Telegram Web Link
አእምሮ ጋዜጣ ላይ አንድ ሰው የኢትዮጵያ ልጆች የፈረንጅ ቋንቋን የሚማሩት ሀገሩን ፈረንጅ ሲገዛው አስተርጓሚ ለመሆን ነው ብለው ጽፈው ብርሃንና ሰላም ላይ ብዙ መልስ ተጽፎላቸው እናገኛለን። አንዱን ላሳያችሁ፡

ሰውየው ምን ያህል እንደተሰማቸው አንብቡትማ። «እኛ ጥቂት ጥቂት የተማርነው ሰዎች» ብለው ነው ራሳቸውን የሚገልጹት እና የተሰደቡ ቢመስላቸው አይደንቀንም። ሀገሪቷን በሁለት መንገድ ጉዳት ብለው ያስቀመጡትንም እዩ። መጨረሻ ላይ «ይህ ሰውዬ ካወራባት መዓት እንዲሰውራት እናምናለን» ሲሉ ግን አሳቁኝ ፡) አእምሮ ሙሉ በሙሉ ስለሌለኝ ያ ሰው መልስ ይስጥ አይስጥ እንጃ። ይሄ ውይይት መኖሩ በራሱ እና በሁለት ጋዜጦች መካከል በ1917 ዓ.ም. ገደማ መደረጉን ስታስቡት ግን ደስ አይልም?

አያሳዝኑም? ወይንስ እኛ ነን የምናሳዝነው?

ብርሃንና ሰላም፣ ቅጽ 1፣ ቁጥር 5፣ ጥር 21 ቀን 1917 ዓ.ም.፣ ገጽ 20።
Manuscript treasures from afroeurasia.pdf
141.5 MB
አዲስ መጽሐፍ ለማስተዋወቅ፡

Manuscript Treasures from Afro-Eurasia፡ Scribes, Patrons, Collectors, and Readers
ለዜና ልሳን ጆርናል አዲሱን ቅጽ (ቅጽ 33፣ ቁጥር 2) ሰሞኑን ለቋል።

ርዕሶቹን እዩማ፡

አድራሻው ይኸው፡ https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/issue/view/1065
ቀኃሥ ፓርላማ ደጅ ላይ፡

ከ፡ አጼ ኃይለሥላሴ - ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ እንግሊዝኛ ትርጉም።

መልካም ዓርብ።
ለምታከብሩ ሁሉ፡ መልካም የትንሣኤ በዓል። እንኳን አደረሳችሁ ❤️

(ይቅርታ ዘገየሁ)
ሰላም ጤና።

እኚህን እዩማ፡ በ19ኛው ክ/ዘ ፈረንሳይ የተላኩ ብራናዎች ስብስብ መሃል የተገኙ አባባሎች ናቸው።

«ዜጋየ መጥቶ ትናንት። አግኝቶ ነበር ጥቂት ከብት
አትዋረዱ እንዲያው ኑሩ ወንድሞቸ ታፈሩ
ወንዱም እንደሴት አርግዞ። የሚሞት ሆነ ተወዝውዞ» ወዘተ...

ለራሳችሁ አንብቧቸው፡፡

ከ፡ MS d'Abbadie 254፣ 19
CALL FOR ABSTRACTS.pdf
93 KB
ሰላም ጤና

ለሐዋሳው Conference call for abstracts ልከን ነበረ ግን ዛሬ አዘጋጆቹ በአንድ ወር ውስጥ ማን ምን እንደሚያቀርብ አሳውቁ ስላሉን ለMay 31, 2025 የነበረው ቀነገደብ ወደ April 30, 2025 ዞሯል ማለት ነው።

Abstract ለመላክ አስበናል ያላችሁን ሁሉ እባካችሁ በቶሎ አሳውቁን።
በተጨማሪም፡ የኛ ፓናል ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወደ 10 ፓናሎች እዚህ ተያይዘው አሉ። You may submit papers to any of them.
Hallo everyone,

መሳተፍ ለምትፈልጉ፡ 20 june 2025 ዕለት ፕሮፍ. ሃጋይ ኤርሊክ ከሃምበርግ ዩኒ ንግግር ያቀርባሉ። ዝግጅቱን በዙምም መሳተፍ ትችላላችሁ። ካሁኑ እያስተዋወቅኩት ስለሆነ ነው -- ገና ወር ከሳምንት አለን።

ርዕሱ፡ Ethiopia and the Middle East over the Last Century ነው።

ሰዓቱ፡ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ።

ማስታወቂያው ይኸው፡
ሰላም ብያለሁ፡

በፕሮፍ. ባሕሩ ዘውዴ ግለታሪክ ላይ የጻፍኩትን ሪቪው ማንበብ ለምትፈልጉ እዚህ ታገኙታላችሁ፡ https://journals.sub.uni-hamburg.de/aethiopica/article/view/2149/2176

PDF ፋይሉንም ከሥር ልኬያለሁ
2025/10/22 16:10:10
Back to Top
HTML Embed Code: