Telegram Web Link
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ጦብያዎች

እመት ገነት አየለ ከዚህ በፊት በሁለት ቅጽ ከፈረንሳይኛ የተረጎመችው የዳባዲ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራራዎች ቆይታዬ መጽሐፍ ሦስተኛ ክፍሉ ሰሞኑን ተመርቋል። አብሶ ከአጼ ቴዎድሮስ መነሳት በፊት ስለነበረው 19ኛ ክ/ዘ ኢትዮጵያ ማወቅ ለምትፈልጉ ጠቃሚ የታሪክ ሰነድ ነው።

የመጽሐፉ ምርቃት የካቲት 15 ቀን ነበረ ግን ዛሬ ገና ነው እኔም ያየሁት። ባይሆን ዋልያ መጻሕፍት ዩትዩብ ላይ ውይይቱን ሊያወጣው ይችላል

[መረጃውን ለሰጠን አባ በዝብዝ እናመሰግናለን ፡)]
ሌላ አዲስ መጽሐፍ ለማስተዋወቅ ያህል፡ Africa as Method: A Handbook of Sources and Epistemologies

ከሥር አያይዤዋለሁኝ።
ሰላም ጤና፡

ሁለት የተለያዩ ዌቢናሮችን ለማስተዋወቅ ያህል ነው።

1. March 24 እና 25 የሚካሄድ Unpacking Mixedness for an Inclusive History of the Red Sea, 1800s-2000s የተባለ ዝግጅት አለ። ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ተመልከቱ፡ https://unifind.unito.it/resource/project/FUSV_HEU_ERC_COG_24_01
ለመመዝገብ እዚህ ሂዱ፡ https://docs.google.com/forms/d/1PdkwFtY60Lr2agORVDR0Kq9NGjGJ9OSxxoZYjSqTMZ4/viewform?edit_requested=true

2. April 2 እና 3 የሚካሄድ “The Black Indian Ocean: Slavery, Religion, and Expressive Cultures (1400-1700),” የተባለ ሌላ ፕሮግራም ነው። የሱን ማስታወቂያ ከሥር አያይዤ ልኬላችኋለሁ። ማስታወቂያው መጨረሻ ላይ ሁለት QR Codeኦች አሉ። በነሱ ነው የምትመዘገቡት/ፕሮግራሙን የምታዩት።

መልካም ዐርብ
ሌላ ማስታወቂያ፡

ቀኃሥ ያረፉበትን እና የኢትዮጵያ ንጉሣዊ ሥርዓት ያበቃበትን 50ኛ ዓመት በማስመልከት Africa የተባለው ጆርናል ከ May 31, 2025 በፊት ስለ ንጉሠ ነገሥቱ ታሪካዊ ጽሑፎችን ማቅረብ ለሚችሉ ጥሪ አቅርቧል። ጽሑፉ 10ሺህ ቃላት መሆን አለበት -- ረዘም ያለ አርቲክል ነው የሚፈለገው።

የጆርናሉ ድረገጽ፡ https://www.viella.it/riviste/testata/15 ይሄ ነው።
ለቅዳሜያችሁ፡

የአንድርያስ እሸቴ ቃለመጠይቅ ከዳግማዊ ዉብሸት ጋር።
ዐቢይ ተክለማርያም "አደናጋሪው ምሑር" ብሎ ስለ ፕሮፍ አንድርያስ እሸቴ የጻፈው የአዲስ ነገር ጽሑፍ ያለው ሰው አለ? ለሥራ ፈልገነው አጥተነው ነው።

አመሰግናለሁ
«ሰው መሆን አለ እንጂ»

ሰሞኑን የጋሽ አለማየሁ ፈንታን፣ ዛሬ ደግሞ የጋሽ መርአዊ ስጦትን እና የፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ወ/ጊዮርጊስን በሞት መለየት ዜና ሰማን።

የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል አካባቢ ላላችሁ ፕሮፍ ኤልሳቤጥን በአካል ባይሆን እንኳን ወይ በስም ወይ በዝና ልታውቋት ትችሉ ይሆናል። የማዕከሉ ዳይሬክተር ነበረች ከተወሰነ ዓመታት በፊት። በቅርብ Modernist Art in Ethiopia የሚል መጽሐፏን አሳትማ ነበር።

ሁሉንም ነፍስ ይማርልን።
አዲስ መጽሐፍ ስለማስተዋወቅ፡ History of Women in Ethiopia
ሰላም ጤና ወገን፡

ይሄን ማመልከቻ እስቲ እዩ። ፕሮጀክቱ ስለ ሴቶች ነው። WomAtWork represents the first comparative investigation into the history of female urban popular professions in in five African countries – Kenya, Ethiopia, Ghana/Gold Coast, Sudan, and Tanganyika/Tanzania – over the course of fifty years (1919-1970). Not only is this topic under-studied in African history, but these professions (i.e. midwives, beauticians, market vendors, craftswomen, wedding or ritual singers) are also characterised by fascinating and unsettling aspects. For example, notions such as a set price for a service and fixed working times or workplace did not apply to many of such professions.

https://euraxess.ec.europa.eu/jobs/314857
ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ 1ኛ ዓመት ቁጥር 4 (ጥር 14 ቀን 1917 ዓ.ም.)

ጋዜጣው በዚህ ዘመን 4 ገጾች ነው ርዝመቱ። የሚያበቃው ታድያ ከጃንሜዳ ሽቅድድም ማሕበር በወጣ ማስታወቂያ ነው።

አጭር ማስታወቂያ ነው። Striking ነገሮች አሉት፡ በዛን ዘመን ማኅበርተኞች ጋዜጣ ማንበባቸው ታውቆ ማስታወቂያ መለቀቁ በጋዜጣ፣ ወራት በፈረንሳይኛ ቀናት ደግሞ በግእዝ ቁጥር መጻፋቸው፣ ማስታወቂያውን የጻፈው ደግሞ ኮምት ጀ ኮሊ የተባለ ሰው መሆኑ (ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ፈረንጅ ይሆን?) ወዘተ። በዘመኑ ለፈረንሳይኛ እናዳላ ነበር መሰል ግን ስዋሰዉም ለየት ይላል አይደል? በደንብ ባያችሁት ቁጥር ጸሐፊው አማርኛን ተወልዶበት አድጎበት ሳይሆን እንደተጨማሪ ቋንቋ የተማረ ይሆን ያስብላል። «መሰብሰብ» የሚለው ቃል ነው እንዲህ ያስባለኝ

-- ይኸው ለማንኛውም፡ እራሳችሁ እዩት
5th Circular_5_List_of_Accepted_panels_ICES22.pdf
1.1 MB
ሰላም ጤና

ሐዋሳ ለሚካሄደው 22ኛው የኢትዮጵያ ጥናት ጉባኤ የተመረጡት ፓኔሎች እነዚህ ናቸው።

ከነዚህ መካከል ይሆናል ላላችሁት abstract ልካችሁ ሥራችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።
CFEE Doctoral program (3).png
2.3 MB
Message from the CFEE (የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል):

"Dear all,

We are pleased to invite you to the CFEE Doctoral Conference, which will take place this Friday, April 4th, 2025. This event will be an opportunity to learn about the work of last year’s scholarship recipients, engage in insightful discussions, and inspire new ideas that could greatly benefit new research.

It will also be a great chance to strengthen your academic network and connect with scholars from various fields.
📅 Date: April 4th, 2025
Time: 9:30 AM – 6:30 PM (lunch provided) ከጥዋቱ 3 ተኩል እስከ ምሽቱ 12 ተኩል
📍 Location: French Center for Ethiopian Studies, Addis Ababa 🇪🇹
🔗 Registration is required: https://forms.gle/7HpSX96iCPD5trF87

💻 The event will also be accessible online via Zoom: https://cnrs.zoom.us/j/91712384824?pwd=BLPWIOUT4W7W48Wl2EwzBQiMdqzUNa.1
Meeting ID: 917 1238 4824
Passcode: CfeeDD2025"
2025/10/22 22:41:58
Back to Top
HTML Embed Code: