Telegram Web Link
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †


              [   ክፍል  አርባ  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ከመናፍስት ጋር በሚደረግ ተጋድሎም ርዳታ ለማግኘት የማይጥር ሰው በእነርሱ ይገደላል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሐኪም ቤት የሚገቡ ሕመማቸውን [ ጉዳታቸውን ] ያሳዩ ፣ ወደ መታዘዝም የሚገቡ ትሕትናቸውን ያሳዩ፡፡

ሕሊናህ የመታዘዝህ መስታወት ይሁን ፣ ይህም የሚበቃ ነው፡፡ ለአባታቸው እየተገዙ በአጽንኦ በአት [ በጸጥታ ] ለሚኖሩ እነርሱን ተቃውመው የሚሠሩት አጋንንት ብቻ ናቸው፡፡ ዳሩ በማኅበር የሚኖሩ ግን ከአጋንንትና ከሰው ልጆች ጋር ይታገላሉ፡፡

የፊተኞቹ [ በአጽንኦ በኣት የሚኖሩት ] ሁሌም ከመምህሩ ዕይታ ሥር ናቸውና ትእዛዛቱን አጽንተው ይጠብቃሉ ፤ የኋለኞቹ [ በማኅበር የሚኖሩት ] ግን ከእሱ አለመኖር የተነሣ በመጠኑ ይጥሷቸዋል፡፡ ሆኖም ይህን ውድቀት አብልጠው ያካክሱ ዘንድ ግጭቶችንና መጸፋቶችን ታግሰው ቀናተኛና ትጉ የሚሆኑ እንዲሁ እጥፍ አክሊላትን ይቀዳጃሉ፡፡

በጥንቃቄ ሁሉ ራሳችንን እንጠብቅ፡፡ ወደቡ በመርከቦች ተሞልቶ ሳለ እርስ በርስ ለመጋጨት ቀላል ነውና ፣ በተለይ ሳይታወቅ በክፉ ጠባይ ትል የተበሳሱ ከሆነ፡፡

በበላዩ ፊት እጅግ ፍጹም የሆነ አርምሞንና አላዋቂነትን እንተግብር ፣ ዝምተኛ ሰው ሁሌም የበዛ እውቀትን የሚያገኝ የፍልስፍና [ የጥበብ ] ልጅ ነውና፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                      💖                     🕊
3
4
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷  " አንተነትህ በእግዚአብሔር ፊት ! "

[   " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! "   ]

[                        🕊                        ]
-----------------------------------------------

❝ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና ፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። አንተን ብቻ በደልሁ ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ ፥ ❞

[ መዝ . ፶፩ ፥ ፫ ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇
5
4🥰1
🕊

† እንኳን ለጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት አባ ድምያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  አባ ድምያኖስ   †   🕊

†  አባ ድምያኖስ ተወልደው ያደጉት ግብጽ ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቻቸው ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነት ዕድሜአቸው ቅዱሳት መጻሕፍትንና በጐ ምግባራትን ተምረዋል:: ዕድሜአቸው ወደ ወጣትነቱ ሲጠጋ ሥርዓተ መነኮሳትን ለማጥናት ወደ ገዳመ አባ ዮሐንስ ሔዱ:: በዘመኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ፈተና ሳያልፍ እንዲመነኩስ አይፈቀድለትም ነበር::

አንድ ሰው ሊመነኩስ ካሰበ በትክክል መናኝ መሆኑ ቢያንስ ለሦስት ቢበዛ ደግሞ ለአሥራ ሁለት ዓመታት እንዲፈተን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታዝዛለች:: ይኸውም "ሥርዓተ አመክሮ" ይባላል:: ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ መቆየት ከፈለገ ግን ይፈቀድለታል::

በዚህም መሠረት አባ ድምያኖስ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በአጭር ታጥቀው ገዳሙን አገልግለዋል:: ገዳሙም ይገባሃል በሚል ዲቁና እንዲሾሙ አድርጓል:: ከዚህ በኋላ ከአባቶች ተባርከው: ገዳሙንም ተሰናብተው ወጡ:: ነገር ግን የወጡት ወደ ዓለም ሳይሆን ራቅ ወዳለ ገዳም ነው::

የረድዕነት ዘመናቸውን ጨርሰዋልና አዲስ በሔዱበት ገዳም ወደ መደበኛው ገድል ተሸጋገሩ:: ያም ማለት በጾም: በጸሎት: በስግደት: በትሕርምት: በትሕትናና በፍቅር ሙሉ ጊዜአቸውን ማሳለፍ ጀመሩ:: በእንዲሕ ያለ ግብርም ዘመናት አለፉ::

የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ አባ ጴጥሮስ በእረኝነት ሥራ የሚያግዛቸው ሰው እንዲፈለግላቸው በጠየቁት መሠረት ትምሕርትም: ጽሕፈትም: በጐ ምግባራትም የተሟላለት ሰው እንደ አባ ድምያኖስ አልተገኘምና ያለፈቃዳቸው ወደ እስክንድርያ ተወስደው የፓትርያርኩ ረዳት ሆነው ተሾሙ:: በረዳትነት በቆዩበት ጊዜ በወንጌል አገልግሎትና በመንኖ ጥሪት ሕዝቡንና ሊቀ ጳጳሳቱን አስደስተዋል::

ልክ አባ ጴጥሮስ ሲያርፉ ሕዝቡና ሊቃውንቱ በአንድ ድምጽ አባ ድምያኖስን ለፓትርያርክነት መርጧቸዋል::

ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት በዘመነ ፕትርክናቸው ከግል የቅድስና ሕይወታቸው ባለፈ እነዚህን ፈተናዎች በመወጣታቸው ይመሰገናሉ::

፩. ሕዝቡ ከሃይማኖታቸው እንዳይወጡና በምግባር እንዳይዝሉ ተግተው አስተምረዋል::

፪. በአካል ያልደረሱባቸውን በጦማር [በመልዕክት] አስተምረዋል::

፫. በዘመናቸው የተነሱትን መናፍቃን ተከራክረው : የተመለሰውን ተቀብለው : እንቢ ያሉትን አውግዘዋል::

፬. ከአንጾኪያ ፓትርያርክ የመጣውን የኑፋቄ ጦማር [መልዕክት] በይፋ ተቃውመው አውግዘዋል::

ለአርባ ሦስት ዓመታት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው ያገለገሉት አባ ድምያኖስ ከብዙ ትጋት በኋላ በመልካም ሽምግልና በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ከግብጽ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዝርዝር ውስጥም አርባ አምስተኛ ሆነው ተመዝግበዋል::

† ልመናቸው : ክብራቸው : ጸጋ ረድኤታቸው አይለየን::

🕊

[ †  ሰኔ ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ ድምያኖስ ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት [ረባን]
፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
፬. ማር ያዕቆብ ግብጻዊ

" ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት : ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ:: " † [ሐዋ. ፳፥፳፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
5
4
#ወዳጆቼ___?

#ኃጢአ መሥራት በራሱ አስቀያሚ ነው፤ ኃጢአት ከሠሩ በኋላ በዚያ ኃጢአት መታበይ ግን እጅግ #ጽኑ_ደዌ ነው፡፡ #ጽድቅን ሠርተው በዚያ በሠሩት ጽድቅ #ከተኩራሩበት ጽድቁን ያጡታል፡፡ ይህ በኃጢአት ሲኾን ደግሞ የባሰ ነው፤ ወደ ከፋ ጥፋት ይወስደናልና፡፡ ከሠራነው #ኃጢአት ይልቅ በሠራነው ኃጢአት መታበይ የሚያመጣው ፍዳ ኵነኔ እጅግ #ጽኑ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#መልካም_ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
7🙏5
🕊

†  እንኩዋን ለሐዲስ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †

🕊  †  ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ  †  🕊

ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕዛብ [ተንባላት] በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር:: በተለይ ተንባላቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በሁዋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር:: ቅዱስ ጊዮርጊስ [ልብ በሉልኝ ሊቀ ሰማዕታት አይደለም] የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር::

እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ [አሕዛብ] ነበር:: ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል:: ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አሕዛባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም:: የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አሕዛባዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ ፯ [7] ዓመት ሞላው::

እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር:: ባይጠመቅም ጸበሉን: እመቱን ትቀባው ነበር:: ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር:: አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ:: ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ [የሰንበት በረከት] አበላችው:: "ጌታየ! ልጄን እርዳው" አለች::

ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ:: ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት:: "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው:: ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር::

አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ:: ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ:: ጥቂት ጊዜ ከቆየ በሁዋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት:: "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው:: ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ:: አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ:: ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ::

ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው መንፈስ ቅዱስ አናግሯቸው "ጊዮርጊስ" አሉት:: እሱም ደስ እያለው: ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ:: ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው:: ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ::

በዚያ ያሉ አሕዛብ በክርስትና ስም: ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ:: ዕለቱኑ አሠሩት:: ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት:- "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ:: ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር: ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት:: [ እንዲሕ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው!!! ]

ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት: አካሉን ቆራረጡት: ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት:: በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት:: እርሱ ግን ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ:: ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው::

በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት:: ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት:: ወደ ባሕርም ጣሉት:: እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር:: በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል::

ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ ጽናትን: ትእግስትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

🕊

† ሰኔ ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ ሰማዕት
፪. አባ ብሶይ አኖብ ሰማዕት [ በአንበሳ ጀርባ ላይ የተቀመጠ አባት ]
፫. ቅዱሳን ፭ቱ "5ቱ" ጭፍሮች [ በብዙ ስቃይ ሰማዕት የሆኑ ባልንጀሮች ]
፬. አባቶቻችን የደብረ ቁዋዐት ጻድቃን

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

" ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ! ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን ? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ  ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: " [፩ቆሮ.፲፥፲፬-፲፰] (10:14-18)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
4
2
#መልክአ_ገብርኤል

✟የአሸናፊና የኃይል መልአክ ገብርኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ከፍጹም ጥፋት እድን ዘንድ ክንፍህን ጋርድልኝ።

✟ወደ ድንግል የተላክ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የደስታ ምስራች ተናጋሪ ገብርኤል ሆይ፤ ሰላም ላንተ ይሁን። ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የደስታ አብሳሪ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የአካላዊ ቃልን የመጸነስ ብሥራት በማኀፀነ ማርያም ላሳደርክ ሰላም ላንተ ይሁን።

✟በመለአከ ሞት ከመውደቅ የምትታደግ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አማላጅነትህን በመታመን ተስፋ እናደርጋለንና በመዓልትም በሌሊትም አንተ ጠብቀን አሜን።

             #ሰናይ__ቀን 🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
10🙏2
        †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል ! ]


" አስማተኛም ፥ መተተኛም ፥ በድግምት የሚጠነቍልም ፥ መናፍስትንም የሚጠራ ፥ ጠንቋይም ፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው ፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።

አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።" [ ዘዳ.፲፰፥፲፩ ]

🔔

በቤተክርስቲያን የማዕረግ ስም እንደ እንጉዳይ የፈሉ ጠንቋዮች ፣ መተተኞችና አስማተኞች የቤተክርስቲያን መከራዎች ናቸው።

እነዚህ የእግዚአብሔር ተቃዋሚዎችና የዲያብሎስ አገልጋዮች በእጃቸው የብዙ ንጹሐን እንባና ደም አለ። በነዚህ ክፉ ሠራተኞች የተነሳ ብዙ ምስኪኖች በየጸበሉና በየሆስፒታሉ ይሰቃያሉ። ብዙዎች ሕይወታቸውን ፣ ጤናቸውንና ሰላማቸውን አጥተዋል። ብዙዎችም ሃይማኖታቸውን ክደው ጠፍተዋል። በነሱ ጠንቅ ቤተክርስቲያን ትሰደባለች። ክብረ ክህነት ይደፈራል። ምዕመናን ንጹሕና እውነተኛ የነፍስ እረኞች ካህናትን እንዲጠሉና እንዲርቁ ይሆናሉ። በነዚህ ግለሰቦች የተነሳ ብዙ የዋሃን ገንዘባቸውን ይጭበረበራሉ። ይታለላሉ። ወደ ልዩ ልዩ አጋንንታዊ አሠራሮች ተስበው ይገባሉ።

ስለዚህም በዘመናችን ቤተክርስቲያን በመናፍቃን እንድትሰደብ ፤ ክብረ ክህነትም እንዲደፈር በማድረግ አባቶቻችን ካህናትን ከምዕመናን ለመለየት ሰይጣን ያዘጋጃቸውን እንዲህ ያሉ የዲያብሎስ ሠራዊቶችን ከእኛ ዘንድ እናርቅ ! እንዲህ ያሉት የክፋት ሠራተኞች ለሐሰተኛ አጥማቂያን የገበያ ምንጭ በመሆን እየተመጋገቡ እንደሚሠሩም እናስተውል !

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
3
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †


           [   ክፍል  አርባ አንድ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ጥቂት እንኳ በውጭ በሚታይ ምልክትም ሆነ ወይም ቃል ወይም አንዳች ፍንጭ ሳታሳይ በውሳጣዊ ነፍስህ ቀናዒ ሁን፡፡ ይህንም ባልንጀራህን አሳንሰህ መመልከትን ስታቆም ብቻ ትፈጽመዋለህ፡፡ ነገር ግን ገና ይህን ለመፈጸም የምታነክስ ብትሆን ፣ እንደ ወንድሞችህ መሰልህ ፣ በመሆኑም እንዲሁ ትዕቢተኛ በመሆን ከእነሱ የተለየህ አትሆንም፡፡

አንድ ልምድ የሌለው ደቀ መዝሙር በሌላው አዝመራ ለራሱ ክብርን እንዲያገኝ አስቦ በአንዳንድ ሰዎች ፊት መምህሩ ከደረሰበት ማዕርግ የተነሣ ሲኩራራ ተመለከትሁ ፤ ሆኖም ግን ሰው ሁሉ ፦ መልካም ዛፍ እንዴት እንዲህ ያለውን ደረቅ ቅርንጫፍ ሊያበቅል ቻለ ? በማለት የጠየቀ ነውና ለራሱ ያተረፈው ብቸኛው ነገር ውርደትን ብቻ ነው፡፡

ታጋሽ ተብለን ልንጠራ የሚገባን በነገር ሁሉ ከሰው ሁሉ ዘንድ የሚደርስብንን ነቀፌታ ስንታገሥ እንጂ ከአባታችን ዘንድ የሚደርስብንን ነቀፌታ ጸንተን ስንታገሥ ብቻ አይደለም፡፡ ለአባታችንማ በሁለቱም - ከአክብሮት በመነጨና እርሱን መታገሥ ግዴታችን በመሆኑም ጭምር እንታገሳለንና፡፡

ይህን ከፈቲው [ ከምኞት ] እንደሚያነጻ የሕይወት ውኃ አድርገህ ዘለፋንና ስድብን ሊያጠጣህ ከሚፈልግ ማንኛውም ሰው ዘንድ ጓጉተህ ጠጣ፡፡ ቀጥሎም ጥልቅ የሆነ የንጽሕና ጎሕ ከነፍስህ ውስጥ የሚወጣና የእግዚአብሔር ብርሃን በልብህ ውስጥ የማይደበዝዝ ይሆናል፡፡

ምክንያቱም ሌቦች በዙሪያ ናቸውና ማንም ሰው አኃው በሱ ጥረት ደስ ሲሰኙ [ ዕረፍት አግኝተው ] ሲመለከት በልቡ ሊታበይ አይገባውም፡፡ ሁሌም ፦ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ፡፡ [ ሉቃ.፲፯፥፲ ] ብሎ የተናገረውን እርሱን አስብ፡፡ ስለ ድካማችን የሚያገኘንን ፍርድ በጊዜ ሞታችን የምናውቀው ይሆናል፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                      💖                     🕊
3
2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷ " የፍቅር ስሜት እና የስጋ ምኞት

[  💖  በቅዱሳን አበው ትምህርት 💖  ]

[                       🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ፍቅር ይታገሣል ፥ ቸርነትንም ያደርጋል ፤ ፍቅር አይቀናም ፤ ፍቅር አይመካም ፥ አይታበይም ፤ የማይገባውን አያደርግም ፥ የራሱንም አይፈልግም ፥ አይበሳጭም ፥ በደልን አይቆጥርም ፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም ፤ ሁሉን ይታገሣል ፥ ሁሉን ያምናል ፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል ፥ በሁሉ ይጸናል። ❞

[  ፩ቆሮ . ፲፫ ፥ ፬ - ፯  ]



🕊                       💖                   🕊
3👏2
2025/07/10 10:12:55
Back to Top
HTML Embed Code: