Telegram Web Link
Audio
🌾#በዓታ_ለማርያም🌾
https://www.tg-me.com/EOTC2921
የእመቤታችንን ጣዕሟን ፍቅሯን ረድኤትና በረከቷን ያሳድርብን

🎤ስብከት በዲያቆን_ደረጄ
Audio
🌾#ሐና_እና_እያቄም🌾
https://www.tg-me.com/EOTC2921

ሐና እና እያቄም በስለት ያገኙሽ /፪/
ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ/፪/
👍1
🌾#ሐናና_ኢያቄም🌾
📖ጥራዝ ፬.ቁ.፹፭
https://www.tg-me.com/EOTC2921

ሐናና ኢያቄም በስለት ያገኙሽ/፪/
ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ/፪/ /፬/ ኧኸ

ለመዳን ምክንያት ድንግል አንቺ ነሽ/፪/
ንጽሕት ቅድስት እያልን እናመስግንሽ/፪/ /፬/ ኧኸ

በቤተ መቅደስ ኖርሽ በቅድስና/፪/
እየተመገብሽ ሰማያዊ መና/፪/ /፬/ ኧኸ

ዕፁብ ነው ድንቅ ነው የአምላካችን ሥራ/፪/
የሰጠን ድንግልን እንዳናይ መከራ/፪/ /፬/ ኧኸ
ዘማሪት አዳነች አስፋው
🌾✞*#አንቺ_የወይን🌾
📖ጥራዝ ፪.ቁ.፯
https://www.tg-me.com/EOTC2921

አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ/2/
ምግብ ሆኖ/2/ ተሰጠን ፍሬሽ ለኛ ቤዛ/2/ ኧኸ
ባንቺ ሰማይነት ድንግል የወጣው ፀሐይ /2/
ብርሃን ነው /2/ ለጻድቃን ስሙም አዶናይ /2 ኧኸ

ፊደል ትመስያለሽ ድንግል ወንጌል ትወልጃለሽ /2/
ለመላእክት /2/ የማይቻል ነበልባሉን የቻልሽ /2/ኧኸ
#አዝ---✞__✞__✞---
የመሶብ ምሳሌ ድንግል የኰከብ መገኛ /2/
በሥጋችን በነፍሳችን እንዳንራብ አንቺ አለሽን ለኛ /2/ ኧኸ
#አዝ---✞__✞__✞---
3👍1
🌾#አንቲ_ውእቱ🌾
📖ጥራዝ ፬.ቁ.፹፩


አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን ዘነበርኪ ውስተ
ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት /2/
ወመላእክት ያመጽኡ ሲሳየኪ ያመጽኡ/2/

#ትርጉም
እመቤቴ ሆይ ከንጹሐን ሁሉ ንጽሕት
ሆነሽ መላእክትም ምግብሽን እያመጡልሽ
እንደ ታቦት በቤተ መቅደስ ኖርሽ፡፡
ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ
👍2
Audio
🌾#ኢያቄም_ወሃና🌾
https://www.tg-me.com/EOTC2921

ኢያቄም ወሃና እናት አባትሽ
ቤተ እግዚአብሔር ወስደው ስለት የሰጡሽ
መና ከሰማያት የወረደልሽ
እጹብ ድንግል የሆንሽ ማርያም አንቺ ነሽ
ኦ እመ ክርስቶስ ማርያም አንቺ ነሽ /፬/

🎤ዘማሪ ክብሮም ግደይ
👍5
#በእንተ_ልደቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾

፩. #በኮከብ_መጽኡ
በኮከብ መጽኡ(፪) ሰብአ ሰገል
ለአማኑኤል(፬) ይስግዱ ለአማኑኤል

፪. #ቤዛ_ኩሉ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ(፪)
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ(፬)
የዓለም ሁሉ መድኀኒት ዛሬ ተወለደ(፪)
የዓለም ሁሉ መድኀኒት ዛሬ ተወለደ(፬)

፫. #አንፈርዐጹ
አንፈርዐጹ ሰብአ ሰገል(፪)
አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ(፪)

፬. #አንፈርዐጹ
አንፈርዐጹ ሰብአ ሰገል ረኪቦሙ ህፃነ ህፃነ(፪)
ዘተወልደ ለነ(፬) ህፃነ ዘተወልደ ለነ

፭. #በቤተልሔም_ተወልደ
በቤተልሔም ተወልደ(፪) አማኑኤል
እምዘርአ ዳዊት (፬) ተወልደ አማኑኤል

፮. #ተወልደ_ኢየሱስ
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም(፪) ዘይሁዳ በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ(፪) በቤተልሔም

፯. #ወወለደት
ወወለደት ወልደ ዘበኩራ(፪)
መንጦላዕተ ደመና ሠወራ(፬)

፰. #ለዘተወልደ
ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ምንተንብሎ ናስተማስሎለመድኀኒነ
አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ(2) ከራድዮን

፱. #ስብሐት_ለእግዚአብሔር
ስብሐት ለእግዚአሔር በሰማያት(፪)
ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብዕ ሃሌሉያ(፫)ሃሌ(፪)ሉያ

፲. #አማን_በአማን
አማን በአማን(፪) መንክር(፪)
መንክር ስብሐተ ልደቱ(፬)
እውነት በእውነት(፪) ድንቅ ነው (፪)
ድንቅ ነው የጌታ ልደቱ(፬)

፲፩. #ይትፌስሃ
ይትፌስሃ አድባረ ጽዮን ወይትሀስያ አዋልደ ኢትዮጵያ
እስመ ተወልደ ብኁተ ልደት መድኀኔዓለምበኢየሩሳሌም መድኀኔዓለም

፲፪. #ዮም_ሰማያዊ
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል
ርዕይዎ ኖሎት (፪)አእኮትዎ መላእክት(፪)

፲፫. #ወእንዘ_ትፈትል
ወእንዘ ትፈትል(፪)ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ
ወይቤላ(፪) እስመ ረከብኪ ሞገሰ በሀበ እግዚአብሔር

፲፬. #ወእንዘ_ትፈትል
ወእንዘ ትፈትል/፪/ ወርቀ ወሜላት
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም

፲፭. #ለድንግል
ለድንግልገብርኤል አብሰራ
ሚካኤል/፪/በክነፍ ጾራ/፪/መንጦላዕተ ደመና ሠወራ

፲፮. #ሊቀ_መላእክት
ሊቀ መላእክት ገብርኤል ዘአብሠራ ለድንግል
ኃያል ኃያል/፬/ ሰዳዴ ሳጥናኤል ኃያል ገባሬ ኃይል

፲፯. #መጽአ_ከመ_ይቤዙ
መጽአ ከመ ይቤዙ ዓለም
የሀበነ ሰላመ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ

፲፰. #በጎለ_እንስሳ
በጎለ እንሰሳ
በጎለ እንሰሳ ተወልደ አማኑኤል

፲፱. #ብርሃን_ዘመፅአ
ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም(፪)
ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም(፬)

፳. #ኢየሱስ_ክርስቶስ
ኢየሱስ ክርስቶስ መፅአ ውስተ ዓለም
በብርሃኑ ንዑ ናንሶሱ

፳፩. #መድኀኒነ
መድኀኒነ ተወልደ ነዋ መድኀኒነ ተጠምቀ ነዋ(፪)
ይዕዜኒ ለሰላም ንትልዋ(፬)

፳፪. #ኢየሩሳሌም_በሆን
እንደ ዮሴፍ ወይ እንደ ሰሎሜ በሆን
ኢየሩሳሌም(3) በሆን አምላክ ሲወለድ ባየን
እንደ እረኞች ወይ ሰብአ ሰገልን በሆን
ኢየሩሳሌም(3) በሆን አምላክ ሲወለድ ባየን

፳፫. #በጎል_ሰከበ
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ከሉ ዓለም(፪)ዮም ተወልደ
በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ
የዓለም መድኀኒት(፪) ዛሬ ተወለደ

፳፬. #እም_ሰማያት
እም ሰማያት ወረደ ወእማርያም ተወልደ(፪)
ከመይኩን ቤዛ(፪) ለኩሉ ዓለም ለብሰ ሥጋ ማርያም
ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ
እንዲሆነን ቤዛ(፪)ለዓለሙ ሁሉ ተዋሐደየማርያምን ሥጋ

፳፭. #የምስራች
የምስራች ደስ ይበለን(፪)
የዓለም መድኃኒት ተወለደልን
ምስራች ደስ ይበለን
የምሥራች ደስ ይበለን(፪)
ጌታችን ተወልዶ አይተነው መጣን(፪)
ንጉሥ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ
ፈልጋችሁ አምጡት በቀን በጨለማ(፪)
ሰብአ ሰገል እንደታዘዙት
በኮከብተመርተው ህፃኑን አገኙት(2)
ሰገዱለት ከመሬት ወድቀው
ወርቅዕጣን ከርቤውንም ሰጥተው(2)

፳፮. #ይኸው_ተወለደ
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)
ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ(3)
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ(3)
ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ(3)
የእስራኤል ንጉሥ ተወልዷል እያሉ(3)
ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ይዘው(3)
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው(3)
ህፃናት እንሂድ ከልደቱ ቤት(3)
ውኃው ሆኗልና ማርና ወተት(3)
በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደእነግዳ(3)
ብስራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ(3)

፳፯. #ሳርቅጠሉ_ሰርዶው
ሳር ቅጠሉ ሰርዶ ሰንበሌጥ ቄጤማው
በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምለም የነበረው
በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተውጠው
ጌታ መወለዱን የምስራች ሰምተው
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ
የታደሉ እረኞች ያደሩ በትጋት
ብርሃን ሆነላቸው በእኩለሌሊት
ጥሪ ተደርጎለት ከሰማይ ሰራዊት
ለመመልከት በቃ የጌታውን ልደት

እረኝነት ትንሽ የወራዳ ግብር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር
አምላክ የመረጠው መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ

የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ
ጌታ ተወለደ የምስራች በሉ
ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉስ
ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ

የሩቅ ምስራቅ ሰዎችሰብአ ሰገል ሰምተው
ሊሰግዱለት መጡ በኮከብ ተመርተው
ዕጣንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ
እንደየስርአቱ እጅ መንሻ ሰጡ
ስለተወለደ መድኅን የእኛ ተስፋ
በደል ተወገደ ኃጢያትም ጠፋ

፳፰. #አንቺ_ቤተልሔም
አንቺ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ መሬት
በአንቺ ተወለደ የዓለም መድኃኒት

ለአዳም ክብር ሲሻ ቤተልሔም
ለሁሉም ሰላም ”
ዛሬ ተወለደ ”
ከድንግል ማርያም ”

እጅ መንሻ አቀረቡ ቤተልሔም
የምሥራቅ ነገሥታት ”
በከብቶች በረት ”
ተኝቶ ላገኙት ”
እሥራኤል ሕዝቤን ቤተልሔም
የሚጠብቃቸው ”
ከአንቺ ይወጣል ብሎ ”
እንደ ነገራቸው ”

፳፱. #እሰይ_እሰይ_ተወለደ
እሰይ እሰይ ተወለደ (፪)
ከሰማየ ሰማያት ወረደ (፪)
ከድንግል ማርያም ተወለደ

እሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
ቸሩ አባታችን ”
መች ትገኝ ነበረ ”
ገነት ምድራችን ”

ብርሃን ወጣላቸውእሰይእሰይ
ለመላ ሕዝቦቹ ”
በጨለማ ጉዞ ”
እንዲያ ሲሰላቹ ”

እንደ ጠል ወረደ እሰይ እሰይ
ከሰማይ ወደ እኛ ”
ወገኖቹን ሊያድን ”
ከኃጢአት ቁራኛ ”
እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ
አንድያ ልጁን ”
እርሱ ወዷልና ”
እንዲሁ ዓለሙን ”

፴. #አዳምን_ያልተወው
አዳምን ያልተወው እንደተሰደደ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተወለደ (፪)
አምላካችን መድኃኒታችን
ተወለደ ለነፃነታችን(፪)
አዳምን ያልተወው እንደ ተጨነቀ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተጠመቀ (፪)
አዳምን ሊጠራ የመጣው ሙሽራ
በገሊላ መንደር ለሠርግ ተጠራ(፪)
ሠርግ ቤት እንዳለ በክብር ተቀምጦ
የወይን ጠጅ ሆነ ውሃው ተለውጦ (፪)
እጅግ ያስደንቃል የጌታችን ሥራ
በገሊላ መንደር ይህን ተአምር ሠራ (፪)
ጌታችን አንድ ቀን ያደረገው ተአምር
ሲያስደንቅ ይኖራል ይህን ሁሉ ፍጡር (፪)
🥰6👍54🙏3👏1😍1
🌾#ቅዱስ_ገብርኤል🌾
⛪️ ታኅሣሥ 19

❖ “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” መዝ.33፥7፤ ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ከእግዚአብሔር ተልኮ በዙሪያቸው ሆኖ ከመከራ እንደሚያድናቸው ያስተምራል፡፡ የመላእክት አንዱ ተግባር መዳንን ይወርሱ ዘንድ ያላቸውን ሰዎች መጠበቅ መሆኑ ተጽፏል፡፡
❖ “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” ዕብ.1፥14፤ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱን ሁሉ ሲያስገዛለት በትዕቢት ተሞልቶ “በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም የሚቃወመኝም የለም፡፡” ኢሳ.10፥13-14 ብሎ በመታበይ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ ዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ አቆመው፡፡ በግዛቱ በልዩ ልዩ የሥልጣን እርከን ላይ ያሉትን ሹማምንቱንና ገዢዎችን ሰበሰባቸው፤ “የመለከትና የእንቢልታ የመሰንቆና የክራር የበገናና የዋሽንትን የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ወድቃችሁ ንጉሥ ናብከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል ስገዱ፡፡ ወድቆም ለማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣል” ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህን አዋጅ የሰሙ የንጉሥ ሹማምንት ሁሉ የመለከቱና የእንቢልታው እንዲህም የዘፈን ድምፅ በተሰማ ጊዜ ተደፍተው ለወርቁ ምስል ሰገዱ፡፡
❖ በባቢሎን አውራጃዎች ላይ የተሾሙ አዛርያ(ሲድራቅ)፣ አናንያና(ሚሳቅ) ሚሳኤል(አብደናጎ) ግን ንጉሥ ላቆመው ምስል አልሰገዱም፡፡ ነገር ሠሪዎችም ይህንን ወሬ ለንጉሥ ነገሩት፤ ንጉሥም እጅግ ተቆጥቶ ወደ እርሱ አስጠራቸው፡፡ እርሱ ላቆመው ለወርቅ ምስል ያልሰገዱ እንደሆነ እጅና እግራቸውን ታስረው ወደ እቶን እሳቱ እንደሚጣሉ አስጠነቀቃቸው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅ ግን “ናብከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አንፈልግም፡፡ ንጉሥ ሆይ! እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፣ ከሚነደውም ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፤ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ፣ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ” ብለው መለሱለት፡፡
❖ የንጉሥ ናብከደነፆር ቁጣ ከፊት ይልቅ እጅግ ነደደ እሳቱንም ሰባት እጥፍ እንዲያቀጣጥሉና እነዚህን ሦስት ብላቴኖች እጅና እግራቸውን አስረው ከእነ ማዕረገ ልብሳቸው ከእቶን እሳት ውስጥ እንዲጨምሩአቸው ትእዛዝን አስተላለፈ። ትእዛዙ አስቸኳይ ነበርና ወደ እሳት ጣሏቸው። ወደ እሳቱ የጣሏቸውም ኃያላን በእሳቱ ወላፈን ተገርፈው ሞቱ፡፡ እንዲህ ሲሆን ሳለ ግን ሠልስቱ ደቂቅ ወደ አምላካቸው “በፍጹም ልባችን እናምንሃለን፣ እንፈራሃለን፣ አታሳፍረን እንጂ ገጸ ረድኤትህንም እንፈልጋለን፡፡” እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ ነቢያትም በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነበረባቸው መከራና ስቃይ ያድናቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጮሁ ይለምኑ ነበርና። "አንስእ ኃይለከ ወነዓ አድኅነነ አምላክ ኃያላን ሚጠነ" እያሉ ለምነዋል።
❖ በብዙ ትንቢትና ኅብረ አምሳል የእግዚኣብሔርን መምጣት በትንቢት ተናግረዋል። እግዚአብሔር አምላክ ጸሎታቸውን ተቀበለ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልንም ከመጣባቸው መከራ ይታደጋቸው ዘንድ ላከው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም እስራታቸውን ፈታ፤ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዘቀዘው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅም መልአኩን ልኮ ከዚህ እቶን እሳት ያዳናቸውን አምላክ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር፤ ስምህም ለዘለዓለም የተመሰገነና የከበረ ነው” በማለት አመሰገኑት፡፡ ምስጋናውም የቀረበው ቅዱሳን መላዕክት ከሠለስቱ ደቂቅና ቅዱስ ገብርኤል ጋር በእሳቱ ውስጥ እየተመላለሱ አመስግነዋል። ሠለስቱ ደቂቅም ከእስራታቸው ተፈተዋል። ይህም በሐዲስ ኪዳን ያሉ ምዕመናን ከኃጢአት እስራት በተፈቱ ጊዜ በጌታ የልደት ወቅት ከመላዕክት ያመሰገኑት ምስጋና ምሳሌ ነው።
❖ "በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው። በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ። እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ"ሉቃ.2፥6 ይላል። ይህ የሚያስረዳን ሠለስቱ ደቂቅ የእግዚአብሔር ልጅ በአምሳለ ገብርኤል በተገለጠላቸውና ባዳናቸው ጊዜ ከመላዕክት ጋር እንዳመሰገኑ ሁሉ በጌታ ልደት ጊዜም እረኞችና መላዕክት በሰው ልጅ ድኅነት ደስ ተሰኝተው "ስብሐት ለእግዚኣብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ" ብለው አመስግነዋል።
❖ የንጉሥ ናብከደነፆርም ሠልስቱ ደቂቅ እሳቱ አንዳች ጉዳት ሳያደርስባቸው በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ ከእነርሱ ጋር አራተኛውንም ተመለከተ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊቀ ካህናቱን ቀያፋን ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ “ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡምን” ዮሐ.11፥49 ብሎ እንዳናገረው እንዲሁ ናብከደነፆርንም “እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን በዚያ አያለሁ ምንም የነካቸው የለም፤ የአራተኛውም መልክ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል” ብሎ እንዲናገር አደረገው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅን መልክ ያለው፤ በኋላም መልአክ ብሎ የተናገረለት ቅዱስ ገብርኤልን ነበር፡፡ ምስጢሩ ግን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በኃለኛው ዘመን ሰው ሆኖ እንዲወለድና የአዳም ልጆችን ሁሉ ሲያቃጥል ከነበረው የኃጢአት እሳት እንደሚያድን ለናቡከደነፆር ሲገልጥለት ነው። ❝እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?❞ አላቸው፤ ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ" ማቴ 16፥16 እንዲል። እንግዲህ ይህን ለቅዱስ ጴጥሮስ የገለጠለትን ምስጢር እግዚኣብሔር በቸርነቱ ለናቡከደነፆር ገልጦለት እንደነበር ማስተዋል ያስፈልጋል።
❖ እግዚአብሔር ለሰዎች በተለያየ መልክ ይገለጥላቸዋል። በዚህ ታሪክ ላይ እንደምናየው የእግዚአብሔር ልጅ በአምሳለ ገብርኤል እንደተገለጠላቸው ያሳያል። ለዚህ ማረጋገጫ መልክዐ ማርያም በሚባለው የጸሎት መጽሐፍ ላይ እንዲህ ይላል። "እግዚአብሔር ኀቤኪ ፈነዎ ቃሎ ገብርኤልሃ አስተማሲሎ። ማርያም አምላከ ዘወለድኪ በተደንግሎ። ..." ይላል። ይህም ማለት እግዚአብሔር አብ ቃል የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስን በገብርኤል አምሳል ወደ አንች ላከው አንችም ማርያም ሆይ አምላክን በድንግልና ወለድሽው ማለት ነው።
#ይቀጥል ---፪
👍1
❖ አንድም ገብርኤል ማለት ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነው (ገብርኤል ብሂል ብእሴ ወአምላክ) እንዲል። የዚህ መልአክ ስም አስቀድሞ የአምላክን ሰው መሆን ይናገራል። ናብከደነፆርም ወደ እሳቱ እቶን በመቅረብ እነዚህ ብላቴኖችን “እናንተ የልዑል አምላክ ባሮች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው፡፡” እነርሱም ከእሳቱ ወጡ ሹማምንቱና መኳንንቱ፣ አማካሪዎችና የሀገር ገዢዎች ሁሉ እሳቱ በእነዚህ ብላቴኖች ላይ አንዳች አቅም እንዳልነበረው፣ ከጠጉራቸው ቅንጣት አንዱን እንኳ እንዳላቃጠለው፣ ሰናፊናቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ፡፡ (እሳቱ የሲኦል ሠለስቱ ደቂቅ ደግሞ የቅዱሳን አበው ምሳሌ ናቸው። ይህም በብሉይ ኪዳን ዘመን ምንም እንኳን አበው ፅድቅ ማድረግ ቢችሉም ድኅነት ያልነበረበት ዘመን ስለነበረ ሁሉም መኖሪያቸው በሲኦል ውስጥ ነበረ።

❖ "ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል" ኢሳ.64፥6 እንዲል። ነገር ግን የእግዚኣብሔር ቸርነት ጠብቋቸው የሲኦል እሳት ግን አያቃጥላቸውም ነበር። ናቡከደነፆር የዲያብሎስ ምሳሌ ነው። ምስሉን አሰርቶ ሲያሰግዳቸው እንደኖረ ዲያቢሎስም ህዝበ እስራኤልን 5500 ዘመን ሙሉ ጣኦት ሲያስመልካቸው ኖሯል። በኃላ ግን ናቡከደነጾር ሰለስቱ ደቂቅ እንዳልተቃጠሉ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር አዳኝነትና አምላክነቱን በመመስከር ከእሳቱ እንዲወጡ እንዳዘዘ ሁሉ ዲያቢሎስም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ሩቅ ብእሲ መስሎት ነፍሱን በሲኦል ስጋውን በመቃብር ለመቆራኘት በመጣ ጊዜ በእሳት አለንጋ አስሮ በገረፈው ጊዜ የእግዚአብሔርን አምላክነት መስክሮ ላጠፋው ጥፋቱ ካሳ እንዲሆን በሲኦል ያሉ ነፍሳትን በሙሉ እንዲወስድ ፈቅዶለታል። "መኑ ዝንቱ ዉዕቱ ስጋ ለቢሶ ዘሞዓኒ" እንዳለ። በዚህ መሰረት ሠለስቱ ደቂቅ በዚህ እሳት ሳይቃጠሉ በናቡከደነፃር ትዕዛዝ እንደወጡ ሁሉ በሲኦል ያሉ ነፍሳትም ራሱ ዲያቢሎስ ፈቅዶ እንደወጡ ያሳያል። በጣም የሚገርመው ናቡከደነፆር የእግዚአብሔርን አምላክነት እንዲህ ብሎ መሰከረ። "መንግስቱ ዘለዓለም ወምኩናኑከኒ ለትውልደ ትውልድ" አለ ይህም መንግስቱ ለዘለዓለም አገዛዙም ለትውልድና ትውልድ ነው" ማለት ነው። ዲያቢሎስም በእለተ አርብ ጌታ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት የእግዚአብሔርን አምላክነት በሚገባ መስክሯል በራሱም ፈቃድ ግዛቱን ሁሉና 5500 ዘመን ሲፈፀም በሶኦል የነበሩ ነፍሳትን አስረክቧል።
❖ ንጉሥ ናብከደነፆርም መልአኩን ልኮ ያዳናቸውን የእነዚህን ቅዱሳንን አምላክ አመሰገነ፡፡ በእነርሱ አምላክ ላይም የስድብን ቃል የሚናገር ሰው እንደሚገደልና ቤቱም የጉድፍ መጣያ እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ አዛርያ አናንያ ሚሳኤልም በንጉሡና በሹማምነቱ ዘንድ ሞገስ አገኙ፤ በክብርም ከፍ ከፍ አሉ። የእግዚኣብሔርም ስም በአህዛብ ሁሉ ተመሰገነ (ዳን.3)። ይህም ቅዱስ ማቴዎስ ከተናገረው ጋር ይዛመዳል እንዲህ ብሏል። "መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።" ማቴ 5፥16 የሰለስቱ ደቂቅ መልካም ስራ በአህዛብ ሁሉ ፊት ብርሃን ሆነ።
❖ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን መንጎቿ የእምነትን ፍሬ ከእነዚህ ብላቴኖች ተምረው እግዚአብሔርን በማምለክ እንዲጸኑና የመልአኩን የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት እንዲረዱ ታህሳስ 19 ቀን ይህን ዕለት ትዘክራለች። በታላቅ ድምቀትም ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እምነት በድርጊት ሊታይ የሚገባው ክርስቲያናዊ ተግባር ነው፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ አምናለሁ የሚል ሁሉ ካመነበት ጊዜ አንስቶ ክርስቶስን መስሎ ለመኖር ሊተጋና መስሎ ሊመላለስ ይገባዋል፡፡ በሠልስቱ ደቂቅ የታየው እምነት በአንድ ጀምበር የተገነባ እምነት ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ በአንድ እግዚአብሔር ታምነው በቅድስና ሕይወት በመመላለስ የመጣ እምነት ነው፡፡ እነዚህ ብላቴኖች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኙትን የድል አክሊል ተስፋ አድርገዋልና አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል የነደደውን የእሳት እቶን አላስፈራቸውም፤ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው ጽኑ እምነት በእሳት ተቃጥለው ለመሞት እንኳ አስጨከናቸው። እንዲህም ሆነው በመገኘታቸው በእምነታቸው እግዚአብሔርን ደስ አሰኙት፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ባለሟሉን ቅዱስ ገብርኤልን በመላክ ከእሳቱ እቶን ታደጋቸው፡፡
❖ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው የድኅነት መንገድ የተጀመረው በቅዱስ ገብርኤል ምስራች አብሳሪነት ነው። "በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት"ሉቃ.1፥26 ይላል። ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል እሳቱን ያጠፋላቸው ዘንድ እንደተላከላቸው ሁሉ በሐዲስ ኪዳንም የውርስ ኃጢአት በክርስቶስ መወለድ ሊጠፋ እንዳለው ዜና ይዞ ተላከ።
❖ ይህ በዓል በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ታህሳስ 19 ከቅዱስ ገብርኤል በዓል ጋር እንዲከበር ያደረገው ቅዱስ ደቅስዮስ ነው። ይህም የጌታ ስጋዌ መጋቢት 29 ስለሚከበር ይህ ወቅት ደግሞ ፆም በመሆኑ በፆም ወቅት የስጋዌውን በዓል ማክበር ተገቢ ስላልሆነ ከላይ በተመለከትነው መሰረት በዚህ ቀን ቤተ ክርስቲያን ስጋዌውን ታከብራለች።

🙏 የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን። 🙏
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
👍1
Audio
#እንደ_አናንያ

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
👍2
🌾#በእምነታቸው_ዳኑ🌾
https://www.tg-me.com/EOTC2921

በእምነታቸው ዳኑ ከዚያ ነበልባል /፪/
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል /፪/

ናቡከደነፆር ጨካኙ ንጉስ
በባቢሎን ሀገር ጣዖት የሚያነግስ
እያለ ስገዱ አማኙን ሲያምስ
ወጣቶች ተነሱ በቅናት መንፈስ
#አዝ
ለሰራኸው ጣዖት አንሰግድም እያሉ
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ልባቸውን ሞሉ
የፈጠረን አምላክ ያድነናል ሲሉ
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል /፪/
#አዝ
ነበልባል ነዲዱ እንዲያቃጥላቸው
በጭካኔ መንፈስ አስወረወራቸው
ገብተው ሲጸልዩ እቶን ሳይነካቸው
መልአኩን ልኮ አበረደላቸው
ገብርኤል /፪/ በመስቀሉ
#አዝ
እንደ ሦስቱ ህፃናት በእምነት ለሚቆው
መልአኩን ይልካል እግዚአብሔር ሲረዳው
እሳቱም ይበርዳል መልአኩ ሲነካው
ገብርኤል /፪/ በመስቀል
#አዝ
🎤ሊቀ መዘምራን ዓባይ አጥሌ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ሆይ እወድሻለሁ።
ድንግል ሆይ አንቺን የሰደበ ሰው እንዴት ይኖራል፤ አይኖርም እንጂ። ምክንያቱም በልጅሽ የፍርድ መጽሐፍ ላይ እናት አባቱን የሰደበ ሰው ይሙት ይላልና፤ ታዲያ የአምላክን እናት ሰድቦማ እንዴት ይኖራል?
አባ ፅጌ ድንግል
🥰205👍1👏1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✞🌾

🕊 #ቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት_ሐዋርያዊ 🕊

ታኅሳስ  ፳፬ [24]

🌾#ልደት
መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ  ካህኑና  እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው  ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ [ ከአረማዊ ጋብቻ ] አድኗቸዋል። በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል።

አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24, 1196 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ 24, 1197 ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።

🌾#ዕድገት
የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን " ይሰኛል። ይሕንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን [ብሉያት ሐዲሳትን] ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ  ተቀብለዋል።

🌾#መጠራት
አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ።

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ፤
" ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት [ ተክለ ሥላሴ ] ይሁን። አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ።

🌾#አገልግሎት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ [ ጽላልሽ ] አካባቢ ብቻ በ ፲ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮዽያ ፪ መልክ ነበራት።

፩. ዮዲት [ ጉዲት ] በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል።
፪. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር።

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት  ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ። ሕዝቡን መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው ማርያኖችን [ ጠንቁዋዮችን ] አጥፍተዋል።

🌾#ገዳማዊ_ሕይወት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ ፫ ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል።

እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ፲፪ ዓመታት በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ ፯ ዓመታት በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ  ጋር ለ ፯ ዓመታት በአጠቃላይ ለ፳፮ ዓመታት አገልግለዋል

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ ዞረሬ ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ ፳፪ ዓመታት ቆመው ጸልየዋል። በተሰበረ እግራቸውም ፮ ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ ፯ ዓመታት ጸልየዋል።

🌾#ስድስት_ክንፍ
ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እሥራኤል  የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር።

የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል  ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር።

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም።
🌾✞ በገሃድ፦
- በቤተ መቅደስ ብስራቱን
- በቤተ ልሔም ልደቱን
- በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
- በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
- በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር።
- የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደሆነው  ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ። በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ  እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ጻድቁን ወደሰማይ አሳረገቻቸው።

🌾✞ በዚያም፦
- የብርሃን ዐይን ተቀብለው
- ፮ ክንፍ አብቅለው
- የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
- ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
- ከ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
- ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
- "ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል።

🌾#ተአምራት
የጻድቁ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
- ሙት አንስተዋል
- ድውያንን ፈውሰዋል
- አጋንንትን አሳደዋል
- እሳትን ጨብጠዋል
- በክንፍ በረዋል
- ደመናን ዙፋን አድርገዋል
- ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና።

🌾#ዕረፍት
ጻድቅ ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው አእላፍ ፍሬን አፍርተው በተወለዱ በ፺፱ ዓመት ከ ፰ ወር ከ ፩ ቀናቸው ነሐሴ ፳፬ በ1296 ዓ/ም ዐርፈዋል። ጌታ ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። ፲ ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል።

የጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የቅድስናና የክብር ስሞች፦
፩. ተክለ አብ፤ ተክለ ወልድ፤ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
፪. ፍስሐ ፅዮን
፫. ሐዲስ ሐዋርያ
፬. መምሕረ ትሩፋት
፭. ካህነ ሠማይ
፮. ምድራዊ መልዐክ
፯. እለ ስድስቱ ክነፊሁ [ባለስድስት ክንፍ]
፰. ጻድቅ ገዳማዊ
፱. ትሩፈ ምግባር
፲. ሰማዕት
፲፩. የኢትዮዽያ መነኮሳት አለቃ
፲፪. ፀሐይ ዘበፀጋ
፲፫. የኢትዮዽያ ብርሃኑዋ
፲፬. ብእሴ እግዚአብሔር [የእግዚአብሔር ሰው]
፲፭. መናኒ
፲፮. ኤዺስ ቆዾስ [እጨጌ]

እነዚህ የአባታችን ስሞች እንደዘመኑ ሰው ለመሞጋገስ የወጡ ሳይሆኑ ሁሉም በትክክል ሥራዎቹንና ለቤተ ክርስቲያን የሆነላትን የሚያዘክሩ ናቸው።

እንኳን ለአባታችን ለቅዱስ ተክለ ሐይማኖት የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!!
🥰12👍3👏1🙏1
🙏11🥰53👍2
#ጌታችን_ስለተወለደባት_ምሽት_ሶርያዊው_ቅዱስ_ኤፍሬም_አንዲህ_አለ
🌾🌾🌾🙏🙏🌾🌾🌾

👉‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን ፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
👉ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት ፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት!
👉ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት!
የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት! ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡
👉ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ! የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››

#የገና_አባት (ቅዱስ ኒቆላዎስ) ለድኆች ሥጦታ ይለግስ የነበረ ቅዱስ አባት ነው። ታሪኩም በስንክሳር ታኅሣሥ 10 ላይ ተጽፎአል። "የገና ዛፍ ባሕላችን አይደለም እነርሱ ክረምታቸውን የሚያስታውሱበት ነው ከእኛ ጋር አይገጥምም" "የተወለደውን ክርስቶስ የበዓሉ ማዕከል እንዳናደርግ ያደርገናል" ማለት ትክክለኛ ነገር ነው። Pagan Origin (የባዕድ አምልኮ መነሻ) አለው ብሎ ጣዖት አምልኮ ነው ማለት ግን ከገደብ ያለፈ ድምዳሜ ነው። በከዋክብት ያመልኩ የነበሩት የጥበብ ሰዎች በሚያመልኩት ነገር ወደ ክርስቶስ ተጠርተዋል ፣ የዙሐል ጣዖት ይከበርበት የነበረውን ዕለት ከክርስትና በኋላ በእስክንድርያ የቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን ሆኗል።
👉የራሳችንን የገና ባሕላዊ አከባበሮች የገና ጨዋታን ፣ ቀጤማ መጎዝጎዝ የመሳሰሉትን ማክበር ይገባናል። ከዚያ ውጪ በክርስትና መንፈስ እስከተቃኘና የጌታን በበረት መወለድ ፣ የሰብአ ሰገልን ጉዞ ፣ ከዋክብቱን ፣ የመላእክትን ዝማሬ ፣ የእረኞችን ደስታ ፣ የሰብአ ሰገልን እጅ መንሻ የሚያሳይ እስከሆነ ድረስ የኛ ባሕል ያልሆነውን ሁሉ ጣዖት ነው ብሎ ማንቋሸሽ ፣ የሚያምር ነገርን ሁሉ ማውገዝ ያስመስላል። ቅዱስ ኒቆላስም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምትዘክረው ቅዱስ ስለሆነ አጋጣሚውን ጻድቁን ለማስተዋወቅም ልንጠቀምበት ይገባል። ሥጦታም የምንሠጣጠው የሰብአ ሰገልን ሥጦታ መነሻ አድርገን ሲሆን ልግስናውን ለነዳያን ብናደርገው የበለጠ በረከት እንቀበልበታለን።
በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
👍6
2025/10/20 03:45:39
Back to Top
HTML Embed Code: