Telegram Web Link
ሌላም ሁለተኛ መጽሐፍ፡ ይሄ በፈረንሳይኛ ቢሆንም ስለ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቫንቶች እና የኢህአዴግ ዘመን አሠራር ነው። ቆንጅዬ ሥራ፡
የግርማ ተስፋው የንጋት መንገደኞች ገበያ ላይ ወጥቷል። ድሮ በሰልፍ ሜዳ ታውቁት ይሆናል ግርማዬን፣ አዲስ ነገርም ላይ እንዲሁ.. ይጽፈዋል አይገልጸውም። ከአብዮቱ ውጥንቅጥ እና የሰው ልጅ ሕይወት አንዱ ካንዱ መተሣሠር ጋር የተያያዙት ድርሰቶቹ የተረሳ የተረጋጋ የመጻፍ እና የማንበብ ዘመንን እንድንናፍቅ ያደርጋሉ። ደስ የሚለው ደግሞ ሰልፍ ሜዳም ላይ እዚህም ድርሰቱ ላይ አህዮች ያላቸው ቦታ ነው ፡) ብዙ አላበላሽባችሁ ታሪኩን፣ መጽሐፉ 400 ብር ነው (ሁሉም ጣራ ነክቷል) ግን ከቻላችሁ አንብቡለት። ካልሆነ ኮንትሮባንድ እንሠራለን እንግዲህ ፎቶ እያነሳን 😁

ለቅምሻ ያህል፡

«ሁለተኛ ልጃቸው ከዘመቻ ተመልሶ ዐብሯቸው መኖር ጀምሮ ነበር። በወንድሙ ሞት ሐዘን ላጠቃቸው እናቱ ለዘር እንኳን ለመትረፍ፣ ወጣቱ ሁሉ እንደ ዐዲስ ሃይማኖት ከሚያብድለት ፖሊቲካ ራሱን ይለያል የሚል ግምት ነበር።

እርሱ ግን ከዘመቻ መልስ የሰፈሩን ወጣት ሁሉ ለኢሕአፓ ከመመልመልም ዐልፎ፣ የእናቱን መኖሪያ ቤት የፓርቲው "የጥናት ማእከል" እንዳደረገው የአደባባይ ምስጢር ነበር። ገዳም ሰፈርን ያስገረመው ግን እናትዬው፣ የገዳም ሰፈር ዋናዋ የኢሕአፓ "የኡኡታ ኮሚቴ" አስተባባሪ መሆን ነበር።

ያኔ፣ በቀይ ሽብር ዘመን የደርግ አብዮት ጠባቂዎች የተጠቆመባቸውን የኢሕአፓ አባላት ለመያዝ እና ለዐሠሣ ወደ ሰፈር ብቅ ሲሉ፣ በ'የሰፈሩ ያሉ የኡኡታ ኮሚቴ አባላት እሪታቸውን ያቀልጡት ነበር - ሊያዝ፣ ሊታሰር፣ ሊገደል የሚፈለገውን ተጠርጣሪ ለማስመለጥ። ማታ፥ ማታ የወይዘሮ አሰለፈች ኡኡታ ቀድሞ ይሰማ ነበር። በዚያ በጨለማ ኡኡታቸውን ሲያቀልጡት የልጃቸውን ደም የተበቀሉ ይመስላቸዋል። ሁለተኛው ልጃቸው 1970 ዓ.ም. መግቢያ ወደ እስር ተወረወረ። እንደ ድፍረቱ፣ እንደ እብደቱ፣ አብዮት ጠባቂዎች እንዴት ነጻ ርምጃ ሳይወስዱበት እንደቀሩ ገዳም ሰፈርን ያስገረመ ጉዳይ ነበር።

ቀይ ሽብር ዐልፎ፣ ሁለተኛው የሶማልያ ጦርነት ካራማራ ላይ በድል ተደምድሞም፣ የወይዘሮ አሰለፈች የምሽት ኡኡታ አልቆመም።»

ገጽ 23
ሐዋሳ ያላችሁ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች (on account of the International Conference of Ethiopian Studies) ረቡዕ ከሰዓት ከፓናል 9.8 በኋላ ለዶ/ር ኤልሳቤጥ ወ/ጊዮርጊስ የተዘጋጀ የማስታወሻ ፕሮግራም አለ እሺ? ከቻላችሁ እንድትገኙ ነው።

ለማትሳተፉ፡ ፕሮግራሙን (የኮንፈረንሱን) እዚህ ማየት ትችላላችሁ፡ https://ices22.hu.edu.et/
ጥያቄ፡

ስለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሥርዓት አወቃቀር በእንግሊዝኛ አርቲክሎች አንብቦ ይታተም አይታተም የሚል ግምገማ መስጠት የሚፈልግ ካለ ጻፉልኝ እባካችሁ። ለጆርናል ሪቪው የሚያደርጉ እየፈለግን ነው።

ከምስጋና ጋር
ፎቶ፡ ብላታ ኅሩይ ወልደሥላሴ በግቢያቸው። አሁን Academy of Sciences የሆነው ማለት ነው።

ከ James De Lorenzi አዲሱ መጽሐፍ፡ Feasting on History: Ethiopia and the Orientalists ገጽ 32
ማስታወቂያ፡
ዛሬ ሸገርደርቢ ወደ አዲስ አበባ ስታድየም ይመለሳል 😍 እቺን በማስመልከት የዛሬ ስንት ጊዜ ስለእግርኳስ ደጋፊዎች የጻፍኩትን አርቲክል በድጋሚ፡
በዛውም ስለ ፀሐይ ግርዶሽ በ1918 ዓ/ም ላይ በብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ምን እንደተባለ ላሳያችሁ።

«ብዙ ያልተማሩ ሰዎች ግን የምትሐት ነገር ይመስላቸውና መዓት ሊመጣ ምልክት ነው እያሉ ያወራሉ ግን በየዘመኑ የሚሆን የፍጥረት ሕግ ነው።» ይሉናል ብርሃንና ሰላሞች።

ቅጽ 2፣ ቁጥር 3፣ 1918 ዓ/ም
የሰሎሞን ገብረየስ መጽሐፍ Ethiopic Hagiographical Texts፡ Textual Transmission, Edition, Translation,
and Interpretation ታትሞ ተለቋል። 🎉

ለኤትዮፒካ መጽሔት supplement ሆኖ ነው የወጣው እና የኔም "Chronicling the Battle of ʾƎmbābo, 1882" ጽሑፍ ውስጡ አለ።

ማውጫውን እና አርቲክሉን ከሥር ልኬያለሁ። ሙሉውን መጸሐፍ ግን ኦንላይን ሲለቀቅ ነው ገና የምናገኘው። እዚህ ቼክ አድርጉ https://www.harrassowitz-verlag.de/Ethiopic_Historiographical_Texts/titel_8566.ahtml
ሰላም ጤና በድጋሚ፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ያለ ሰው ወይንም ሌላ፡ ቻሌንጅ ጋዜጣ ያለው ይኖር ይሆን?
2025/10/21 23:04:13
Back to Top
HTML Embed Code: