Telegram Web Link
🕊                      †                        🕊

    [   እ ን ኳ ን     አ ደ ረ ሳ ች ሁ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ በቅዱስ ፡ ሚካኤልም ፡ ጸሎትና ፡ ልመና ፡ ሀገር ፡ ከጥፋት ፡ ትድናለች።

ይልቁንም ፡ የቅዱስ ፡ ሚካኤል ፡ በዓሉ ፡ በሚከበርበት ፡ ዕለት ፡ ወይንና ፡ ስንዴ ፡ ጧፍ ፡ ዕጣን ፡ ለቤተ ፡ ክርስቲያኑ ፡ መባ ፡ የሰጠ : እስከ ፡ ግማሽ ፡ እንጀራም ፡ ቢሆን ፡ ለተራበ ፡ ያበላ ፡ እንዲሁም ፡ ቀዝቃዛ ፡ ውሀ : ለተጠማ ፡ ያጠጣ ፡ በክብር ፡ በምስጋና ፡ ዕድል ፡ ፈንታው ፡ ከቅዱሳንና ፡ ከሰማዕታት ፡ ጋር ፡ ይሆናል ፡ እስከ ፡ ዘላለሙ ፡ አሜን። ❞

[    ድርሳነ ሚካኤል     ]

🕊

❝ በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል ፤ ❞ [ ዳን.፲፪፥፩ ]


🕊                    💖                       🕊
4🔥1
7
🕊                      †                        🕊
        
 [ የመንፈሳዊ መርሐ-ግብር ጥሪ ! ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና በፍቅር በአንድነት አደረሰን አደረሳችሁ።

🕊

የኃያሉ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ምክንያት በማድረግ ከአምስት ዓመታት በላይ የተዘጋ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ማሰሪያ ማኅበር የቴሌግራም ገጽ ላይ ይህ መርሐ-ግብር ተዘጋጅቷል።

[  https://www.tg-me.com/DabiKidusMikael ]


መርሐ-ግብሩ ከሰኔ 10 እስከ 12 /10/2017 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ቀናት የተዘጋጀ ሲሆን ዛሬ ፍጻሜው ይሆናል።

ዛሬ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ

🕊                    💖                       🕊

በዛሬው መርሐ-ግብር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፦

🕊 [ የንታ ኃይለ ማርያም ዘውዱ ]
እና
🕊 [ የንታ መዝገበ ቃል ] ይገኛሉ።

በማኅበሩ አባላትም ፦

▷ ስንክሳር የዕለቱ
▷ መንፈሳዊ ጭውውት
▷ መንፈሳዊ ግጥም
▷ ምክረ አበው
▷ ቅኔ በሊቃወንተ ቤተክርስቲያን
መንፈሳዊ ድራማና መዝሙራት በዘማርያን ይቀርባል።

[   https://www.tg-me.com/DabiKidusMikael  ]


🕊                    💖                       🕊
👍4
                          †                           

🕊      †    ቅድስት አፎምያ    †       🕊

🕊

ከቅዱስ አስተራኒቆስ ጋር በተቀደሰ ትዳር የኖረች
- ምጽዋትን ያዘወተረች
- በፍቅረ ቅዱሳን የጸናች
- ንጽሕናዋን ጠብቃ ሰይጣንን ያሳፈረች ደግ እናት ናት::

ዛሬ የቅዱስ ሚካኤልን ስዕል ታቅፋ : በትእምርተ መስቀልም አማትባ አርፋለች : ቅዱሱ መልአክም ወደ ገነት አሳርጓታል::


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
5🔥1
                          †                           

🕊    †  ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ  †     🕊


የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ::

- በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ::
- በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ::
- በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ::
- ምጽዋትን ያዘወተረ::
- አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
¤ አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
6👏1
                          †                           

[     የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት    ]

       
🕊  በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ  🕊
             
" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ፥ ያድናቸውማል። " [መዝ.፴፬፥፯]

🕊

" ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ " [ዘፍ.፵፰፥፲፮]

† ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
2🥰2🙏2
Audio
3
9
🕊

[ † እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እና ለጻድቁ አባ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊 †  ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት  †  🕊

† ቅዱስ ገብርኤል :-

- በራማ ከሚኖሩ ሊቃናት አንዱ::
- አርባብ በሚባሉ አሥር ነገዶች ላይ አለቅነትን የተሾመ::
- የስሙ ትርጓሜ "እግዚእ ወገብር" [ጌታና አገልጋይ] አንድም "አምላክ ወሰብእ" [የአምላክ ሰው መሆን] ማለት የሆነ::
- በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላእክት ያረጋጋ::
- ብርሃናውያን መላእክትን የሚመራ::
- በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አብሣሪነቱ በስፋት የተነገረለት::
- በተለይ ደግሞ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው የመሆን ዜና ይሸከም ዘንድ ያደለው::
- ከድንግል ማርያም ጎን በፍጹም የማይርቅ::
- በፈጣን ተራዳኢነቱ ብዙ ቅዱሳንን ያገለገለ ታላቅ ቀናዒ መልአክ ነው::

በዚሕች ዕለት እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ባቢሎን ልኮታል:: ሊቀ መላእክት ነቢዩ ዳንኤልን ከአናብስቱ ጥርስ እንዳዳነው መጽሐፍ ነግሮናል::

ይልቁኑ ታላቁ ነቢይ ዳንኤል የተማረኩ ወገኖቹን መመለስ እያሰበ በሃዘን ሲጸልይ በዚሕ ቀን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ዳስሶታል:: ባርኮታል:: አጽናንቶታል:: ለዳንኤል በዋነኛነትም ሦስት ምሥጢራትን ገልጾለታል:-

፩. የቤተ እሥራኤልን ከሰባ ዘመን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ::

፪. የክርስቶስን ሰው መሆንና መሞት::

፫. የሐሳዌ መሲሕን በመጨረሻ ዘመን መምጣት ነግሮታል:: ስለዚህም እኛ ቅዱስ ገብርኤልን እንድናከብረው : በጸሎትም እንድንጠራው አባቶቻችን አዝዘውናል::

🕊 † አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም †  🕊 

† ጻድቁ ሃገራቸው መካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ሲሆን የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ባልንጀራ ናቸው:: ከሕፃንነታቸው ጀምሮ በክርስትና አድገው : ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረው ወደ ገዳም መንነዋል::

ከታላቁ ኮከበ ገዳም አባ ኢላርዮን ሥርዓተ መነኮሳትን አጥንተው አባ ኤስድሮስን በረድዕነት አገልግለዋል::

ከብዙ ዓመታት ትሕርምትና ገዳማዊ ሕይወት በኋላ የቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ጳጳስ ሆነው ተሹመዋል:: በጵጵስናቸው ዘመን አንድ ከባድ ስሕተት ሠርተው ነበር::

እርሱም ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ከምእመናን የተሠበሠበውን ገንዘብ ለግል ጉዳያቸው አውለው ልብሳቸውና ቤታቸው ወርቅ በወርቅ ሆኖ ነበር:: ፈጣሪ ግን ይሕንን ብክነት ከእርሳቸው ያርቅ ዘንድ ቅዱስ ኤጲፋንዮስን ላከው::

እርሱም በምክንያት ከቆጵሮስ ኢየሩሳሌም ገባ:: ጓደኛ ናቸውና አሳምኖ የወርቅ ንብረቶቹን ሁሉ ወሰደ:: ለነዳያንም ሰጣቸው:: አባ ዮሐንስ ሊቁን "እቃየን ካልመለስክ" ብለው ቢይዙት ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ጸልዮ ዐይናቸው እንዲታወር አደረገ:: አንዳንዴ የታወረ ልብ የሚገለጠው እንዲሕ ነውና::

በደቂቃዎች ልዩነት ዐይነ ስውር የሆኑት አባ ዮሐንስ አለቀሱ:: ሊቁንም "ራራልኝ : አማልደኝ?" አሉት:: እርሱም ጸልዮ አንድ ዐይናቸውን ብቻ አበራላቸው:: "ለምን?" አሉት:: "ተግሳጽ ነው" አላቸው::

ከዚያች ቀን በኋላ አባ ዮሐንስ ወደ ልቡናቸው ተመለሱ:: ቤታቸውን ገዳም አደረጉት:: በሚደነቅ ቅድስና : ፍቅርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ምዕመናንን አገልግለው በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፈዋል::

† የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት : የአባ ዮሐንስ በረከት አይለየን::

🕊

[ †  ሰኔ ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት [ወደ ዳንኤል የወረደበት]
፪. አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
፫. አባታችን ቃይናን [ከአዳም አራተኛ ትውልድ]
፬. አባ ማትያን ጻድቅ

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
፫. ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
፬. ቅዱስ አስከናፍር
፭. አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች
፮. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፯. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

" . . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም: ተናገረኝም:: እንዲህም አለ :- "ዳንኤል ሆይ! ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ::" † [ዳን. ፱፥፳-፳፪]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
4
7
#ነገ ለአንተ የተሸለ ነው"

ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ #ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ #ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ #መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ #ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል ፡፡
ቅዱሳን #ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ #ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም #ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት #ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና።
ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ ለራስህ ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ #ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!!
(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)

         #_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
11🙏8👍1
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  †

[ †  እንኩዋን ለአራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊 † አራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት † 🕊

፬ [4] ቱ ቅዱሳን አበው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ሲሆኑ ስማቸው አባ አክራ አባ ዮሐንስ : አባ አብጥልማ እና አባ ፊልዾስ ይባላሉ:: ከመከራ ዘመን በፊት [ማለትም በቀደመ ሕይወታቸው]  ካህናትና ሃብታሞች ነበሩ:: ሀብቱ ግን በሥራ ብቻ የተገኘ ነው::

ታዲያ ቅዱሳኑ በያሉበት ሆነው በሀብታቸው እንግዳ እየተቀበሉ : ድሆችን እያበሉ: በክህነታቸው ደግሞ እያስተማሩና እየናዘዙ ትጉሃን ስለ ነበሩ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ነበራቸው:: በእንዲህ ያለ ግብር ሳሉ ዘመነ ሰማዕታት አሐዱ አለ:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" እያሉ መኩዋንንቱና ነገሥታቱ ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሰቃዩ ገቡ::

በዚህ ጊዜ ፬ [ 4 ] ቱ ቅዱሳን አንድ ነገር መከሩ:: በየእሥር ቤቱ የተጣሉ ክርስቲያኖችን ለማገልገል ቆረጡ:: እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩ እሥረኞችን ያጽናኑ ገቡ:: የራበውን ያበላሉ: የተሰበረውን ይጠግናሉ: በቁስሉም ላይ መድኃኒትን ያደርጉ ነበር:: የመከራው ዘመን ግን እየረዘመ: ግፉም ከልክ እያለፈ መጣ::

በዚህ ጊዜ ፬ [ 4 ] ቱ ቅዱሳን ትልቁንና የመጨረሻውን ውሳኔ አስተላለፉ:: ከሰማዕታት ወገን ይቆጠሩ ዘንድ መርጠዋልና: ክርስቶስን በሞቱ ይመስሉት ዘንድ ሽተዋልና: የሩጫቸው መጨረሻ ሰማዕትነት እንዲሆን መረጡ::

አራቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሰብስበው ለነዳያን
አካፈሉ:: በትከሻቸው ካለች አጽፍ በቀር ስባሪ ገንዘብ ከሃብታቸው አላስቀሩም:: ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት አደባባይ [ዐውደ ስምዕ] አደረጉ::

በዙፋኑ የተቀመጠው የመኮንኑ ግርማ: መሬት ላይ የፈሰሰው የወገኖቻቸው ደም: የሠራዊቱ ድንፋታ ቅዱሳኑን አላስፈራቸውም:: በይፋ "ክርስቲያን ነን" ሲሉ ተናገሩ:: በዘመኑ እንዲሕ ብሎ መናገር አንገት የሚያስቆርጥ ትልቅ ድፍረት ነበር::

መኮንኑም ከበጐ ሃይማኖታቸው ይለያቸው ዘንድ በእሳት አቃጠላቸው:: እግዚአብሔር አዳናቸው:: በቀስትም: በስለትም: በብረትም ለቀናት አሰቃያቸው:: ቅዱሳኑ ግን አምላካቸውን አምነው ሁሉን በአኮቴት ተቀበሉ:: በመጨረሻ ግን በዚሕች ዕለት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ተገድለዋል:: ስለ ምጽዋታቸው: በጎ አገልግሎታቸውና ሰማዕትነታቸው ጻድቅ: ፈራጅ ከሆነ ፈጣሪ አክሊልን ተቀብለዋል::

የበረከት አምላክ ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን::

🕊

[ † ሰኔ ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን አበው ሰማዕታት [አባ አክራ: አባ ዮሐንስ: አባ አብጥልማ: አባ ፊልዾስ]

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አቡነ አረጋዊ [ ዘሚካኤል ]
፪. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፫. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ሙሴ [ የእግዚአብሔር ሰው ]
፭. አባ ስምዖን ገዳማዊ
፮. አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፯. እናታችን ቅድስት ነሣሒት

" እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን። " [ዕብ.፮፥፲-፲፫] (6:10-13)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
4
2025/07/11 18:52:37
Back to Top
HTML Embed Code: