Telegram Web Link
#አባታችን__ተክለሃይማኖት

እልፍ አእላፍ ቢኖሩ ቃላት
ሥራው ብዙ ነው
#የተክለሃይማኖት
የምድር ስፋት ቢሆንም ሰሌዳ
ሁሌም አዲስ ነህ ሁሌም እንግዳ
ተክልዬ ተክልዬ ስንልህ
#ኢትዮጵያን
አስባት ዛሬም አትተዋት

#_ሰናይ_ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
12
🕯🕯🕯💖🕯🕯🕯

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ [ ጥቁሩ ሙሴ ]

ከሽፍትነት ህይወት ተጠርቶ በቅድስናና በንጽህና ህይወት ያሸበረቀ ገዳማዊ !

🕊

በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን ራሱን "አንተ ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ ፥ ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር::

ከቆይታ በኋላም በመነኮሳት ላይ እረኛ [አበ ምኔት] ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ:: የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ አጣፍጦ: ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ::

ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ፫፻፸፭ ዓ.ም [375 ዓ/ም] በርበረሮች [አሕዛብ] ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ፯ [7] ደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚሕች ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል::

ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው ያድለን::

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
1
4
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷   "  ብ ን ኖ ር ም ብ ን ሞ ት ም " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[                       🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና ፥ ለራሱም የሚሞት የለም ፤ በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና ፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።

ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና። ❞

[  ሮሜ . ፲፬ ፥ ፯  ]



🕊                       💖                   🕊
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🕊                      💖                      🕊


🕊  ተ ዋ ሕ ዶ   ሰ ማ ያ ዊ ት  🕊  ]


❝ የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ❞ [ ሮሜ.፲፬፥፲፯ ]


💖 O R T H O D O X Y  💖    ]


†                        †                         †
💖                     🕊                      💖
🙏4
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ †

[ †  እንኩዋን ከዘመነ ጸደይ ወደ ዘመነ ክረምት መሸጋገሪያ ለሆነችው ዕለትና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ   † ]

ስንዱ እመቤት ቤተ ክርስቲያን [ሃገራችን] ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት መጸው [ጽጌ] : ሐጋይ [በጋ]: ጸደይ [በልግ] ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::

በተለይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና "ሽሽታችሁ [ስደታችሁ] በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" ብሎናልና [ማቴ.፳፬፥፳] (24:20) ልንጸልይ ይገባናል:: በዘመነ ክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ የለበትምና ፍሬ ምግባር ሣናፈራ ሞት እንዳይመጣ: አንድም ክረምት የዝናብና የጭቃ ጊዜ በመሆኑ እንኩዋንስ ለስደት ለኑሮም አይመችምና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጸልይ:-

"በዝንቱ ክረምት በመዋዕሊነ:
እንበለ ፍሬ እንዘ በቆጽል ኀሎነ:
ናስተበቁዐከ እግዚኦ ኢይኩን ጉያነ::"
[ክረምት በተባለ በእኛ እድሜ:
ፍሬ ሳናፈራ በቅጠል /ያለ መልካም ሥራ/ ሳለን:
አቤቱ ጌታ ሆይ ስደትን አታምጣብን]

ቸሩ አምላካችን ከዘመነ መጸው በሰላም ያድርሰን:: ተረፈ ዘመኑንም የንስሃ: የፍሬና የበረከት ያድርግልን::

በዚሕች ዕለት እነዚህ ቅዱሳን ይከበራሉ:-

🕊 † ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ  †  🕊

በዘመነ ሐዋርያት ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ ማርያም ትባል ነበር:: እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ ቢሆንም ገና በልጅነቱ ድንግል ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች:: አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር:: ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል:: ቅዱስ ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል:: [ዮሐ.፲፬፥፳፪] (14:22)

ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ አሕጉራትን ዙሯል:: አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል:: አንዲት አጭር [ባለ አንድ ምዕራፍ] መልእክትም ጽፏል:: አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው:: ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ ደርቧል::

🕊 † ቅዱሳን ዺላጦስና አብሮቅላ †  🕊

ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን:: የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል:: የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል:: ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል:: በመጨረሻ ግን በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል::

ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ፴፮ [ 36 ] ቱ ቅዱሳት አንስት ነው:: ጌታችንን ተከትላ: ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ: ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ ዐርፏለች:: ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ::

ጌታችን ከሐዋርያው ይሁዳ: ከዺላጦስና አብሮቅላም ጸጋ በረከትን ያድለን::

🕊 

[ †  ሰኔ ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ [ከ፸፪ (72) ቱ አርድእት]
፪. ሰማዕቱ ዺላጦስ መስፍን
፫. ቅድስት አብሮቅላ [ሚስቱ]
፬. አባ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት
፭. የጸደይ መውጫ / የክረምትመግቢያ

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. አቡነ አቢብ /አባ ቡላ/
፮. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

" የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ : የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው : ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ: ምሕረትና ሰላም : ፍቅርም ይብዛላችሁ:: ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: " [ይሁዳ.፩፥፩] (1:1)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🙏2
1
"#ልጆቼ ! መንፈሳዊ ተጋድሎን አትፍሩ፥ ከእርሱም አትሽሹ፡፡ ተጋድሎ ከሌለ ምግባር ትሩፋትም የለምና፡፡ እምነትና ፍቅርም ካልተፈተኑ በእውን ከእናንተ ጋር ስለ መኖራቸው ርግጠኛ መኾን አይቻልምና፡፡ እነዚህ በርግጥ እናንተ ገንዘብ አድርጋችሁ እንደ ኾነ የሚታወቀው መከራ ሲገጥማችሁ ነውና፡፡ ስለዚህ ተጋድሎን አትፍሩ፥ ከእርሱም አትሽሹ፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#መልካም_ቀን🙏

የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
11🙏1
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

     [   በእርሱ ሞት ከብረናል  !    ]

🕊                    💖                       🕊


❝ መናፍቃን ምን ይላሉ ? የባሕርይ አምላክ እግዚአብሔር አንድ አይደለምን ፤ ሃይማኖትስ አንዲት አይደለችምን ?

እርሱ አንድ ወልድ አንድ ጌታ ነው ፤ ቃል በዕሩቅ ብእሲ አላደረም ፤ በክብሩም አላስተካከለውም ፤ ብዙ ሰዎች በድንቁርና አስበው እንደ ተናገሩ በኅድረት የልጅነትን ክብርና አምላክነትንም አልሰጠውም ፤ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእግዚአብሔር [ ከዘለዓለም ] የተገኘ የእግዚአብሔር ቃል እርሱ ነፍስን ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ሆነ እንጂ። [ ዮሐ.፩ ፥ ፩ - ፲፬ ]

በእርሱ ሞት ከብረናል ፤ በመለኮቱ ሞት ሳይኖርበት በሥጋ ሞተ ፤ ምንጊዜም ቢሆን እርሱ የሕይወት ልጅ ሕይወት ነው። ይኸውም ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ልደት ነው ፤ ወደ ሕይወት ሥጋ ደፍሮ በመጣ ጊዜ ሞት እንዲህ ድል ተነሣ ፤ መፍረስ መበስበስም በእርሱ [ በክርስቶስ ] እንዲህ ጠፋ ፤ ሞትም ድል ተነሣ። [ ዮሐ.፩፥፬ ]

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት እውነት እላችኋለሁ የወልደ ዕጓለ እመሕያውን ሥጋውን ካልበላችሁ ደሙን ፤ ካልጠጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት የላችሁም አለ ፤ የጌታችን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ ሕይወትን የሚያድል ነውና ፤ የዕሩቅ ብእሲ ሥጋ አይደለም ፤ አስቀድሜ እንደ ተናገርኩ ከሕይወት ከቃል ጋር በኅድረት አላስተካከለውም ፥ አንድ ባሕርይ በመሆን ቃል የተዋሐደው ሥጋ ነው፡ እንጂ። [ ዮሐ.፮፥፶፫-፶፯ ] ❞

[    🕊   ቅዱስ ቄርሎስ   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                     🕊                      💖
3
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †


           [   ክፍል  አርባ ሦስት  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ሳታቋርጥ ከአሳብህ ጋር ታገል ፣ ምንም ያህል የሚዋትት ቢሆን ይመለስ ዘንድ ወዳንተ ጥራው፡፡ ጌታ ገና ከመታዘዝ በታች ሆነው በሚኖሩት ዘንድ ፍጹም ከሁከት ነጻ የሆነ ጸሎትን የሚሻባቸው አይደለም፡፡ ሳታቋርጥም አሳብህ ወደ ነበረበት ይመለስ ዘንድ ጥራው አንጂ አሳቦችህ ሲሰረቁ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ አለመታወክ የመላእክት ብቻ ገንዘብ ነውና፡፡

እስከ ደኀሪተ እስትንፋሱ ድረስ ተጋድሎውን ላለመተው ፣ በሥጋውና በመንፈሱ አንድ ሺህ ሞቶችን ለመታገስ በስውር ቃል የገባ ሰው ፣ በቀላሉ በማናቸዉም በእነዚህ መሰናክሎች የሚወድቅ አይደለም፡፡

የልብ መወላወልና በአንድ ቦታ አለመጽናት [ በአጽንኦ በኣት አለመኖር ] ሁሌ ለመሰናክልና ለጥፋት ይዳርጋልና፡፡ እንዳለመታገሥ ያለ ፍሬ ቢስ ነገር የለምና በቀላሉ ከቦታ ወደ ቦታ [ ከአንዱ ገዳም ወደ ሌላው ገዳም ] የሚዘዋወሩ ፈጽሞ የወደቁ ናቸው፡፡

ወደማታውቀው ሐኪምና ሐኪም ቤት የመጣህ እንደ ሆነ ፣ እንደ አልፎ ሂያጅ ሆነህ በስውር በዚያ የሚኖሩትን ሁሉ ሕይወትና መንፈሳዊ ልምድ መርምር፡፡ ከሐኪሞቹና ከሞግዚቶቹ ረብ [ በቁዔት ] ፣ ከሕመሞችህም ማረፍ ፣ በተለይም ልዩ የሆነውን በሽታህን በተመለከተ ፣ ይኸውም መንፈሳዊ ትዕቢት ነው ፣ ዕረፍት እንዳገኘህ ከተሰማህ ፣ እንግዲያውስ ወደ እነሱ ዘንድ ሂድና ይህንኑ በትሕትና ወርቅ ግዛ ፣ ውሉንም በአገልግሎት ፊደላት አድርገህ መላእክትን እንደ ምስክር ቆጥረህ በመታዘዝ ብራና ላይ ጻፈው፡፡

የገዛ ፈቃድህንም ብራና በፊታቸው ቀዳድና አጥፋው፡፡ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር ክርስቶስ አንተን የገዛበትን ዋጋ አባከንህ፡፡ ገዳም ከመቃብር በፊት ያለ መቃብርህ ይሁን፡፡ ማንም ሰው እስከ ትንሣኤ ዘጉባኤ ድረስ ከመቃብር የሚወጣ አይደለምና፡፡ አንዳንዶች መቃብራቸውን ቢተዉ ግን ሙት እንደ ሆኑ አስተውል ! ይህ በእኛ ላይ እንዳይሆንብን ጌታን እንለምነው፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                      💖                     🕊
2025/07/09 03:11:11
Back to Top
HTML Embed Code: