🌾✞ #ሕፃን_ተወልዶልናልና ✞🌾
በስመ አብ ወወለወድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
👉ልደታትን ስንመለከት ብዙ አሉ፦ ልደተ አዳም ከምድር፣ ልደተ ሔዋን ከአዳም
፣ልደተ ሙታን ከመቃብር፣ ልደተ ሕፃናት ከእናታቸው ማህፀን የሚጠቀሱት ናቸው፡፡የእነዚህ ሁሉ ልደት ለራሳቸው እንጂ ለእኛ አይደሉም።
👉#ህፃን_ተወለልዶልናልና የሚለው ግን ለእኛ ነው፡፡ የአምላክን መወለድ ብዙ ነቢያት በብዙ ሕብረ ትንቢት
ተናግረዋል በብዙ ሕብረ አምሳል መስለዋል፡፡
👉ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ አይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ዳግምም ዓለማትን በፈጠረበት
በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን።ዕብ፡1፥1 በብዙ ሕበረ አምሳል በብዙ ሕብረ ትንቢት እግዚአብሔር ከተናገረባቸው ነቢያት አንዱ ኢሳይያስ ነው። ኢሳይያስ ከነቢያት ወንድሞች
በተለየ መልኩ የአምላክን ሰው መሆን የተናገረ ነቢይ ነው። መወለዱን፣ስሙን፣ከማን እነደሚወለድ ፣ለሰው ልጆች ያደረገውን የቤዛነት ስራ መከራ መቀበሉን ፣በጎል መወለዱን
በግልፅ ከተናገሩ የተነሳ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ወንጌላዊ ነቢይ
የሚል ቀጽል ሰጥተው ይጠሩታል፡፡የትንቢት መጽሐፉንም ደረቅ
ሐዲስ በማለት ሰይመውታል፡፡ይህም ማለት ስለክርስቶስ መወለድ በምሰሌ ያይደለ በቀጥታ የተናገረ በመሆኑ ነው
ለምሳሌ የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡
👉"ጌታ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ
ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"ኢሳ፡7፥14 ከላይ ባጭሩ እንዳየነው ከማን እንደምትወልድ ስሙን ማን አንደሆነ በግልጽ እስቀምጧል፡፡
👉"በስድስተኛው ወር ገብርኤል መላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ ከዳዊት ወገን የሆነ ስሙ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ከታጨች ከድንግል ዘንድ የዚህች ድንግል ስሟ ማርያም ነው"ሉቃ፡1፥26 በማለት ወንጌለዊው ገልጧል።
👉"በነቢይ ከጌታ ዘንድ እነሆ ድንገል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች
ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለውን ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። ማቴ፡1፥22
ኢሳይያስ "ሕፃን ተወልዶልናል" ብሎ ለእኛ መዳን የተወለደው ነገረን ቀጥሎም ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል።" ይላል። ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን መድኃኒት ለሆነን እንደመጣ
ሊያሳይ፡፡ ከዚህ በመቀጠል እርሱን ለመግለጥ የተጠቀማቸው
ቃላት በጣም የሚደንቁ ናቸው፡፡
#ስሙ_ድንቅ_መካር_ኃያል_አምላክ_የዘላዓለምአባት_የሰላምአለቃ
በሚሉ #ሰባት ቃላት ገልጾታል ቁጥሩ በእብራዊያን ዘንድ ፍጹም ነው። ከላይ ኢሳይያስ የተጠቀማቸው ሰባት ቃላት ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን የሚያስረዱ ናቸው፡፡ ሕፃን ብሎት ነበር
ሕፃን የሚለው ስም ታህታዊ ማንም በሥጋ የወለደ ሰው ሲወለድ
የሚጠራበር ነው ፡፡ ሰው መሆኑን ለመግለጥ ሕጻን አለው አምላክነቱን ለማስረዳት ስሙም ብሎ ጀምሮ በሰባት ቃለት አስረድቶናል፡፡
➊✝#ስሙ
ስለ ስሙ ቅዱሳት መጻፍት ሲናገሩ ኢየሱስ ፣አማኑኤል፣ ክርስቶስ
፣መድኃኔዓለም የሚባሉት ስመ ስጋዌ ናቸው። ሰው በመሆኑ የተጠራባቸው ኢየሱስ፦ማለት መድሐኒት ማለት ነው፡፡ አማኑኤል፦ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። ከእኛ ጋር፦ ሲባል
ከስጋችን ሥጋ ከደማችን ደምን ነስቶ ሰው የሆነ አምላክ ማለት
ነው። ክርስቶስ፦ማለት መሲህ ፣ሹም፣ንጉሥ ፣አለቃ ማለት ነው፡፡
መድኃኔዓለም፦ማለት የአለም መድኃኒት የዓለም ቤዛ ደሙን አፍስሶ ሥጋውን ቆርሶ በደሙ ዓለምን የዋጀ ማለት ነው፡፡
👉"ልጅም ትወልዳለች እርሱም ሕዝቡን ከኃጢያታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለች" ማቴ፡1፥21
👉"ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ እርሱ በመጣ ጊዜ ሁሉን ይነግረናል አለችዉ ኢየሱስም የምትናገሪዉ እርሱ እኔ ነኝ አላት።"ዮሐ፡1፥42
👉"እኛ ራሳችን ሰምተነዋል አርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን።"ዮሐ፡4፥42
ከላይ የተመለከትናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስሙንና ግብሩን የሚገልጡ ናቸው፡፡ ትርጉሙ ከተግባር ጋር የተያያዘ
ነውና ይህንን ነው ኢሳይያሰ “ሕፃን ተወለደልን” በማለት የተነገረለት ኢሳይያስም ሕጻን ብሎ የጠራዉ ሰዉ ሲሆን አምላክነቱ አልተለወጠምና አምላክነቱን መግለጥ የሚችሉ
ቃላት ከስሙ ጀምሮ ተጠቅሟል
ስሙ አዳኝ ነው።
👉"አቤቱ በስምህ አድነኝ።"መዝ፡53፥1
👉ስሙ ቅዱስ ነው፤ እርሱ ለእኔ ታላቅ ስራ አድርጎል እና ስሙም ቅዱስ ነው።"ሉቃ 1፥50
👉ስሙ፦ አጋንንትን ይገዛል "አጋንንት በስምህ ተገዙልን።"ሉቃ 10፥17
👉ያመኑትን እነዚህን ምልክቶች ይከተሏቸዋል በስሜ አጋንትን ያወጣሉ እባቦችን ይይዛሉ የሚያሰክር መርዝ ቢጠጡ አይገድላቸውም።ማር 16፥17
👉ስሙ፦ ስግደት የሚገባው ነው ?"እግዚአብሔር/እግዚአብሔርነቱ/
ያለልክ ከፍ ከፍ አድርገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለዉን ስም ሰጠው ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከኩ ዘንድ።" ቆላ 2፥9-11
👉ስሙ፦ ምስጋና ይገባዋል
👉"በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ
ስምህ ይቀደስ.."ማቴ 6፥9
➋✝#ድንቅ
ድንቅ፦ማለት ቃል እነደሚገባው አድርጎ የማይገልጠዉ ቃላት ላጣንለት ነገር የምንጠቀመዉ ነዉ በህቱም ድንግልና ተጸንሶ በህቱም ድንግልና መወለዱን ሲደንቅ የሚኖር ነውና በኪሩቤል
ላይ የሚገለጥ ስጋን ለብሶ መወለዱን የማይወስነዉ መወሰኑ የማይዳሰሰው መዳሰሱ የማይታየው መታየቱ የማይጨበጠው እሳተመለኮት በጨርቅ መጠቅለሉ በጎል መጣሉ የሚደንቀን ነው እነኳን ለኢሳይያስ ለመላእክትም ድነቅ ነው። ሰማይ ዙፋኑ የሆነ አምላክ በትህትና መገለጡ ድሆች እንኳ ባልተወለዱበት የከብቶቸች በረት መወለዱ ድንቅ ነው፡፡
👉"በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ"(እግዚአብሔርን ስራህ
ድንቅ ነው በሉት) መዝ፡65፥3 ሕፃናትን በእናታቸው ማህጸን የሚጠብቃቸው ሕጻን ሆነ ይህ እንዴት አይደንቅ
👉"ስራህ ድንቅ ነው ነፍሴም እጅግ ታዉቀዋለች።"መዝ 138፥12
በላይ በሰማይ በኪቤል ጀርባ በምድር በእናቱ እቅፍ መታየቱ ድንቅ ነው?
"ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ ይህም ከጌታ
ዘንድ ሆነ ለዓይናችን ድንቅ ነው።"መዝ 117፥22 ማቴ 22፥42
➌✝#መካር
ሰው ለመሆን መወሰኑን በልብ የመከረውን በነብያት ያናገረውን
ያን የፈጸመ ምክረ ከይሲን በምክሩ የሻረ ዲያብሎስን ያሣፈረ በልቡ ጥበብ ከሰው ልጆች በተለየች ምክሩ አዳምን ነጻ ያወጣ መካር ነው፡፡👉"ግሩም ምክሩ እምጎለመኸያው (ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ልዩ ነው)"መዝ 65፥5 በዚህ በልዩ ምክሩ ዲያብሎስ የመከራቸውን የነፍስና የስጋ ተዋህዶ በሥጋ ተወለደ ይህ የዲያብሎስን ስራ ያፈርስ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። 1ኛ ተሰ 3፥7👉"ውዕቱ ጥበቡ ወምክሩ ያድኅነነ መጸአ (እርሱ የአብ ጥበቡና ምክሩ ሊያድነን መጣ)" ይለዋል ቅዱስ ያሬድ፤

👍7
➍✝#ኃያል
ኃያልነት የበሕርይ ገንዘቡ ነው "ኀይሉ ለአብ ወጸጋ ለአህዛብ…”የአብ ኃሉ እርሱ ነው ለአህዛብም ጸጋን የሚሰጥ “ እነዳለ መጽሐፈ ኪዳን፡፡ መንግሥትህ ያንተ ናትና ኃይል ምስጋና ክብር ለዘላለሙ” ማቴ 6፥13 በኃይሉ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃዉን ሊነጥቀዉ እንዴት ይቻላል።ማቴ 12፥29👉“ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም /ደካማ/አይደለም ነገር ግን በእናንተ ኃለኛ ነው በድካም ተሰቅሏልና ነገር ግን በእግዚአበሔር /በእግዚአብሔር/ኃይል በሕይወት ይኖራል 1ኛ ቆሮ 13፥3-5
👉“የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው” 1ቆሮ 1፣24-26 ሰዎች ይህንን የእግዚአብሔር ኃይል አላወቁም ነበር።
👉“የእግዚአብሔርን ኃይል አታዉቁም እና ትስታለችሁ” ማቴ 22፥22
➎✝#አምላክ
➏✝#የዘላለም_አባት
➐✝#የሰላም_አለቃ
{ ትንቢተ ኢሳያስ (ምዕራፍ 9፥6:7) }
👉"ሕፃን ተወልዷልና ወንድ ልጅም ተሰቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ ስሙም ድንቅ መካር ሀያል አምላክ፡ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፡ ለአለቆች ሰላምን ለዕርሱም ህይወትን አመጣለሁና፡ ከዛሬ ጀሞሮ እስከ ዘልአለም ድረስ በፍርድና በፅድቅ ያፀናውና ይደግፈው ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፡ በዳዊት ዙፋን መንግስቱም ትፀናለች ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንነት ይህንን ያደርጋል።"
🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾
ውድ የተዋሕዶ ቤተሰቦች የሆናችሁ የእናቱ የእናታችን የቅድስተ ቅዱሳን የንጽሕይተ ንጹሐን የድንግል ማርያም የዓሥራት የአደራ ልጆች የሆናችሁ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
በዓሉ፦
🕊የሰላም
😁የደስታ
👩❤️👨የፍቅር
🧖♂የጤና
👨👩👧👦የመተሳሰብ
🐥የመተዛዘን
🌾የበረከት
🌽የእረድኤት
⛪️የስኬት
🌻የቅንነት ይሆንልን ዘንድ የፈጣሪ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አሜን!!!
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://www.tg-me.com/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

Telegram
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦
✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪
#ለተጨማሪ፦👇✞👇
https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

🙏11🥰2👍1👏1
Forwarded from የአብነት ትምህር ቤት
፠ ✞✞✞ የልደት ሥርዓተ ማኅሌት ✞✞✞ ፠
እንኳን ለብርሃነ ለደቱ በሰላም አደረሳችሁ!!!
፩. ነግሥ / ለአፃብዒክሙ /
ሰላም ለአፃብዒክሙ እለ እምአጽፋር ኢይትሌለዩ፤
ለቤትክሙ ሥላሴ ዘኢየሐልቅ ንዋዩ፤
አመ አብዓልክሙ ሰብአ ድኅረ አንደዮ ጌጋዩ፤
ዘኢርእዩ እምቅድመ ዮም መላእክተ ሰማይ ርእዩ፤
ወአግብርተ ሰብእ መላእክት ተሰምዩ ።
ዚቅ፦
ርእይዎ ኖሎት አእኰትዎ መላእከት ፨ ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ፨ ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ።
ወረብ፦
ርእይዎ ኖሎት ርእይዎ ኖሎት አእኰትዎ መላእከት፤
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል።
፪ . ነግሥ / ለልደትከ /
ሰላም ለልደትከ ኦ አማኑኤል፤
ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ ብሉየ መዋዕል፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአብ ቃል፤
እፎ እፎ አግመረተከ ድንግል፤
ወእፎ እንዘ አምላክ ሰከብከ በጎል።
ዚቅ፦
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ ፨ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ ፨ እፎ ተሴሰየ ሐሊበ ከመ ሕፃናት ።
ወረብ፦
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ ኀደረ ማኅፀነ ድንግል፤
እፎ ተሴሰየ ተሴሰየ ሀሊበ ከመ ሕፃናት ተሴሰየ።
፫. ለዝክረ ስምከ / መልክአ ኢየሱስ /
ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሐላ ዘኢይሔሱ፤
ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሡ፤
አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ፤
አህጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ።
ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፨ ንሰብክ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ፨
ወተወልደ በሥጋ ሰብእ፨ እንዘ ኢየዓርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፨
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ ሥጋ ኮነ ወተወልደ፨ ትጉሃን የአምኑ ልደቶ ፨ ወሱራፌል ይቀውሙ ዓውዶ፨ መጽአ ይቤዝወነ ውስተ ዓለም ፨ የሀበነ ሰላመ ፨ ጋዳ ያበውኡ ቍርባነ።
ወረብ፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ንሰብክ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት፤
ወተወልደ በሥጋ ሰብእ።
፬. ለአጽፋረ እዴከ / መልክአ ኢየሱስ /
ሰላም ለአጽፋረ እዴከ ዘኅበሪሆን ጸዓዳ፤
በምግባር ወግእዝ እለ ይትዋሐዳ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ምስፍና አባሉ ለይሁዳ፤
ለመንግሥትከ ሰፋኒት እንዘ ይትመሐለሉ ዐውዳ፤
ሰብአ ሰገል አወፈዩ ጋዳ።
ዚቅ፦
አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል አምኃሆሙ ፨ አምጽኡ መድምመ ፨ ረኪቦሙ ሕጻነ ዘተወልደ ለነ።
ወረብ፦
አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል፤
አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ።
፭. እምኲሉ ይኄይስ / መልክአ ኢየሱስ /
እምኵሉ ይኄይስ በሥላሴከ ተአምኖ፤
ወበወላዲትከ ተማኅፅኖ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ እምቤተ መንግሥት ወተክህኖ፤
ተሰብኦተከ እመቦ ዘያስተሐቅር መኒኖ፤
ያንኰርኵር ታሕተ ደይን ግዱፈ ከዊኖ።
ዚቅ፦
ወካዕበ ተማኅፀነ በማርያም እምከ፨ እንተ ይእቲ እግዝእትነ፨
ወትምክሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ።
ወረብ፦
ትምክሕተ ዘመድነ ትምክሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ፤
ይእቲ እግዝእትነ እግዝእትነ ማርያም ድንግል።
፮. ኦ ዝ መንክር / ማኅሌተ ጽጌ /
ኦ ዝ መንክር በዘዚአኪ አምሳል፤
ኮከበ ትንቢት ዘቦቱ መልክአ ሕጻን ሥዑል፤
ሠረቀ ያርኢ ተአምርኪ ድንግል፤
ወመርሖሙ ለሰብአ ሰገል እምርኁቅ ደወል፤
ጽጌኪ ኀበ ሀሎ ይሰክብ በጎል።
ዚቅ፦
ወኖሎት በቤተልሔም አንከሩ እምዘርእዩ ወሰምዑ ሰብአ ሰገል ፨ ርእዮሙ ኮከበ መጽኡ እምርኁቅ ብሔር ፨ ከመ ይስግዱ ለወልድኪ ወይግነዩ ለኪ።
°༺༒༻° አንገርጋሪ °༺༒༻°
ሃሌ ሉያ ዮም ፍሥሐ ኮነ፤
በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤
እምቅድስት ድንግል፤
ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤
ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ፤
አማን መንክር ስብሐተ ልደቱ።
°༺༒༻° አመላለስ °༺༒༻°
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤
እምቅድስት ድንግል ድንግል ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ።
°༺༒༻° እስመ ለዓለም °༺༒༻°
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም ዘይሁዳ ፨ አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ ፨ ሰብአ ሰገል አምጽኡ ሎቱ ጋዳ ፨ ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ።
°༺༒༻° አመላለስ °༺༒༻°
ተወልደ ኢየሱስ በቤተ ልሔም በቤተ ልሔም ዘይሁዳ
በቤተ ልሔም፤ አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ አሜሃ ይሰግዳ በቤተልሔም።
°༺༒༻° ዕዝል °༺༒༻°
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ፤
ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኀደረ፤
ዮም ተወልደ እግዚእ ወመድኅን ቤዛ ኵሉ ዓለም።
ምልጣን፦
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ፨ እግዚእ ወመድኅን
፨ ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ ፨ ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ።
አመላለስ፦
ቤዛ ኵሉ ዓለም ዮም ተወልደ፤
ቤዛ ኵሉ ዓለም ዮም ተወልደ።
°༺༒༻° አቡን በ፩ ሃሌ °༺༒༻°
ዮም በርህ ሠረቀ ለነ ፨ ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ
ማኅጸነ ድንግል ፆሮ ፨ እንዘ አምላክ ውእቱ ኀደረ ወተገምረ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ፨ ኮነ ሕጻነ ንዑሰ ዘአልቦ መምሰል ተወልደ ፨ ፀሐየ ጽድቅ ሠረቀ።
°༺༒༻° ዓራ °༺༒༻°
ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ፨ ምንተ ንብሎ ናስተማስሎ ለመድኃኒነ ፨ አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራድዮን ፨ ዖፍ ጸዓዳ ንጉሥ አንበሳ ፨ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ።
°༺༒༻° ሰላም °༺༒༻°
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፨ ንሰብክ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ ፨
ወተወልደ በሥጋ ሰብእ ፨ እንዘ ኢየዓርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ ፨ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ ሥጋ ኮነ ወተወልደ ፨ ትጉሃን የአምኑ ልደቶ ፨ ወሱራፌል ይቀውሙ ዓውዶ ፨ መጽአ ይቤዝወነ ውስተ ዓለም ፨ የሀበነ ሰላመ ፨ ጋዳ ያበውኡ ቍርባነ።
✞✞✞✞✞✞✞༒ ተፈጸመ ༒✞✞✞✞✞✞✞
© ፍሬ ማኅሌት

🙏13👍5❤3🥰2
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቀ
ፒሎፓዐዴር
🕊✞ #በዕደ_ዮሐንስ ✞🕊
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
ሠማያዊ/4/ሠማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
አዳም ያጠፋውን ልጅነት ሊያስመልስ
በሠላሳ ዘመን ተጠመቀ ኢየሱስ
እርሱ አምላክ ሢሆን ፈጥሮ የሚገዛ
ወረደ ወደምድር እንዲሆነን ቤዛ
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
ሊያጠፋው አቅልጦ እንደ አምላክነቱ
እረግጦ ሊሠርዝ እንደ ሠውነቱ
የፍጥረቱ ጌታ በዮርዳኖስ ቆሟል
የእዳውን ፅህፈት በስልጣኑ ሽሯል
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
የአንድነት ሶስትነት ተገልጧል ምስጢሩ
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቆ መምህሩ
አብም በደመና ለልጁ መስክሯል
በአምሳለ ርግብ መንፈስ ቅዱስ ወርዷል
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
ሲነገር እንዲኖር የእርሱ ትህትና
ለዓለም እንዲገለጥ የባሪያው ልዕልና
ተጠማቂው ሄደ ወደ አጥማቂው
አምላክ የሠራልን ስርዓቱ ይህ ነው
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
ሠማያዊ/4/ሠማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
አዳም ያጠፋውን ልጅነት ሊያስመልስ
በሠላሳ ዘመን ተጠመቀ ኢየሱስ
እርሱ አምላክ ሢሆን ፈጥሮ የሚገዛ
ወረደ ወደምድር እንዲሆነን ቤዛ
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
ሊያጠፋው አቅልጦ እንደ አምላክነቱ
እረግጦ ሊሠርዝ እንደ ሠውነቱ
የፍጥረቱ ጌታ በዮርዳኖስ ቆሟል
የእዳውን ፅህፈት በስልጣኑ ሽሯል
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
የአንድነት ሶስትነት ተገልጧል ምስጢሩ
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቆ መምህሩ
አብም በደመና ለልጁ መስክሯል
በአምሳለ ርግብ መንፈስ ቅዱስ ወርዷል
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
ሲነገር እንዲኖር የእርሱ ትህትና
ለዓለም እንዲገለጥ የባሪያው ልዕልና
ተጠማቂው ሄደ ወደ አጥማቂው
አምላክ የሠራልን ስርዓቱ ይህ ነው
#አዝ•••••••✞✞✞•••••••
👍5
እግዚኦ መርሀ.3gpp
1.1 MB
🕊✞ #እግዚኡ_መርሐ ✞🕊
እግዚኡ መርሐ ዮርዳኖስ አብጽሐ
ወበህየ ዮሐንስ ወበህየ ፍፁመ ተፈስሐ/፪/
ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው
በዚያችም ቀን ዮሐንስ በዚያችም ቀን ፈፅሞ ደስ አለው።
እግዚኡ መርሐ ዮርዳኖስ አብጽሐ
ወበህየ ዮሐንስ ወበህየ ፍፁመ ተፈስሐ/፪/
ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው
በዚያችም ቀን ዮሐንስ በዚያችም ቀን ፈፅሞ ደስ አለው።
👍5
ይትፌሳህ ሰማይ.3gpp
699.4 KB
🕊✞ #ይትፌሳሕ 🕊✞
ይትፌሳሕ ሰማይ በልደቱ
ወትትሐሰይ ምድር በጥምቀቱ ለመድኃኔዓለም ሶበ ሶበ ይወርድ ወልድ ውስተ ምጥማቃት
ትርጉም፦ ሰማይ በልደቱ ይደሰታል ምድርም በመድኃኔዓለም ጥምቀት ትደሰታለች ወልድ ወደ መጠመቂያው በወረደ ጊዜ፡፡

👍4
🌾✞ #ከተራ_የጥምቀት_ዋዜማ ✞🌾
✔ #ከተራ ማለት "ከበበ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን፡ ትርጕሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡
✔ #ከተራ_ለምን_ተባለ?
በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር 10 ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናምና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ #ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
✔ አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
✔ አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
✔ውኃ የሚከተርበት ቦታ " #ባሕረ_ጥምቀት (ጥምቀተ ባሕር)" (የታቦት ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር 11 ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡
✔ #ሥርዐተ_ከተራ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ እንዲል፡፡
✔ የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜ፤ ባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓለማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡ የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጐን፤ መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡ እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብስ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጽናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ደባትር ሃሌታ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡ የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ ሕዝቡም "ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ" እንዲሉ እንደየ ችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥ ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡ ነገር ግን ሴቶችና ልጆች እንደፈለጋቸው ከፊትም ከኋላም ሆነው ይሄዳሉ፡፡
✔ ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ የዓመቱ #ተረኛ_ደብር (የምራት ባለተረኛ) “ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥምቃት፤ በፍሥሓ ወበሰላም" (እግዚአብሔር ወልድ በሰላምና በደስታ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከሰማያት ወደ መጠመቂያው ወረደ) የሚለው ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተድርጐ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ግሱን ለመቃኘትና ለማሸብሸብ፣ ማኅሌት ለመቆም፣ ቅዳሴ ለመቀደስና ሌላውንም ሥርዐት ለመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኞች) ሲሆኑ ለቀጣዩ (ለከርሞ) ዓመት ተረኞች የሚሆኑና በአሁኑ ዓመት የምራት ባለተረኞችን የሚረዱት ገዳማትና አድባራት ደግሞ ‹‹አንሺዎች›› ይባላሉ፡፡
✔የከተራ ዕለት የየአጥቢያው ሕዝብ በየዓመቱ ተራ እየገባ ራት ከየአካባቢው ስለሚያመጣ ያ ሲበላና ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ወዲያው የሌሊቱ ጸሎት(ስብሐተ ማኅሌቱ) በተረኛው ደብር ካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራል (እንደ ቀጨኔ ባሉ ታላላቅና የሊቃውንት መፍለቂያ አድባራት ተረኛ ቢሆኑም /በጥምቀተ ባሕሩና በቤተ ክርስቲያናቸው ጭምር/ ባይሆኑም በቤተ ክርስቲያናቸው ማኅሌቱን ቆመውና ቅዳሴውን ቀድሰው ያድራሉ)፡፡ ቅዳሴው የሚቀደሰው ከሌሊቱ 7-9 ሰዓት ነው፡፡
✔ በከተራ ዕለት የሚከናወኑ ድርጊቶች ምሳሌነት አላቸው እነዚሁም፤
#ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ
#ታቦቱን_አክብሮ_ይዞ_የሚሄደው_ካህን የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ምሳሌ
#ባሕረ_ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ ምሳሌ
#ታቦታቱን_አጅበው_የሚሄዱት_ምዕመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩ ሰዎች ምሳሌ
#ታቦታቱ_በከተራ_ዕለት_ከመንበራቸው_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_መውረዳቸው መድኀኔዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተራውን ሲጠብቅ አድሮ መጠመቁን ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡››ማቴ፡ 3፥13
#ጥምቀቱ የሞቱ፤ አርአያ፤ የመቃብሩ አምሳል ነው፡፡
✔ በዓለ ጥምቀት ሰንበት (ቅዳሜና እሑድ ላይ) ካልዋለ የሚታረሰው መሬት ረድኤት በረከት ስለሚገኝበት ገበሬው አንድ ሁለት ፈር ያርሳል፡፡
✔ በዓለ ጥምቀት ዐቢይ በዓል ስለሆነ የጥሉላት (የፍስክ) ምግብም ጭምር ስለምንመገብበት ዘንድሮ ሰኞ ስለሚውል ዋይዜማውን እሑድን የጋድ ጾም (ከጥሉላት መባልዕት) እንጾማለን፡፡ የሚቈርብ ሰው ግን አክፍሎ ያድራል፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921

🥰9👍6❤2
🌾✞ #ጥምቀት ✞🌾
በአብ ስም በወልድ ስም በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ አሜን፡፡
✔ጥር ፲፩ በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሐንስ ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ፡፡
✔ይችም ዕለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች። ትርጓሜው መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው።
✔ልዩ የሆነች የሦስትነቱን ምሥጢር ገልጦባታልና አብ ከሰማይ ሁኖ የምወደው በርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት እያለ ሲመሰክር ወልድም በዮርዳኖስ ወንዝ ቁሞ ሳለ መንፈስ ቅዱስም በነጭ ርግብ አምሳል በወልድ ራስ ላይ ሲቀመጥ ታየ፡፡
✔ይህን አጥማቂው ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፡፡ "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከውኃ በወጣ ጊዜ ወዲያውኑ ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በጌታችን ራስ ላይ ተቀመጠ ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል መጣ ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ነው እርሱንም ስሙት፡፡" የሚል።
✔በዚች ዕለት ጌታችን ራሱን ገልጦአልና ከዚህ በፊት ሠላሳ ዓመት ያህል ራሱን አልገለጠም ነበር፡፡
✔በዚች ዕለት ለእስራኤል ልጆች ራሱን ገለጠ፡፡ እንሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ ብሎ መጥምቁ ዮሐንስ እንደገለጠው የከበረ ወንጌል ምስክር ሆነ፡፡
✔እኔ አላውቅም ነበር ነገር ግን እስራኤል ያውቁት ዘንድ በውኃ ላጠምቅ ስለዚህ መጣሁ አለ፡፡
✔በዚህም በዓል የእግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ የጌትነቱ ክብር ተገልጧል እርሱም የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት ለማስወገድ የሚሠዋ የእግዚአብሔር አማናዊ በግ ነው፡፡ ስለዚህም ይህ በዓል በክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ዘንድ የከበረና ከፍ ከፍ ያለ ሆነ፡፡
✔በርሱም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ በአከበረው ውኃ ይነጹበታል፡፡
✔የተቀበሉትንም ንጽሕና ጠብቀው ቢኖሩ በውስጡ የኃጢአታቸውን ሥርየት ያገኛሉ፡፡
✔ስለዚህ ከክፉ ነገር ሁሉ ተጠብቀን የፈጣሪያችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቸርነቱ ብዛት ልናመሰግን ይገባናል፡፡ እርሱ ስለ እኛ ሰው ሁኖ ከኃጢአታችን አድኖናልና።
☞ "እውነት እውነት እልሃለሁ ዳግመኛ ከውሃና ከመንፈስቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም።" ዮሐ 3÷5
☞ "እንሆም፥ድምፅ፡ከሰማያት፡መጥቶ፦ በርሱ፡ደስ፡የሚለኝ፡የምወደ፟ው፡ልጄ፡ይህ፡ነው፡አለ።"ማቴ፡3፥17
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላምና በጤና አደረሳቹ!!!🙏

❤7👍7🥰2
✞~ #ኢየሱስ_እናቱን_ተቆጥቷት_ይሆንን? ~✞
✅✞የቃና ሰርግ ቤት ታሪክ ለጊዜው እናቆየውና አንድ ልጅ በአደባባይ በሰዎች ፊት እናቱን በምንም ምክንያት ቢቆጣ እንኳን ከሃይማኖት አንጻር ከሥነ ምግባርም አንጻር የሚደገፍ ሥራ አይደለም፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችን ‹እናቱን በቁጣ ተናገራት› የሚለው አስተሳሰብም እንዲሁ ብዙ የሚያመጣው ጣጣ አለ፡፡ ‹‹እናትና አባትህን አክብር››፣ ‹‹እናቱን የሰደበ ይሙት›› የሚለውን ሕግ የሠራ አምላክ ‹እኔን ምሰሉ› እያለ ለሰው ልጆች አርኣያ ሊሆን በመጣበት በዚህ ዓለም ራሱ እናቱን በአደባባይ በሰው ፊት ያቃልላታል ብሎ ማሰብ እጅግ ከባድና ለብዙ ሰዎች የኃጢአትን በር ወለል አድርጎ ከፍቶ መረን የሚለቅ ነው፡፡ (ዘጸ. ፳፥፲፪ ፣፳፩፥ )
✅✞ እመቤታችንን የጎዱ መስሏቸው ‹ጌታ እናቱን ተቆጣ› ብለው የሚሰብኩ ሰዎችም ሳያውቁት እየተናገሩ ያሉት በእመቤታችን ላይ ሳይሆን በራሱ በጌታችን ላይ ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው?›› ብሎ የተናገረ ንጹሐ ባሕርይ ነው፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፮) ‹የሚጤስን የጧፍ ክር የማያጠፋ ፣የተቀጠቀጠ ሸንበቆን የማይሰብር› በአነጋገሩ ጭምት ነው፡፡ ስንክሳሩም ‹‹ወንድሜ ምእመን ሆይ ጌታችን ለንጽሕት እናቱ ለድንግል ማርያም ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ጊዜዬ ገና አልደረሰም በማለቱ የክብርት እናቱን ቃል እንዳቃለለ አታስብ›› ይላል፡፡ (ስንክ. ጥር ፲፪ ቁ. ፵)
✅✞ በማስከተልም ‹‹ጌታችን የሰማያዊውና የመለኮታዊ አባቱን ክብር እንደጠበቀ ይታወቅ ዘንድ እንዲሁ ከእርስዋ ፍጹም ሥጋንና ፍጽምት ነፍስን ነሥቶ ከመለኮቱ ጋር ያዋሐደውን የእናቱን ክብር ጠበቀ፡፡ በወንጌል ይታዘዛትና ይላላካት ነበር ተብሎ እንደተጻፈ›› ይላል፡፡ (ስንክ.ጥር ፲፪ ቁ. ፵፪)
✅✞ በእርግጥም ጌታችን የባሕርይ አባቱን አብን ክብር እንደጠበቀ በራሱ አንደበት ‹‹አባቴን አከብራለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፱) ለእመቤታችንና
ለአሳዳጊው ዮሴፍም እንዲሁ ‹‹ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ሉቃ. ፪፥፶፩) እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ስለ ወይኑ
የነገረችውም የልጅዋን መታዘዝ በልብዋ ትጠብቀው ስለነበር እና እንደሚታዘዛት
ታስብ ስለነበር ነው፡፡
✅✞ እስቲ ነገሩን ሌሎች ከሚያዩበት ማዕዘን ለመመልከት እንሞክር፡፡ እውነት ግን ጌታችን እናቱን ሊቆጣ የሚችልበት ምን ምክንያት ነበረው? ከላይ እንደተመለከትነው የለመነችው ስለ ራስዋ ጥቅም አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ልመናዋ ከሚያስፈልግ ነገር ውጪ ይደረግ የተባለ አላስፈላጊ የቅንጦት ልመና አይደለም፡፡ በሰርግ ቤት ሙሽሮችን ለዕድሜ ልክ ውርደት ሊዳርግ የሚችል የወይን ጠጅ እጥረት በተከሰተበት ሰዓት ‹ወይን እኮ የላቸውም› ብሎ ማመልከት እንኳን በሩኅሩኁ አምላክ ፊት ይቅርና በእኛ በጨካኞቹ የሰው ልጆች ፊት እንኳን
ሊያስቆጣ የሚችል ነገር አይደለም፡፡
✅✞ የለመነችው እንደ አይሁድ ምልክት ለማየት ጓጉታ አይደለም፡፡ እንደ ፈሪሳዊያንና ሰዱቃውያን ‹አይተን እንድናምንህ ምን ምልክት ትሠራለህ?› ‹ከሰማይ ምልክት ልናይ እንወዳለን› የሚል የፈተና ጥያቄ አልጠየቀችም፡፡ (ማቴ. ፲፮፥፩ ፤ዮሐ. ፮፥፳) ተአምር የማየት ምኞት አድሮበት እንደጠየቀው እንደ ሄሮድስም በአጋጣሚው ልጠቀምና ተአምር ልይ ብላም አይደለም፡፡ (ሉቃ. ፳፫፥፰) ደግሞስ ያለ ወንድ ዘር በማኅጸንዋ አድሮ በታተመ ድንግልና ሲወለድ ያየች እናት ሌላ ምን ተአምር
ሊያስደንቃት ይችላል?
✅✞ የሰርጋቸው ቀን የኀዘናቸው ቀን ሊሆን ስለተቃረበ ሙሽሮች ተጨንቃ መለመንዋ እንዴት የሚያስቆጣ ሊሆን ይችላል? ያለጊዜው ስለለመነችውና ስለቸኮለች ተቆጣት እንዳንል ልመናዋን ትንሽ ብታዘገየው ኖሮ ነገሩ ይፋ እየሆነ ፣ ሙሽሮቹ መዋረዳቸው ነው፡፡ ስለዚህ የደረሰችው በሰዓቱ ነው፡፡
✅✞ የጌታችን አሠራር እንዲህ አልነበረም፡፡ የቅዱስ ጴጥሮስ አማት በንዳድ በታመመች ጊዜ እንዲፈውሳት ሲለምኑት እሺ ብሎ ንዳዱን ገሥፆ አላቀቃት፡፡ (ሉቃ.፬፥፴፱) የአንድ መቶ አለቃ ልጅ በታመመ ጊዜ የአይሁድ ሽማግሌዎች ሊያማልዱ በመቶ አለቃው ተልከው መጡ፡፡ ጌታችን ከይሁዳ ነገድ መሆኑን በማሰብም ‹‹ይህን ልታደርግለት ይገባዋል፤ ሕዝባችንን ይወዳልና ምኵራብም ራሱ ሠርቶልናል ብለው አጽንተው ለመኑት። ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ።›› የመቶ አለቃውንም ልጅ በመጨረሻ ፈወሰው፡፡ (ሉቃ. ፯፥፪-፮) እነዚህ ሰዎች ተአምር እንዲያደርግ ሲጠይቁት እሺ ያለ ጌታ እናቱ ስትለምነው ይቆጣል ብለን እንዴት እንቀበል? የአይሁድን ሽማግሌዎች እንኳን ያልተቆጣውን ጌታ በምን
አንደበታችን እናቱን ተቆጣ ልንለው ይቻለናል?
✅✞ ከሁሉ በላይ ቅዱስ ዳዊት ‹‹ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን›› እንዳለው በረከሰ አንደበታችን ፣ በሚወላውል ልባችን፣ በሚባክን ሃሳባችን ወደ እርሱ የምንጸልየውን የእኛን የኃጢአተኞቹን ጸሎት ለምን ጸለያችሁ ብሎ ያልከለከለ አምላክ ንጽሕት እናቱ በፍጹም ትሕትና ለለመነችው ልመና የቁጣ ምላሽ ሠጠ ማለት እንዴት እንደፍራለን? ዳዊት ‹‹በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ›› ብሏል፡፡ እርሱ በልቡ በደል ስለሌለ ጌታ ከሰማው በሃሳብዋ ድንግል የሆነች እናቱን እንዴት አልሰማትም እንላለን? (መዝ.
፷፮፥፲፱-፳)
✅✞ እመቤታችን የጠየቀችው ይህን ያህል የማይጠየቅ ነገር ነው እንዴ?
የመንግሥትህን እኩሌታ ፣ የሥልጣንህን ፈንታ ሥጠኝ አላለችውም፡፡ የጠየቀችው ስለ ድሆቹ ሙሽሮች ነው፡፡ እኛ በረባ ባልረባው ስንዘበዝበው የምንውለውና የምናድረው ታጋሽ አምላክ ለእናቱ ለእኛ የሠጠውን ነገር ይነሣል ማለት ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ ‹አብን አሳየንና ይበቃናል› ፤ ‹እሳት ከሰማይ ወርዶ ሕዝቡን ያጥፋቸው› ፤ ‹በግራ ቀኝህ አስቀምጠን› የሚሉ ደቀ መዛሙርትን ታግሶ ለሦስት ዓመት ከሦስት ወራት ያስከተለ ጌታ ቅድስት እናቱ ተገቢ ልመና በተገቢ ሰዓት ስትለምነው ሊቆጣ አይችልም፡፡
✅✞ እንደ ወንጌሉ ብቻ ከሔድን ደግሞ እመቤታችን ከዚህ በፊትና በኋላ ምንም ነገር ስትለምነው አልተጻፈም፡፡ በወንጌል ለተጻፈው ለዚህ ብቸኛ ልመናዋም መልሱ
ቁጣ ነው ብለን አምነን መቀመጥ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ፈጽሞ የሚዋጥልን
ሃሳብ አይደለም፡፡ በልጅነትዋ ወልዳው ለተሰደደችው ፣ በነፍስዋ የኀዘን ሰይፍ
ላለፈባት እናቱ አንዴ ብትለምነው ተቆጣ ብለን እንዴት እንናገራለን?
✅✞ ጌታችን በዚህ ሰርግ ቤት እንኳንስ እንዲህ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የሚተረጉመው ‹ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ› የሚል የአክብሮት ንግግር ተናግሮ ቀርቶ ፤ ለእናቱ የተናገረው በቀጥታና በግልፅ የቁጣ ንግግር ቢሆን ኖሮ እንኳን ጾመን ጸልየን ፣ ወድቀን ተነሥተን ምሥጢራዊ ትርጉሙን እንፈልጋለን እንጂ ሰማይና ምድር ቢነዋወጥ ‹ጌታ እናቱን ተቆጣ› ብለን አናምንም!!!
🌾ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ~ቃና ዘገሊላ ገጽ 81

"ፓትርያርክ መሆን አይገባኝም ስላሉ ብቻ መንበራቸውን ጥለው እንዳይሄዱ በወታደር ይጠበቁ የነበረት ከወላይታ የተገኙት ወላይተኛ ተናጋሪው ቅዱስ ፓትርያሪክ"
➥የቀደመው ስማቸው አባ መልአኩ ይባላሉ። ምንም እንኳን ውልደታቸው በጎንደር ጋዢን በምትባል ስፍራ ቢሆንም ረጅም ዕድሜያቸውን ያሳለፉት እና አብረው የኖሩት ማህበራዊ ስነልቦናቸው ያገኙት ወላይታ በሚባል ደቡባዊ ምድር ላይ ነው።
➥ከሀገሬው በላይ ወላይተኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከውልደት ስፍራቸው በቀር አኗኗር እና አዋዋላቸው ሙሉ በሙሉ ከአንድ የወላይታ ገበሬ የተለየ አልነበረም።
➥የመጽሐፍት ትርጓሜ በእዚሁ በወላይታ ምድር ባሉ ጉባኤ ቤቶች አጠኑ። ስርዓተ ገዳም ከተማሩ በኃላ በእዚያው ወላይታ በሚገኘው ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም መኖከሱ። የብህትህና ህይወታቸው በወላይታ ምድር ጀመሩ።
➥ከ1926-1968 ለ42 ዓመታት ወላይታ ላይ በወላይተኛ ቋንቋ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽመው ከ300,000 በላይ ኢ- አማንያንን እንዳስጠመቁ እና ከ65 በላይ አብያተክርስቲያናትን አሳንጸዋል። በእዛ ዘመን አስበኅዋል ወዳጄ?
➥የደርግ መምጣትን ተከትሎ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን 2ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ የነበሩት ብጽኡ አቡነ ቴዎፍሎስን ተገደሉ። በመሆኑም ቅድስት ቤተክርስቲያን 3ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ ለመምረጥ 909 አከባቢያቸውን የሚወክሉ አባቶች በአዋጅ ሰበሰበች።
➥ከ565 ወረዳዎች ለማዕረገ ፕትርክና መንፈስ ቅዱስ የሚመርጠውን አባት ይገኝ ዘንድ ሁለት ሁለት ተወካይ ይላክ ዘንድ ታዘዘ። ገና ማዕረግ ጵጵስናን ያልተቀበሉት በቁምስና ያሉት መኖክሴው የወላይታው አባት የሆኑት አባ መላእኩ ከወላይታ "ተወካይ ሆኜ አልሄድም" ብሎ እንቢ ማለትን ከጅምሩ ቢያሳውቁም በገዳሙ አባቶች ትዕዛዝ እና ቃለ ውግዘት የወላይታ አውራጃን ወክለው ተላኩ። ገና ማዕረግ ጵጵስና ሳይቀበሉ በቁምስና ማዕረግ መሆናቸው ደግሞ ለዬት ያደርገዋል።
➥በስተመጨረሻም የመጨረሻው 5 ዕጩ ውስጥ ስማቸው ተካተተ። ከአንድ ቆሞስ እና ከሶስት ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ለ3ተኛው የፕትርክና የአገልግሎት ሥልጣን ለውድድር ተቀመጡ። ከየወረዳው ለመጡት ለመራጩ ተወካዮችም ግን እንቢታቸውን እና ከውድድሩ እንዲያስወጧቸው እንዲህ ብለው ተናገሩ
➥<< "እኔ ባህታዊ ነኝ ..ጥዬው የመጣሁት ህዝብ አለኝ ፣ ኑሮዬ በጫካ ነው እና የከተማውን ህይወት ለምጄ መምራት አይቻለኝም ።የበቁ አባቶች አሉ እና እኔን በእዚህ ምርጫ ውስጥ አወዳድራችሁ መንፈስ ቅዱስን አታሳዝኑ፣ እኔን ከምርጫው ሰርዙኝ " >> ብለው ለጉባኤው በተደጋጋሚ እየጮኹ ቢነግሩም ሰሚ አጡ።
➥በስተመጨረሻም ከሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተወዳድረው በአብላጫ ድምጽ መኖክሴው መናኝ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን 3ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ ሆነው ተመረጡ። በ1968 ሐምሌ ወር ላይ መዓረገ ጽጽስና ተቀብለው ከወር በኃላ በጉባኤው ምርጫ መሰረት
"አባ ተክለሃይማኖት ሣልሳዊ የኢትዮጽያ ፓትርያሪክ" ተብለው ተሾሙ።
➥ከተሾሙ በኃላም በብህትህና ወደ ወላይታ ተመልሰው በገዳማቸው በዓት ለመዝጋት መንበራቸው ጥለው ሊሸሹ በተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም የደርግ ወታደሮች እየያዟቸው መለሱ።
➥በስተመጨረሻም መንበራቸውን ጥለው እንዳይሄዱ በመኖርያ ቤታቸው ጥበቃ ተመደበ። መውጫ መግቢያቸው ከደርግ ወታደሮች እውቅና ውጪ እንዳይሆን ተደረገ።
➥ወዳጄ...መንፈስ ቅዱስ ሲመርጥ እንዲህ ነው። ዳዊትን ከእረኝነት ንጉስ ያደረገ አምላክ፣ ሳሙኤልን ከመካኒቷ ማህጸን አውጥቶ ነብይ ብሎ የሾመ ጌታ፣ ሙሴን ከውሐ ላይ ታድጎ ነጻ አውጭ አድርጎ የቀባ እግዚአብሔር ምርጫው ኮታ ሳይሆን ጸጋ ነው።
➥እኚኽ አባት ለጸጋ ፕትርክና የሚገቡ አባት መሆናቸውን ባገለገሉበት 12 የፕትርክና አገልግሎት ዓመታት ገለጡ።
➥ጫማን ለመንግስት ፕሮግራሞች ብቻ ይጫሙ እንደነበር ይነገራቸዋል።ከፆም ጸሎት በቀር ቅርባቸው የሚሆን ሰው አልነበረም።
ደምወዛቸውን ለነድያን እና ለወላይታ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት መኖኮሳት ቀለብ በቋሚነት ይልኩ ነበር።
➥ለቁመተ ሥጋ ብቻ ተመጋቢ የሆኑ ይህኝ አባት በስተመጨረሻ በሥጋ ድካም ሲያርፉ የከበረች ሥጋቸው 25 ኪግ ብቻ እንደነበር ይታወቃል።
ይህኝን አባት ዛሬም ድረስ የወላይታ ኦርቶዶክሳውያን ያለስስት በዓለ ረፍታቸውን አስበው በገዳማቸው ይዘክራሉ። የቅዱስነታቸው የከበረች በረከታቸው ትደርብን አሜን!!!

👍26🙏16❤4👏3🥰2