Telegram Web Link
ሰላም ብያለሁ፡

በፕሮፍ. ባሕሩ ዘውዴ ግለታሪክ ላይ የጻፍኩትን ሪቪው ማንበብ ለምትፈልጉ እዚህ ታገኙታላችሁ፡ https://journals.sub.uni-hamburg.de/aethiopica/article/view/2149/2176

PDF ፋይሉንም ከሥር ልኬያለሁ
ጦብያን በታሪክ
Erlich announcement.pdf
ሰላም ጤና፡

ጁን 20 ከሃምበርግ ዩኒቨርሲቲ ሊተላለፍ የነበረው የፕሮፌሰር ሃጋይ ኤርሊክ ሌክቸር በወቅታዊ ቀጠናዊ ችግሮች ምክንያት ተሰርዟል።

(ከይቅርታ ጋር እንግዲህ ዓለሚቷን የምታዩአት ናት።)

ስለአካባቢው ይበልጥ ለመረዳት ለምትፈልጉ ግን The Red Sea: The Sad Sea የተባለው መጽሐፋቸውን ተርጉሜው የለ? እሱን ከሥር እልክላችኋለሁ -- ቀለል ያለ የታሪክ ሥራ ነው።
Co_opt_and_repress_Dynamics_of_youth_government_relations_in_post.pdf
814.1 KB
ሰላም ወገን፣ ተጠፋፋን ይቅርታ። ሥራ በዝቶ ነው።

በቅርብ የታተመ አሪፍ ጽሑፍ አለ፡ Co-opt and repress: Dynamics of youth-government relations in post-2018 Ethiopia ነው ርዕሱ።

(Perhaps አንዱን ጸሐፊ (አማንን) ታውቁት ይሆናል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካል ሳይንስ መምህር ነበረ። አስተምሯችሁ ከነበረ)
ወመዘክር አባቷን አጣች አ? የአዋቂዎች ቤት ነበረ ድሮም ግን ይኩኖዬ ቤት እንዳለን እንዲሰማን አርጎን ነበረ። የማያግዘው የገጠር ትምህርት ቤት፣ ቤተመጻሕፍት አልነበረም። ተማሪ/ተመራማሪ ማየት የሚፈልገው ሰነድ ሲኖር ይኩኖ ምንም አይነት ውስብስብነት ሳያበዛ ባንዴ ነገሮችን ያቃልልልን ነበረ። በየጊዜው ሊቃውንትን እያሰባሰበም ጉባኤዎን ያካሄድም ነበረ። እዚህም ካስታወሳችሁ ገነተ ማርያምን መጽሐፍ ስናሰባስብላት ልንናገር የማንችለውን ያህል ነበረ የቻለልን። መቼም ኢትዮጵያ የሚሠራላትን አትወድም። በጳውሎስ ኞኞ ቃላት፡ ደኅና እንሁን ብቻ

Just a post of appreciation and respect። ይቅናህ ይኩኖዬ!
ፎቶ፡ አራዳ-የአውቶሞቢሎች ማቆሚያ፣ 1920 ዓ.ም.
በዘውዲቱ ጊዜ ስለሴቶች ትምህርት ቤት መቋቋም ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ላይ አንድ እህት የጻፉትን እዩማ።

ከብርሃንና ሰላም ጋዜጣ፣ አንድኛ ዓመት፣ ቅጽ 32፣ 1917 ዓ.ም.
ከፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል የተለቀቀ የሴሚናር ማስታወቂያ፡

Title: A Geopolitical Perspective on Livestock Exports from the Horn of Africa
Speaker: Dr. Géraldine Pinauldt (Associate Research Fellow at IRIS, Doctor in geography & geopolitics)
Date and Time: Thursday, July 24, 2025, at 2:00 PM (Addis Ababa time)
Venue: At the CFEE or online via Zoom

Zoom link: https://cnrs.zoom.us/j/91776559120?pwd=RucQ3l58cVI571qOxtL18b4YaBeDva.1
ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ውስጥ ነፍ ግጥሞች ነው ያሉት። ሰዉ እንዲታተምለት ደብዳቤም ሲልክ፣ አርቲክሎችም ሲያስገባ ስነግጥም አብሮ ይልካል። አንድ ላሳያችሁ፡

አንደኛ ዓመት፣ ቅጽ 47፣ (ገጽ 209b) ተስፋዬ ካሣ ከሚባል ጸሐፊ የተላከ።
ሰላም ጤና፡

PhD ትምህርት መከታተል ለምትፈልጉ እስቲ ይሄን መጥሪያ ተመልከቱ።
መልካም ዐውዳመት። እንኳን አደረሳችሁ ለሁላችሁም!

🌼🌼🌼
ሃምቡርግ ዩኒ የቤተመጻሕፍት ክፍል ሁለት የሥራ ማስታወቂያዎችን ለቋል። ግዕዝ የምትችሉ እና ሌሎቹን መስፈርቶች የምታሟሉ እስቲ አመልክቱ። ድረገጹ በጀርመንኛ ቢሆንም ጉግል ትራንስሌት ይመልስላችኋል፡

https://www.uni-hamburg.de/stellenangebote/ausschreibung.html?jobID=a384b7ae6bf37a5c1acb06617bc695c952312241
ሰላም ብያለሁ፡

ስለ ባርያ ንግድ በኢትዮጵያ አዲስ መጽሐፍ ተለቋል። ከሥር ልኬላችኋለሁ ማየት ለምትፈልጉ፡
2025/10/21 14:08:46
Back to Top
HTML Embed Code: