"#ልጆቼ ! መንፈሳዊ ተጋድሎን አትፍሩ፥ ከእርሱም አትሽሹ፡፡ ተጋድሎ ከሌለ ምግባር ትሩፋትም የለምና፡፡ እምነትና ፍቅርም ካልተፈተኑ በእውን ከእናንተ ጋር ስለ መኖራቸው ርግጠኛ መኾን አይቻልምና፡፡ እነዚህ በርግጥ እናንተ ገንዘብ አድርጋችሁ እንደ ኾነ የሚታወቀው መከራ ሲገጥማችሁ ነውና፡፡ ስለዚህ ተጋድሎን አትፍሩ፥ ከእርሱም አትሽሹ፡፡"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#መልካም_ቀን🙏
የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#መልካም_ቀን🙏
የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
❤11🙏1
🕊 † 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ በእርሱ ሞት ከብረናል ! ]
🕊 💖 🕊
❝ መናፍቃን ምን ይላሉ ? የባሕርይ አምላክ እግዚአብሔር አንድ አይደለምን ፤ ሃይማኖትስ አንዲት አይደለችምን ?
እርሱ አንድ ወልድ አንድ ጌታ ነው ፤ ቃል በዕሩቅ ብእሲ አላደረም ፤ በክብሩም አላስተካከለውም ፤ ብዙ ሰዎች በድንቁርና አስበው እንደ ተናገሩ በኅድረት የልጅነትን ክብርና አምላክነትንም አልሰጠውም ፤ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእግዚአብሔር [ ከዘለዓለም ] የተገኘ የእግዚአብሔር ቃል እርሱ ነፍስን ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ሆነ እንጂ። [ ዮሐ.፩ ፥ ፩ - ፲፬ ]
በእርሱ ሞት ከብረናል ፤ በመለኮቱ ሞት ሳይኖርበት በሥጋ ሞተ ፤ ምንጊዜም ቢሆን እርሱ የሕይወት ልጅ ሕይወት ነው። ይኸውም ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ልደት ነው ፤ ወደ ሕይወት ሥጋ ደፍሮ በመጣ ጊዜ ሞት እንዲህ ድል ተነሣ ፤ መፍረስ መበስበስም በእርሱ [ በክርስቶስ ] እንዲህ ጠፋ ፤ ሞትም ድል ተነሣ። [ ዮሐ.፩፥፬ ]
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት እውነት እላችኋለሁ የወልደ ዕጓለ እመሕያውን ሥጋውን ካልበላችሁ ደሙን ፤ ካልጠጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት የላችሁም አለ ፤ የጌታችን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ ሕይወትን የሚያድል ነውና ፤ የዕሩቅ ብእሲ ሥጋ አይደለም ፤ አስቀድሜ እንደ ተናገርኩ ከሕይወት ከቃል ጋር በኅድረት አላስተካከለውም ፥ አንድ ባሕርይ በመሆን ቃል የተዋሐደው ሥጋ ነው፡ እንጂ። [ ዮሐ.፮፥፶፫-፶፯ ] ❞
[ 🕊 ቅዱስ ቄርሎስ 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖

❤3
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
[ ክፍል አርባ ሦስት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ ሳታቋርጥ ከአሳብህ ጋር ታገል ፣ ምንም ያህል የሚዋትት ቢሆን ይመለስ ዘንድ ወዳንተ ጥራው፡፡ ጌታ ገና ከመታዘዝ በታች ሆነው በሚኖሩት ዘንድ ፍጹም ከሁከት ነጻ የሆነ ጸሎትን የሚሻባቸው አይደለም፡፡ ሳታቋርጥም አሳብህ ወደ ነበረበት ይመለስ ዘንድ ጥራው አንጂ አሳቦችህ ሲሰረቁ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ አለመታወክ የመላእክት ብቻ ገንዘብ ነውና፡፡
እስከ ደኀሪተ እስትንፋሱ ድረስ ተጋድሎውን ላለመተው ፣ በሥጋውና በመንፈሱ አንድ ሺህ ሞቶችን ለመታገስ በስውር ቃል የገባ ሰው ፣ በቀላሉ በማናቸዉም በእነዚህ መሰናክሎች የሚወድቅ አይደለም፡፡
የልብ መወላወልና በአንድ ቦታ አለመጽናት [ በአጽንኦ በኣት አለመኖር ] ሁሌ ለመሰናክልና ለጥፋት ይዳርጋልና፡፡ እንዳለመታገሥ ያለ ፍሬ ቢስ ነገር የለምና በቀላሉ ከቦታ ወደ ቦታ [ ከአንዱ ገዳም ወደ ሌላው ገዳም ] የሚዘዋወሩ ፈጽሞ የወደቁ ናቸው፡፡
ወደማታውቀው ሐኪምና ሐኪም ቤት የመጣህ እንደ ሆነ ፣ እንደ አልፎ ሂያጅ ሆነህ በስውር በዚያ የሚኖሩትን ሁሉ ሕይወትና መንፈሳዊ ልምድ መርምር፡፡ ከሐኪሞቹና ከሞግዚቶቹ ረብ [ በቁዔት ] ፣ ከሕመሞችህም ማረፍ ፣ በተለይም ልዩ የሆነውን በሽታህን በተመለከተ ፣ ይኸውም መንፈሳዊ ትዕቢት ነው ፣ ዕረፍት እንዳገኘህ ከተሰማህ ፣ እንግዲያውስ ወደ እነሱ ዘንድ ሂድና ይህንኑ በትሕትና ወርቅ ግዛ ፣ ውሉንም በአገልግሎት ፊደላት አድርገህ መላእክትን እንደ ምስክር ቆጥረህ በመታዘዝ ብራና ላይ ጻፈው፡፡
የገዛ ፈቃድህንም ብራና በፊታቸው ቀዳድና አጥፋው፡፡ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር ክርስቶስ አንተን የገዛበትን ዋጋ አባከንህ፡፡ ገዳም ከመቃብር በፊት ያለ መቃብርህ ይሁን፡፡ ማንም ሰው እስከ ትንሣኤ ዘጉባኤ ድረስ ከመቃብር የሚወጣ አይደለምና፡፡ አንዳንዶች መቃብራቸውን ቢተዉ ግን ሙት እንደ ሆኑ አስተውል ! ይህ በእኛ ላይ እንዳይሆንብን ጌታን እንለምነው፡፡ ❞
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]

🕊
[ † እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን † 🕊
† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ "አውሴ" ይባላል:: ዘመኑ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ፪፻፲፭ [215] ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ ፹ [80] ዓመቱ : ኢያሱ ደግሞ ፵ [40] ዓመቱ ነበር::
ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ፵ [40] ቀን የታሠበላቸውን መንገድ ፵ [40] ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም::
አውሴን "ኢያሱ" ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት "መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:- ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ [ጥላ] እንዲሆን ነው::
ቅዱስ ኢያሱ በበርሃ ለ፵ [40] ዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዝዞታል [አገልግሎታል]:: እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል::
በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን : ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው ፹ [80] እየሆነ ነበር::
† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን [አስተዳዳሪ] እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ
¤ ሕዝቡን አሻግሮ
¤ የኢያሪኮን ቅጥር ፯ [ 7 ] ጊዜ ዙሮ
¤ በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ
¤ የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::
የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዚያን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል : በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚያች ዕለትም ለ፲፪ [12] ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም [በኤሎም ሸለቆ] አቆመ::
ሰባት አሕጉራተ ምስካይ [የመማጸኛ ከተሞችን] ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ፵ [40] ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ አላቸው :-
"እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: [ኢያ.፳፬] (24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ ፫ [3] ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::
ይህችውም የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ ፫ [3] ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ፫ [3] ወገን [በነፍስ: በሥጋ: በልቡና] ድንግል ናት:: አንድም በ፫ [3] ወገን [ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት] ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው አባ ሕርያቆስ "ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" [የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ] ሲል ያመሰገናት::
ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ፹ [80] ዓመት: በተወለደ በ፻፳ [120] ዓመቱ [ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ፻፲ [110] ዓመቱ ይላል] በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ፴ [30] ቀናት አለቀሱለት::
† በወዳጁ በኢያሱ እጅ የአሕዛብን ቅጥር ያፈረሰ እግዚአብሔር የእኛንም የኃጢአታችንን ግንብ በወዳጆቹ ምልጃ ያፍርስልን:: ከቅዱሱ ነቢይም በረከትን ያሳትፈን::
🕊
[ † ሰኔ ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን
፪. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት [ቅዳሴ ቤቱ]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
† " አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" † [ኢያሱ.፳፬፥፲፬] (24:14)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

❤4🙏1
#እግዚአብሔርን_ተስፋ አድርግ ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ
#እግዚአብሔርም በፍጥረታቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር በዝምታ ይሠራል። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው #የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሰራ አድርገው ያስባሉ፡ እነርሱ #እግዚአብሔር አይሰራም በሚያስቡበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ በጥልቅ እየሰራ ነው፡ ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ #የእግዚአብሔርን ሥራና የስራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይነቻቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል፡" #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፡፡" መዝ 26 € 14::
አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#_ሰናይ_ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

❤8🙏8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
†
[ የቤተ ክርስቲያን መከራዎች ! ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
- ሐሰተኛ አጥማቂያን
- በጠበል ስም ገንዘብ መሰብሰብ
- ሐሰተኛና አጋንንታዊ ልምምዶች
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
[ የቤተ ክርስቲያን መከራዎች ! ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
- ሐሰተኛ አጥማቂያን
- በጠበል ስም ገንዘብ መሰብሰብ
- ሐሰተኛና አጋንንታዊ ልምምዶች
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬