Telegram Web Link
🕊

[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ሐናንያ እና ለሰማዕቱ ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

🕊 † ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ † 🕊

† ሐናንያ ቁጥሩ ከ፸፪ ቱ አርድእት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ተመዝግቦ ከተቀመጠልን ከጥቂቶቹ ዋነኛው ነው:: ከነገደ እሥራኤል ተወልዶ : በሕገ ኦሪት አድጐ : ከወጣትነት ዕድሜው ትንሽ እልፍ ሲል ጌታችን ወንጌልን ማስተማር ጀምሯልና ጠራው:: እርሱም በበጐ ፈቃድ ተከትሎታልና ከ፸፪ ቱ አርድእት ደመረው::

ለ፫ ዓመታት ከጌታ እግር ተምሮ : ከዕለተ ስቅለት በፊት ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ነበር:: ምክንያቱም ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈልን ሰብዐው አርድእት "ጌታ ሆይ! አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ማለታቸውን አስቀምጦልናል:: [ሉቃ.፲፥፲፯] ቅዱስ ሐናንያ በበዓለ ዕርገት ተባርኮ በ፶ ኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::

በሚያስተምር ጊዜ የሶርያዋን ደማስቆን ማዕከል አድርጐ ነበር:: በሁዋላም አበው ሐዋርያት የዚህች ከተማ የመጀመሪያው ዻዻስ አድርገው ሹመውታል:: ጌታ ባረገ በ፰ ኛው ዓመት ክርስቲያኖችን ያሰቃይ የነበረው ሳውል [የሁዋላው ቅዱስ ዻውሎስ] ወደ ደማስቆ የተጉዋዘው ክርስቲያኖችን በተለይም ቅዱስ ሐናንያን ለማሠር ነበር::

ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ይሆን ዘንድ መብረቅ ዐይኑን አጠፋው:: ወዲያውም ጌታችን ሳውልን ወደ ሐናንያ እንዲሔድ ነገረው:: ከ፫ ቀናት በሁዋላ ጌታችን ለሐናንያ ተገልጦ አነጋግሮታል::

ሳውል [ዻውሎስ] ወደ ሐናንያ የደረሰው በመሪ ነበር:: ፪ ቱ እንደተገናኙ ቅዱስ ሐናንያ ሳውልን አስተማረው : ፈወሰው : አጠመቀው : በጐ መንገድንም መራው:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ሐዋርያ የቅዱስ ዻውሎስ የንስሃ አባቱ ይሰኛል:: [ሐዋ.፱፥፩-፲፱]

ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ሐናንያ ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን አስተማረ:: መከራንም ተቀበለ:: በመጨረሻም በዚህ ቀን ክፉዎች ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል::

🕊 † ቅዱስ ቶማስ ዘሰንደላት † 🕊

† በ፫ ኛው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ሰማዕታት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ወደ ሰማዕትነት ሕይወት የገባው በ፲፩ ዓመቱ በመላእክት መሪነት ነው:: ገና ወደ ምስክርነት አደባባይ እንደ ቀረበ መኮንኑ "ክርስቶስን ካድና ልሹምህ" ቢለው ሕጻኑ ቅዱስ ቶማስ ተቆጥቶ : "አንተ ሰነፍ መኮንን" ብሎ ገስጾ : በጐችን ይመልስባት በነበረችው ጅራፍ ገርፎታል:: ይሔም በዘመኑ የመጨረሻው የድፍረት ደረጃ ነበር::

† በዚህም ምክንያት በሕጻን ገላው ላይ የተቀበለው መከራ ሊናገሩት ይከብዳል::

¤ ግርፋት
¤ እሳት
¤ አራዊት በእርሱ ላይ አልፈዋል::

አካሉ ተቆራርጧል:: አንድ ጊዜም "ለጣዖታችሁ እንድሰግድ አምጡት" ብሏቸው ልክ ከፊቱ ሲደርሱ ወደ ጌታ ቢጸልይ መሬት ተከፍታ ውጣቸዋለች:: እሱን ያሰቃየው የነበረውን መኮንንም ከደዌው አድኖ ከነ ሠራዊቱ አሳምኖታል:: ሕጻኑን ቅዱስ ቶማስን ግን ያላመኑ አረማውያን በዚህች ቀን አንገቱን ሰይፈውት በሰማዕትነት ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔዷል::

† አምላከ ቅዱሳን ከሐዋርያው በረከት : ከሰማዕቱም ምልጃ አይለየን::

🕊 † ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ  †  🕊

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው: በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው::

ሊቁ የተወለደው መጋቢት ፳፯ ቀን በ፬፻፴፫ ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር::

አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ገና በ፫ ዓመቱ እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ-እኔስ ፫ ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ::

ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም :-

፩. ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ
፪. ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ
፫. ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው::
ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል::

ቅዱስ ያዕቆብ ፯ ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ፭ ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ፲፪ ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው::

"እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በሁዋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን: ዕጸበ ገዳምን: ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ: ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ [በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት] ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል:: በዘመኑም:-

፩. የ፬፻፶፩ ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል
፪. ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል
፫. በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል
፬. ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል::

በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በሁዋላ በተወለደ በ፸፪ ዓመቱ በ፭፻፭ ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ ፳፯ ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ::  ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች::

አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን::

🕊

[ † ሰኔ ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ [ከ፸፪  ቱ አርድእት]
፪. ቅዱስ ቶማስ ሰማዕት [ዘሰንደላት]
፫. ቅዱስ አልዓዛር ነዳይ [በነዌ ደጅ የወደቀ : ቀጥሎ ደግሞ በአብርሃም እቅፍ ውስጥ የተገኘ ጻድቅ - ሉቃ.፲፮፥፲፱]
፬. ቅዱስ ማማስ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
፪. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፫. ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ]
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፭. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
፮. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
፯. ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

" በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ:: ጌታም በራዕይ :- "ሐናንያ ሆይ!" አለው:: እርሱም "ጌታ ሆይ! እነሆኝ" አለ:: ጌታም :- ተነስተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሒድ:: በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ:: እነሆ እርሱ ይጸልያልና:: ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቷል" አለው::" † [ሐዋ.፱፥፲-፲፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር
† ወለወላዲቱ ድንግል
† ወለመስቀሉ ክቡር

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †            †            †
▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬
💖               🕊                  💖
4
#መድሐኒአለም_አባቴ
ዛሬም የወደድከኝ ተመስገን!

#የነፍሴ ንጉስ የህይወቴ ቤዛ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! #አመሰግንሃለሁ ። እኔን መውደድህ ይገርመኛል እንደሞተ ውሻ የምቆጠረውን #ማፍቀርህ ይደንቀኛል ። ኣምላኬ ሆይ ! ምኔን አይተህ ነው #የወደድከኝ ? ራሴን በጽሞና ሳየው ራሴን እንኳ መውደድ አቃተኝ ። አንተ ግን ህይወት ንጹህ ሳለህ እንደ ወንጀለኛ ተከሰስክልኝ ። የኔ አፍቃሪ ንጉስ #የማይገባኝን ልትሰጠኝ የማይገባህን መከራ ተቀበልክልኝ ።የምለው ባጣ እንዲሁ #ተመስገን ! እልሃለው ።በማላውቀው ጉዳይ እፈርዳለሁ አንተ ግን ብምታውቀው ጉዳይ ትምራለህ ። እባክህን እውቀትና ዕድሜ ያልለወጠኝን እባክህ አንተ #የልቤ ጌታ ለውጥልኝ ። እንደወደድከኝ መጠን ልወድህ #አልችልም ነገር እባክህን አቅም ስጠኝና እንደ አባቶቼ ቅዱሳን አብዝቼ #ልውደድህ! ዛሬም ተመስገን!

በማይቀየረው #ፍቅርህ በማይጠቁረው ፊትህ ለዘላለሙ አሜን !

#መልካም__ቀን🙏

የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
8🙏4
                       †                        

እንኳን ከዘመነ ፀደይ [ በጋ ] ወደ ዘመነ ክረምት የመሸጋገሪያ ዕለት በሰላም አደረሰን።

    🕊       ዘመነ ክረምት         🕊

" ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል ፤ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል ፤ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም።" [መዝ.፻፵፯፥፰]

🕊                        💖                     🕊


አራቱ አዝማናት [ ወቅቶች ] :-

፩. ዘመነ ክረምት [ ከሰኔ ፳፮ (26) እስከ መስከረም ፳፭ (25) ]
፪. ዘመነ መፀው [ ከመስከረም ፳፮ (26) እስከ ታኅሣሥ ፳፭ (25) ]
፫. ዘመነ ሐጋይ [ ከታኅሣሥ ፳፮ (26) እስከ መጋቢት ፳፭ (25) ]
፬. ዘመነ ፀደይ [ ከመጋቢት ፳፮ (26) እስከ ሰኔ ፳፭ (25) ] መሆናቸው ይታወቃል::

ዘመነ ፀደይን [ በጋን ] የባረከ አምላክ ዘመነ ክረምትን እንዲባርክልን : የንስሐ ጊዜም እንዲያደርግልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን::

" የክረምት ጥቅሙ ይበልጥ የሚታወቀው ወራቱ ካለፈ በኋላ ነውና፡፡ የዚያን ጊዜ የአበባው ማበብ ፣ የአዝመራው ማፍራት ፣ ሌሎች ዕፅዋትም በቅጠላቸውና በፍሬያቸው በወርሐ ክረምት ያገኙትን ጥቅም ግልጽ አድርገው ይናገራሉና ! "

[  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ]


🕊                        💖                     🕊
5
3
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †


           [   ክፍል  አርባ አራት  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

ይህችውም ሆድህ ናት .......

❝ ሕዋሳት ትእዛዛትን ከባድ ሆነው ሲያገኙዋቸው ፣ ይበልጥ ሰነፍ የሆኑት ራሳቸውን በጸሎት ማስጠመድ እንዲሻላቸው ይመርጣሉ፡፡ ሆኖም ቀላል የሆነውን ነገር በታዘዙ ጊዜ ግን ከእሳት እንደሚሸሽ ከጸሎት ይሸሻሉ፡፡ ወይም [ ይበልጥ ሰነፍ የሆኑ ትእዛዛትን ከባድ ቀላል የሆነውን ትእዛዝ ሆነው ሲያገኟቸው ፣ ጸሎት እንደሚሻላቸው ይመርጣሉ ፣ እንዲፈጽሙ ሲነገራቸው ግን ከእሳት እንደሚሸሽ ከጸሎት ይሸሻሉ ] ፡፡

አንዳንዶች አንድን የተለየ ተግባር ይፈጽማሉ ፤ ይሁን እንጂ ስለ አንድ ወንድም ይህንኑም ተዉት፡፡ አንዳንዶች በስንፍና ምክንያት ሕሊና ብለው በእርሱ ጥያቄ ይህንኑም ተግባሮቻቸውን ተዉ ፤ ሌሎች ግን ከውዳሴ ከንቱ የተነሣ ፣ ሌሎችም ከቀናኢነት የተነሣ ይህን አልተዉትም፡፡

ራስህን በግዴታዎች ካሰርክ ፣ ዓይነ ነፍስህም እንዳልጠራ ካሰብህ ፣ ትተወው ዘንድ ዕረፍትን አትጠይቅ፡፡ አማናዊ ነገሮች በየትም ስፍራ አማናዊ ናቸው ፣ የዚሁ ተቃራኒም እንዲሁ ነው። በዓለም ውስጥ ሐሜት ለብዙ መለያየቶች መንስኤ ሆኖዋል ፤ በማኅበር ግን በላተኝነት ውድቀቶችንና አለመታዘዝን ሁሉ ያመጣል፡፡

በእመቤትህ ላይ ከሰለጥንክባት [ ይህችውም ሆድህ ናት ] ፣ ማንኛውም የመኖሪያ ስፍራ ፈቃድን መተው [ መቲረ ፈቃድን ] ያጎናጽፍሃል ፣ እሷ ብትሰለጥንብህ ግን ከመቃብር ታወጣሃለች ፣ ከዚያም በየስፍራው ለአደጋ የተጋለጥህ ትሆናለህ፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                      💖                     🕊
1
2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷     "  እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር አ ለ !  " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[           🕊   ስብከት    🕊              ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬


❝ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ ፤ ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ፥ ያሳያል።

እርሱ ብቻ የማይሞት ነው ፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል ፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም ፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን ፤ አሜን። ❞

[  ፩ጢሞ . ፮ ፥ ፲፬ - ፲፮  ]



🕊                       💖                   🕊
6🙏1
3
🕊

[ †  እንኩዋን ለስደተኛው ሊቀ ዻዻሳት "አባ ቴዎዶስዮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † ]

🕊   †  አባ ቴዎዶስዮስ   †   🕊

ጻድቁ ሊቀ ዻዻሳት ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ከልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ በመንኖ ጥሪት የሚኖር ደግ ሰው ነበር:: ያ ዘመን መለካውያንና ልዮናውያን [ክርስቶስን ፪ [2] ባሕርይ የሚሉ] የሰለጠኑበት ዘመን ነበር:: በአንጻሩ ደግሞ ተዋሕዶን የሚያምኑ ሊቃውንትና ምዕመናን ቁጥራቸው የተመናመነ ነበር::

ችግሩ ግን ይህ ብቻ አልነበረም:: በጊዜው ተዋሕዶን አምኖ መገኘት እስከ ሞት የሚደርስ ዋጋንም ያስከፍል ነበር:: ለዚሕም ነው ሮማውያን ሃይማኖትን በግድ ለማስለወጥ ከነገሥታቱ ጋር የተቆራኙት:: ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ደሴት ውስጥ ከተገደለ በሁዋላ በግብፅ የተሾሙ ሊቃነ ዻዻሳት አብዛኞቹ መከራና ስደትን ቀምሰዋል:: ትልቁን ቦታ ግን አባ ቴዎዶስዮስ ይወስዳል::

አባ ቴዎዶስዮስ ለእስክንድርያ [ግብፅ] ፴፫ [33] ኛ ፓትርያርክ ነው:: እረኝነት [ዽዽስና] እንዳሁኑ ዘመን ሠርግና ምላሽ አይደለምና ገና እንደ ተሾመ የቀረበለት ጥያቄ አንድ ነበር:: "ተዋሕዶን ትተህ መለካዊ ትሆናለህ ወይስ የሚከተልብህን ፍርድ ትቀበላለህ?" አሉት:: ይህንን ያሉት ከንጉሡ ዮስጢያኖስ የመጡ መልእክተኞች ነበሩ:: መልሱ ፈጣን ሆነባቸው:: "እኔንም ሆነ ሕዝቤን ከቀናችው እምነታችን በምንም ልትለዩን አትችሉም" አላቸው::

በዚህ ምክንያት በቀጥታ ግዞት [ስደት] ተፈረደበት:: ወደ በርሃ ሲያግዙት ካህናት : መምሕራንንና ምዕመናንን አደራ ብሏቸው ነው የሔደው:: መናፍቃኑ እሱን ካሰደዱ በሁዋላ ሕዝቡን ለመቀየር ብዙ ደክመዋል:: ግን ሊሳካላቸው አልቻለም:: ምክንያቱም አደርነትን የማይረሱ ደጋግ መምሕራን ነበሩና ነው::

በዚያ ላይ አባ ቴዎዶስዮስ ጦማር [መልእክት] በየጊዜው ይጽፍላቸው ነበር:: እጅግ ብዙ ከሆኑት መልእክቶቹ የተወሰኑት ዛሬም ድረስ ሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ::

በዚሕ አስቸጋሪ ዘመን መልካም ነገሮችም ነበሩ:: ቀዳሚው ማሕቶተ ተዋሕዶ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ ሲሆን ፪ [2] ኛው ደግሞ የንጉሡ ሚስት የተባረከችው ታኦድራ ናት::

አባ ቴዎዶስዮስ በግዞትና በስደት ሳለ ንግሥቲቱ ትራዳው : ምዕመናንንም ትንከባከብ ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ከሊቀ ዻዻሱ ዘንድ ክህነትን ተቀብሎ ከሶርያ እስከ ምድረ ግብጽ ስለ ተዋሕዶ ሕልውና ተጋድሏል:: ምናልባትም ከሐዋርያው ቅዱስ ዻውሎስ በሁዋላ በፈሊጥ ክርስትናን በማስፋፋት ቀዳሚ አባት ነው:: [በነገራችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብ ማሰርን ያስተማረ አባትም ነው]

፪ [2] ቱ [አባ ቴዎዶስዮስና ቅዱስ ያዕቆብ] ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ ስለ ደከሙ የዘመኑ ምዕመናን በስማቸው "ያዕቆባውያን እና ቴዎዶስዮሳውያን" ተብለው ተጠርተዋል:: አባ ቴዎዶስዮስ ግን ሲታሠር ሲፈታ : ሲሰደድ ሲመለስ ብዙ ተሰቃየ::

ሕዝቡን ግን በመልካም እረኝነት ጠብቆ : ከተኩላ አፍ ታደገ:: በዚህች ቀንም ዐርፎ ተቀብሯል:: በፓትርያርክነት ያገለገለባቸው ዘመናት ፴፪ [32] ዓመታት ሲሆኑ ከእነዚህ ዓመታት ፳፰ [28] ቱ ያለቁት በስደትና በመከራ ነው::

እግዚአብሔር የአባቶቻችን ስደት አስቦ ከነፍስ ስደት ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

🕊

[ † ሰኔ ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ዻዻሳት
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ
፫. ቅዱስ ባስልዮስ
፬. ቅዱስ ባሊዲስ

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]

" ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና:: " [ማቴ.፭፥፲] (5:10)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
5🙏1
3
ድል አለ በስምህ ድል አለ በቃልህ ተራራው ይናዳል #አማኑኤል ስልህ ባህር ይከፈላል መድሀኒአለም ስልህ የመኖራችን ትርጉም የቀራኒዮ ንጉስ የድንግል ማርያም ልጅ ቸሩ #አማኑኤል ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ #ሲከፍችሁ ክንዱን ዘርግቶ አለሁ ይበላችሁ 🙏 በያለንበት ሁላችንንም ይጠብቀን

                  
#ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
8🙏2
2025/07/08 19:15:14
Back to Top
HTML Embed Code: