Telegram Web Link
📌ሀገራችን ኢትዮጵያ በሉሰበርግ ልትመሰገን ነው

‎የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የአውሮፓ ጉብኝትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት በሉክሰምበርግ ከተማ ማዘጋጃ ቤት  የማስታወሻና የምስጋና ዝግጅት የፊታችን ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም  ይካሄዳል።

‎በዕለቱ የኢትዮጵያና የሉክሰምበርግ ሠዓሊያን  ወቅቱን የሚያስታውስና ነጻ የፈጠራ ሥራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን የሥዕል ትርዒት ይከፈታል ተብሏል።

‎በመርሃግብሩ ላይ አስር የሀገራችን ሠዓሊዎች ሥራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ሠዐሊና መምህር ኃይሉ ክፍሌ ሀገሩን ወክሎ ንግግር እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።

‎የንጉሱ የሉከሰምቦርግ ጉብኝትለየት  የሚያደርገው በወቅቱ በነበረው የአንደኛው  የዓለም ጦርነት ጉዳት ምክንያት የገንዘብ  ልግስና ማድረጋቸው ሲሆን ፣በዚህ ዝግጅት  ላይም የከተማዋ ከንቲባና ንጉሳዊያን ቤተሰቦችንጨምሮ  ታላላቅ  እንግዶች  በመገኘትንግግር  እንደሚያደርጉ፣ ኢትዮጵያንም እንደሚያመሰግኑ ይጠበቃል ።

‎ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ከዚህ የአውሮፓ ጉብኝት  በኋላ መከፈቱን ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የመቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል ልዩ ፕሮግራም ነገ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር ለሁለት ዓመታት የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ነገ ሐሙስ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል ልዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅት ላይ አርቲስት እታፈራሁ መብራቱ የክብር እንግዳ በመሆን የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ቃልና ሙዚቃ" የተሰኘ ውይይት ነገ ይካሄዳል። ይህ ልዩ ውይይት ነገ ጥር 1 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ውይይት ላይ የሙዚቃ ባለሞያዋ ትሬዛ ዮሴፍ ዳሰሳ ታቀርባለች ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ጀቢና"ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው።

በደራሲና ዳይሬክተር ሳሙኤል ተሻገር የተዘጋጀውና "ጀቢና" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ለእይታ ይበቃል። "ጀቢና" በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ ፊልም እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በአሁን ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በለታሪክ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበ ነው።

በፊልሙ ላይ ቤተልሔም ሸረፈዲን፣እታፈራሁ መብራቱ፣ ካሣሁን ፍስሃ(ማንዴላ)፣ ናትናኤል መኮንን፣አስራት ታደስ እና ሌሎችም ተውነውበታል።

ይህ ፊልም ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የድምፃዊ አህመድ ሁሴን(ማንጁስ) አልበም

የድምፃዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) "አልጣሽ" ሲል የሰየመውን የመጀመሪያ አልበሙን በዚህ ወር ለአድማጮች እንደሚያደርስ ተገልጿል።

በዚህ አልበም ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን በግጥም ይልማ ገብረዓብ ፣ ናትናኤል ግርማቸው ፣ መሰለ ጌታሁን ፣ ተስፋ ብርሀን በዜማው አበበ ብርሀኔ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ አህመድ ተሾመ(ዲንቢ)) በቅንብር አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሽዎታ አብዛኛውን ያቀናበረ ሲሆን ቀሪውን ከአቤል ጳውሎስ በጋራ ሰርተውታል፡፡

ይህ የድምጻዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) አዲስ አልበም ጥር 16 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለሙዚቃ አድማጮች ይደርሳል፡፡

ድምጻዊው "ደሴ ላይ" ፣ "ልቤ አቃተው" እና ሌሎችም ነጠላ ሙዚቃዎች ከዚህ ቀደም ለአድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"KITFO film festival" ነገ ይካሄዳል!

(መግቢያው በነፃ ነው)

ፕሪስቲጅ አዲስ የኢትዮጵያን የጥበብ ኢንዱስትሪ ላቅ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ሲሆን ከ2012 ዓም ጀምሮ ወጣትና አንጋፋ ለሆኑ የፊልም ባለሙያዎች ተሞክሯቸውን ለወጣቶች ሚያጋሩበት አስተማሪ የሆነ መድረክን ገንብቷል።

ይህንን ተግባሩን ያጠናክር ዘንድ "KITFO film festival" የተሰኘ  የፊልም ፌስቲቫልመቀመጫውን አሜሪካ ካደረገው "KITFO TV" ጋር በመተባበር አዘጋጅቷል ።

ዝግጅቱም ነገ አርብ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን የባህል ማዕከል የሚካሄድ ሲሆን በዚህም ፌስቲቫል ስድስት ሀገርኛ እንዲሁም ኢንተርናሽናል ፊልሞች ይቀርባሉ።ነፃ ምግብና መጠጦችም ይኖራል።መግቢያውም ሙሉ በሙሉ በነፃ ነው።

ይህንን የፊልም ፌስቲቫል ነገ ከቀኑ 7:00 ጀምሮ መታደም ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ኤም  ኤን ጂ ፊልም ፕሮዳክሽን እና ኢቨንት ኩባንያ የፊልም ስክሪፕት ግዢ ስምምነት ተፈራረመ። 

ስምምነቱ ኩባንያው እየሰራ ከሚገኘው የፊልም ማርኬቲንግ ሥራ በተጨማሪ በፊልሙ ኢዱስትሪውን ውስጥ ለመፍጠር ላልመው በጎ ተፅዕኖ የመጀመሪያ እርምጃ መሆኑን በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አስታውቋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ቢሮውን ከመክፈቱ አስቀድሞ ከፓራ ማውንት፣ ሶኒ ፒክቸርስ እና ሌሎች የፊልም ኩባንያዎች ጋር ሥራዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን በኢትዮጵያ ቢሮውን በከፈተ ማግስት በተለያዩ በጎ ተግባራትን ሲፈፅም እንደቆየም ሰምተናል።

የኩባኛውን በኢትዮጵያ ሥራ መጀመር በማስመልከት በመጀመሪያ የወደቁትን አንሱ የነድያን መርጃ ማሕበር የተለያዩ የምግብ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከ6 ወር በኋላ ደግሞ ለንሕምያ የኦቲዝም ሴንተር የተለያዩ የንፅሕና እና መማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረግ ችሏል።

በዛሬው ዕለት የተደረገው የፊርማ ሥነሥርዓት የፊልም ሀሳብ ያላቸው ደራሲያን ስክሪፕታቸውን ሸጠው በሌሎች አካላት ሥም ለዕይታ ይበቃ የነበረበትን ልማድ በማስቀረት ደራሲያን በፊልም ፕሮዳክሽን ውስጥ እውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ለማሳየት የተደረገ እንደሆነም ከመድረኩ ለማወቅ ችለናል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
በ3.5 ሚሊዮን ብር የታተመው የአርቲስት መሀሙድ አህመድ የህይወት ታሪክ መጻሕፍ ተመረቀ

የአርቲስት መሀሙድ አህመድ ካሁን ቀደም ያልተሰሙ የህይወት ገጽታዎች ያካተተውና በደራሲ ወሰን ደበበ ማንደፍሮ የተዘጋጀው
መጻሕፍ ትላንት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በማሪዮት ሆቴል ተመረቋል።

አርቲስት መሀሙድ አህመድ ላለፉት 63 ዓመታት በሙዚቃው ዓለም ያሳለፋቸውን ውጣ ውረዶች ፣ የቤተሰብ የኋላ ታሪክና የወዳጅ ጓደኞቹን እንዲሁም የሙያ ባልደረባዎቹን ምስክርነት አካቶ የያዘው የሕይወት ታሪክ መጻሕፍ ለማዠጋጀት አስር ዓመታት እንደፈጀ በምርቃት ዝግጅት ላይ ተገልጿል።

ንብ ባንክ በ3.5 ሚሊዮን ብር ህትመቱን ስፖንሰር ማደርጉ
በዕለቱ ተገልጿል። መጻሕፉ ለምረቃ በበቃበት ዕለት በልዩ
ሁኔታ የታተመውንና አምስት ሺህ ብር ዋጋ የተቆረጠለት መጻሕፍ ለሽያጭ ቀርቦ በማሪዮት ሆቴል የተገኙ እንግዶች ገዝተዋል።

በልዩነት ግን ኢንጂነር ቢጃናይ እና ዶ/ር ሐውለት አሕመድ 500 መጻሕፍትን በ2.5 ሚሊዮን ብር የገዙ ሲሆን የሰን ሻይን ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በ500 ሺ ብር 100 መጻሕፍት ገዝተዋል።

ዘገባው የባላገሩ ቴሌቪዥን ነው።
📌"ደህና ይግጠምሽ" ሙዚቃ ቪዲዮ ተለቀቀ

የድምጻዊ መሳይ ተፈራ "ደህና ይግጠምሽ" የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ጥር 2 2017 ዓ.ም በራሱ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች አድርሷል።

የሙዚቃው ግጥም በናትናኤል ግርማቸው፣ዜማ ደግሞ በመሳይ ተፈራ ካሣ ተሰርቷል።ታምሩ አማረ በሙዚቃ ቅንብር የተሳተፈ ሲሆን የሙዚቃ ቪዲዮውን ሱራፌል መዝገበ ዳይሬክተር አድርጓል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

ገጣሚና ጋዜጠኛ ዲበኩሉ ጌታ የበኩር ስራው የኾነውን "የምድር ዘላለም" ከፃፈ በኋላ ዘለግ ላሉ አመታት "ሰው እስካለ ድረስ" የተሰኘውን የግጥም መድበል ሲያሰናዳ ቆይቷል።

"ሰው እስካለ ድረስ" ከበርካታ ግጥሞቹ መካከል በዚህ ኮረብታ ኮረኮንች በሆነው የሕይወት ጎዳና በማይረብሽ መልኩ ለግጥም አፍቃሪያንና ተደራሲያን ይሆኑ ዘንድ ተመርጠው የታተሙ ናቸው።

ግጥም የሕያው ስሜቶች ምስክሮች ናቸው እንዳለው ባለቅኔው፣ የዲበኩሉ ግጥሞች ምስክሮች ናቸው።

በተለያዩ ጊዜያት የተፃፉ ልዩ ልዩ ጭብጥ ያላቸው ግጥሞችን ያካተተው መድበሉ፤ በ126 ገጾች ተቀንብቦ በ297 ብር ለአገር ውስጥ፣ በ20 ዶላር ለውጭ አገር ገበያ ቀርቧል፡፡"ሰው እስካለ ድረስ" በሁሉም መጻሕፍት መደብር እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አዲስ አድማስ ጋዜጣ 25 ዓመት ሞላው!

የአዲስ አድማስ ጋዜጣ የመጀመሪያው ዕትም ለንባብ የበቃው ታህሳስ 29 ቀን 1992 ዓ.ም ነው፡፡ ጋዜጣው ባሳለፍነው ማክሰኞ ታህሳስ 29 2017 ዓ.ም 25ኛ ዓመት ሞላው፡፡

ይህንንም ምክንያት በማድረግ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም የ25ኛ ዓመት ልዩ ዕትም ለንባብ በቅቷል።

ጋዜጣው በእርግጥም ልዩ ዕትም ነው፡፡ በተባ ብዕራቸው የሚታወቁ የአገሪቱ አንጋፋ ደራስያንና ጸሃፍት በሳል ጽሁፎቻቸውን ያቀርቡበታል፡፡

የተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ጥበባዊ ርዕሰ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡ ከአዲስ አድማስ ጋር የተያያዙ ማራኪ ትዝታዎችና ገጠመኞች ይነበቡበታል፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት በአዲስ አድማስ ላይ ከወጡ ጽሁፎች የተመረጡ በዚህ ልዩ ዕትም ተካተዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"የሎሚ ጭማቂ ትዝታ" መጽሐፍ እሁድ ይመረቃል

በደራሲ አህመድ ሁስ የተዘጋጀው "የሎሚ ጭማቂ ትዝታ" የተሰኘ  የልቦለድ መጽሐፍ ነገ እሁድ ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ልዩ ልዩ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
📌የአንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ የስንብት የሙዚቃ ኮንሰርት እንዴት ነበር?


የጋሽ ማሕሙድ የምስጋና ምሽት በአብዛኛው ጥሩ ዝግጅት የተደረገበትና በርካታ ሞያተኞችም የተሳተፉበት ለሌሎች አንጋፋ ሞያተኞችም ክብርና እውቅና የመስጠትን ልምምድ አስፈላጊነት ያሳሰበ ዝግጅት ነበር ።


የፕሮግራሙ ትልቅ ችግር ሰዓቱ ነበር።ለጋሽ ማሕሙድ ፍቅርና ክብራቸውን ለመግለጽ ኮንሰርቱን የታደሙትን ዕድሜያቸው 60ዎቹና ሰባዎቹን የተሻገሩ ትልልቅ ሰዎችን እስከ ሌሊት ስምንት ሰዓት ማስጠበቅ በፍጹም ትክክል አይደለም።ይህ አይነቱ የክብር መግለጫ ስነስርዓት ቀደም ብሎ ተጀምሮ የሚደረጉ ንግግሮችና ሌሎች ፕሮግራሞችም ቀልጠፍ ብለው ማለቅ ነበረባቸው።


ጋሽ ማሕሙድ ጉንፋን ይዞት ያሰባቸውን ሙዚቃዎች መጫወት ባይችልም ጥቂት ስራዎቹን በትግል ዘፍኗል።አክብረው ለመጡ አድናቂዎቹ ሲል አንድ ዘፈን ከተጫወተ በቂ ነበር ። የቀረው ፐርፎርማንስ ግን ለእርሱም ለአድማጩም አሳቃቂ ኾኖ ተሰምቶኛል ።


ከምሽት ሶስት ሰዓት ጀምሮ በአዳራሽ ለተገኘው ታዳሚ ከሌሊቱ ዘጠኝ ተኩል ሊዘፍን የወጣውን ኤፍሬምን ጨምሮ እዚያ የተገኙ ድምጻውያን ከራሳቸው ዘፈኖች ይልቅ የጋሽ ማሕሙድን ስራዎች በራሳቸው ቃና በመጫወት ቢያከብሩት ምሽቱ የእርሱ መኾኑን አስረግጠው ማሳየት ይችሉ ነበር ። የውጪ ሀገር ልምድ ይህን ያሳያል ። የትላንቱ የነርሱ ተሳትፎ የማሕሙድን መብራት መሻማት መስሏል ። እርግጥ ስጦታዎችን በመስጠት ክብራቸውን ገልጸዋል ። በጎው ነገር ያ ነው ።


ይህን መሰሉ ዝግጅት ዋና ፊታውራሪ መኾን የነበረበት መንግስት የኋላ ወንበር መያዙ አስተዛዛቢ ነው ። የድሬደዋ አስተዳደር የምስጋና ሰርተፍኬት ልኳል ።


የነጻነት መድረክ መሪነት ፍጹም ዝግጅት ያልተደረገበትና የተዝረከረከ ነበር ። ለቴሌቪዥን ዝግጅቱ ከሚያደርገው ዝግጅትና የአቅራቢነት ለዛ ጥቂቱን እንኳ አላየኹም ።


ከነእንከኖቹም ቢኾን ይህን መሰሎቹ የምስጋና መድረኮች መለመድ ይኖርባቸዋል ። ይህን ዝግጅት ያሰናዱት ኹሉ ምስጋና ይገባቸዋል ።

በዮሴፍ ጥሩነህ የተጻፈ

@EventAddis1
📌የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዕጩ ተሿሚ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በነበሩት አቶ መሐመድ እድሪስ ምትክ ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) እንዲሾሙ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእጩነት ያቀረቧቸው ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኮሚኒኬሽን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሆኑ በዩንቨርስቲው የማርኬቲንግና ኮሚኒኬሽን ረዳት ፕሮፌሰር መሆናቸው ታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው በላኩት ደብዳቤ ፣"የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣንን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ዶ/ር ሳምሶን መኮንን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ እንዲሾሙ እጠይቃለሁ" ብለዋል።

በደብዳቤው ላይ የተጠቀሰው አዋጅ ድንጋጌ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በባለስልጣኑ ቦርዱ ተመልምሎ በመንግሥት አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሰየም የሚገልጽ ነው።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ነፃ መሆን እንዳለበት በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 17 ስር ተደንግጓል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበለትን የሹመት ጥያቄ በነገው ዕለት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

የባለስልጣኑ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር በቅርቡ በአቶ ብናልፍ አንዷለም ምትክ የሰላም ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአስቻለው ፈጠነ አዲስ ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል

የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ(አርዲ) "አሞራው ካሞራ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የሙዚቃው ሥራውን ነገ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በብርቧክስ ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል።

ሙዚቃው ለአፄ ቴዎድሮስ የልደት መታሰቢያ የተሰራ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ከዚህ ቀደም "እናትዋ ጎንደር" እና "ካሲናው ጎጃም" በተሰኙ ሙዚቃዎች ከፍተኛ ተደማጭነትን አግኝቷል።

በተጨማሪም ባሳለፍነው ዓመት ጥር ወር በለቀቀው "አስቻለ" የሙዚቃ አልበም ተወዳጅነትን አትርፏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
2025/07/12 15:37:18
Back to Top
HTML Embed Code: