Telegram Web Link
ከ 100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የጨረቻ ቁርቁራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በካህናት እጦት ምክንያት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ በዛሬው ዕለት ተከብሯል ! 

ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ደሴ]

በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በደሴ ዙሪያ ወረዳ ከ 100 ዓመታትን በላይ ባስቆጠረው በጨረቻ ቁርቁራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በዛሬው ዕለት ተከብሯል ።

የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ሰኔ 12 ቀን የሚከበር ቢሆንም በአካባቢው ላይ አገልጋዮች ባለመኖራቸው ምክንያት በዛሬው ዕለት ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳው ሊቀ ካህናት መምህር ቤዛ ደሴ እንዲሁም ከደሴ ከተማ የተሰባሰቡ ሊቃውንት ፣ ካህናት በተገኙበት የተከበረ ሲሆን ሊቀ ካህናቱ ባስተላለፉት መልእክት ደብሩን ወደ ቀደመው ክብር ፣ አገልግሎት ለመመለስ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ዘጋቢ :- ዲ/ን አዶንያስ ሀብታሙ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
" አንድ አባት በታጣቂዎች ተገድለዋል። ቤታቸውንም አቃጥለውታል። ሁለቱ ይገደሉ ይኖሩ ገና አልታወቀም " - ዝቋላ አንድነት ገዳም

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን የሚገኘው ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም የ " ኦነግ ሸኔ ሠራዊት" ያላቸው ታጣቂዎች፤ " ገዳሙን እናጠፋለን " በሚል እቅድ በተደጋጋሚ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

አርብ ምሽት ተከፈተ ባለው ጥቃት፣ " አንድ አባት በታጣቂዎች ተገድለዋል። ቤታቸውንም አቃጥለውታል። ሁለት አባቶች ይገደሉ ይኖሩ ገና አልታወቀም። የሟቹ ቀብር ዛሬ ከቅዳሴ በኋላ ተፈጽሟል። ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ሠራዊት ናቸው። አስከሬን ስናመጣ በአካባቢው ነበሩ " ሲል ተናግሯል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት በገዳሙ ውስጥ በሚገኝ ዋሻ የሚኖሩ ሁለት መነኮሳት ይሙቱ ይኑሩ እንደማይታወቅ አስረድቶ፤ " በሕይወት ካሉም እሰየው ከሌሉም አስከሬናቸውን እናመጣለን "  ብሏል። 

በገዳሙ የተለያዩ ዋሻዎች አምስት አባቶች ከጥቃቱ ማምለጣቸውን የገለጸው ገዳሙ፣ " የታጣቂዎች እቅዳቸው ገዳሙን እናጠፋለን የሚል ነው " ብሎ፣ ሰሞኑንም ጥቃት ለመሰነዘር ያደረጉት ሙከራ ባለመሳካቱ የአሁኑን ጥቃት እንዳደረሱ አስረድቷል።

" ባለፈው ሳምንት የገዳሙን አካባቢ ህዝብ ሰብስበው ‘ወደ ገዳሙ ትመሩናላችሁ’ ብለው፤ አስገድደው ይዘዋቸው በዚህ በሂደት ላይ እያሉ መከላከያ ሠራዊት መጥቶ ከለላ አድርጎ ታጣቂዎቹ ወደ መጡበት ተመልሰው ነበር። በዚያ ቁጭት ነው ይህንን ድርጊት የፈጸሙት " ነው ያለው።

“ እናም እቅዳቸው በዚህ የሚገታ አይደለም ሁኔታው ስላልተመቻቸውና ስላልተሳካላቸው እንጂ ገዳሙን የማጥፋት እቅዳቸው ቋሚ ነው " ብሏል።

ሰሞኑን የተገደሉት አባት በደብረ ሊባኖስና በሌሎች የተለያዩ ገዳማት የኖሩ፣ ከዚያም በዝቋላ ገዳም ሲያገለግሉ ቆይተው ተፈቅዶላቸው ዋሻ የገቡ የበቁ አባት እንደነበሩ፤ በ2016 ዓ/ም አራት አባቶች በታጣቂዎች እንደተገደሉ አስታውሶ፣  "የአሁኑ ሟች ጋር በአጠቃላይ አምስት አባቶች ሰማዕትነት ተቀብለዋል” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
//በፓሪስ እጅግ ጥዑም ስብከት// በር...
ፓሪስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ደስታ ምንድንው?
  
           
Size:-66.5MB
Length:-1:11:51

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሰኔ 21  ሰኔ ጐልጐታ ወሕንፀተ ቤተክርስቲያን
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ሰኔ ጐልጐታና ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን (ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ለታነጸበት) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

‹‹ሰኔ ጐልጐታ ፤
ችግር የምትፈታታ፡፡››

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህች  ቀን (ሰኔ 21) ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ በሚባል ቦታ ላይ እንባዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ሰኔ ጐልጐታን ተመልከት

✤✤ ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን፤

ሰኔ 21 ከእመቤታችን #33ቱ በዓላት አንዱ ሲኾን፤ ሕንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል፡፡ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በአምላክ እናት ስም የታነጸችው በዚሁ እለት በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡
አናጺውም ደግሞ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ቦታው በፊልጵስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፤ ጥንተ ነገሩስ (ታሪኩ) እንደምን ነው ቢሉ፤
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን መደኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ‹‹ሑሩ ወመሐሩ ኵሎ አሕዛበ፤ አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ፡፡›› /ማቴ. 28፥19/ ባላቸው ቃል መሠረት ሐዋርያት በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::

የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6፥ 56) አበው ሐዋርያት ቊርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው  ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን፣ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲህ ይከናወን ነበር፡፡ ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኵራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቊጥር እጅጉን በመብዛቱ /በተለይ ቅዱስ ዻውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ::/ በዚህ ምክንያት መምህራን ሕዝቡን ‹‹ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?›› ቢሏቸው ‹‹እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት ቤት የለን››ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ዻውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች ቤት ‹‹ለምን አናንጽም?›› ብለው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ግን ‹‹ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም›› አለ:: (ለዚህ ነው ዛሬም ሊቀ ዻዻስ ካልፈቀደ ቤተክርስቲያን የማይታነጸው፡፡) ከዚያ ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ዼጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱ ቅዱስ #ዼጥሮስም ‹‹የጌታችን ፈቃዱመኾኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ›› ብሎ አዋጅ ነገረ::

በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔያቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መላአክትን አስከትሎ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ፤እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ኹሉንም ሐዋርያት በሩቅም በቅርብም ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ በሚባል ሃገር ሰበሰባቸው፡፡ ከዚያም በስተምሥራቅ ከከተማ ወጣ ወዳለ ሥፍራ ወሰዳቸው፡፡

በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ 3ቱንም ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡
እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም በእጃቸው እየለመለሙ (እየሳቡ) ቁመቱን 24፥ ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ዕጽብት፥ ግርምት የምትኾን 3 ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን በ52 ዓ/ም ሰኔ 20 ቀን አነጹ፡፡
ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ፤ ጌታችንም በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት፤ ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ፡፡›› ብሏቸው ዐረገ፡፡

✜ በማግስቱ ሰኔ 21 ዕለት ደግሞ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዞ ወረደ:: ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፤ አስቀድሞ ቤተክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዐተ ቤተክርስቲያንን አሳየ:: ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ ‹‹አርሳይሮስ›› ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ‹ ‹‹አክስዮስ››(አክዮስ)እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ ‹‹ይደልዎ›› በአማርኛው ደግሞ ‹‹ይገባዋል፤ ያስምርለት›› እንደ ማለት ነው::

ጌታችን ይህን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማኅደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ኾኖ፣ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቆመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::
በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው:: ‹‹ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን አንጹ፤ ይህችን  እለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::›› ብሏቸው ከድንግል እናቱና ከመላእክቱ ጋር ዐረገ::

✤✤ ሥርዐተ ማኅሌቱ እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠሙበበት ዘንድ የሁለቱንም (የላይ ቤት የግምጃ ቤትና የታች ቤት የበአታን) አብነት አስቀምጠንላችኋል፤ በቢጫ የተቀለመው የላይ ቤት (የግምጃ ቤት) አብነትን ለምትከተሉ አድባራት ሲኾን፤ ሰማያዊ የተቀለመው ደግሞ የታች ቤትን (የበዓታን) የአቋቋም ይትበሃል ለምትጠቀሙ ሲኾን፤ ሁለቱም የላይ ቤቱና ያየታች ቤቱ የሚተባበሩበት ላይ ደግሞ ዘግምጃ ቤት ወዘበዓታ ብለን በፈዛዛ ጥቁር አስቀምጠንላችኋል፡፡ መልካም ማኅሌት፨

ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ቀ.ደ.ሰ.መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት፡፡
✼ የድንግል እመቤታችን ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን::
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
Forwarded from Cross bot
How old are you ?
Forwarded from Qualitybuttonbot
Salphina gudda

Video sukkaneessaa Donald Trump hadhaa mana nama irratti hojjette Video isaa ilaalu yo barbaaddan bakka watch jedhuu tuqun ilaala

ትልቅ ነውር ነው።

ዶናልድ ትራምፕ በሰው ቤት ምሬት ሲያደርጉ የሚያሳይ ዘግናኝ ቪዲዮ ቪዲዮውን ማየት ከፈለጉ የምልከታ ቁልፍን ይጫኑ
2025/06/27 01:51:10
Back to Top
HTML Embed Code: