Telegram Web Link
👉🏿Windows 11 SE won’t be sold separately, can’t be reinstalled once removed
👉🏿Tesla Supercharger network reaches new milestone: 30,000 chargers worldwide
👉🏿Twitter Will Soon Let You Set NFT Profile Pictures
👉🏿WhatsApp Beta Now Lets You Hide Last Seen Status from Specific People
👉🏿PUBG New State iOS release delayed to November 12
👉🏿YouTube will now hide public dislike counts on videos
@endu12endu
@yoni709
@ethiotec
👍1
ዲቪ ለምትሞሉ በሙሉ ❗️
ዲቪ ሎተሪ ሲሞላ የሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ስህተቶች ምን ምን ናቸው?

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ ወይም ድቪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ትወስዳለች። ከነዚህ 50 ሺህ የድቪ እድለኞች ውስጥ እስከ 40 ሺህ ያህሉ አፍሪካዊያን ናቸው፡፡

ኢትዮጵያዊያን የድቪ ሎተሪ ማመልከቻን በብዛት ከሚሞሉ መካከል ዋነኞቹ ሲሆኑ በየዓመቱ በአማካኝ ከ2 ሺህ እስከ 4 ሺህ ድረስ የእድሉ ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ ይገለጻል፡፡

የ2025 የድቪ ሎተሪ ማመልከቻ ጊዜ ካሳለፍነው መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት የሆነ ሲሆን እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የድቪ ማመልከቻ ሲሞላ በተደጋጋሚ የሚፈጸሙ ስህተቶች ምን ምን ናቸው? የሚሉትን እንደሚከተለው አዘጋጅተንላችኋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን አመልካቾችን ጨምሮ በመላው ዓለም ከሚፈጸሙ ስህተቶች መካከል የመጀመሪያው ስምን እና የልደት ቀንን በትክክል አለመሙላት ነው፡፡ በነዚህ ስህተቶች ምክንያት በየዓመቱ በርካቶች የድቪ እድለኞች ቢሆኑም በመጨረሻም ቪዛ ለመከልከላቸው ዋነኛው ምክንያት ይሆናል፡፡

ሁለተኛው ተደጋጋሚ የሚፈጸመው ስህተት የድቪ ማመልከቻን ከአንድ ጊዜ በላይ መሙላት ሲሆን ማመልከቻዎትን ከአንድ ጊዜ በላይ ከሞሉ ማመልከቻዎ ውድቅ ይደረጋል፡፡

ትክክለኛውን የድቪ ሎተሪ ማመልከቻ ድረገጽ አለመጠቀም ሌላኛው በተደጋጋሚ የሚፈጸም ስህተት ሲሆን የሶስተኛ ወገን ድረገጽን ተጠቅመው ማመልከት የለቦትም፡፡

አራተኛው ተደጋጋሚ ስህተት የድቪ ማመልከቻ ፎርምን በሌላ ሰው ማስሞላት ሲሆን ይህም ለተለያዩ ስህተቶች የሚያጋልጥ በመሆኑ የድቪ ማመልከቻዎትን ራስዎ ቢሞሉ የተሻለ ይሆናል፡፡

እንዲሁም የድቪ ማመልከቻ ሲሞላ ሙሉ የቤተሰብን ሁኔታ አለመሙላት አምስተኛው ተደጋጋሚ ስህተት ሲሆን በተለይም የባል ወይም ሚስት ስም፣ የልጆች ስም እንዲሁም የትዳር ሁኔታን በትክክል አለመሙላትም የድቪ እጣ ቢደርስዎትም ቪዛ ሊያስከለክልዎ ስለሚችል በትክክል ስለ መሙላትዎ እርግጠኛ ይሁኑ፡፡

ሌላኛው በአመልካቾች የሚፈጸም ተደጋጋሚ ስህተት ደግሞ ጥራቱን የጠበቀ ፎቶ አለመጠቀም ሲሆን ማመልከቻዎትን ሲሞሉ ጥራቱን የጠበቀ ፎቶ መያዝዎን ያረጋግጡ፡፡
@endu12endu
@yoni709
❤1
DV 2025ን ያለ ማንም እገዛ  እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?

📌ዲቪ 2025 ያለ ማንም እገዛ ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ፦

›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከመስከረም 23 እስከ ጥቅምት 27/2016 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።

⚡️የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦

📌እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም-

📌ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም
📌ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
📌ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ ፎርም መሙያዉ መግባት።

⚡️ፎርም አሞላል

📌1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣ First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።

📌2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።

📌3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year ( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.

📌4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.

📌5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር

📌6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ

📌7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል * በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ ፣JPEG Format መሆን አለበት።

📌8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት

📌9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ

📌10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል

📌11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት

📌12. What is the highest level of education you have achieved, as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ

📌13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር ሁኔታ መምረጥ

📌14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።

⚡️በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን DV-2025 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2025 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ።




@endu12endu
@ethiotec
👍7😱2🤔1🙏1
✳️ ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች

🈴 1. የሀርድዌር መቃረን
ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት
Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ
Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request
channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡
እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን
አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር
IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር
የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት
ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም
የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት
ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡
በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር
ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት
ይችላል፡፡

🈴 2. የተበላሸ ራም
ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው
የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue
screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት
ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር
( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር
የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር
አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር
እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም
የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር
ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት
ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ
ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና
የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም
ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns
ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ
ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል
በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡

🈴3.ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)
እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት
ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡
እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2
ወይም F10 (እንደ
ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ
በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ
ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ
ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡
ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት
ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ
ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ
የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር
ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ
ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡
ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል
ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡

🈴 4.ቫይረስ
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት
ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች
ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች
የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን
በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ
ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን
ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር
ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን
ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡

🈴5.መጋል
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው
እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ
በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር
ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው
ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ
ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ
ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ
ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር
ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል
ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ
በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡
@endu12endu
@ethiotec @yoni709
Server(ሰርቨር) ምንድን ነው?
ሰርቨር ማለት በሁለት ይከፈላል እነሱም Hardware Server and Software Server በማለት።

ሰርቨር ማለት ከስሙ እንደምንረዳው አገልጋይ ማለት ሲሆን ለ Client Devices አገልግሎት የሚሰጥ ማለት ነው። በዚህም የሶፍትዌር ሰርቨር የምንላቸው
ዌብ ሰርቨር፣ ዶሜን ኔም ሰርቨር፣ ሜይል ሰርቨር በጥቂቱ መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም ስርቨር የሆኑ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጥቀስ ይቻላል ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ሰርቨር፣ ኡቡንቱ ጥቂቶች ናቸው።

Hardware Server የምንለው የኮምፒውተር አይነት ሲሆን መረጃን ለመያዝ የሚያገለግልና በክሊያንት ኮምፒውተሮች መረጃውን እንዲደርስና ዋና መረጃው የሚቀመጥበት ማለት ነው። ሰርቨር ኮምፒውተር በጣም በጣም ከፍተኛ የሆነ መረጃን የመያዝ አቅም ያለው፣ መረጃን ፕሮሰስ የማድረግ አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመስራት አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ በዋጋ፣ በአካላዊ ከመደበኛው ኮምፒውተር የሚተልቅ እቃ ነው።

በአንድ ሰርቨር ኮምፒውተር ለብዙ ክሊያንት ኮምፒውቲንግ እቃዎች(ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ ደስክቶፕ፣ ካሜራ፣ ፕሪንተር ወዘተ...) በአንድ ላይ ኔትወርክ በመጠቀም እርስ በራሳቸው እንዲተዋወቁ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ መረጃውን እንዲጋሩ ያደርጋል።

Client Devices የምንለው ማንኛውም የኮምፒውቲንግ እቃዎች ከሰርቨሩ ጋር በመግናኘት መረጃዎችን አሳሾችን(Browsers) በመጠቀም መረጃን የምንጠቀምበት እቃዎችን ያካትታል ለምሳሌ አሁን የምንጠቀምበት ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ሞባይል ስልክ ስልካችን ክሊያንት ዲቫይስ የሆነበት ምክንያት ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቱቭ ስንጠቀም መረጃውን ከሰርቨር ኮምፒውተር ላይ ኔትወርክ በመጠቀም የሚያመጣልንና ስለምንጠቀም ነው። በአጠቃላይ ሰርቨር ኮምፒውተር ማለት በጣም ብዙ መረጃዎችን አምቆ የያዘ ለተጠቃሚዎች በክሊያንት ኮምፒውተር አማካኝነት በመጠቀም መረጃን ከሰርቨር ኮምፒውተር በማምጣት ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ነው።

ክሊያንትና ሰርቨር ኮምፒውተር የሚገናኙበት ፕሮቶኮል TCP/IP ይባላል። TCP/IP በዋናነት መልእክቶች ከሰርቨር ኮምፒውተር ወደ ክሊያንት ኮምፒውተር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ ሲሆን በLAN Local Area Network ወይም በWAN Wide Area Network ክሊያንት ኮምፒውተሮችን ከሰርቨር ኮምፒውተሮች ጋር በማስተሳሰር መረጃን መለዋወጥ ያስችላል።
@endu12endu
@yoni709
@ethiotec
👍5
🎚 "ቴክኖሎጂ በመቃብር ስፍራ ላይ:"

🎚 #በጃፓን አገር   QR code የተገጠመላቸው የመቃብር  ሐወልቶች አየተበራከቱ ይገኛሉ

🎚 የኮዶቹ ጥቅም @QR ኮዱን በስልክ ስካን ሲደረግ ስለ #ሟቹ ማንነት ዝርዝር #መረጃን ይሰጣል።
🤩3
Lenovo Core i3
7th Gen
CPU : 2.3GHz
RAM : 4GB
HDD : 1TB

መግዛት የሚፈልግ ካለ
📱0945957800 ወይም @mIKI4595
❤2👍2
ዲቪ ለምትሞሉ በሙሉ ❗️
ዲቪ ሎተሪ ሲሞላ የሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ስህተቶች ምን ምን ናቸው?

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ ወይም ድቪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ትወስዳለች። ከነዚህ 50 ሺህ የድቪ እድለኞች ውስጥ እስከ 40 ሺህ ያህሉ አፍሪካዊያን ናቸው፡፡

ኢትዮጵያዊያን የድቪ ሎተሪ ማመልከቻን በብዛት ከሚሞሉ መካከል ዋነኞቹ ሲሆኑ በየዓመቱ በአማካኝ ከ2 ሺህ እስከ 4 ሺህ ድረስ የእድሉ ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ ይገለጻል፡፡

የ2025 የድቪ ሎተሪ ማመልከቻ ጊዜ ካሳለፍነው መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት የሆነ ሲሆን እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የድቪ ማመልከቻ ሲሞላ በተደጋጋሚ የሚፈጸሙ ስህተቶች ምን ምን ናቸው? የሚሉትን እንደሚከተለው አዘጋጅተንላችኋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን አመልካቾችን ጨምሮ በመላው ዓለም ከሚፈጸሙ ስህተቶች መካከል የመጀመሪያው ስምን እና የልደት ቀንን በትክክል አለመሙላት ነው፡፡ በነዚህ ስህተቶች ምክንያት በየዓመቱ በርካቶች የድቪ እድለኞች ቢሆኑም በመጨረሻም ቪዛ ለመከልከላቸው ዋነኛው ምክንያት ይሆናል፡፡

ሁለተኛው ተደጋጋሚ የሚፈጸመው ስህተት የድቪ ማመልከቻን ከአንድ ጊዜ በላይ መሙላት ሲሆን ማመልከቻዎትን ከአንድ ጊዜ በላይ ከሞሉ ማመልከቻዎ ውድቅ ይደረጋል፡፡

ትክክለኛውን የድቪ ሎተሪ ማመልከቻ ድረገጽ አለመጠቀም ሌላኛው በተደጋጋሚ የሚፈጸም ስህተት ሲሆን የሶስተኛ ወገን ድረገጽን ተጠቅመው ማመልከት የለቦትም፡፡

አራተኛው ተደጋጋሚ ስህተት የድቪ ማመልከቻ ፎርምን በሌላ ሰው ማስሞላት ሲሆን ይህም ለተለያዩ ስህተቶች የሚያጋልጥ በመሆኑ የድቪ ማመልከቻዎትን ራስዎ ቢሞሉ የተሻለ ይሆናል፡፡

እንዲሁም የድቪ ማመልከቻ ሲሞላ ሙሉ የቤተሰብን ሁኔታ አለመሙላት አምስተኛው ተደጋጋሚ ስህተት ሲሆን በተለይም የባል ወይም ሚስት ስም፣ የልጆች ስም እንዲሁም የትዳር ሁኔታን በትክክል አለመሙላትም የድቪ እጣ ቢደርስዎትም ቪዛ ሊያስከለክልዎ ስለሚችል በትክክል ስለ መሙላትዎ እርግጠኛ ይሁኑ፡፡

ሌላኛው በአመልካቾች የሚፈጸም ተደጋጋሚ ስህተት ደግሞ ጥራቱን የጠበቀ ፎቶ አለመጠቀም ሲሆን ማመልከቻዎትን ሲሞሉ ጥራቱን የጠበቀ ፎቶ መያዝዎን ያረጋግጡ፡፡
@endu12endu
@yoni709
ኤሎን መስክ  ትዊትር /twitter / የትስስር ገጽ በ44 ቢሊዮን ዶላር ከገዛው በኋላ

1. ስሙ ከትዊተር (twitter ) ወደ ኤክስ (X) ቀይሮታል
2. 80%  የቀድሞ ሰራተኞችን  ከድርጅቱ አባሯል ወይም  በራሳቸው  ለቅቀዋል
3.የማረጋገጫ ምልክትን (vervied badge) በወርሃዊ ክፍያ እንዲሆን አድርገዋል
4.አካውንት ለመክፈት አንድ ዶላር ክፍያ ይጠይቃል
5.የድምጽ እና ቪዲዮ ኮል ወይም የመደዋወያ አገልግሎትን አስጀምሯል
6.የተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር የ11 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ @endu12endu @yoni709
#እንድታውቁት

Computer Vision Syndrome(CVS)

- ለረጅም ሰዓት ኮምፒውተር ወይም ዲጂታል ስክሪን áˆ‹á‹­ መመልከት (ጊዜ ማሳለፍ) ዓይናችን ላይ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ጫና ያሳድራል፤  ከዚህ ጋር ተያይዞ የተለያዩ ችግሮች አብረው ይከሰታሉ፡፡

እነዚህ ችግሮች የሚከሰተቱትም áŚ

▪️ሳያቋርጡ ለረጅም ሰዐት መጠቀም
▪️የክፍላችንና የስክሪናችን ብርሀን ሳይመጣጠን ሲቀር
▪️ስክሪናችን ከዓይናችን የተመጠነ ርቀት ላይ ሳይቀመጥ ሲቀር
▪️ልክ ያልሆነ አቀማመጥ
▪️ያልታከመ የዕይታ ችግር ካለ     

ምልክቶቹ ፦

- ብዥ ማለት
- የዓይን መድረቅ፣የዓይን መቅላት
- ከዕይታ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የራስ ምታት(Eye strain)
- ዓይን መድከም (eye fatigue)
- የአንገትና ትከሻ ህመም

ምን እናድርግ ?

- ስክሪናችንን ከዓይናችን ቢያንስ ከ40-50cm(በክንድ ርቀት) ላይ ማስቀመጥ
- ክፍላችን በቂ ብርሃን እንዲኖረዉ ማድረግ
- የዕይታ ችግር ካለ ወደ ህክምና በመሄድ መታከም
- የአንገትና የትከሻን ህመም ለመከላከል አቀማመጣችንን ማስተካከል
- ከስክሪን ጨረር የሚከላከሉ መነፅሮችን እንደ(Blue cut, Anti-reflective coating) መነፅሮችን መጠቀም
- በየመሀሉ ዕረፍት መውሰድ (በየ20 ደቂቃው ዓይን ዘና እንዲል ለ20 ሰከንድ ያህል ከስክሪኑ ራቅ ወዳሉ ነገሮች መመልከት)
- ዓይን ማርገብገብ (እንባ በደንብ እንዲሰራጭና ዓይናችን ለብዙ ሰዐት ትኩረት ከማድረግ የተነሳ የሚመጣውን የዓይን ድርቀት ይከላከላል፡፡)

▫️በዚህ ጊዜ የአብዛኞቻችን ህይወት ከዲጂታል ስክሪን ጋር የተቆራኘ ነውና የዓይናችን ጤንነት ግድ ሊለን ይገባል። @endu12endu @yoni709
👍1
✳️ላፕቶፓችን ያለኛ ፍቃድ ፍላሽ ዲስክ እንዳይቀበል ማድረግ እንዴት እንደ ሚቻል ላሳያችሁ።

⚡️ፍላሽ ዲስክ ፋይሎችን የምናስቀምጥበትና በቀላሉ ይዘነው የምንቀሳቀሰው ማሽን ነው፡፡ በስራ ምክንያትም ይሁን በሌላ ፋይሎችን ለማስተላለፍና ኮፒ ለማድረግ ሰዎች የሚጠቀሙበት ፍላሽ ዲሰኮች ላፕቶፓችን ላይ እንሰካል፡፡

⚡️ላፕቶፓችን ላይ ያገኘነውን ፍላሽ ዲስክ የምንሰካ ከሆነ ደሞ ላፕቶፓችን አደጋ ውስጥ ይገባል፡፡
ምክንያቱም ፍለሽ ዲሰክ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን ቫይረሶችንም ስለሚያስቀምጥ ያገኘነውን ፍላሽ ላፕቶፓችን ላይ የምንሰካ ከሆነ በፍላሽ ዲሰኮች አማካኝነት ቫይረሶች ወደ ኮፒውተራችን በመግባት ላፕቶፓችን ላይ አደጋ ሊያደርሱ ይችላል፡፡

⚡️ከኛ ፍቃድም  ውጪ ሳናውቀው አንድ ሰው ተደብቆ ላፕቶፓችን ላይ ፍለሽ ዲሰክ በመሰካት ላፕቶፓችንን ክጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡

⚡️ስለዚህ በተለይ ያለኛ ፍቃድና እውቀት ላፕቶፓችን ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ለማድረግ የሚከተሉትን ስቴፖች መከተል ነው፡፡

1ኛ፡-መጀመሪያ Start በተንን ክሊክ እናደርግና gpedit.msc ብለን እንፅፍና ኢንተር እንጫናል፣

2ኘ፡- የተለያዩ አማራጮች የያዘ ሊስት ይመጣል፤ ሊስቱ ውስጥ “Local Group Policy Editor” የሚለውን ምረጡ፣

3ኛ፡-ከዚያ የሚከተለውን መንግድ ተከተሉ ፤ computer configuration>administrative templates>system>Removable storage access

4ኛ፡-አሁን በቀኝ በኩል ከሚመጡ አማራጮች ውስጥ “All Removable Storage Classes: Deny all access” የሚለውን ክሊክ ማድረግ፣

5ኛ፡- “Enable” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣

6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡

⚡️አለቀ፡፡ ካሁን በኋላ ማንም ሰው ፍላሽ ዲስኩን ላፕቶፓችሁ ላይ መሰካት አይችልም፡፡

⚡️ምናልባት ይህንን የከለከላችሁትን አክሰስ መመለስ ስትፈልግ ከላይ ከ1 እስከ 4 ስቴፖችን እንዳሉ ተከተሉ እና፣

5ኛ፡- “Not Configure” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣

6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ በማድረግ ወደ ነበረበት መመለስ እንችላለን፡፡
@endu12endu
@yoni709
👍1
እንማማር
A to Z የኮምፒዩተር አቋራጭ  መንገዶች የምንላቸውን እነሆ።
( Shortcuts )

✅ ትዕዛዛት፡-👇

CTRL + A =>> Select all
CTRL + B =>> Bold
CTRL + C =>> Copy
CTRL + D =>> Fill down cell
CTRL + E =>> Center Alignment
CTRL + F =>> Find
CTRL + G =>> Go to current
CTRL + H =>> Replace
CTRL + I =>> Italic
CTRL + J =>> Full justification
CTRL + K =>> Create hyper link
CTRL + L =>> Left Alignment
CTRL + M =>> Tab
CTRL + N =>> New page
CTRL + O =>> Open
CTRL + P =>> Print
CTRL + R =>> Fill right cell
CTRL + S =>> Save
CTRL + U =>> Underline
CTRL + V =>> Paste
CTRL + X =>> Cut
CTRL + Y =>> Redo
CTRL + Z =>> Undo

@endu12endu
@yoni709
👍2
የቢሯችን  ወይም  ቤታችን   #WiFi እንዳይጠለፍ እና ለመረጃ ጥቃት እንዳያጋልጠን በምን መልኩ መከላከል እንችላለን?

ባለንበት የዲጂታል ዘመን በተለይም በከተሞች አካባቢ ከቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር በተያያዘ  የዋይ ፋይ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ተበራክቷል፡፡ ብዙ ጊዜ ለቤት ዉስጥ አገልግሎትም ሆነ ለመስሪያ ቤት ያስገጠምነዉ ዋይፋይ እኛ ያሰብነዉን አገልግሎት እየሰጠን ከሆነ ሾለ ደህንነቱ ብዙም ግድ አይሰጠንም፡፡ ነገር  ግን ይሄ ተግባር ፍፁም ስህተት የሆነና ብዙ ችግሮችን ሊያስከትል የሚችል ጎጂ ልምድ ነው፡፡

ለምንጠቀማቸው ዋይፋዮቻችን ተገቢውን የደህንነት ስርዓት ተግባራዊ የማናደርግ ከሆነ የሳይበር ወንጀለኞች አውታረ-መረቡን /networks/ በመጠቀም ምስጢራዊ መረጃዎችን መመንተፍ እና ዋይፋዩን በሚገባው ፍጥነት እንዳንጠቀም አገልግሎቱን  ሊያስተጓጉሉብን ይችላሉ፡፡

በመሆኑም ከአገልግሎት መስተጓጎል እና ከመረጃ መዝባሪዎች  ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጮች ተግባራዊ ማድረግ  ይመከራል፡፡

• ጠንካራ የይለፍ ቃል /password/ ይጠቀሙ
የዋይፋይ ራውተሮች ሲመረቱ ነባሪ መጠቀሚያ ስም /default username/ እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃል ይኖራቸዋል። የራዉተሩ አምራች ከታወቀ እነዚህን የዲፎልት መጠቀሚያ ስሞችን እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃላትን ለመገመት በጣም ቀላል ነው፡፡ በመሆኑም የግል ዋይፋዮቻችን ደህንነት ለማረጋገጥ ጠንካራ የይለፍ-ቃሎችን መጠቀም ይገባል፡፡

• የበይነ-መረብ አገልግሎት መስጫ መለያ ይቀይሩ /SSID/
እያንዳንዱ ራውተር ከነባሪ መጠቀሚያ ስም ማለትም “ነባሪ” /default/ ጋር ስለሚመጣ የአውታረ መረባችንን አገልግሎት መስጫ መለያ ስም /SSID/ መለወጥ ያስፈልጋል። ይህንን በራውተራችን ገመድ አልባ መሰረታዊ ቅንብር ገጽ /wireless basic setting page/ በመሄድ መጠሪያውን በመለወጥ የዋይፋያችንን ተገማችነት በማስቀረት ለጥቃት እንዳንጋለጥ ማድረግ እንችላለን፡፡

• አውታረ-መረባችንን መመስጠር
የዋይፋይ ራውተራችን ከመረጃ ጠለፋ እና የአገልግሎት መስተጓጎል ለመከላከል የአውታረ-መረብ ምስጠራን መተግበር አስፈላጊ ነዉ፡፡

• ሎጊንግ መፍቀድ (Enable Logging)
ሎጊንግ አማራጭን ስንፈቅድ (Enable) የዋይፋይ ኔትዎርካችንን እንዳይጠለፍ ለማድረግ ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ነዉ፡፡ በዋይፋይ ራውተራችን ውስጥ ያለው የመለያ ባህሪ ሁሉንም የአይፒ አድራሻ ይመዘግባል፡፡ እንዲሁም ሁሉንም የግንኙነት ሙከራዎች ዝርዝር ይሰጣል። ምንም እንኳን ይህን ተግባራዊ ማድረግ ዋይፋያችንን ከጠላፊዎች የማይጠብቅ ቢሆንም ማንኛውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይረዳናል፡፡ ይህንን ስርዓት "Enable" ማድረግ ይገባናል፡፡

• የዋይፋይ ሲግናል ማስተካከል
የዋይፋይ ሲግናላችን ጠንካራ እና በአጭር የቆዳ ስፋት ብቻ የምንጠቀም ከሆነ የዋይፋዩን ሲግናል አቅም መቀነስ ይኖርብናል፡፡ ይህን ለማድረግ የራውተራችንን ሞድ 802.11n ወይም 802.11b ምትክ 802.11g መጠቀም ይመከራል፡፡

• የራውተራችንን ፈርምዌር ማዘመን
ራውተራችን ፈርምዌር /Firmware/ የሚባል ሶፍትዌር አለው፡፡ ፈርምዌር ጊዜው ያለፈበት እና በወቅቱ ያልዘመነ ከሆነ ለአንዳንድ የደህንነት ሰጋቶች የተጋለጠ መሆኑ አይቀርም፡፡ ምንም እንኳ የዘመናዊ ራውተሮች ፈርምዌር በራሳቸው የሚያዘምኑ ቢሆንም እርግጠኛ ለመሆን በየጊዜው መዘመናቸውን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡
• የራውተራችን ፋየርዋል ማንቃት መጠቀም

የራውተራችንን ፋየርዎል/firewall/ ተግባራዊ ማድረግ ወይም ማንቃት ይኖርብናል፡፡ ይህን በማድረጋችን ሊከሰት ከሚችል ተጨባጭ የሳይበር
@endu12endu
❤1
2025/07/13 16:46:54
Back to Top
HTML Embed Code: