Telegram Web Link
3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                         †                         

[ አ ን ድ ቀ ን ...... ! ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል። ❞

[ ፩ ዮሐ . ፪ ፥ ፲፯ ]



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
🕊

[ †  እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ [ ሕንጸታ ] በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊   †   በዓለ ሕንጸታ    †   🕊

†  በዚሕች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች::
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" [አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ] [ማቴ.፳፰፥፲፱] (28:19) ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::

የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና [ዮሐ.፮፥፶፮] (6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር::

በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ::

በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው::

ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: [ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::]

ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ::

በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ::

ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው::

እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል::

ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን::

† አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን::

🕊

[ † ሰኔ ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫. ቅዱሳን ሐዋርያት
፬. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ [ ዕረፍቱ ]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት [ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ [ ንጉሠ ኢትዮጵያ ]
፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

" በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: " † [፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
6
4
ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው ፤ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ፤ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
፤ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
ወ.ሮ ሰዎች ምዕ. 8፣36_39

          
#_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
6😢4🙏3👍1
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

     [   ትንሣኤውንም እናምናለን  !    ]

🕊                    💖                       🕊


❝ እኛ ግን የዳንበትን አዳኛችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን ሕማሙን በፈቃዱ ስለእኛ በሥጋ ያደረገውን ሞቱን እናስተምራለን ፤ ትንሣኤውንም እናምናለን ወደ ሰማይ ማረጉንም እናስተምራለን ፤ በሙታን በሕያዋን ይፈርድ ዘንድ የሚመጣበትን ዳግመኛ ምጽአቱን ፤ እርሱ የሚያወርሳት ለዘለዓለም የማታልፍ መንግሥተ ሰማያት እንዳለች እናምናለን። [ ማቴ.፲፥፳፰-፮ ። ግብ.ሐዋ.፩፥፲፩ ]

በኦሪት የተጻፈውን ቃል ምክንያት አድርገው ለእግዚአብሔር ቀድሞ ሥጋ እንደ ነበረው የሚናገሩ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰውን በእኛ አምሳል እንፍጠር አለ በእኛ አምሳል ያለውም ስለሰው ሥጋ ነው የሚሉ አሉ። [ዘፍ.፩፥፳፮ ]

ነገር ግን እንዲህ አይደለም እርሱ ስለ ውሳጣዊ ሰውነታችን [ ነፍስ ] ተናገረ እንጂ እርሱ ሁልጊዜ በመታደስ ጸንቶ ይኖራልና። አፍአዊ ሰውነታችን [ ሥጋ ] ይሞት ዘንድ እስኪነሣ ድረስም ይፈርስ ይበሰብስ ዘንድ እንዳለው ነገሩ የታወቀ ነው ፤ ውሳጣዊው ግን አይሞትም አይፈርስም አይበሰብስም። [ ፪ቆሮ.፬፥፲፮ ]

የበቃ ቢሆን ወደ መንግሥተ ሰማያት ይወስዱታል ፤ መውጣት ሳይኖር ሁል ጊዜ በዚያ ይኖራል።የበቃ ባይሆን ግን ወደገሀነም ይወስዱታል ፤ ፍጻሜ ሳይኖረው ለዘለዓለም በዚያ ይኖራል። [ ማቴ.፳፭፥፵፮ ]

ሰው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ በጎ ሥራን ቢሠራ እግዚአብሔርን እንደሚመስል እግዚአብሔር ገልጦልን ይኸን ቃል እንተረጕማለን ፤ ምድራዊ አዳምን መምሰል ገንዘብ እንደ አደረግን ሰማያዊ ክርስቶስን መምሰልን ገንዘብ እናደርጋለን ተብሎ እንደ ተጻፈ። [ ፩ቆሮ.፲፭፥፮-፵፱ ]

ውሳጣዊ ሰውነት ግን የማይለወጥ ዕውቀት ያለው ነፍስ ነው ፤ ዳግመኛም እግዚአብሔር በሥጋ ተሰውሮ ያለ ነፍስን በቸርነቱ እግዚአብሔርን የሚመስል አድርጎ ፈጠረው ፤ እግዚአብሔር ጥንቱን ሥጋ አይደለምና አይወሰንምና ጌታ እሳት ነው ፤ ብርሃንም ነው ፤ ማንም ማን አይቀርበውም ፤ ሕሊናም መርምሮ አያገኘውም አይመረመርም ከላይ ሆኖ ሰማይን ፡ ይሸፍናል ፤ ከታች ሆኖ ምድርን ይሸፍናል።

ፍጥረት ሁሉ ፤ ሰማያት በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ፤ ምድርም ፤ በምድር ላይ ያለ ሰው ሁሉ ከብቱም አውሬውም ሁሉ የሚንቀሳቀሱትም ወፎችም ፤ የምድረ በዳ ዛፎችም ሁሉ ባሕርም ፤ ፈሳሾችም በውስጣቸውም ያሉ ሁሉ በእርሱ ጸንተው ይኖራሉ መጽሐፍ እንደ ተናገረ ሁሉም በእርሱ ተፈጥሮአልና። [ መዝ.፻፵፰፥፩—፲፬ ። ዮሐ.፩፥፫ ቆላ.፩፥፲፭-፲፰ ] ❞

[    🕊   ቅዱስ ቄርሎስ   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                     🕊                      💖
🕊                    💖                       🕊


[ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ ! ]

❝ ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እም ኩሉ ሕዝብ ❞

[ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላምታ ይገባል። ] [አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]

" በመላእክት ፊት እዘምርልኻለሁ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ። "  [መዝ.፻፴፯፥፪ ]

🕊                    💖                       🕊

ቤተ ክርስቲያንን  “ ቅድስት ” አላት ስለምን ቢሉ ?

የቅድስት ሥላሴ አንድነት ሦስትነት ይነገርባታልና ፤ አንድም ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ አክብሯታልና። አንድም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ደሙ ለምእመናን ይሰጥባታልና፡፡ አንድም በኀጢአት የረከሰ ሰው በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆባት ይቀደስባታልና።

“ ማኅደረ ስብሐት ” [ የምስጋና ማደሪያ ] አላት ፦

የልዑል እግዚአብሔር ምስጋና በጸሎተ ኪዳን ፣ በስብሐተ ነግህ ፣ በጸሎተ ቅዳሴ ፣ በማሕሌት ፣ በሰዓታት ፣ በሰባቱ ጊዜያት ኹሉ ይነገርባታልና።

“ የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] ” አላት ፦

የመንግሥቱ ወንጌል በሚነገርበት ፣ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ በሚፈተትበት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን የጸለዩትን ጸሎት ለማሳረግ በቀን ስድስት መቶ በሌሊት ስድስት መቶ መላእክት ይጠብቋታልና።

“ እመ ኵሉ ሕዝብ ” የሕዝብ ኹሉ እናት ይላታል ፦

እናት ልጆቿን እንድታሳድግ ፣ እንድትጠብቅ ፣ ወደ ቀና ጐዳና መርታ እንድታደርስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በምስጢረ ቤተ ክርስቲያን ይልቁኑ በሥጋውና በደሙ እናድግባታለን ፤ በርቱዕ ትምህርቷ ከክሕደት እንጠበቅባታለን ፤ በመጨረሻም ወደ አምሳያዋ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት መርታ ታደርስናለችና። [ ገላ.፬፥፳፮-፳፯ ] ❞

🕊   †   በዓለ ሕንጸታ    †    🕊


💖                   🕊                   💖
2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷ " ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ! "


[    💖    አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ    💖     ] 

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

❝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ፥ አቤቱ ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች ፤ መቼ እደርሳለሁ ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ ?

ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ። ❞

[  መዝ . ፵፪ ፥ ፩ - ፫  ]


🕊                       💖                     🕊
4
2
ሰኔ____21

እንኳን
#ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ ሰኔ ጐልጐታና ሕንጸተ ቤተ ቤተክርስቲያን (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችኹ

#ድንግል_ሆይ_ዝም_አትበይ🙏😢😢
ጨለማችን ጨልሟል ውስጣችን ቃል በሌለው
#ኃዘን ውስጥ ወድቋል ። አሰገራሚው መድኃኒት በውስጥሸ የተገኘ ፡ ምድርን የሸፈነ ፀሐይ የተገለጠብሽ #የዳዊት ልጅ እናታችን ማርያም ሆይ ዝም አትበይ በእውነት ዝም አትበይ ። ትላንት ልመናሽ እንደጋረደን ዛሬም #ቃል_ኪዳንሽ ጥላ ይሁነን ።
#ድንግል_ሆይ....የመጣብንን እሳት ፡ከፊታችን
የቆመውን ደንቃራ በቃህ እንዲለው
#በልጅሽ ፈት ቁሚልን ።

#እናታችን__ሆይ ...አለማችን የዶኪማስን ቤት ሆኗል ፡ ሠርጉ ወደ ሙሾ ጠጁም ወደ መርዝነት ተቀይሯልና ....እንደ ልማድሽ ልጄ ሆይ በይልን ።
ከቀኝ ከግራ የሌለው የቃል ኪዳን ሕዝብሽን ሞት እንዳይበላው መድኃኒት ተብሎ ከተጠራው ልጅሽ ለምኚልን ። አንቺ
#በሥላሴ ፊት ሞገስ ያለሽ ሙሽራ ማርያም ሆይ ሠዓሊ ለነ እያልን በፊትሽ የመረረ #እንባችንን እናፈሳላን ። ሚረዳን የልጅሽ እጅ ሚፈውሰንም እርሱ ብቻ ነውና ዝም አትበይ ።
ኢየሩሳሌምን ስለ ዳዊት የጋረድካት ጌታ ሆይ ስለ እናትህ ብለህ የሚሮጠውን መልአከ ሞት ያዘው። ደምህ ይጋርደን
#ሐጢአታችንን_አታስብብን

የእናታችን እረድኤት በረከት ፍቅር አይለየን አሜን
🙏🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
18
†                       †                         †

[ እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል አደረሰን ፥ አደረሳችሁ ! ]


🕊 ሰኔ ጎለጎታ 🕊

💖

" ምሕረትን የምትለምኚ ድንግል እናቱ ፤
አንድያው ልጅሽ አያጥፋን በከንቱ ! "

"በእንቲአነ በሊዮ ሰአሊተ ምሕረት እሙ ፤
ኢታማስን ግብረ እዴከ እንተ ለሐኮ ቀዲሙ ! " [ አርኬ ]

[ ሰኔ ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫. ቅዱሳን ሐዋርያት
፬. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፭. ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ
፮. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፯. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፰. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር [ሰማዕት]
፱. አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
4
2025/07/09 19:11:48
Back to Top
HTML Embed Code: