ ልንማጸነው ይገባል፡፡
🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞🙏
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
Telegram
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
🌾✞ #የመንፈስ_ስንቅ ✞🌾
❖ውድ የተዋህዶ ልጆች እጅግ ጠቃሚ የሆነ ምክር እነሆ፤ ሁሉም ልብ ብሎ ሊሰማውና ሊተገብረው የሚገባ መንፈሳዊ ስንቅ፦
❖የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ፫ኛው የግብፅና የአሌክሳንድሪያ ሊቀ ጳጳሳት መንፈሳዊ ስብከት፤ በእውነቱ በረከታቸውና ጸሎታቸው አይለየን አሜን፡፡🙏

“…እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።” ራእ 1፥7
"…በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤ በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና። እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ። ማቴ፥ 24 ፥ 19-22
“… አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።” ራእ 22፥20

❤1